Telegram Web Link
Forwarded from ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 (🤴ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ🤗)
​​#በሰሙነ_ሕማማት_የሚፈጸሙ_ሥርዓቶች

1, #ስግደት :-
በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል።

2, #ጸሎት :-
በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው።

በእነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ።

3, #ጾም :-
በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት / አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች አይበሉም። በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ #አንድ_ሰዓት እንድንጾም; ይኸውም ቆሎ;ዳቦ;ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል።

4, #አለመሳሳም :-
አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም። መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ገላ.3:13 ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29

5. #አክፍሎት :-
እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው።

6, #ጉልባን :-
ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው።

7, #ጥብጠባ :-
ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው። ይህም የጌታ ምሳሌ ነው።

8, #ቄጠማ :-
ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን።

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻም ወድካም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም።

  #ሼር_ሼር_ሼር

🔔አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ💒
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
    👆🏾𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒👆🏾

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
👍61
Forwarded from ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 (🤴ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ🤗)
መዝሙረ ዳዊት @eotc_books_by_pdf.docx
6.3 MB
📚⛪️መዝሙረ ዳዊት📚⛪️

አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚


📚 በሕማማት የሚፀለየውን የእያንዳንዱን ተከፍሎ ከታች ተቀምጧል

❖ የዳዊት መዝሙራት በጠቅላላው መቶ ሃምሳ እና የነቢያት ጸሎት በቤተክርስትያን በሰባቱ ዕለታት ተከፋፍለው ይጸለያሉ ፤ እነርሱም

የሰኞ ከመዝሙር 1 – 30 (ፍካሬ ፥ አድኅነኒ ፥ አምላኪየ)
የማክሰኞ ከመዝሙር 31 – 60 (ብፁዓን ፥ ከመያፈቅር ፥ ለምንት ይዜኃር)
የረቡዕ ከመዝሙር 61 – 80 (አኮኑ ፥ እግዚኦ ኩነኔከ)፤
የሀሙስ ከመዝሙር 81 -110 (እግዚአብሔር ቆመ ፥ ይኄይስ ፥ ስምዐኒ)
የአርብ ከመዝሙር 111 – 130 ( ብፁዕ ብእሲ ፥ ተፈሣሕኩ)
የቀዳሚት ከመዝሙር 131 – 150 (ተዘከሮ ፥ ቃልየ) እና
የእሑድ የነቢያት ጸሎት እና መኃልየ መኃልየ ዘሰሎሞን ናቸው።

  #ሼር_ሼር_ሼር

🔔አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ💒
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
    👆🏾𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒👆🏾

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
👍61🎉1
Forwarded from ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 (🤴ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ🤗)
🧎‍♂ስንሰግድ ምን እያልን እንሰግዳለን ⁉️


​​ሥርዓተ ጸሎት ሰሙነ ሕማማት ከሰኞ እስከ ዕሮብ  ካህናት እያዜሙ እየሰገዱ እኛም እየተቀበልን እያዜምን የምንሰግድበትን   ሥርዓት ለማውቅ እና ለመፈፀም ከስር ያንብቡ

❖ የጸሎተ ሐሙስና የዕለተ ዓርብ ሥርዓተ ጸሎት !

👉 ከሰኞ ጀምሮ እስከ ዓርብ ድረስ ባሉት ቀናት ውስጥ  በመጀመሪያ ዲያቆኑ ቤተ ክርስቲያኑን ሦስት ጊዜ ዞሮ ደወል ካሰማ በኋላ መቶ አምሳው ዳዊት ይታደልና ይደገማል፡፡ የሰባት ቀናት ውዳሴ ማርያምና አንቀጸ ብርሃን  እስከ ይዌድስዋ  ድረስ ታድሎ ይደገማል፡፡ ከዚያም “እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም ዓመ ከመ ዮም ያብጽሐኒ ያብጽሕክሙ አግዚአብሔር በፍሥሓ ወበሰላም” ተብሎ አቡነ ይደገምና  በዐራቱም ወንጌላት መሠረት ለእያንዳቸው በእየዕለቱና  ሰዓቱ የተመደበውን አቡነ ካህናቱ በቀኝና በግራ እየተፈራረቁ  ይመራሉ፡፡ ካህናቱና ሕዝቡም ይቀበላሉ፡፡ በመቀጠል፡- (ትእዛዝ፡ ሕዝቡ በጸሎት በተሰበሰቡ ጊዜ ጠዋት ወይም በ3፣ በ6፣በ9፣ በ11ሰዓተ መዓልት መጀመሪያ ሕዝቡ እየሰገዱና እየተከተሉ እንዲህ ይበሉ፡፡ )

✥ "ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም ፡፡"

✥ "አማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም፡፡"

✥ " ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም፡፡ "
✥ " ኃይልየ ወጸወንየ ውእቱ እግዚእየ፤ እስመ ኮንከኒ ረዳእየ እብል በአኰቴት ፡፡"

ትእዛዝ፡ በዚህ ጊዜ ካህኑ እየተከተሉ አቡነዘበሰማያት ይድገሙ ።
ይህን የላይኛውን ጸሎት እያመላለሱ ከአቡነ ዘበሰማያት ጋር 12 ጊዜ ይበሉ

❖ " ለአምላክ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም፡፡

❖ "ለሥሉስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ለማሕየዊ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ለዕበዩ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖"ለእዘዙ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ለመንግሥቱ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ስለልጣኑ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ለኢየሱስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

"ለክርስቶስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ለሕማሙ  ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ለመስቀሉ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም፡፡ "

ትእዛዝ፡- ይህ ሦስት ጊዜ እየተመላለሰ ይባላል፡፡በመጨረሻም የሚከተለውን ሦስት ጊዜ እያመላለሱ ይበሉ፡፡

❖ "ለከ ይደሉ ኃይል፣ ወለከ ይደሉ ስብሐት ወለከ ይደሉ አኰቴት ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለመ ዓለም"

ትእዛዝ፡- ካህኑ ‹ጸልዩ በእንተ ጽንዓ ዛቲ . . .› ብሎ በሚያነብ ጊዜ በየምዕራፉ "እግዚኦ ተሳሃለነ" እየተባለ ይሰገዳል፡፡

ትእዛዝ፡- ከዚህ ሁሉ በኋላ ሕዝቡ የሚከተሉትን ጸሎት በግራና በቀኝ ይበሉ፤

"ክርስቶስ አምላክነ፤ ዘመጽአ ወሐመ በእንቲአነ በሕማማቲሁ ቤዝወነ፤  ንሰብሖ ወናልዕል ስሞ ኅቡረ፤ እስመ ውእቱ ገብረ መድኃኒተ በዕበየ ሣህሉ" (በዐርብ) ዘሐመ ወሞተ በእንቲአነ ይባላል፡፡

ትእዛዝ፡- ቀጥሎም ሕዝቡ በሁለት ክፍል ሆነው የሚከተለውን ጸሎት ሁለት ጊዜ በመከታተል አንድጊዜ በማስተዛዘል ይበሉት፡፡

ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤#ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤

#አብኖዲ  ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን

#ናይን፣ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን ፤

#ታዖስ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤

#ማስያስ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤

#ኢየሱስ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤

#ክርስቶስ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤

#አማኑኤል ናይን፣ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤

#ትስቡጣ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን

ትእዛዝ፡- ከዚህ በኋላ ኪርያላይሶን አርባ አንድ ጊዜ ይባላል፡፡

ይኸውም  በአንድ ወገን 20 ጊዜ በሌላው ወገን 21 ጊዜ በጠቅላላው 41 ጊዜ ኪርያላይሶን  ኪርያላይሶን  ኪርያላይሶን  እየተባለ ይሰገዳል፡፡

በመጨረሻ ጊዜ፡-

✥ ስብሐት ለእግዚአብሔር ኪያነ ዘፈጠረ ከመ ናምልኮ (እናመልከው ዘንድ ለፈጠረን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል)፡፡

✥ ስብሐት ለማርያም እመ አምላክ እግእዝትነ ወመድኃኒትነ (እመቤታችንና መድኃኒታችን ለሆነች ለአምላክ እናት ለማርያም ምስጋና ይገባል)፡፡

✥ ስብሐት ለመስቀለ ክርስቶስ ዕፀ መድኃኒት ኃይልነ ወፀወንነ(ኃይላችን መጠጊያችን ለሆነ ድኅነት ለተገኘበት ለክርስቶስ ምስጋና ይገባል)፤፤ ጸሎተ ሃይማኖትን ሐመ  እስከ ሚለው ድረስ መድገም ነው፡፡  /ከሰኞ እስከ ረቡዕ ይባላል/


  #ሼር_ሼር_ሼር

🔔አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ💒
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
    👆🏾𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒👆🏾

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
👍91
Forwarded from ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 (🤴ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ🤗)
👉🏾ሰሙነ ህማማት

👉🏾የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ወዳጆች ወገኖች ከኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ ቻናል የሚተላለፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት በያላችሁበት የምትከታተሉ በእግዚአብሔር ሰላምታ ሰላም
እንላችኋለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን እያልን፤ ዛሬ በርዕሱ እንደተጠቀሰው " ሰሙነ ህማማት " በሚል ርዕስ ነው የምንነጋገረው፣ አንብባችሁ ትማሩበት ዘንድ አደራ እንላለን፦

የሰሙነ ሕማማት ሰኞ" መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው"ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሆሣዕና ዕለት "ቢታኒያ አድሮ በማግሥቱ ከቢታኒያ ሲመጡ ተራበ" ማርቆስ ምዕራፍ 11ቁጥር 11-12፣ ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፣ ነገር ግን ከቅጠል በቀር ፍሬ አላገኛባትም "ከአሁን ጀምሮ  ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት" በለስ የተባለች ቤተ "እስራኤል" ናት፣ ፍሬ የተባለች "ሃይማኖትና ምግባር" ናት፣ ከእስራኤል ፍቅርን ሃይማኖት ምግባርን ፈለጋ አላገኘም፣ እስራኤልም "ሕዝብ እግዚአብሔር መባል እንጂደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት በመረገሙ ምክንያት እርሱ ከለያቸው በስተቀር ደግ ሰው ጠፋብት፡፡

በለስ "ኦሪት ናት" ኦሪት በዚህ ዓለም ስፋነ ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያት ልሽር አልመጣሁም፣ ልፈፅም እንጂ በማለት ፈፀማት፣ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሱ ድህነት አላደረገባትምና፤ ፍሬ በአንቺ አይሁን አላት፣ ድህነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደ መድርቅ ፍጥና አለፋት
በለስ ኃጢአት ናት የበለስ ቅጠል ሰፊ እንድሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፋና አገኛትበለስ ሲበሉት ይጠፍጣል ቆይቶ ግን ይመራል፣ ኃጢአትም ሲሠሩት ደስ ደስ ያሰኛል፣ ኋላ ግን ያሳዝናል፣ ወደ እርሷም ሄዶ ማለትም ከኃጢአት ጋር ዋለ፣ ኃጥእ ከመባል በቀር በአንደበቱ ሐሰት በሰውነቱ ክፋት እንዳልተገኘበት ለማመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፡፡

በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር ዓይኑን ለማለት ነው፣ ስትረገም ፈጥና መድረቋም በአዳም ምክንያት ያገኛትን ዕዳ በደል በእርሱ ካሣነት እንደጠፋችልን ለመግለፅ ነው
አንጸሆተ ቤተ መቅደስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፣ ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፣ ቤተ መቅደስ፣ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ "ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆነ ቢያገኘው "ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፣ እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አድርጋችኋት" ብሎ የሚሸጡትን ሁሉ ገለበጠባቸው፣ገርፎም አስወጣቸው፣ ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልፅ ነው፡፡

አቤቱ ማረን ይቅር በለን


  #ሼር_ሼር_ሼር

🔔አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ💒
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
    👆🏾𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒👆🏾

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
👍11🔥1
Forwarded from ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 (🤴ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ🤗)
የሰሙነ ሕማማት ማክሰኞ

#የጥያቄ_ቀን_ይባላል

ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተመቅደስ ምክንያት፣ ሹመትን ወይም ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን፣ ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና፤ የጥያቄ ቀን ይባላል፡፡

ጥያቄውም ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር፣ ተዓምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታትን፣ በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ? የሚል ነበር፡፡ /ማቴ. 21፥23-27፣ ማር. 11፥ 7-35፣ ሉቃ.21፥23-27፣ ማር.11፥27-33፣ ሉቃ. 20፥1-8/፤ እርሱም ሲመልስ፤ «እኔም አንድ ነገር እጠይቃችኋለሁ፣ እናንተም ብትነግሩኝ በማን ሥልጣን እነዚህን እዳደርግ እነግራችኋለሁ፡፡ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረ፣ ከሰማይ ነውን? ወይስ ከሰዉ? በእግዚአብሔር ፈቃድ፣ ወይስ በሰው ፈቃድ?» አላቸው፡፡ እነርሱም ከሰማይ ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም ይለናል፤ ከሰው ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል፣ እንደ መምህርነቱ ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን፤ ተባብለው ከወዴት እንደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት፡፡ እርሱም እኔም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ አልነግራችሁም አላቸው» ይህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸውን ሁሉ በራሱ ሥልጣን እንዲያደርግ አጥተዉት አልነበረም፣ ልቡናቸው በክፋትና በጥርጥር ስለተሞላ እንጂ፡፡

#የትምህርት_ቀንም_ይባላል፡-

በማቴ. 21፥28፣ ማቴ. 25፥46፣ ማር.12፥2፣ ማር.13፥37፣ ሉቃ. 20፥9፣ ሉቃ. 21፥38 የሚገኙት ትምህርቶች ሁሉም የማክሰኞ ትምህርት ይባላሉ፡፡ በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረ፣ የትምህርት ቀን ይባላል፡፡ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከሥጋዊ ነገር ርቆ በዚህ ሰሞን የሃይማኖት ትምህርት ሲማር ሲጠይቅ መሰንበቱም መጽሐፋዊ ሥርዓት ነው፡፡


አቤቱ ማረን ይቅር በለን


  #ሼር_ሼር_ሼር

🔔አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ💒
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
    👆🏾𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒👆🏾

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
👍72🎉1
Forwarded from Qualitymovbot
😍ለፕሮፋይል የሚሆኑ ገራሚ ፎቶዎችን ለማግኘት JOIN አድርጉ👇👇👇👇👇👇👇
👍4🙏4
Forwarded from ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 (🤴ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ🤗)
📚ሕማማት ትረካ ማውጫ📖

📌ምዕራፍ አንድ፦ አሳልፎ የሚሰጥህ ማነው⁉️
https://youtu.be/lMZJoIYzY0Q?si=HE3DWXvFh6FlkYv0

📌ምዕራፍ ሁለት ፦ ሊቀ ካህናት በካህናት አለቆች ግቢ
https://youtu.be/WWl4YmHv2CE?si=j8vU0xeN0SpBggh5

📌ምዕራፍ ሦስት ፦ የዓለማት ገዢ በይሁዳ ገዢ ፊት
https://youtu.be/nITjkN2PTaE?si=Mu3F3Koh2VXaWVyG

📌ምዕራፍ አራት ፦ የመከራ ጉዞ ወደ መከራ
https://youtu.be/GPhuamxFzBU?si=E6H5c9Dp-BvRZd0E

📌ምዕራፍ አምስት ፦ የመጨረሻዎቹ የጌታችን ትምህርቶች
https://youtu.be/1Vzn4TJZwqc?si=PzrynZAGW7lonwhV

📌ምዕራፍ ስድስት ፦ የማይሞተው ሞተ
https://youtu.be/zaAXRqoZrvE



ሁላችሁም ኦርቶዶክሳዊያን ይህን መጽሐፍ አዳምጡት የጌታችንን ህማም ትማሩበታላችሁ SUBSCRIBE ማድረግ አይረሳ
👍61
|°°ለጀማሪ የግእዝ ቋንቋ ወዳጆች ሁሉ
  🙌 ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ @lesangeez128 እየሰጠን እንደሆነ ይታወቃል ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና  በቅርቡ በonline ስለሚጀመር በዚህ #ዙር ላይ 20 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁዠለጀማሪችሁን እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
#ለሁለት ወር የመማሪያ ክፍያ #250ብር ብቻ ለበለጠ መረጃ በ @asrategabriel ያነጋግሩን አልያም በ +251970908094 ይደውሉልን።

   🤲ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም🧑‍🎓
👍31
Forwarded from ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 (🤴ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ🤗)
የብርሃን እናት @eotc_books_by_pdf.pdf
94.6 MB
📚⛪️የብርሃን እናት📚⛪️

ጸሐፊ ፦ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚


ይህ መጽሐፍ በግሩም አጻጻፍ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ስለ እናታችን ስለ ድኅነታችን ምክንያት ድንግል ማርያም የብርሃን እናትነት የተጻፈና በዕንባ እየታጀቡ የሚያነቡት መጽሐፍ ነው ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን አድርሱ!!

  #ሼር_ሼር_ሼር

🔔አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ💒
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
    👆🏾𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒👆🏾

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
👍86
Forwarded from ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 (🤴ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ🤗)
📕ትንሿ ቤተክርስቲያን.PDF

በኦርቶዶክሳዊ ጋብቻ ቤተሰብ እና የሕጻናት አስተዳደግ በጣም ተወዳጅነት ያተረፈውን መጽሐፍ በዚህ ቻናል በቅርቡ ይለቀቃል ከዚያ በፊት የናንተን ፍላጎት ምን ይመስላል የሚለውን ከታች ባስቀመጥነው ምርጫ መሠረት አድርገን እንለቃለን

ቢያንስ በየሚዲያው የምናያቸውን ሥርዓት እና ልቅ የሆነ አስተዳደግ የሚታይባቸውን ሕጻናት እግዚአብሔር በቤተሰብ ላይ አድሮ እንዲረዳቸው ይህ መጽሐፍ እጅጉን ጠቃሚ ነውና ሼር ማድረግ አትርሱ


📌መጽሐፉ የሚለቀቅበት ቻናል
https://www.tg-me.com/+rqHLqXClTZA0YmU0


ሼር በማድረግ ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን እናድርስ

መጽሐፉ በቶሎ እንዲለቀቅ 📚ትንሿ ቤተክርስቲያን.PDF የሚለውን አንዴ በመጫን ይምረጡ።
👍234
የግእዝ ቋንቋ ለሁለት ወር ስልጠና ተጀምሯል
መሠረታዊ የቋንቋ ትምህርት
  🙌 ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ @lesangeez128 እየሰጠን እንደሆነ ይታወቃል ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና  በቅርቡ በonline ስለሚጀመር በዚህ #ዙር ላይ 20 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁዠለጀማሪችሁን እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
#ለሁለት ወር የመማሪያ ክፍያ #250ብር ብቻ ለበለጠ መረጃ በ @asrategabriel ያነጋግሩን

ለበለጠ መረጃ
☎️በ +251970908094 ይደውሉልን።

   🤲ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም🧑‍🎓
👍2
Forwarded from ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 (🤴ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ🤗)
ትንሿ ቤተክርስቲያን @eotc_books_by_pdf.pdf
191.3 MB
📚⛪️ትንሿ ቤተክርስቲያን📚⛪️

ተለቀቀ

ጸሐፊ ፦ መምህር ገብረእግዚአብሔር ኪደ
አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚


በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ስለ ኦርቶዶክሳዊ ጋብቻ ስለ ሕጻናት አስተዳደግ የተለያዩ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን የጠበቁ ኦርቶዶክስ መሆን እንዴት መታደል እንደሆነ የምንመለከትበት መጽሐፍ ነው እንዲህ አይነት እጆችን እግዚአብሔር ይባርክ ሁላችሁም አንብቡት ለውድ ምእመናንም ሼር በማድረግ በማዳረስ አስነብቡ !!

በዚህ ቻናል የዱሮና አዳዲስ ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ በPDF ይቀርባሉ ከ120,000በላይ ኦርቶዶክሳዊያን አሉ ይቀላቀሉን ያንብቡ
👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾
@EOTC_BOOKS_BY_PDF

📚መልካም ንባብ👨‍💻
     🤗መልካም ምሽት🤗

#ሼር_ሼር_ሼር

🔔አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ💒
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
    👆🏾𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒👆🏾

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
👍83🥰1
Forwarded from ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 (ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ)
step 1

Task የሚለውን እንገባለን። ከዛ special በሚለው ስር የሚሰሩ taskoch አሉ ለምሳሌ ቴሌግራም ጆይን ማለት ፣ ቲዊተር follow ማድረግ ፣ ዌብሳይት ማይት ፣ ሶልያና አካውንት መክፈት ሊሆን ይችላል go የሚለውን ነክታችሁ ትገባላችሁ። የታዘዛችሁት ካደረጋችሁ በኋላ እና ተመልሳችሁ check ትሉታላችሁ። 29 second ከቆጠረ በኋላ እንደገና check ትነካላችሁ ከዛን claim ማድረግ ነው።

እንዲሁም league እና ref tasks የሚለው በመግባት claim የሚለው ከመጣላችሁ claim በማድረግ ኮይን መሰብሰብ ትችላላችሁ።

.
.
.

START አድርጉ

https://www.tg-me.com/tapswap_mirror_1_bot?start=r_5967909285
👍14😱1
Forwarded from ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 (🤴ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ🤗)
🎼ዘፈን ለምን ይከለከላል ⁉️

➭ ዘፋኝነት የተከለከለበትን ምክንያት በግድ ማወቅ አለብኝ ለምን ትላለህ?

➨ ምክንያቱን ማወቅህ አያፀድቅህም አለማወቅህም አያስኮንንህም፡፡ ነገር ግን ዘፋኝ ብትሆን ትጠየቅበታለህ፡፡ ባትዘፍን ደግሞ ታዛዥ ተብለህ በእግዚአብሔር ዘንድ ትመሰገነበታለህ፡፡ ስለዚህ የሚመለከትህን ለምን አታደርግም?

➣ . . . ዘፈን ለምን እንደተከለከለ መዘርዘሩ ምስጢሩን እንደሚያጠበው መገለጹ ትክክል ነው፡፡ ቢሆንም ይሕ እንዳለ ሆኖ የተወሰኑ ነጥቦችን በማንሳት የዘፈንን ጎጂ ገጽታ ማሳየት ይገባል፡፡

ሀ. ዘፈን የአጋንንት ስራ ነው፡፡ አጋንንት ይዘፍናሉና፡፡

➣ ለዚህ ምንም ማስተባበያ አያስፈልገውም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹በዚያም አጋንንት ይዘፍናሉ›› በማለት ስለ አጋንንት ዘፋኝነት ይናገራል፡፡ ኢሳ 13፥21 አትዝፈኑ ማለት የአጋንንትን ሥራ አትሥሩ ማለት መሆኑን ተረዳ፡፡
ይህን በተመለከተ መጽሐፈ መቃብያን ደግሞ እንዲህ ይላል ‹‹ . . . እየዘፈኑም ከአጋንንት ጋር ይጫወቱ ነበር፡፡ አጋንንትም ጫወታቸውንና ዘፈናቸውንም ሁሉ ያደንቁላቸው ነበር፡፡›› የዚህ ስፍራ አገላለጥ ደግሞ ለየት የሚለውን አጋንንትን ዘፋኞች ብቻ ሳይሆኑ ከዘፈን አድናቂዎች ጎራ መሰለፋቸው ነው፡፡

➾ ዘፈን የአጋንንት ስራ መሆኑን ስታውቅ አይንህ ተገልጦ አንድ ምሥጢር መመርመር ይጀምራል፡፡ እስኪ ሀገራችንን ጨምሮ የጃማይካውያንንና የአንዳንድ የአፍሪካንና የሌሎችንም አህጉራት ዘፋኞችን ድርጊት ልብ ብለህ መርምር፡፡ ደግሞም ፀጉራቸውን አንጨብርውና በመናጥና በአሺሽ ጦዘው አንገታቸውን በማወናጨፍ የሚዘፍኑት ዘፈን መገኛውም እንደሆነ ማስተዋል ሞክር፡፡ የባለ ዛሮች ዝየራ አይተህ የምታውቅ ከሆነ ፍፁም ተመሳሳይ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡
ባለውቃቤዎችስ ሲደነፉ ተመልክተህ አታውቅምን? የባለ ውቃቤዎች ድንፋታ ደግሞ ቁርጥ እዋኽ፣ እዋኽ እየተባለ የሚዘፈነውን ባህላዊ ዘፈን ይመስላል፡፡ ፍከራው ቀረርቶውና በየብሄረሰብ የምትመለከተውን ዘፈንና ጭፈራ ብትመረምር ከዚህ የቀረበ መመሳሰል አታጣበትም፡፡ ቅዱስ ሐዊ እንደተናገረው ‹‹ዘፈንና ዳንስ ከሰይጣን የተገኘ›› ነውና፡፡

➨ አጋንንት ዘፋኞች ብቻ ሳይሆኑ የዘፈንና የጭፈራ ዓይነት ሁሉ ምንጮች ናቸውና፡፡ ከዚህ በኋላ የእኔ ስጋት ዘፋኞች እና ጨፋሪዎች አዳዲስ የዘፈን እና ጭፈራ መንገድ ለመኮረጅ ሲሉ አጋንንት ያደሩባቸው ሰዎች ፍለጋ በየፀበል ስፍራው መዞር እንዳይጀምሩ ነው፡፡ ምክንያቱም እንዲህ ያሉ ሰዎች የሚሹት ገንዘብንና ዝናን ብቻ እንጂ ሃይማኖት እና ምግባርን አይደለምና፡፡

➲ ለ. ክርስትያን የሆነ ሁሉ ዘፋኝነት በቅዱሳን መጻሕፍት የተከለከለ ተግባር መሆኑን ማወቅ አለበት፡፡

⚠️ ዘፋኝነት እንደ መተዳደርያ ስራም ተደርጎ መታየት የለበትም፡፡ በዘፋኝነት ‹‹ሥራ›› የተሰማሩ ክርስትያኖች በሃይማኖት ለመኖር ከወደዱ በንስሐ እንደተመለሱ ዝሙት አዳሪዎችና ቀማኞች ሁሉ እነርሱም ሌላ የስራ አማራጭ መፈለግ ይኖርባቸዋል፡፡

በዘመናችን የሐጢያት ተግባራት በሙሉ ገቢ ማግኛ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ገቢ ያስገኘ ተግባር በሙሉ ገቢ ማግኛ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ገቢ ያስገኘ ተግባር በሙሉ ግን እንደ ሙያ (ፕሮፌሽን) መቆጠር የለበትም፡፡ ‹‹መተዳደሪያዬ ነው›› እያሉ ሕሊናን የሚቆጠቁጥና መንፈሳዊነትን የሚጋፋ ስራ ከመስራት መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡ አትስረቅ አታመንዝር ያለ እግዚአብሔር ‹‹አትዝፈን›› ደግሞ ብሏል፡፡ ታዲያ በመንፈሳዊ ጎዳና ለሚመለከተው ዘፈን ከስርቆትና ከምንዝር በምን ይለያል? ሁሉም የእግዚአብሔርን ሕግ በማፍረስ አንድ ናቸውና፡፡ ምን ላድርግ? መተዳደሪያዬ ነው እያሉ በዘፋኝነት ጸንቶ ከመኖር አማራጭ መሻት ይበጃል፡፡ በዚህ ዓለም ስጦታው ዘፋኝነት ብቻ የሆነና ሌላ ምንም ዓይነት ተውህቦ (ስጦታ) የሌለው ሰው የለም፡፡ እንዲህ ቢሆን ኖሮ ፈጣሪም ዘፋኝነትን ባላወገዘ ነበር፡፡ አንበሳ ምግቡ ሥጋ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ አንበሳ ሳር እንዲበላ ማድረግ እንደማያቻል ሁሉ ዘፋኞች እንደሌላው ሰው በሌላ የሥራ ዘርፍ ተሰማርተው መኖር የማይችሉ ቢሆኑ ኖሮ ፈጣሪ ዘፋኝ አትሁኑ የሚል ትእዛዝ አይሰጥም ነበር፡፡ ስለዚህ ካሰቡበት እንደሌላው ሰው ሁሉ ዘፋኞችም ሌላ የስራ አማራጭ አላቸው፡፡

➼ ፍትሐ ነገሥት መንፈሳዊ ሥራን አስመልክቶ ሲናገር ‹‹ስለ ተግባረ እድ ግን በዓለም ከሚሠሩ ሥራዎች መንፈሳዊ ህግን ከሚቃወም ሥራ በቀር ሁሉንም ሊሰሩ ይገባል፡፡
እንደ ዘፋኝነት፣ እንደ መጥፎ ጨዋታ፣ በእግር አንደማሸብሸብ (ዳንስና ጭፈራ) ካልሆነ በቀር፡፡ ይሕ የአበው ቃል ዘፋኝነት በመንፈሳዊ እይታ እንደስራ መቆጠር እንደሌለበት ያስረዳል፡፡

➲ ሐ. ዘፋኝነት ‹‹የስጋ ስራ›› በመሆኑ ሀጥያት ነው፡፡

➣ ገላ 5፡21 ስለዚህ ዘፈን መዝፈን በመጽሐፍ ቅዱስ በእጅጉ ይከለከላል፡፡ ክርስትያኖች በመንፈሳዊ ሀሳብ መመላለስ እንጂ እንደ ዘፈን ያለውን ስጋዊ ስራ መስራት የለባቸውም፡፡ በመንፈስ ተመላለሱ፤ የስጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ›› ተብሏልና፡፡ ገላ 5:21

➲ መ. ዘፈን በመንፈሳውያን መጻሕፍት ተወግዟል ዘፋኝነትም ተከልክሏል፡፡

➣ ሐመር መጽሔት ይህን ሲያስረዳ ‹‹ዛሬ የአለም ሕዝብ የሚያዘወትረውን ዘፈን ሐዋርያት በትምህርታቸው ደጋግመውና አጥብቀው ተቃውመውታል ይላል

በእርግጥም ሐዋርያት በዲድስቅልያ ‹‹አትኩኑ ዘፋንያነ››፤ ‹‹ዘፋኝ አትሁኑ›› ብለዋል፡፡ ዲድስ አን7
ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹በቀን እንደምንሆን በአግባቡ እንመላለስ፡፡ በዘፈንና በስካር አይሁን›› ብሏል፡፡ ሮሜ 13፡13 ቅዱስ ጴጥሮስ ደግሞ " በስካር እና በዘፈን የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል፡፡" ይለናል 1ኛ ጴጥ 4፡3

➣ በላይኛው አንቀጽ በሰፈረው የሮም ክታቡ ቅዱስ ጳውሎስ ዘፋኝነትን ከዝሙትና ከስካር ጋር አስተካክሎ አስቀምጦታል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ደግሞ ‹‹በቀን ሲዘፍኑ እንደ ተድላ ይቆጥሩታል፡፡ ነውረኞችና ርኩሳን ሆነው ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣ ይዘፍናሉ፡፡›› በማለት ዘፋኝነትን የርኩሳንና የነውረኞች ተግባር አድርጎታል፡፡ 2ጴጥ 2፡13-15

➭ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እነዚህን የዘፈን ሰዎች በሌላ ማንነታቸው ሲገልጻቸው ደግሞ ‹‹ምንዝር የሞላባቸው ኃጢአትን የማይተዉ ዓይኖች አሏቸው፡፡ የማይፀኑትንም ነፍሳት ያታልላሉ፡፡ መመኘት የተለመደ ልብ አላቸው፡፡ የተረገሙ ናቸው፡፡›› ይላል 2ጴጥ2፡13-15
መጽሐፈ ሐዊ ደግሞ ‹‹ከሰይጣን የተገኘ ነውና ዘፈንንና ዳንስን ከኛ ማራቅ ይገባናል፡፡›› ይለናል፡፡ መጽ ሐዊ አን50

➨ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ደግሞ ከማዘዝ አልፎ ዘፈንን እንተው ዘንድ !"ዘፈንን ትተዉ ዘንድ እማልዳችኋለሁ" በማለት ይማፀናል (ተግ ዘዮሐ አፈ 28)

⚠️ ዘፈንን አንተውም ላሉ ደግሞ መጽሐፈ ሐዊ "በዘፈን ፀንተው የሚኖሩ ይፈረድባቸዋል" በማለት ሲያስጠነቅቅ እናገኛለን፡፡ መጽ ሐዊ አን 12 ይህ የሐዊ ቃል ሐዋርያው "የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው፡፡ እርሱም ዝሙት .. ስካር፣ ዘፋኝነት እንደነዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርሱም›› ማለት በምን ይለያያሉ

🗣 Share በማድረግ ትውልዱን እንታደግ


🔔አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ💒
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
    👆🏾𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒👆🏾

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
👍335🔥1👏1😱1
Forwarded from ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 (🤴ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ🤗)
🙏🏾ይቅርታ


ዛሬ ዲያቆን አቤኔዘር ይጽፋል ✍🏾


እግዚአብሔር ሆይ...!
አንተ በጣም ለበርካታ ዓመታት ብዙ ኃጢአት ስሰራ ዝም ብለኸኝ የተዋረድኩትን ከማንም ያነስኩትን በአንተ ክብር አከበርከኝ ዛሬ ግን ራሴን ስመለከት...


አንተ እንዳከበርከኝ እና የኔን ስራ ስመለከት በራሴ አዘንኩኝ ...!

ታዲያ ማዘኔ ብቻ ምን ይሰራል ወዳንተ ተመለስኩ ስል ድጋሜ እጠፋለሁ ጌታ ሆይ አንተ የተሰበረን ልብ ለመጠገን በንጹሕ ልብ አንዲት ቃልን ብቻ ስትሻ እኔ ግን...!😭

ብዙ ምክንያት እየፈለኩ ከፊትህ ኮብልዬአለሁና ይቅርታ 🙏🏾

አቤቱ ጌታ ሆይ ትናንት ነገን ያያል ብለው ላላሰቡ በምህረት አሳልፈህ እንደ ሰው ሳይሆን እንደ ምህረትህ ብዛት ከቤተ መቅደስህ ታቆሞኛለህ ።

ፍቅርህ ኃጢአቴን ያስረሳኛል እሱ ደሞ በውሰጤ ድፍረትን ይጭራል አምላኬ ሆይ...

ጌታ ሆይ የድፍረት ኃጢአት እንዳይገዛኝ ባርያህን ጠብቅ እንዳለ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ዛሬም እኔን ታናሽ ብላቴናህን አድነኝ።

ብዙ ኃጢአት አውቃለሁ ግን የራሴን ሳስብ ሆድ ይብሰኛል ጌታ ሆይ ይቅርታ...

የበደልኳቸውን ይቅርታ ማለት ተስኖኛልና ይቅርታ

የይቅርታ ትርጉም አልገባኝምና ይቅርታ

ፍቅርህ አልገባኝምና ይቅርታ

እያወኩህ ያውቃል ተብሎ ሲታሰብ ከሌሎች የባሰ አስቀይሜሃለውና ይቅርታ...

በልባቸው እንደ ጽላት ያኖሩህ ቃልህን በየቀኑ የሚማሩ በፍቅር የሚወዱህን ሳይ እቀናለሁ

እያወቁ እየተመለከቱ የማያውቁ እየመሰሉ ስለፍቅር ብለው ዝም እያሉ በሰዎች ግፍ እየደረሰባቸው ይቅር ሲሉ ስመለከት እቀናለሁ!

ሊገሏቸው ለሚቀምሩባቸው የህይወት መንገድን ሲጦቁሙ ሳይ እገረማለሁ እጽናናለሁ ለካ ፍቅርህ የገባቸው አሉ እላለሁ።

አምላኬ ሆይ ሌባውንም የሚሰረቀውንም
-ሰሪውንም አፍራሹንም
-ገንቢውንም ናጁንም
-አፍቃሪውንም ተጠያፊውንም
-ገዳዩንም ተገዳዩንም
-አማኙንም ተጠራጣሪውንም የፈጠርከው አንተ ነህ እኔንም ኃጢአተኛውን የፈጠርክ አንተ ነህ ግን ግብሬ እና ስሜ አንድ ጋር አልሄድ አለኝና አቤቱ ጌታ ሆይ ይቅርታ ...🙏🏾🥲🙏🏾


📌ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ

አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚

•➢ ሼር // 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄

🔔አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ💒
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
    👆🏾𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒👆🏾

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
👍129😱1💯1
Forwarded from ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 (🤴ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ🤗)
ይስራ አይስራ እርግጠኛ አይደለውም። ነገር ግን ምንም ወጪ እስከሌለው መሞከሩ ክፋት የለውም። ምንአልባት ከጠቀመን! 🎁START🧲 ይበሉት።
👍7
Forwarded from ማራናታ ᴘʀᴏⓂᴏᴛɪᴏɴ
አሁን ONLINE ላይ ላላችሁ ብቻ መንፈሳዊ ጥያቄ ና መልስ ልንጀምር ነው ገብታችሁ ተሳተፉ
👇🏾በጥያቄ እና መልሱ
1⃣ ለወጣ 500 ብር ካርድ 💸
2⃣ ለወጣ 250 ብር ካርድ 💸
3⃣ ለወጣ 100 ብር ካርድ 💸

📍👉🏾 ዝግጁ ከሆናችሁ ብቻ 💸𝐒𝐓𝐀𝐑𝐓💸 የሚለውን ይጫኑት።
👍1👏1
2025/10/26 04:38:42
Back to Top
HTML Embed Code: