ዐውቃለሁ ተጠፋፍተናል ግን. . .
.
ይኼ ቻናል ከነ ቤተሰቦቹ በእጅጉ ናፍቆኛል። ከእናንተ ጋር ቃላትን፣ሐሳቦችንና ስሜቶችን መጋራት እኔ ዘንድ እንደ ዕድል የሚቆጠር ነገር ነው። ዕድሉ ስላለ ብቻ ደግሞ ያሰብኩትን እና የጻፍኩትን ግሳንግስ ሁሉ እዚህ አላመጣም። (መጥፋቱ ከመጠንቀቅም የመነጨ ነው ለማለት ነው)
.
ላለፉት ብዙ ቀናት በጥሞና እና ከሥነ-ጽሑፍ ካልራቁ ሌሎች ሥራዎች ጋር ስታገል እንዲሁም ትንሽ እረፍት ስወስድ ቆይቻለሁ። ከአሁን በኋላ በሚከተሉት ቀናት ውስጥ አዳዲስ ነገሮች ይዤ እንደምመጣ ተስፋ አደርጋለሁ። የሚመጡት አዳዲስ ነገሮች ይሳኩ ዘንድ ደግሞ የእናንተ እገዛ እና ተሳትፎ ከምንግዜውም በላይ ያስፈልገኛል። ብዙዎቻችሁ በዚህ ቻናል ለብዙ ጊዜያት በመቆየታችሁ፣ በቅርብ የተቀላቀላችሁን ወዳጆች ደግሞ በምትሠጡት በጎ አስተያየቶች ምክንያት ከእናንተ የምፈልገውን ነገር እንደማላጣ ልቤ ያምናል። በዚህ ጉዳይ ላይ በሰፊው እመለሳለሁ።
.
ሙስሊም ወንድምና እህቶቼ እንኳን ለ1445ኛው ዓመተ ሒጅራ የዒድ አል ፊጥር በዓል በኸይር አደረሳችሁ!
.
ሁላችሁንም እወዳችኋለሁ❤
.
@huluezih

ስለ መጽሐፍት ቀን ሲነሣ. . .
.
አንዳንድ በተለያየ መልኩ የተበደሉ መጽሐፍት መደርደሪያችን ውስጥ አይጠፉም። ከየት እንዳመጣናቸው የማናውቃቸው፣ ሀፍረት ይዞን የገዛናቸው፣ መርጠን ገዝተናቸው የመነበብ ዕጣ ያልሠጠናቸው. . .በብዙ መንገድ የተበደሉ መጽሐፍት ይኖሩናል።
.
"ስለ ትናንሽ አለላዎች" መደረደሪያዬ ውስጥ ካሉ እጅግ ከሚያሳዝኑኝ መጽሐፍት በቁንጮነት ይቀመጣል። መጽሐፉን ከገዛሁት ከብዙ ጊዜያት በኋላ አማራጭ ሳጣ ነበር ያነበብኩት። አንብቤ ስጨርሰው በእጅጉ ተቆጨሁ..."እስከዛሬ ለምን አባቴ ነው ያላነበብኩት?" የሚል ፀፀት ወረረኝ።
.
ዮናስ አ.(አ ማንን እንደሚወክል አላወቅኩም) ይባላል ደራሲው። ሥሙንም ሠምቼው አላውቅም። ወጣትም ጎልማሳም ሊኾን ይችላል(አጻጻፉ ወጣትነትን ቢያስገምትም)፣ ማንም ሲያወራለት አልገጠመኝም። ግን በጣም የሚደነቅ የሥነ-ጽሑፍ ችሎታና ዕውቀት እንዳለው መጽሐፉን ያነበበ መረዳት ይችላል። ቋንቋው፣ ገለጻው፣ "በድንገተኛ መገለጥ (instant realization) በኩል የሚነግረን ንዑስ ታሪኮች...ለዛ አላቸው።
በርግጥ አጻጻፈ-ዘይቤውን የዚህ ዘመን ደራሲዎችን የሚያጠቃው የአዳም ረታ ሕፅናዊነት ያጠቃዋል። መጽሐፉን ሳነብ በተደጋጋሚ "ግራጫ ቃጭሎችን" በትውስታ አነፈንፍ ነበር።ቢኾንም ንባብ ወዳጅን በሚመጥን ደረጃ የተጻፈው መጽሐፍ ነው "ስለ ትናንሽ አለለዎች"
.
ያልተወራለት፣ብዙ ማሕበራዊ ገፆች ያላስተዋወቁትን መጽሐፍ የማመን ችግር ስላለብን ነው እንጂ አንገታቸውን ደፍተው ሲሠሩ ከርመው እንዲህ ድንገት ብቅ የሚሉ ገሞራ ጸሐፊዎች አሉ። ያላነበባችሁት ሰዎች ይኽን መጽሐፍ አንብቡት። ከታተመ 5 ዐመት ሊኾነው ነው...ጃዕፈር ጋር አይጠፋም። ደራሲውን የምታውቁ ካላችሁ አመሥግኑልኝ...ሥነ-ጽሑፍ ላይ ተስፋ እንዳንቆርጥ ስላደረግከኝ!
እናንተስ underated ወይም ብዙ ያልተባለላቸውን ምርጥ መጽሐፍት ታውቃላችሁ? እስቲ ንገሩኝ!

የቲኬት ሽያጭ ተጀምሯል! 🎫
.
በጉጉት የሚጠበቀው የሊቀ-ቀንበር የወግና የመዝናኛ ድግስ የመግቢያ ቲኬቶች ለገበያ ቀርበዋል። ቲኬቶቹ የት ይገኛሉ?
1. ቤተል ሚስተር ኮፊ፣ ፋሚሊ ታወር 4ኛ ፎቅ
2. ዋልያ ቡክስ (4 ኪሎ ኢክላስ ህንጻ)
3. the hungout cafe (አዶት ሲኒማ ህንጻ ground ላይ)
.
ባሉበት ኾነው ቲኬቱን በሞባይል ባንኪንግ ለመቁረጥ :-
1000413125654 Feysel
በዚህ አካውንት በመቁረጥ ስክሪንሾቱን የዝግጅቱ ዕለት መግቢያ ላይ እያረጋገጡ መታደም ይችላሉ።
.
የቲኬቱ ዋጋ:-
መደበኛ :- 200 ብር
ቪ.አይ.ፒ:- 300 ብር
.
መሠናዶው የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 24 ብስራተ-ገብርኤል አካባቢ በሚገኘው አዶት ሲኒማ ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ይካሔዳል።