Telegram Web Link
ያንቺ እቃ

አንድ ቀን ተነስተሽ ጠላሁህ
ብትይኝ፥
በስድብ ጎርፍ አጥበሽ ወደ ጥልቅ ብጥይኝ፥

ከልቤ አውጥቼ በቃ ረሳሁህ፥
እንካ ውሰድልኝ ልብህ ይኸዉልህ፥

እንዲ እንኳን ብትይኝ ከልብሽ አምርረሽ፥
የፍቅራችን ጊዜ እንደዋዛ ረስተሽ፥

እቃሽን ሰብስበሽ ልትወጪ ከቤቴ፥
አንድ እቃ ረስተሻል የኔ ሆድ በሞቴ

በሄድሽበት ሁሉ ካንቺ ጋር ውሰጂኝ
እኔም ያንቺ እቃ አካልሽ እኮ ነኝ።

© ናትናኤል

@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
"ንስሐ ዘሥጋ"
(መልአኩ ስብሐት ባይህ)
*************
ንፅፅራዊ ሁነት
ምፀታዊ ግነት
ሰዋዊ ሀቅነት፡፡

ከእንካ ያዥ ንሺ ያዥ ተቀድቶ
ተብላልጦ ተናንሶ ተዳድቶ፡፡
ተኳርፎ ተጋምጦ
ተቋርሶ ተቋምጦ፡፡

በድርድር ተስማምቶ
ህሊናው ከህሊናዋ አውግቶ፡፡
ባለመሰማት ተሰምቶ
በንሳ አሳልፍ ንሺ አሳልፊ ተቃምቶ፡፡
ዕውኑን በህልሙ ተቀምቶ
በጋርዮሽ ግርዶሽ ተቀራምቶ
በእንዳተነፍሺ እንዳተነፍስ ተግባብቶ፡፡

በስሜት ምዘዛ
እርሱ በስሎ እርሷ ለዛ
ወጥሮ ይዟት ይዛው ደንዝዛ፡፡
በድንፋታ ብግነት ጥማት
ከንፈሩ ከንፈሯን ሲማጠጣት፡፡
አክናፋቸውን ሰብረው
በሩካቤ በረው
ለመዋደቅ ጥረው፡፡

በእልህ አሟጣጭ ፍርገጣ
በኃላይ ግብግብ እርገጣ፡፡
ሲለግሳት ስትቀበል ገባ-ወጣን
ሲያሸታት እንደ ማዕጠንቱ እጣን።

ሲስምባት አካሉን ከአካሏ ለጥፎ
በምላሱ አርጥቦ አፍዝዞ - አደንዝዞ
አርዶ አብርዶ ቆርጦ - ቀጥፎ፡፡

በውስጣዊ ፍመት
በስሪያዊ ግመት
ተያይዛው ተያይዟት
ያቺን ሰዓት ያቺን ዕለት
ለራሳቸዉ እንጂ ለሌላ ላይነግሯት
ተማምነው ተማምለዉ ለሊቷን ሰወሯት።
.
.
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
#እምወድሽዋ! ቅዳሜዋ! ሸጋዬዋ!


ሸጊቷ ቅዳሜ!!!!!


ዘበናይ ቅዳሜ!!!!!!!!!
ሽሙንሙን ፣
ሽሙንሙን፣
ሽቅርቅር፣
ፍንድቅድቅ፣
ፍልቅልቅ በይልኝ፣
ሳቄ ይቀድመኛል፣
ሰማዩ ሲገለጥ፣ አንች ስትመጭልኝ።


እስክስ ቅዳሜ! !!!!!!


ከሰኞ እስከ አርብ ፤
ባለቃ በምንዝር ፣ ታምሜ ተምሜ ፤
የምታከምብሽ ፤
ባለሟል፤ እንዴት ነሽ ቅዳሜ! !!!!!!

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️



ቅዳሜያችን፣
የቅኔ ጎርፍ የሚጎርፍባት፣ የእሁድን እረፍት እያሰብን
የምንወዳቸውን መፅሃፍት
የምናነብባት፣ ነፍስያችንን በቅጡ ለማዳመጥ ፋታ
የምንወስድባት፣ ከወዳጅ ዘመድ የምንዘያየርባት ደርባባ
ቀናችን ናት!!!!!

@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
ጉዳዩ:-ቀጥሮ መጥፋት

ይድረስ በእመጣለሁ ተስፋ፣
ገጣሚዎችን ሁሉ ቀጥረሽ በይፋ፣
ቀኑ ብሏቸው ኣልገፋ፣
ምሽቱ ረዝሞ እንደ ቀያፋ፣
ኣይነጋ የለምና ሲነጋ፣
ለመምጣት ጓግተው ኣንቺ ጋ፣
ውበትሽን ፍለጋ፣
ፏ ፍክት ብለው እንደ በጋ፣
ሽር ሽቅርቅር ብለው እንደ ቀጋ፣
ልክ ሲደርሱ ቦታው ጋ፣
ኣንቺ ጋ፣
ውበትሽን ፍለጋ፣
እመጣለው ብለሽ ከቀጠሮ ቦታ፣
ኣንቺ ኣትታዪም ቦታው ላይ ነግሷል ጭርታ፣
ገጣሚዏቻችን ኣነሡ ብዕርናብራና፣
ከውበትሽ ጀመሩና፣
ኣሞጋግሠው ቀጠሉና፣
ስለመቅረትሽ ሲያነሡ፣
የኣንባቢውን ኣንጀት በጥበብ ኣራሡ፣




እናም ላንቺ ምስጋናዬን ኣደርሳለው፣
ኣንቺ ባትቀጥሪያቸው፣
ደግሞ ባትጠፊ ከፊታቸው፣
ሸሽገውን ነበር ይህን ጥበባቸው፣
(የዱድያሌብ ገፅ)
ይድረስ ገጣሚውን ሁሉ
እየቀጠርሽ ለምትሰለቢው ኮረዳ😘
@hutoffun
መሀል ፒያሳ
🚏🚏🚏

ጠዋት ተነስቺ ስራ የማልሄደው፣?
ፒያሳ ኣደባባይ ሄጄ ምቀመጠው፣?
የኣራዳው ታቦት ገዝ'ቶኝ፣
የኣቡኑ ሀውልት ገርሞኝ፣
የተገራው ፈረስ ማርኮኝ፣
የካቶሊኩ ቸርች ስቦኝ፣
ሠባ ደረጃው ኣስቀንቶኝ፣
ኣይምሰልሽ ውዴ...
እንደው ተረድተሽኝ መውደዴ፣
ምናልባትም ነገረውሽ ባንቺ ስለ ማበዴ፣?
በናፍቆትሽ ስለዛለው ክንዴ፣
ብትመጪ ኣስታውሰሺኝ ላንዴ፣🥺
ብዬም እንዳይመስልሽ ሇዴ።

እንኳንና ከሀገር ርቀሽ፣?
ብትሄጂም ሠፈር ቀይረሽ፣
ዳግም ወደ ፒያሳ እንደማይዞር ፊትሽ፣?
አውቃለሁ ልንገርሽ።

እኔ ምቀመጠው መሀል ፒያሳ ጋ
ኣንቺን ስለማስብ ሲመሽም ሲነጋ
እንደው ቢደርስሽና ካ'ገር ቤት ጥሪ፣
"ማን ቤት ላርፍ ነው?"ብለሽ ስትፈሪ፣
እንደ ድንገት ሆኖ እኔን ብታስቢኝ፣
ከዛ ደሞ ብትደውዪልኝ፣
ያው እንደነገርኩሽ ሁሌ ፒያሳ ነኝ፣
ለታክሲ እንዲመቸኝ፣
መሀል ከተማ ነኝ፣
"ቦሌ ነኝ!"ብትዪኝ፣
ሀውልቱ ጋ ሄጄ ሸገር እይዛለሁ፣
ሜክሲኮ ብትዪኝ በባስ እደርሳለሁ፣
4,5,6 ብትፈልጊ 7 የፈለግሺው ኪሎ፣
ፈረንሳይ መርካቶታ ካልሽም ሠፈረ ወሎ፣
ጦር ሃይሎች ሳሪስ፣
መገናኛ ካዛንችስ፣
ልደታ ሆነ ለገሀር፣
ብሄራዊ ኣልያም ጉራር፣
ያሻሽ ቦታ ና ብትዪኝ፣
ለታክሲ እንዲመቸኝ፣
ሁሌ ፒያሳ ነኝ፣
መሀል ከተማ ጋ፣
እንዳላስጠብቅሽ ስለምሠጋ።
(የዱድያሌብ ገፅ)
ይድረስ ለ"🗼"
@hutoffun
"ኣንተ ኣብርሃም፥
የኦሪት ስብሐት፣
የእነ እስማኤል፥
የይስሐቅ ኣባት፣
ልክ እንደ ኣክሱም ራስ፥
ቀርፀሀት ራሴን፣
በፍቅር ጧፍ፥
ለኩሳት ነፍሴን።"
(ቴዲ ኣፍሮ)
ከ "ጥቁር ሰው" ኣልበም የተወሰደ
@hutoffun
"ኣንገትሽ ላይ ኣርጊኝ፥
እንደ ማር ትሬዛ፣
ወዲህ ወዲያ እንዳልል፥
ኣደብ እንድገዛ።"
(ቴዲ ኣፍሮ)
@hutoffun
ልብሽን ኣልኩ እንጂ
❤️❤️❤️❤️

በየመንገዱ ዳር ሠዎች እያስቆሙኝ፣
እጆቼን ኣጣብቀው ሠላምታ ሲሠጡኝ፣
ያንቺን ስም ኣንስተው ለጠየቁኝ ሁሉ፣
ጥላኝ ኮበለለች ወስዳ ሀብቴን ሁሉ፣
እያልኩኝ ሳወራ ሰዎቹ ያዝናሉ።
ልክ ቤት ስገባ ስሜን አጠፋኸው፣
ምን ኣይነት ውሸት ነው?
እኔ ኣንተን ጥዬ ወዴት ኮበለልኩኝ?
መች ኣሽኮለሌ ኣልኩኝ?
ብለሽ ታኮርፌያለሽ
እውነቱን ልንገርሽ....
ልብሽን ኣልኩ እንጂ በድንሽ ተቀምጧል፣
መቼስ ኣትክጂኝም ልብሽ ሀብቴን ይዟል።


ሀ-ሀሳቤም,ሀይሌም
ብ-ብሶቴም,ብርታቴም
ት-ትኩረቴም,ትንፋሼም
(የዱድያሌብ ገፅ)
@hutoffun
"እንደ ኣንፀባራቂ፥
መልክሽ ሲያበራ፣
መቃው ኣንገትሽ፥
ከሩቅ ሲጣራ፣
ተልፈሰፈስኩኝ፥
ጉልበት ኣነሠኝ፣
ልቤ ተነካ ፥
መቻል ኣቃተኝ።"
(ከተሾመ ምትኩ)
ከ"ሰማይ ሲላወስ" የተወሰደ
@hutoffun
ጉዳዩ #ልምድን_ስለመጻፍ

ይድረስ ለማፈቅርሽ..ይድረስ ለምወድሽ
ጠልተሽ ላባረርሽኝ..በገዛ ፈቃድሽ::
ቀድሞ ለነበርሽው..የፍቅር አቻዬ
በቅጡ ይጤንልኝ..ይህ ማመልከቻዬ::-
ጥረቴን..ልፋቴን..ድካሜን..ትጋቴን..
ለፍቅር እንደገበርኩ..ቀንና ሌሊቴን..
ችዬ ያካበትኩትን..የዘመናት ልምዴን..
ከልብ ማፍቀሬን..አጥብቄ መውደዴን..
...ንፁህ ሆኜ መኖሬን..
ፈጣሪን መፍራቴን..
...ፍጥረቱን ማክበሬን..
ልዩ ሐሴትእንዳለኝ..ማንም እማይቀማኝ..
እንደሆንኩኝ ታማኝ..እንደነበርኩ አማኝ..
ካሻሽ ወንጀለኛ..
ወይም ኃጢኃተኛ..
ሁሉንም ዘርዝረሽ..በይፋ አውጂልኝ
የሔዋን ዘር በሙሉ..ልምዴን እንዲያውቅልኝ
"ለሚመለከተው ሁሉ"
በሚል ዐብይ ርዕስ..ማስረጃ ጻፊልኝ::
ከሰላምታ ጋር
ያንቺው የፍቅር አጋር!!
@hutoffun
እንዲሁ ለምወድሽ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
አንቺ ባትኖሪም ፣ ስላንቺ እፅፋለሁ
አንቺ ባትሰሚኝም ፣ ስላንቺ አወራለሁ
አንቺ ባትቀጥሪኝም ፣ አንቺን 'ጠብቃለሁ
ውዴ ሙሽራዬ ፣ ፍቅሬ አፈቅርሻለሁ ።
@hutoffun
Mug
በፈለገበት ዲዛይን እዘዙን በ ፎቶም እንሰራለን ለማንኛውም event የ ሜሆኑ
🤳0920605610
🤳 0944740222
በቴሌግራም ይዘዙን
@Masreadvert2044
''የአንድ ሰው ሒወት አለፈ"
አንዲት የ40 አመት ሴት ታክሲ ተሳፍራ ወደ መስሪያ ቤት በመሄድ ላይ ነበረች፡፡
የቀን ጎዶሎ ሆኖባት የተሳፈረችበትን ታክሲ መፈጠንን ጉብዝና መደረበን እርድና ያደረገ ሌላ ባለታክሲ አደጋ አደረሰበት፡፡ግጭቱ ጠንከር ያለ የነበረው በሷ በኩል ነበርና ሒወቷ አለፈ ፡፡ፖሊስ ማንነቷን ለማጣራት መታወቂያ ሲፈልግ ቦርሳዋ ውስጥ የቤተሰብ ፎቶ አገኘ፡፡በቅርብ ከገጠር ያመጣቻቸው ከሷ ውጪ ጧሪ የሌላቸው እናቷ፣ሶስት የሷን እንክብካቤ የሚሹ ጠረኗን የሚናፍቁ ልጆቿ፣ እሷ እና በቅርቡ ሒወቱ ያለፈው ሀዘኑ ያለወጣላት ባሏ በጋራ የተነሱት ፎቶ፡፡ከሰአታት በኀላ ዜናው ሲዘገብ "በአዲስ አበበ እንትን ክ/ከ በደረሰ የመኪና አደጋ ሶስት ከባድ ሁለት ቀላል አደጋ ተመዝግቧል፡፡የአንድ ሰው ሒወትም አልፏል፡፡" አድማጭና ተመልካችም "ተመስገን ብዙ ሰው አልሞተም"(እውነት ቀመስ ልብ ወለድ) እወነት የዚች እናት ሞት የአንድ ሰው ሞት ነው?
አሁንም በኮረና ምክንያት እየሆነ ያለው ይህ ነው፡፡የአንድ ሰው ሒወት አለፈ ስንባል ከአንድ ሰው ጀርባ ያሉ አብረው የሚከስሙ ነፍሶችን ልብ ሳንል ብዙ ሰው አልሞተም በሚል መዘናጋታችን ጨምሮ የራሳችንን እና የወገኖቻችን ተመን የሌለው ነፍስ ከመቅጠፍ እንታቀብ፡፡🙏
ያለ በቂ ምክንያት ከቤት የምቶጡም የለት ጉርሳቸውን ለማግኘት ግድ መውጣት ላለባቸው ምስኪን ወገኖች ጦስ አትሁኑ፡፡🙏
ሁላችንም በልባችን አስቸካይ አዋጅ አውጥተን ተግባራዊ እናርገው እንጂ እንደ እንሳሳ ደምብ አስከባሪ የሚያግደን(የሚጠበቀን) አንሁን፡፡🙏


ዜና ሆኖ ሲቀርብ፣የአንድ ሰው ህልፈት፡
የሰማ ጉድ ይላል፣ለጥቂት ሰአታት፡
ለቤተሰቡ ግን፣ለወዳጆቹ ግን፣የዘላለም ፀፀት፡፡

ለወዳጆ Share




@hutoffun
የሠርግሽ ዕለት
(አማኑኤል አለሙ ኑርጋ) አሙ
.
.
ሠርግ ቤቱ-ወደ'ኔ
ይሁን እኔ-ወደ'ሱ
ማን- 'ንደመጣ ፣እንጃ አለሁ ከድግሱ


አባትሽ ከርቀት እየገላመጡኝ
ጮማ እየጎረሱ
እኔን አላመጡኝ

አ ስ ታ ወ ሱ ኝ...

በጉርምስናችን
የምወድሽ ልጅ ነኝ
እንጃ ምን እንዳሉ!


አንቺ ግን 'ረሳሽ...?
'ባስኳላ ቤት ሳለን
'ባንድ የቀን ጎደሎ
ቦርሳዬን ብከፍተው
ተስፋ 'ንደጉድ ሲተ'ን
እንዳላየ ('ያ)ለፍሽው!?


ቆሌ ቢያዳሽቅም
የተስፋዬ ክህደት
ሳላየው ቢያመልጥም
እንደ ጉም ትንታ
ምን ብዬ ልውሰደው
የ'(ያ)ኔሽን ዝምታ!? Damnshit!!!


እንደ ሚመጣጠን፣
እኩል 'ንደሆነ-ቁጥር
የሰው ነፃ ፍቃድ፣
በ'ግዜር ሃይል ይጣፋል
እንዴት ከልቤ ላይ
ተስፋ ተ'ኖ ይጠፋል?
.

@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
እምወድሽዋ! ቅዳሜዋ! ሸጋዬዋ!


ፅና!!!!!!

ሃገሩ በሞላ፤
ድምፅህን ባይሰማው፤ ለጀማው ባትደምቅም፤
ሰው የለኝም ብለህ፤ ከጀመርከው መንገድ መሄድ እንዳትደክም፤
እስከዛሬ ድረስ፤
ከጩኸት በስተቀር፤
እውነት በሰው ብዛት፤
ፍትህ በሰው ብዛት፤ተበይኖ
አያውቅም!!!!"

((( ጃ ኖ ))💚💛❤️

ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!

@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
አቋም ስለሌለሽ፤በሄድሽበት ሁሉ፣
ሆዴ ባለኝ አፍሽ፤ሆዳም አልሽኝ አሉ፣
ልሁን ሆዳም በዪኝ፤አልቀየምሽም፤
አባቴ አልሽኝ እንጂ፤እናቴ አይደለሽም።

እንኳን ተለያይተን፣
ያኔ በፍቅር አብደን፤መውደድ አሳምሞን፣
ንብ ነሽ አላልኩሽም፤ማሬ ያልሽኝ ሰሞን።
ከአካሉ ቀጥሎ፤መንፈሱን ለመጣል፣
በለውጥ ውስጥ ያለ ነው፤ያለፈን ማጣጣል።

እኔ ግን እንዳንቺ...
አፌ ስለማይስት፤በየደረስኩበት
ግራ’ግር አልልም፤ገራገር ባልኩበት።😊

@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
. . . #የእኔና_አንቺ_ፍቅር . . .

ያኔ ገና ፍቅርን ስንጀምር ❤️. . . እኔና አንቺ ሆነን . . . 💗አንቺ ለኔ ስትኖሪ፣ ህይወቴ እንዲበራ መንገዴን በፍቅር ስትመሪ💘 . . . እኔ አንቺን ብቻ . . .
. . . . 💖ከሁሉ አስበልጬሽ ላንቺ ለመሞት ቃል የገባውት . . . ፍቅር አንተ ነህ ብለሽኝ ማፍቀር እንዳንቺ ነው ያልኩት💓 . . .
. . ."እድሜ ልኬን ካንተው ጋ ነኝ፡፡ ቃሌ ለዘለአለም ነው 💞"ብለሽኝ ነበር ውዴ . . .
. . .ምናልባት አሁን እየኖርኩ ያለውት ከ ዘለአለም ብሀላ ይሆን እንዴ?💔
. . . ተአምር ቢፈጠር ጊዜውም ቢከፋ . . . አንተን አለውጥህም አለም ብትጠፋ . . .ብለሽ የገባሽልኝ ቃል ዛሬ የት ጠፋ?
. . .💥 እኔ ሳላውቀው አለም ጠፍታ ይሆን እንዴ? . . .
. . .💔ካንተ የሚለየኝ ሞት ነው ብለሽ ነበር ውዴ?
ምናልባት ሳላውቀው ሞተን ይሆን እንዴ? . . .🖤 . . .

@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
ተገልባጯ ምድር



ሰኞና ሰኔ ወር የተገጣጠሙ 'ለት፣
ኣሁን ያለንባት እቺ 'ርኩሷ መሬት፣
ትጠፋለች ኣሉ ትገለበጥና፣
ገና በጠዋቱ ይህን ሰማሁና፣
እንደማንም ፍጡር ፈራ ኣልኩኝና፣
ደግሞ ተመልሼ ሣጤነው ነገሩን፤
ይቺ ዓለም ተቃንታ ኣሳር ካስበላችን፣
እስኪ ተገልብጣ ሀሴትን ታላብሰን፣
ፈጣሪም ይማረን በደስታ ይካሰን።
(የዱድያሌብ ገፅ)
ይድረስ "በተቃና ዓለም፤ ኑሮ ለተገለበጠብን"
@hutoffun
@hutoffun
2025/07/07 02:49:32
Back to Top
HTML Embed Code: