Telegram Web Link
በፍቅር ላለመውደቅ ሞክር
ምክንያቱም የወደቀ ነገር ሁሉ ይሰበራል 💔

@loverzonn
@loverzonn
🍃🌹🍃......

❤️ግን በቃ እረሳሁህ❤️

አውቃለሁ ከባድ ነው ትዝታ፣
ከምንጩ ማድረቅ የፍቅርን ጠብታ፣
ግን በቃ እረሳሁህ፣
ከአዕምሮዬ ፋቅኩህ፣
ከልቤ አወጣሁህ፣
አዲስ ሕይወት ጀመርኩ፣
ትዝታህን ትቼ
በተስፋ ተራመድኩ።💔
🥀💗🥀💗🥀💗🥀💗🥀 💚💚💛💛❤️❤️ 💙💜@loverzonn
በመጀመሪያ የፍቅር ቀጠሮ ጊዜ...

1.ስለራስህ ህይወት አካብደህ አታውራ።
2. ኢንተርቪው አታስመስለው።
3. ትኩረቱን ጠቅልለህ አትውሰድ።
4. ሃሳብህን ከእሷ አትበታትን።
5. ሁል ግዜ ጥሩ ለብሰህ ሂድ።
6. እውነተኛ ለመሆን ሞክር።
7. ስላለፈ የፍቅር ህይወቷ ከመጠየቅ ተቆጠብ።
@loverzonn
🌹🍃እንደዚም አለንዴ🍃🌹




ምን ልበል ስላንቺ ቃላቶቼም ፈሩ፡
አንደበቴም ሞተ ሳይገባ ካፈሩ፡
አይኔም አላይ አለ ግርማሽ አሳውሮት፡
እግሬም አልፀናልኝ ክብርሽ አሸብሮት፡
እጄም ከፍ አለብኝ ድንቅ ውበትሽ ማርኮት፡
እንደዚም አለንዴ ማማር በተፈጥሮ፡
ሰዓሊ ማይስለው ቀለምን አጣምሮ፡
ፀሀፊ ማይገልፀው በብዕር ሞንጭሮ፡
ዘፋኝ የማይዘፍነው ድምፁን አሳምሮ፡
ምሁር ማይደርስበት ዝንት ተመራምሮ፡
ጨረቃን ሰማሗት እሪ ወየው ስትል፡
ፀሀይም በንዴት ፍጥረትን ስታግል፡
ኮከቧም አዝና ወዲያ ስትኮበልል፡
ደመናም ተከፍቶ ዞር ሲል ገለል፡
እንዲ ብስጭት ያሉት ዳሩ ባንቺ ላይ ነው፡
የጨረቃን ድምቀት ለራስሽ አርገሽው፡
የከዋክብትን ውበት በድፍረት ዘርፈሽው፡
የፀሀይን ሙቀት ይዘሽ አፍነሽው፡
የደመናን ግርማ በሀይል ነጥቀሽው፡
አኖረብሽ እንደው ያን ፀዳል ጥበቡን፡
ውበቱን ደፋብሽ ከሱ የሆነውን፡
እኔም ተገርሜ በውበትሽ ውዴ፡
ብዬ ትቼዋለው እንደዚም አለንዴ፡



┄┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄

          



           ❤️ #ፍቅር_ያሸንፋል❤️

🀄️🀄️ሉን👉 @loverzonn
🀄️🀄️ሉን👉 @loverzonn
🌹🍃እኔ ወድሻለሁ🍃🌹



በካፊያ ዝናብ ተኝቶ እንደማለም፣
በተስኪያን ስሞ ደሞ እንደመሳለም፣

እኔ ወድሻለሁ
ተጠምቶ እንደመርካት ተርቦ እንደመጥገብ፣
ነጠላ አጣፍቶ
ጧፍ በእጅ ይዞ የመዘመር አጀብ፣

በዚህ ሁሉ መውደድ እኔ ስውተረተር፣
ያንቺ ጠብ አይልም
በአንደበት ብቻ ሁሌ እንደምሰማው ፖለቲካ ቀመር፣

ቢሆንም ግን ዳሩ እኔ ወድሻለሁ፣
እንዳገሬ ገንዘብ
ትቀየሪ እንደሆን እጠብቅሻለሁ፡፡



┄┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄

          

           ❤️ #ፍቅር_ያሸንፋል❤️

🀄️🀄️ሉን👉 @loverzonn
🀄️🀄️ሉን👉 @loverzonn
🌹🍃አፍቅሬ ያጣሁሽ🍃🌹





አፍቅሬ ያጣሁሽ ያልሰመረው ህልሜ፡
ብመኝሽ ያልመጣሽ ደግሜ ደግሜ፡
ዞረሽ ያላየሽኝ ተሰባብሮ ቅስሜ፡
መጥተሽ ያላደሽው ባንቺ ታምቶ ስሜ፡

ልቤን አሳጥተሽ የፍቅርን ምላሽ፡
በባዶ ሸኘሽው ላይ ታች አንከራተሽ፡
እኔ ነኝ ምስኪኑ አፍቅሬ ያጣሁሽ፡

አይኖቼ አልቦዘኑም አልደከሙም ለ እንባ፡
ሙሾ አወርዳለው እጄ ላትገባ፡
ቀኑ አልነጋ አለኝ ቀትር ጨልሞብኝ፡
ምሽቱም ከሲኦል እኩያ ሆኖብኝ፡
መኖር ልክ እንደ ሞት መስሎ እየታየኝ

ከላዬ ላይ ይውረድ ጨርቄ ምን ያረጋል፡
አልግባ ከቤቴ ካደባባይ ልዋል፡
ሰንደል በፀጉሬ ኮተቱን በእጆቼ፡
ቆሻሻን ወድጄ ንፁውን ጠልቼ፡

በዛጋ እንዳትሄጂ ተይ እብድ አለ ካሉሽ፡
ስለማንም አይደል ላንቺ የነገሩሽ፡
እስካሁንም ድረስ በእብደት የማፈቅርሽ፡
እኔው ነኝ፡
እኔው ነኝ ውዴ ሆይ አፍቅሬ ያጣሁሽ፡
ስለማንም አይደል ላንቺ የነገሩሽ፡፡


ማስታወሻነቱ ፍቅራችሁ ተቀባይነት ላጡ።




┄┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄

           #ናቲ_ፍስሀ ነኝ



          

🀄️🀄️ሉን👉 @loverzonn
🀄️🀄️ሉን👉 @loverzonn
አሷ፦ ፍቅር ቆንጆ ነኝ
እሱ፦ አይደለሽም
እሷ፡ እንዲያዉ ግን በ አዕምሮህ ዉልብ ብዬ አላውቅም?
እሱ፡ አዎ አታውቂም
እሷ፡ እሺ ትወደኛለህ❤️
እሱ፡ አልወድሽም
እሷ፡ እሺ ትፈልገኛለህ😍
እሱ፡ አልፈልግሽም
እሷ፡ እሺ ትቼህ ብሔድ ታለቅሳለህ
እሱ፡ አላለቅስም
እሷ፡ በቃ ምንም አታደርግም😳
እሱ፡ ምንም አላደርግም
እሷ፡ ካንተ ህይወት እና ከኔ የማንን ትመርጣለህ😳
እሱ፡ የኔን


ከዛም ተናዳ እና አኩርፋ ትታው ልትሔድ ስትል እጇን ይዞ👫

➔የኔ ፍቅር ቆንጆ ያልሆንሽዉ ከቁንጅና በላይ ስለሆንሽብኝ ነው።

➔በአምሮዬ ዉልብ የማትዪዉ ሁሌም አዕምሮዬ ዉስጥ ስለሆንሽ እና ጠፍተሽ ስለማታውቂ ነው።
እና ደግሞ የማልወድሽ ቃላት በማይገልፀዉ ንፁህ ፍቅር ስለማፈቅርሽ ነው የማልፈልግሽ ምክንያት ስለሚያስፈልገኝ ነው

➔ትተሽኝ ስትሔጂ የማላለቅሰዉ በሄድሽበት ቅፅበት ቀድሜሽ ስለምሞት ነው።

➔ምንም ነገር የማላደርገዉ ሁሉን ነገር ላንቺ ስለማደርግ ነው
ካንቺ ህይወት የኔን የመረጥኩት ህይወቴ አንቺ ስለሆንሽ ነው የኔ ፍቅር😘😘😘😘😘😘😘






Share @loverzonn 🙏🙏🙏
#ሴት_ልጅ_ማለት_ለኔ

💋`በመጀመርያ`` ምድር ላይ ከማንም ጋር የማላወዳድራት እናቴ ትሆናለች

💋ሲቀጥል በጣም የምወዳት የምታስብልኝ እህቴ ትሆናለች

💋ከዛም የማፈቅራት ምትንከባከበኝ ውዷ ባለቤቴ ትሆናለች

💋በመጨረሻም የምሳሳላት ልጄ ትሆናለች

እናትህን ሰው ምን እንደሆነ ትማርባታለህ
እህትህን ሰው ማን እንደሆነ ታይባታለህ
ባለቤትህን ስለሰው ያወከውን ትኖርባታለህ
ሴት ልጅህን የሰው መሆን ፀጋህን ታውቅባታለህ

*.......🌹🌹🌹🌹🌹.......*
••●◉Join us share




┄┄┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄┄`
@loverzonn
@loverzonn
​​❥🍃🌹🍃..........

♥️እስከምትችል ድረስ ፍቅርን ስጥ
እያወክ አትበድል በቻልከው መጠን
ለማስደሰት ጣር አንተ ስትቀርበው
እሱ በእጥፍ የሚርቅህ ከሆነ ተወዉና ሌላ አማራጭ ፈልግ አንዳንዴ ሰዋች ስትከተላቸው
መሔጃ ያጣህ ይመስላቸዋልና!

🌹𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑🌹
@loverzonn
🌹🍃የፍቅር ምርጫዬ🍃🌹





አንተ ነህ የኔ አለም ልቤን የረታኸው
በፍቅር ሰንሰለት አስረህ የገረፍከው
መተከዜ በዛ ጭንቀቴም ጨመረ
ፍቅርህ በልቤ ውስጥ ደልቶት እየኖረ
አልችል አለኝ ልቤ ከቶ አንተን ለመርሳት
አይኔም አላይ አለ ካንተ ሌላ ተባዕት
ሆድዬ ተረዳኝ እኔ እወድሀለሁ
አልሰቃይብህ እጎዳብሀለሁ
ደስታዬ ነህ አንተ ሳቄም ጨዋታዬ
በፍቅርህ ተጎዳሁ ተረዳኝ ፍቅርዬ
ልቤም አዘነልህ ባንተ ፍቅር ታሞ
ያገግም ይሆናል በፍቅርህ ታክሞ

🌹🍃ከምሬ_ነው_ውዴ🍃🌹

ምናለ ባየኸው የልቤን ጭንቀቱን
አንተን እያሠበ ቀን እና ለሊቱን
ፍቅር ሲባል ለካ እንደዚህ ያስፈራል
ከወደዱት ሰው ውጭ ማሰብም ያስጠላል
ስቀመጥ ስነሳ አንተን አስባለሁ
ግን ያንተን ባላውቅም እኔ እወድሀለሁ

🌹🍃ልጠይቅህ_ማሬ🍃🌹

ምን ማለት ነው እስኪ ፍቅር ማለት ላንተ
ይቆጭሀል እንዴ ለፍቅር ብትሞት
አላስጨንቅህም መልሱ ይቆይ ካንተ
ሳቄም ጨዋታዬም ጠፋ ደበዘዘ
አይኔ አይንህን ተርቦ በናፍቆት ፈዘዘ

🌹🍃ተረዳኝ _ውዴ 🍃🌹
,
ለሊቱ ሲረዝም ቀን ሲጨልምብኝ
አሳልፈዋለሁ አንተን እያሰብኩኝ
እኔም ተጨንቄ አንተን አስጨነኩህ
ምንነበረ ያኔ ፍቅሬን ባልነገርኩህ

🌹🍃ፍቅሬ🍃🌹
,
ስምህን ሲጠሩ በዛ መጨነቄ
ከሠውነት ወጣሁ በፍቅርህ ወድቄ
በፍቅርህ ታምሜ እንዳልሞት አደራ
ስማኝ አንተን አንተን እያልኩኝ ስጣራ
እሺ በለኝ አንተም ፍቀድ ይሄን ብቻ
እኔም ያንተ ልሁን አንተም የኔ ብቻ


┄┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄

          

           ❤️ #ፍቅር_ያሸንፋል❤️

🀄️🀄️ሉን👉 @loverzonn
🀄️🀄️ሉን👉 @loverzonn
"ፍቅር እውነተኛ ስሜት ነው። የሌሎችን ስሜት ሳይሆንየራስህን ስሜት የምታዳምጥበት ፤ ልብህን ከፍተህ የምታስቀምጥበት፤ በደስታው ደምቀህ በሀዘኑ መፍትሔ የምትሻበት ፤ ዛሬን ኑረህ ነገን የምታልምበት ፤ አዲስ ነገር የምታይበት ፤ ከራስህ አልፈህ ለሌሎች ምታስብበት ስብእናን ሚያጎናፅፍህ ፀጋ ነው፡፡

💞 #ፍቅር_የሆነች ምሽት ተመኘዉላቹ💜
@loverzonn
♡~ፍቅር ምንድነው?~♡

☞ተማሪ፡ - መምህር ፍቅር ምንድን ነው?

☞መምህር፡ - አሰብ አደረጉና ፍቅርን ለማስረዳት አንድ የቤት ስራ
ልስጥህ ዛሬ ከትምህርት መልስ ወደ አንድ የስንዴ እርሻ ቦታ ሂድ ከዛም
እርሻ ውስጥ መርጠህ ትልቅ የሆነውን ስንዴ ይዘህና ግን መጀመሪያ ከያዝክው ስንዴ የተሻለ ስታገኝ በእጅህ የያዝከውን ስንዴ መጣል አለብህ ተመልሰህ ማንሳት ክልክል ነው፡፡

☞ተማሪው፡- ወደ ስንዴው ማሳ ሄደ የመጀመሪያውን ስንዴ አነሳ ትንሽ
ሄድ ሲል ሌላ አገኘ አሁንም ሲፈልግ ሌላ አገኘ እንዲ እንዲ እያለ ሲጥል ሲያነሳ ቆይቶ በመሐል ቆም ብሎ ሲያስብ እስካሁን ሲያነሳቸው
በነበሩት ስንዴዎች መካከል ምንም ልዩነታቸው አልታይ አለው በከንቱ ጊዜውን ማቃጠሉ አናዶት ባዶ እጁን ወደ መምህሩ ተመለሰ፡፡

☞መምህር ፡ - ትልቁን ስንዴ አገኘህ

☞ተማሪ፡ - መምህር በከንቱ ነው ሳነሳ ስጥል የዋልኩት ሁሉም ስንዴዎች ያው ናቸው፡፡

☞መምህር፡ - ፍቅርም እንዲህ ነው በጅህ የያዝካትን መርጠህ ከያዝክ በኋላ ሌላ አዲስ ስታይ ታምርአለች አዲሶን ከያዝክ በኃላ ሌላ አዲስ ስታይ እሷም ታምር አለች አንተ የተውካትን ሌላ ይዞት ስታይ ያኔ በቁጭት ትቃጠላለህ ከመጀመሪያዎ የተለየ ሌላ ፍቅር ከአዲሷ አይዝህም::

"ፍቅር ማለት መጀመሪያ አይተህ ከወደድካት ጋር የሚሰማህ ስሜት ነው
ከዛ በኃላ የምታገኘው ፍቅር ሳይሆን ወረት ነው ፍቅር የሚይዝህ አንዴ ነው፡፡" በሚል መለሱለት፡፡

ህይወት ጉዞ ሲሆን ይህን ጉዞ ጣፋጭ የሚያደርገውና ትርጉም
የሚሰጠው ደግሞ ፍቅር ነው፡፡

🌹━━━✦◉●••┈❀┈┈••●◉✦━━ 🌹

@loverzonn




┈┈••◉❖◉●••┈❀┈┈••◉❖◉●••┈┈
ናፍቆት ግን ምንድነው?

.
ፀሐይ መውደድህ ላይ፣
ያረስርሰኛል. . .
ናፍቆት ዝናብ ኾኖ፤
ላባው ቅለትህ ላይ፣
ያንገዳግደኛል. . .
ናፍቆት ሰማይ ጭኖ።
.
ናፍቆት ግን ምንድነው?
ምንድነው ግን ናፍቆት?
ከእልልታና ሲቃ፣
የሚቀየጥ ብሶት?
ወይስ. . .
ከጭምት አርነት፣
የሚፀነስ ድሎት?
.
ናፍቆት ግን ምንድነው?
እብደት ነው ልበልህ?
በእኩለ-ሌት ጽልመት፣
ቀትርን የሚያስናፍቅ፤
በቁንፅል ሐሳብ ስለት፣
ድባቴን የሚያስፍቅ?
.
ናፍቆት ግን ምንድነው?
ዘመቻ ነው ልበልህ?
ለጣዝማው ለማሩ ከንብ የሚያቧቅስ፣
በተስፋ ድግስ ላይ በአጀብ የሚያስለቅስ?
በህመም ድንኳን ውስጥ ለአፍታ የሚያስደንስ?
.
ናፍቆት ግን ምንድነው?
ምንድነው ግን ናፍቆት?
እንዲህ ነው ለማለት ውስጤ ተደናቅፎት፣
ይናፍቃል ልቤ . . .
የናፍቆትን ፍቺ ላይመልሰው ታቅፎት
እንደዚያ ነው ናፍቆት?

@loverzonn
2025/07/13 15:20:58
Back to Top
HTML Embed Code: