Telegram Web Link
____ የምዕዳን ጀምበር ____
.......©ሲራክ
አንቺ ሁኚ ÷ ደማም ፣
እኔ ልሁን÷ አመዳም ፣
በፍቅርሽ ነው እንጂ ÷
በቃልሽ አልደማም ።
...............
@hutoffun
የልጅነት ወግ 😮 (2)
..................
" ተማሪዎች፡ በሩጫ ጎበዝ ማነው? "
" አየለ...አየለ...አየለ ነው ቲቸር! "
" አየለ የታለ? "
" አቤት ቲቸር! "
" ቤቴን ታውቀዋለህ? ከዮሴፍ ወረድ ብሎ "
" አዎ "
" በሩጫ ሄደህ፡ መነጽሬን አምጣልኝ ጎሽ! "
" ቀጥሎ ፈተና አለ ቲቸር "
" ልጅ አየለ"
" አቤት ቲቸር! "
" ሩጥ! "
መላላክም ማርክ ነበረው ያኔ።
🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣


ዮኒ ሚባል ጂኦግራፊ የዘለለው ልጅ ነበር።
" ኢትዮጵያን የሚያዋስኑ ሃገሮች እነማን ናቸው? "
ሲባል፡-
" አጠገቧ ያሉት ናቸዋ! "
" ጥራ! "
" በዛ በኩል ሱዳን..." በአገጩ እየጠቆመ.....
" አብሮ አደጎችህ ናቸውንዴ? ግሜ! "
" ይቅርታ ቲቸር፡ እነ ሱዳን "
" መግረፊያህን ይዘህ ና! "
መግረፊያውን ያመጣል፤ ማርክ ያገኛል
( አሁን ፈንጅ አምካኝ ሆኗል! )
....የጂኦግራፊ ችግር ያለበት ሰው ፈንጅ ሊያመክን?...🤦‍♀🤦‍♀🤦‍♀🤦‍♀🤦‍♀




ጂኦግራፊ አስተማሪያችን፡ ሃይለኛ ነበሩ! ብዙ ጺም ነበራቸው።
" ፍቅሬ! "
" አቤት! "
" ከመምህር ባዩ ዳስተር ተውሰህ አጽዳ! "
መምህር ባዩ ጋር እሄድና፡-
" ቲቸር ሞገስ ዳስተር ብለዋል! " ስላቸው
" እሱ ደግሞ ከልመና አይወጣምንዴ? " ብለው ይሰጡኛል።......ስደርስ
" አመጣህ? ጎሽ! ምን አለህ? "
" ከልመና አይወጣም ወይ ብለዋል " አልኩ!
...መልእክት በማድረስ ለመመስገን ነበር....
መሬቱ ግድግዳ እስኪመስለኝ ሲግናሌን በቦክስ አመሰቃቅለው ለቀቁኝ!
****
👊👊👊👊👊👊👊👊




መምህራን ሲያፈቅሩስ?

" ስማ! ባዩሽ የት ነው ሰፈሯ? "
ባዩሽ በአማርኛ ትምህርት፡ ሰቃይ ነበረች!
...ሁሌም አረፍተ ነገር እንዳነበበች ነበር.....
" አላውቅም ቲቸር! "
" እወቅ! "
አጠናሁና ተዘጋጀሁ!
" እህሳ! "
" አየር ጤና! "
በፈተና ማግስት፡ ማርክ ይሰጡኛል ስል፡
" የወላጅ ክትትል አይለየው! " ብለው እርፍ!
...😒እቺ ባዩሽ ገግማ ነው መሠለኝ
@hutoffun
....."መምጣትሽን አምናለሁ".......

መኖርሽን ለምጄ ሳጣሽ ይጨንቀኛል
ከጎኔ ሆነሽ ውለሽ ስቴጅ ይከፋኛል
መለየት ሲለየን ፍፁም ስትርቂ ካይኔ
በሀሣብ ሠመመን ያሳለፍሽዉን ከኔ
በትዝታ ዛሬውን ትቼ ከትላንት እቀዝፋለሁ
አብረሽኝ በሆንሽ ብዬ ፍፁም እተክዛለሁ
ትላንትናችን አልፎ ዛሬ ላይ ብንቆምም
ዛሬም በሀሳቤ ሁሌም ካንቺዉ ጋር ነኝ
ጠረንሽን ንፋሡ በሄድኩበት እያሣበኝ
ጨዋታ ሣቅሽን ልቤ እያስታወሠኝ
ትመጫለሽ ብዬ ዛሬም አስባለሁ
ከዛ ከቸትዝታ ባህ ር ከቀዳንበት
ከዛ በፍቅር ባህር ከሠመጥንበት
እኔና አንቺ ብቻ ከምናውቀው ቦታ
ዛሬ ትመጣ ይሆን
ነገ ትመጣ ይሆን
እያልኩ እጠብቃለሁ
መምጣትሽን ዛሬም አምናለሁ
መቅረትሽን ማሠብ ለኔ ህመሜ ነው
ትዝ ይልሻል ከዛ ትልቁ ዛፍ ያኖርነው
ላርቅሽ ላትርቂኝ ብለን ተማምለን
ለዛ በድን ዛፍ ያኖርነው ቃላችን
ዛሬ ግን የለሽም ያለነው እኔና ቃላችን
አሁንም ተስፋዬ ሙሉ ነዉ
መምጣትሽን ዛሬም እመኛለሁ



@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
!!፨ ፨ ተሰውረሽ ነበር ፨ ፨!!

ከግዙፏ ምድር ከሰዎች ጋጋታ፣
ከባህሩ ጥልቀት ከሰማይ ከፍታ።
ከአእዋፍት ጋራ በክንፍ በርሬ፣
ምድርን ሳስሣት በጥልቀት መርምሬ።

ከደረቅ ከየብሱ ወደ ባሕር ወድቄ፣
የሃሳቧን ፍቅሬን'' ለማግኘት ከጥልቁ ጠልቄ፣
ስፈልግሽ ነበር ተስፋሽን ሰንቄ።
ከባህር ፍጥረት ጋር ላገኝሽ ስጣጣር፣
አንቺ ግን የለሽም በሰውነት አካል ተሰውረሽ ነበር።

ከባህሩ ወጥቼ ወደ ግዙፍ ጫካ፣
ከዛፎቹ ሞገስ ከታላቁ ዋርካ።
ከቅንጣቷ ተክል ከትንሿ ሳር ስር፣
የሃሳቧ ፍቅሬን'' አንቺኑ ለማግኘት በምድር ላይ ስዞር፣
ላገኝሽ አልቻልኩም እመኚኝ የኔዋ ተሰውረሽ ነበር።

ከጫካውም ወጣው ወደ ፀሃይ ሃሩር፣
በክንፌ በርሬ ወደ አሸዋው ግግር።
ከበረሃው ሙቀት ነጥቄሽ ለማምለጥ፣
ስዝቅ ስቆፍር የአሸዋን ረመጥ።
የሃሳቧ ፍቅሬ'' ላገኝሽ ስለፋ ስበር ስሽከረከር፣
አሁንም ፍቅሬ ሆይ ተሰውረሽ ነበር ።

ምድርን ከባህሯ ከየብሷ አስሼ፣
ከጫካው በረሃ ሁሉን አዳርሼ።
የሃሳቧ ፍቅሬ'' አንቺኑ ፍለጋ ስሽከረከር በእግሬ፣
ከግዙፏ አለም በክንፍ በርሬ።
ፍጥረታትን ሁሉ ብጠይቅ እርዳታ፣
የት እንደምትገኝ የመኖሪያሽ ቦታ።
የአኗኗርሽ ዘዴ የሰውነት ተርታ፣
ስኬትና ሀዘንሽ ለቅሶና ደስታ።
አስቤ ነበረ አንቺኑ ለመማር እስከሞት ለመኖር፣
ግን እመኚኝ ውዴ ላገኝሽ አልቻልኩም ተሰውረሽ ነበር።

ባትሰወሪማ

ባትሰወሪማ ከፊቴ እያለሽ በቀናቶች ሁሉ፣
ውስጥሽን እንዳላይ ልቤ መከለሉ።
እንደምን አድርጎ ከቶ እንዴት ይሆናል፣
ይልቅስ ፍቅሬ ሆይ የሰው ሁሉ ፍጥረት ተሰውረሽ ነበር ቢሉ ይሻለናል።

ባትሰወሪማ
አንቺን አስተውሎ ማየት ሲችል ልቤ፣
ከአለም ፍጥረታት ሲያስስ ሲፈልግ ሀሳቤ።
እንዴት አላገኘሽ አንቺ አዚው እያለሽ፣
ይልቅስ ፍቅሬ ሆይ አይኔ ብቻ እንጂ ልቤ አንዳያይሽ ነበር ተሰውረሽ።

ግና.... ግና....
ያሁሉ መከራ ሁሉም አለፈና፣
በተስፋ መቁረጥ ውስጥ በከንቱ ጎዳና።
ፍቅሬን ስፈልግ ሲያስስ የነበረ፣
ስንተያይ ስንኖር ያልተቀራረበ።
ለካስ አንቺ ነበርሽ ተፈላጊዋ ሰው፣
ባይኔ እያየውሽ ልቤ የተጋረደው።
አሁን ድንገት ሲናድ የልቤ ግርዶሽ፣
ልቤ ውስት ተገኘ ተጽፎ ስምሽ።
እንኳንም አወኩሽ ሳያመልጠኝ ጊዜው፣
ልቤም ልብ አገኘ አብሮት የሚያኖረው፣
ውዴ እስከመጨረሻው እስከለተ ሞቴ አ።ፈ።ቅ።ር።ሻ።ለ።ው።

ግና እስከዛሬ አይኔ ሲመለከት ማስተዋሉን ትቶ፣
እያየሁሽ ስኖር ያላየሁሽ ከቶ።
ምን ይሆን ምክንያቱ ሳስብ ስመረምር፣
እንዲ ይላል ውስጤ በልቤ ሚዛን ላይ ተሰውረሽ ነበር።


ተፃፈ ፨ በ ተወልደ እንግዳው ፨
👉 @te_best 👈
👉 @te_best 👈



@hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈
ቀረሽ እንደዋዛ
•┈┈•✦•┈┈•
እንደ ድመቶቹ
የትም እንደሚያድሩት
እንደ ስልክ እንጨቶች
እንደ ዛፍ ሃረጎች
እንደ ቤት ክዳኖች
ብርድ አቆራመደኝ
ስጠብቅ ስጠብቅ
"ትመጫለሽ ብዬ ሳይ ማዶ ሳይ ማዶ
የልጅነት ዓይኔ ሙዋሙዋ እንደ በርዶ"
ትመጫለሽ ብዬ ደቂቃ ስ ቆጥር
ትመጫለሽ ብዬ ሰዓቱን ስቆጥር
ትመጫለሽ ብዬ ባዝን ባንጎራጉር
ትወጫለሽ ብዬ በበራፍሽ ብዞር
ብርድ አቆራመደኝ
የመንገድ መብራቶች አይተው አፌዙብኝ
ውርጩ ቀለደብኝ
ጨለማው ሳቀብኝ።
አለመምጣትሽን
አውቀዋል ያውቃሉ
መስኮቶች ጨልመው
ቤቶች ተቆልፈው
ከተማው ሲተኛ
አይተዋል ያያሉ
አለመምጣትሽን
አውቀዋል ያውቃሉ።
-------------------------------

©ገብረክርስቶስ ደስታ
@hutoffun
@hutoffun
@hutoffun
ተንስዑ _ለጸሎት
ያኔ.....ከቅዳሴዉ ሥፍራ ከጸሎቱ ቦታ
ሠዎች ነጭ ለብሰዉ ሲቆሙ በተርታ
ቄሱም ተንስዑ ሲል ልቤ ሲያመነታ
ተስዐለነ ለማለት አፌም አይፈታ።
ያኔ.....ቃጭሉ ሲቃጨል ዜማዉ ሲንቆረቆር
ደዉሉ ሲደወል ጌታን ለማመስገን ሁሉም ሲወዳደር
ካህኑም ሲቀድስ ተንስዑ ሲል ገና
ተሰጥኦ ይመልሳል ተስዐለነ ይላል ህዝቡ በየተራ
ከአርያም መንደር ከቅዱሱ ሥፍራ
ቅዱስ ቅዱስ ሲሉ ከመላእክት ጋር
እጣኑ ሲያርግ ዉዳሴዉ ሲሰማ
የኔ ልብ እዚያዉ ነዉ ከመላእክቱ ጋር አልሄደም ራማ ።
ያኔ.....ሁሉም በየተራ አክሊሉን ሲቀዳጅ
ጸሎቱ ሲሰማ ከእግዜር ከአምላኩ ደጅ
እመቤቴ ማርያም ጸሎቱን ስትሰማዉ
ፊቱ እንደ ፀሀይ ሲያበራ ለሚያየዉ
መልአክ ይመስላል እዚያ ሚያስቀድሰዉ
ጌታንዉን ለማምለክ ከሚንበረከከዉ
ከጽርሀ አርያም ልቡ ከደረሰዉ
ከዚያ ሁሉ ቅዱስ መስቀሉን በመሳል ልቡ ከሚያለቅሰዉ
እኔም ከዚያ አለዉ ከቶ ባለማፈር በመሀል ቆምያለዉ
በልቤ ሳልሰግድ በእግሬ እወድቃለሁ
የእጣኑን ሽታ በዉስጤ ሳይሰርግ እንዲሁ ምገዋለሁ ።
ዛሬ.....ከቅዳሴዉ ሥፍራ ከጸሎቱ ቦታ
መሔድ የለም አሉ ሁሌ ጠዋት ማታ
የለም የካህን ድምፅ የሚስረቀረቀዉ
ተንስዑ ለማለት አልቆመም ከቦታዉ
ህዝቡም የለም ከቶ ተስዓለነ አይል አይንበረከክም እንደድሮ መቶ
ቁርባን አይቀበል ቃጭልም አይሰማ
የለም የእጣን ጢሱ የለም ጎንበስ ቀና
መሐረነ ናፍቋል ቅዱስ ቅዱስ ማለት ከመላእክት ጋራ
ዛሬ ግን የኔ ልብ በጸጸት ይደማል
የካህኑን ተንስዑ ሁሌም ይናፍቃል
ምንም ድምፅ ሳይሰማ ተስዓለነ ማለት በጣም ይዳዳዋል
የእጣን ጢሱን ሽታ በልቡ ይምጋል
ያኔ ባለመስማት ያጠፋዉን ጊዜ በብርቱ ይረግማል
ተንስዑ ሚለዉን ቃል ደጋግሞ ይሰማል
የካህናቱን ሥርዓት በልቡ ይስለዋል
አሁንም ደጋግሞ በጸጸት ይደማል
ብቻ ይምጣ ይላል ደግሞ የዚያን ጊዜ
አንዴ ብቻ አይደለም ተስዓለነ እላለሁ እልፍ አእላፍ ጊዜ
አምላኬ እባክህ አምጣዉ ያንን ጊዜ
ካህኑም ደግሞ ይበል ደግሞ ደጋግሞ ይበል ተንስዑ ለጸሎት ተንስዑ ለቅዳሴ ።
🍂🍂🍂🍂
ተፃፈ በናርዶስ


@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
ልጠይቅሽ
---------------
ለትንታው ለቁርጠቱም
ለውጋቱም ለእንቅፋቱም
"እኔን!" እያልሽ እኔ እንድቆም
አንቺ ታመሽ እኔ ስድን
ብኩን ነፍሴን ሳደነድን
ልብ ያላልኩሽ ቀኔን ሳድን
እናታለም "እንዴት ነሽ ግን?"
-----------------------
© ሰለሞን ሳህለ
@hutoffun
ኢዛና የአስማትና የጥበብ መፃህፍት
የኢትዮጵያን የብራና የጥበብ መጻህፍትን በቻናላችን ለተለያዩ ጥያቄዎች @Ezana19 እኔን የምታገኙበት ገጽ ነው፡፡ የአባቶቻችንን ታላቅ ጥበብ በመመርመር እና በማጋራት የጥንቷን ታላቋንና ዘመናዊቷን ኢትዮጵያ እንፍጠር፡፡


ኀበ ሖርኩ ሑሪ ወኀበ ኀደርኩ ኅድሪ፡፡
ኀበ ነበርኩ ንበሪ፡፡
ማርያም ድንግል ዘተናገርኩ ሥመሪ፡፡
የማነ እዴኪ በላዕሌየ አንብሪ፡፡
እለ ይፃረሩኒ ተፃረሪ ወምክሮሙ ዘርዝሪ፡፡፡
https://www.tg-me.com/Ezanaethiopianasmat
አዝማሪና የውሃ ሙላት
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
አንድ ቀን አንድ ሰው ተነስቶ ሲሄድ፣
የወንዝ ውሃ ሞልቶ ደፍርሶ ሲወርድ፣
እዚያው እወንዙ ዳር እያለ ጎርደድ፤
መሰንቆ እየመታ ድምጡን አሳምሮ፣
አንድ አዝማሪ አገኘ ሲዘፍን አምርሮ።
ምነው አቶ አዝማሪ ምን ትሰራለህ?
ብሎ ቢጠይቀው ምን ሁን ተላለህ።
አላሻግር ብሎኝ የውሃ ሙላት፣
እያሞጋገስኩት በግጥም ብዛት፣
አባብለዋለሁ እስኪ ምናልባት፤
ልቡን አራርቶልኝ ቢያሻግረኝ ብዬ፣
'አሁን ገና ሞኝ ሆንህ ምነዋ ሰውዬ።
ነገሩስ ባልከፋ ውሃውን ማሞገስ፣
ግን እንደዚህ ፈጥኖ በችኮላ ሲፈስ።
አስተውለህ እየው አንተም ብትሆን ደግሞ፣
እንዴት መስማት ይቻል የሰው ነገር ቆሞ።
እስኪ ተመልከተው ይህ አወራረድ፣
ያልሰማው ሲመጣ የሰማው ሲሄድ፤
ድምጡን እያውካካ መገስገሱን ትቶ፣
ማን ይሰማኝ ብለህ ትደክማለህ ከቶ።
ተግሳፅም ለተግባር ካልሆነው አራሚ፣
መናገር ከንቱ ነው ካልተገኘ ሰሚ።
---------------------------

ታሪክና ምሳሌ
©ከበደ ሚካኤል
@hutoffun
Today is Her Highness's Birthday🥳🥳🥳🥳🤩🤩🤩
ሌሎች ተሠምተው ማይታወቁ የጂጂ ዘፈኖች ካላችሁ 👉@Mahiletaybot👈በዚህ ቦት አጋሩን🙏🙏🙏

@hutoffun
@Dawit7king
እናመሠግናለን🙏🙏🙏🙏
@hutoffun
@YTMMNSMH
እናመሠግናለን👍👍👍
@hutoffun
@abeluaa
እናመሠግናለን😌😌😌
ባክሽ ሰይጣን ሁኚ

ባክሽ ሴጣን ሁኚ፣
ደስታ የተለየው፣
ጨቅጫቃ ነዝናዛ፤
ለአያያዝ አይመች፣ ወልጋዳ ጠምዛዛ፣
አይመች ለፍቅር፣ እሾህ ቀናተኛ፣
ትህትና ያልተጠጋው፣ ለካፊ መገኛ፡፡
ባክሽ ሴጣን ሁኚ፣
ባክሽ ሲዖል ሁኚ፣
ነፍሴን አንገብግቢያት፣
አቃጥያት፣ ጥበሻት፡፡
መልአክ ከሆንሽማ፣
ችሮታሽ - ንፍገቴን፣
ሳቅሽ - ጭቅጭቄን፣
ፍቅርሽ - ጥላቻዬን፣
እምነትሽ - ዝሙቴን፣
ያሳብቅብኛል፤
ባክሽ ሴጣን ሁኚ፣ ለኔ እሱ ይሻለኛል።

© ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ
@hutoffun
@hutoffun
@hutoffun
(Santa_¥e)

እውነት እልሀለሁ
እውን አንተን መሳይ የዋህ ፍቅሩን ክዶ፣
የጠላህ እንደሆን ልቤ ሌላ ለምዶ😒
ምህረት ያሳጣው...
ለሰሚ ማይመች ሀያል ቅጣት ይቅጣው፣
ዘላለም አለሙን አፍቃሪ ያሳጣው😏

እውነት እልሀለሁ
አንተን የያዙ እጆች ሌላ ሰው ካቀፉ
ያለአንዳች ስስት ከአካላቴ ጎለው
ተነጥለው ይጥፉ፣
ነፍሴን የሚያስቷት የሚያጎድፏት ሁሉ
ላንተ ፍቅር ሲባል ተቆርጠው ይጣሉ😔

እውነት እልሀለሁ
በውጫው ውበት ነፍሴ ተመክታ🤦‍♀
ካንተ በላይ ቆንጆ...ሞልቷል ያልኩህ ለታ
ከስቼ ጠቋቁሬ እንደፅጌ🥀 ልርገፍ፣
በምንገድ ስታየኝ ሌላ ሴት መስዬህ
እያየኸኝ እለፍ😒

እውነት እልሀለሁ
የመጨረሻዬ ነህ....
ብዬ የገባሁትን ፅኑ ቃሌን ጥሼ🤔
የከዳሁህ እንደሁ ማተቤን በጥሼ፣
እሱ አይለመነኝ......የጠላሁህ ጊዜ፣
ጭንቄን ያበርክተው ይዋጠኝ ትካዜ፣

ግና ፍቅረይ...
አዲስ ቆንጆ ለምዶ ቀድሞ የሸፈተው
ያንተው ልብ እንደሆን😳ሌላዋን የሻተው

ተጨማሪ ወዷል ቢሉኝ🙄 እውነት እልሀለሁ
ደስታህ ደስታዬ ነው 😁 ቆሜ እድርሃለሁ።።
...
🙈🙈🙈

✌️✌️
#No_malekakes😌

@hutoffun
@hutoffun
@hutoffun
#ምንሼ #ነው #ጋሼ
ባለፈው ተዘርፈን ~ ስንደነባበር
አራዳ ነኝ ብለህ ~ ነግረኸን አልነበር
ታዲያስ ያራዳ ልጅ
እኛ ነጋ ስንሞት ~ ጠባ ስንገደል
እዛ እናንተ ግቢ ~ ሁሉ ፒስ ነው አይደል?
አረ ረ ረ …………… ሼ
ያራዳ ልጅ ብዬ ~ እኔ ራሴ አንግሼ
ጀለስካ ነው ብዬ ~ ዙፋኑን ለግሼ
ሞተን አለቅን እኮ ~ ምንሼ ነው ጋሼ
#አረ #ምንሼ #ነው
ያራዳ ልጅ ብለን ~ ፈቅደን እንድትመራን
ቆጥበን ቆጥበን
በጠራራ ፀሀይ ~ ጨቡ ምታሰራን ?
አረ ምንሼ ነው
ባላየ ላሽ እያልክ ~ ምታስጨፈልቀን
ካለፈ በኋላ
ፍሉካ ከች ብለህ ~ በወሬ ምትጨምቀን
#ምንሼ
ያራዳ ልጅ ሆነህ ~ ፋራን ምትወክለው
መቃብራችን ላይ ~ አበባ ም‘ተክለው
#ምንሸት #ነው
መለኛ ነህ ስንል ~ በተስፋ ትንበያ
አረ አታወዛግበን ~ አትሰክሰን በያ

አምነን እንዳንተኛ ~ አራዳ ነው ብለን
ወይ ከተነቃቃን ~ አልባንንም በለን

የአራዳ ልጅ ጭዌ ~ ላራዳ ባይጠፋም
እንዲህ መጨካከን ~ ጨርቆስን አይነፋም
===||===
ከሙሉቀን ሰ•

@hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈
#ሰያሚዋና_እጮኛዎቿ

ህዝብ ሀገር ያገዝፋል፣
ጦሱም ሆነ ዝናው ለራሷ ይተርፋል።

የሀገር ስያሜን በተመለከተ፣
ምላስ አጣጥሞ ለላንቃ እየጋተ፣

አዕምሮው አስቦ አንጀቱ እየራሰ፣
አቻ ፍቺ አዝሎ ቅኔ እየወረሰ፣

ግሩም ፍቺ አዘል ቃል፣
ስያሜ ያጸድቃል፣
ትርጉም ከርሷ ውጪ ሊያገኝ ቢንጠራራ ፍለጋው ያበቃል።

ሰያሚው ሲያሸልብ ለህዝብ ያሰራጫት፣
ስሟና ትርጉሟ ይቀራል ለሚያጫት፣
አንዱ ሊያፋፋት ነው ሌላኛው ሊያቀጫት።

ስም አውጪው አባቷ ሲለይ ከሕይወቷ፣
ያጫት እንዳታዝን በብቸኝነቷ፣
ያገባት ሊያረግድ ሊሆናት ኩራቷ፣
ወዳጇ ነው የሷ እስትንፋስ ጥራቷ።
ሌላው የኔ ቢጤ...
ሰያሚው አባቷ በደምና በላብ፣
ሌት ተቀን ከስቦ ያወራሳት ቀለብ፣
ሊቋደስ ሊበላ ልጅ መስሎ ሰራዊት፣
ህይወቱን አትርፎ አስበላት አራዊት።


ከሰው ልጅ ጎደና ወጥታ ብትመነምን፣ብትመስል ታናሿን፣
ያለ እድሜዋ አየች አንጋጣ 'ኩዮቿን፣
ለእርሱ ስትገብር ስትለግሰው ደሟን፣
የሚመልስ አጥታ አባት አያቶቿ ያወጡትን ስሟን።

ተጻፈ በአንዋር ዩሱፍ

@hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈
ሲኒማ

ህልምና ቅዠቱ ፥ በመሳ ተጭኖ ፥
......................የሚባንን ዜጋ
በሞላባት አገር ፥
ተስፋ አይኑ ሲጠፋ ፥ በሰቀቀን ቀጋ
አዳሜ ሲያነባ...........ሄዋን ስትላጋ
የለትለት መድረኩ ላንድ የሚዘረጋ
ድርሳንሽ ህሊና...መቼትሽ የኔ አልጋ ።

አብርሀም_ተክሉ

@hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈
#የእግዜር #በግ

አቤል በግ አወጣ
ቃየን ስንዴ አመጣ
ፈጣሪም መረጠ ~ ፈጣሪም ወደደ
የቃየንን ትቶ ~ የአቤልን ወሰደ
ቀናቶች ~ ከነፉ
ዘመናት ~ አለፉ
ሌላ ትውልድ መጣ ~ አብርሃም ተገኘ
ልጁን ለመሰዋት ~ ከልቡ ተመኘ
• • •
ጨለማን ከብርሀን ~ ሁን ብሎ የለየ
በአብርሀም እምነት ውስጥ ~ ይስሀቅን ስላየ
ታዛዡን ሊታደግ ~ አዳኝ እጁን ሰድዶ
ለወደደው ሰጠ ~ ከወደደው ወስዶ
===||===

ከሙሉቀን ሰ•


@hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈
ሌላ እንዴት ያፍቅርሽ

ፈጣሪ ውብ አርጎ ከነ ደም ግባትሽ፤
ከዝምታሽ እኩል እንዲናፈቅ ድምጽሽ፤
በፍቅር ህገ ደምብ ስንቱን ሀገር ገዛሽ።

ባንቺ ህግና ደምብ ባንቺ ንግስና ስር፣
ከጥንት ዠምሬ እተዳደር ነበር።

ያፈቀረ ይሙት ፣
ፍቅሩን ሀብል ሰርቶ አንጠልጥሎ ይገትት፣
የሚል ህግ እንዳለሽ ለምን ሳይካተት፣

ከደምቦችሽ መህል ደምብ ቁጥር ሰጥተሽ፣
አንቀፅ አብጅተሽ፣
አስገቢው በናትሽ፣
እኔ ላንቺ ሞቼ ሌላ እንዴት የፍቅርሽ።

ተጻፈ በአንዋር የሱፍ

@hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈
2025/07/05 06:32:15
Back to Top
HTML Embed Code: