🌹።።።።።🌹የፍቅር ጅማሮ🌹።።።።🌹
አዳምና ሄዋን ፍቅራቸው ሲጀመር
ታሪኩ እንዲህ ነበር
ሄዋን ፍቅር ይዟት ተጨንቃ ተጠባ
ስትል ፈራ ተባ
ቆይታ ቆይታ
እንደዚ አለችው አዳምን ተጣርታ
"ምን ብዬ ልንገርህ
አዳም የኔ ፍቅር
ፍቅርህን እሻለሁ
በጣም እወድሃለሁ
መልሥህን ንገረኝ እባክህ በሞቴ
ፍቅሬን ተቀበለኝ አዳም አካላቴ"
በማለት ጠይቃው ልቧ ሲንሠፈሠፍ
"ምን አማራጭ አለኝ!" አላትና እርፍ
ከዚያን ጊዜ ወዲህ ምን በፍቅር ብታልቅ
ከሡ ይምጣ እንጂ እሷ ጠይቃ አታውቅ!
*....*...❣🌹❣🌹❣🌹❣🌹❣....*...*
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
አዳምና ሄዋን ፍቅራቸው ሲጀመር
ታሪኩ እንዲህ ነበር
ሄዋን ፍቅር ይዟት ተጨንቃ ተጠባ
ስትል ፈራ ተባ
ቆይታ ቆይታ
እንደዚ አለችው አዳምን ተጣርታ
"ምን ብዬ ልንገርህ
አዳም የኔ ፍቅር
ፍቅርህን እሻለሁ
በጣም እወድሃለሁ
መልሥህን ንገረኝ እባክህ በሞቴ
ፍቅሬን ተቀበለኝ አዳም አካላቴ"
በማለት ጠይቃው ልቧ ሲንሠፈሠፍ
"ምን አማራጭ አለኝ!" አላትና እርፍ
ከዚያን ጊዜ ወዲህ ምን በፍቅር ብታልቅ
ከሡ ይምጣ እንጂ እሷ ጠይቃ አታውቅ!
*....*...❣🌹❣🌹❣🌹❣🌹❣....*...*
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
የጥበብ ጎጆ
🌹።።።።።🌹የፍቅር ጅማሮ🌹።።።።🌹 አዳምና ሄዋን ፍቅራቸው ሲጀመር ታሪኩ እንዲህ ነበር ሄዋን ፍቅር ይዟት ተጨንቃ ተጠባ ስትል ፈራ ተባ ቆይታ ቆይታ እንደዚ አለችው አዳምን ተጣርታ "ምን ብዬ ልንገርህ አዳም የኔ ፍቅር ፍቅርህን እሻለሁ በጣም እወድሃለሁ መልሥህን ንገረኝ እባክህ በሞቴ ፍቅሬን ተቀበለኝ አዳም አካላቴ" በማለት ጠይቃው ልቧ ሲንሠፈሠፍ "ምን አማራጭ አለኝ!" አላትና እርፍ ከዚያን…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from 666( ኢልሙናቲ ) ሀይማኖት ምዝገባ ማእከል via @Josy_Button_Bot
እንደ ቀድሞው ባላስቀድስ ፥ ባላነጋ ማህሌት ቆሜ
"ሁሩ በሰላም" ሲል ቄሱ ፣ አሜን ባልል ተሳልሜ
ለበረከት ባልጋፋ ፣ ደጀሰላም ተሰይሜ
ዘመን ባመጣው ቡታንታ ፣ አፍ አፍንጫዬን ጠርቅሜ
ነገን ለማየት ጓጉቼ ፣ አልፎ አልፎ ከቤት ብወጣም
"ሰላም ነህ ? የሚል አላጣም
ኧረ ሰላም ነኝ በጣም
።።።።።
ሴት ልጁን የሚደፍር አባት ፣ በየቦታው ፈልቶ እንደአሸን
ወይ ብልቱ ሳይቆረጥ ፣ ዜና ሲሆን ሳይረሸን
እየሰማሁ እያየሁኝ ፣ ስጋ ነፍሴ ምን ቢረበሽ
"ምን የሚሉት ሞኝነት ነው ? ፥ ገዳይ ይዞ ከሞት መሸሽ?
የሚል ጥያቄ ራሴን ፣ ከመጠየቅ አልቦዝንም
ሁሉ ነገር ሰላም ነስቶኝ ፣ በሰላም መኖር ባላምንም
ሰላም ነህ ካሉኝ ሰላም ነኝ ፣ ሰላም ነኝ ሰላም ባልሆንም።
።።።።።
ዛፍ በደጃፌ መትከሌ ፣ ባይሆን እንኳ አጉል ቅንጦት
ከታች ግድብ ለሚገድብ ፣ ጣና ምንጩን አረም ውጦት
ቄሱም ዝም ሸሁም ዝም ሲል ፣ የፀሎት መፅሀፍ ፈልጌ
ብተኛም ትራስ አድርጌ
አካል መንፈሴ ቢዝልም ፣ በሰላም እጦት ጠውልጌ
ሰላም ነህ ካሉኝ ሰላም ነኝ ፣ ሰላም ነኝ እናቴ ትሙት
ሰኔና ሰኞ በሰላም ነው? ፣ ያለ እስካርፕ የገጠሙት?
✍✍✍በላይ በቀለ ወያ
@hutoffun
"ሁሩ በሰላም" ሲል ቄሱ ፣ አሜን ባልል ተሳልሜ
ለበረከት ባልጋፋ ፣ ደጀሰላም ተሰይሜ
ዘመን ባመጣው ቡታንታ ፣ አፍ አፍንጫዬን ጠርቅሜ
ነገን ለማየት ጓጉቼ ፣ አልፎ አልፎ ከቤት ብወጣም
"ሰላም ነህ ? የሚል አላጣም
ኧረ ሰላም ነኝ በጣም
።።።።።
ሴት ልጁን የሚደፍር አባት ፣ በየቦታው ፈልቶ እንደአሸን
ወይ ብልቱ ሳይቆረጥ ፣ ዜና ሲሆን ሳይረሸን
እየሰማሁ እያየሁኝ ፣ ስጋ ነፍሴ ምን ቢረበሽ
"ምን የሚሉት ሞኝነት ነው ? ፥ ገዳይ ይዞ ከሞት መሸሽ?
የሚል ጥያቄ ራሴን ፣ ከመጠየቅ አልቦዝንም
ሁሉ ነገር ሰላም ነስቶኝ ፣ በሰላም መኖር ባላምንም
ሰላም ነህ ካሉኝ ሰላም ነኝ ፣ ሰላም ነኝ ሰላም ባልሆንም።
።።።።።
ዛፍ በደጃፌ መትከሌ ፣ ባይሆን እንኳ አጉል ቅንጦት
ከታች ግድብ ለሚገድብ ፣ ጣና ምንጩን አረም ውጦት
ቄሱም ዝም ሸሁም ዝም ሲል ፣ የፀሎት መፅሀፍ ፈልጌ
ብተኛም ትራስ አድርጌ
አካል መንፈሴ ቢዝልም ፣ በሰላም እጦት ጠውልጌ
ሰላም ነህ ካሉኝ ሰላም ነኝ ፣ ሰላም ነኝ እናቴ ትሙት
ሰኔና ሰኞ በሰላም ነው? ፣ ያለ እስካርፕ የገጠሙት?
✍✍✍በላይ በቀለ ወያ
@hutoffun
#እልፍኟ
ባለፈው አመት ላይ ና ብለኸኝ ነበር
ብዙ ጊዜ ነግረህ ከእልፍኙ እንዳልቀር
ይኸው በአመቱ
ቃልህን አክብሬ ከእልፍኝህ ብገባ
ስም ዝርዝር ውስጥ
የለው ከእልፍኙ እንዳልገባ
ማንም ማይቀርበት
ቤቴ የሁሉም ነው ሲለን የነበረ
ዛሬ በስም ሆኗል የሁሉ እንዳልነበረ
ጥሩ የሚለብሱ ከውስጡ ቢገቡ
ልባሰቸው ነው እንጂ ክፋትን ሚያስቡ
ሚያውደው ሚቀቡት የልብሳቸው ሽቶ
ግብራቸው ሲያጠፋው ስራቸው ከርፍቶ
እልፍኟም የለችም ያቺ የፍቅር ቤት
ዛሬ ተቃርማዋት አድርገዋታል
የግብዞች መሬት
✍ብላቴናው
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
ባለፈው አመት ላይ ና ብለኸኝ ነበር
ብዙ ጊዜ ነግረህ ከእልፍኙ እንዳልቀር
ይኸው በአመቱ
ቃልህን አክብሬ ከእልፍኝህ ብገባ
ስም ዝርዝር ውስጥ
የለው ከእልፍኙ እንዳልገባ
ማንም ማይቀርበት
ቤቴ የሁሉም ነው ሲለን የነበረ
ዛሬ በስም ሆኗል የሁሉ እንዳልነበረ
ጥሩ የሚለብሱ ከውስጡ ቢገቡ
ልባሰቸው ነው እንጂ ክፋትን ሚያስቡ
ሚያውደው ሚቀቡት የልብሳቸው ሽቶ
ግብራቸው ሲያጠፋው ስራቸው ከርፍቶ
እልፍኟም የለችም ያቺ የፍቅር ቤት
ዛሬ ተቃርማዋት አድርገዋታል
የግብዞች መሬት
✍ብላቴናው
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
<< አባ >>
ስምህ ገናና ነበር
የኔ የስም መጠሪያዬ
ከስሜ ስምህ ተከትሎ
የሙሉነት መታያዬ
አባትነትህ ልዩ ነው
ከነውጠኞች የሚበልጥ
ለኔ ለልጅህማ
አለምን ሁሉ ሚገለብጥ
.. ዛሬ ግን..........
አባ ፈራሁ ተጨነኩኝ
ስሷ ልቤ ተቀየመች....
ካልጠበኩህ ቦታ ተገኝተህ
ምስኪን ልቤ አለቀሰች...
አዎን አባ ተቀየምኩህ
አምርሬ አነባሁኝ...
እጅህ ቀሚሴን ሲገልብ
ከባትነትህ ጠፍቶ
የአውሬ ፊትህን አየሁኝ.....
.......ግን ያልገባኝ የኔ አባት......
ምን የማታውቀው ውበት
የቱ የተደበቀ ደም ግባት
ከእኔ አልጅህ ዘንድ አየህ...
ልብህ ለሴሰኝነት ተገዝቶ
ከአባትነትህ አስበልጦ
እርካታህን ያስመረጠህ
እስኪ ተናገር ካለ
ያላየኸው የደበኩህ ልጅነቴን
ስታቅፈኝ እኮ ታውቀዋለህ
ስትኮረኩር
ስትደባብስ ሰውነቴን
አባዬ.....
አሁንም አባቴ ነህ
ስምህን የምጠራበት
ያሳደገኝ ነውና
አንገቴን ሳልደፋ በፊት
ምጠራ' የኮራሁበት
* * * * * *
ስምህ ገናና ነበር
የኔ የስም መጠሪያዬ
ከስሜ ስምህ ተከትሎ
የሙሉነት መታያዬ
* * * * * *
አዎን አባዬ...
ትዝ ይልሀል...አፌን ስፈታ ገና
አባዬ ነበር ያልኩኝ
የማነሽ ሲሉኝ እንኳን
ያባቴ ልጅ ነበር ያልኩትኝ
ዛሬ ግን....
ሴሰኝነትህ በለጠ~ ከትውስታችን አለፈና
ከእናቴ ያጣኸውን ከኔ ከልጅህ ፈለክና
እናቴ ስታልፍ እንኳን
አንተ ነበርክ እናቴ
ሰው በራበኝ ግዜ እራሱ
ሆነሀልም ጓደኛዬ....
ከዛ ሚበልጠው ግን
አባቴ ብዬህ ነበር
እኔነቴን የሚገልፅ
ክብር መከታዬ እንደ ነበር
አሁንማ....
አንተው በፈጠርከው ገላ ላይ
ተረማምደህ አረከስከው
የወደፊት እኔነቴን
በአውሬነት ደመሰስከው
አዎን የኔ....... ጀግና አባት
እውትትም ወንድ ወጥቶሀል
ሴት የሆንክ መስሎኝ ነበር
እኔን ለማሳደግ፣
ስመለከት ከሴት መሀል
ብዬ ነበር የኔ አባት
እውነትም እናት ሆኗል
ስሷ ልቤን አስከፋሀት
አዎን አባ ተቀየምኩህ
እንድተኛ
ተረት በነገርከኝ ቦታ ላይ
ዛሬ ግን
ከጭኖቼ መሀል አገኘሁህ.....
📩ይድረስ📩
<< በከባቷ ህይወቷን ለተቀማችው ህፃን>>
✍ተፃፈ በ ማክቤል
ሰኔ,2,2012
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
<< አባ >>
ስምህ ገናና ነበር
የኔ የስም መጠሪያዬ
ከስሜ ስምህ ተከትሎ
የሙሉነት መታያዬ
አባትነትህ ልዩ ነው
ከነውጠኞች የሚበልጥ
ለኔ ለልጅህማ
አለምን ሁሉ ሚገለብጥ
.. ዛሬ ግን..........
አባ ፈራሁ ተጨነኩኝ
ስሷ ልቤ ተቀየመች....
ካልጠበኩህ ቦታ ተገኝተህ
ምስኪን ልቤ አለቀሰች...
አዎን አባ ተቀየምኩህ
አምርሬ አነባሁኝ...
እጅህ ቀሚሴን ሲገልብ
ከባትነትህ ጠፍቶ
የአውሬ ፊትህን አየሁኝ.....
.......ግን ያልገባኝ የኔ አባት......
ምን የማታውቀው ውበት
የቱ የተደበቀ ደም ግባት
ከእኔ አልጅህ ዘንድ አየህ...
ልብህ ለሴሰኝነት ተገዝቶ
ከአባትነትህ አስበልጦ
እርካታህን ያስመረጠህ
እስኪ ተናገር ካለ
ያላየኸው የደበኩህ ልጅነቴን
ስታቅፈኝ እኮ ታውቀዋለህ
ስትኮረኩር
ስትደባብስ ሰውነቴን
አባዬ.....
አሁንም አባቴ ነህ
ስምህን የምጠራበት
ያሳደገኝ ነውና
አንገቴን ሳልደፋ በፊት
ምጠራ' የኮራሁበት
* * * * * *
ስምህ ገናና ነበር
የኔ የስም መጠሪያዬ
ከስሜ ስምህ ተከትሎ
የሙሉነት መታያዬ
* * * * * *
አዎን አባዬ...
ትዝ ይልሀል...አፌን ስፈታ ገና
አባዬ ነበር ያልኩኝ
የማነሽ ሲሉኝ እንኳን
ያባቴ ልጅ ነበር ያልኩትኝ
ዛሬ ግን....
ሴሰኝነትህ በለጠ~ ከትውስታችን አለፈና
ከእናቴ ያጣኸውን ከኔ ከልጅህ ፈለክና
እናቴ ስታልፍ እንኳን
አንተ ነበርክ እናቴ
ሰው በራበኝ ግዜ እራሱ
ሆነሀልም ጓደኛዬ....
ከዛ ሚበልጠው ግን
አባቴ ብዬህ ነበር
እኔነቴን የሚገልፅ
ክብር መከታዬ እንደ ነበር
አሁንማ....
አንተው በፈጠርከው ገላ ላይ
ተረማምደህ አረከስከው
የወደፊት እኔነቴን
በአውሬነት ደመሰስከው
አዎን የኔ....... ጀግና አባት
እውትትም ወንድ ወጥቶሀል
ሴት የሆንክ መስሎኝ ነበር
እኔን ለማሳደግ፣
ስመለከት ከሴት መሀል
ብዬ ነበር የኔ አባት
እውነትም እናት ሆኗል
ስሷ ልቤን አስከፋሀት
አዎን አባ ተቀየምኩህ
እንድተኛ
ተረት በነገርከኝ ቦታ ላይ
ዛሬ ግን
ከጭኖቼ መሀል አገኘሁህ.....
📩ይድረስ📩
<< በከባቷ ህይወቷን ለተቀማችው ህፃን>>
✍ተፃፈ በ ማክቤል
ሰኔ,2,2012
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
ይድረስ ለኮሮና
እንደምን ነህ ኮቪድ.......... እንዴት ነህ ኮሮና?፣
እኛን አሉ አትበለን .............የለንም በደህና።
*******
ዕድሜ ይንሳህና............... ከመጣህ በኋላ፣
ሰው ከሰው እራቀ ............እጅ ከፊት ተጣላ፣
ጥሮ ግሮ መብላት............አፈር ድሜ በላ።
*****
ደጅ አድባሩ ሜዳው ........ቀዬው ተናፈቀ፣
ሰው በረንዳን ፈርቶ..........ማጀት ተደበቀ።
*****
አለም ተናወጠች............ ተናጋ ሰላሟ፣
እጃችን በውሀ............... እየሳሳ ሟሟ።
******
መሳቅ ታሪክ ሊሆን......... አፋችን ታፈነ፣
በስጋት መነመን............ "ገል"አችን ተነነ።
*******
እናም ኮሮናዬ
እኛን እንዳየህን፣
ከሰሪያችን ውጪ ......መመኪያ የሌለን፣
ምስኪን ፍጥረቶች ነን።
*********
በጠባብ ጎጆ ውስጥ ........ሀያ ሁነን ኗሪ"፣
ላንድ ሟች አሰከሬን........ አስር ሺ ቀባሪ።
ሰርጋችን ገበያው....... ቤተ እምነት ተዝካሩ፣
ስብከታችን ህብረት........ ሚሉን "ተደመሩ"።
ወባ ታይፈስ ታይፎድ........... የብሔር በሽታ፣
ሚንጡን ነንና............... እኛ ላይ አትበርታ።
ይልቁንስ ኮቪድ
የእኛን አንተን መናቅ .........."አፉ" በለንና፣
አሳዘኑኝ በለው ...............ለላከህ ሂድና።
ገጣሚ/10 ያብ(ባባ)
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
እንደምን ነህ ኮቪድ.......... እንዴት ነህ ኮሮና?፣
እኛን አሉ አትበለን .............የለንም በደህና።
*******
ዕድሜ ይንሳህና............... ከመጣህ በኋላ፣
ሰው ከሰው እራቀ ............እጅ ከፊት ተጣላ፣
ጥሮ ግሮ መብላት............አፈር ድሜ በላ።
*****
ደጅ አድባሩ ሜዳው ........ቀዬው ተናፈቀ፣
ሰው በረንዳን ፈርቶ..........ማጀት ተደበቀ።
*****
አለም ተናወጠች............ ተናጋ ሰላሟ፣
እጃችን በውሀ............... እየሳሳ ሟሟ።
******
መሳቅ ታሪክ ሊሆን......... አፋችን ታፈነ፣
በስጋት መነመን............ "ገል"አችን ተነነ።
*******
እናም ኮሮናዬ
እኛን እንዳየህን፣
ከሰሪያችን ውጪ ......መመኪያ የሌለን፣
ምስኪን ፍጥረቶች ነን።
*********
በጠባብ ጎጆ ውስጥ ........ሀያ ሁነን ኗሪ"፣
ላንድ ሟች አሰከሬን........ አስር ሺ ቀባሪ።
ሰርጋችን ገበያው....... ቤተ እምነት ተዝካሩ፣
ስብከታችን ህብረት........ ሚሉን "ተደመሩ"።
ወባ ታይፈስ ታይፎድ........... የብሔር በሽታ፣
ሚንጡን ነንና............... እኛ ላይ አትበርታ።
ይልቁንስ ኮቪድ
የእኛን አንተን መናቅ .........."አፉ" በለንና፣
አሳዘኑኝ በለው ...............ለላከህ ሂድና።
ገጣሚ/10 ያብ(ባባ)
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
Forwarded from 666( ኢልሙናቲ ) ሀይማኖት ምዝገባ ማእከል via @Josy_Button_Bot
ንቃ
.
.
''ባለፀጋ እኮ ነህ ዘመንን የጨበጥክ
ጊዜን የመሰለ ውድ እንቁን የተቸርክ
ብትፈልግ ዛሬ አለህ ካሻህ ደሞ ነገ
ወይ ደሞ ቡሀላ
ተንፈላሰህ ተኛ ህይወት ልኳን አልፋ
አትጎድል አትሞላ''
ብሎ ያጃጃለህ የቀድሞ ወዳጅህ
ሄዷል አንተን ጥሎ ጊዜን ተከትሎ
ይልቅስ ልንገርህ
የጊዜ ባለቤት እራሱ ነውና
ብዙም አትኮፈስ ብዙም አትዝናና
ቡሀላንስ ተወው የኔ ያልካት አሁን
አሁን ''አሁን'' ያልካት
አለፈች አየሀት አሁን ላይ ቅድም ናት
ከእጅህ ላይ የለችም ያንተ አይደለችም
ቅድም አሁን ስትል ለማለትህ እንኳን
ማስረጃህስ የታል?
ይልቅ ከሰማህኝ ልብ በለኝማ
ይዘህ ካልተገኘህ አማኝም እማኝም አታገኝምና
ተነሳ ተራመድ ከዘመኑ ጋራ
ህይወት ልክ የላትም አትሞላም አትፍራ ።
✍ሀወኒ ገመቹ
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
.
.
''ባለፀጋ እኮ ነህ ዘመንን የጨበጥክ
ጊዜን የመሰለ ውድ እንቁን የተቸርክ
ብትፈልግ ዛሬ አለህ ካሻህ ደሞ ነገ
ወይ ደሞ ቡሀላ
ተንፈላሰህ ተኛ ህይወት ልኳን አልፋ
አትጎድል አትሞላ''
ብሎ ያጃጃለህ የቀድሞ ወዳጅህ
ሄዷል አንተን ጥሎ ጊዜን ተከትሎ
ይልቅስ ልንገርህ
የጊዜ ባለቤት እራሱ ነውና
ብዙም አትኮፈስ ብዙም አትዝናና
ቡሀላንስ ተወው የኔ ያልካት አሁን
አሁን ''አሁን'' ያልካት
አለፈች አየሀት አሁን ላይ ቅድም ናት
ከእጅህ ላይ የለችም ያንተ አይደለችም
ቅድም አሁን ስትል ለማለትህ እንኳን
ማስረጃህስ የታል?
ይልቅ ከሰማህኝ ልብ በለኝማ
ይዘህ ካልተገኘህ አማኝም እማኝም አታገኝምና
ተነሳ ተራመድ ከዘመኑ ጋራ
ህይወት ልክ የላትም አትሞላም አትፍራ ።
✍ሀወኒ ገመቹ
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈