Telegram Web Link
ብዙ ብዙ ማለት እፈልጋለሁ...አሁን ግን አልችልም። ጅማሮው ላይ የተገኛችሁልኝ ሁሉ ውለታችሁ አለብኝ። ድጋፋችሁን ወድጄዋለሁ፣ መኖራችሁ ቀና እንድል አድርጎኛል። ክበሩልኝ!🙏
በመጨረሻም. . . .
ከአራት መንፈቀ-ዓመታት በላይ የለፋሁበት ሦስተኛው መጽሐፌ በትናንትናው ዕለት በተዘጋጀው የሊቀ-ቀንበር የወግ ድግስ ላይ ይፋ ኾኗል። ምናባዊ-ልቦለዶች(fantasies) በብዛት ያካተተው ይኽ ሥራ በቅድመ-ክፍያ የሚገዙትን ሦስት መቶ ሰዎች ይጠብቃል። በትናንትናው መድረክ የተወሰኑ ሰዎች አስቀድመው በመግዛት ወደ ህትመት ቤት የሚያደርገውን ጉዞ አስጀምረውታል። ሦስት መቶ ሰዎችን እንደማላጣ ተስፋ በማድረግ እነሆ በማህበራዊ ገጾችም ላይ ይፋ አድርጌዋለሁ። የአንዱ መጽሐፍ ዋጋ 500 ብር ብቻ ነው!

1000413125654 -Feysel Mohammed
የገዛችሁ ስክሪንሾት በማድረግ ላኩልኝ መጽሐፉ እንደታተመ በቅድሚያ ለእናንተ ይሠጣል!
#ሰንባች
.
@huluezih
@huluezih
አላውቅበትም!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
ዘመኑ ግሪምቢጥ፤
ተጋግሮ እንደ ሊጥ!
የኋሊት ኾነና ነፍስ እያስነገደ፤
አያልፍለትም ማንም ለሰው ካልሰገደ!
.
ከፍ ብል በእሱ ነው፣
ዝቅም ብል ለአምላኬ፤
ሰው አክብሬ ነው እንጂ. . .
አላውቅም አምልኬ!
.
ተነጥሎ ቆሞ ይፋለማል ልቤ፤
ከዘመኑ አይደለም፣ከሰው ጋር ነው ፀቤ!
.
ይደናገረኛል!
በውሰት ሕሊና ፣አስልቶ መደምደም፣
ስለማልችልበት፣እየጣሉ መቅደም፤
ከውሻ አሳንሰው፣ነፈጉኝ ዕድሉን፣
ስለማላውቅበት ጭራ አቆላሉን!
.
ጥቅስ እያጣቀሱ፣
ቃለ-አምላክ እያነሱ፣
ቢሰብኩም ታግዘው፣ በሳይንስ በፈለክ፤
አንድ ኾነው አያውቁም
"ማክበር" እና "ማምለክ"!
.
@huluezih
@huluezih
ቅድመ-ምሥጋና!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
"እንዲህ ቢኾንስ?"
"እንዲያ ባይኾንስ?"
የሚል ክፉ አመል፣ለምን አስጨነቀኝ?
አንተን ያክል ጌታ፣ተግቶ እየጠበቀኝ፤
ከግራዬ ሲጎድል፣ሞልተኸልኛል በቀኝ!
.
እንደነበርክልኝ. . .
እንዳለህልኝ. . .
ደሞ አትተወኝም፣ልክ እንደ እስካሁኑ፤
ገና ላሰብክልኝ፣
ላመሥግን ከአሁኑ!
.
@huluezih
@huluezih
Audio
መልካም የአባቶች ቀን!

(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih
አዝናለሁ አልወደቅኩም!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
አንድ ኀሙስ እንደቀረው፣
የብሶት ዜማ የማንጎራጉረው፤
ስለጠፋኝ አይደለም. . .
መንገድ ስለቀረሁ!
ቀናነት ሳይከብድ፣
መኾን ሲቻል መልካም፤
ተንኮል ለመጎንጎን፣
ለደከሙት ድካም. . .
"እሪ!ኩም! ዘመዳ!
"ዘመዳ እሪ!ኩም!"
እኔ ግን. . .
አዝናለሁ! አልወደቅኩም!
.
እበቅላለሁ እያልኩ. . .
በአፍ-ጢሜ ስተከል፤
ማቆጥቆጥ ሲመስለኝ፣
ከሥሬ መነቀል፤
ከአረም ጋራ ኾነ. . .
የእኔ አበቃቀል!
ሆድ ባይብሰኝም. . .
"እሪ!ኩም! ዘመዳ!
ዘመዳ እሪ!ኩም!"
አዝናለሁ! አልወደቅኩም!
.
ግፊያና ግፍተራ የፍቅር መሰለኝ፤
እኔ እንደሁ' ስወድ. . .
ወትሮም ዓይን የለኝ!
ዝቅ ማለት ጎዳኝ፣
መች ዐውቃለሁ ብልጠት?
ላከበርኩት ሁሉ፣ማጅራቴን መሥጠት!
ሰው ነኝና. . .ተጓዥ!
መንገድ ነውና... ጎዝጓዥ!
ሞክሬ. . ዳክሬ. . .
ከጭቃ ውስጥ እሾህ አላመለጥኩም፤
ግን አዝናለሁ! አልወደቅኩም!
.
የሌላውን ወድቀት አስበልጦ 'ሚሻው፤
ካቲማው አያምርም ዳሩ መጨረሻው፤
ብትካኑበትም...አጣጣል ብታውቁም፤
አዝናለሁ አልወደቅኩም!
.
@huluezih
@huluezih
ልቤ ግን እንዴት ነው?
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
አፈነኝ. . .
አሰረኝ. . .የጥያቄ ግርዶ. . .
"ሰው እንዴት ይሔዳል?
ድንገት እንደ መርዶ?"
.
የኾነው ሁሉ ኾኖም. . .
ልቤ ተከተለሽ!
(አይገርምም?)
ከክህደትሽ ይልቅ ውህደትሽ ተጫነው፤
አንቺ ተዘቅዘቂ!
ልቤ ግን እንዴት ነው?
.
@huluezih
@huluezih
ልብ 'ሚነካ ገዢ!🥺
.
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የኾነው ይኽ ወጣት "በ500 ብር መጽሐፍ መግዛት ባልችልም ሕልምህን እውን ለማድረግ ያለኝን 400 ብር ልኬያለሁ" ብሎኛል። ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ነበር የተሰማኝ። ዙሪያዬ ላይ በቅርብም በሩቁም የማውቃቸው ብቻቸውን መጽሐፉን አሳትመው ከሽያጩ ያወጡትን ወጪ መሸፈን የሚችሉ በርካታ ሰዎች አሉ። በእዚህ ዓይነት መነጽር ነገሩን ዐይተው ለማበረታታት የጋረዳቸው ግርዶ ስላለ እንጂ! ይኽ መጽሐፍ ለህትመት በቅቶ ለንባብ ሲደርስ የእንደዚህ ዓይነት ሰዎችን ውለታ ልረሳው አልችልም። አልቅስ አልቅስ የሚያስብል ማበረታቻ ነው። ከገዛኸው መጽሐፍ በላይ ቅንነትህ ለእንደኔ ዓይነት ሰዎች ትልቅ ማነቃቂያ ነው። ለአንተ ሲል ያሳክልኝ🙏 በሙሉ ልቤ አመሠግናለሁ።
.
አሁንም ቅድመ-ሽያጩ እንደቀጠለ ነው!
1000413125654 Feysel
#ሰንባች
Audio
በድጋሚ በድምጽ የተዘጋጀ
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih
#ላሽ_ታግ-Time
.
ቢንቢ ትሙት የት አባቷ!
.
ሌሊቱን ሙሉ ከቢንቢ ጋር የማያባራ ጦርነት ገጥሜ ሳልተኛ ነው ያደርኩት! ቢንቢዎች ሰይጣን መረጃ ለመሰብሰብ የሚጠቅማባቸው መሣሪያዎች ስለሚመስሉኝ በጣም ያስጠሉኛል። አዕምሯቸውን ለእኩይ ዓላማ ማስፈፀሚያ ካላዋሉት ለምን ጨለማን ተገን አድርገው፣ ለሊትን መርጠው ጆሮ ላይ ብቻ የተቃጣ ጥቃት ይፈጽማሉ ታዲያ? ፀረ ሰላም ነፍሳት ናቸው!
.
ገና መብራቱን ከማጥፋቴ አንድ የሳንቾ ዓይነት ድምጽ ያለው ጎልማሳ ቢንቢ ቀኝ ጆሮዬ ላይ የመክፈቻ ንግግር 'ሚመስል ነገር አደረገብኝ። ችላ ብዬ...ጆሮዬን በብርድ ልብሴ ሸፍኜ ተጠቅልዬ ተኛሁ። አልመች ያለው ይኽ ጎልማሳ ቢንቢ ተናዶ ሔደና ተጨማሪ የቢንቢ ኃይል አስከትሎ መጥቶ፣ ብርድ ልብሴ የማያቆመውን ድምጽ ማጉያ በመጠቀም በሙሉ ባንድ በኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር ጀምሮ "ለሰው ልጆች ሰላም" በሚል ህብረ ዜማ ጫፉን ከያዝኩት እንቅልፍ አቆራረጡኝ። ይኽን ጊዜ ነው እንግዲህ ብልጭ ያለብኝ!
.
መብራቱ አብርቼ ዋጋቸውን ልሠጣቸው ስል ከአካባቢው ተሰወሩ። እኩይ ዓላማ እንዳላቸው ማረጋገጫው መብራት ሲበራ መሰወራቸው ነው! የሠሩት ሥራ ወንጀል ባይኾን ለምን ይጠፋሉ?
ከእልህ አስጨራሽ ክትትል በኋላ ሁለት ቢንቢዎችን በቁጥጥር ሥር አውዬ አስከሬናቸው ለገናዥ እንዳይመች አድርጌ በትራስ አፍኜ ጨፈለቅኳቸው።
.
አንድ ሰውዬ "ቢንቢዎች ለምንድነው ጆሮ ላይ ብቻ 'ሚጮሁት?" ተብሎ ተጠይቆ "እና ቂጥህ ጆሮ የለው!" ማለቱ ትዝ ይለኛል።
እኔ እንቅልፌን ሰውቼ የደረስኩበት ነገር "ሰው ከእንቅልፍ የሚያገኘውን ፍሰሃ ለማኮላሸትና ቀኑ እንዲዛባ ለማድረግ" መኾኑን ተረድቻለሁ!

እሱ እንዳለው ያ ጠላቱ
ቢንቢ ይሙት የት አባቱ!
#ሞትለቢንቢ
.
@huluezih
@huluezih
ቀርተሻል መሰለኝ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
በዚህ ፉንጋ ክረምት
በዝናብ. . .
በካፊያ. . .
በውርጩ ስልተ-ምት፤
ሐምሌ ባጨቀየው፣በረጠበው ኮረት፤
እየጠበቅኩሽ ነው በቃሌ መሰረት!
(ዘይግተሻል!)
.
ደሞ ነገር በላሁ ደርሶ አብሰለሰለኝ፤
ሲሉ እንደሰማሁት ቀርተሻል መሰለኝ!
.
ግዴየለም!
ጡር እና ግፍ ሳትፈሪ
ከቀረሽም ቅሪ!
ልቤ ነግሮኝ ነበር፣ፊቱንም ስትቀጥሪኝ፤
ብቻ መቅረትሽን ነይና ንገሪኝ!
.
("የቀሩት" ናቸው የሚያሳምሙን!🙂
.
@huluezih
@huluezih
2025/07/02 05:43:03
Back to Top
HTML Embed Code: