Telegram Web Link
Forwarded from ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 (ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ)
🤗የመልካም ስራችሁን ውጤት ተመልከቱ ለጥምቀት የገዛችሁት ቲሸርት እዚህ ላይ ውሏል እግዚአብሔር ይመስገን


አሁንም ማገዝ የምትፈልጉ

1000261754987
ኬንቾ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን
ብላችሁ ማስገባት ትችላላችሁ።
2👍2
Forwarded from ማራናታ ᴘʀᴏⓂᴏᴛɪᴏɴ
🙏 በማርያም ይሄን ቻናል ሳታዩ እንዳታልፉት JOIN የምትለውን ብቻ ይንኳት።🙏
9👍3
Forwarded from ማራናታ ᴘʀᴏⓂᴏᴛɪᴏɴ
ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን

@BiniGirmachew 👈🏾
👍4
Forwarded from ማራናታ ᴘʀᴏⓂᴏᴛɪᴏɴ
🧠የአእምሮ ጤናና የአእምሮ ህመም
ስለ አዕምሮ ሕመም ምን ያህል  ያውቃሉ?
የአዕምሮ ሕመም ምንድን ነው?
የአዕምሮ ጤና ማለት ምን ማለት ነው?

ስለ አዕምሮ መረበሽ ማለት ምን ማለት ነው?

የአንድ ሰው አዕምሮ  ጤነኛ አይደለም የሚባለው መቼ ነው?...ሙሉውን ለማንበብ


ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን
www.tg-me.com/Binigirmachew
👍3🎉1
Forwarded from ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 (🤴ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ🤗)
የዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት ገብርኄር

​​​​​​የዐብይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት ገብርኄር ይባላል፡፡

ገብርኄር ማለት ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ስለ ታማኝ አገልጋይ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ስንኖር ለፈጣሪያችን ያለንን ታማኝነትና የምናገኘውን ዋጋ በመዋዕለ ሥጋዌው
አስተምሯል፡፡

ቅዱስ ያሬድ ለዜማ መክፈያነት የዐብይ ጾምን ሳምንታትን ሲከፍል ገብርኄርን ተጠቅሟልና እኛም ስለ ገብር ሄር ጥቂት እንበል፡፡ ልዑል እግዚአብሔር አምላካችን በነቢዩ አንደበት አድሮ፤ “እከሥት በምሳሌ አፉየ፤ ወእነግር አምሳለ ዘእምትካት፤ አንደበቴን /ነገሬን/ በምሳሌ እገልጣለሁ፤ ከቀድሞ ጀምሮ የነበረ
ታሪክና ምሳሌ እናገራለሁ” አለ፡፡

ይህም ማለት ወንጌልን በምሳሌ አስተምራለሁ፤ በመልከ ጼዴቅ ዘመን አስቀድማ የተሠራችና ታይታ የጠፋችውን ወንጌልን እናገራለሁ፡፡ ይህን ታላቅ ምሥጢር ሐዋርያው ሲያብራራ “ከመ በአሚን ያጸድቆሙ እግዚአብሔር ለአሕዛብ አቅደመ አሰፍዎቶ ለአብርሃም ከመ ቦቱ ይትባረኩ ኲሎሙ አሕዛብ ፤  በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ” ብሏል፡፡ /ገላ. ፫፥፰፣ መዝ. ፸፯፥፪

በዚሁ መሠረት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያትን ለልዩ ልዩ ወገኖች በልዩ ልዩ ምሳሌ አስተምሯል፤ ከላይ በተገለጠው ኃይለ ቃል መነሻነት ሁለት ምሳሌያትና አንድ ቃለ ትንቢት ቀርበዋል፡፡ ከምሳሌያቱ
የመጀመሪያው በዐሥሩ ደናግል አንጻር የቀረበው ምሥጢር ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ ወጥተው ወርደው ነግደው ያተርፉበት ዘንድ ገንዘቡን ስለሰጠ አንድ ነጋዴ የሚናገረው ነው፡፡

የትንቢቱ ምሥጢራዊ ይዘት የሚያስረዳውም ስለ ኅልቀተ ዓለም አይቀሬነት ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ ዕትማችን ወጥተው ወርደው ነግደው እንዲያተርፉበት ከጌታቸው የተሰጣቸውን መክሊት ስለተቀበሉት አገልጋዮች ሕይወት እንመለከታለን፡፡ ፈጣሪያችን አእምሮውን ለብዎውን /ማስተዋሉን/ ያድለን፡፡

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ ያስተማራቸው ምሳሌያዊ ትምህርቶች በቅዱስ መጽሐፋችን በሰፊው ተጽፈው እናገኛለን፡፡ የእነዚህ ትምህርታዊ ምሳሌዎች መሠረታዊ ሀሳብና ዓላማም የእግዚአብሔርን መንግሥት የምናገኝበትን የታማኝነትን ሥራ እንዴት መሥራት እንደሚገባንና መሥራትም እንደምንችል ማስተማር ነው፡፡

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለመንግሥተ ሰማያት ምሥጢር ያስተማራቸው ብዙ ምሳሌዎች ያሉ ሲሆን ከእነዚህ ብዙ ምሳሌያዊ ትምህርቶች መካከልም እንዲያተርፉበት መክሊት ስለተሰጣቸውና ስለተመሰገኑት መልካም አገልጋዮች፣ እንዲሁም መክሊቱን በመቅበሩ ምክንያት በጌታው ስለተወቀሰውና ፍርድን ስለተቀበለው ሰነፍ ሰው ታሪክ፣ የታሪኩም ምሥጢር ምን እንደሚመስል የተጻፈው ትምህርት ነው።

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን ምሳሌ የተናገረው /ያስተማረው/ በሚከተለው መልኩ ነበር፤ ‹‹ወደ ሌላ ሀገር የሚሔድ ሰው ባሮቹን ጠርቶ ያለውን ገንዘብ እንደሰጣቸው እንዲሁ ይሆናልና ለእያንዳንዱ እንደ ዓቅሙ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ ሀገር ወዲያውኑ ሔደ፡፡

አምስት መክሊትም የተቀበለው ሔዶ ነገደበት ሌላም አምስት አተረፈ፣ እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ፣ አንድ የተቀበለው ግን ሔዶ ምድርን ቆፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረ፡፡

ከብዙ ዘመንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣና ተቆጣጠራቸው፡፡ አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክቦ፡- ጌታ ሆይ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት አለ፡፡
ጌታውም፡- መልካም አንተ በጎ ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው፡፡

ሁለት መክሊት የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፡- ጌታ ሆይ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፡፡ እነሆ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍሁበት አለ፡፡
ጌታውም፡- መልካም አንተ በጎ ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው።

አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፡- ጌታ ሆይ ካልዘራህበት የምታጭድ ካልበተንህበትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ፈራሁም ሔጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት ፤ እነሆ መክሊትህ አለልህ አለው፡፡
ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው፡- አንተ ክፉና ሐሰተኛ ባሪያ ካልዘራሁበት እንዳጭድ ካልበተንሁበትም እንድሰበስብ ታውቃለህን? ስለዚህ ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበር።

እኔም መጥቼ ያለኝን ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር፡፡ ስለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት ዐሥር መክሊትም ላለው ስጡት። ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ይበዛለትማል። ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል፡፡

የማይጠቅመውንም ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል የሚል ነው፡፡

መክሊት ጥንት የክብደት መለኪያ ነበር:: አንድ መክሊት 30 ኪሎ ግራም ያህል ነው፡፡ በዚህ ምሳሌ ላይ እንደተገለጸውም መክሊት የሚለው ቃል ገንዘብን ያመለክታል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምሳሌ ውስጥ እርሱን የምናገለግል ሁላችን እንደየዓቅማችን ማድረግ የሚገባንን መንፈሳዊ የአገልግሎት ሥራንና በአገልግሎታችን ውጤታማ በመሆናችንም ከእርሱ የምናገኘውን ዘለዓለማዊ ክብርና ዋጋን እንዲሁም መሥራት የሚገባንን ባለማድረጋችንም ምክንያት የሚገጥመንን መለኮታዊ ቅጣትን አመልክቶናል፡፡

በዚህ ምሳሌ ውስጥ ባለ አምስት የተባለው በቂና ፍጹም ትምህርት ተምሮ ሌላውን መክሮ አስተምሮ ራሱን አስመስሎ የተካ ያወጣ ነው፡፡

በተመሳሳይም ባለ ሁለት የተባለው እንደ መጀመሪያው ሁሉ ተምሮ ሌላውን መክሮ አስተምሮ ራሱን አስመስሎ ያወጣ ሲሆን ባለ አንድ የተባለው ደግሞ ተምሮ ሳያስተምር የቀረ በስንፍና በቸልተኝነት በማን አለብኝነት ሕይወት ተገድቦ የቀረ ሰው ነው፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ከታች INSTANT VIEW የሚለውን በመጫን ያንብቡ
                 👇👇👇
https://telegra.ph/የየዐቢይ-ጾም-ስድስተኛው-ሳምንት-ገብርኄር-ታማኝ-አገልጋይ-04-13

አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚

👇🏾📽የግእዝ ትምህርት በyoutube🖥👇🏾
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
👍112🎉1
Forwarded from ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 (🤴ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ🤗)
🤗የመጽናኛ ቃል🗣

በዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ


እግዚአብሔር አምላካችን ሁል ጊዜ ከኛ ጋር እንዳለ በምን እናውቃለን ብለን ራሳችንን እንጠይቃለን እኔንም ጨምሮ ያው በህይወት አምላካችን ነጻ ፈቃድ ስለሰጠን ማመን እና አለማመን ለኛ ተትቷል ነገር ግን የእግዚአብሔርን ድንቅ ስራ ሁልጊዜም ከጎናችን እንደሆነ የምንረዳው እኛ በህይወታችን ቦታ እንደሰጠነው መንገድ ይለያያል።

ይህን ስላችሁ ግን እናንተ ብትተዉትም እሱ ግን አይተዋችሁም "ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም ስላለ" ነገርግን እግዚአብሔር በህይወታችን በሰጠነው ቦታ ላይ እኛን ለማዳን የብርሃን ፍጥነት ጊዜ አይወስድበትም።

እግዚአብሔር ጊዜን ጠብቆ የሚሰራ አምላክ ነውና "ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሰራው" እንደሚለው ቅዱስ መጽሐፉም

👉🏾 እንግዲህ ከዚህ ቀጥሎ የምጽፈውን ታሪክ ከሌሎች አባቶች የሰማሁትን ነው እናንተም ሰማታችሁት ሊሆን ይችላል ግን ላልሰሙት መጽናኛ ይሆናል ብዬ በሥላሴ ስም መጻፍ እጀምራለሁ ።

ከአንድ ቤተሰብ የተወሰኑ ልጆች ከአያታቸው ወዳጅ ዘመድ ለበዓል ለመጠየቅ ሊሄዱ በተሰናዱበት ጊዜ መኪናው ሊነሳ ሲል አያታቸው የተወሰነ እንቁላል በዘምቢል አድርገው ይዘው መጥተው "ልጆቼ እንግዲህ ወዳጅ ዘመድ ለመጠየቅ የሚሄዱትን እግዚአብሔር ይወዳልና በመንገዳችሁ ከእናንተ ጋር ይሁን" አለቻቸው።

ከነርሱም መካከል አንዱ "አያቴ እንደምታዪው መኪናው ለኛም አልበቃም ባይሆን ከተመቸው እንቁላሉ ከሚቀመጥበት ከኮፈን ውስጥ ከእንቁላሉ ጋር ይቀመጥ" አለ ቆፍጠን ብሎ አያታቸውም ልባቸው ተሰብሮ እያነቡ ልጆቼ እንዲህ አይባልም ብለው ሸኟቸው በመንገዳቸውም በጣም ሀይለኛ ዝናብ ዘንቦ አስፓልቱ መንሸራተት ጀምሮ ከአንድ መኪና ጋር ተጋጭተው ሁላቸውም ህይወታቸው አለፈ።

አያታቸውም በቶሎ ተጠርተው እሬሳውን ወስደው ልሄዱ ሲሉ በሀዘን ውስጥ ሆነው አንደኛው የልጅ ልጃቸው የተናገረው ትዝ በ
ብሏቸው የተጋጨውን መኪና ኮፈኑ እንዲከፈት አዘዙ ባዩትም ነገር በጣም ደነገጡ።

ለካ እግዚአብሔር በኮፍኑ ውስጥ ይቀመጥ ሲባል የማይቀመጥ የሚንቅ መስሏቸው ነበረ ልጆቹ ነገር ግን እንቁላሉ ገለባው እንኳን አልተደፋም እንኳን ሊሰበር ይህን ያዩት የልጆቹ አያት ወደ እግዚአብሔር በማልቀስ ለልጅ ልጆቻቸው ጸሎት አደረጉ።

ከዚህ ታሪክ ምን እንማራለን እግዚአብሔር በህይወታችን ውስጥ በሰጠነው ቦታ ምን ያህል እንደሚሰራ ነው እርሱ ታማኝ ነው ታማኝ የሆነ(ምእመናንን) ይፈልጋል እግዚአብሔር በህይወታችን እንዲሰራ እንፍቀድ እርሱ የሰራውን ማንም አያፈርሰውምና።

እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን ዛሬ የት ነበርን ብለን ራሳችንን እንጠይቅ።
በቅርብ ጊዜ ብዙ ሰዎች በበሽታ በጦርነት በጸብ ሲሞቱ እኛን ለዛሬ ያበቃን አምላክ እኮ በኛ ጽድቅ አይደለም በቸርነቱ ነውና በፊቱ ስንቆም በፍርሃት ይሁን ።

ዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር


አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚

👇🏾📽የግእዝ ትምህርት በyoutube🖥👇🏾
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
👍12🥰21🙏1
Forwarded from ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 (🤴ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ🤗)
🌿🤴​​​​ሆሳዕና🤴🌿

በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊ፤ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ዘመሩ? (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ. 12÷12-15)

🌿የዘንባባ ዝንጣፊ፦
👉 ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሄርን አመስግኖበታል የደስታ መግለጫ በመሆኑ አነተ ደሰታ የምታስገኝ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡

👉 ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው(
👉 ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው
👉 ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው

👉 ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው
👉 ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው አኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳእና በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡

🌴የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ፦
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በሃጥያት የመረረውን ሂወታችን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።

👉 የቴምር ፍሬ የሚገኘው ከዛፉ ከፍታ ላይ ነው አንተ አምላካችን ልዑለ ባህሪ ነህ ከፍ ከፍ ያልክ አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
👉 የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ ባህሪ ነህ ሲሉ ነው።
👉 የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንት ባህሪ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው።

🪵የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ፦
👉 የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡
👉 የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ሃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው።

👉 ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ህይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
👉 በኦሪት ግዜ የወይራ ዘይት ለመስዋአትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኗልና።

በዓሉን በዓለ ክብር በዓለ ፍስሐ ያድርግልን፡፡ ከመጣብን መቅሰፍት መከራ እሱ በሀይል በስልጣኑ ይሰውረን ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን።

አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺‌‌
👍10👏3
Forwarded from ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 (🤴ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ🤗)
ሕማማት @eotc_books_by_pdf (1).pdf
74.2 MB
📚⛪️ሕማማት📚⛪️

ብዙዎቻቹ በውስጥ መስመር ያለ watermark ይሰራ ብላችሁ ስለጠየቃችሁን ተሰርቶ ቀርቧል እናንተም በበኩላችሁ ለሌሎች በማካፈል አንብቡ አስነብቡ።

🤗መልካም የበረከት ጾም ይሁንልን🤗

አዘጋጅ ፦ @Ethio_Pdf_Books
አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚

  🔔አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ💒
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
    👆🏾𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒👆🏾


➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
👍1
Forwarded from ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 (🤴ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ🤗)
​​​​​​በሰሞነ ሕማማት የሚጸለዩት እና የማይጸለዩት ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው?

ሼር በማድረግ ለወዳጆቻችሁ አድርሱ አሳውቁ‼️

➦ከነገ ጀምሮ የጌታችንን ሕማም የምናስብበት ሰሞን ነው። እንደ ቅድስት ቤተ-ክርስትያናችን ሥርዓት በዚህ በሰሞነ ሕማማት የምንጸልያቸውና ለጊዜው የምንታቀባቸው ጸሎቶች አሉ።

👉 🛐በሰሞነ ሕማማት የምንጸልያቸው ጸሎቶች
የትኞቹ ናቸው?


በሰሞነ ሕማማት አጥብቀን የምንጸልያቸው ጸሎቶች ውዳሴ ማርያም:ዳዊት: ሰይፈ ሥላሴ:ሰይፈ መለኮት:ድርሳነ ማሕየዊ ውዳሴ አምላክ ናቸው።

➦እመቤታችን ድንግል ማርያም በዚህ በሰሞነ ሕማም በልጅዋ ምክንያት ብዙ እንግልት ስለደረሰባት የእሷን ምስጋና የሆነውን ውዳሴ ማርያም አናስታጉልም። ውዳሴ ማርያም ማመስገኛ መማጸኛ ስለሆነ እንጸልያለን። ምክንያቱም በዚህ በሰሞነ ሕማማት መከራ ተቀብሎ ሞቶ ሕይወቱን የሰጠንን ጌታ በሥጋ ወልዳለችን በውዳሴዋ እናስባታለን።

➦የቅዱስ ዳዊት ድርሰት የሆነው ታላቁ መዝሙረ ዳዊት በትንቢት ክፍሉ ስለ ጌታችን ሕማም ስቃይ እና ሞት የሚናገርና በዳዊት ምስጋና በምድር የሰው ልጆች በሰማይ ቅዱሳን መላእክት ስለሚያመሰግኑ እንጸልየዋለን።

➦ሰይፈ ሥላሴ ከሦስቱ አካላት እግዚአብሔር ወልድን የሚያመሰግን አምላክነቱን የሚመሰክር እና የሚመሰጥር በመሆኑ እንጸልየዋለን።

➦ሰይፈ መለኮት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ስለ ምስጢረ መለኮት እና ስለ ጌታችን አምላክነት ስለሚናገር እንጸልየዋለን።

➦ድርሳነ ማሕየዊ በቅዱስ ዮሐንስ ወልደ-ነጎድጓድ የዓይን እማኝነት እና የቃል ምስክርነት የተጻፈና የጌታችንን መከራ ስቃይ እንግልት እና ሞት በልዩ ሁኔታ የሚናገር በመሆኑ ልክ እንደ ውዳሴ ማርየም የየእለት/የየቀን ስላለው ብንጸልየው በዓይነ ሕሊና ቀራንዮ ወሰዶ በነፍሳችን የጌታችንን ሰማያዊ ውለታ የሚስልብንና በመጸለያችን ልዩ ጸጋና ክብር የሚያሰጥ የቃል-ኪዳን ጸሎት በመሆኑ በዚህ በሰሞነ ሕማማት ብንጸልየው እጅጉን እንጠቀምበታለን። ውዳሴ አምላክም የጌታችን ምስጋና በመሆኑ መጸለይ እንችላለን።

👉🛐 በሰሞነ ሕማማት የማይጸለዩት ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው?

➦በሰሞነ ሕማማት የማይጸለዩትን ጸሎቶች ጠቅለል አድርገን ስናያቸው ድርሳናት ገድላት እና መልካ መልኮች ናቸው። ይህም የሆነው በሰሞነ ሕማማት ጌታችን ለእኛ ለሰው ልጆች ብሎ የተቀበላቸውን ስቃይ እና መከራ ሞት የምናስብበት እና የምናለቅስበት እንጂ ሌሎቹን በድርሳናቸው በገድላቸው በመልካቸው የምናመሰግንበት ጊዜ ስላልሆነ ነው።

➦በተረፈ በዚህ በሰሞነ ሕማማት ለራሳችሁ ለሀገራችሁ ብቻ አትጸልዩ ለዓለም ሕዝብ ለአሕዛብ በሙሉ ጸልዩ። ምክንያቱም ለእነሱ የመጣ ሰማያዊ ቁጣ በቀጥታም በተዘዋዋሪም ለእኛም ይተርፋልና። እነሱ ሲለበለቡ እኛ መቃጠላችን እነሱ ሲሰበሩ እኛ ወለም ማለታችን እነሱ ሲሞቱ ሞት ደጃፋችን መቆምን በማሰብ ለእነሱም እንጸልይ። የእነሱ መከራ ሲርቅ ነው የኛም የሚርቀው።
✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር✞
✞ወለወላዲቱ ድንግል✞
✞ወለመስቀሉ ክቡር✞
✞አሜን✞
#ሼር_ሼር_ሼር

🔔አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ💒
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
    👆🏾𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒👆🏾

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
1👍1
Forwarded from ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 (🤴ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ🤗)
ሰይፈ_ሥላሴ_ወሰይፈ_መለኮት_@eotc_books_by_pdf.pdf
48.8 MB
📚⛪️ሰይፈ ሥላሴ ወ ሰይፈ መለኮት📚⛪️


አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚

#ሼር_ሼር_ሼር

🔔አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ💒
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
    👆🏾𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒👆🏾

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
👍31
Forwarded from ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 (🤴ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ🤗)
ድርሳነ_ማኅየዊ_መልክአ_ማኅየዊ_@eotc_books_by_pdf.pdf
111.1 MB
📚⛪️ድርሳነ ማኅየዊ📚⛪️


አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚

  #ሼር_ሼር_ሼር

🔔አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ💒
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
    👆🏾𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒👆🏾

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
👍2
Forwarded from ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 (🤴ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ🤗)
ግብረ ሕማማት @eotc_books_by_pdf.pdf
150.5 MB
📚⛪️ግብረ ሕማማት📚⛪️

📕ይህን ግብረ ሕማማት የሚለው መጽሐፍ 261Mb የነበረ ሲሆን እኛ ሁሉም የኦርቶዶክስ አማኝ ሊያነበው ይገባል ብለን በ150Mb አቅርበነዋል።

አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚

  #ሼር_ሼር_ሼር

🔔አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ💒
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
    👆🏾𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒👆🏾

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
2025/10/26 07:36:42
Back to Top
HTML Embed Code: