Telegram Web Link
ሰባተኛ ሳምንት ኒቆዲሞስ ቻሌንጅ

1)ምሽታችንን ቃለ እግዚአብሔርን በማዳመጥ ማሳለፍ
2)ለሕማማት ሳምንት መዘጋጀት
3)ያልተረዳናቸውን ነገሮች መምህራንን መጠየቅ
4)ኪዳን ማድረስ
5)ለዚህ ሳምንት መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በኒቆዲሞስ ሰንበት ቅዳሴ የሚነበበውን ወንጌል ዮሐ. 3 :1 – 12፣ የሚነበቡትን መልዕክታት ሮሜ. 7:1 – 19 ፣
1ኛ ዮሐ 4፡ 18 - 21 ማጥናት እንዲሁም የሚሰበከውን ምስባክ መዝ 18፡3 – 4 መጸለይ
ከ እነዚህም የወደዳችሁትን ቃል ያጋሩን..
እንኳን ከዘጠኙ ዐበይት የጌታ በዓላት (ብሥራት ልደት ጥምቀት ደብረ ታቦር ሆሳዕና ስቅለት ትንሣኤ ዕርገትና ጰራቅሊጦስ) አንዱ ለሆነው ለሆሳዕና በዓል በሰላም አደረሳችሁ::
መርገመ በለስ
በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ” ማር ፲፩፥፲፬ በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል።
የትምህርት ቀን
በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪።
ምክረ አይሁድ
ረቡዕ ዕለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል። ሉቃ ፳፪፥፩-፮

የመልካም መዓዛ ቀን
ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በስምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ ማርያም እንተ ዕፍረት/ባለሽቶዋ ማርያም/ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ማቴ ፳፮፥፮-፯ የመዓዛ ቀን ይባላል።

የዕንባ ቀን
ባለሽቱዋ ሴት (ማርያም እንተ ዕፍረት) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አጥባለችና ማር ፲፬፥፱ የዕንባ ቀን ይባላል።
ሕጽበተ ኅሙስ
ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትሕትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል።

የምሥጢር ቀን
ከሰባቱ ምሥጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምሥጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምሥጢር ቀን ይባላል።
የስቅለት ዓርብ
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል።
2025/07/04 19:39:57
Back to Top
HTML Embed Code: