Telegram Web Link
🌹🌺🌹🌺🌹🌺🌹🌺🌹🌺
ክፍል 8⃣

ፀሀፊ አቢ

#ያልተፈታ_ቅኔ

ሀምዛ ዝም ብሎ ይጨቀጭቀኛል ለሱ ምላሽ መስጠት አልፈለኩም አንድ ነገር ለማለት በሞከርኩ ቁጥር እምባ እየቀደመኝ ተቸገርኩ አንዳንዴ ህመማችንን መግለፅ ሲያቅተን ዝምታን እንመርጣለን እንዲሁም መረዳት እየቻለ መረዳት የማይፈልግም ሰው ሲገጥመን ያለንን አቅም ለማስረዳት ከማባከን እንቆጠባለን በቃ በኔ ስሜት ውስጥም የሆነው ይህ ነው ሀምዛ ሁሉንም እያወቀ ላለመረዳት ሲል ብቻ ሁሉንም ጥለን እንድንሄድ ከጥዋት ጀምሮ ይነዘንዘኛል። የምሰማውን እንዳልሰማሁ ሆኜ እያለፍኩት ነው የማታ አዳሬን እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው ለነገሩ በሱም አይፈረድም ውስጤ ምን ያክል በፍቅሯ እየነደደብኝ እንዳለና ለምን ስለሷ ሳላውቅ ይሄን ያክል እንዳፈቀርኳት አለማወቄን እንዴት ሊረዳኝ ይችላል ህመሜን በውስጤ አምቄ ዝም ማለቴንስ እንዴት ይገባዋል። በኔ ጫማ እስካልተራመደ ድረስ በጫማዬ ቀዳዳ በኩል እያለፉ ስለሚወጉኝ እሾኮችና እየረገጥኩ ስለማልፋቸው ጠጠሮች ሊረዳኝ አይችልም።
በዚ መሀል አንድ ሀሳብ ብልጭ አለብኝ ቀጥታ ወደሪሀና ዞሬ አፈጠጥኩባት የደነገጠች ትመስላለች አይታኝ በሀፍረት አንገቷን ሰበረች። ዝም ልላት አልፈለኩም
"ታውቂ ነበር አይደል?" አልኳት በጥርጣሬ አስተያየት እያየዋት
"ብ ብ ሩ ኬ አንተ እንዳሰብከው አይደለም" አለች እየተርበተበተች
"ምኑ ነው እኔ እንዳሰብኩት ማይሆነው! እ ንገሪኛ ሁሉንም እያወቅሽ የጓደኛሽን ጊዜያዊ ክፍተት እንድሞላ ለምን አደረግሽ!!? ለምንድነው ይሄን ድራማ መጫወት የፈለግሽው? እ ንገሪኛ" ብዬ ራሴን መቆጣጠር እስኪሳነኝ ድረስ ጮህኩባት ሀምዛም እስካሁን አላሰበውም መሰለኝ ይህን ሀሳብ ካነሳሁ ቡሀላ መሀል ከመግባት ይልቅ በግርምት የሚፈጠረውን መከታተል መርጧል።
" እየውልህ ብሩክ ተረጋጋና ሁሉንም ላስረዳህ" አለች ሪሀና እጄን ይዛ ልታስቀምጠኝ እየሞከረች ይበልጥ ተናደድኩባት ብሰማት ጥፋቷን ላለማመን ስትል ሌላ የውሸት ታሪክ የምትፈጥር መሰለኝ ብቻ አፌ ላይ የመጣልኝን ቃል " አስመሳይ" ብቻ ብያት ከሆስፒታሉ መውጣት ጀመርኩ ሀምዛ እየተከተለ ይጠራኛል ሪሀና ግን እዛው በቆመችበት አፏን እንደያዘች ያን የሶስት ወር ምሽጌን፣ ያን የፍቅሬን ገነት፣ ያን መኖሬን የረሳሁበትንና፣ ብዙ የሆንኩበትን ሆስፒታል ለቅቄ ወጣው።
ገና እግሬ ውጪውን ሲረግጥ ዳግም እንደማልመለስ ውስጤ ሹክ አለኝ እምባዬ ሲመጣ ደግሞ ሶስት ወር ሙሉ የረሳሁት ወንድነቴ ትዝ አለኝ በራሴ ተገርሜ ፈገግ አልኩኝና እምባዬን ዋጥ አድርጌ መንገዴን ቀጠልኩ።
ሁሌም ቢሆን ለነገሮች ጥያቄን የማያጣው ሀምዛም ዝምታዬን ተጋርቶኛል። በዝምታ ውስጥ እንደሆንን የሀምዛ ቤት ደረስን። ቁልፉን መክፈት ሲጀምር ብቻዬን መሆን እንደምፈልግ ነግሬው ልሄድ ስል እሱ ሚሄድበት እንዳለ ነግሮኝ ከፍቶ አስገባኝና ከፈለኩት እንድደውልለት አዞኝ ሄደ።
አልጋው ላይ ጋደም ብዬ አይኖቼን ጨፈንኳቸው እያንዳንዱ ነገር አንድ በአንድ ይታወሰኝ ጀመር የበፊቱ ማንነቴ ፣ፊርዱን ሳላውቃት በፊት የነበረኝ ሰላምና መረጋጋት፣ ያወኳት ቀን የተሰማኝ እንግዳ ስሜት፣ የቀጠሮው ቀን፣ ከአደጋው ቡሀላ ፊርዱን እያየው ያሳለፍኳን እያንዳንዷ ለሊት፣ ቀስ በቀስ መልኩን የቀየረው ፍቅሯ ብቻ ሁሉም ነገር ትንሽ ፈገግ አልኩኝ መልሼ ደግሞ ሁሉም ነገር ገደል ሲገባ ተሰማኝ ሁሉንም ነገር መተው እንዳለብኝ ልቤን ማሳመን ጀመርኩ ፊርዱን ልተዋት፣ ውዴን ልረሳት፣ ከሂወቴ ላሶጣት አቀድኩ መወሰን ልቻል አለመቻሌን ሳላረጋግጥ ብዙ እቅዶችን አቀድኩ........

ክፍል 9⃣
ይቀጥላል
┄┄┄┄┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄┄
:¨·.·¨:
🌺 እኔ እና እሷ🌹
┈┈••◉❖◉●••
••●◉Join us share◉●••
❤️ @Lovers_Zonn ❤️
━━━━━✦✿🌹✿✦━━━━━━━
◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
◉--ᴀʙɪ-ʙᴀʙᴀ--◉
◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
┄┄┄┄┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄┄
:¨·.·¨:
🌺 እኔ እና እሷ🌹
┈┈••◉❖◉●••
••●◉Join us share◉●••
❤️ @Lovers_Zonn ❤️
━━━━━✦✿🌹✿✦━━━━━━━
◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
◉--ᴀʙɪ-ʙᴀʙᴀ--◉
◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
​​ማንኛውም የሰው ልጅ ፈልጎ ወይም
አስቦበት አያፈቅርም! ነገር ግን በአሁኑ ስአት ማፍቀር በሁለት ይከፈላል፡፡
1 ምክኒያታዊ ማፍቅር እና
2 ምክኒያት አልባ ማፍቅር ናቸው
1 ምክኒያታዊ ማፍቅር ማለት በጥቅም ,በውጫዊ ውበት ,ብቸኝነትን ለመርሳት ,የሚወዱትን ሰው ለማስቀናት ,የሚፈልገውን እስከሚያገኘ ድረስ ...ይቀጥላል በእነዚህ ምክኒያት ያፈቀረን ሰው ሲፈልገን መጥቶ ስንፈልገው ጠፍቶ ሂወታችንን
የሚያናውጥ እና በማፍቀራችን እንድንፀፀት አልያም ፍቅርን እንድንጠላ የሚያደርገን አፍቃሪ ነው።
2 ምክኒያት አልባ ማፍቅር ማለት ሳያስብበት (ሳይዘጋጅበት ) በአጋጣሚ እራስን በማያውቁት ቦታ ውስጥ ሰምጦ ማግኘት ነው። የት ? እንዴት ? መቼ ?ለምን ? =መልስ የለም ! ብቻ የልብ ትርታን ነው፡፡ የሚያዳምጠው በደስታም ይሁን በሀዘን ሁሌም ከሚያፈቅረው ሰው ጎን አይጠፋም ከእሱ ደስታ ይልቅ ያፈቀረውን ሰው ደስታ ይመርጣል ,ፍቅር መስጠት እንጂ መቀበል አይሻም
እየተጠላ ይወዳል ,እየተራቀ ይቀርባል ይህ ነው ምክኒያት አልባ ፍቅር ።
እናም አፍቃሪም ይሁን ተፈቃሪ ከምክኒያታዊ ( ግዜአዊ ) ፍቅር ይልቅ ምክኒያት አልባ (ዘላቂ)ፍቅርን መረዳት ቢችል መልካም ነው እላለሁ እናንተስ? ምን ትላላቹ ሀሳባቹን ከስር ባለው Account ላኩልኝ።

@kana_ze_gelila_12


┄┄┄┄┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄┄
:¨·.·¨:
🌺 እኔ እና እሷ🌹
┈┈••◉❖◉●••
••●◉Join us share◉●••
❤️ @Lovers_Zonn ❤️
━━━━━✦✿🌹✿✦━━━━━━━
◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
◉--ᴀʙɪ-ʙᴀʙᴀ--◉
◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
ክፍል 9⃣

ፀሀፊ አቢ

#ያልተፈታ_ቅኔ

ቀናት ቀናትን እየወለዱ ሳምንታትን ማስቆጠር ጀምረዋል ባዲስ መንፈስ ወደስራዬ ከተመለስኩ አራተኛ ቀኔን አስቆጥሪያለው። ጥዋት ወጥቼ ራሴን በስራ ጠምጄ ውዬ ማታ እገባለው። ስለፊርዶስ ከሰማው በጣም ቆየው ቢሆንም ግን ሁሌ አስባታለው ለሀምዛ እንደምረሳት ቃል ስለገባሁለት እሱ ፊት የረሳዃትና ደስተኛ የሆንኩ አስመስላለው ይሁን እንጂ ፊርዱ ለሰከንድ ከአይምሮዬ ጠፍታ አታውቅም ሁሌ አስባታለው በርግጥ ከነበረችበት ሆስፒታል አገግማ መውጣቷንና የአክስቷን ቤት ትታ ሙባረክ ጋር እንዳረፈች ከሪሀና ሰምቻለው ነገር ግን ሀምዛ ከሪሀና ጋር እንደምደዋወል አያውቅም ስልኳንም በድብቅ ነው ከስልኩ ላይ የወሰድኩት አላስችል ሲለኝ ስለደህንነቷ ደውዬ እጠይቃታለው ዛሬም ከስራ መልስ ልደውልላት አስቢያለው።
ምሳ ሰአት ደርሶ ስለነበር ከሀምዛ ጋር ምሳ ለመብላት ወደ ምግብ ቤት ሄድን ምግቡን ካዘዝን ቡሀላ እስከሚመጣ ድረስ ሀምዛ የባጥ የቆጡን ይለፈልፋል በሱ ቤት እኔ እንዳይደብረኝና አሪፍ ሙድ ላይ እንድሆን በማሰብ ነበር ይህንን ማድረግ ከጀመረም ቆይቷል ነገር ግን እኔ ጋ ምንም አዲስ ነገር የለም ሊኖር የሚችለው ፊርዱ ስትኖር ብቻ ነው ያው ቃሌን ያከበርኩ ለመምሰል ያወራውን ሳልሰማ ሲስቅ ብቻ አብሬው እስቃለው ሀሳቤ ሌላ ጋር ቢሆንም ትኩረቴ እሱ ጋር ያለ አስመስላለው እሱም ብዙም አይጫነኝም ይሁን እንጂ ያ አሰልቺ የማያልቅ ጥያቄው ዛሬም ድረስ አለ ሁሌም ቢሆን ለሚወራው ነገር ጥያቄ አያጣም ምንም ባልመልስለትም ሲጠይቀኝ ገና ይደክመኛል።
በዚ ሁኔታ ውስጥ ሆነን ምሳችንን ከበላን ቡሀላ ወደስራ ገባን።
ከሰአት ቡሀላ አብዛኛውን ጊዜ ገበያ አይኖረንም ያው ተዘጋ ላለመባል ብቻ ሱቅ ውስጥ እንገኛለን። ሰአቱም ወደማምሻው እየተቃረበ ነው ፀሀይ ወደመግቢያዋ ተቃርባለች በጊዜ መግባት ስለፈለኩ ሱቁን ዘግቶ እንዲመጣ ለሀምዛ ነግሬው ጃኬቴን ደርቤ ከስራ ወጣሁ።
ስልኬ ካርድ ስላልነበረው አካባቢው ላይ ካገኘሁት ሱቅ ካርድ ገዝቼ ሞላሁና በቀጥታ ለሪሀና ደወልኩላት ነገር ግን ስልኳን አታነሳም ደግሜ ደወልኩ አሁንም አይነሳም እቤት ገብቼ እደውላለው ብዬ መንገዴን ቀጠልኩ። ብዙም ሳትቆይ ሪቾ ደወለች አነሳሁት እና "ቅድም እኮ ስደውልልሽ አታነሺም በሰላም ነው?" አልኳት
"አዎ በሰላም ነው የት ነህ?"
"ከስራ ወደቤት እየገባሁ ነው ምነው"
" ምንም ሀምዛ አብሮክ አለ እንዴ?"
"እረ የለም እሱ ቆይቶ ነው ሚገባው ደግሞም በሱ ፊት እንዴት እደውላለው?"
"እሺ በቃ እቤት ስትገባ ደውልልኝ" ብላኝ ስልኩን ዘጋችው። ሁኔታዋ ግራ ስላጋባኝ መልሼ ደወልኩላት ሳይነሳ ዘጋችው። ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ እየጓጓው የእርምጃ ፍጥነቴን ጨምሬ እቤት ደረስኩ። እንደገባው ቀጥታ ደወልኩላት መስመሩ ተይዟል ይላል ስልኳ ጭንቅንቅ አልኩኝ መልሼ ስደውል አነሳችው
"ሄሎ ሪች"
" እ ብሩኬ ገባህ?"
"አዎ ምንድነው ቆይ?"
" መጀመሪያ ተረጋጋ ከዛ ዝም ብለህ አዳምጠኝ"
"ምንድነው እሱ ፊርዱ ደና አይደለችም እንዴ?"
" አዎ ህመሙ ትንሽ ስለባሰባት በድጋሚ ሆስፒታል ገብታለች"
" ምን! ቆይ የት ሆስፒታል ነው ንገሪኝ አሁኑኑ እመጣለው"
"አሁን መምጣት የለብህም ባይሆን ሌላ ቀን ሀምዛ ካወቀ ያዝንብሀል ተረጋግተህ እደር እኔ ያለችበትን ሁኔታ በየሰአቱ ቴክስት አረግልሀለው አትጨነቅ አሁን ስልኩን መዝጋት አለብኝ ደና እደር"
" ቆይ አንዴ ሄሎ.........ሄ ሄሎ" ዘጋችው።
ስልኩን እንደያዝኩኝ ፈዝዤ ቀረሁ ይሄ ነገር መቼ ነው ሚያበቃው? ብዬ ራሴን ጠየኩ ምን ማድረግ እንዳለብኝ እንኳን አላውቅም ፈጣሪ ግን ምን አድርጌው ነው ይሄን ያክል የሚቀጣኝ አልኩኝ
የማታውቀኝ ፍቅሬ በድጋሚ ታማ ሆስፒታል ነው ያለችው እኔ ደግሞ እቤት አልጋዬ ላይ ኡፍፍፍፍ እንዴት ይጨንቃል። በዚ ሁኔታ ውስጥ እንዳለው ሀምዛ መጣ ተነስቼ በሩን ከፈትኩለትና ገባ
"እራት በላህ? ወይስ ወጥተን እንብላ?" አለኝ ጫማውን እያወለቀ
"በልቻለው አንተ በልተህ ና" አልኩትና ፊቴን እንዳያየው ከፊቱ ዞር አልኩኝ
" እኔማ ቅድም የበላነው ራሱ አልተወራረደልኝም ግን አንተ ምን ሁነህ ነው ዛሬ ችግር አለ እንዴ?"አለኝ
ኤጭ ጀመረው ደሞ እያልኩኝ በውስጤ
" ትንሽ ራሴን አሞኝ ነው ስተኛበት ይተወኛል" አልኩት
ዝም አለኝና መሳቢያው ውስጥ የሆነ ነገር ማንኮሻኮሽ ጀመረ ከትንሽ ቆይታ ቡሀላ " እንካ ይሄን ውሰድበት ይተውሀል" ብሎ ፓራሴታሞልና ውሀ ሰጠኝ ትቀበልኩትና ለማረሳሳት ያክል ስልኬን አቀብለኝ ብዬው ሲዞር ክኒኑን ኪሴ ውስጥ ከተትኩትና ውሀውን ጠጥቼ ብርጭቆውን ሰጠሁት " በል ተሸፋፍነህ ተኛ ነገ ካልተሻለህ ሀኪም ቤት እንሄዳለን" ብሎኝ ብርጭቆውን ሊመልስ ሄደ "ውይይይይይ ሀምዛ" እያልኩ ስልኬን አንስቼ ለሪቾ " አሁን እንዴት ናት" ብዬ ቴክስት አረኩላትና ቴክስት ስትልክ እንዳይሰማ ስልኬን ሳይለንት አደረኩት። ከደቂቃዎች ቡሀላ መለሰችልኝ " እስካሁን አልነቃችም ዶክተሮቹ ጭንቅላቷ ውስጥ ደም መፍሰሱን ነግረውናል እና ቀዶ ጥገና ሊደረግላት ነው ከ 2 ሰአታት ቡሀላ ወደ ሰርጀሪ ክፍል ያስገቧታል" አለቺኝ የምይዘው ጠፋኝ ፊርዱ አሳዘነቺኝ ይሄኔ ባንተዋወቅ ኖሮ ይሄ ሁሉ ነገር አይፈጠርም ነበር ራሴን አምርሬ ጠላሁት በሷ ቦታ እኔን ባረገኝ ብዬ ተመኘው ሁሉንም ነገር ጥዬ መጥፋት አማረኝ ግን ወዴት?
ለሪቾ "እባክሽ የሆስፒታሉን አድራሻ ንገሪኝ ነገ ልምጣ?"
ብዬ ፃፍኩላት እና ምላሿን መጠበቅ ጀመርኩ ነገር ግን ምንም ምላሽ የለም ለሊቱን ሙሉ ምላሿን ስጠብቅ አደርኩ።
ጥዋት ሀምዛን ስራ እንዳይረፍድበት ቀሰቀስኩትና ትንሽ ማረፍ እንደምፈልግ ነግሬው ለቦስ ትንሽ እንዳመመኝና የኔን ቦታ እንዲሸፍን አሳምኜው ወደስራ ላኩት። ገና እንደወጣ በቀጥታ ለሪቾ ደውልኩላት ብዙም ሳይጠራ አነሳችው
"ሄሎ ብሩክ አለች ሪቾ በደከመ ድምፅ"
" ሄሎ ሪች ፊርዱ እንዴት ሆነች?"
"አሁን ነቅታለች ግን ዶክተሮቹ የመዳን ተስፋዋ የመነመነ እንደሆነ ነግረውናል ሙባረክም ነገ ወደመጣበት ሀገር ሊመለስ ነው ብሩኬ ግራ ገብቶኛል" አለችኝ እምባ በተቀላቀለው የሲቃ ድምፅ
" እንዴት ማለት? ባክሽ ሲቀልዱ ነው ቆይ ድና አልነበር እንዴ? አትመኛቸው እነሱን ቶሎ ይሻላታል እመኚኝ". አልኳት ምን እንደማወራ እንኳን በቅጡ አላውቅም ብቻ በድጋሚ የሆስፒታሉን አድራሻ ስጠይቃት ልትሰጠኝ ፍቃደኛ አልሆነችም ግራ እየገባኝ ስልኩን ዘጋሁና እንደእብድ ከራሴ ጋር ማውራት ጀመርኩ ፊርዱ የኔ ምን ሆንሽብኝ? የኔ ንግስት ምን አገኘብኝ? ሳታውቂኝ ብዙ አወኩሽ ሳትነኪኝ ብዙ ዳበስኩሽ ሳታይኝ አፈቀርኩሽ ታድያ ምን አጥፍቼ ነው ጥለሺኝ ለመሄድ መንገድ የጀመርሽው? ማፍቀሬ ጥፋት ነበር እንዴ? አታደርጊውም! በጭራሽ አታደርጊውም እያልኩ በሚያቃጥል እምባ ብቻዬን ታጠብኩ ከአካሌ ላይ አንድ አካል የጎደለ መስሎ ተሰማኝ ሞት አሰኘኝ ከፊርዱ መቅደም አማረኝ ሌላ ምንም አልፈለኩም ይሄን የስቃይ አለም በራሴ ፍቃድ ልገላገለው ወሰንኩ ትክክለኛ ውሳኔ መሆኑን ለልቤ ነግሬ ከውደኩበት ተነሳሁ......

ክፍል🔟
ይቀጥላል....
ክፍል 🔟

ፀሀፊአቢ

#ያልተፈታ_ቅኔ

አንድም ቀን እቅዴ ተሳክቶልኝ አያውቅም ደና ልገላገላት የነበረችውን አለም ሀምዛ በግድ እንድኖራት ፈረደብኝ ከሞት አፋፍ ላይ አስጥሎ ዳግም ወደ ህይወት አመጣኝ ደሞኮ የሚገርመኝ ሁሉንም ነገር እያየ የሚጠይቀኝ ነገር ነው። በጣም እንደተናደደብኝ ያስታውቃል እኔ ግን በስራዬ ቅንጣት ታክል ሀፍረትም ሆነ ስህተት የሰራሁ መስሎ አልታየኝም እንደውም ከሰአታት በፊት ለምን እንዳዳነኝ ተናድጄ ስጮህበት ነበር። ብቻ ሁሉም አለፈና የሚሰለቸው የሀምዛ ጥያቄ ጀምሯል
" ለምን እንዲ ማድረግን መረጥክ እኔንስ ለማን ትተህ ነው ይሄን የማይረባ ውሳኔ ልትወስን የቻልከው ቆይ እስኪ ንገረኝ ላንተ መሞት ቀላል ነው እንዴ?" አለኝ ሀምዛ በርግጥ ለአንዱም ጥያቄው መልስ አልነበረኝም "ቆይ አንተ ስራ አልነበርክ እንዴ እንዴት ልትመጣ ቻልክ?" አልኩት አጋጣሚው እየገረመኝ
" ከኔ ልትደብቅ ሞከርክ እንጂ ሁሉንም አውቅ ነበር ያላወኩ የመሰልኩት አንተን ላለማሳቀቅና ቢያንስ እኔ ጎን ስትሆን የረሳሀት መምሰልህ ትንሽ ሊጠቅምህ ይችላል ብዬ ስላሰብኩ ነው እንጂ ሁሉንም ነገር አውቃለው ማታ ተኝተህ ስልክህን አይቼው ነበር ይሄን ልታስብ እንደምትችል ስለገባኝ ነው የተፈጠረውን ለቦስ ነግሬው የተመለስኩት" አለኝ ፊቱን ጭፍግግ አድርጎ
ምን እንደምለው ግራ ገባኝ " በጣም ይቅርታ ሀምዚ አንተ ትለያለክ" ብዬ አቀፍኩት
" ድጋሚ እንደዚ አይነት ነገር ብታስብ ቀድሜ ነው እሺ ምገልህ" ብሎ አሳቀኝ
በል አሁን ተነስ ፊርዱ ያለችበትን ሆስፒታል እኔ ስለማውቀው በቀጥታ መሄድ እንችላለን ብሎኝ ስልኬን ኪሴ ውስጥ ከተትኩና ወደሆስፒታሉ አመራን በመሀል ለሪቾ ደውለንላት ነበር ነገር ግን አታነሳም።
ሆስፒታል እንደደረስን ሂሳብ ከፍለን ከታክሲው ወረድንና ወደ ውስጥ አቀናን። የተኛችበትን ክፍል አጠያይቀን መግባት ጀምረናል ልክ ስንደርስ የፊርዱን አክስትና ሪቾን እያለቀሱ አገኘናቸው በድንጋጤ ውስጥ ሆኜ "ምንድነው" አልኳት ለሪቾ ምንም ሳትመልስልኝ ከፊርዱ ክፍል ሁለት ዶክተሮች ወጡ በቀጥታ አጠገባቸው በመሄድ "ድናለች አይደል? እንውሰዳት?" እያልኩ ጥያቄን በጥያቄ ማከታተል ጀመርኩ
"" በጣም እናዝናለን ብዙ ሞከርን ግን ህይወቷን ማትረፍ አልቻልንም ፈጣሪ ብርታቱን ይስጣቹ"" አሉን ቀለል አርገውት የሰማሁትን ማመን ከበደኝ እግሮቼ መቆም አቃታቸው ተብረክርኬ ወደኩ ምንም የማለት አቅምን አጣው ብቻ ዝም ብዬ የሚፈጠረውን ማየት ብቻ ሆነ ስራዬ እምባዬም የት እንደገባ አላውቅም ድምፄም መውጣት አቃተው ዝምታን ለብሼ ዝምታን ጎርሼ እንደምንም ከወደኩበት ተነስቼ እግሬ ወደመራኝ አቅጣጫ መጓዝ ጀመርኩ ሀምዛ እጄን ይዞ ወደፊት መምራት ጀመረ እቤት አስገብቶኝ አጠገቤ በዝምታ ተቀመጠ እሱም ምን ማለት እንዳለበት ራሱ ግራ ሳይገባው አልቀረም ቀና ብዬ ሳየው ፊቱ በእንባ ታጥቦ ይመለከተኛል ከተቀመጥኩበት ወደ መሬት ዝርግፍ አልኩኝ ያኔ ነው እንባዬ የመጣልኝ እየጮህኩ እዬዬዬ ማለት ጀመርኩ አንዳንዴ አልቅሰን የሚድኑልን ህመሞች በማባበል ሊሽሩ አይችሉም ሀምዛም ለዛ ነው እንዳለቅስ የፈቀደልኝ አቅሜ እስኪዳከም ድረስ አለቀስኩ ማመን አለብኝ ግን ደሞ ይሄን ሊያምንና ሊቀበል የሚችል ጥንካሬ የለኝም ሁሉም አካላቶቼ አልታዘዝ አሉኝ ብቻ እዛው እንደተዘረገፍኩ መሸ ሀምዛ ደግፎ አልጋ ላይ አስተኛኝና የሚበላ ነገር ሊያመጣልኝ ሄደ።
ብዙም ሳይቆይ ምግቡን ይዞ መጣና መብላት እንዳለብኝ ደጋግሞ ማሳመን ጀመረ።
"በቃ ከዚ በላይ ማዘን የለብህም ፈጣሪ ያለው ነው የሆነው እንዲ ነበር የተፃፈው" አለኝ ሀምዛ
ምግቡን በሳህን እያቀረበ
አንድ ጉርሻ አንስቶ ወደኔ እጁን ዘረጋ ገና ምግቡን ሳየው አስጠልቶኛል እንኳን ልበላ ይቅርና ፊቴን በማዞር የመብላት ፍላጎት እንደሌለኝ ነገርኩት ሊጫነኝ ስላልፈለገ ውሀ ብቻ ጠጥቼ እንድተኛ አደረገ።
ቀናት ቀናትን እየወለዱ ፊርዱ ከዚ አለም ከተለየችና እኔም ካልጋ መነሳት ካቆምኩ ሳምንትን አስቆጠሩ ከቀናት ቡሀላ ሪቾ ልትጠይቀኝ መጣች ገና ሳያት እምባዋን ማፍሰስ ጀመረች ከራሴ እምባ ጋር እየታገልኩ "አታልቅሺ"ብቻ አልኳት ትንሽ ከቆየች ቡሀላ የምትሄድበት ቦታ እንዳለ ነገረችኝና ፊርዱ ከመሞቷ በፊት ለኔ የፃፈችውን ወረቀት ሰጥታኝ ተሰናብታን ሄደች።
ግራ ገባኝ ፊርዱ እኮ እኔን አታውቀኝም እንዴት ፃፈችልኝ ብቻ ጥያቄዬን አቁሜ ደብዳቤውን በፍጥነት ከፈትኩት ደብዳቤው እንዲህ ይላል

#ሰላም ላንተ ይሁን ብሩኬ......

ክፍል1⃣1⃣ እና የመጨረሻው ክፍል
ይቀጥላል.......



┄┄┄┄┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄┄
:¨·.·¨:
🌺 እኔ እና እሷ🌹
┈┈••◉❖◉●••
••●◉Join us share◉●••
❤️ @Lovers_Zonn ❤️
━━━━━✦✿🌹✿✦━━━━━━━
◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
◉--ᴀʙɪ-ʙᴀʙᴀ--◉
◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
ክፍል 1⃣1⃣
#የመጨረሻው_ክፍል

ፀሀፊ አቢ

#ያልተፈታ_ቅኔ

ሰላም ላንተ ይሁን ብሩኬ እንዴት ነህ? እኔ እንኳን ስላንተ ከሰማሁ ቡሀላ ከበፊቱ ይልቅ ደህንነት እርቆኛል ምናልባት ሳላውቅ እንዳስቀየምኩህ አውቀህ ናፍቄህ ትመጣለህ ብዬ በር በሩን ሳይ ውዬ አድራለው። ያንተን ያህል ባይሆንም በስቃይ ውስጥ ሆኜም በብዙ አስቤሀለው። ይህንን ደብዳቤ እስከፃፍኩባት እለት ድረስ በይመጣል ተስፋ ስጠብቅህ ነበር ነገር ግን አንተ አልመጣህም የኔም ደህንነት ከቀን ወደ ቀን እየጠፋ ሄዷል።

ብሩክ ምናልባት ይሄ ደብዳቤ ቆይቶ ሊሆን ይችላል የሚደርስህ ቢሆንም ግን እንድታውቀው የምፈልገው ነገር አለ።
በርግጠኝነት አንተ ምታስበው የቀጠሮው ለት ወዳንተ ስመጣ ይሄ ሁሉ ነገር እንደተፈጠረ ነው አይደል?? ግን እንደዛ አይደለም ያንተን ቀጠሮ ሰርዤ የ ሙባረክን ቤተሰቦች ለማየት እና እኔ ጋር መልእክት ስለነበራቸው እሱን ላደርስ እየሄድኩ ነው አደጋው የደረሰው። ስለዚህ አንተ ራስህን እንድትወቅስ የሚያደርግህ ምንም ነገር የለም። ደሞ ሳልነግርህ ሙባረክ ማለት በቤተሰብ የተመረጠልኝ እጮኛዬ ነበር ነገር ግን አሁን የመጣው ባለበት ሀገር ሌላ ቤተሰብ እንዳለው ሊነግረኝ ነው። ለሱም ቢሆን እንዲ ስለሆነለት ፈጣሪዬን አብዝቼ አመስግኜዋለው ቢያንስ ቢያንስ በኔ ምክንያት ህይወቱ አይበላሽም ልክ ነኝ አይደል??

ደሞ ሪቾ ቀድማ ሁለንም ነገር ስላልነገረችህ እንደተናደድክባት ነግራኛለች። ሁሉንም ያልነገረችህ ላንተ አስባ ነው አትቀየማት እሺ
ሌላው ደግሞ አይኔን ሳልገልጥ ላደረክልኝ እና ለሆንክልኝ ነገር በጣም ነው ማመሰግነው ፈጣሪ ብሎ ድኜ ውለታህን መመለስ ብችል ደስ ይለኝ ነበር ግን ያ የሚሆን አይመስለኝም እኔም ብሆን የመዳን ተስፋዬ ተሟጦ መሞቻዬን ቀን እየጠበኩ ነው።

ብሩኬ አንዳንዴ ይሆናል ብለን የጠበቅነው ፍፁም ተቃራኒው ሆኖ ስናገኘው የምንይዘው የምንጨብጠውን እናጣለን ሁሉም ውሸት ይመስለናል ግን እውነታው ይሄ ነው።

ሁሉም ነገር ለበጎ ነው።

ከፊርዶስ

አንብቤው እንደጨረስኩ እምባዬን ዘረገፍኩት ለካ ፊርዱ እንደምትሞት ታውቅ ነበር፣ ለካ እሷ ጠብቃኝ ነበር ለምን አልሄድኩም? በፈለገቺኝ ሰአት ለምን ከጎኗ አልነበርኩም? እሱም ለበጎ ነው?? ከእለታት አንዱ ቀን ያገናኘን አምላክስ እንዲ ነው የሚለያየን? አልኩት ሀምዛን ቀና ብዬ......አይቶኝ አንገቱን ደፋ እኔም ወረቀቱን እንዳቀፍኩኝ ከተኛሁበት አልጋ ላይ ለመነሳት እግሬን ማነቃነቅ ጀመርኩ ሀምዛ በደስታና በድንጋጤ ውስጥ ሆኖ በፍጥነት እንድነሳ ይረዳኝ ጀመር.....ከብዙ ጥረት ቡሀላ በእግሬ ቆምኩ ሀምዛ ዘሎ አቀፈኝ ሁለታችንም ተቃቅፈን አለቀስን ህመሜ በእንባ ታጥቦ ይወጣ ይመስል ለጉድ አነባሁ። በዚ ሁኔታ ቀኑ መሽቶ ነጋ ለሊቱን ሙሉ ሳልተኛ አደርኩ ጠዋት ሀምዛን ቅሰቀስኩትና ስራ እንዲሄድ ካደረኩ ቡሀላ ልብሴን ቀያይሬ በቀጥታ ፊርዱ ቀጥራኝ ወደቀረችበት ሆቴል አመራሁ እንደደረስኩ ያኔ የተቀመጥኩበትን ቦታ በአይኔ ስቃኘው ሰው አልተቀመጠም በቀጥታ ሄጄ ወንበሩን ስቤ ተቀመጥኩኝ።
አስተናጋጇ መጥታ "ምን ልታዘዝ" አለችኝ ቀና ብዬ አየዃት ያኔ የታዘዘቺኝ ልጅ ነበረች
"ውሀ" አልኳትና አንገቴን ደፋሁ። ብዙም ሳትቆይ ውሀውን አመጣችልኝ። ከፍቼው አንድ ተጎነጨውና ከኪሴ እስኪርብቶ እና ማስታወሻ ደብተሬን አውጥቼ መሞነጫጨር ጀመርኩ


ለምን እንዲ ሆነ ማነው ሚጠየቀው፣
ያፈቀረሽ ልቤ? ወይስ እኔን ሳያውቅ የሞተው ልብሽ ነው።
ማነው ጥፋተኛው ተከሶ ሚቀጣው፣
የቀረበሽ ገላ? ወይስ እንቅልፍሽ ነው።
ንገሪኝ ማንስ ነው ሀይማኖቱን ገፍቶ ፍቅርን ያከበረ፣
ያዩሽ አይኖች ናቸው? ወይስ ልብ የሚሰርቅ ውበትሽ ነበረ።
እስኪ በይ ንገሪኝ ፅድቅ የሰራው ማነው ማንስ ሀጢያተኛ፣
ያጠፋውን ቀጥቶ ማነው የሚፈርደው ተከራክሮ ለኛ።
በእምባ መራቅ የለም ብቻ አላውቅልሽም፣
ከእለታት ባንዱ ቀን ላፈቀረሽ ልቤ ምላሽ አልሰጠሽም፣
ሲያስብሽ ውሎ ላደረልሽ ገላ ትንሽ አላዘንሽም፣
ትተሺኝ ስትሄጂ ላልኖር እንደምችል እንዴት አላሰብሽም
ብቻ አላውቅልሽም።

የፃፍኩትን ደግሜ ለራሴ አነበብኩት ትንሽ ፈገግ አስባለኝ ያኔ የፊርዱን ስልክ
#ያልተፈታ_ቅኔ ብዬ ሴቭ ያረኩት ትዝ አለኝ። እውነትም ያልተፈታሽ ቅኔ ነሽ አልኩ በልቤ። ድንገት የእጅ ሰአቴን ሳየው ነው ብዙ እንደቆየው የገባኝ ማስታወሻዬን ከደንኩትና ሂሳቤን ከፍዬ ከሆቴሉ በቀጥታ ወጣሁ።


ተፈፀመ

እንዴት ነበር ታሪኩ😀
👍4
#የውሸት_ፍቅር_ላይ፦ አብሮህ ላለመቆየት ፈልጎ
ሁሌም ስህተቶችህን የሚፈልግ ሰው እንዳለ ሁሉ?
#እውነተኛ_ፍቅር_ላይ፦ አንተን ላለማጣት ሲል ብቻ
ዘወትር ለስህተቶችህ እውር የሚሆንም ሰው አለ!
ፈጣሪ የናንተ የሆነውን እውነተኛ ፍቅር ይስጣችሁ።

#Abi🍁


┄┄┄┄┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄┄
:¨·.·¨:
🌺 እኔ እና እሷ🌹
┈┈••◉❖◉●••
••●◉Join us share◉●••
❤️ @Lovers_Zonn ❤️
━━━━━✦✿🌹✿✦━━━━━━━
◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
◉--ᴀʙɪ-ʙᴀʙᴀ--◉
◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
👍1
መናገርና🌬 መፃፍ ከምችለው በላይ🤦‍♀ የቃላቶች ጋጋታ🙇‍♀ ከሚገልፁት በላይ ነው የናፈከኝ🤴 ግን ላይህ👀 አልመጣሁም🚶‍♀ ያ ሰው👩👨 ማየት👀 አስጠላኝ እና አልመጣሁም 🚶‍♀😞መጥላት ስልህ ያው መራቅ🚶‍♀ መርጬ እንጂ ሌላ ነገር አስቤ🤔 አደለም በማይሆን ሰአት መጣህ በዝምታ 🤐 አትመተጣም ብዬ መኖርን🧍‍♀ ቀጥዬበት ነበር😒 እድሉን አግኝቼ😊 እንደጎዳሀኝ በጎዳውህ እላለው🥺 ግን እኔንጃ 🤷‍♀ እድሉንም ባገኝ ማደርገው 😒ግን አይመስለኝም🙅‍♀ ያው ታውቅ💁‍♀ የለ ሰው መጥላት አልችልም🙇‍♀ አንተን 🤴ደሞ መጣላት እና መጉዳት ማይታሰብ🤔🥺 ነው የወደድኩህ 😍መስፈርት አውጥቼ አልነበረም🤷‍♀ እንዲ አርግና🤔 ሁን ብይህ አላቅም አደል😳 ላንተ ያለኝን ስሜት 🥰 አንተ🤴 ብቻ ሳትሆን እኔም👸 አይገባኝም🤷‍♀ ተመፃደኩብህ እንዴ🤔 በርግጥ ፊትህ ቆሜ🧍‍♀ እንዲህ እንደማልልህ እና አቅሙም እንደሌለኝ ታውቃለህ🙇‍♀ ያው በፁሁፍ ስለሆነ ቀሎኝ እንጂ🙁 እሱ🤴 እየጠራሁት🌬 አይሰማኝም🙉 እየነገርኩትም🌬 ቢሆን አይረዳኝም🤷‍♀😞 ለዛም ነው ከሰው👱‍♀👱‍♂ ጋር መኖር 🏠አሁን ላይ ሚከብደኝ☹️ ሁሉም እንዳንተ🤴 ነው ሚመስለኝ😊 እሚመጣ🚶‍♀ እንጂ እማይደርስ🚶 ያለሁበት መንገድ🛣 ዳር ጥንድ👩‍❤️‍👨 ጥንድ👩‍❤️‍👨 ሆነው ፍቅረኛሞች❤️ መንገዱን🛣 ሞልተውታል 🥺በነሱ አልቀናም😔 እኔ 👸በጀመሩ ሳይሆን በጨረሱ ነው ምቀናው😍😞 እኔም👸 ብዙ ጊዜ ጀምሬ ነበር💔 ግን በቃ🤷‍♀ የእውነት አልነበረም😭 ግን አንድ ቀን አይቀርም😞 እኔም👸 ትልቅ ሰው እሆናለው ትልቅና ደስተኛም😂 ቤተሰብ👨‍👩‍👧‍👦 ይኖረኛል እያየዋቸው👀 ነገሮች ቀስ በቀስ መልካቸውን መቀየረራቸውን ቀጠሉበት🤷‍♀ ቢሆንም ግን ዛሬም ተመስገን🙏 እግዚአብሔር ለምን አይቀጣም ወይም አይፈርድም አትበል🙅‍♀ መቅጣት እና መፍረድ ከጀመረ እማ ካንተ 👨ነበር የሚጀምረው።

@Atni16 🥀💔


┄┄┄┄┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄┄
:¨·.·¨:
🌺 እኔ እና እሷ🌹
┈┈••◉❖◉●••
••●◉Join us share◉●••
❤️ @Lovers_Zonn ❤️
━━━━━✦✿🌹✿✦━━━━━━━
◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
◉--ᴀʙɪ-ʙᴀʙᴀ--◉
◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
2👍1
Forwarded from ᴋᴀʟɪɴᴀ 🚩 (🦋ᴋᴀʟɪɴᴀ)
Wendoche love sizachw endelj yhonalu mibalw history ewnt nw 😂

- የምታፈቅራትን ልጅ online እያየሀት የምታወራው ይጠፋብሀል😔

- በአካል ስታገኛት ደግሞ ከማፈርህ የተነሳ ሰላም አትላትም😔

- እሷን hi ብለሀት እሷ ignore asebw misemahn🙆‍♀

Letewat belh setwesn esua metmexaws negr🙆‍♀😂😂😂

@kalina_kitaye💚
❤️🌺

ፍቅር ያልተለመዱ ህጎች ያለው ጨዋታ ነው ከሚገባው በላይ ትሸነፋለህ ካሰብከውም በላይ ታፈቅራለህ
#ታድያ እውነተኛ ፍቅር ባፈቀሩት ሰው ድክመት እየተጠቀሙ መጉዳት አይደለም።
#‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌atni


┄┄┄┄┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄┄
:¨·.·¨:
🌺 እኔ እና እሷ🌹
┈┈••◉❖◉●••
••●◉Join us share◉●••
❤️ @Lovers_Zonn ❤️
━━━━━✦✿🌹✿✦━━━━━━━
◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
◉--ᴀʙɪ-ʙᴀʙᴀ--◉
◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
ምናልባት ከኔ መለየቷ አስደስቷት ይሆናል..አዝናም ሊሆን ይችላል።
እኔ ግን ሄጃለው.... መሄዴም አይቆጭኝም....ደሞም ለምን እንደማይቆጭኝ ታውቂያለሽ..???
በውሸት አንደበት አልቀረብኩሽም።
ሰው ሁሉ ቢርቅሽም፣ እኔ ግን
ካጠገብሽ አልጠፋሁም።
ባጠፋም ይቅርታ ጠይቄሻለው።
ቃል ገብቼ አልተውኩም...ቃሌንም ሞልቻለው። በሱም ደስተኛ ነኝ።

ላንቺ ግን ከፋኝ... የፍቅር ትርጉሙ ላልገባሽ፣ ወዳዘነበለበት ምትወድቂ። ያጀበሽ ሁሉ የዘላለምሽ ሚሆን የመሠለሽ። ትላንትን ረስተሽ ያንቺ ያልሆነው ነገን ለምትመኚ።
ብቻ ምንም ምልሽ ነገር የለኝም።
ምክር እና ይቅርታ ለሚያስተውል ሰው ነው።።።።

ማን እንደሆንኩ ታውቅያለሽ፣፣፣



┄┄┄┄┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄┄
:¨·.·¨:
🌺 እኔ እና እሷ🌹
┈┈••◉❖◉●••
••●◉Join us share◉●••
❤️ @Lovers_Zonn ❤️
━━━━━✦✿🌹✿✦━━━━━━━
◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
◉--ᴀʙɪ-ʙᴀʙᴀ--◉
◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
🍁🌹....
ለአንዳንድ ሰዎች ፍቅር ማለት አፍቅሬሻለው ስትላቸው እኔም ብሎ መመለስ ብቻ ይመስላቸዋል።


┄┄┄┄┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄┄
:¨·.·¨:
🌺 እኔ እና እሷ🌹
┈┈••◉❖◉●••
••●◉Join us share◉●••
❤️ @Lovers_Zonn ❤️
━━━━━✦✿🌹✿✦━━━━━━━
◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
◉--ᴀʙɪ-ʙᴀʙᴀ--◉
◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
ማውራት ፈልገህ ነገር ግን ማውራት እንደሌለብህ አውቀህ ዝምታን ከመረጥክ እመነኝ የመኖር ትርጉም ገብቶሀል።
Abi🍁
​​💋💋💋💋💋ለሴቶች ብቻ ስለ ወንድ💋💋💋💋💋

❤️1, አንድ ወንድ ለትክክለኛ ምክንያት ክወደደሽ
#sex አይፈልግም አንቺ
እስክትጠይቂው ድረስ

❤️2, አንድ ወንድ ከመደወሉ በፊት ምን እንደሚልሽ ያቅዳል

❤️3, ምንም ወንዶች ሰለ ዳሌ እና ጡትሽ ቢያወሩም personality
ወሳኝነት አለው

❤️4, ወንዶች ሰሜታዊ ናቸው ይደብቁታል እንጂ

❤️5, አንደ ወንድ በጭራሽ አይቶሽ የማያውቅ ከሆነ አይወድሽም ምናልባት ረጅም ጊዜ chat ካላረጋችሁ 8ወር+

❤️6 ወንዶች እውነተኛ ሴት ይወዳሉ

❤️7, ወንዶች ሁሌም ላንቺ ጥሩ ሰው ለመሆነ የሞከራሉ

❤️8, ወንዶች ከወደዱሽ ጉራ አያበዙም

❤️9, ወንዶች በቀላሉ ይቀናሉ

❤️10, ወንዶች በሴቶች ግራ የጋባሉ

❤️11, ወንድ ልጅ ሰታወሩ አይንሽን በጣም ካየሽ ያልተመቸው ነገር አለ

❤️12, ወንዶች ሴቶች ሲያለቅሱ ማየት አይወዱም

❤️13, ምንም ብር ባይኖራችውም ወንዶች የረከሰ ቦታ ሲወስዱስሽ ጥሩ
ስሜት አይሰማቸወም

❤️14, አብዛኛዎቹ ወንዶች ቆንጆ ሴት ሳይሆን ንጹህናዋን የምትጠብቅ እና
ለሰው የምትቀርብ አይነት ሴት የሚፈልጉት

❤️15, አንድ ወንድ አልተረዳሽም ሲልሽ ማለት የፈልገው እኔ እንደማሰበው
እያሰብሽ አይደለም ለማለት ፈልጎ ነው

❤️16, አንድ ወንድ የእውነት ከወደደሽ መጥፎ በህሪሽን በሙሉ የቀበልዋል

❤️17, ወንዶች በሴቶች ፈገግታ እጅጉን የማረካሉ

❤️18, ወንዶች እጃቸውን በሴቶች ሲነኩ ደስ የላችዋል

❤️19, ወንዶች እናታቸውን ይወዳሉ

❤️20, ወንድን ልጅ ችግሩን ሲነግርሽ ምክር ባትሰጪውም ችግር የለወም
የሚሰማው ሰዉ ብቻ ነው የሚፍልገው

❤️21, የሴቶች ቁመት ለወንዶች መንም ላይሆን ይችላል ክብደታቸው ግን
ትርጉም አለው

Abi✌️
3👍3
Forwarded from Agent kemal (『AbI BaBa』)
Morning fams...🍁🍁🍁

ከራሱ ጋር ሲሆን ሰላም ያልሆነ ሰው ከቀረው አለም ጋርማ መቼም አይስማማም፤ ስለዚህ መጀመሪያ ከራስህ ጋር ታረቅ! ያኔ ለአለም ሁሉ ትተርፋለህ።
Abi🍁
Forwarded from የኔ ደብዳቤ💌
ብቸኝነት ሲሰማህ ሳይሆን ዝግጁ ስትሆን አፍቅር😒

@bemye🌹
2025/07/10 12:10:10
Back to Top
HTML Embed Code: