ገጣሚ የግድ መጎሳቆል ፣ መንጨባረርና ፣ መዝረክረክ አለበት ያለው ማነው? ያው ሹሩባዬ የንግስናዬ ጅማሬ ነው። ስነግስ ሙሉ ይሆናል ። ከዚህ ቀደም እንደነገርኳችሁ የንግስና ስሜ "ተክለ መቃር" ይባላል ። እስቲ ከተነገሩልኝ ብዙ ትንቢቶች ውስጥ አንዱን ልጋብዛችሁ።
።።።።
"ላጤ በላይ" ያሉት ፣ አጤ ተክለ መቃር
የኢትዮጵያ ግሳት ፣ የጠላቶቿ ቃር
በነገሰ ጊዜ
መቀራረብ እንጂ ፣ አይኖርም መቃቃር!
(ንጉስ ተክለ መቃር ዘእም ነገደ ሰው!)
።።።
👉ደግሞ እሰሩኝ አሏቹ😂
#ሼር
@hutoffun
።።።።
"ላጤ በላይ" ያሉት ፣ አጤ ተክለ መቃር
የኢትዮጵያ ግሳት ፣ የጠላቶቿ ቃር
በነገሰ ጊዜ
መቀራረብ እንጂ ፣ አይኖርም መቃቃር!
(ንጉስ ተክለ መቃር ዘእም ነገደ ሰው!)
።።።
👉ደግሞ እሰሩኝ አሏቹ😂
#ሼር
@hutoffun
በመፈለግ ውስጥ አለመፈለግ
ትመጣለች ብዬ ዘወትር ጥበቃ
ደግም እንደገና ኧረ ትቅር በቃ
ወይ ብትመጪ ወይ ብትቀሪ ምን አለበት
ሁለት ሀሳብ ይዞኝ እንዲ ስንከራተት
የኔ ናት እያለ ልቤ ሲጠብቃት
በተስፋ ጭላንጭል በምናቡ እያያት
ተስፋ አልቆርጥም በሷ ብትዘገይም በጣም
ፈጣሪ የሰጠኝን ማንም አይወስዳትም
ይህን እያሰበ ልቤ ባለተስፋው
ሌላኛው ተነሳ ተስፋ የቆረጠው
አሁን ረስቻታለሁ ወጣለች ከሀሳቤ
ይህን ተናገረ ተስፋ የቆረጠው ልቤ
ብትመጣ ብትሄድ እኔ ምን አገባኝ
ከተጣላንማ ምንም ደንታ የለኝ
ልቤ ሲወዛገብ ተከፍሎ ለሁለት
እንግዲ ላስማማ ሁለቱን በአንድነት
መቼም አትመለሽ ቅሪ በሄድሽበት
ልቤ በትዝታሽ ይኖራል ደስ ብሎት
ዘኢትነውም
@hutoffun
@hutoffun
ትመጣለች ብዬ ዘወትር ጥበቃ
ደግም እንደገና ኧረ ትቅር በቃ
ወይ ብትመጪ ወይ ብትቀሪ ምን አለበት
ሁለት ሀሳብ ይዞኝ እንዲ ስንከራተት
የኔ ናት እያለ ልቤ ሲጠብቃት
በተስፋ ጭላንጭል በምናቡ እያያት
ተስፋ አልቆርጥም በሷ ብትዘገይም በጣም
ፈጣሪ የሰጠኝን ማንም አይወስዳትም
ይህን እያሰበ ልቤ ባለተስፋው
ሌላኛው ተነሳ ተስፋ የቆረጠው
አሁን ረስቻታለሁ ወጣለች ከሀሳቤ
ይህን ተናገረ ተስፋ የቆረጠው ልቤ
ብትመጣ ብትሄድ እኔ ምን አገባኝ
ከተጣላንማ ምንም ደንታ የለኝ
ልቤ ሲወዛገብ ተከፍሎ ለሁለት
እንግዲ ላስማማ ሁለቱን በአንድነት
መቼም አትመለሽ ቅሪ በሄድሽበት
ልቤ በትዝታሽ ይኖራል ደስ ብሎት
ዘኢትነውም
@hutoffun
@hutoffun
ልመላለስበት
🚶♂🚶♂🚶♂🚶♂
ኣይንና ኣፍንጫሽን፥
ያንን ዕንቍ ከንፈር፣
የሠራ ኣካልሽን፥
እንዲሁ ሣማትር፣
እረፊው ልንገርሽ፥
ኣይኖቼን ያመኛል።
ደሞ ስታዋሪኝ፥
ስትቀበጠበጪ፣
ስትሞላቀቂ፥
ስትሞላፈጪ፣
የኔን ተራ ጆሮ፥
ላንቺ የሠጠኹ 'ለታ፣
የጆሮ ህመሜ፥
በኔው ላይ በረታ።
ያንን ሽቱ ጠረን፥
ተጠግቼሽ ላንዴ፣
ያሸተትኩበት ቀን፥
ተላውሷል ሇዴ።
ወደ'ኔ ስትመጪ...፣
መላው ሠውነቴን፥
በህመም ብትነጪ፣
ሌላውን ተዪና፥
እግሮቼን ኣትቅጪ።
ተንከባክበሽ ስጪኝ፥
ካንቺ ዘንድ ካዋልኩት፣
ከእኔ ቤት ኣንቺ ቤት፥
ልመላለስበት።
(የዱድያሌብ ገፅ)🤨
ይድረስ ለእግሬ'ዬ
@hutoffun
@hutoffun
@hutoffun
🚶♂🚶♂🚶♂🚶♂
ኣይንና ኣፍንጫሽን፥
ያንን ዕንቍ ከንፈር፣
የሠራ ኣካልሽን፥
እንዲሁ ሣማትር፣
እረፊው ልንገርሽ፥
ኣይኖቼን ያመኛል።
ደሞ ስታዋሪኝ፥
ስትቀበጠበጪ፣
ስትሞላቀቂ፥
ስትሞላፈጪ፣
የኔን ተራ ጆሮ፥
ላንቺ የሠጠኹ 'ለታ፣
የጆሮ ህመሜ፥
በኔው ላይ በረታ።
ያንን ሽቱ ጠረን፥
ተጠግቼሽ ላንዴ፣
ያሸተትኩበት ቀን፥
ተላውሷል ሇዴ።
ወደ'ኔ ስትመጪ...፣
መላው ሠውነቴን፥
በህመም ብትነጪ፣
ሌላውን ተዪና፥
እግሮቼን ኣትቅጪ።
ተንከባክበሽ ስጪኝ፥
ካንቺ ዘንድ ካዋልኩት፣
ከእኔ ቤት ኣንቺ ቤት፥
ልመላለስበት።
(የዱድያሌብ ገፅ)🤨
ይድረስ ለእግሬ'ዬ
@hutoffun
@hutoffun
@hutoffun
#የዘንድሮ_ነገር
ሟችን ባጀብ መቅበር
ተከልክሎ ባገር
የዘንድሮ ነገር
ተጎልቶ መድከም
ሐዘንን እንደ ዘውድ ለብቻ መሸከም!
በየሰው ጉንጭ ላይ ፤እንባ ቀልጦ እንደ ሰም
ደረት ሳይጎሰም
ፍታት ሳይፈታ
ያለ ምንም ሙሾ፤ ያለምን ዋይታ
ብቻየን ቀብር ዋልሁ
ከእድሜየ መካከል፤ አንድ አመቴ ሞታ ።
🧿በእውቀቱ ስዩም🧿
@hutoffun👈
@hutoffun👈
ሟችን ባጀብ መቅበር
ተከልክሎ ባገር
የዘንድሮ ነገር
ተጎልቶ መድከም
ሐዘንን እንደ ዘውድ ለብቻ መሸከም!
በየሰው ጉንጭ ላይ ፤እንባ ቀልጦ እንደ ሰም
ደረት ሳይጎሰም
ፍታት ሳይፈታ
ያለ ምንም ሙሾ፤ ያለምን ዋይታ
ብቻየን ቀብር ዋልሁ
ከእድሜየ መካከል፤ አንድ አመቴ ሞታ ።
🧿በእውቀቱ ስዩም🧿
@hutoffun👈
@hutoffun👈
#እህትህ_በሆንኩኝ
ባትጠላኝ ባልጠላህ
ባትርቀኝ ባልርቅህ
ምስጢርህን ተካፋይ
ሚስትነትን ሽሮ
ቢያረገኝ እህትህ
ከእናትህ የወጣሁ ያባትህ አሻራ
ጠላትህ ባልመስልህ ባንሆን ባላጋራ
አላጣህም ነበር አስተሳስሮን ደሜ
እህትህ ተብዬ ብትባል ወንድሜ
ወደህ የማትፍቀው ጠልተህ የማትሽረው
በደም አስተሳስሮ ፈጣሪ ያኖረው
ፍቅርስ ይሄ ነው ቆርጠህ የማትጥለው።
@hutoffun👈
@hutoffun👈
ባትጠላኝ ባልጠላህ
ባትርቀኝ ባልርቅህ
ምስጢርህን ተካፋይ
ሚስትነትን ሽሮ
ቢያረገኝ እህትህ
ከእናትህ የወጣሁ ያባትህ አሻራ
ጠላትህ ባልመስልህ ባንሆን ባላጋራ
አላጣህም ነበር አስተሳስሮን ደሜ
እህትህ ተብዬ ብትባል ወንድሜ
ወደህ የማትፍቀው ጠልተህ የማትሽረው
በደም አስተሳስሮ ፈጣሪ ያኖረው
ፍቅርስ ይሄ ነው ቆርጠህ የማትጥለው።
@hutoffun👈
@hutoffun👈
ዘፈን revolution
ክፍል-፩
🎼🎤🎷🎺🎻
ድሮ ዘፈን ስትዘፈን ገና ድሮሮሮ....
ምትና ቅላፄ ግጥምም ነበራት፣
ትጋራት ነበር የጥበብን ስልት።
ደሞ ስትል ቆየት...
ትናጥ ትጥመለመል ትለጠጥ ነበረ፣
እንዳበበች ሔዳ ትኮስም፣ትሳሳ ትታመም ጀመረ፣
ከጥበብ 'ርቃ ስሜት ሇና ስትቀር፣
ተጨዋወቱባት ኣረጓት ምንቅርቅር።
ድምፀቱ ቀረና መልክ ብቻ ሇነ፣
ጭፈራ ተተካ መላላጥ ሠፈነ።
ኣጥንት ነኪን ግጥም ኣባረሩትና፣
ኣንተ ኣራሙን ግጥም በሞቴ ግባ ና፣
ያው ኣሁን እንደምናያት...
ከምት ፣ከዜማ፣ ከጥበብ 'ርቃ፣
ቀርታለች በመንገድ፥ ፌርማታ ኣዘባርቃ።
..አይይይይይ ሙዚቃ
(የዱድያሌብ ገፅ)
@hutoffun
ክፍል-፩
🎼🎤🎷🎺🎻
ድሮ ዘፈን ስትዘፈን ገና ድሮሮሮ....
ምትና ቅላፄ ግጥምም ነበራት፣
ትጋራት ነበር የጥበብን ስልት።
ደሞ ስትል ቆየት...
ትናጥ ትጥመለመል ትለጠጥ ነበረ፣
እንዳበበች ሔዳ ትኮስም፣ትሳሳ ትታመም ጀመረ፣
ከጥበብ 'ርቃ ስሜት ሇና ስትቀር፣
ተጨዋወቱባት ኣረጓት ምንቅርቅር።
ድምፀቱ ቀረና መልክ ብቻ ሇነ፣
ጭፈራ ተተካ መላላጥ ሠፈነ።
ኣጥንት ነኪን ግጥም ኣባረሩትና፣
ኣንተ ኣራሙን ግጥም በሞቴ ግባ ና፣
ያው ኣሁን እንደምናያት...
ከምት ፣ከዜማ፣ ከጥበብ 'ርቃ፣
ቀርታለች በመንገድ፥ ፌርማታ ኣዘባርቃ።
..አይይይይይ ሙዚቃ
(የዱድያሌብ ገፅ)
@hutoffun