ገነታዊ ኑሮ
ዘመን ያልሻረው መሪ፣
ያልተቀጣ ኣሽከርካሪ፣
ያላለቀሰ ዘማሪ፣
ያልተደበደበ ኣዝማሪ፣
ያልተገረፈ ተማሪ፣
ያልተማረረ ኣስተማሪ፣
የለምና በዚች ደባሪ፣
ኣሳፋሪ ሰርሳሪ መሠሪ::
ምድር ቀሪ ስለሆንኩኝ
አንድ ሀሳብ ኣለኝ
.
.
.
.
ስጠኝና የሙሴን በትር
ኣንግሰኝና በውቧ ሀገር
እንደ ዳዊት እንደልቤ ብለኸኝ
እንደ ሰለሞን ጥበብ አድለኸኝ
ጠይሟን ሳባዬ ከምስራቅ ኣምጥተህ
እንዳትመለስ ገዝተህ
ባይህ ብጠብቅህ ገነት ስለማቶስደኝ
ባይሆን የምድሩን ኑሮ ገነታዊ ኣድርግልኝ::
(የዱድያሌብ ገፅ)
ይድረስ ገነት ሲያምረው ለቀረ
@hutoffun
ዘመን ያልሻረው መሪ፣
ያልተቀጣ ኣሽከርካሪ፣
ያላለቀሰ ዘማሪ፣
ያልተደበደበ ኣዝማሪ፣
ያልተገረፈ ተማሪ፣
ያልተማረረ ኣስተማሪ፣
የለምና በዚች ደባሪ፣
ኣሳፋሪ ሰርሳሪ መሠሪ::
ምድር ቀሪ ስለሆንኩኝ
አንድ ሀሳብ ኣለኝ
.
.
.
.
ስጠኝና የሙሴን በትር
ኣንግሰኝና በውቧ ሀገር
እንደ ዳዊት እንደልቤ ብለኸኝ
እንደ ሰለሞን ጥበብ አድለኸኝ
ጠይሟን ሳባዬ ከምስራቅ ኣምጥተህ
እንዳትመለስ ገዝተህ
ባይህ ብጠብቅህ ገነት ስለማቶስደኝ
ባይሆን የምድሩን ኑሮ ገነታዊ ኣድርግልኝ::
(የዱድያሌብ ገፅ)
ይድረስ ገነት ሲያምረው ለቀረ
@hutoffun
"አልስማ ክፉሽን"!
።።።።።።።።።።።።።
ልትርቂ ነው መሰል፥ ልትኮበልይ ደግመሽ
ነጋ ያልኩት ሰማይ ተመልሶ ሊመሽ።
ያልጠገብኩት ዓለም ጠኔው ሊያራውጠኝ
ብቻነት ላንቃውን ፈልቀቆ ሊውጠኝ።
የምጣትሽ ብስራት ፥ ሳይበቃ ተዘክሮ
ትካዜውን ሳይተው ፥ ይህ ልቤ ተመክሮ
ገና ሳልጠለል ፥ መኖርሽ ዛፍ ግርጌ
እልልታዬን ሳልጨርስ ፥ ድምጼን ከፍ አድርጌ
"ተነሳች"ን ሰማሁ ፥
መቼ ገባሽና ፥ ገና መቼ መጣሽ?
መቼ ተቀምጠሽ ፥ ልትሄጅ የወጣሽ ?
ተመልከቻት ፀሐይ!
አኩርፋ ቆዝማ ፥ ቀዝቅዛለች በቀን
ባንድ ጣራ እያለን ፥ ታይቷት ተራርቀን።
እኔንስ ገርሞኛል !
ለመምጣት ችኮላ ፥ለመሄድ መጣደፍ
ለመግባት እሩጫ ፥ ለመመለስ ከደፍ
ልክ እንደወታደር!
ግዳጅ እንደላኩት ፥ አስይዘው አደራ
ሀገር ተወራበት ፥ ጦር እንዳሰማራ
ደም እንዳበረረው!
እንደጠራው ሞቱ ፥ እያክለፈለፈ
ልብሽ በልቤ በር፥ እየሮጠ አለፈ።
(እንቺማ የቃል ስንቅ!
መብረርሽ ባልከፋ ፥ ማዳረስሽ ሀገር
ከሰበዝ አይጠናም ፥ የወፍ ጎጆ ማገር።)
ቆም በይ አንዳንዴ!
ወርደሽ ተራመጂ ፥ እግሮችሽም ይስሩ
ድልድይ ይሆኑሻል'
ክንፎችሽ አንድ ቀን ፥ ድንገት ቢታሰሩ።
የኔም ፀሐይ ትጥለቅ፥ እንኳን ቀርቶ ማኩረፍ
ነፍሴ ሲዖል ትጣል ፥ ዘላለም አትረፍ
ሂጂ አታመንቺ ፥
ቀልብሽ አይከፈል ፥ አይበትነው መቅረት
መንፈስሽን ሰቅዞ ፥ አይናጠው ወረት።
ሒጂ እሸኝሻሁ!
የልቤን ኅቱም ሀቅ ፥ ቃልኪዳኔን ትቼ
ዞር ብዬ ላላይ፥
ፍቅር ይሉትን ቃል ፥ ላልመልስ ፈትቼ
ጠርቅሜ ዘግቼ ፥ የነፍሴን ወጋግራ
ስትሄጂ ተመለስሁ ፥ ሳልል ቀኝ ግራ።
እኔ ግን እንዳንቺ…
አልጨክንምና…
ብርብር ስትይ ፥ ተማምነሽ ክንፍሽን
እግዜር አደራውን ፥ አልስማ ክፉሽን!
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
።።።።።።።።።።።።።
ልትርቂ ነው መሰል፥ ልትኮበልይ ደግመሽ
ነጋ ያልኩት ሰማይ ተመልሶ ሊመሽ።
ያልጠገብኩት ዓለም ጠኔው ሊያራውጠኝ
ብቻነት ላንቃውን ፈልቀቆ ሊውጠኝ።
የምጣትሽ ብስራት ፥ ሳይበቃ ተዘክሮ
ትካዜውን ሳይተው ፥ ይህ ልቤ ተመክሮ
ገና ሳልጠለል ፥ መኖርሽ ዛፍ ግርጌ
እልልታዬን ሳልጨርስ ፥ ድምጼን ከፍ አድርጌ
"ተነሳች"ን ሰማሁ ፥
መቼ ገባሽና ፥ ገና መቼ መጣሽ?
መቼ ተቀምጠሽ ፥ ልትሄጅ የወጣሽ ?
ተመልከቻት ፀሐይ!
አኩርፋ ቆዝማ ፥ ቀዝቅዛለች በቀን
ባንድ ጣራ እያለን ፥ ታይቷት ተራርቀን።
እኔንስ ገርሞኛል !
ለመምጣት ችኮላ ፥ለመሄድ መጣደፍ
ለመግባት እሩጫ ፥ ለመመለስ ከደፍ
ልክ እንደወታደር!
ግዳጅ እንደላኩት ፥ አስይዘው አደራ
ሀገር ተወራበት ፥ ጦር እንዳሰማራ
ደም እንዳበረረው!
እንደጠራው ሞቱ ፥ እያክለፈለፈ
ልብሽ በልቤ በር፥ እየሮጠ አለፈ።
(እንቺማ የቃል ስንቅ!
መብረርሽ ባልከፋ ፥ ማዳረስሽ ሀገር
ከሰበዝ አይጠናም ፥ የወፍ ጎጆ ማገር።)
ቆም በይ አንዳንዴ!
ወርደሽ ተራመጂ ፥ እግሮችሽም ይስሩ
ድልድይ ይሆኑሻል'
ክንፎችሽ አንድ ቀን ፥ ድንገት ቢታሰሩ።
የኔም ፀሐይ ትጥለቅ፥ እንኳን ቀርቶ ማኩረፍ
ነፍሴ ሲዖል ትጣል ፥ ዘላለም አትረፍ
ሂጂ አታመንቺ ፥
ቀልብሽ አይከፈል ፥ አይበትነው መቅረት
መንፈስሽን ሰቅዞ ፥ አይናጠው ወረት።
ሒጂ እሸኝሻሁ!
የልቤን ኅቱም ሀቅ ፥ ቃልኪዳኔን ትቼ
ዞር ብዬ ላላይ፥
ፍቅር ይሉትን ቃል ፥ ላልመልስ ፈትቼ
ጠርቅሜ ዘግቼ ፥ የነፍሴን ወጋግራ
ስትሄጂ ተመለስሁ ፥ ሳልል ቀኝ ግራ።
እኔ ግን እንዳንቺ…
አልጨክንምና…
ብርብር ስትይ ፥ ተማምነሽ ክንፍሽን
እግዜር አደራውን ፥ አልስማ ክፉሽን!
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
#ሀንግ #ኦቨር
የደሀውን ለቅሶ ~ የምስኪኑን ጩኸት
አላሰማም ብሎህ ~ የቢላዎች ፉጨት
ነብስህ ተከልላ ~ በስጋ አለም ስላቅ
ከታናሽ ላይ ቆርጠህ ~ አጉርሰህ ለታላቅ
ለማወራረጃ ~ ብርጭቆ ብትይዝም
ቀዝቀዝ ያለ ሁሉ ~ አያቀዘቅዝም
አያጠፋልህም
የነብስህን እሳት ~ ከስጋህ ነጥሎ
አያበርድልህም
የውጪው ቀዝቃዛ ~ የውስጥን ቃጠሎ
እውነቱ እንደዚህ ነው ~ እመነኝ ግዴለም
ከእርዛት ነጥቆ ~ በሚደርብ አለም
የሚያልበው ሁሉ ~ የሞቀው አይደለም
#ዛሬ
በንብረትህ ብዛት~ፍቃድ ስር ብትወድቅም
በጉብዝናህ ወራት ~ ለማሰብ ባትፈቅድም
ልክን ማሳወቅ ነው ~ የመለኪያ ጥቅም
#ከሰማህ #ልንገርህ
ግፍ እንደ ፍግ ሆኖህ
ከእድሜህ በላይ በቅለህ~ከሀገሬው ብትበልጥም
ደሀ ባፈሰሰው
የእንባ በረዶ ~ ውስኪ አይጨለጥም
===||===
ከሙሉቀን ሰ•
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
የደሀውን ለቅሶ ~ የምስኪኑን ጩኸት
አላሰማም ብሎህ ~ የቢላዎች ፉጨት
ነብስህ ተከልላ ~ በስጋ አለም ስላቅ
ከታናሽ ላይ ቆርጠህ ~ አጉርሰህ ለታላቅ
ለማወራረጃ ~ ብርጭቆ ብትይዝም
ቀዝቀዝ ያለ ሁሉ ~ አያቀዘቅዝም
አያጠፋልህም
የነብስህን እሳት ~ ከስጋህ ነጥሎ
አያበርድልህም
የውጪው ቀዝቃዛ ~ የውስጥን ቃጠሎ
እውነቱ እንደዚህ ነው ~ እመነኝ ግዴለም
ከእርዛት ነጥቆ ~ በሚደርብ አለም
የሚያልበው ሁሉ ~ የሞቀው አይደለም
#ዛሬ
በንብረትህ ብዛት~ፍቃድ ስር ብትወድቅም
በጉብዝናህ ወራት ~ ለማሰብ ባትፈቅድም
ልክን ማሳወቅ ነው ~ የመለኪያ ጥቅም
#ከሰማህ #ልንገርህ
ግፍ እንደ ፍግ ሆኖህ
ከእድሜህ በላይ በቅለህ~ከሀገሬው ብትበልጥም
ደሀ ባፈሰሰው
የእንባ በረዶ ~ ውስኪ አይጨለጥም
===||===
ከሙሉቀን ሰ•
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
እኔስ ረሳሁሽ
እኔስ ረሳሁሽ ይብላኝ ለማይረሳሽ
ተይዞ ለቀረው በገመዱ ፍቅርሽ።
እኔስ ረሳሁሽ በቅቶኛል ልፋቱ
በጥይቱ ፍቅርሽ ተመቶ መሞቱ
አነቺ ካልወደድሽኝ ከሌለሽ ስሜቱ
እኔን ምን አስለፋኝ አቃዠኝ በከንቱ።
መርከብ ከምፈልግ ከairport ቆሜ
ብተውሽ ይሻላል እንዳገኝ ሰላሜ።
በርግጥ በርግጥ አንቺ ነሽ ሰላሜ
የበሽታዬ ፈውስ በህመሙ እድሜ።
የደስታዬ ምንጭ በህይወት ዘመኔ
ባትወጂኝ እንኩዋን ብትርቂ ከጎኔ።
ሳቅሽ ሳቅ ሆኖልኝ ፀሐይ ፈገግታሽ
ጨለማን አርቆ ቢከበኝ ፍቅርሽ።
ግን ምን ጥቅም አለው የሳቅሽ ብርሃን
አንቺ ካልኖርሺበት ከንቱ ነው ብቻውን።
በጣም ስለበቃኝ አንቺን መጨቅጨቁ
ጭራሽ የማትወጂኝ ሆኗልና ሀቁ።
ስለዚህ አወጣሁሽ ከልቤ መቃብር
በአንዱ ወገን ብቻ ስለማይሆን ፍቅር
እኔስ ረሳሁሽ ይብላኝ ለማይረሳሽ
ተይዞ ለቀረው በገመዱ ፍቅርሽ።
Natta
@hutoffun
እኔስ ረሳሁሽ ይብላኝ ለማይረሳሽ
ተይዞ ለቀረው በገመዱ ፍቅርሽ።
እኔስ ረሳሁሽ በቅቶኛል ልፋቱ
በጥይቱ ፍቅርሽ ተመቶ መሞቱ
አነቺ ካልወደድሽኝ ከሌለሽ ስሜቱ
እኔን ምን አስለፋኝ አቃዠኝ በከንቱ።
መርከብ ከምፈልግ ከairport ቆሜ
ብተውሽ ይሻላል እንዳገኝ ሰላሜ።
በርግጥ በርግጥ አንቺ ነሽ ሰላሜ
የበሽታዬ ፈውስ በህመሙ እድሜ።
የደስታዬ ምንጭ በህይወት ዘመኔ
ባትወጂኝ እንኩዋን ብትርቂ ከጎኔ።
ሳቅሽ ሳቅ ሆኖልኝ ፀሐይ ፈገግታሽ
ጨለማን አርቆ ቢከበኝ ፍቅርሽ።
ግን ምን ጥቅም አለው የሳቅሽ ብርሃን
አንቺ ካልኖርሺበት ከንቱ ነው ብቻውን።
በጣም ስለበቃኝ አንቺን መጨቅጨቁ
ጭራሽ የማትወጂኝ ሆኗልና ሀቁ።
ስለዚህ አወጣሁሽ ከልቤ መቃብር
በአንዱ ወገን ብቻ ስለማይሆን ፍቅር
እኔስ ረሳሁሽ ይብላኝ ለማይረሳሽ
ተይዞ ለቀረው በገመዱ ፍቅርሽ።
Natta
@hutoffun
Forwarded from Qualitybuttonbot
✝የአብነት ትምህርት✝
የአብነት ትምህርት መማር ይፈልጋሉ?
✝ግዕዝ ሲማሩ ዕውቀትዎትን አዳብረው ግስ አገላብጠው የግዕዝ ቋንቋን መናገር ይችላሉ!!
በቻናላችን በሚሰጠው ትምህርት ተቀላቅለው መማርና ዕውቀትዎን ማሳደግ ይችላሉ!!
👇✝ተቀላቀሉን✝👇
https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAFLvqSNaKPXNxFAPBA
የአብነት ትምህርት መማር ይፈልጋሉ?
✝ግዕዝ ሲማሩ ዕውቀትዎትን አዳብረው ግስ አገላብጠው የግዕዝ ቋንቋን መናገር ይችላሉ!!
በቻናላችን በሚሰጠው ትምህርት ተቀላቅለው መማርና ዕውቀትዎን ማሳደግ ይችላሉ!!
👇✝ተቀላቀሉን✝👇
https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAFLvqSNaKPXNxFAPBA
ጠላት
"""""""
የአንድ ዛፍ ጠማማ፥
በህይወት ሲሳሳት፤
የወገኑን ፍቅር፥
ውለታ በመርሳት፤
ሙሉ ደን ያጠፋል፥
ክብሪት ሆኖ እሳት፤
የእርኩሰትም እርኩስ፥
የጥፋትም ጥፋት!
ተበላሽቶ ሲያድግ
ያንድ ዛፍ ቅርንጫፍ፥ የግንዱ ብቅያ፤
ብረት ቆብ አር'ጎ
ደን ይጨፈጭፋል፥ 'በጅቶ መጥረቢያ፤
ቢፈጥረው አድርጎ
የተንኮል፣ የክፋት፣ የሴራ ምስያ!
እንዲ ነው እንግዲህ፥
በፍጥረታት ሜዳ፤
እምነትም ሲበላ፥
ያመኑት ሲከዳ!
ወንዝ ለወንዝ ምሎ፥
ካፍንጫ ስር በቅሎ፥
ድክ ድክ ብሎ፥ የሚገነድሰው፥
መሬት የሚያስልሰው፤
"ማን ነው ጠላት?" ቢሉ
......... ሰው ነው ጠላት የሰው....!
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
"""""""
የአንድ ዛፍ ጠማማ፥
በህይወት ሲሳሳት፤
የወገኑን ፍቅር፥
ውለታ በመርሳት፤
ሙሉ ደን ያጠፋል፥
ክብሪት ሆኖ እሳት፤
የእርኩሰትም እርኩስ፥
የጥፋትም ጥፋት!
ተበላሽቶ ሲያድግ
ያንድ ዛፍ ቅርንጫፍ፥ የግንዱ ብቅያ፤
ብረት ቆብ አር'ጎ
ደን ይጨፈጭፋል፥ 'በጅቶ መጥረቢያ፤
ቢፈጥረው አድርጎ
የተንኮል፣ የክፋት፣ የሴራ ምስያ!
እንዲ ነው እንግዲህ፥
በፍጥረታት ሜዳ፤
እምነትም ሲበላ፥
ያመኑት ሲከዳ!
ወንዝ ለወንዝ ምሎ፥
ካፍንጫ ስር በቅሎ፥
ድክ ድክ ብሎ፥ የሚገነድሰው፥
መሬት የሚያስልሰው፤
"ማን ነው ጠላት?" ቢሉ
......... ሰው ነው ጠላት የሰው....!
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
አትፅናኝ
(መዘክር ግርማ)
።።።።።።
ሞትን አንመልሰዉ፣ እናውቃለን አይሸሽ
ስንት ጥፍራም ኀዘን አይተናል መሰለሽ!
ስንት ጥፍራም ኀዘን፣ እንደማቀይር አምነን
ስንት ጥፍራም ኀዘን፣ እንደማይቀር አምነሽ፤
ዳሩ ታውቂዋለሽ።
፣
አቀጣጡ ክፋት፤
አመጣጡ ም‘ፃት፤
ግን ከሄደው ሁሉ፣ ከተመላለሰዉ
ምን ይባላል ይኼ፣ ባንቺ የደረሰዉ?!
ምን ይባላል ይኼ? አንቺስ ምን ልትባይ?
እኩይ ነዉ እታለም፣ ሽንገላ እንደ ሥራይ።
፣
በእድፋም ጥፍሩ፣ ቧጦሽ ጥፍራም ኀዘን
መፅናናት መመኘት፣ ምንድነዉ መማፀን?
ምንድን ነዉ ዕንባ አባሽ?
ምንድን ነዉ ማገገም?
ዕንባሽን ማድረቂያ፣ አልሰጥሽም ማ‘ረም።
እሪ በይ!
ቢል በይ!
ኩርምት በይ–ዋኔ!
ላንቺ መፅናናትን፣ አልመኝም እኔ።
ወይኔ በይ!
ወዮ በይ!
ተይ አልልም ጭራሽ፤
አለመፅናናት ነዉ፣ አንቺን የሚያፅናናሽ!
፣
የሚገርም አይነት ጽሑፍ፣ ለዛውም የግጥም ጽሑፍ ማንበብ እንዲህ ከፍ ያደርጋል ለካ!
፣
መዘክር ግርማ (ወደ መንገድ ሰዎች: 2010 ዓ·ም)
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
(መዘክር ግርማ)
።።።።።።
ሞትን አንመልሰዉ፣ እናውቃለን አይሸሽ
ስንት ጥፍራም ኀዘን አይተናል መሰለሽ!
ስንት ጥፍራም ኀዘን፣ እንደማቀይር አምነን
ስንት ጥፍራም ኀዘን፣ እንደማይቀር አምነሽ፤
ዳሩ ታውቂዋለሽ።
፣
አቀጣጡ ክፋት፤
አመጣጡ ም‘ፃት፤
ግን ከሄደው ሁሉ፣ ከተመላለሰዉ
ምን ይባላል ይኼ፣ ባንቺ የደረሰዉ?!
ምን ይባላል ይኼ? አንቺስ ምን ልትባይ?
እኩይ ነዉ እታለም፣ ሽንገላ እንደ ሥራይ።
፣
በእድፋም ጥፍሩ፣ ቧጦሽ ጥፍራም ኀዘን
መፅናናት መመኘት፣ ምንድነዉ መማፀን?
ምንድን ነዉ ዕንባ አባሽ?
ምንድን ነዉ ማገገም?
ዕንባሽን ማድረቂያ፣ አልሰጥሽም ማ‘ረም።
እሪ በይ!
ቢል በይ!
ኩርምት በይ–ዋኔ!
ላንቺ መፅናናትን፣ አልመኝም እኔ።
ወይኔ በይ!
ወዮ በይ!
ተይ አልልም ጭራሽ፤
አለመፅናናት ነዉ፣ አንቺን የሚያፅናናሽ!
፣
የሚገርም አይነት ጽሑፍ፣ ለዛውም የግጥም ጽሑፍ ማንበብ እንዲህ ከፍ ያደርጋል ለካ!
፣
መዘክር ግርማ (ወደ መንገድ ሰዎች: 2010 ዓ·ም)
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
.
ታሪክ መልኩን ቀይሮ እየተደገመ እንዳለ ሲገባን
ሀዘናችንንም በባለቅኔ ቀለም እንዲህ ደገምነው ጌታ ሆይ የት ነህ ፍጥረትህን በምህረት አስብ
እውነት ከመንበርህ የለህማ!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ምነዋ መንግሰተ ሰማይ! የምህረትሽ ቀን ራቀ?
ምነው ትንግርትሽ ረቀቀ ?
ምነው ኪዳንሽ ታጠፈ … ወዝሽ ወዘናሽ ነጠፈ?
እንደ ዳጉሳ ድፍድፍ … ላቦትሽ ተንጠፈጠፈ
አሳርሽ ጠሎ አሰፈፈ፤
......//...........
ምነው ጭር አለ ቀየው! ሀሩር ነዲዱ በረታ
ኮርማው ጥማዱ ተረታ
ምነው ነበልባሉ አየለ … ማሳው ተንቀለቀለ
ነቀለ ሞፈር ሰቀለ ተግድራ ደቀለ
ምነው ምድር ጨነገፈች ዝላ ተርገፈገፈች?
ካስማ እንደተደገፈች ምነው ተሳታብብ ረገፈች?
......//.....
ምነው ወላድ ተንሰለሰለ … ልሳነ ቃሉ ሰለለ
በቁሙ ከስሞ ከሰለ
አቤት የርግማን ቁርሾ
በንጣይ እርሾ መነሾ!
ምነው ላይፀድቅ በቀለ!
የሰው ልጅ ዋጋ ቀለለ
ትቢያ አፈር ተቀላቀለ
....//.....
ምን ይሉታል ይሄነን ፍርድ
እንዲህ ያለ ጉድ አለ እንዴ?
እግዜር ወንዱ እግዜር መንዴ!
ደረቅ ጡት እየጠባን ቁረንጮ ስንገተግት፤
ከመንግስተ ሰማይ የምህረት ግት፤
ምነው የማርያም ልጅ የስርየት ቀንህ ራቀ፤
ምነው ታምርህ ረቀቀ፤
.....//....
የኛስ ይሁን እንዳሻው ለእጥፍ ፈተና ከፈጠርከን
ለፍታችሁ ተፍታችሁ ኑ ካልከን
ለቀብር አፈር ከወጠንከን
ግን ፡- ግን ብላቴኖች ምን በደሉ
የማንን አደራ በልተው የማነን አማና አጎደሉ
እንብርታቸው ያላረረ
አጥንታቸው ያልከረረ
ሰማይ በቀል እንደቋጠረ
እጣቸውን እየመጠረ
መንገዳቸውን በእሾህ እያጠረ
እንደ ደራሽ ውሃ አግተልትሎ
በራብ አኮርማጅ ተልትሎ
ከእናት እቅፍ በግፍ ነጥቆ
ሲሰልፍብን ባጭር ታጥቆ
እያየህ ዝም ካልክማ
እውነት እውነት ከመንበርህ የለህማ!
.....//....
በማን ሊዳኝ ነው ቅጣቱ የሰው ዘር አንዲት ቅንጣቱ
ያባወራ ባላውራጣቱ
እንደ በልግ አውድማ ነዶ … ምድር ለቅልቆ ከምሮ
ነፍስ ከእስትንፋስ ነጥሎ … ሲኦል እቶን ውስጥ ሞጅሮ
በነበልባል መንሽ እየዘራ በረሀብ አራገበው
ሰው እርጥቡን አንገበገበው
ነፍስ ይማር እርካቡ ረገበ
ቀብርም አስከሬን ጠገበ
ፀሀፊም ድርሳን ዘገበ፡፡
.....//.....
ባይበላውም ያባለው!
መቸም ተጠቀም አላለው
አይ ወልዴ አባ ግድ የለው!
በየጥሻው ተወትፈን እንደተምች ስንረፈረፍ
ቅኔ በበቀቀን ሲዘረፍ
አቀርቅረን ስናንቋርር
ቅሪታችንን ስናንቃርር
እንደቀላጤ አከንባሎ ቁልቁሉ ባፍጢም ተተክለን
በእርኩስ አመዳይ ተበክልን
እንዲህ የትም ስንቀር እያየህ ዝም ካልክማ
እውነት እውነት ከመንበርህ የለህማ።
....//...
የከተማው ባህታዊ(አያ ሙሌ)
#ከዳግም_ህይወት....
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
ታሪክ መልኩን ቀይሮ እየተደገመ እንዳለ ሲገባን
ሀዘናችንንም በባለቅኔ ቀለም እንዲህ ደገምነው ጌታ ሆይ የት ነህ ፍጥረትህን በምህረት አስብ
እውነት ከመንበርህ የለህማ!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ምነዋ መንግሰተ ሰማይ! የምህረትሽ ቀን ራቀ?
ምነው ትንግርትሽ ረቀቀ ?
ምነው ኪዳንሽ ታጠፈ … ወዝሽ ወዘናሽ ነጠፈ?
እንደ ዳጉሳ ድፍድፍ … ላቦትሽ ተንጠፈጠፈ
አሳርሽ ጠሎ አሰፈፈ፤
......//...........
ምነው ጭር አለ ቀየው! ሀሩር ነዲዱ በረታ
ኮርማው ጥማዱ ተረታ
ምነው ነበልባሉ አየለ … ማሳው ተንቀለቀለ
ነቀለ ሞፈር ሰቀለ ተግድራ ደቀለ
ምነው ምድር ጨነገፈች ዝላ ተርገፈገፈች?
ካስማ እንደተደገፈች ምነው ተሳታብብ ረገፈች?
......//.....
ምነው ወላድ ተንሰለሰለ … ልሳነ ቃሉ ሰለለ
በቁሙ ከስሞ ከሰለ
አቤት የርግማን ቁርሾ
በንጣይ እርሾ መነሾ!
ምነው ላይፀድቅ በቀለ!
የሰው ልጅ ዋጋ ቀለለ
ትቢያ አፈር ተቀላቀለ
....//.....
ምን ይሉታል ይሄነን ፍርድ
እንዲህ ያለ ጉድ አለ እንዴ?
እግዜር ወንዱ እግዜር መንዴ!
ደረቅ ጡት እየጠባን ቁረንጮ ስንገተግት፤
ከመንግስተ ሰማይ የምህረት ግት፤
ምነው የማርያም ልጅ የስርየት ቀንህ ራቀ፤
ምነው ታምርህ ረቀቀ፤
.....//....
የኛስ ይሁን እንዳሻው ለእጥፍ ፈተና ከፈጠርከን
ለፍታችሁ ተፍታችሁ ኑ ካልከን
ለቀብር አፈር ከወጠንከን
ግን ፡- ግን ብላቴኖች ምን በደሉ
የማንን አደራ በልተው የማነን አማና አጎደሉ
እንብርታቸው ያላረረ
አጥንታቸው ያልከረረ
ሰማይ በቀል እንደቋጠረ
እጣቸውን እየመጠረ
መንገዳቸውን በእሾህ እያጠረ
እንደ ደራሽ ውሃ አግተልትሎ
በራብ አኮርማጅ ተልትሎ
ከእናት እቅፍ በግፍ ነጥቆ
ሲሰልፍብን ባጭር ታጥቆ
እያየህ ዝም ካልክማ
እውነት እውነት ከመንበርህ የለህማ!
.....//....
በማን ሊዳኝ ነው ቅጣቱ የሰው ዘር አንዲት ቅንጣቱ
ያባወራ ባላውራጣቱ
እንደ በልግ አውድማ ነዶ … ምድር ለቅልቆ ከምሮ
ነፍስ ከእስትንፋስ ነጥሎ … ሲኦል እቶን ውስጥ ሞጅሮ
በነበልባል መንሽ እየዘራ በረሀብ አራገበው
ሰው እርጥቡን አንገበገበው
ነፍስ ይማር እርካቡ ረገበ
ቀብርም አስከሬን ጠገበ
ፀሀፊም ድርሳን ዘገበ፡፡
.....//.....
ባይበላውም ያባለው!
መቸም ተጠቀም አላለው
አይ ወልዴ አባ ግድ የለው!
በየጥሻው ተወትፈን እንደተምች ስንረፈረፍ
ቅኔ በበቀቀን ሲዘረፍ
አቀርቅረን ስናንቋርር
ቅሪታችንን ስናንቃርር
እንደቀላጤ አከንባሎ ቁልቁሉ ባፍጢም ተተክለን
በእርኩስ አመዳይ ተበክልን
እንዲህ የትም ስንቀር እያየህ ዝም ካልክማ
እውነት እውነት ከመንበርህ የለህማ።
....//...
የከተማው ባህታዊ(አያ ሙሌ)
#ከዳግም_ህይወት....
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
#ለዒዴ_በላሁ_ሰርቼ
አካሌ ውስጡ ተንጦ ስሜቴ ቢዘባረቅም፤
ቀኑ ዒዱ ነውና መደሰቴን ግን አለቅም፤
እምባዬን እየዘራሁኝ የዒዴን ቀን አላበላሽም፤
ሳለቅስ ባድር ስንሰቀሰቅ፤
እንደ ስለት ልጅ ብነፋረቅ፤
ጊዜ በጠፍር ታስሮ ይመለስ ዘንድ ቢጎተት፤
ካለፈና ከነጎደ ተመልሰን ላንሰራበት፤
ተሰናብቶን ኮብልሏል ቀጥሮን ለቀጣይ አመት።
በማለቁ ባልደሰትም ተስፋዬን ግን አለምልሜ፤
ለመጪው አመት አልሜ፤
ልጸልይበት ደጋግሜ፤
የተቸገረን አለሁ ልለው ከፊቱ ቆሜ፤
በተስፋ ቅመም ቀምሜ፤
ሀዘኔን ከታትፌ በደስታ እያጣበኩኝ፤
ለራሴ ቃል ገብቼ፤
አዕምሮዬን አጎልብቼ፤
በመኖር ተስፋ አጣፍጬ ፤
ለዒዴ በላሁ ሰርቼ።
✍ተጻፈ በአንዋር ዩሱፍ
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
አካሌ ውስጡ ተንጦ ስሜቴ ቢዘባረቅም፤
ቀኑ ዒዱ ነውና መደሰቴን ግን አለቅም፤
እምባዬን እየዘራሁኝ የዒዴን ቀን አላበላሽም፤
ሳለቅስ ባድር ስንሰቀሰቅ፤
እንደ ስለት ልጅ ብነፋረቅ፤
ጊዜ በጠፍር ታስሮ ይመለስ ዘንድ ቢጎተት፤
ካለፈና ከነጎደ ተመልሰን ላንሰራበት፤
ተሰናብቶን ኮብልሏል ቀጥሮን ለቀጣይ አመት።
በማለቁ ባልደሰትም ተስፋዬን ግን አለምልሜ፤
ለመጪው አመት አልሜ፤
ልጸልይበት ደጋግሜ፤
የተቸገረን አለሁ ልለው ከፊቱ ቆሜ፤
በተስፋ ቅመም ቀምሜ፤
ሀዘኔን ከታትፌ በደስታ እያጣበኩኝ፤
ለራሴ ቃል ገብቼ፤
አዕምሮዬን አጎልብቼ፤
በመኖር ተስፋ አጣፍጬ ፤
ለዒዴ በላሁ ሰርቼ።
✍ተጻፈ በአንዋር ዩሱፍ
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
ስላንቺ አይደለም
~~~~
°
( አብርሃም ታደለ አጥራ)
፧
ፀጉሯ ሀር ነው - ሰውን ሚያሳስት
በጀርባዋ ውሎ - አንገቷን ሚጎትት
ግንባሯም የፀዳ - ሁሉን ያማለለ
ከቅንድቧ በላይ - ፀጉሯን ያዘለ፣
.....እያልኩኝ ብፅፍም
ስለኔ ነው አትበይ
ስላንቺ አይደለም
ስላንቺ የሚፃፍ - እኔ ዘንድ አልዋለም፤
፡
አይኗም ባለ ጨረር - ደርሶ የሚዋጋ
አንስቶ አፍርጦ - ከመሬት ሚያላጋ
ስልኩክ አፍንጫዋም - ቁልቁል ያዘመመ
ለአይኖቿ ውበት - ዘብነት የቆመ
እያልኩኝ ባወራ - ቃላት ብለቃቅም
ሙች ሙች አለሜ
ስለኔ ነው አትበይ - ስላቺ አይደለም፤
፡
ከጉንጯ ላይ ውሎ - ብቅ ጥልቅ የሚለው
ሚሞት ሰው ካገኘ - ስርጉዷም ገዳይ ነው
ከንፈሯም እንጆሪ - ፊቷን የመጠነ
ላይኛው ለስልሶ - ታቹ የቀጠነ
እንቡጥቡጥ ስጋ ነው - ሳሙኝ ሳሙኝ የሚል
ቁንጅናዋን አዝሎ - ካይን ላይ ሚንቋለል
ብዬ ብተይብም - እጅግ ተገርሜ
ላንቺ እንዳይመስልሽ - እመኚኝ አለሜ፤
፡
ከናፍርቷን ገፍተው - ሾልከው የሚታዩት
ከወተትም ነፅተው - እሸት የመሰሉት
እነዛ ጥርሶቿ - ስቀው ሲፈግጉም
ልብን ለመተርከክ - ጉልበት አይፈልጉም
እያልኩኝ ስለፍፍ
ካልሽኝ ስለኔ ነው
እኔን አለማመን - ታውቅያለሽ መብትሽ ነው፤
፡
ስለ አንገቷስ ቢሆን
ምን አይነት ቃል ይሻል - የቱስ ይገልፀዋል
ተቋጭቶ ላይሳል
እንዲው በደፈና - ባይወራ ይሻላል
ብቻ ..
ከአገጯ በታች - ቆሞ መሰደሩ
ደረቷን ሊገናኝ - ድልድዩን ማሰሩ
ያያት ሰው ፈራጅ ነው
ድንቀ ቅርፅ ፊቷ - ሊያዝል መፈጠሩ፣
እናም ይሄን ሰምተሽ
ስለኔ ነው አትበይ - ስላንገት ሳወራ
ብዙ ሚያምር አለ - ከእንስቶች ተራ፤
፡
ተክለ ሰውነቷ
ዳሌና ጡቶቿ
ተሸክመው የኖሩት - እነዛ እግሮቿ
ትርኪ ምርኪም ቢሆን - ሲጫሙ ያምራሉ
የውበቷን ፀዳል - እጅግ ይገልፃሉ
መሬቱም ፍራሽ ነው - እሷ ስትረግጠው
እንቅፋቶች ሁሉ
ሟሙተው ይሰርጋሉ
ለሷ ያደላሉ - ከሌሎች አብልጠው
ብዬ ስቸከችክ
ይህ ሁሉ ለኔ ነው - ብሎ ቢዘርፍ አፍሽ
እመኚኝ የኔ ውብ
የተፃፈው ሁሉ - ላንቺ አይመሰልሽ
፡
# ባይሆን ..
ይሄ ሁሉ ነገር - በግርምት መፃፌ
በገላሽ ወደብ ላይ - ሄጄ መንሳፈፌ
ለኔ ነው ቢያስባለሽ
ብታውቂ ነውና - ቀድሞውን ውበትሽ
እኔ አልቀየምሽ፣
ግና አትሳሳች
ይሄ ሁሉ ነገር - ስላንቺ አይደለም
ስላንቺ የሚፃፍ - አንዳች ነገር የለም
አድናቆቴ ሁሉ
አግራሞቴ ሁሉ
በገላሽ ላይ ውሎ - የሚብከነከነው
አንቺን ውብ አድርጎ
የቀመረሽ ጌታን - ማወደሴ'ኮ ነው።
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
~~~~
°
( አብርሃም ታደለ አጥራ)
፧
ፀጉሯ ሀር ነው - ሰውን ሚያሳስት
በጀርባዋ ውሎ - አንገቷን ሚጎትት
ግንባሯም የፀዳ - ሁሉን ያማለለ
ከቅንድቧ በላይ - ፀጉሯን ያዘለ፣
.....እያልኩኝ ብፅፍም
ስለኔ ነው አትበይ
ስላንቺ አይደለም
ስላንቺ የሚፃፍ - እኔ ዘንድ አልዋለም፤
፡
አይኗም ባለ ጨረር - ደርሶ የሚዋጋ
አንስቶ አፍርጦ - ከመሬት ሚያላጋ
ስልኩክ አፍንጫዋም - ቁልቁል ያዘመመ
ለአይኖቿ ውበት - ዘብነት የቆመ
እያልኩኝ ባወራ - ቃላት ብለቃቅም
ሙች ሙች አለሜ
ስለኔ ነው አትበይ - ስላቺ አይደለም፤
፡
ከጉንጯ ላይ ውሎ - ብቅ ጥልቅ የሚለው
ሚሞት ሰው ካገኘ - ስርጉዷም ገዳይ ነው
ከንፈሯም እንጆሪ - ፊቷን የመጠነ
ላይኛው ለስልሶ - ታቹ የቀጠነ
እንቡጥቡጥ ስጋ ነው - ሳሙኝ ሳሙኝ የሚል
ቁንጅናዋን አዝሎ - ካይን ላይ ሚንቋለል
ብዬ ብተይብም - እጅግ ተገርሜ
ላንቺ እንዳይመስልሽ - እመኚኝ አለሜ፤
፡
ከናፍርቷን ገፍተው - ሾልከው የሚታዩት
ከወተትም ነፅተው - እሸት የመሰሉት
እነዛ ጥርሶቿ - ስቀው ሲፈግጉም
ልብን ለመተርከክ - ጉልበት አይፈልጉም
እያልኩኝ ስለፍፍ
ካልሽኝ ስለኔ ነው
እኔን አለማመን - ታውቅያለሽ መብትሽ ነው፤
፡
ስለ አንገቷስ ቢሆን
ምን አይነት ቃል ይሻል - የቱስ ይገልፀዋል
ተቋጭቶ ላይሳል
እንዲው በደፈና - ባይወራ ይሻላል
ብቻ ..
ከአገጯ በታች - ቆሞ መሰደሩ
ደረቷን ሊገናኝ - ድልድዩን ማሰሩ
ያያት ሰው ፈራጅ ነው
ድንቀ ቅርፅ ፊቷ - ሊያዝል መፈጠሩ፣
እናም ይሄን ሰምተሽ
ስለኔ ነው አትበይ - ስላንገት ሳወራ
ብዙ ሚያምር አለ - ከእንስቶች ተራ፤
፡
ተክለ ሰውነቷ
ዳሌና ጡቶቿ
ተሸክመው የኖሩት - እነዛ እግሮቿ
ትርኪ ምርኪም ቢሆን - ሲጫሙ ያምራሉ
የውበቷን ፀዳል - እጅግ ይገልፃሉ
መሬቱም ፍራሽ ነው - እሷ ስትረግጠው
እንቅፋቶች ሁሉ
ሟሙተው ይሰርጋሉ
ለሷ ያደላሉ - ከሌሎች አብልጠው
ብዬ ስቸከችክ
ይህ ሁሉ ለኔ ነው - ብሎ ቢዘርፍ አፍሽ
እመኚኝ የኔ ውብ
የተፃፈው ሁሉ - ላንቺ አይመሰልሽ
፡
# ባይሆን ..
ይሄ ሁሉ ነገር - በግርምት መፃፌ
በገላሽ ወደብ ላይ - ሄጄ መንሳፈፌ
ለኔ ነው ቢያስባለሽ
ብታውቂ ነውና - ቀድሞውን ውበትሽ
እኔ አልቀየምሽ፣
ግና አትሳሳች
ይሄ ሁሉ ነገር - ስላንቺ አይደለም
ስላንቺ የሚፃፍ - አንዳች ነገር የለም
አድናቆቴ ሁሉ
አግራሞቴ ሁሉ
በገላሽ ላይ ውሎ - የሚብከነከነው
አንቺን ውብ አድርጎ
የቀመረሽ ጌታን - ማወደሴ'ኮ ነው።
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
*ክ.ፍ.ተ.ት*
ታስታውስ እንደሆን
እኔ እና አንተ ሆነን ተፈጥሮን ስንዳኛት
ሁለት ነበር መልኳ
መንቶ ነበር ልኳ
ከእኔ እና አንተ አይዘልም እ ና ነው ታሪኳ
.
አዳም እና ሔዋን
እሣት እና ውሃ
ጥቁር እና ነጩ
ቀዝቃዛ እና ሙቁ
ንጋት እና ፅልመት
መሞት እና ህይወት
ወዘተ ወዘተ እየተባባልን ተፈጥሮን ስንዳኛት
መቼ አስተዋልነው በ እ ና መካከል የተፃፈን ውበት
...
አየህ ሳስተውለው የተፈጥሮን ል'ቀት
ስውር ነው ጥበቡ ደፍረው የማይዳኙት
...
እናልህ
ከአዳም እና ሔዋን የቀደመ ውበት
በ እ ና መካከል የታለፈ ክፍተት
የአዳም ማዳረሻ የሚሉት አፍላነት
...
ደግሞ ሌላ ክ ፍ ተ ት
ጥቁር እና ነጩ የሚገለጡበት
የሆነ አይነት ውበት
...
ደግሞ ሌላ ክ ፍ ተ ት
ቀዝቃዛ እና ሙቁ የሚጣመሩበት
ለብታ የሚሉት
...
አየህልኝ አይደል በ እ ና መካከል የተፃፈ ቅኔ
ከንጋቴ በልጦ ከፅልመቱ ቀድሞ ሲያውለኝ ከቀኔ
....
ታዘብክልኝ አይደል ህይወት ቀን ሲገፋ ሞቱን ሲያቃርበው
በእርጅና መንገድ ሞትን ሲያላምደው
...
አየህልኝ አይደል በእና መካከል የታለፈን ዕውነት
የተፈጥሮን ጥልቀት የውበትን ውበት
....... .//........
በ ሔለን ፋንታሁን
፰-፱-፳፻፲፪
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
ታስታውስ እንደሆን
እኔ እና አንተ ሆነን ተፈጥሮን ስንዳኛት
ሁለት ነበር መልኳ
መንቶ ነበር ልኳ
ከእኔ እና አንተ አይዘልም እ ና ነው ታሪኳ
.
አዳም እና ሔዋን
እሣት እና ውሃ
ጥቁር እና ነጩ
ቀዝቃዛ እና ሙቁ
ንጋት እና ፅልመት
መሞት እና ህይወት
ወዘተ ወዘተ እየተባባልን ተፈጥሮን ስንዳኛት
መቼ አስተዋልነው በ እ ና መካከል የተፃፈን ውበት
...
አየህ ሳስተውለው የተፈጥሮን ል'ቀት
ስውር ነው ጥበቡ ደፍረው የማይዳኙት
...
እናልህ
ከአዳም እና ሔዋን የቀደመ ውበት
በ እ ና መካከል የታለፈ ክፍተት
የአዳም ማዳረሻ የሚሉት አፍላነት
...
ደግሞ ሌላ ክ ፍ ተ ት
ጥቁር እና ነጩ የሚገለጡበት
የሆነ አይነት ውበት
...
ደግሞ ሌላ ክ ፍ ተ ት
ቀዝቃዛ እና ሙቁ የሚጣመሩበት
ለብታ የሚሉት
...
አየህልኝ አይደል በ እ ና መካከል የተፃፈ ቅኔ
ከንጋቴ በልጦ ከፅልመቱ ቀድሞ ሲያውለኝ ከቀኔ
....
ታዘብክልኝ አይደል ህይወት ቀን ሲገፋ ሞቱን ሲያቃርበው
በእርጅና መንገድ ሞትን ሲያላምደው
...
አየህልኝ አይደል በእና መካከል የታለፈን ዕውነት
የተፈጥሮን ጥልቀት የውበትን ውበት
....... .//........
በ ሔለን ፋንታሁን
፰-፱-፳፻፲፪
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
Forwarded from 666( ኢልሙናቲ ) ሀይማኖት ምዝገባ ማእከል via @Josy_Button_Bot
Forwarded from 666( ኢልሙናቲ ) ሀይማኖት ምዝገባ ማእከል via @Josy_Button_Bot
ላትመለስ ነው ወይ?
🙄🙄🙄🙄
ከትንሹ ገንዘብ እስከ ትልቁ ጊዜ፣
እንኳንና ደስታ ሲያንገላታኝ ትካዜ፣
ካጠገቤ ሆነህ እንዳላባበልከኝ፣
ያንን ሁሉ ጥፋት ኣፉ እንዳላልከኝ፣
እውነት እቺ ጥቂቷ ናት ጭልጥ ያረገችህ፣
እውነት እቺ ጥቂቷ ናት ከኔ ያራቀችህ፣
ከሆነስ ሆነና ላትመለስ ይሁን እንዲ የቀረኸው፣
ኣላምንም ብሏል ልቤ እስኪ ይፍራ እውነቱን ንገረው ።
ወይ እድል ስጠኝ ይቅርታ ልበልህ፣
ወይም እንደ ድሮ ኣፉ በለኝ ቀድመህ ።
ልቤ ተወዛግቧል ቁርጡን ኣሳውቀኝ፣
ቅረቢኝ ወይም ቅሪብኝ በለኝ።
ኧረ ግን ኧረ ግን
ላትመለስ ይሆን?
ኣየሁት የሚል ጠፍቷል፣
ፍንጭህንም ሳይቀር ደብቀህብኛል፣
ልቤ በመወላወል መፅናት ኣቅቶኛል::
ደግሞ በሌላ ጎን...
"ይመጣል ኣይመጣም
ትቶሽ ሄዷል መቼም ኣይተውሽም"
እያሉ ሰዎች ያወናብዱኛል፣
ለምን ኣትነግረኝም እጅጉን መሮኛል።
በርግጥ ብትመለስ የድሮውን ኣንተን፣
ያንን ቅልስልሱን ቶሎ ይቅር ባዩን፣
ላላገኘው እችላለሁ....
ግን ችግር የለም ይበለኝ! እችለዋለሁ፣
ጥፋቴ ነውና እቀበለዋለሁ፣
ግን ደሞ ባትመለስና ብትቀር ከመስክ፣
ህይወቴም ዓለሜም ኣንተ ስለሆንክ፣
ስህተቴን የሚቋቋመው አዕምሮዬ ይክደኛል፣
ልክ ኣንተ እንዳደረከው ጠፍቶ ይኮበልላል።
(የዱድያሌብ ገፅ)
ይድረስ በመጠበቅ ወጋገን ለተጠመድሽ ሁላ😂
@hutoffun
@hutoffun
🙄🙄🙄🙄
ከትንሹ ገንዘብ እስከ ትልቁ ጊዜ፣
እንኳንና ደስታ ሲያንገላታኝ ትካዜ፣
ካጠገቤ ሆነህ እንዳላባበልከኝ፣
ያንን ሁሉ ጥፋት ኣፉ እንዳላልከኝ፣
እውነት እቺ ጥቂቷ ናት ጭልጥ ያረገችህ፣
እውነት እቺ ጥቂቷ ናት ከኔ ያራቀችህ፣
ከሆነስ ሆነና ላትመለስ ይሁን እንዲ የቀረኸው፣
ኣላምንም ብሏል ልቤ እስኪ ይፍራ እውነቱን ንገረው ።
ወይ እድል ስጠኝ ይቅርታ ልበልህ፣
ወይም እንደ ድሮ ኣፉ በለኝ ቀድመህ ።
ልቤ ተወዛግቧል ቁርጡን ኣሳውቀኝ፣
ቅረቢኝ ወይም ቅሪብኝ በለኝ።
ኧረ ግን ኧረ ግን
ላትመለስ ይሆን?
ኣየሁት የሚል ጠፍቷል፣
ፍንጭህንም ሳይቀር ደብቀህብኛል፣
ልቤ በመወላወል መፅናት ኣቅቶኛል::
ደግሞ በሌላ ጎን...
"ይመጣል ኣይመጣም
ትቶሽ ሄዷል መቼም ኣይተውሽም"
እያሉ ሰዎች ያወናብዱኛል፣
ለምን ኣትነግረኝም እጅጉን መሮኛል።
በርግጥ ብትመለስ የድሮውን ኣንተን፣
ያንን ቅልስልሱን ቶሎ ይቅር ባዩን፣
ላላገኘው እችላለሁ....
ግን ችግር የለም ይበለኝ! እችለዋለሁ፣
ጥፋቴ ነውና እቀበለዋለሁ፣
ግን ደሞ ባትመለስና ብትቀር ከመስክ፣
ህይወቴም ዓለሜም ኣንተ ስለሆንክ፣
ስህተቴን የሚቋቋመው አዕምሮዬ ይክደኛል፣
ልክ ኣንተ እንዳደረከው ጠፍቶ ይኮበልላል።
(የዱድያሌብ ገፅ)
ይድረስ በመጠበቅ ወጋገን ለተጠመድሽ ሁላ😂
@hutoffun
@hutoffun
ልክ እንደ ተራ ሰው
እመነኝ ወዳጄ ዘመንህን ጨርሰሀል፣
የልብ ምቴም ሳይቀር ተቀይሮብሀል፣
"ልሄድ ነው!"ስትለኝ የሚጎርፈው እንባዬ፣
መሄድህን ኣስቦ 'ሚርድልህ ገላዬ፣
ውዴ እመነኝ ኣሁን የለም፣
"እንዴት ሆኖ?"ላልከው እኔም ኣልገባኝም።
ብቻ ልቤ መሮብሀል፣
አጠገብህ ላይደርስ ምሎልሀል።
"እስኪ ትርታሽን አድምጪ!"ብለኸኝ ኣልነበር፣
በደንብ ኣዳመጥኩት ባይነግረኝም ኣዲስ ነገር፣
"ትዝታችንን አስቢ!"ያልከኝንም ኣረሳሁትም፣
ችግሩ ፍቅር 'ሚሸት ነገር ኣላገኘሁበትም፣
ያሳለፍነውንም ጊዜ ኣስታወስኩት፣
ለካስ በማይሆን ልጅ ነበር የታወርኩት።
በቃህ....ሆዴ!!!
ምንም ቦታ ላታገኝ ልቤን ኣታድርቀው፣
የተቆለፈ በር እንደ ጅል ማንኳኳቱን ተወው፣
አውጥቶ ጥሎሀል ልክ እንደ ተራ ሰው::
(የዱድያሌብ ገፅ)
ይድረስ "ለቆራጥ ልቦች"
@hutoffun
እመነኝ ወዳጄ ዘመንህን ጨርሰሀል፣
የልብ ምቴም ሳይቀር ተቀይሮብሀል፣
"ልሄድ ነው!"ስትለኝ የሚጎርፈው እንባዬ፣
መሄድህን ኣስቦ 'ሚርድልህ ገላዬ፣
ውዴ እመነኝ ኣሁን የለም፣
"እንዴት ሆኖ?"ላልከው እኔም ኣልገባኝም።
ብቻ ልቤ መሮብሀል፣
አጠገብህ ላይደርስ ምሎልሀል።
"እስኪ ትርታሽን አድምጪ!"ብለኸኝ ኣልነበር፣
በደንብ ኣዳመጥኩት ባይነግረኝም ኣዲስ ነገር፣
"ትዝታችንን አስቢ!"ያልከኝንም ኣረሳሁትም፣
ችግሩ ፍቅር 'ሚሸት ነገር ኣላገኘሁበትም፣
ያሳለፍነውንም ጊዜ ኣስታወስኩት፣
ለካስ በማይሆን ልጅ ነበር የታወርኩት።
በቃህ....ሆዴ!!!
ምንም ቦታ ላታገኝ ልቤን ኣታድርቀው፣
የተቆለፈ በር እንደ ጅል ማንኳኳቱን ተወው፣
አውጥቶ ጥሎሀል ልክ እንደ ተራ ሰው::
(የዱድያሌብ ገፅ)
ይድረስ "ለቆራጥ ልቦች"
@hutoffun
ሄዋን ምን ፈየደች?
😏😏😏😏
ገና ድሮ...
ለኣዳም ሄዋን ሳትሠጠው፣
ውብ ህይወት ነበረው፣
ችግሩ ሚጀምረው ካፈጣጠሯ ነው፣
የጎን ኣጥንቱን የተሻማችው፣
ኋላም ርስት ምድሩን ኣሳጣችው።
ታድያ ሄዋን ምን ፈየደች?
ደሞ በዚ ኣላበቃች፣
ከባዱን ስህተት ሠራች፣
"ለምን እኔ ብቻ?" ስትልም ኣሰበች
ኋላም ለባሏ አጎረሰች።
ሄዋን የእባብን ኣመጣጥ ፩ም ሳታስበው፣
"የሠማይ ንግስት ሇይ!"መባሏ ልቦ እያሻፈደው፣
በከፍታ ወጋገን በመታበይ መንፈስ ተመልታ፣
ወጣች ከ'ርስቷ በለሲቷን ኣስነብታ።
በፍጥረት እንባ መንገስ በፍጡር ደም መክበር፣
ስለሌለ በዚያች እውነተኛ ምድር፣
ከገነት ተባረረች ጦሷንም ለኛ ኣስተረፈች።
እና ታድያ ሄዋን ምን ፈየደች?
ደሞ ቆይታ ቆ........ይታ
በንስሐ ለመፅዳት ከኣዳም ተለይታ፣
ስትፀልይ ባእቷን ዘግታ፣
ከይሲው ተጠቅሞ የመላዕክት ሠላምታ፣
ኣላት "ፀሎትሽ ተሠምቷል ከጌታ"።
ድጋሚ ኣመነችው ምንም ሳታጣራ፣
ራሷን ልክ እንደ ብፁዕ ቆጥራ፣
"ይበቃኛል ሱባዔ'ዬ፣
ከዚህ በላይ ኣይቀጣኝም ቸሩ ጌታዬ"።
ብላ እንደ ልማዷ ኣዳሟን ጎትታ፣
ኣስወጣችው ከዚያ ታላቅ ተመስጦ ከድንቁ ዝምታ::
እኮ እስኪ ሄዋን ምን ፈየደች?
(የዱድያሌብ ገፅ)
ይድረስ "እ🤔"
@hutoffun
😏😏😏😏
ገና ድሮ...
ለኣዳም ሄዋን ሳትሠጠው፣
ውብ ህይወት ነበረው፣
ችግሩ ሚጀምረው ካፈጣጠሯ ነው፣
የጎን ኣጥንቱን የተሻማችው፣
ኋላም ርስት ምድሩን ኣሳጣችው።
ታድያ ሄዋን ምን ፈየደች?
ደሞ በዚ ኣላበቃች፣
ከባዱን ስህተት ሠራች፣
"ለምን እኔ ብቻ?" ስትልም ኣሰበች
ኋላም ለባሏ አጎረሰች።
ሄዋን የእባብን ኣመጣጥ ፩ም ሳታስበው፣
"የሠማይ ንግስት ሇይ!"መባሏ ልቦ እያሻፈደው፣
በከፍታ ወጋገን በመታበይ መንፈስ ተመልታ፣
ወጣች ከ'ርስቷ በለሲቷን ኣስነብታ።
በፍጥረት እንባ መንገስ በፍጡር ደም መክበር፣
ስለሌለ በዚያች እውነተኛ ምድር፣
ከገነት ተባረረች ጦሷንም ለኛ ኣስተረፈች።
እና ታድያ ሄዋን ምን ፈየደች?
ደሞ ቆይታ ቆ........ይታ
በንስሐ ለመፅዳት ከኣዳም ተለይታ፣
ስትፀልይ ባእቷን ዘግታ፣
ከይሲው ተጠቅሞ የመላዕክት ሠላምታ፣
ኣላት "ፀሎትሽ ተሠምቷል ከጌታ"።
ድጋሚ ኣመነችው ምንም ሳታጣራ፣
ራሷን ልክ እንደ ብፁዕ ቆጥራ፣
"ይበቃኛል ሱባዔ'ዬ፣
ከዚህ በላይ ኣይቀጣኝም ቸሩ ጌታዬ"።
ብላ እንደ ልማዷ ኣዳሟን ጎትታ፣
ኣስወጣችው ከዚያ ታላቅ ተመስጦ ከድንቁ ዝምታ::
እኮ እስኪ ሄዋን ምን ፈየደች?
(የዱድያሌብ ገፅ)
ይድረስ "እ🤔"
@hutoffun
#ልጅነትና_እውቀት
.
ይመስለኝ ነበረ
.
.
ከእለታት አንድ ቀን
ጦርነት ሁሉ አልቆ፥ ሰላም የሚሰፍን
ይመስለኝ ነበረ
ትልልቅ ሰው ሁሉ
ሚስጥር የሚደብቅ፥ ገመና የሚሸፍን።
.
ይመስለኝ ነበረ
ቤተስኪያን ሂያጅ ሁሉ፥ እውነት የሚናገር
ሰው የመሬት ዜጋ
መሬትም የሰው ልጅ፥ ሁሉም የራስ ሃገር፡፡
.
ይመስለኝ ነበረ
የታመመ ሁሉ ፥ ታክሞ የሚድን
የተራበ ጠግቦ
የምስጋና ንፋስ፥ ምድርን የሚከድን።
.
ይመስሉኝ ነበረ
አብረው ያየኋቸው፥ ከልብ ሚዋደዱ
‘ሚዋደዱ ሁሉ
የማይለያዩ፥ የማይከዳዱ።
ሰው በሙሉ መልካም
ያጠፋ እንኳን ቢኖር፥ ወዲያው የሚቀጣ
መጥፎው ተወግዶ
ደግ የሚነግስበት፥ ዘመን የሚመጣ።
.
ይመስለኝ ነበረ
.
.
ማደግ ደስ የሚያሰኝ
ለሚራበሽ አለም፥ መድሃኒት የማስገኝ
በመኖሬ ምክንያት
የሌላውን ህይወት፥ ሳሻሽል የምገኝ፡፡
.
.
ይመስለኝ ነበረ....።
.
.
የዋህ ልጅነቴን
አደግሁና አየሁት፥ ትዝብቴ አሳቀቀኝ
ሃሳቤን ቢያውቁብኝ
መሳቂያ መሆኔን፥ ማን አስጠነቀቀኝ?
.
አደግሁና ጀመርኩ
በያደባባዩ፥ መካሰስ መወንጀል
ባከማቸሁት ላይ
ነጥቆ ማከማቸት፥ ያማኜን መከጀል።
በሰው ሰራሽ ድንበር
በሰው ሰራሽ ቀንበር፥ ቡድን እየሰራሁ
እንደ ሰኔ መሬት
እየተሸናሸንኩ፥ መባላት ከዘራሁ
ማነው ያስተማረኝ
ታቦት ሰርቆ መሸጥ፥ ክህነቴን ጥዬ
ማነው የነገረኝ
ሸንግሎ ማሳደር፥ የእግዜር ሰው ነኝ ብዬ?
የሚል ጥያቄ አለኝ
ለዚያ ልጅነቴ፥ ለዛሬው ማደጌ
ማን ያብራራልኛል
በሽታ መፍጠሬን፥ መድሃኒት ፈልጌ?
መሳሪያ ፈልስፌ
ጠብ-መንጃ መሸጤን፥ ለጦር ማስታጠቄን
ማን ይመልስልኝ
የማደግ ክፋቴን፥ የልጅነት ሃቄን?
.
አለም አኬልዳማ
በእድሜዬ እሾህ ማሳ፥ ደማምቼ ባለፍኩ
አደግሁና ገባኝ
ሌላው ምን አገባኝ.. ራሴን ካተረፍኩ?
© Haileleul_Aph
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
.
ይመስለኝ ነበረ
.
.
ከእለታት አንድ ቀን
ጦርነት ሁሉ አልቆ፥ ሰላም የሚሰፍን
ይመስለኝ ነበረ
ትልልቅ ሰው ሁሉ
ሚስጥር የሚደብቅ፥ ገመና የሚሸፍን።
.
ይመስለኝ ነበረ
ቤተስኪያን ሂያጅ ሁሉ፥ እውነት የሚናገር
ሰው የመሬት ዜጋ
መሬትም የሰው ልጅ፥ ሁሉም የራስ ሃገር፡፡
.
ይመስለኝ ነበረ
የታመመ ሁሉ ፥ ታክሞ የሚድን
የተራበ ጠግቦ
የምስጋና ንፋስ፥ ምድርን የሚከድን።
.
ይመስሉኝ ነበረ
አብረው ያየኋቸው፥ ከልብ ሚዋደዱ
‘ሚዋደዱ ሁሉ
የማይለያዩ፥ የማይከዳዱ።
ሰው በሙሉ መልካም
ያጠፋ እንኳን ቢኖር፥ ወዲያው የሚቀጣ
መጥፎው ተወግዶ
ደግ የሚነግስበት፥ ዘመን የሚመጣ።
.
ይመስለኝ ነበረ
.
.
ማደግ ደስ የሚያሰኝ
ለሚራበሽ አለም፥ መድሃኒት የማስገኝ
በመኖሬ ምክንያት
የሌላውን ህይወት፥ ሳሻሽል የምገኝ፡፡
.
.
ይመስለኝ ነበረ....።
.
.
የዋህ ልጅነቴን
አደግሁና አየሁት፥ ትዝብቴ አሳቀቀኝ
ሃሳቤን ቢያውቁብኝ
መሳቂያ መሆኔን፥ ማን አስጠነቀቀኝ?
.
አደግሁና ጀመርኩ
በያደባባዩ፥ መካሰስ መወንጀል
ባከማቸሁት ላይ
ነጥቆ ማከማቸት፥ ያማኜን መከጀል።
በሰው ሰራሽ ድንበር
በሰው ሰራሽ ቀንበር፥ ቡድን እየሰራሁ
እንደ ሰኔ መሬት
እየተሸናሸንኩ፥ መባላት ከዘራሁ
ማነው ያስተማረኝ
ታቦት ሰርቆ መሸጥ፥ ክህነቴን ጥዬ
ማነው የነገረኝ
ሸንግሎ ማሳደር፥ የእግዜር ሰው ነኝ ብዬ?
የሚል ጥያቄ አለኝ
ለዚያ ልጅነቴ፥ ለዛሬው ማደጌ
ማን ያብራራልኛል
በሽታ መፍጠሬን፥ መድሃኒት ፈልጌ?
መሳሪያ ፈልስፌ
ጠብ-መንጃ መሸጤን፥ ለጦር ማስታጠቄን
ማን ይመልስልኝ
የማደግ ክፋቴን፥ የልጅነት ሃቄን?
.
አለም አኬልዳማ
በእድሜዬ እሾህ ማሳ፥ ደማምቼ ባለፍኩ
አደግሁና ገባኝ
ሌላው ምን አገባኝ.. ራሴን ካተረፍኩ?
© Haileleul_Aph
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
#ቀሽም_ብይን
ምሩቅ ጥበብ ሰሪ
የሸራ ቀበኛ ፥ የቀለም ቀማሪ
ጠቢባን ጠበብቶች
የቀለም አባቶች
የብሩሽ አርበኛ ፥ የኪነት ገማቾች
በዘመን የቆሙት
ከትውልዱ ወጥተው ፥ የሚተዛዘቡት
አልያ ....ዘመን አልፈው
በነጠረ ስራ....
ከኛ ጀምበር ጥላ ፥ በሞገስ የቆሙት
መናኛም.....ሆኑ ...ዝነኛ
ትሁትም ....ሆኑ ....ጉረኛ
እርቃን አፍቃሪዎች!
ምስል ደጋሚዎች!
ምጡቅ አሳቢዎች!
ብቻ.....ሰአሊ የሆኑ
ሸራ የወጠሩ ፥ ብሩሽ የዘገኑ
ሁለት ግዜ ነው.... የሚስሉ
ሁለት ግዜ ነው ....የሚያጤኑ
#አንድ...
በረጅም ግዜ ተመስጦ ...በጥቂት ግዜ መቃኘት
የሚፈለገውን ውበት ፥ ተኩሮ በማየት
በህሊና ችንካር ሸራ
ያኔ ነው ፥ የጥበብ ሽል ፥ ፅንሱ የሚዘራ
#ሁለት...
እንግዲህ በሀሳብ ፥ ምስሉ እንደታያቸው
በውን አለም ሸራ ...ይጫራል ንድፋቸው
አይን እና እጆቻቸው ፥ እኩል እስከቻሉ
የግል አይናቸውን ፥ ለሰው ይቸራሉ
ያዩትን ...ለማውረድ
ፅንፉን ለማዋደደ
ጣጥረው..
ጫጭረው...
ሞንጭረው...
የለቀለቁትን.... አቅመ ጥበብ ቅይጥ
ጋለሪ እያገባ ...ወዳጅ እንዲያቋምጥ
ሁለቴ ተረግዞ...ሁለቴ ይማጣል
አፍቃሪው በርትቶ....
ወላድ ለመጠየቅ ...አውደርይ ይወጣል
በዚህ ኩናቴ ውስጥ...
አንዳቹም ሰአሊ
ልጁን የሰቀለ ፥ በቤት በጋለሪ
እስኪያረጅ ...እስኪሸጥ
ማንጠልጠል ይወዳል ፥ ጭንቁን እንደ ትሪ
የብሩሹ አጣጣል ፥ ቀለም ስብጥሩ
የመልእክቱ ምጥቀት ፥ ብራና ሚስጥሩ
ገለፃው......ውብቱ
ጨረሩ ....ሙቀቱ
ሺህ ግዜ ፥ እልፍ አመት
እኛን ቢገርመንም...
ቢያጅበንም ...ደርሶ
የሁለቴ ምጥ ነው
ዘመን የሚሻገር ፥ በቀለማት ርሶ
አየሽልኝ ውዴ....
እንዲህ ያለውን ሰው
ወሮታው ሲዘከር ስላንጠለጠለ
በምናቤ ጓዳ...
የማይከስም ምስልን...ራሴ ላስጠለለ
አፍቃሪነት ዳሩ...
ከጠቢብም በላይ ...ጥበብ እንዳዘለ
ምስክሬ ነፍሴ
ባገኘው ወረቀ....አንቺን እንደሳለ
ምን ይሆን መስፈርቱ
ማነው የሚረዳ...
አይኔ በከደነ ፥ ገፅታሽ ሲቀዳ
ምስልሽ ሲንቀራወዝ ...በህልሜ ሰሌዳ
በውኔም በወረቀት ፥ ሲብስ በግድግዳ
የብዙ ብዙን ምጥ....አዕላፈ ውልጃ
ከሁለት ግልግል...ካንድ ተኩል ውርጃ
ለማመዛዘኛ....ቢጠፋ ብልሀቱ
ተደብቄ ኖርኩኝ ፥ የመልክሽ ሎሬቱ ።
✍ አብርሀም_ተክሉ ( መርዕድ)
@Abrham_teklu
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
ምሩቅ ጥበብ ሰሪ
የሸራ ቀበኛ ፥ የቀለም ቀማሪ
ጠቢባን ጠበብቶች
የቀለም አባቶች
የብሩሽ አርበኛ ፥ የኪነት ገማቾች
በዘመን የቆሙት
ከትውልዱ ወጥተው ፥ የሚተዛዘቡት
አልያ ....ዘመን አልፈው
በነጠረ ስራ....
ከኛ ጀምበር ጥላ ፥ በሞገስ የቆሙት
መናኛም.....ሆኑ ...ዝነኛ
ትሁትም ....ሆኑ ....ጉረኛ
እርቃን አፍቃሪዎች!
ምስል ደጋሚዎች!
ምጡቅ አሳቢዎች!
ብቻ.....ሰአሊ የሆኑ
ሸራ የወጠሩ ፥ ብሩሽ የዘገኑ
ሁለት ግዜ ነው.... የሚስሉ
ሁለት ግዜ ነው ....የሚያጤኑ
#አንድ...
በረጅም ግዜ ተመስጦ ...በጥቂት ግዜ መቃኘት
የሚፈለገውን ውበት ፥ ተኩሮ በማየት
በህሊና ችንካር ሸራ
ያኔ ነው ፥ የጥበብ ሽል ፥ ፅንሱ የሚዘራ
#ሁለት...
እንግዲህ በሀሳብ ፥ ምስሉ እንደታያቸው
በውን አለም ሸራ ...ይጫራል ንድፋቸው
አይን እና እጆቻቸው ፥ እኩል እስከቻሉ
የግል አይናቸውን ፥ ለሰው ይቸራሉ
ያዩትን ...ለማውረድ
ፅንፉን ለማዋደደ
ጣጥረው..
ጫጭረው...
ሞንጭረው...
የለቀለቁትን.... አቅመ ጥበብ ቅይጥ
ጋለሪ እያገባ ...ወዳጅ እንዲያቋምጥ
ሁለቴ ተረግዞ...ሁለቴ ይማጣል
አፍቃሪው በርትቶ....
ወላድ ለመጠየቅ ...አውደርይ ይወጣል
በዚህ ኩናቴ ውስጥ...
አንዳቹም ሰአሊ
ልጁን የሰቀለ ፥ በቤት በጋለሪ
እስኪያረጅ ...እስኪሸጥ
ማንጠልጠል ይወዳል ፥ ጭንቁን እንደ ትሪ
የብሩሹ አጣጣል ፥ ቀለም ስብጥሩ
የመልእክቱ ምጥቀት ፥ ብራና ሚስጥሩ
ገለፃው......ውብቱ
ጨረሩ ....ሙቀቱ
ሺህ ግዜ ፥ እልፍ አመት
እኛን ቢገርመንም...
ቢያጅበንም ...ደርሶ
የሁለቴ ምጥ ነው
ዘመን የሚሻገር ፥ በቀለማት ርሶ
አየሽልኝ ውዴ....
እንዲህ ያለውን ሰው
ወሮታው ሲዘከር ስላንጠለጠለ
በምናቤ ጓዳ...
የማይከስም ምስልን...ራሴ ላስጠለለ
አፍቃሪነት ዳሩ...
ከጠቢብም በላይ ...ጥበብ እንዳዘለ
ምስክሬ ነፍሴ
ባገኘው ወረቀ....አንቺን እንደሳለ
ምን ይሆን መስፈርቱ
ማነው የሚረዳ...
አይኔ በከደነ ፥ ገፅታሽ ሲቀዳ
ምስልሽ ሲንቀራወዝ ...በህልሜ ሰሌዳ
በውኔም በወረቀት ፥ ሲብስ በግድግዳ
የብዙ ብዙን ምጥ....አዕላፈ ውልጃ
ከሁለት ግልግል...ካንድ ተኩል ውርጃ
ለማመዛዘኛ....ቢጠፋ ብልሀቱ
ተደብቄ ኖርኩኝ ፥ የመልክሽ ሎሬቱ ።
✍ አብርሀም_ተክሉ ( መርዕድ)
@Abrham_teklu
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈