Telegram Web Link
ይኽን ሁሉ ኖረናል? ወይስ ገና ለመኖር ደጋግመን እየሞከርን ፈር ሳይዝልን ነው እዚህ የደረስነው? ብዙ ኖረን ነው ከምናስታውሰው ይልቅ የረሳነው የበዛው? የሕይወት ትርጉም ዘልቆን ነው ወይስ ከሕይወት ተኳርፈን....ገና በወጣትነት እኩሌታ ላይ ቆመን የእርጅና ጫፍ ሐሳብ ሮጦ ያልጠገበ ልባችንን እንደ አለት ያከረደደው? "ምን ያህል ኖርን?" ይልቅ "ምን ያህል ቀረን?" ለእኛ የቀለለ ጥያቄ የኾነው መቼ ነው? ጨለማን በብዙ ለምደን ሲነጋ ጀንበሯ እየፀለመች እንጂ እየበራች መኾኗን ለማመን ይቸግረናል።ጨለማን የለመደ ትውልድ ውስጥ ንጋት ቅንጦት ይኾናል።ግን እኮ ወጣት መኾን ደስ ይል ነበር...በአንድ ወቅት...
ምን እያልኩ ነው? አላውቅም! የልደቴ ቀን ሲመጣ የተዘበራረቀ ሐሳብ አስባለሁ...ቢኾንም ደስ ይላል ወጣትነት...አበቃ ብለን ሲነጋ በአዲስ ኃይል ከምንም መጀመር ....ደስ ይላል...ሁሉም አዲስ ቀን ለወጣት አዲስ ነገር ይዞ መምጣቱ!
.
#ዝም_ብሎ_ሐሳብ
.
@huluezih
ግን እኔ ሰው አይደለሁም?!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
የነካሁት ይረክሳል፣ያሰርኩት ይላላል፤
ዓለም ከእኔ ጋራ ቂም ያለው ይመስላል!
ሁሉ እንዲኾን በጎ. . .
ሁሉ እንዲኾን ደግ. . .
እሳት ጨብጫለሁ፣ልቤን ለመታደግ!
እንደ ሞላ ጭስ፣እንደ ነዲድ እጣን፣
መግቢያ አይጠፋውም. . .
የጠመደኝ ሰይጣን!
አታሎኝ. . .
አዝ'ሎኝ. . .
ማረፊያ ቀልሼ ለአፍታ አልቆየሁም፤
ግን እኔ. . . ሰው አይደለሁም?!
.
የሔድኩ ይመስለኛል. . .
መንገድ ሲያመነምነኝ፤
እንደ ሰፌድ ላይ ሩጫ. . .
ዞሬ ዞሬ እዚያው ነኝ!
በዕጣ መዝገቤ ላይ አምላክ ከነደፈው፤
ሽንፈት ብቻ ነው ወይ ለእኔ የተጻፈው?
በምን መላ አድርጌ ልቤን ላስተናብረው?
ከጦር ስጠብቀው ቃል እየሰበረው!
ተወራጨሁ. . .
ተገጫጨሁ. . .
ለማንም አልኾንኩም፣ለእኔም አልበቃሁም
ቆይ ግን ሰው አይደለሁም?
.
@huluezih
@huluezih
. . . of the day😎 is back!
. . .of the day!😎
. . .of the day!😎
. . .of the day!😎
. . . of the day!😎
ጥሩ እና መጥፎ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
መጥፎው ነገር. . .
ሕይወት ውስብስብ ናት፣የማትፈታ ትብታብ፤
የመባዘን መዝገብ፣የድባቴ ኪታብ።
.
መጥፎው ነገር. . .
ሕይወት ልክ እንደ ወንዝ ናት!
እንባችን እንጂ አይመለስም ትናንት።
ካገኘነው በላይ ያጣነው 'ሚገደን፣
ከማለሙ ቀድመን መታመሙን ለምደን!
.
ጥሩው ነገር. . .
ለመፍጠር የኛን ቀን. . .
ታግለን!
ተፋልመን!
አልያም ተናንቀን. . .
እንደ ዐፄ በጉልበት ወይ ደሞ በሰላም፤
ሁሉም ነገር ያልፋል. . .
ብንወድም ብንጠላም!
.
ጥሩው ነገር. . .
የማለዳ ተስፋችንን፣ቢበላውም ጤዛ፤
በሕላዌ መስክ ላይ. . .
ምን ትግል ቢበዛ፣
እኛም ልክ እንደ ሕይወት
አይደለንም ዋዛ!
.
@huluezih
@huluezih
"የሴቶች ቦታ ኩሽና ነው!"
.
ይኽ የተፈፀመው በሐገረ ጀርመን ነው። እየተካሔደ የነበረው የእግር ኳስ ጨዋታ በሴት ዳኛ እየተመራ ነበር። በጨዋታው መሐል በተፈፀመ የጨዋታ ሕግ-ጥሰት (Foul) እንስቷ ዳኛ ከሪም ዴሚርባይ ለተባለ ቱርካዊ ተጫዋች ቀይ ካርድ በመሥጠት ከሜዳ እንዲወጣ ትዕዛዝ ታስተላልፋለች። በውሳኔው የተበሳጨው ተጫዋች ውሳኔውን በጸጋ ከመቀበል ይልቅ ወደ ዳኛዋ ተጠግቶ "አንቺ ኩሽና ውስጥ ነው መኾን የነበረብሽ፣ቦታሽ እዚህ አይደለም!" ሲል ተደመጠ።
.
ከጨዋታው በኋላ ለፊፋ የከሰሰችው ዳኛዋ ጉዳይዋ በፍጥነት ትኩረት ተሠጥቶት ተጫዋች ለቅጣት ተዳረገ። ጉዳዩ እዚህ ጋር አያበቃም። በተጫዋቹ ላይ ከተላለፉት ቅጣቶች መካከል "ተጫዋቹ በጀርመን የታዳጊ ሴቶች ሊግ ዳኛ ኾኖ አምስት ጨዋታዎችን እንዲመራ" የሚል ይገኝበት ነበር። በውሳኔው መሠረት በመጀመሪያ የዳኝነት ቅጣቱ ላይ ካፖርቱን፣ ቡትስ ጫማውን በማድረግ ጨዋታ ሊመራ ሳይኾን ፊልም የሚሠራ ተዋናይ በመምሰል ጨዋታውን መምራት ጀመረ። በጨዋታውም ለ8 ሴት ታዳጊ ተጫዋቾች ስምንት ቀይ ካርዶችን ሠጥቷል።ከጨዋታው በኋላ "ለምን ይኽን አደረግክ?" ተብሎ ሲጠየቅ "ምክንያቱም ሴቶች ኳስ ሜዳ ሳይኾን ኩሽና ነው ቦታቸው!" የሚል ለቅጣት የዳረገውን ንግግር መድገሙ አነጋጋሪ ጉዳይ ኾኗል! 😏
.
@huluezih
@huluezih
ቅዳሜ የመጽሐፍ ምርቃት አለ! የሚመቻችሁ ተጋብዛችኋል!
ትናንትና ስለ መጽሐፍ ምርቃቱ በቂ መረጃ ስላልሠጠሁ ይቅርታ እየጠየቅኩ ነገ ቅዳሜ ከቀኑ 9:00 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ ቡክስ አሚን አሚንዬ የተሠኘውን መጽሐፍ በጋራ እንመርቃለን። እዚያው እንገናኝ!
ከልጅነት አንዲት ገጽ
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰደብኩት ስድብ ‹‹ከብት›› የሚል ነበር፡፡የሰውነት ማጎልመሻ መምህር ነበር የሰደበኝ፡፡ በወቅቱ ምንም አልመሰለኝም ነበር፡፡እየዋለ እያደር ግን ይነደኝ ጀመር፡፡ ስድቡ አይደለም. . .ግልጽ አለመኾኑ እንጂ፡፡ ‹‹ከብት ሲል ምን ማለቱ ነው? ብዙ ዓይነት ከብት አለ…የትኛውን ነው ሊለኝ የፈለገው? በሬ ነው? በግ ነው? ላም ነው? የጋማ ነው ወይስ ያልጋማ ነው?››

ለዚህ ስድብ ያበቃው. . .ሰውነታችንን እንዴት እንደምናጎለምስ ለማስተማር እየሞከረ ሳለ ከጓደኞቼ ጋር ስሳሳቅ በማየቱ ጓደኞቼ ፊት ሊያሸማቅቀኝ አስቦ ‹‹በዚያ በበጋ!›› የሚለውን መዝሙር እንድዘምር አዘዘኝ፡፡እኔም አሻፈረኝ አልኩት፡፡
.
በመሠረቱ በዚያ በበጋ የሚባለውን መዝሙር አሁንም ድረስ አልወደውም፡፡ አለመውደድ ብቻ ሳይኾን ይኽ መዝሙር የእኛን ትውልድ ያሰናከለና ዛሬም ድረስ ከመዝሙርነት የዘለለ ተልዕኮ እንዳለው አምናለሁ፡፡
.
ከሥር መሠረቱ ላስረዳ!
በእኛ ዘመን አንድ ተማሪ አዕምሮው ለትምህርት ዝግጁ መኾን አለመኾኑ ሳይጣራ ነው ወደ ትምህርት ቤት የምንላከው፡፡የቀኝ እጅህ በጭንቅላትህ ዞሮ ግራ ጆሮህን ከነካ አለቀ! ማምኮ ደብተርህን ይዘህ፣ የዳርማር ቆዳ ጫማህን ተጫምተህ፣ ከአባትህ ሱሪ በተረፈ ጨርቅ ዩኒፎርም ተሰፍቶልህ ወደ ትምህርት ቤት ትሔዳለህ፡፡ እኔ ተፈጥሮ እጄ አጭር ስለነበረ በዘጠኝ ዓመቴ ነው ትምህርት የጀመርኩት፡፡እጅህ ረጅም ከኾነ ደሞ በአራት ዓመትህም ተማሪ ቤት ከመግባት የሚያድንህ ምድራዊ ኃይል የለም!
.
የመጀመሪያ ቀን ትምህርት ቤት ስሔድ አባቴ ነበር ያደረሰኝ፡፡ ለራሱ ካስሰፋው ሱሪ በተረፈው ጨርቅ ዩኒፎርም ስላሰፋልኝ የዚያን ቀን አንድ ዓይነት ነበር አለባበሳችን፡፡ በዚህ ምክንያት የኾነ ባዕድ ስሜት እየተሰማኝ ነበር፡፡ የኾነ አለ አይደል. . .አባቴን ትምህርት ቤት የማደርሰው ዓይነት ስሜት፡፡
የመጀመሪያ ክፍለ ጊዜዬ ላይ አንዲት መምህርት ገብታ ‹‹በዚያ በበጋ›› የሚለውን መዝሙር ታዘምረን ጀመር፡፡ ግጥሙን ታስታውሳላችሁ?
‹‹በዚያ በበጋ፤በዚያ በበጋ
እጮኛ ጠፍቶ ፍለጋ!››
.
ጥያቄ አይኾንባችሁም?! አንድ ተማሪ በልጅነቱ ዕውቀትን ፍለጋ በሔደበት ትምህርት ቤት ‹‹ዕጮኛ ጠፍቶ ፍለጋ!›› የሚባለውን መዝሙር መማሩ ወደ ብልጽግና የምናደርገውን ጉዞ አያደናቅፍም ወይ?. . .አያሳስብም?
.
‹‹መሸበትና ሰው ቤት ገባ፣
ልጅቷን ዐያት፣ተከናንባ
ወደዳት! ወደዳት! ይዟት ጠፋ በለሊቱ. . .

ከዚህ ግጥም መረዳት ያለባችሁ የመጀመሪያው ነገር የእኛ ዘመን ልጆች እንደምንከናነብ ነው፡፡ ወላጆቻችን ብርድ እንዳይመታን የማያለብሱን ነገር አልነበረም፡፡ አጋነንክ አትበሉኝና አንድ ክረምት ላይ ብርድ እንዳይመታኝ እናቴ ጋቢ፣ብሉኮ፣ የአባቴን ጃኬትና የእሷን ፎጣ ደራርባ ብርድ እንዳይመታኝ ስትሞክር ሙቀት መታኝ! ከሰሚ ሰሚ የሰማሁት ነው!
.
እና የበዚያ በበጋ አስቀያሚው ነገር ጠያቂ ትውልድ እንዳይፈጠር ማድረጉ ይመስለኛል፡፡ ተከናንባ ዐይቶ የወደዳትን ልጅ ይዟት ጠፋ፣ ከዚያ ዓባይ ደርሰው ለመሻገር ሲጥሩ እሱ ምንም ሳይኾን እሷ ሠጠመች፡፡እሱ አልቅሶ እንደተመለሰ ነው ታሪኩ የሚነግረን፡፡
.
ብዙ መሠረታዊ ጥያቄዎችን የሚያስነሣ መዝሙር ነው፡፡ ለምሳሌ ልጅቷን ይዟት የጠፋው በበጋ ነው፡፡አባይ ደግሞ በበጋ አይሞላም፡፡ክረምት ቢኾን መስመጧ ያሳምነኝ ነበር፡፡ ‹‹በቃ ሞተች አዘነላት!›› በሚል ምክንያት እንዴት ከሕግ ሊያመልጥ ቻለ? ይኼ መዝሙር በፍትሕ ተስፋ እንድቆርጥ ያደረገኝ ያኔ ነው፡፡ ገድሏት አባይ በረሃ ላይ ቀብሯትስ ቢኾን? ይኼ መዝሙር ሊነግረን የፈለገው ነገር. . .ሲመስለኝ ‹‹እዚህ ሐገር ውስጥ የሚገደል ሰው ገዳዩ ተጣርቶ ለሕግ ስለማይቀርብ ተማሪዎች ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ ፖለቲካ ውስጥ ላለመግባት መሞከር እንዳለባቸው ነው!››
.
ያ ሰውነቱ ያልጎለመሰ ሰውነት ማጎልመሻ መምህር ይኼን ዘምር ሲለኝ አልዘምርም ብዬ ነው እንግዲህ ‹‹ከብት!›› የተባልኩት፡፡ አድጌ ከዩኒቨርሲቲ ተመርቄ ወጥቼ እንኳ አንድ ቀን ያን መምህር አግኝቼ ‹‹ከብት! አይደለሁም!›› ብዬ ‹‹የከብትን ዘርፈ ብዙ የሌማት ትሩፋቶች›› ለማስረዳት ዕድሉን ባገኝ ብዬ እመኝ ነበር፡፡ ደስ የሚለው ነገር ምኞት ብቻ ኾኖ አልቀረም፡፡ የዛሬ አምስት ዓመት አካባቢ መምህርነቱን ትቶ በሌላ የሥራ ዘርፍ ተሠማርቶ አገኘሁት፡፡ አዲሱ ሥራ ምን ቢኾን ጥሩ ነው? ወተት አከፋፋይ! በስተመጨረሻም የከብት ጠቃሚነት ገብቶታል ማለት ነው! ይኼ….ከብት!
.
@huluezih
@huluezih
. . .of the day!😎
. . .of the day!😎
. . .of the day!😎
. . .of the day!😎
. . .of the day!😎
2025/07/06 12:33:33
Back to Top
HTML Embed Code: