Telegram Web Link
የመጣላቸውን የመተንፈሻ አጋዥ የሕክምና ቁስ ይቅርብኝ ብለው አሳልፈው ለሌላ ወጣት የሰጡት የ72 ዓመቱ ጣሊያናዊው ካህን ጁሴፔ ቤራርዴሊ በኮሮና ክፉኛ ከተጠቁት የጣሊያን ከተማ አንዷ በሆነችው ካስኒኞ ውስጥ ካህን ነበሩ

በኮሮና ታምመው ሎቭር በተባለ ሆስፒታል ተኝተውም ነበር፡፡ ሕመሙ መተንፈስን አዳጋች ስለሚያደርገው በሕይወት ለመቆየት የመተንፈሻ አጋዥ መሳሪያ ግድ ይላል፡፡

የመተንፈሻ አጋዥ መሳሪያ ከፍተኛ እጥረት አለ፡፡
ካህኑ የሚያገለግሉበት ቤተ ክርስቲያን ምዕመን የካህኑን ሕይወት ለማዳን የመተንፈሻ አጋዥ መሳሪያውን ገዝቶ ለአባ ጁሴፔ ቤራርዴሊ ቢሰጣቸውም፣ እሳቸው ግን ለአንድ አይተውትም ለማያውቁት ወጣት ታማሚ አሳልፈው ሰጥተዋል የእሳቸው ሕይወት አልፏል

ምንጭ-BBC

@kinegroup
@kinegroup
ጠቃሚ መረጃ ሰለ ኮሮና (ኮቪድ 19)
..
(በጌትነት ተመስገን )
መጋቢት 22 ቀን 2012
ምሽት 5:30
....
☞ * መጋቢት 4 ቀን 2012 ዓ.ም
1. የ48 ዓመት የጃፓናዊ[ከብርኪናፋሶ]
..
☞ * መጋቢት 6 ቀን 2012 ዓ.ም
2. የ44 ዓመት ጃፓናዊ[ በንኪኪ]
3. የ47 ዓመት ጃፓናዊ [ በንኪኪ ]
4.የ42 ዓመት ኢትዮጵያዊ [ በንኪኪ]
..
☞ * መጋቢት 7 ቀን 2012 ዓ.ም
5. የ34 ዓመት ኢትዮጵያዊ [ከዱባይ ]
..
☞ * መጋቢት 8 ቀን 2012 ዓ.ም
6.የ59 ዓመት እንግሊዛዊት [ከዱባይ ]
..
☞ * መጋቢት 11 ቀን 2012 ዓ.ም
7.የ44 ዓመት ጃፓናዊ [ በንኪኪ]
8.የ85 ዓመት ኢትዮጵያዊ [ካልተገለጸ የውጭ ሀገር]
9.የ39 ዓመት ኦስትሪያዊ [ካልተገለጸ የውጭ ሀገር]
..
☞ * መጋቢት 13 ቀን 2012 ዓ.ም
10.የ28 ዓመት ኢትዮጵያዊ [ ቤልጂየም]
11.የ34 ዓመት ኢትዮጵያዊ [ከዱባይ ]
..
☞ * መጋቢት 15 ቀን 2012 ዓ.ም
12.የ34 ዓመት ኢትዮጵያዊ [ከዱባይ ]
..
☞ * መጋቢት 18 ቀን 2012 ዓ.ም
13.የ72 ዓመት ሞሪሸሳዊ [ ከኮንጎ ብራዛቪል]
14.የ61 ዓመት ኢትዮጵያዊ [ በንኪኪ]
15.የ28 ዓመት ኢትዮጵያዊ [ከእስራኤል]
..
☞ * መጋቢት 20 ቀን 2012 ዓ.ም
16.የ26 ዓመት ኢትዮጵያዊ [ ከካሜሮን ]
17.የ14 ዓመት ኢትዮጵያዊ [ በንኪኪ]
18.የ48 ዓመት ኢትዮጵያዊ [ በንኪኪ]
19.የ38 ዓመት ኢትዮጵያዊ [ከዱባይ ]
20.የ35 ዓመት ኢትዮጵያዊት [ከዱባይ]
..
☞ * መጋቢት 21ቀን 2012 ዓ.ም
21. የ37 ዓመት ኢትዮጵያዊ [ከአሜሪካ ]
22. የ32 ዓመት ኢትዮጵያዊት [ከዱባይ ]
..
☞ * መጋቢት 22 ቀን 2012 ዓ.ም
23.የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊ [ከዱባይ ]
24.የ36 ዓመት ኢትዮጵያዊ [ከዱባይ ]
25.የ60 ዓመት ኢትዮጵያዊ [ከፈረንሳይ ]
26.የ42 ዓመት ኢትዮጵያዊት [ከአውስትራሊያ ]
.......
በአጠቃላይ
# ሰባት ሰዎች በንኪኪ በቫይረሱ ተይዘዋል
# 19 ሰዎች ከውጭ ሀገር ቫይረሱን ይዘው ገብተዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ
ከዱባይ 9
ከአወስትራሊያ 2
ከፈረንሳይ 1
ከአሜሪካ 1
ከካሜሮን 1
ከኮንጎ ብራዛቪል 1
ከቤልጂየም 1
ከቡሩኪናፋሶ 1
ያልታወቁ የውጭ ሀገራት 2
ድምር ........................26
...
# 19 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ
# ሰባቱ ደግሞ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ናቸው ከነዚህ ውስጥ
ጃፖናዊያን 4
እንግሊዛዊት 1
ኦስትሪያዊ 1
ሞሪሸሳዊ 1 ናቸው፡፡
...
# ሁለቱ ጃፖናዊያን ለተሻለ ህክምና ወደ ጃፖን አምርተዋል፡፡
# በለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ያሉ ሃያ ሁለት ታማሚዎች ይገኛሉ፡፡
#ሁለት ታማሚዎች በጽኑ ህሙማን ህክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው
ይገኛል፡፡
#ሁለት ታማሚዎች ሙሉ በሙሉ ከበሽታው አገግመዋል፡፡
.....
በኢትዮጵያ በኮሮና (ኮቪድ 19)ቫይረስ የተገኙባቸው ከተሞች
....
1.አዲስ አበባ 19
2.አዳማ(ኦሮሚያ ክልል) 3
3.ባህርዳር አማራ ክልል) 1
4.አዲስ ቅዳም (አማራ ክልል) 1
5.ድሬዳዋ 1
ድምር ............................ 26
.....
የኢትዮጵያ አጎራባቾች ሀገራት በኮሮና (ኮቪድ 19 )ቫይረስ የተያዙ የሰዎች ቁጥር መረጃ
....
1.ኬንያ 59
2.ጂቡቲ 30
3.ኤርትራ 15
4.ሱዳን 7
5.ሶማሊያ 3
6.ደብቡ ሱዳን 0
#ኢትዮጵያ 26
ድምር...............140
.....
ምንጭ
Worldometer
Ministry of Health,Ethiopia
መቀመጫውን በአሜሪካ ቨርዲንያ ያደረገው አለም አቀፍ ፖሊሲዎችና የፖለቲካ ትንታኔ አቅራቢ የሆነው politico የተሰኘው የዜና ምንጭ በኢትዮጲያ አሁን ያለው የህዝብ ቸልተኝነት በዚሁ ከቀጠለ ከ28 ሚሊዮን ህዝብ በላይ በኮሮና ቫይረስ ሊጠቃ ይችላል ይለናል፡፡
እኔም እላለሁ በእናንተ ቢሆን አንድም ቀን አናድርም ነበረ እያልኩ ለሀገሬ ህዝብ ደግሞ እባካችሁ እንደተባለው ቸልተኝነት ዋጋ እንዲያስከፍለን የምንባለውን ነገር እንተግብር፡፡
#ጥንቃቄ_ይደረግ...! አስቸኳይ ስለሆነም ለፈጣሪ ብላችሁ #ሼር_ሼር_ሼር አድርጉት
እባካችሁ እባካችሁ ....ጥንቃቄ ይደረግ
ኮሮናን ለመከላከል በሚል አልኮል የተቀባ እጅ እሳት ያለበት አካባቢ መገኘቱ አደገኛ ነው።
ከላይ በምስሉ ላይ የምትመለከቷት እህታችን ኮሮናን ለመከላከል በሚል አልኮል የተቀባ እጇን ባለማወቅ እሳት አካባቢ በማስጠጋቷ ጉዳት ደርሶባታልና እባካችሁ ላልሰማ አሰሙ ጥንቃቄም አድርጉ!
ዶናልድ ትራምፕ ለዶክተር ቴድሮስ ምላሽ ሰጡ!

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም ላይ የከፈቱትን የቃላት ጦርነት ቀጥለውበታል።ዶ/ር ቴድሮስ ትናንት "ጤናን ወደ ፖለቲካ አንጠምዝዘው" ማለታቸውን ተከትሎ ትራምፕ ዋይት ሐውስ ውስጥ በሚካሄደው ዕለታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ምላሽ ሰጥተዋል።

ዶክተር ቴድሮስ "ፖለቲካውን ትተን ወረርሽኙን ለማቆም ካልሰራን ሬሳ ሳጥን ማብዛት ነው" ስለማለታቸው ምላሽ የሰጡት ትራምፕ…"ምን ማለታቸው ነው ተጨማሪ ሬሳ ሳጥን ሲሉ…መጀመርያ እሱ (ዶ/ር ቴድሮስ) አገለግለዋለሁ ለሚለው ሕዝብ ኃላፊነቱን መወጣት ነበረበት።"

"ሁሉም ሥራው ቻይናን መሠረት ያደረገ ነው፤ ድንበር አትዝጉ፣ ከሰው ወደ ሰው አይተላለፍም ሲል ነበረ፤ ድንበር አትዝጋ ቢለኝም እኔ ግን ዘግቻለሁ…(ከዓለም ጤና ድርጅት በተቃራኒው ስለሄድን ነው ሰው ማዳን የቻልነው)" ብለዋል ትራምፕ። ትራምፕ ለዓለም ጤና ድርጅት የሚያዋጡትን 400 ሚሊዮን ዶላር፣ ቻይና ከምትሰጠው 40 ሚሊዮን ዶላር ካወዳደሩ በኋላ ይህንን ፈንድ የመስጠቱን ጉዳይ እንደሚያጤኑት ተናግረዋል።በተመሳሳይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ማይክ ፖምፔዎ "ለዓለም ጤና ድርጅት የምንሰጠውን ገንዘብ እናጤነዋለን" ብለዋል ዛሬ፡፡

Via BBC
@kinegroup
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንትና የወቅት የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሲሪል ራማፎሳ የአለም አቀፉን ጤና ድርጅት ጄኔራል ዳይሬክተር ዶከተር ቴድሮስ አድሃኖምን እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት ጄኔራል ዳይሬክተር ቴድሮስ አድኃኖም የኮሮናቫይረስ ለመቆጣጠር ያደረጉት ጥረትን በከፍተኛ ሁኔታ ማውገዛቸውን ተከትሎ ነው ራማፎሳ መግለጫውን የሰጡት።

በትናንትናው እለት ባወጡት መግለጫ የአፍሪካ ህብረትም ሆነ እሳቸው ከዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም ጎን እንደሚቆሙና የቫይረሱን መዛመት ለመቆጣጠር አለም አቀፋዊ ህብረት እንደሚያስፈልግ አፅንኦት ሰጥተዋል።

Via:- BBC - Getty Images
@kinegroup
ቻይና ውሻን እንደሚበላ ከብት ሳይሆን እንደቤት እንሰሳ የሚያይ ረቂቅ ህግ አዘጋጅታለች

ዉሻ እንደከብት ታርዶ የሚበላባት ቻይና አዲስ ህግ እያረቀቀች ሲሆን ይሄም ህዝቦቿ ውሻን እንደቤት እንሰሳ እንዲያዩ እንጂ አርደው ለምግብነት እንዳያውሏቸው ያዛል ሲል ስካይ ኒውስ ዘግቧል።

Via Tesfaye Getnet
@kinegroup
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የመጀመሪያዋ ሰለባ የሆኑት የ60 ዓመት ኢትዮጵያዊት እናት የቀብር ስነ ስርዓት በድጋሚ ተከናወነ።

የመጀመሪያው የቀብር ስነ ስርዓት ያለ ሟች ቤተሰብ እውቅና እንዲከናወን አድርገዋል የተባሉ አንድ የአዲስ አበባ ከተማ የየካ ክፍለ ከተማ ኃላፊም ከስራቸው መባረራቸውን ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። 

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ባለፈው እሁድ መጋቢት 27፤ 2012 ህይወታቸው ያለፈው ኢትዮጵያዊት እናት የመጀመሪያ የቀብር ስነ ስርዓት የተፈጸመው የዕለቱ ዕለት፣ ምሽት ሶስት ሰዓት ገደማ፣ በቀጨኔ የመቃብር ስፍራ ነበር።

በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ እንዲገኙ ያልተደረጉት ቤተሰቦቻቸው ባቀረቡት ቅሬታ የሟች አስክሬን በነጋታው 10 ሰዓት ገደማ ከተቀበረበት ተቆፍሮ ወጥቶ፤ ከሁለት ሰዓት በኋላ በለቡ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በድጋሚ መቀበሩን ጉዳዩን በቅርበት የተከታተሉ የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ምንጮች ገልጸዋል። 

ተጨማሪ ለማንበብ ⬇️

https://bit.ly/2yK5KsI
የታማሚዎቹ ሁኔታ :-

ታማሚ 1 :- እድሜ 33 : ዜግነት ኢትዮጵያ ሴት ስትሆን ከአሜሪካ የመጣች ናት በለይቶ ማቆያ ያለች

ታማሚ 2 :- እድሜ 30 : ዜግነት ኢትዮጵያ ሴት ስትሆን ከዱባይ የመጣች ናት በለይቶ ማቆያ ያለች

ታማሚ 3 :- እድሜ 29 : ዜግነት ኢትዮጵያ ወንድ ሲሆን ከዱባይ የመጣ ነው በለይቶ ማቆያ ያለች

ታማሚ 4 :-እድሜ 42 : ዜግነት ኢትዮጵያ የጉዞ ታሪክ የለውም
@kinegroup
ተመስገን 10 ሰው አገግሟል

በኢትዮጵያ ተጨማሪ ስድስት ግለሰቦች ከኮሮና ቫይረስ አገግመዋል።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 10 ደርሷል።
@kinegroup
"የኮሮና ቫይረስን ለመመከት" ከ300 ሺ በላይ አባላቱን ማሰማራቱን የብልጽግና ፓርቲ አስታወቀ።

@kinegroup
በአዲስ አበባ 1200 የሚጠጉ የምግብ ባንኮች ተቋቁመዋል።

የምግብ ባንኮቹ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ችግር የሚገጥማቸው ዜጎችን ለመደገፍ ነው ብለዋል ኢ/ር ታከለ ኡማ።
ኢ/ር ታከለ በመስጠት ላይ ባሉት መግለጫቸው ነዋሪዎች በየአካባቢው በተዘጋጁት የምግብ ባንኮች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
በአዲስ አበባ 1200 የሚጠጉ የምግብ ባንኮች ተቋቁሙ።
የምግብ ባንኮቹ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ችግር የሚገጥማቸው ዜጎችን ለመደገፍ ነው ብለዋል ኢ/ር ታከለ ኡማ።
ከዚህ በተጨማሪም በከተማዋ የቤት ለቤት የኮሮና ቫይረስ ልየታ እንደሚደረግ ተናግረዋል።
የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በልየታው ላይ የሚሳተፉ ይሆናል።
መደበኛ ትምህርት መቋረጡን ተከትሎ ተማሪዎች በቤታቸው ሆነው በቴሌቪዥን እንዲከታተሉ እንደሚደረግ የተናገሩት ኢ/ር ታከለ ሂደቱ አሳታፊና ሳቢ እንደሚሆን ተናግረዋል።
በንግድ ላይ የተሰማሩ ዜጎች የገጠማቸውን ችግር አስመልክቶ አስተዳደሩ መፍትሄዎችን እያመቻቸ እንደሆነና የኮንዶሚኒየም ቤቶች ወርሀዊ ክፍያ እፎይታ እንዲኖረው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ እንደሚገኝ ኢ/ር ታከለ ገልፀዋል።
በተጨማሪም ከቫይረሱ መከሰት ጋር ተያይዞ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር የሚደረገው ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደቀጠለ ኢ/ር ታከለ ኡማ በመግለጫቸው አንስተዋል።

Via mayor office of Addis Ababa
@kinegroup
የ75 አመቱ የኡጋንዳ ፕሬዝደንት ዩዌሪ ካጉታ ሙሴቪኒ "ውጪ ስፖርት መስራት አቁሙ፣ ፖሊሶቻችን ዱላ ስለሚወዱ ሊመቷችሁ ይችላሉ፣ ቤት ውስጥ እንደኔ እንቅስቃሴ አድርጉ" ብለው ህዝባቸውን ሰሞኑን ሲመክሩ ቆይተው ይችን ፎቶ ዛሬ ለጥፈዋል።

@kinegroup
‼️ #አዎጁ_ክልከላን_በሚመለከት ‼️

ማንኛውም ሃይማኖታዊ ይሁን ፖለቲካዊ ስብሰባዎች፣ እድር፣ ደቦ፣ እቁብና ሌሎችም ከ4 ሰው በላይ ስብሰባዎች ክልክል ናቸው።

ከአራት ሰዎችም ቢሆኑ ሁለት የአዋቂ ሰው እርምጃ የጠበቀ መሆን እንዳለበት አቃቤ ህጓ አብራርተዋል።

ቀብርና ሌሎች አስፈላጊ ጉዳዮች ሲኖሩ ግን እየታዩ ሊፈቀዱ የሚችሉበት አሰራር መኖሩን ጠቁመዋል።

ታራሚዎች ከጠበቆቻቸው ጋር አስፈላጊው ጥንቃቄ ተደርጎ እንዲገናኙ የሚፈቀድ ቢሆንም ጥየቃ ለሚሄዱ ሰዎች የማይፈቀድ መሆኑ ተገልጿል።

በፖሊስ የተያዙ እስረኞችንም ስንቅ ከማቀበል በስተቀር መገናኘት የተከለከለ መሆኑን አስረድትዋል።

በድንበር አካባቢ ከካርጎ፣ የደረቅና ፈሳሽ ጭነት አገልግሎቶች በስተቀር ሌሎች እንቅስቃሴዎች ዝግ ተደርገዋል።

የቤት ተከራዮች በራሳቸው ፍላጎት ካልወጡ በስተቀር ማስውጣትና ኪራይም መጨመር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተከልክሏል።

ሰራተኞችን መቀነስና የስራ ቅጥር ውል ማቋረጥም መከልከሉን ወይዘሮ አዳነች አብራርትዋል።

በዚህ ደንብ መሰረት ተማሪዎችና መምህራን በኦን ላይን ካልሆነ በአካል እንዲገናኙ አይፈቀድም።

ስፖርታዊ ጨዋታዎች፣ የህፃናትም ይሁን የሌሎች መጫወቻ ስፍራዎች እንዲሁም የእጅ መጨባበጥ ሰላምታ የተከለከለ መሆኑን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በትራንስፖርት ዘርፍም አገር አቋራጭ ካለው ወንበር ከ50 በመቶ በላይ ተሳፋሪ መጫን የተከለከለ ነው፡፡

Via FBC
@kinegroup
@kinegroup
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማስፈፀሚያ ደንብ ይፋ ሆነ

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈፀሚያ ደንብን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ይፋ አደረገ።

በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣው ረቂቅ አዋጅ ትናንት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፅጽደቁ ይታወቃል።

የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የአዋጁን ማስፈፀሚያ ደንብ አጠቃላይ ይዘት በሚመለከት ዛሬ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በህገ መንግስቱ አንቀፅ 94 ንኡስ ቁጥር 4 መሰረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈፀሚያ ደንብ ማውጣት እንዳለበት ይደነግጋል።

በዚህም መሰረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያወጣውን ማስፈፀሚያ ደንብ አጠቃላይ ዝርዝር በሚመለከት ወይዘሮ አዳነች አብራርተዋል።

ማስፈፀሚያ ደንቡ አጠቃላይ አራት ዋና ዋና ከፍሎች ያሉት ሲሆን ይሄውም ክልከላን የሚያስቀምጥ፣ ግደታዎችን የሚጥል፣ የአስፈፃሚ አካላትን ክንውን እንዲሁም ልዩ ልዩ ድንጋጌዎችን የያዘ መሆኑ ተጠቅሷል።

ክልከላን በሚመለከት ማንኛውም ሃይማኖታዊ ይሁን ፖለቲካዊ ስብሰባዎች፣ እድር፣ ደቦ፣ እቁብና ሌሎችም ከ4 ሰው በላይ ስብሰባዎች ክልክል ናቸው።

አራት ሰዎችም ቢሆኑ ሁለት የአዋቂ ሰው እርምጃ የጠበቀ መሆን እንዳለበት አቃቤ ህጓ አብራርተዋል።

ቀብርና ሌሎች አስፈላጊ ጉዳዮች ሲኖሩ ግን እየታዩ ሊፈቀዱ የሚችሉበት አሰራር መኖሩን ጠቁመዋል።

ታራሚዎች ከጠበቆቻቸው ጋር አስፈላጊው ጥንቃቄ ተደርጎ እንዲገናኙ የሚፈቀድ ቢሆንም ጥየቃ ለሚሄዱ ሰዎች የማይፈቀድ መሆኑ ተገልጿል።

በፖሊስ የተያዙ እስረኞችንም ስንቅ ከማቀበል በስተቀር መገናኘት የተከለከለ መሆኑን አስረድተዋል።

በድንበር አካባቢ ከካርጎ፣ የደረቅና ፈሳሽ ጭነት አገልግሎቶች በስተቀር ሌሎች እንቅስቃሴዎች ዝግ ተደርገዋል።

የቤት ተከራዮች በራሳቸው ፍላጎት ካልወጡ በስተቀር ማስወጣትና ኪራይም መጨመር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተከልክሏል።

ሰራተኞችን መቀነስና የስራ ቅጥር ውል ማቋረጥም መከልከሉን ወይዘሮ አዳነች አብራርተዋል።

በዚህ ደንብ መሰረት ተማሪዎችና መምህራን በኦን ላይን ካልሆነ በአካል እንዲገናኙ አይፈቀድም።

ስፖርታዊ ጨዋታዎች፣ የህፃናትም ይሁን የሌሎች መጫወቻ ስፍራዎች እንዲሁም የእጅ መጨባበጥ ሰላምታ የተከለከለ ነው።

በትራንስፖርት ዘርፍም አገር አቋራጭ ካለው ወንበር ከ50 በመቶ በላይ ተሳፋሪ መጫን የተከለከለ ነው፡፡

ኢዜአ

@kinegroup
በአለም ላይ እስካሁን ከኮሮና ወይም Covid 19 የዳነ ሰው 390,598 መሆኑን ቢቢሲ ዘገበ
2025/07/13 21:01:50
Back to Top
HTML Embed Code: