Telegram Web Link
ኢጃት ለሕፃናት ድጋፍ ለማድረግ ተጨማሪ የመግባቢያ ስምምነቶች ተፈራረመ።

| ጃንደረባው ሚዲያ | የካቲት 2017 ዓ.ም|

አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጠቅላይ ቤተ ክህነት የማኅበራት ማደራጃ መምሪያ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ከመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ፣ መንበረ ፓትርያርክ ቅ/ቅ ማርያም ገዳም እና ደብረ ገሊላ አማኑኤል ሰንበት ትምህርት ቤቶች ጋራ ለጋራ ሥራ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ::

በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ስር ካሉት 23 ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው ጃን ቂርቆስ ከሰኔ 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ከመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ እና ከገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ሰንበት ትምህርት ቤቶች ጋር በመተባበር ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው 100 ሕፃናት የገንዘብ፣ የአልባሳት፣ የህክምና፣ የስልጠና እና የመሳሰሉ ድጋፎችን ሲያደርግ ቆይቷል። የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማም የሕፃናቱ አካላዊ እድገት፣ ጤና፣ የአዕምሮ መጎልበት፣ መንፈሳዊ እድገት አንዲሁም ማኅበራዊ ግንኙነት መዳበር ነው፡፡

በእነዚህ ሁለት አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ላይ ፕሮጀክቱ የሕፃናቱን ሁለንተዊ እድገትን ከማስጠበቅ አኳያ አበረታች ውጤት ስለተገኘበት በያዝነው 2017 ዓ.ም. ደግሞ ተደራሽነቱን በማስፋት ከመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ፣ መንበረ ፓትርያርክ ቅ/ቅ ማርያም ገዳም እና ደብረ ገሊላ አማኑኤል ሰንበት ትምህርት ቤቶች ጋር በመተባበር ለ 230 ሕፃናት ለሶስት አመት የሚቆይ ድጋፍ ለማድረግ በኢትዮጵያዊው ጃንደረባው ትውልድ ማህበር እና በሰንበት ትምህርት ቤቶቹ መሀከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል።
የሳምንት ሦስት ምኩራብ ቻሌንጅ ከዕለታዊ የመንፈሳዊ መግባራት መከታተያ ጋር

1)ብዙ ጊዜ የምናጠፋበት የእጅ ስልካችን ውስጥ ያሉ ወደ ክርስቶስ እንዳንቀርብ የሚያደርጉ አላስፈላጊ የሆኑ ገጾችን : ዘፈኖችን ሌሎችም የማይጠቅሙ ፋይሎች: መተግበሪያዎች ጠርጎ ማስወገድ

2) ለአእምሮአችን እረፍት በምናገኝባት ቅድስት ቤተክርስቲያን በመገኘት የጽሞና ጊዜ ማሳለፍ

3)በምኩራብ ሰንበት የሚነበበውን ወንጌል ዮሐ 2:12-ፍጻሜው
እንዲሁም መልእክታቱን ቆላ 2:16-ፍጻሜው
ያዕ 2:14-ፍጻሜው ማስታወሻ በመያዝ ማጥናት

4)በዚህ ሳምንት ውዳሴ ዘአምላክ የተባለውን የ7ቱ ቀናትን ውብ ጸሎት መጸለይ

5) ወንድምን ማማትን (ሀሜትን) ማስወገድ

ይህ ሳምንታዊ ቻሌንጅ እንዴት እየጠቀማችሁ እንደሆነ ያጋሩን::
የቅድመ ጋብቻ ትምህርቱን ብቻ የምትፈልጉ በዚህ ሊንክ

https://forms.gle/3CdAefMd9SVsBvj68

የቅድመ ጋብቻ ትምህርቱንና የብዙኃን ጋብቻ ላይ መሳተፍ ለምትፈልጉ እጮኛሞች በዚህ ሊንክ

https://forms.gle/cFzxBNkYzro5cDNW7

ለበለጠ መረጃ
0922071777
+251111267883
ደውለው ይጠይቁ።
የትዳር ሕይወት ስንቅ እንዳልይዝ፤ ጋብቻዬንስ በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እንዳላደርግ የሚከለክለኝ ምንድን ነው?
ሳምንት 4 መጻጉዕ ቻሌንጅ

1.ለንስሐ መዘጋጀት(ከንስሐ አባታችን ጋር ለመገናኘት በቅድሚያ ከራሳችን ጋር በመሆን ለኑዛዜ መዘጋጀት)

2.በግል ወይም በቡድን በመሆን የታመሙትን: የሚረዳቸው ዘመድ የሌላቸውን ወገኖችን መጠየቅ

3)ቅርባችን በሚገኝ ጠበል ቦታ በመሔድ መጠመቅ/መጠጣት

4)በሐዘን/ጭንቀት ያሉትን በእግዚአብሔር ቃል ማጽናናት : ድካማቸውን ማገዝ

5)የበገና ዝማሬዎችን ማዳመጥ

6)ወንጌል ፡- ማር. 2 ፥ 1- 12
መልእክታት
ገላ. 6 ፥ 1– 9
ያዕ. 3 ፥ 14– 18

የሐዋ. 3 ፥ 12 - 16
መዝ. 40(41) ፥ 3 - 4
ሳምንት 5 ደብረዘይት ቻሌንጅ

1) ራሳችንን ፈትሸን: ንስሐ ገብተን : ወደ ንስሐ አባቶቻችን ቀርበን የተናዘዝን : የተሰጠንን ቀኖና የጨረስን እና "እግዚአብሔር ይፍታ" ተብለን የተዘጋጀን ከንስሐ አባታችን ጋር በመማከር ከቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ መቀበል


2)ራሳችንን ፈትሸን ለኑዛዜ የተዘጋጀን ወደ ንስሐ አባቶቻችን በመቅረብ ኑዛዜ መፈጸም : ቀኖና መቀበል

3)ክርስቶስ ዳግም ሊፈርድ ሲመጣ የሚጠይቀንን 6ቱ ቃላተ ወንጌልን መፈጸም ለዚህም በግላችን ወይም ከ6ቱ ቃላተ ወንጌል ጉዞ መሳተፍ

4)የታሰሩ ሰዎችን መጠየቅ

5)በደብረዘይት ሰንበት በቅዳሴ የሚነበበውን ወንጌል
*ማቴ 24:1-36
የሚሰበከውን ምስባክ መዝ 45:2-3
እንዲሁም የሚነበቡትን መልእክታት
*1ኛ ተሰ 4:13-18
*2ኛ ጴጥ 3:7:15 ማስታወሻ በመያዝ ማጥናት

6)በሰው ከመፍረድ መቆጠብ

7)በዚህ ጾም ምን እንዳሻሻልን:ምን እንደተጠቀምን ራሳችንን መመዘን

ስለዚህ፥እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችኹ፡ኑሩ፥የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና" -ማቴ 24:44
ሰባተኛ ሳምንት ኒቆዲሞስ ቻሌንጅ

1)ምሽታችንን ቃለ እግዚአብሔርን በማዳመጥ ማሳለፍ
2)ለሕማማት ሳምንት መዘጋጀት
3)ያልተረዳናቸውን ነገሮች መምህራንን መጠየቅ
4)ኪዳን ማድረስ
5)ለዚህ ሳምንት መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በኒቆዲሞስ ሰንበት ቅዳሴ የሚነበበውን ወንጌል ዮሐ. 3 :1 – 12፣ የሚነበቡትን መልዕክታት ሮሜ. 7:1 – 19 ፣
1ኛ ዮሐ 4፡ 18 - 21 ማጥናት እንዲሁም የሚሰበከውን ምስባክ መዝ 18፡3 – 4 መጸለይ
ከ እነዚህም የወደዳችሁትን ቃል ያጋሩን..
2025/07/01 21:12:35
Back to Top
HTML Embed Code: