እኔ እኮ አምንሻለሁ
በፍቅርሽ ታዉሬ ማሰብ ስላቃተኝ
ዝም ብየ አምንሻለሁ አንቺ እንደነገርሽኝ
አሁን በተለየ ትላንት ያወራሽኝ
ነቅቸ ነው እንጂ ሙቼ ነበር ያልሽኝ
የባለፈውማ እውነት ነው አምናለሁ
ከስድተኛ ፎቅ ወድቄ ድኛለሁ
ደሞ የሳምንቱ በጣም ግልፅ እውነት
እቀድመዋለሁ ንፋስን በፍጥነት
የፊቴ ብርሃን ከ ፀሀይ ይደምቃል
በአንድ ቀን ብቻ የሺ ልብ ይሠርቃል
ደሞ እኮ የድምፄ ከመሆኑ ምቹ
አንድ ጊዜ ብዘፍን አይተርፉም ወፎቹ
ደሞም ፕላስቲክ ነኝ እተጣጠፋለሁ
ሳልበላ ሳልጠጣ ሺ አመት እኖራለሁ
ሌላም ብዙ እውነት ስለምትነግሪኝ
እኔ እኮ አምንሻለሁ የለህም ብትይኝ
@hutoffun 👈🏽
@hutoffun 👈🏽
በፍቅርሽ ታዉሬ ማሰብ ስላቃተኝ
ዝም ብየ አምንሻለሁ አንቺ እንደነገርሽኝ
አሁን በተለየ ትላንት ያወራሽኝ
ነቅቸ ነው እንጂ ሙቼ ነበር ያልሽኝ
የባለፈውማ እውነት ነው አምናለሁ
ከስድተኛ ፎቅ ወድቄ ድኛለሁ
ደሞ የሳምንቱ በጣም ግልፅ እውነት
እቀድመዋለሁ ንፋስን በፍጥነት
የፊቴ ብርሃን ከ ፀሀይ ይደምቃል
በአንድ ቀን ብቻ የሺ ልብ ይሠርቃል
ደሞ እኮ የድምፄ ከመሆኑ ምቹ
አንድ ጊዜ ብዘፍን አይተርፉም ወፎቹ
ደሞም ፕላስቲክ ነኝ እተጣጠፋለሁ
ሳልበላ ሳልጠጣ ሺ አመት እኖራለሁ
ሌላም ብዙ እውነት ስለምትነግሪኝ
እኔ እኮ አምንሻለሁ የለህም ብትይኝ
@hutoffun 👈🏽
@hutoffun 👈🏽
Forwarded from 666( ኢልሙናቲ ) ሀይማኖት ምዝገባ ማእከል via @Josy_Button_Bot
📚📚📚📚
ቢታነፅ ቢወቀር
(በእውቀቱ ስዩም)
እኔም አንድሰሞን
ልክ እንደሶሎሞን
"ሁሉም ከንቱ ከንቱ ነፋስን መከተል"
ላይጥሉ መታገል: ላይከብሩ መባተል
እያልሁ አጨልሜ
በራሴ ለግሜ
እፈላሰፍ ነበር::
ከዚያ አንቺን አገኘሁ
በጉዋሮ በር በኩል: ሰሎሞኔን ሸኘሁ
መፈጠሬን ወደድሁ
ነፋስ አሳድጄ እንደቆቅ አጠመድሁ::
ከፀሓይዋ በታች :ግልገል ፀሃይ ፈጠርሁ
ለኦናው አምፖሌ: ብርሃን አበደርሁ
ማቅ የነበረው ጨርቅ: ሸማ ሆኖ ቆየኝ
"ከንቱ "የነበረው "አንቱ "ሆኖ ታየኝ::
ለካስ
ጠቢብ ቢያስተምረው
መከራ ቢመክረው
አካሉና ልቡ : ቢታነፅ ቢወቀር
ሰው አቅሙን አያውቅም : ካልወደደ በቀር::
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
ቢታነፅ ቢወቀር
(በእውቀቱ ስዩም)
እኔም አንድሰሞን
ልክ እንደሶሎሞን
"ሁሉም ከንቱ ከንቱ ነፋስን መከተል"
ላይጥሉ መታገል: ላይከብሩ መባተል
እያልሁ አጨልሜ
በራሴ ለግሜ
እፈላሰፍ ነበር::
ከዚያ አንቺን አገኘሁ
በጉዋሮ በር በኩል: ሰሎሞኔን ሸኘሁ
መፈጠሬን ወደድሁ
ነፋስ አሳድጄ እንደቆቅ አጠመድሁ::
ከፀሓይዋ በታች :ግልገል ፀሃይ ፈጠርሁ
ለኦናው አምፖሌ: ብርሃን አበደርሁ
ማቅ የነበረው ጨርቅ: ሸማ ሆኖ ቆየኝ
"ከንቱ "የነበረው "አንቱ "ሆኖ ታየኝ::
ለካስ
ጠቢብ ቢያስተምረው
መከራ ቢመክረው
አካሉና ልቡ : ቢታነፅ ቢወቀር
ሰው አቅሙን አያውቅም : ካልወደደ በቀር::
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
ያኔ....
በህይወት ሸለቆ ረዥም በሚመስለው በዚህ አጭር ጉዞ፤
ሁሉም በራሱ አውድ የግል መስመር ይዞ።
ይነጉዳል ይሔዳል ከጥልቁ ተዘፍቆ፤
ለመኖር ተሸጦ ከአዕምሮ ጓዳ ህሊናተፍቆ፤
አረሙ ለምልሞ ከመልካም ዘር ልቆ፤
በደግ ልቦና ትዕቢት ሰርፆ ዘልቆ።
አበቦች አብበው እሾህ እያፈሩ፤
እርግቦች ፈልፍለው እባብ ከፈጠሩ፤
ውል ማሰሪያው ጠፍቶ ሲበላሽ ውጥኑ።
ያኔ....
ያኔ አለም ሚዛኗን ፍርዷን ታፀናለች፤
መኖር አለመኖር ከምርጫ ታንሳለች።
ፅልመት ማቅ ይሆናል ከነጎድጓድ ጋራ፤
ብርሀን ትጠፋለች ፀሀይ ፊቷ ዞራ፤
በአስተሳሰብ ዝቅጠት በኛ ነውር አፍራ።
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
በህይወት ሸለቆ ረዥም በሚመስለው በዚህ አጭር ጉዞ፤
ሁሉም በራሱ አውድ የግል መስመር ይዞ።
ይነጉዳል ይሔዳል ከጥልቁ ተዘፍቆ፤
ለመኖር ተሸጦ ከአዕምሮ ጓዳ ህሊናተፍቆ፤
አረሙ ለምልሞ ከመልካም ዘር ልቆ፤
በደግ ልቦና ትዕቢት ሰርፆ ዘልቆ።
አበቦች አብበው እሾህ እያፈሩ፤
እርግቦች ፈልፍለው እባብ ከፈጠሩ፤
ውል ማሰሪያው ጠፍቶ ሲበላሽ ውጥኑ።
ያኔ....
ያኔ አለም ሚዛኗን ፍርዷን ታፀናለች፤
መኖር አለመኖር ከምርጫ ታንሳለች።
ፅልመት ማቅ ይሆናል ከነጎድጓድ ጋራ፤
ብርሀን ትጠፋለች ፀሀይ ፊቷ ዞራ፤
በአስተሳሰብ ዝቅጠት በኛ ነውር አፍራ።
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
........"እማይወለድ ምጥ"......
ወዮ አለ ጉራጌ ፡ ኸረግ ሲል አማራ
ያልጠበቀው ደርሶ ሲጨነቅ ሲፈራ፡፡
እኔም በአንደበቴ እግዚኦን ላክልበት፡ጨንቆኛል ጠቦኛል አጣሁ ምገባበት፡፡
መሮኛል ፡ አው..እውነት ከፍቶኛል
መፍትሄው ጠፍቶኛል፡፡
ፍርሀት ወርሶኛል
ኸረ ወዲያ😔 ..በቃ ሰልችቶኛል፡፡
ምክንያቴን ስናገር ውስጥ ውስጤን ያመኛል
መፍትሄው ላይመጣ ብሶት ይወረኛል፡፡
✍✍✍......
ጭንቅ ፡ ትልቅ ጭንቅ
ክፉ ዘመን ፡ ከክፋቱ ሊርቅ፡፡
ሀሳብ ፡ በጣም ኢምንት ሀሳብ
ክፉን ዘመን ንቆ ፡ ደግን ዘመን መካብ፡፡
ለበጣ ፡ ልክ ያጣ ለበጣ
ወገን ወረግቡ ፡ መካኑ ሲታጣ፡፡
ጊዜው ደጉን ጥሎ ፡ ክፉውን ሲያወጣጣ
ትውልድ ፌዝን ብቻ ፡ ቁም ነገር ሲታጣ፡፡
✍✍✍...
ሁሉ ሲያምጥ ውሎ
የመውለጃው ቀን ረዝሞ እንደቀንዘል
እጸጹን አግዝፎት ከዘጠኝ ወር ላይዘል፡፡
እንዲያው ብኩን መሆን ላይቆም መንከባለል
እንዲያው ህላዌነት ትርጉም አልባ እምነት፡፡
✍✍✍.....
ዘንድሮማ ፡ ዘንድሮ...አለም ሰለጠነች አሉ ኒዩክለር አመንጥቃ
ብሩን ከባንክ ከካዝናው አጭቃ፡፡
ረጅም ፎቅ ሰርታ ሰማይ ጠቀስ ስትል
ሰማይ ወዲያ ብላ ከዋክብትን ብትል፡፡
ይመስላታል እንጂ ከምድር አትዘልም
መሬት ችላ ካሉት ሰማይ ሰማይ የለም፡፡
ውስጥዋን አሳድፈህ ፡ ውጪን ማጌጥ የለም፡፡
✍✍✍....
ሀሳብዋ ደብዝዞ ፡ ገላዋ ቢበራ
ምድር ሜዳን እንጂ ፡ አታክልም ጋራ፡፡
ደሞ'ስ አንተነትህ ፡ የተፈጠርክበት
ከአፈር መሆኑን ልብህ ባያምንበት፡፡
ፎቁን ሰርተህላት
በወርቅ አስጊጠዓት
ሆቴል ብትከፍትላት
አሸከምካት እንጂ ምንም አልሰራላት፡፡
@hutoffun 👈🏽
@hutoffun 👈🏽
@hutoffun 👈🏽
ወዮ አለ ጉራጌ ፡ ኸረግ ሲል አማራ
ያልጠበቀው ደርሶ ሲጨነቅ ሲፈራ፡፡
እኔም በአንደበቴ እግዚኦን ላክልበት፡ጨንቆኛል ጠቦኛል አጣሁ ምገባበት፡፡
መሮኛል ፡ አው..እውነት ከፍቶኛል
መፍትሄው ጠፍቶኛል፡፡
ፍርሀት ወርሶኛል
ኸረ ወዲያ😔 ..በቃ ሰልችቶኛል፡፡
ምክንያቴን ስናገር ውስጥ ውስጤን ያመኛል
መፍትሄው ላይመጣ ብሶት ይወረኛል፡፡
✍✍✍......
ጭንቅ ፡ ትልቅ ጭንቅ
ክፉ ዘመን ፡ ከክፋቱ ሊርቅ፡፡
ሀሳብ ፡ በጣም ኢምንት ሀሳብ
ክፉን ዘመን ንቆ ፡ ደግን ዘመን መካብ፡፡
ለበጣ ፡ ልክ ያጣ ለበጣ
ወገን ወረግቡ ፡ መካኑ ሲታጣ፡፡
ጊዜው ደጉን ጥሎ ፡ ክፉውን ሲያወጣጣ
ትውልድ ፌዝን ብቻ ፡ ቁም ነገር ሲታጣ፡፡
✍✍✍...
ሁሉ ሲያምጥ ውሎ
የመውለጃው ቀን ረዝሞ እንደቀንዘል
እጸጹን አግዝፎት ከዘጠኝ ወር ላይዘል፡፡
እንዲያው ብኩን መሆን ላይቆም መንከባለል
እንዲያው ህላዌነት ትርጉም አልባ እምነት፡፡
✍✍✍.....
ዘንድሮማ ፡ ዘንድሮ...አለም ሰለጠነች አሉ ኒዩክለር አመንጥቃ
ብሩን ከባንክ ከካዝናው አጭቃ፡፡
ረጅም ፎቅ ሰርታ ሰማይ ጠቀስ ስትል
ሰማይ ወዲያ ብላ ከዋክብትን ብትል፡፡
ይመስላታል እንጂ ከምድር አትዘልም
መሬት ችላ ካሉት ሰማይ ሰማይ የለም፡፡
ውስጥዋን አሳድፈህ ፡ ውጪን ማጌጥ የለም፡፡
✍✍✍....
ሀሳብዋ ደብዝዞ ፡ ገላዋ ቢበራ
ምድር ሜዳን እንጂ ፡ አታክልም ጋራ፡፡
ደሞ'ስ አንተነትህ ፡ የተፈጠርክበት
ከአፈር መሆኑን ልብህ ባያምንበት፡፡
ፎቁን ሰርተህላት
በወርቅ አስጊጠዓት
ሆቴል ብትከፍትላት
አሸከምካት እንጂ ምንም አልሰራላት፡፡
@hutoffun 👈🏽
@hutoffun 👈🏽
@hutoffun 👈🏽
........"ኑሮን ምን ላድርገው"......
አቦ ምን ላድርግህ ምንስ አደረኩኝ
በሀሳብ ነጎድጓድ የምታስጨንቀኝ
ምን ወንጀል ሰርቼ እንድህስ ያረከኝ
በጭንቀት ታጅቤ ራሴን የሳትኩኝ
በፍቅር ትዝታ ቀልቤን የረሳሁኝ
ፍቅር ፍቅር እያልኩ ልቤን ያቃጠልኩኝ
በልጂቷ ፍቅር ባጥር ተከብቤ
ሳስባት ብኖርም ላልዘልቀው አስቤ
እንደዚህ ከምሆን አቦቦ ከጭንቅ አውጣኝ
ከማልቀስ ከማሰብ ብትገላግለኝ
ከዚህ ሁሉ ጣጣ ባጭሩ ቢበቃኝ
ኑሮን አመቻችተህ ወይም ባንድ አድርገኝ
በጣም ብዙ ጊዜ በፍቅሯ ታሰርኩኝ
በጣም ብዙ ግዜ በጣምም ለመንኩኝ
ትንሽም አዝናልኝ ተስፋን አነገብኩኝ
ግን ታዳ። 😢😡
ሀሳቤን ተረድታ ፍቅሬን ተረድታልኝ
ስወዳት እንደኖርኩ በጥቂቱ አውቃልኝ
እሽታም ተብዬ ጭንቀቴን አክማኝ
ታዳ ከዚህ በላይ እሷስ ምን ታድርገኝ
ብቻ
ፍራት ፍራት ሲለኝ
ጭንቅ ጭንቅ ሲለኝ
ከሀገር ወጥቸ ልሄድ ነው ስትለኝ
ሌላ ሰው እንዳላት ብዬ ጠረጠርኩኝ
ጭንቀቱ በዛብኝ ልትርቀኝ መሰለኝ
አቦ በልክ ሁን መንታ ልብ አታርገኝ
አቦ ምን ላድርግህ ምንስ አደረኩኝ
የፈለኩትማ ከሷ ጋር አኑረኝ
እሷንም እንደኔ ፍቅር አስይዝልኝ
እሷ ከጠላችኝ እኔንም አስጠላኝ
የሁልጊዜን ጭንቀት ከንግድህ አንሳልኝ
ከሀሳብ ገላግለክ አቦ ሰላም ስጠኝ
ተረማመድ ከሰው እንግድህ ልቀቀኝ(2)
@hutoffun 👈🏽
@hutoffun 👈🏽
@hutoffun 👈🏽
አቦ ምን ላድርግህ ምንስ አደረኩኝ
በሀሳብ ነጎድጓድ የምታስጨንቀኝ
ምን ወንጀል ሰርቼ እንድህስ ያረከኝ
በጭንቀት ታጅቤ ራሴን የሳትኩኝ
በፍቅር ትዝታ ቀልቤን የረሳሁኝ
ፍቅር ፍቅር እያልኩ ልቤን ያቃጠልኩኝ
በልጂቷ ፍቅር ባጥር ተከብቤ
ሳስባት ብኖርም ላልዘልቀው አስቤ
እንደዚህ ከምሆን አቦቦ ከጭንቅ አውጣኝ
ከማልቀስ ከማሰብ ብትገላግለኝ
ከዚህ ሁሉ ጣጣ ባጭሩ ቢበቃኝ
ኑሮን አመቻችተህ ወይም ባንድ አድርገኝ
በጣም ብዙ ጊዜ በፍቅሯ ታሰርኩኝ
በጣም ብዙ ግዜ በጣምም ለመንኩኝ
ትንሽም አዝናልኝ ተስፋን አነገብኩኝ
ግን ታዳ። 😢😡
ሀሳቤን ተረድታ ፍቅሬን ተረድታልኝ
ስወዳት እንደኖርኩ በጥቂቱ አውቃልኝ
እሽታም ተብዬ ጭንቀቴን አክማኝ
ታዳ ከዚህ በላይ እሷስ ምን ታድርገኝ
ብቻ
ፍራት ፍራት ሲለኝ
ጭንቅ ጭንቅ ሲለኝ
ከሀገር ወጥቸ ልሄድ ነው ስትለኝ
ሌላ ሰው እንዳላት ብዬ ጠረጠርኩኝ
ጭንቀቱ በዛብኝ ልትርቀኝ መሰለኝ
አቦ በልክ ሁን መንታ ልብ አታርገኝ
አቦ ምን ላድርግህ ምንስ አደረኩኝ
የፈለኩትማ ከሷ ጋር አኑረኝ
እሷንም እንደኔ ፍቅር አስይዝልኝ
እሷ ከጠላችኝ እኔንም አስጠላኝ
የሁልጊዜን ጭንቀት ከንግድህ አንሳልኝ
ከሀሳብ ገላግለክ አቦ ሰላም ስጠኝ
ተረማመድ ከሰው እንግድህ ልቀቀኝ(2)
@hutoffun 👈🏽
@hutoffun 👈🏽
@hutoffun 👈🏽
................"እንባዬ"..................
ማንም በሌለበት፣በዛ ሙሉ ቤቴ ብቻዬን ቀርቼ
ሲኖረኝ የመጣ፣ሳጣ የሚያቅፈኝ ወዳጄን አጥቼ
ይሄው እኖራለው ከ እንባ ተሟግቼ
እባክህ እንባዬ ናልኝ ቶሎ ድረስ
ልቤን ሊመታት ነው የሀዘን መትረየስ
አውቃለው አንተ ጋር አይጠፋም መፍቴሁ
መጥተ እጠብልኝ ሀዘኔን ፍታሁ
እኔስ ግራ ገባኝ ሳስብ ያንተን ነገር
በደስታም ባዘንም መምጣጥክ የማይቀር
ሰው ተደስቶ፣ድብልቅልቅ ብሎበት ሰማይ ከምድሩ
ሌላውም ተከፍቶ ልቡ ተሰባብሮ፣ሊከፈል ብድሩ
እንባውም ይመጣል፣ልቡም ይታደሳል
የጎዳውን ረስቶት፣ይቅር ይባባላል
ይቅርታን ጠይቆ፣ፍቅርን ይለግሳል
እንባዬ......ባለ ውለታዬ
ሰው ሁሉ ይቅርብኝ ሁነኝ መከታዬ
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
ማንም በሌለበት፣በዛ ሙሉ ቤቴ ብቻዬን ቀርቼ
ሲኖረኝ የመጣ፣ሳጣ የሚያቅፈኝ ወዳጄን አጥቼ
ይሄው እኖራለው ከ እንባ ተሟግቼ
እባክህ እንባዬ ናልኝ ቶሎ ድረስ
ልቤን ሊመታት ነው የሀዘን መትረየስ
አውቃለው አንተ ጋር አይጠፋም መፍቴሁ
መጥተ እጠብልኝ ሀዘኔን ፍታሁ
እኔስ ግራ ገባኝ ሳስብ ያንተን ነገር
በደስታም ባዘንም መምጣጥክ የማይቀር
ሰው ተደስቶ፣ድብልቅልቅ ብሎበት ሰማይ ከምድሩ
ሌላውም ተከፍቶ ልቡ ተሰባብሮ፣ሊከፈል ብድሩ
እንባውም ይመጣል፣ልቡም ይታደሳል
የጎዳውን ረስቶት፣ይቅር ይባባላል
ይቅርታን ጠይቆ፣ፍቅርን ይለግሳል
እንባዬ......ባለ ውለታዬ
ሰው ሁሉ ይቅርብኝ ሁነኝ መከታዬ
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
📚📚📚📚📚📚📚
አንድ እውነት አንድ ቀን
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
.
አንድ እንጨት አይነድም
አንድ እግር አይሔድም"
አንድ እጅ ብቻውን ፣ አያጨበጭብም"
ብሎ ይተርታል...
ህብረትና ብዛት ፣ የሚመስለው አቅም
ሁሉን ለማዳን ሲል...
አንድ እንደሚሰቀል ፣ ፈፅም አያውቅም፡፡
፡፡፡፡፡
እርግጥ ነው
እውነት ነው
አንድ እንጨት ባይነድም ፣ አንድ ጧፍ ይነዳል
አንድ እግር ባይሔድም...
ያለምንም እግር ፣ በደረት ይኬዳል
አንድ እጅ ብቻውን
ባያጨበጭብም
አንድ ጣት ይሾማል ፣ አንድ ጣት ያወርዳል
አንድነት አቅም ነው!!!
አንድ እውነት ይዳኛል ፣ አንድ ቀን ይፈርዳል!!!
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈🏾
አንድ እውነት አንድ ቀን
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
.
አንድ እንጨት አይነድም
አንድ እግር አይሔድም"
አንድ እጅ ብቻውን ፣ አያጨበጭብም"
ብሎ ይተርታል...
ህብረትና ብዛት ፣ የሚመስለው አቅም
ሁሉን ለማዳን ሲል...
አንድ እንደሚሰቀል ፣ ፈፅም አያውቅም፡፡
፡፡፡፡፡
እርግጥ ነው
እውነት ነው
አንድ እንጨት ባይነድም ፣ አንድ ጧፍ ይነዳል
አንድ እግር ባይሔድም...
ያለምንም እግር ፣ በደረት ይኬዳል
አንድ እጅ ብቻውን
ባያጨበጭብም
አንድ ጣት ይሾማል ፣ አንድ ጣት ያወርዳል
አንድነት አቅም ነው!!!
አንድ እውነት ይዳኛል ፣ አንድ ቀን ይፈርዳል!!!
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈🏾