Telegram Web Link
. . .of the day!😎
. . .of the day!😎
. . .of the day!
. . .of the day!😎
የማለዳ ማስታወሻ #151
.
ሌቦች ባገኘኸው አጋጣሚ ሁሉ የምትሰርቅ ይመስላቸዋል። ውሸታሞች ንግግርህ ሁሉ ውሸት ነው ብለው ያምናሉ። የማያምኑህ ሰዎች ብዙ ሰዎችን የከዱ ናቸው። ገዳዮች አንተ ፊት እንቅልፍ አይጥላቸውም፣እንደምትገድላቸው እርግጠኛ ስለሚኾኑ። "ማንንም አላምንም!" የሚሉት ለማንም የማይታመኑ ሰዎች ናቸው።
.
በአዕምሮዋቸው የፈጠሩት ማንነትህ ያንተ ባሕሪ ላይ የተመሠረተ ሳይኾን በእነሱ ልምድ ላይ የቆመ እውነት ነው። ስጋታቸው የሚመነጨው ከስብዕናቸው ነፀብራቅ እንጂ ካንተ ጉድለት አይደለም። በውንጀላቸው ውስጥ ማንነታቸውን ታያለህ።
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih
. . .of the day!😎
አሳዛኝ ይኹን ወይ አዝናኝ መኾኑ ያልታወቀ ዜና!
.
ይኽ በአፍሪካዋ ማላዊ የተከሰተ ነው። ወጣቱ እንደምንም አየር ማረፊያ ውስጥ በመግባት ተደብቆ ያለ ፓስፖርት እና ያለ ምንም ፍቃድ ከሐገር ለመውጣት የአውሮፕላኑ ክንፍ ላይ የመደበቂያ ሥፍራ ሲፈልግ በቁጥጥር ሥር ውሏል።
.
ይኽ ወጣት በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ በሠጠው ቃል "እዚህ ሐገር መሮኛል...ከማላዊ የተሻለ ሥፍራ ላይ የተሻለ ሕይወት መኖር ስለምፈልግ ነው ይኽን ያደረግኩት" ብሏል። ይኹን እንጂ ወጣቱ አውሮፕላኑ ከማላዊ ተነሥቶ ወደ ደቡብ ሱዳኗ ጁባ ሊበር እንደነበር አላወቀም።"የትም ይኹን!" በሚል የፈፀመው ድርጊት መኾኑን ዘገባዎች ያሣያሉ።
.
የእኛስ ሐገር ወጣት? ዕድሉን ቢያገኝ ይኽን ያደርግ ይኾን? ከነምስቅልቅሉም ቢኾን ከሐገር የተሻለ ቦታ አለ?
.
@huluezih
@huluezih
የማለዳ ማስታወሻ #152
.
ለአታካች ችግሮች፣ ለቀን ጎዶሎዎች፣ ለተሳቢ ድብርት፣ ለሥም አልባ በደሎች፣ለጥልፍልፍ አዙሪቶች እና ለሌሎችም የስሜት ደዌዎች ትልቁ መድኃኒት ጊዜ ነው። ዛሬን ገፍቶ ነገ ላይ መድረስ፣ ውሎ ማደር።
.
በሚታይ እና በማይታይ ቁስል ማለፍ በሰው የተፈረደ የዓለም ወግ ነው።የትናንት ቁስል የተፈጠረ ቀን የሚያመውን ያኽል ዛሬ አያምም። ጠባሳው እንጂ ህመሙ ዛሬ አብሮን አይደለም። አዕምሯችን ላይ አስቀምጦት ካለፈው ጥቁር ትዝታ በቀር ሲነካ እንደፊቱ አያንከባልለንም።
.
"ቁስል ግን ለምን ጠባሳ ጥሎ ያልፋል?" ሲል ጠየቀ ብላቴናው።
"ሰዎች ከምን ይማሩ?" ጠቢቡ መለሰ።
.
ያንቺ ቁስል ለታናሽ እህትሽ መንገድ መጠቆሚያ ፍኖት ቢኾንስ?
በስህተትም በዕጣ ፈንታም ያመመህ ህመም ከርሞ ጠባሳ ሲኾን ብርሃን የሚረጭ ጥበብ ይፈልቀዋል። ቀን መግፋት ለቻለ ጠባሳ ማለት ሕይወት የሸለመችው ኒሻን፣ ዓለም የነቀሰችው የልህቀት ንቅሳት ነው።
.
የትኩስ ቁስልን ቅጽበት ችሎ ማደር፣ ቀን መግፋት፣ ዛሬ መቃጠል ውስጥ የተሻለ ነገን መሳል መቻል ቁልፉፍ መኾኑን ብዙ የሕይወት በሮች የተዘጋባቸው አበው በቅኔ አጽንኦት ሠጥተው፣ ከቁስላቸው ትምህርት እንቀስም ዘንድ እንዲህ የሚል መልዕክት አስቀምጠውልናል:-
.
"ወተቱን በማታ ታበላሻላችሁ፣
ቀን እንዲህ ይገፋል፣
እኔ ላሣያችሁ!"
.
የዛሬን ቀን እንግፋ...ነገ ተዓምር አለ።
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih
. . .of the day!😎
የማለዳ ማስታወሻ #153
.
ሁለታችንም ተሰባብረን ነው የተገናኘነው። ከስባሪያችን ጋር እንዴት እንደምንኖር ብልሃት በጠፋን ሰዓት። ተፈጥሯዊ ስብዕናችን ከጠፋን በኋላ፣ የጨለማ ውስጥ መቅረዛችን በስህተቶቻችን ንፋስ ሲጠፋ፣ ትርጉም ያጣንበት እስትንፋሳችን የትም የሚዘራበት አሳቻ ላይ ነው የተገናኘነው።
.
ስንገናኝ ስብራቶቻችን አጋመዱን፣ ጉድለቶቻችን አስተሳሰሩን፣ አንዳችን በአንዳችን ተፅናናን። ሁለታችንም ልክ ወጥመድ ውስጥ እንደገቡ ዓሣዎች ነበርን። የዝለት መንገዶቻችን የሚመሳሰል፣ የእኔን የወጥመድ
ሥቃይ ወጥመድ ውስጥ ስለኾነች ብቻ የምትረዳ፣ ወጥመዱን በማወቄ ብቻ መጠመዷ እንደራሴ ኾኖ የሚያመኝ ስለኾነ ተሰናሰልን።
.
ግን ጊዜ ትርጉሙን በጊዜ ውስጥ ቀየረው። በጊዜ ሒደት ወጥመዱን ስለምደው ህመሜን የሚረዳልኝ ሳይኾን ከህመሜ የሚፈውሰኝን ፍለጋ ጀመርኩ። "አይዞሽ! ወጥመዱን ቻል አድርጊው! ህመምሽን ቻይው!" የሚላት ድምጽ ሳይኾን ወጥመዱን በጥሶ እንደ ነፃ ወፍ እንዳሻች የሚያደርጋት እንደሚያስፈልጋት አመንኩ። የተሰበረ ሰው ሰባራ ሰው አይጠግንም። የታመመ ልብ የቆሰለን ልብ ማከም አይችልም። "አይዞሽ!" እያልኩ ጊዜዋን አላባክንም። እየተረዳችኝ እኔን ለመፈወስ አቅም የላትም። ወጥመዴን ተሸክሜ ቦታ ቀየርኩ። እያወቅኳት ልረሳት፣ እየሳሳሁላት ልሸሻት ተራመድኩ። መንፈስ ሳይራራቅ አካል ይራራቅ አይደል?...እንደዚያ ኾነ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih
👍1
እናመስግን!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
መዝነን ያለፍናቸው. . .
አቅልለናቸው ያለፉ. ..
ድንገት ስናኮበኩብ፣
ሊያቆዩን የለፉ፣
ያውቁ ነበር. . .
አንድ ቀን እንደሚፀፅተን፣
ይቅርታ እንደምንሻ፣
ቁጭቱ ሲያቅተን!
.
አሉ ደሞ ሰዎች. . .
እነሱን ተክተው፣ወደ እኛ ሚመጡ፣
በገፋናቸው ሰዎች መንበር ሚቀመጡ፣
ስንቃጠል. . .
ስንበግን. . .
ያጣናቸውን ሰዎች ከልብ እናመስግን!
.
@huluezih
@huluezih
👍1
. . .of the day!😎
Audio
"የሚያስፈራኝ"
.
(#ፈይሠል_አሚን)
. . .of the day!😎
. . .of the day!😎
. . .of the day!😎
የማለዳ ማስታወሻ #154
.
እርግጠኛ አይደለሁም። ቃላት ከእምነት ባሕር ውስጥ ሊዘፍቁኝ በርትተዋል። ዓይኖች፣ እርምጃዎች ግን ልቤን ቀዝቃዛ ውርጭ እየረጩ ያጠራጥሩኛል።በአፍ የሚዘንቡ ቃላትን አላምንም። ባየሁትና በዳሰስኩት ኹሉም እርግጠኛ አይደለሁም።
.
ያለኝን ኹሉ ልሠጥ ይደናገረኛል። እንቁላሉን ኹሉ በአንድ ቅርጫት አላስቀምጥም፣ ልቤ እሺ አይለኝም። ልቤን ያለ ምጣኔ ከፍቼ የመጣውን ኹሉ አላ ስገባም። መቀበል እንጂ መሥጠት የሚሰስቱ እጆች እምነቴን ያጎድሉታል። እርግጠኛ አይደለሁም።
.
መጠንቀቅ ተፈጥሯዊ ቢኾንም. . .ዕድሎችን የሚዘጋ እክል ነው። ነጅሰውን በሔዱ ሰይጣኖች ምክንያት አርፍደው የመጡ መላዕክት እንዳይጠጉን በጥንቃቄ ሥም በራችንን ቆልፈንባቸዋል። ለትናንት ሥብራታችን ቀን የጠራው ጠጋኝ እንዳይጠጋው ደብቀነዋል። እንጥፍጣፊ ድፍረቴን ይዤ በሬን ልከፍት እልና...ሰይጣኖች የመጀመሪያ ሰሞን መላዕክ ይመስሉ እንደነበር አስታውሼ... እጄን እሰበስባለሁ።
.
እርግጠኛ አይደለሁም። ቀጣይ በምራመደው መንገድ፣ አስከትዬ ከምቀልሰው ጎጆ አሁን ላይ ቆሜ ሳስብ እርግጠኛ አይደለሁም። እርግጠኛ የኾንኩት በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ፣ በምንም ዓይነት ቅርቃር ሥር ሁሌም ራሴን እኾናለሁ። ሰው በቆመበትና ባለፈበት መንገድ ውሳኔዬን ወጥኜ የሰው ሕይወት አልኖርም። ዛሬም እንደትናንቱ፣ ነገም እንደዛሬው እኔ እኔ ነኝ። በራሴ ዓይን፣ በራሴ ልብ በራሴ እግር ብወድቅም ወደፊት፣ ብቆምም በራሴ ምሕዋር ላይ እየቆምኩ ሕይወትን እከተላለሁ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih
መስከረምን እወዳታለሁ 5
.
(በየዓመቱ መስከረም 1 ላይ ብቻ የሚነበበው ታሪክ እነሆ ክፍል 5)
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
"ዓመት ምን ያክል ይረዝማል?" ብባል "እንደከረሙበት ቅርቃር!" ይኾናል መልሴ። ሰዎች አዲስ ዓመት ሲመጣ፣ አደይ ሲያብብ፣ የክረምት ኮስታራ ደመና በመጪው ፀደይ ሲገፋ፣ መስከረምን ጠብቀው ነሻጣቸውን አንግበው ነገን በጉልህ ለማለም ይታትራሉ፤ ትናንትን በልምድ ሞረዳቸው ሞርደው እንደ ዐውዱ አዲስ ለመኾን ያልማሉ። በአዲስ ልብስ፣ በአዲስ ሐሳብ፣ አዲስ ራዕይ አዲስ ለመኾን ይጥራሉ። የእኔ መስከረም ኹሌም ልቤ ውስጥ ናትና የእኔ መንገድ ከዚህ ይለያል። ከልጅነት እስከ ወጣትነት ያፈቀርኳት መስከረም አርጅታብኝ አታውቅም። እሷ ስለ ራሷ ከምታወቀው በላይ ዐውቃታለሁና ዛሬም መዓዛዋ የማይለዝዝ ጽጌረዳዬ ከመኾን የዘመን ቅብብሎሽ አላገዳትም። እሾኋ ቢበዛብኝም።
.
"ዓመት" የሚሉት የጊዜ ሰንሰለት በልቤ አቆጣጠር ከቀትር እስከ ምሽት እንኳ አይረዝምም። ዙሪያችን ያሉ ቅጽበታት ታሪክ ኾነው ቢያልፉም፣ ያየናቸውና የነካናቸው ሰዎች አፈ-ታሪክ ብቻ ኾነው ለዘላለም ቢያሸልቡም፣ የእኛ ያልናቸው የተፈጥሮ ጥሪቶች እጃችንን ፈልቅቀው ቢከዱንም፣ እንደእኔ የማይና'ወጥ ፍቅር ልቡ ላይ ለተከለ ሰው "ዓመት" ከቀትር እስከ ምሽት እንኳ አይረዝምም።
.
ይኽ ዓመት በውዷ መስከረም ሕይወት ውስጥ መራራው ዘመን ነበር። እንደ ወታደር በኹሉም አቅጣጫዋ ሳይደክሙ ዘብ የሚቆሙላት አባቷ ወደ አፈር የተመለሱበትና ዓይኖቿ እያዩ የተቀበሩበት ዓመት ነበር። ከአባቷ ሞት ቀደም ብሎ ያ ፓይለት አፍቃሪዋ በጋራ የወጠኑትን የትዳር ጉዞ አፍርሶ ሌላ ትዳር የመሠረተበት አስደንጋጭ ስብራት አሳልፋለች። ዋነኛ ምክንያቱ ድንገት የጀመራት እንግዳ ህመም ነበር። ህመሟ ሥም አልነበረውም። ግን ከአቅሟ በላይ ያማታል። ሣቋን፣ ወዟን፣ የደስ ደሷን እና ሞላ ያለ ሰውነቷን ነጥቋታል። ውበት አፍቃሪው ፓይለት አካላዊ ውበቷን ሲያጣ መስከረምን ሸሻት።
.
ከአባቷ ሞት በኋላ መስከረም ሥሟን መምሰል ተሳናት። እንደ ነሐሴ አጋማሽ የሚዘንብ እንባ ከጉንጯ የማይጠፋ፣ እንደ ጳጉሜ ያጠረ አቅም ብቻ ቀርቷት ውሎ አዳሯ አልጋ ላይ ኾነ።
.
በብርታቷ ዘመን አጃቢዋ ብዙ ነበር።ያኔ ጓደኞቿ እንኳን ተቆጥረው ተጠርተውም አያልቁም። አፍቃሪዎቿ በወል አይታወቁም። ያ ኹሉ ሰው በክፉ ቀኗ ለምዱን አውልቆ አውሬነቱን አሣያት። የአባቷን ለቅሶ ሰምተው አንድ ቀን ብቻ ለይስሙላ መጡ፣ ይስሙላቸው ሳይመክን ህመሟን ሰሙና "ይማርሽ!" "ለማለት ብቅ አሉ። በዚያው ጠፍተው ቀሩ።
.
እኔስ?
ለእኔ የመስከረም ቁስሎች የምወዳት ነፍሷን አልነኩብኝም። ምንም የተቀየረ ነገር የለም። እንደውም ያልነበረኝን ሐዘኔታ ውስጤ ጠንስሷል። ሥራ ቦታ ኾኜ "ማን ያበላት ይኾን? ማንስ ያጠጣታል? መፀዳጃ ቤት ማን ያደርሳታል?" እያል በጭንቀት እባክናለሁ።
.
ከሥራዬ እየበረርኩ ወደ ሰፈራችን እመለሳለሁ። ወደ ቤቴ ጎራ ሳልል የመስከረምን በር ከፍቼ እገባለሁ። ዘወትር የተለመደ አዲስ ፊት ታሣየኛለች. . ."ደ'ሞ መጣህ!" ዓይነት ፊት።
.
ቁራኛው ከኾነችው አልጋ አጠገብ እቀመጥና ግልምጫዋን እና ስድቦቿን በትዕግስት አደምጣለሁ።ህመሟ እና ድንጋጤዋ ከፈጠረባት ብሶት የተወለዱ እንጂ የክፋት ስድቦች አለመኾናቸውን ጠንቅቄ ዐውቃለሁ። ትናንት የሚሰማኝ ልዩ ስሜት ዛሬም ሳይዛነፍ መስከረምን እወዳታለሁ። ከፊቱ የበለጠ ብትጠላኝም፣ ስታየኝ የሚፋፋም ንዴት ከፊቷ ላይ ቢነሣም የነበረኝ ሞገደኛ ተስፋ ዛሬም አለ።
.
ሰው ሰውን የሚወደው የሚስብ ልዩ መስህብ ስላለው አልያም የሚገፋ መጥፎ ህመም ስለሌለው ነው። ይኽን በመስከረም ሕይወት ውስጥ የተማርኩት ልዩ ትምህርት ነው። የእኔ ፍቅር ለምን እንዲህ እንደኾነ ግን አላውቅም። መስከረምን ስወዳት ለምን ምክንያት የለኝም? ጥላቻዋ ለምን ተስፋ አያስቆርጠኝም፣ ህመሟ የተሻለ ዕድል እንዳለኝ ለምን አይነግረኝም? እኔ ለመስከረም የምኾንላትን ሲሶ ያክል እሷ እንደማትኾንልኝ እየገባኝ ለምን በየቀኑ ነፍሴን እገብርላታለሁ?
መልሱ እንደ ጥያቄው አይከብድም!
"ምክንያቱም ፍቅር ዕውር ነው! ፍቅር ውስጥ ስሌት ስለሌለ ነው"
.
ለዓመት አድርሶ ክፍል ስድስትን ያስነብበን🙏
.
@huluezih
@huluezih
እስቲ የገባው ካለ?🙄
2025/07/12 10:45:20
Back to Top
HTML Embed Code: