የማለዳ ማስታወሻ #155
.
"ከከፍታው ላይ ለመዝለል ትክክለኛው ሰዓት ለመዝለል የፈራኽበት ሰዓት ነው!" የሚል ጥቅስ ወደ ራሴ እንድመለከት መስኮት ከፈተልኝ። ከተከፈተው መስኮት አጮልቄ ወደ ራሴ ተመለከትኩ። ከከፍታው ላይ ለመዝለል እጅግ የፈራሁበት ሰዓት ነው። ልብ አድርጉ! የቆምኩበት ከፍታ የእኔ ቦታ አይደለም።
.
ሕሊናዬ ይነግረኛል..."ብትዘል ትወድቃለህ፣ ትሰበራለህ!" ይለኛል። ልቤም ዝም አይልም "ብትዘል ክንፍ እንዳለህ ካመንክ ትበራለህ እንጂ አትወድቅም። ዝለል! ዝለል!" እያለ ያደፋፍረኛል። በሕሊናዬና በልቤ ተቃርኖ መሐል አሁን ከፍታው ላይ በፍርሃት ቆሜያለሁ!
.
ደፍረው የዘለሉ፣ በጥሰው የወጡ፣ ቆፍረው ያመለጡ፣ ዘልለው የተረፉ ሁሉ በአንድ ወቅት እንደኔ በፍርሃት ወደ ራሳቸው ምህዋር የሚያሸጋግራቸውን ዝላይ አልፈዋል። ከፀፀት እና ቁጭት በአንዲት ውሳኔ ሳቢያ ተርፈዋል። እነዚህ ሰዎች የኾኑትን ልኾን እኔም የእኔ ካልኾነ ከፍታ ላይ ልዘል ነው። ከተረፍኩ የራሴን ከፍታ ከጠጠር ጀምሬ ልገነባ፣ ካልተረፍኩ ከስህተቴ ልማር የፈራሁትን ላደርግ፣ ግራ የገባኝን ጨክኜ ልወስንበት. . . እዘላለሁ!!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih

ይድረስ ለመላው ዓለም:-
.
ጉዳዩ:- ሲቃዬን ስለ ማጋራት
.
ያቆዩኝ ጠቢባን አዛውንቶች አልፈዋል፤ የተረከቡ ብርቱ ወጣቶች ረግፈዋል።የፀነስኳቸው ፅንሶች መክነዋል፤ የወለድኳቸው ሕጻናት በአጭር ተቀጭተዋል። እናቶች የእንባ ቀረጢታቸው ደርቆ በደማቸው እያነቡ ነው፤ አባቶች የልጆችን መቃብር መቆፈር ታክተዋል።በተስፈኛ መዳፎች የተገነቡ መኖሪያዎች እሳት በልቷቸው አመድና ስባሪ ኾነዋል። ከውኃ ይልቅ ደም በዋዛ ይገኝ ጀምሯል። ከአዕላፍ ዜጎች መካከል በጣት የሚቆጠሩ ዕድለኞች "ለጊዜው" ተርፈዋል። የጠላት ብትር ሳይበቃ ከጠላት ወዳጆች ማጥፊያ እሳት የፈረደበት ገላዬን ያዳክመዋል። ተመልካች ከሩቅ በለሆሳስ "አትተርፍም" እያለ ያንሾካሹካል። መመንመኔ፣ መውደሜ፣ማለቄ ለጠላቴ "ፈጣሪ የለም!" ከሚል እብሪት ውጪ የነገረው ነገር የለም። እምነት ያለው ኹሉ በምድሬ እያለቀ ነው። ቆልፎ የተቀመጠ፣ የፈራ፣ አቅም ያጣ እንኳ ከፍሙ አይተርፍም። ማንም "ነግ በእኔ" ብሎ ሲቃዬን አይሰማም። ከጥይት የተረፈ ከረሃብ አያመልጥም፣ ከረሃብ እንኳ ቢተርፍ የቀበራቸው የሕይወቱ ትርጉሞች የኾኑ አብራኮች መንፈስ በሰላም አያኖረውም።
ደክሞኛል. . .
ተስፋ ቆርጫለሁ. . .
ካለኝ ውስጥ የቀረኝ የለም. . .
.
እየሞትኩ ነው!
ከአክብሮት ጋር
የናንተው ጋዛ

እስቲ ቅዳሜን በመዝናናት አሳልፉ! እነሆ ግብዣ!https://youtu.be/tiGoNakcRQE