Telegram Web Link
ፐ! ሬድዮ ሲባል ሰምታችኋል? ያልሰማችሁት ስላልነገርኳችሁ ነው😊 አሁን ግን እነሆ ቅዳሜ ፐ! ሬድዮን ልንጀምር ነው! ቅዳሜ ቀጠሮ እንዳትይዙ🙏

https://youtu.be/CZEhv3bmB3E?si=hmBcxykUdzAodqG-
በቀጠሯችን መሠረት እነሆ የመጀመሪያው ክፍል ፕሮግራማችን ተለቋል፡፡ ግቡና ፈታ በሉ…እያያችሁ ስለምታበረታቱኝ ከወዲሁ አመሠግናለሁ!
https://youtu.be/ZbmgOkZp7Fc
ጽሑፍና እኔ ምን አኮራረፈን?
.
ጅማሮውን ከማላውቀው ጊዜ አንሥቶ መጻፍ ይደክመኝ ጀምሯል። መጻፍ የምፈልገው ሐሳብ በምናቤ እየተከሰተ፣ ቃላት ስንኝ እየኾኑ በአዕምሮዬ እየተመላለሱ፣ ትዝብት አንቀጽ ሙሉ ፊደል አምጥቶ እንድጽፍ እየጋበዘኝ በማላውቀው ዐዲስ ስሜት ምክንያት ሳልጽፍ እቀራለሁ።በጣም ብዙ ጊዜ! ከቀናት በኋላም እነዚህ ጎትጓች ሐሳቦች ተስፋ ቆርጠው ይጠፉብኛል።
.
በምዕራባውያን ሥነ-ጽሑፍ ውስጥ "Art Attack" የሚባል ጽንሰ-ሐሳብ አለ። አንድ "የጥበብ ሰው" የሚጽፈው ሐሳብ ኖሮት ነገር ግን የሚጽፍበት ጊዜ አጥቶ ሐሳቡ አየር ላይ ሲቀርና ሲረሳ ለሚከሰት "ጥበብ-ነክ በሽታ" የተሠጠ ሥያሜ ነው። ቃሉ "heart attack" ከሚለው ቃል ስለተፈለፈለ "Art attack" ን "የጥበብ ድካም" ብለን ልንተረጉመው እንችላለን። "Hear attack"ን "ልብ ድካም" እንደምንለው ሁሉ ማለት ነው።
.
ረዥም ጊዜያትን በሥራ፣ በኑሮ በ"ወጣ ገባ"፣ በድንገተኛ ክስተቶች ውስጤ ላይ ስባትል ይኽ "Art attack" የተባለ በሽታ ሳያገኘኝ የቀረ አይመስለኝም። ወትሮም "እስቲ ልጻፍ" ብዬ የምቀመጥ ጸሐፊ አልነበርኩም። ሌላ ጉዳይ ላይ እያለሁ ጎትቶ ብዕር የሚያስጨብጥ ሐሳብ ካልመጣ በቀር በእቅድ ለመጻፍ ብዬ አልቀመጥም። ለዚያ ነው..."ሥነ-ጽሑፍ እንድጽፈው ያዘኛል እንጂ እኔ ሥነ-ጽሑፍን ተጻፍልኝ ብዬ አላዘውም" የምለው።
.
አንድ ጸሐፊ ለመጻፍ ከሐሳብ ባሻገር ብዙ ግብዓቶች ያስፈልጉታል። በዋናነት የሚጽፍበትና የጻፈውን የሚያርምበት በቂ ጊዜ፣ እንዲሁም የአዕምሮው ሰላም ፊታውራሪ ኾነው ከፊት ይሰለፋሉ።
.
አሁን ለመጻፍ የተሻለ ሁኔታ ላይ ነኝ። አሁን ቶሎ ቶሎ ሐሳብ የምንቀያየርበት፣አብረን ሕይወትን ከተለያየ አቅጣጫ የምናይበትና የምንዝናናበት ጊዜ መጥቷል። በተጨማሪ ደሞ "ክባዳም ትረካዎች" የተሰኘውን የወግ ቡፌ ከጽሑፍ ባሻገር በቪድዮም ዩቲዩብ ላይ የምንጋራ ይኾናል። ስለ ትዕግስታችሁ ላመሠግናችሁ ነው የመጣሁት...ክበሩልኝ🙏
.
#ፈይሠል_አሚን
.
@huluezih
1
. . .of the day!😎
. . .of the day!😎
ከመሸም ቢኾን ተጋበዙልኝ😊😎

https://youtu.be/bIyqzFyEjPA
👍1
የማለዳ ማስታወሻ #156
.
ከትናንቴ ጋር ነው ፉክክሬ. . .
ከነበርኩበት አንድ ደረጃ ከፍ ብዬ ትናንቴን ቁልቁል ማየት፣ የትናንት መንገድ ያሳደፈው ልቤን ንፁህ አድርጎ ማቆየት፣ ያለፉ ሕፀፆቼን እንደ መጽሐፍ እያነበብኩ፣ እሾሃማ ትዝታዎቼን እንደ መስታወት እየወለወልኩ የተሻለውን እኔ በኩራት መመልከት፣ ትናንት እየጎተተ ኋላ እንዳያስቀረኝ ራሴን ከጸጸት መመከት! ወደ ኋላ እንዳይራመድ እግሬ፣ከትናንት ጋር ነው ፉክክሬ!
.
ደሞ ከዛሬ ጋር ነው ትግሌ. . .
የቆጡ ክፉኛ እያጓጓኝ፣ ያለፈው ቁጭት አባብሎ እያስጠጋኝ፣ በእጄ ያለው እንዳይበተን፤ "እደርስበታለሁ!" ያልኩት በቸልታ ወበቅ እንዳይተን፣ ወደፊት መራመድ፣ ካልኾነም መንፏቀቅ ከወደቅኩም ወደ አቅጣጫዬ ዞሬ መውደቅ. . .ብቻ ዛሬን በከንቱ፣ዛሬን በዋዛ አለመልቀቅ! ሳላሳብብ በዕጣዬ፣ሳላማኸኝ በዕድሌ፣ ባለ'ኝ እና ባገኘሁት ፈቅ ለማለት ከዛሬ ጋር ነው ትግሌ!
.
ከነገ ጋር ቃልኪዳኔ. . .
ዕድሜና ጤና በአጭር ሳያስቀሩኝ፣ የሞት መላዕክት በድንገት ሳይጠሩኝ፣ ጡቤን ልደረድር፣ የሕይወቴን ቅኔ ልሰድር፣ ልደርስበት ብዙ ለከፈልኩለት ነገ ቃል ገብቻለሁ. . . ተሸርፌም፣ተሰብሬም፣ ጎድዬም ቢኾን እመጣለሁ! የወጣሁትን አቀበት ነገ ላይ ቆሜ ቁልቁል ዐያለሁ. . .እዚህ ላለመቅረት ለነገ ቃል ገብቻለሁ. . .ለዘመናት የሚነገር ተረክ ከጉዞዬ ለቅሜ በስልቻዬ ይዣለሁ! አልቀርም እመጣለሁ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih
1
ፏ ያለ ቅዳሜ ምሽት እንዲኾንላችሁ የተዘጋጀ. . .😎

https://youtu.be/QUerfOu_GY0
. . .of the day!😎
. . .of the day!😎
👍1
. . .of the day!😎
. . .of the day!😎
መቼም አትፈርዱብኝም ብዬ ነው https://youtu.be/hq29vU302rc
. . .of the day!😎
Audio
ቀን በእኔ፣ቀን ላንቺ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih
. . .of the day!😎
Audio
ይኼን ብቻ ዐውቃለሁ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih
1
2025/07/08 20:24:49
Back to Top
HTML Embed Code: