የዓመቱ ምርጥ ሥጦታ!
.
ደጋግመህ የምታደርገውና ተደጋጋሚ ውጤት የምታይበት(ምናልባትም ውጤት የማትጠብቅበት) ነገር ተስፋ ሊያስቆርጥህ ቋፍ ላይ ሲደርስ እንደ ፀሐይ ሙቀት የሚያነቃቃህ፣ እንደ ነዳጅ ኃይል የሚሠጥህ ተስፋ ይወልዳል። ይኽ ከኑሮና ከዓመታት ሥራ የተገኘ ልምድ ነው። አንድ ሰው ለዓመታት ጽሑፎቼን ያነበበ እና ማንበቡንም የወደደ ሰው የሠጠኝ ሥጦታ ነው። ከጽሑፎቼ መካከል ደስ ያሰኙትን፣ልቡን ያንኳኩለትን አንጓዎችና ስንኞች ወስዶ ከቴሌግራም ቻናሌ አርማ ጋር በቲሸርት ላይ አትሞ በሥጦታ መልክ ሠጠኝ። ቀላልና ጊዜ የማይወስድ ሥራ ሊኾን ይችላል...ነገር ግን እኔ ዘንድ የፈጠረው መነቃቃት እንዲህ ተብሎ የሚገለጽ አይደለም። የምትሠራው ነገር ለአንተ የዕለት አዘቦታዊና ተለምዷዊ ግብርህ ሊኾን ይችላል...የሥራህ ጥላህ ግን ማን ጋር ደርሶ ምን ዓይነት ፍሬ እንደሚያፈራህ በቀላሉ አትረዳም። keep going!
ለዚህ ውድ ሥጦታ ውድ ምሥጋና አቅርቤያለሁ🙏

👍1
ራሱን ድል' ባለ ሠርግ ያገባውን ሰው ላስተዋውቃችሁ!
.
አንቷን ቾቫል ይባላል። የፈረንሳይ ዜጋ ነው። በ"ሕጋዊ መንገድ" ራሱን አግብቷል። ሰውዬው እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው 17 ጊዜ ከተለያዩ ሴቶች ጋር የፍቅር ግንኙነት ሞክሮ ባለመሳካቱና "ለትዳር የሚኾነኝን አጥቻለሁ!" በሚል ምክንያት ነው።
.
በምዕራባውያኑ ዓለም sologamy (ከራስ ጋር ጋብቻ መፈጸም አዲስ ነገር ባለመኾኑ ራሱን ከማግባቱ በላይ ለሠርጉ የተጠቀመው ልብስ የሶሻል ሚድያውን ትኩረት ስቦ ነበር። የሙሽራ ሱፍ እና የሙሽሪትን ቬሎ አቀናጅቶ በማሰ'ፋት ብዙ ገንዘብ የፈሰሰበት የራሱ ሠርግ ላይ ዘንጦበታል። የዚህ ልብስ ዲዛይነር የኾነው ልብስ ሰፊም ገበያው እንደደራለት ተዘግቦ ነበር። በሶሻል ሚድያ ወሬው ከተዘዋወረ በኋላ የተሠጡት አስተያየቶች አስቂኝ ነበሩ። ከአስተያየቶቹ መካከል "መልካም ጫጉላ" ተብሎ ከሥራው ቦታው የተሠጠው የእረፍት ፍቃድ ላይ የተመሠረተ አስተያየት ይገኝበታል።
.
እኛ ሐገር ይኽ ቢከሰት ካለው የሠርግ ባህልና ወግ አንጻር ምን ያክል ከባድ እንደሚኾን ሳሉት? "አናስገባም ሠርገኛ፣ ደጅ ይተኛ!" የሚለው ባህል እንዴት ይኾናል? ጥሎሹስ? ለራሱ ጥሎሽ ገዝቶ ራሱ ሲወስደው አስቡት! ኧረ ቅልቅልስ? ማን እና ማን ሊቀላቀል ነው?😅
.
@huluezih

🤣1
የምፈልግበት ቦታ ላይ ባሰብኩት ሰዓት አልደርስም. . .ምክንያቱም :-
👉አላጭበረብርም
👉አልዋሽም
👉አልሰርቅም
👉አላታልልም
👉አላጎበድድም(አላሽቃብጥም)
👉ዙሪያዬ ያሉትን አልጠልፍም
👉በሰዎች ደስታ አልናደድም
👉አልመቀኝም
ስለዚህ ሕልሜ ላይ ለመድረስ እዘገያለሁ። የዚህ ዘመን ጽልመታዊ ጎን ይኽ ነው። ስኬትህ ሕሊናን በሚጎዱ ፋሻዎች የተጠቀለለ ነው። ቢኾንም ግን ዘግይቼም ቢኾን እደርስበታለሁ። Life is not easy...and so am I.
.
(#ፈይሠል_አሚን)