Forwarded from || 𝙱𝚒𝚕𝚊𝚕 𝚏𝚊𝚛𝚒𝚜 𝚘𝚏𝚏𝚒𝚌𝚒𝚊𝚕 || (Bilal Faris)
ሰው እና ጫማ ካሳመሙህ
ልክህ አይደሉም ማለት ነው
የሰውን ልጅ መደገፍ ትተህ አላህን ተደገፍ ያኔ አልገፋህ ያለህ ተራራ እንደጉም ይተናል ላጣሀው ነገር ጠይቅ በምንም ጉዳይ ላይ ሁን አመስግን አላህ ስለሚጠላኝ ነው አትበል በመጥላት ቢሆን ፈተና ነብዩላሂ ዘከርያ በመጋዝ አይገዘገዙም የኛ ነብይ ጧዒፍ ላይ እንደዛ አይደበደቡም ወንድሜ ትንሽ ታገስ ትልቅ ድል ከመከራ ጋር ነው
@bilal_faris_official
Forwarded from habib
ስለ ቢድዐ ለሁለት መከፈል
ከኢብኑ ተይሚያህ
ለፍጡር ፈጣሪ እንዳለው ሁሉም የሚያውቀው ጉዳይ ነው ዐቂደቱ ነሰፊያ በዶክተር
● ለፍጡር ፈጣሪ እንዳለው ሁሉም የሚያቀው ጉዳይ ነው..!
.
➲ ዓቂደቱ ነሰፍያ ⓴
በዶክተር ሸይኽ አቡ-በክር ሱለይማን [አሏሕ ከሙሉ ቤተሰባቸው ጋ..! በአፊያ ያኑርልን]
.
ሸር ማድረግዎን እንዳይዘነጉ...!

ኪታቡን ለሚፈልግ...!
:
https://www.tg-me.com/DanaKnowledgeTable1/509
:
JOIN
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
ፍልስጤማዊያኖች

ሞትን ቅንጣት ሳትፈሩ ለሞት በመሽቀዳደም በአይሁዳዊያን ትገደላላችሁ ።
እንዴት እድለኛ ናችሁ።እጣችሁም ያስቀናል
ጠላቶቻችሁ እሳት ይዘው እንኳን ለናንተ ሞት ዕድል ነውና ፥ከምንም አትቆጥሩትም ።


ሸሒድነት ❤️ ሽልማት ነው።
ፕሮፋይል በማድረግ ላልደረሰው በማድረስ የዒልም መስፋፋት ሰበብ እንሁን🙏



✍️ምዝገባውን ለማከናወን ፦
http://www.tg-me.com/Assunnahislamicschool_bot


   ▾ ለበለጠ መረጃ እና ዝርዝር በቴሌግራም ቻናላችን ላይ ያገኛሉ።


@DaralHijrataynIslamicSchool
ሰበር አሳዛኝ ዜና ፦ በአዲስአበባ መሳለሚያ ሻንቅላ ወንዝ አካባቢ የሚገኘዉ ኑርጋ መስጂድ መንግሥት ለመንገድ ልማት ይፈለጋል በሚል የመንግሥት ፀጥታ አካላት በተገኙበት ህጋዊ ካርታ ያለዉ መስጂድ ፍፁም ኢ ፍትሐዊ በሆነ መልኩ መፍረሱ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል ፡፡ የአካባቢው ማህበረሰብ በህገወጡ ሱልጣን አማን ለሚመራዉ ለአዲስ አበባ መጅሊስ ሄደዉ ያመለከቱና ያሳወቁ ቢሆንም ሪያድ ጀማል የተባለ ግለሰብ ግን ምንም ማድረግ አንችልም ሲል እንደመለሰላቸዉም ከደረሰን መረጃ ለመረዳት ችለናል።

  በሌላ ዜና የአዲስአበባ መጅሊስ የሚቃወም ሰልፍ በአል አንሲ መስጂድ ተካሄደ ስድስት ኪሎ አካባቢ በሚገኘዉ አል አንሲ መስጂድ በቅርቡ ከህዝቡ እዉቅና ዉጪ በአዲስ አበባዉ ሱልጣን አማንና መሀመድ አባተ አማካይነት ለመስጂዱ ናዚርና አስተዳደር በማድረግ የወሰኑት ህገወጥ ዉሳኔ በዛሬው ዕለት ከጁምአ ሰላት በሗላ የመስጅዱ ተጠቃሚዎ ማህበረሰብ ተቃዉሞዎቹን በዚህ መልኩ አሰምተዋል።

የአዲስ አበባው ጠንካራው መጅሊስ በዚህ 3ትወር ውስጥ ብቻ የህዝበ ሙስሊሙን መብትና ጥቅም አሳልፎ እንደሰጠ እንዲሁም የመብት ተሟጋቾችን በማስፈራራትና በማሳሰር የሰራው ግፍና በደል ለታሪክ ይቀመጥ፡፡ ይህን ሁሉ ሲፈፀም ዝም ያለው ኡስታዝና አክቲቪስት  በመጅሊስ ሰበብ ሲጮህ የነበረው  ፍላጎቱ ምን እንደሆነ በዚህ አጭር ጊዜ ህዝበ ሙስሊሙ መረዳቱን መረጃ ሰጭችን ትዝብቱን በሚያሳዝን መልኩ ገልፆልናል።
በእነ ሙፍቲ ወቅት ቢሆን ኑሮ እንኳን መስጅድ ፈርሶ በሚናገሩት ንግግር እንኳ ቃላት እየተሰነጠቀ ምን ይባሉ እንደነበር አሏህ ይወቀው!!

SHARE  SHARE  SHARE ያድርጉ
LIKE LIKE LIKE LIKE በማድረግ የእርስወን ድርሻ ለሌሎች በማዳረስ ይወጡ


በቴሌግራም ይከታተሉን
https://www.tg-me.com/stop_wahababizm
#እኔ_ኡለሞቸን_ተቋሜን_መስጅዴን_የምጠብቀው_ጀግናው_የሙፍቲ_ትውልድ_ነኝ
#ነገ ኮቻ
የGC ተማሪዎች ፕሮግራም ዝግጅቱን አጠናቆ ታዳሚዎችን በመጠባበቅ ላይ ነው
ዱብ በሉልን
Forwarded from ሰሊ አለል ሀቢብ😘 Solelahu alyhi weselem
💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎#መታለፍ_የሌለበት_አንገብጋቢ_ትምህርት💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎

#ሙስሊም_ከሆናችሁ_ይሄንን_መልዕክት_በሚገባ_አንብቡት🌷🌷

⬅️وَذَكِّرْ فَإِنَّ الذِّكْرَىٰ تَنفَعُ الْمُؤْمِنِينَ➡️

📌📌ገሥጽም፤ ግሣጼ ምእመናንን ትጠቅማለችና፡፡📌📌  ዛሪያት

🖌#ለምንድን ነው  በመስጂድ ውስጥ  እየተኛን  በፓርቲዎች ላይ  ነቃ  የምንለው
🖌#ለምንድነው ከአላህ  ጋር ማውራት እየከበደን አሉባልታ  ወሬዎችን  ለማውራት  የሚቀለን
📖#ለምንድነው ለጌታችን የመፅሐፍ መልእክት (የቁርአን መልእክት)  ችላ ለማለት እየቀለለን  አስቀያሚ መልእክቶችን ለመመለስ  የሚቀለን
#አንተ ወይም #አንቺ  ይሄንን መልእክት ለጓደኞችህ(ሽ)  ታስተላልፈለህ  ወይስ  ችላ  ትለዋለህ
#አላህ_እንዲህ_ብሏል  "አንተ  እኔን ከጋደኞችህ  ፊት ብታስተባብለኝ እኔ አንተን  የትንሳኤ ቀን  አስተባብልሀለው (ነፍግሀለው)

📌#እያንዳንዱ_ሙስሊም_አሁኑኑ 📌

?"#አስተግፊሩላህ_ወአቱቡ_ኢለይህ"         #3 ጊዜ  ይበልና📍
 
🖊#ይህንን_መልእክት_በcontact_ላይ_ለሚገኙ_ሙስሊሞች_ያስተላልፉ

📌📌#ኢንሻአላህ  በትንሽ  ደይቃ ውስጥ በቢሊየን  የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ይሉት እና የአላህ ቁጣ  ይበርድልናል📌📌

📝#እስካሁን_ያለውን_በማንበብህ_ሽ_ያጣሀው_ሽው_ምንም_ነገር_የለም_ስለዚህ_ቀጣዩንም_አንብብ(ቢ)

#የአዛን ጥሪ  ስትሰማ(ሚ) ቶሎ ተነስተህ(ሽ) መልስ(ሽ) (ለሰላትም ተቻኮል(ይ))  የስልክህ(ሽ)ን ጥሪ  ስትሰማ(ሚ) ለማንሳት  እንደምትቻኮለው(ይው)🏃
#ቁርአንን  በተመስጦ  አንብብ(ቢ) የተላከልህን መልእክት እንደምታነበው(ቢው)
#አላህን ፍራ(ሪ) ሞትን እንደምትፈራው(ሪው)
#ሞትን አስታውስ(ሽ) ስምህን(ሽን)  እንደምታስታውሰው(ሽው)

#አንድ_ሰጋጅ_ምን_ያህል_ደይቃ_ነው_ለሰላት_የሚወስደው?

"#ፈጅር"        4-6 ደቂቃ
"#ዝሁር"        6-8  ደቂቃ
"#አስር"         6-8 ደቂቃ
"#መግሪብ"    5-7 ደቂቃ
"#ኢሻ"          7-10 ደቂቃ

👉በአጠቃላይ 28-39 ደቂቃ ከ24 ሰአት ውስጥ
👉እኛ ለአላህ ብለን እምንጠቀመው ሰአት  አለን?
👉80%  ሰዎች  #ይህንን_መልእክት አያስተላልፉም  አንተ  ወይም አንቺ ከሚልኩት  እንድትሆን(ኚ)  አመኛለው


       ➡️#የቂያማ_ምልክቶች⬅️

#ግብረ_ሰዶም
#ሰዎች_ስለሌሎች_አያት_ቅድመ_አያ_ክፋት_እና_ቂም_ማውራት
📍#ልብሶች አብዛኛውን  የሰውነት ክፍል የሚያሳዩ መሆናቸው
📍#በሰማይ ላይ ብዙም ከዋክብት አይኖሩም
📍#ትላልቅ ህንፃዎች መብዛት
📍#የደጃል መምጣት
📍#የኢማም አህመድ መምጣት
📍#የኢሳ አለይሂሰላም መውረድ
📍#የእጁጅ እና መእጁጅ መምጣት
📍#ፀሀይ በገባች መውጣት( የይቅርታ  በር በተዘጋ  ጊዜ)
📍#ከመሬት ውስጥ አንዲት  ፍጡር  መውጣት እና ትክክለኛ አማኞችላይ ምልክት ማድረጓ
📍#ለ40 ቀናት ጉም መነሳት  እና በዛምክንያትም እውነተኛ አማኞች ምንም እውቀትም ሆነ ስሜት ሳይሰማቸው መሞት
📍#ከባድ እሳት መነሳት በዛም ብዙ  ነገሮች  መውደም
📍#የካአባ መፍረስ
📍#ቁርአን ከሰውም ልብ  ከወረቀትላይ መነሳት
📍#የጡሩንባ  መነፋት  በመጀመርያው እንስሳዎች አና  ሰዎች መሞት
📍#በሁለተኛው ሲነፋ የአላህ   ፍጥረት በሙሉ  እንደገና  ይነሳሉ ለፍርድ በአረፈት  መሬት ላይ ይሰበሰባሉ።

#ፀሀይ_ወደ_ምድር_በጣም_ትቀርባለች

#️ነብዩ_ሙሀመድ_ሰለላሁ_ዐለይሂወሰም_እንዳሉት" ይህንን ዜና ለአንድ  ሰውያደረሰ (#ያስተላለፈ) በፍረዱ ቀን  ጀነት ላይ ቦታ ይዘጋጅለታል።

📝ይህንን መልእክት በስልካችሁ contact  ላይ ላሉ ሙስሊሞች በሙሉ ላኩ ይህን መልእክት ችላ ካልከው(ሽው) #የረሱልን_ንግግር አስታውሱ።

📝#ይህንን_መልእክት ለሌሎች አስተላልፍ(ፊ)

📌📌"#ላኢላሀ_ኢላ_አንተ_ሱብሀነከ_ኢኒ_ኩንቱ_ሚነዟሊሚን" 📌📌

➡️አላህን ከማምለክ ከሚዘናጉት አሏህ ይጠብቀን።

📝#ይህንን_መልእክት አንዳነበብክ/ሺ ለሁሉም በcontact  ላይ  ለሚገኝ ሙስሊም  አስተላልፍ(ፊ)

#️እባካችሁ_እንዳታቋርጡት

✏️#አላህ_ሁላችንንም_ወደሱ_ይመልሰን
ለኔው ሲል ነበር መቁሰል መድማቱ ዲንጋይ ማሰሩም ሲራብ አንጀቱ ይብላኝ ለደህኔው ለእንደኔ አይነቱ በዱንያ ቅባት ለወዛው ፊቱ
ዛሬ ሰኞ የረጀብ ወር የመጀመሪያው ቀን ነው💫

[በረጀብ ወር ከተከሰቱት መካከል ..]

★የተቡክ ዘመቻ በሂጅራ አቆጣጠር በ9 አመት በረጀብ ወር በ10ኛው ቀን ላይ ነበር የተካሄደው።

★የሐበሻው ንጉስ ነጃሺይ በሂጅራ አቆጣጠር በ9ነኛው አመት በረጀብ ወር ላይ ነበር ያረፉ። በመልእክተኛው ﷺ  ትዕዛዝ ሱሓባዎች ወደ ሐበሻ በተጓዙ ጊዜ ነጃሺይ መጠጊያ ሆነዋቸው ነበር። መልእክተኛው ﷺ ወደ እስልምና በጠሯቸውም ጊዜ ነጃሺይ እስልምናን በመቀበል ከደጋግ የአሏህ ባሪያዎችም ሆነዋል። ነጃሺይ ባረፉ ጊዜ  መልእክተኛው ﷺ በሳቸው ላይ ሶላተል غጋኢብ ሰግደዋል።

★ኸሊፋው ዑመር ኢብን አል-ዐዚዝ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) በሂጅራ አቆጣጠር በ101 አመት ላይ በረጀብ ወር በ39 አመታቸው ነበር ያረፉ። ዓሊም፣ወልይ፣ ተቂይ፣ዛሂድ ነበሩ። ከሰይዱና ሐሰን ኢብኑ ዐልይ በመቀጠል 6ተኛው ኺላፋ ነበሩ።

★በረጀብ 27ተኛው ለይል ነበር መልእክተኛው ﷺ የኢሰራእና ሚዕራጅ ጉዞ ያደረጉት።በዚህ ጉዟቸው በመካ ሀገር ከኡሙ ሀኒእ ቤት በመነሳት ወደ መስጅደል አቅሷ በመጓዝ ነቢያቶችን  በአጠቃላይ ኢማም ሆነው አሰግደዋል። ከዛም ወደ 7ቱ ሰማይ እና ከዛም በላይ በመሄድ እጅግ ድንቅ ነገሮችን በመመልከት ሶላትን ተቀብለው መጠዋል።

★ኢማሙ ሻፊዒይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ)  በሂጅራ አቆጣጠር በ204 አመት ላይ  በረጀብ ወር በ54 አመታቸው ነበር ያረፉ። ኢማምነታቸው የተስፋፋ እንዲሁም መዝሃባቸው እውቅናን ያገኘ ነበሩ።  ቲርሚዚይ በዘገቡት ሶሒሕ ሐዲስ  “የቁረይሽ ዓሊም ምድርን በእውቀት ይሞላል”የሚል መጧል፤ በሐዲሱም የተፈለጉት ኢማሙ ሻፊዒይ ናቸው።

#አሏህ_ሆይ! የረጀብ ወርን በረከት፣ የሻዕባን ወርን እዝነት፣የረመዷን ፆምን ምንዳ ወፍቀን! 🤲

:¨·.·¨: ❀
 `·. ሑሰይን የዐብደሪይ ወዳጅ
T.me/husseyn_y_abdery_wedaj
Forwarded from IkhläS TübÉ ( የሙፍቲ ትውልድ) (Abdi Ikhlas)
ከቱርክ የመሬት መንቀጥቀጥ ምን እንማራለን

1.ሳታስበው ወይም ሳታውቀው ሕይወትህ በሰከንድ ውስጥ ሊለወጥ ይችላል። ምንም ዓይነት ዋስትና የለህም

2. ያለ ምንም የገንዘብ ችግር ተረጋግተህ እየኖርክ በድንገት የዘካ ገንዘብ ተቀባይ ልትሆን ትችላለህ።

3. ህይወት በጣም አጭር ናት እንዳለመታደል ሆኖ ያለንበትን ህይወት ለሰከንድ አመስግነን አናቅም

4. ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር ቂም ይዘን ሌሊት እንተኛለን ጠዋት ምን እንደሚፈጠር በማናቅበት ሁኔታ ቱርክ ላይ ይህ ነው የተፈጠረው ወደ ንጋት ላይ ነበር የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው የደረሰው ነገ እነቃለሁ ብሎ በዚህ ሁኔታ የተኛ ስንቱ ይሆን

5. ብዙዎቹ ሟቾች የረመዳንን ወር አቅደው እና በጉጉት ሲጠባበቁ የነበሩ ይሆናሉ። ረመዳን እንደማይደርሱ ግን አያውቁም ነበር😢

አንተስ ነገ ለመኖርህ ምን ዋስትና አለህ ???

★★ዛሬን ባለንበት ሁኔታ ለአኼራ የሚጠቅመንን እንሰንቅ ኸይር ስራዎች እናብዛ ተውበት እናድርግ

#አላህ_ሆይ! ረመዳን ከሚደርሱት አድርገን ። የሞቱትን አንተው ማራቸው የተጎዱትንም አንተው ጠግናቸው 🤲

اللهم ردنا إليك رداً جميلاً. اللهم ردنا إليك وأنت راضٍ عنا
ጀማላቸው መጥቶ፡ ቀልቤን ተ‘መጠነው
በዓጀም እንዝርቴን፡ እስቲ ልወጥነው
የውዱ‘ሳት ላንቃ፡ ሆዴን አቃጠለው
ናፋቂው ሚሻለው ሙራዱን ማየት ነው
የሙራዱ ዓይነታ፡ እንደምነው ጦይባ።
ቀድ ኧም፝ ሸርቀን ወገርባ
.
አሏሁመ ሶልሊ ዓላ ሙሀመዴ
ሸምሱከ ጧሊዑ ፤ ፊ‘ነዋሂ ጦይባ
ቀድ ኧም፝ ሸርቀን ወገርባ
.
እንግዲህ ምን አለ ተነውሬ ብነጠል
በወስፋቹሁ ገመድ ቀልቤ ሲንጠለጠል
በወርያቹሁ ብራቅ ልቤ ሲጎነጠል
ምን ይተርፋችኋል ዘላለም ብቃጠል
ክፍሌን ግለጡልኝ በሐድራችሁ ልግባ
ቀድ ኧም፝ ሸርቀን ወገርባ
.
አሏሁመ ሶልሊ ዓላ ሙሀመዴ
ሸምሱከ ጧሊዑ ፤ ፊ‘ነዋሂ ጦይባ
ቀድ ኧም፝ ሸርቀን ወገርባ
.
ምንነው ያንን ጀማል እኔም ባስተውለው
መሃባው ለቀልቤ ደርሶ ታበሰለው
የመደዱን ግባት እያስተካከለው
ልቤን አቃጠለው ወስፋን ብኸይለው
ሰይፋ ተለተለው ቀልቤን እንደ ዱባ
ቀድ ኧም፝ ሸርቀን ወገርባ
.
አሏሁመ ሶልሊ ዓላ ሙሀመዴ
ሸምሱከ ጧሊዑ፤ ፊ‘ነዋሂ ጦይባ
ቀድ ኧም፝ ሸርቀን ወገርባ
.
ሰማይ ሲያጉረመርም፡ መደዱ እንደ ዝናብ
በክፍያም አይደል ፡ ሊያጎርፍ በጥጋብ
የሱ ቅልብተኛ ፡ የለበትም ራህብ
ጀዝቡ ይጎትታል ፡ ወዳጁን ለመሳብ
በከውኑ ይጮሃል ፡ የውዱ ለለባ
.
አሏሁመ ሶልሊ ዓላ ሙሀመዴ
ሸምሱከ ጧሊዑ ፤ ፊ‘ነዋሂ ጦይባ
ቀድ ኧም፝ ሸርቀን ወገርባ
.
ዘላለም ለቅሶ‘ነው ዳኢም እንጉርጉሩ
የወዳጁህ ደረት ፡ ባንቱ ተጎርጉሮ
የቀልብ እድምተኛ ፡ ጦይባ ላይ ጨፍሮ
አቤት! አቤት! ይላል ፡ ቆሞ ተደርድሮ
አንዳንዱ እዛ መሃል ይባላል ና ግባ
ቀድ ኧም፝ ሸርቀን ወገርባ
.
አሏሁመ ሶልሊ ዓላ ሙሀመዴ
ሸምሱከ ጧሊዑ ፤ ፊ‘ነዋሂ ጦይባ
ቀድ ኧም፝ ሸርቀን ወገርባ
.
የገባማ ጊዜ ፡ ሁሉም ይገለጣል
ያንን ጀማል ማየት ፡ ለዳኢም ይሰጣል
የኛ ቢጤ ደግሞ፡ ቆሞ ያዳምጣል
ተራ‘ኢስቲ‘መርቀው፡ በደጃፍ ይቀልጣል
ምን ይፈረድ ይሆን ?! ለሚስኪን ገገባ
ቀድ ኧም፝ ሸርቀን ወገርባ
.
አሏሁመ ሶልሊ ዓላ ሙሀመዴ
ሸምሱከ ጧሊዑ ፤ ፊ‘ነዋሂ ጦይባ
ቀድ ኧም፝ ሸርቀን ወገርባ
🍀 🍀 🍀
Forwarded from Muhib Menzuma😍 (life.of_muhammed😍)
#እንዴት ነሁ
ቢስሚላሂ ብዬ ለክፈተው ኡባቡን
ጥቂት ልነካካው እስኪ አህባቡን
እስኪ ልከምለት ቁስሉን የልቡን
መዲና ላስገባው ሩህ እና ቀልቡን
ያጉርፈው እንቡን እየናፈቀሆ

አዳምጠው የወስፉን የማማሩን ለዛ
ፀጉሩ ረዥም ነበር ከመሩ የበዛ
የመስል ነበረ በቅቤ የወዛ
ክርድድ አይደለም በጣም አይደል ለዛ
የሽታው መአዛ የራቀነው ሪው


ያየው እንዳወራን የመልኩን ኸበር
ይመስል እንደነበር ግንባሩ ጀንበር
ሀዒሻ መርፌ ጠፍቱዋት ጨለማ ነበር
በሱ ኑር ተገኘ ሲገባ ከበር
ስንቱ ባንቱ ፍቅር ናፍቆ ሞተልሁ

አፍንጫው ስልክልክ ቀጥ ያለ ተስሎ
በምን ይመስልሀል እሱንስ ማን መስሎ
ቢገኝም ተኛ ለይ አደምይ መስሎ
ሀቂቃ ገዳይ ነው ጉበትን አቁስሎ
ኸረ እንደው (አምሳያ መስሎ) ውዴ
ታጣልሁ


ቅንድቡን አዳምጠኝ ነፍቆቱ የስጠማል
ማማሩ ጥቁረቱ ትዝታው ያደማል
ጉንጉኑ እንደ ሀር ሙሉ ነው ይገጥማል
ያየው ሁሉ መልኩን ዳይም ይገረማል
ይሄን ጉድ ሲያሰማ እኛም ናፈቅነሆ

ካለየሁትማ ያንን ፊተ መላካም
በሌላ ጥማቴ በምንም አይረካም
በምድር ያለ ባር ብጠጣ ተመልካም
ዝለቆ ለዮት ሳይመጣብኝ ድካም
የሐያት በረካ ግታዬ አንቱ ነሆ


የንጉሶች መሪ የሁሉ አለቃ
ስምሆ የደመቀው ከ ፀሀይ ጨረቃ
ሁሊም ስል ዘከረሁ የ አላህ ሚስጥር እቃ
የከውኑ መሸሻ የሚስኪም ጠበቃ
ሚን ገርቢ ወሸረቃ ስንቱ አበደልሁ

በስምሁ ከብሬ ከፈይዱሁ ጠጥቼ
ከወንጀሌ ሁሉ ባንቱ ተጥራርቼ
በናፍቆት ሰክሬ ጌታዬ እስከመቼ
ጀማልሁ ዘልቆልኝ እንዳይሁ ጠርቼ
እንዳልሞት ፈንድቼ ጌታዬ አልጣሁ(አደራሁ)


ባጣው ሆድ ብሶኝ ነው የሚጎርፈው እንቤ
ታድያ እንዴት ልደሳ ርቆብኝ ቀለቤ
ምነው በደረስኩ ምን አለበት ጋልቤ
እኔስ ምን ለሁን ጠና መንገብገቤ
መች ይሁን አሳቤ ሞልቶ የማየሆ

ለበልሁ ሀያቴ ላንቱ ነው መኖሬ
ልበልሁ ቀለቤ ባንቱ ነው መክበሬ
መከታዬ ዋሴ ለለህዴ ለቀብሬ
ካላንቱ የለኝም ለሁለት አገሬ
ልሞት ነው ሰክሬ ውዴዋ እንዴት ነሁ


ካላየሁትማ ያንን ፊተ መልካም
በሌላ ጥማቴ በምንም አይረካም
በምድር ባህርን ብጠጣ ተመልካም
ዝለቁና ልዩህ ሳይመጣብኝ ድካም
የ ሀያት በረካም ጌታዬ አንቱ ነሁ

እንዴት ነው ብትለኝ የጉንጮቸ መልክ
እጅግ ድንበር አለፏል የማማሩ ለክ
እያለው ይመስላል ግታችን ማሊክ
መልክን ላድርግልህ አንተ እንደፈለክ
እነኳን ሰው መላይክ መቼ መሰለሆ

የሙስጠፋ ጀማል ስንቱን አስደለቀው
በምንባ እስደፈቀው አያንሰቀሰቀው
ገብቶ ኩላሊቱን እየጠበሰቀው
አጂብ ነው ሲሰራው ለጉድ ነው የራቀው
ሰንቱን ጉድ ኯረቀው ግተዬ ባረው

በፀጉሩ ስር ዘልቆ የግምባሩ ኑር
ሲጨላም የወጣች ይመስላል ጀምበር
ለጉድ አርጎ ከልቆ አላሁ አክበር
ሁሉም በርሱ አለቀ በርሱ ሲጀመር
ኑሩን ሙነወር አድርጎ ከልቆ


ለበልሁ ሀያቴ ላንቱ ነው መኖሬ
ልበልሁ ቀለቤ ባንቱ ነው መክበሬ
መከታዬ ዋሴ ለለህዴ ለቀብሬ
ካላንቱ የለኝም ለሁለት አገሬ
ልሞት ነው ሰክሬ ውዴዋ እንዴት ነሁ

እንዴት ነው እንዴት ነው
እንዴት ነው አረ እንዴት ነው ሙሀመድ
አምሳያው የጠፋው የከንፈሩ ማማር
ምላሱ ሲናገር የጣፈጠ እንደ ማር
ነው እና ሰያመጣው ከሱ ሁለ እነዲማር
የሰማውን ሁሉ አዝኖለት እንዲማር
የአለሙን ንጉስ ይገርማል ሻመሆ


ፂሙ መርዘሙጋ ብዛቱ የደመቀ
የጉንጮቹ ማማር ቅላቱ የራቀ
የመስላል ጨረቃ ሞልቶ የዘለቀ
አንደሱ አሳምሮ ሌላ መች ከለቀ
ሁሉን እያረቀ አላ ዘይ ነሆ
🥁👏🥁👏🥁👏🥁👏🥁👏🥁👏

በዚህ ቻናል👇
የ መንዙማ
Lyrics
Audio
Vedio
እንዲሁምየ ተላያዩ የሀድራ ላይ ቅጂዎችን ለማግኘት JOIN ይበሉ👇
ለመቀላቀል ይህን ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/muhib_7
https://www.tg-me.com/muhib_7
https://www.tg-me.com/muhib_7
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ሼር ሼር
Forwarded from IkhläS TübÉ ( የሙፍቲ ትውልድ) (Abdi Ikhlas)
በነፃ ሀጂ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበላቸው…

ያለፉት 15 አመታት ባጠራቀሙት ገንዘብ ያለፈው ረመዷን ላይ መዲና መስጂደ ነበዊ ላይ በባዶ እግራቸው ልብ በሚነካ ሁኔታ ሲሰናበቱ የሚያሳየው ቪዲዮ አለማችን ላይ እጅግ ቀልብ የሳበ ነበር። ይህ በእድሜ የገፉት ፓኪስታናዊ አባት ከፓኪስታን ከሳኡዲ ከቱርክ ሙሉ ወጫቸውን ሸፍነው ሀጅ ለማስደረግ በተለያየ አቅጣጫ ጥሪ እየቀረበላቸው እንደሚገኝ ሀረመይን ሸሪፈይን የተባለው ገፅ ዘግቧል።
[ የሚስጢር ባለቤት ሆይ! ሚስጢሩ ተጋለጠ!!]

*አስገራሚና አስተማሪ ታሪክ*

...ማሊክ ኢብኑ ዲናር (ረሒመሁሏህ) እንዲህ ይላል፡- በስራ ከተማ ገባሁ ...አንድ ቀን ሰዎች በታላቁ መስጂድ ከዙሁር ሶላት ጀምረው እስከ ዒሻእ ሶላት በኃላ ድረስ ተሰብስበው አሏህን ሲለምኑ ተመለከትኩ .... "ምን አጋጠማችሁ ?"  አልኳቸው።

እነሱም "ሰማይ ውሃ ከማውረድ ተቆጠበ፣ ወንዞቹም ደረቁ፣አሏህ ዝናብ እንዲያወርድልን ዱኣ እያደረግን ነው" አሉ።

ማሊክ እንዲህ ይላል፡- "ከዛም ሁሉም ወደ ቤታቸው ሄዱ፤ ለሀገሪቷ እንግዳ ስለነበርኩ በመስጅድ ውስጥ ተቀምጬ ቆዬሁ። በዚህ ሰኣት አንድ ጥቁር፣ አፍንጫው አጭር፣ ሆዱ የገፋ ፣ ከድህነቱ የተነሳ በአንድ ቁራጭ ልብስ  እፍረተ ገላውን የሸፈነ፣ ሌላኛውን ጫንቃው ላይ ያደረገ ሰውዬ ወደ መስጅድ ገብቶ ሁለት ረከዓ ሰገደ፤ ከዛም በመስጅዱ ውስጥ ሰው መኖሩን ለማረጋገጥ ግራ ቀኝ ዞረ... እኔ ያለሁበት ቦታ ትንሽ የተደበቀ ስለነበር ሳያዬኝ ቀርቶ ሰው የለም በማለት ወደ ቂብላ ዞሮ እጆቹን በማንሳት፡- "አሏህ ሆይ! ባሮችህን ስርኣት ለማስያዝ ዝናብ እንዳይወርድ አግደሃል፤ በባሮችህ ኃጢኣት ላይ ታጋሽና ይቅር ባይ የሆንከው ጌታ ሆይ!  ባሮችህን ውሃ ታጠጣቸው ዘንድ እማፅንሃለሁ!" አለ።

እጆቹን ከማውረዱ ሰማዩ ጨለመ፣ ደመናም ከየቦታው መጦ ከደመነ በኃላ ዝናቡ ዘነበ። ሰውዬው በጣም ስላስደነቀኝ ከመስጅድ ወጥቶ ወደ ቤቱ ሲሄደ ተከተልኩት... የተወሰነ ከተጓዘ በኃላ አንድ ቤት ውስጥ ገባ፤ ቤቱን በማግስቱ ለማግኘት ብዬ በሩ ላይ በጭቃ ምልክት አደረኩና ተመለስኩ።

በማግስቱ ፀሀይ ስትወጣ መንገዶቹን ተከትዬ ምልክት ያደረኩበትን ቤት ደረስኩ፤ ቤቱ የባሪያ መሸጫ ቤት ነበር ። የባሪያ ነጋዴውን "ባሪያ መግዛት እፈልጋለሁ" አልኩት። ነጋዴውም ረዢምና አጭር የተለያዩ ባሪያዎችን አሳዬኝ... የፈለኩትን ስላላገኘሁ "ከነዚህ ውጪ ሌላ አለህ?" አልኩት።

ባሪያ ነጋዴው፡- "ከነዚህ ውጭ የሚሸጥ ምንም የለኝም" አለ።
ማሊክ፦"ተስፋ ቆርጬ ከባሪያዎች ቤት ውጭ ተቀምጬ ባለሁበት ሰኣት ከበሩ አቅራቢያ ከእንጨት የተሰራ ጎጆ አየሁና..በዚህ ጎጆ ውስጥ ሰው አለ ወይ? " አልኩ።

ባሪያዎቹ " አንተ ባርያ መግዛት ነው የምትፈልገው በዚህ ውስጥ ያለው ባሪያ ግን ላንተ የሚገባ ባሪያ አይደለም አይመጥንህም" አሉ።

ማሊክ ፦"ላየው ፈልጋለሁ ይውጣ ብያቸው ባሪያው ከጎጆው ሲወጣ ያ! ትላንት በመስጅድ ውስጥ ሲሰግድ ያዩሁት ሰውዬ ነበር" አለ።

ማሊክ ለባሪያ ነጋዴው "ልገዛው እፈልጋለሁ" አለ።
ነጋዴው፦ " ይህ ባሪያ ለምንም ነገር ስለማይሆን ከሸጥኩልህ በኃላ ምናልባት አታሎ ነው የሸጠልኝ ብለህ ስሜን ታጠፋ ይሆናል!" አለ።
ማሊክ፦"እንዳሰብከው አይደለም ልገዛው ስለፈለኩ ነው" አለ....ነጋዴውም በርካሽ ዋጋ ሸጠለት ።

ማሊክ እንዲህ ይላል ፦ ይህን ባሪያ ወደ ቤቴ ወስጄው የተወሰነ ከተቀመጠ በኃላ አንገቱን ቀና አደረገና ጌታዬ ሆይ! ጥንካሬን ከፈለግክ ከኔ የሚበረታ አለ፣ ዝናን ከፈለክ ከኔ የበለጠ ቆንጆ አለ፣ ለስራ ከሆነ ደግሞ ከኔ የበለጠ አዋቂ አለና ለምን ገዛኸኝ?" አለ።

ማሊክ፦ "ትላንት የበስራ ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ ባጋጠማቸው ድርቅ ምክንያት በመስጅድ ውስጥ ከዙሁር ሶላት እስከ ዒሻእ ሶላት በኃላ ድረስ ዱኣ ሲያደርጉ ቆይተዋል...
ነገር ግን ልምናቸው ተቀባይት አላገኘም ነበር። አንተ ግን መስጅድ ገብተህ እጆችህን አንስተህ አሏህን በለመንክ ሰኣት ልመናህ ተቀባይነትን አግኝቶ ዝናብ ወረደ” አለው።

አገልጋዩ፡-" ምናልባት ሌላ ይሆናል! ምንስ አሳወቀህ ምናልባት ያየኸው ሌላ ሰው ሊሆን ይችላል” አለ።

ማሊክ፦"ይልቁንስ! አንተ ነህ" አልኩት፤ አገልጋዩም፡- "አውቀኸኛል?"አለ፤
ማሊክ፦"አዎ!" አለ፤
አገልጋዩ ፡- "እርግጠኛ ነህ? " አለ፤
ማሊክ "አዎ!"አለ።

ማሊክ እንዲህ ይላል፦ "በአሏህ እምላለሁ! ከዛ በኋላ ወደኔ አልተመለከተም፤ ወዲያውኑ ለአሏህ ሱጁድ ወረደ...ስግደቱንም አራዘመ፤ ወደሱ በደንብ ስቀርብ፦ «የሚስጢሩ ባለቤት ሆይ! ሚስጥሩ ተጋለጠ፣ ይህ ሚስጢር ተስፋፍቶ ህይወትን መቋቋም አልችልም።» ሲል ሰማሁ ... ብዙም ሳይቆይ ነፍሱ ከሱ ተለይታ ይችን ዓለም ተሰናበተ።" #ሱብሐን_አሏህ

አንዳንድ የአሏህ ባሮች መልካም ስራቸውንም ሆነ ከአሏህ ዘንድ ያላቸውን ደረጃ በዚህ ልክ ነበር የሚደብቁ፤ እኛስ በኛና በአሏህ መካከል የቱን ያህል የመልካም ስራ ሚስጢር አለን!።

አሏህ ሆይ! ነውራችን ሸፍንልን፣ ላንተ ያለንን ፍራቻ ከአለት የጠና አድርግልን!
አሏህ ሆይ! ከንፁህ፣ ጨዋ፣ ታማኝ፣ አንተን ሲቀርቡ ከሚጽናኑ፣ መልካም ስራቸው ላንተ ከሆኑ ባሮች ያድርገን!
አሏህ ሆይ! በፍላጎትህና ውሳኔህ ደስተኞች አድርገን፣ቃል በገባህላቸው የዘላለም ደስታ ከሚጠቃቀሙ ባሮችህ አድርገን!።

:¨·.·¨: ❀
 `·. ሑሰይን የዐብደሪይ ወዳጅ
T.me/husseyn_y_abdery_wedaj
Forwarded from 🤩Street🤩 Life🙏
As wr wb
If you love Allah: Send this 99names to 11 Muslims, your biggest problem will be solved In Sha Allah .
۞ الله ۞ الرحمن ۞ الرحيم ۞ الملك ۞ القدوس ۞ السلام ۞ المؤمن ۞ المهيمن ۞ العزيز ۞ الجبار ۞ المتكبر ۞ الخالق ۞ البارئ ۞ المصور ۞ الغفار ۞ القهار ۞ الوهاب ۞ الرزاق ۞ الفتاح ۞ العليم ۞ القابض ۞ الباسط ۞ الخافض ۞ الرافع ۞ المعز ۞ المذل ۞ السميع ۞ البصير ۞ الحكم ۞ العدل اللطيف ۞ الخبير ۞ الحليم ۞ العظيم ۞ الغفور ۞ الشكور ۞ العلي ۞ الكبير ۞ الحفيظ ۞ المقيت ۞ الحسيب ۞ الجليل ۞ الكريم ۞ الرقيب ۞ المجيب ۞ الواسع ۞ الحكيم ۞ الودود ۞ المجيد ۞ الباعث ۞ الشهيد ۞ الحق ۞ الوكيل ۞ القوي ۞ المتين ۞ الولي ۞ الحميد ۞ المحصي ۞ المبدئ ۞ المعيد ۞ المحيي ۞ المميت ۞ الحي ۞ القيوم ۞ الواجد ۞ الماجد ۞ الواحد ۞ الأحد ۞ الصمد ۞ القادر ۞ المقتدر ۞ المقدم ۞ المؤخر ۞ الأول ۞ الآخر ۞ الظاهر ۞ الباطن ۞ الوالي المتعالي ۞ البر ۞ التواب ۞ المنتقم ۞ العفو ۞ الرءوف ۞ مالك ۞ الملك ۞ ذو ۞ الجلال ۞ والإكرام ۞ المقسط ۞ الجامع ۞ الغني ۞ المغني ۞ المانع ۞ الضار ۞ النافع ۞ النور ۞ الهادي ۞ البديع ۞ الباقي ۞ الوارث ۞ الرشيد ۞ الصبوراللهم ارزق من
نشرها الفردوسئ الاعلى
አሏህን እምትወዱ ከሆነ ይሄን 99 የአሏህ ስም ለ11 ሰው ላኩ ይሄን ካረጋቹ ኢንሻ አሏህ ትልቁ ችግራቹ ይወገድላችዃል ።
2024/04/29 13:05:46
Back to Top
HTML Embed Code: