Telegram Web Link
ያን ፍቅር ባወራ አንደበት
ስምሽን እንዲ አወድሼ
ግድ የለም ህመሙን እችላለሁ
ጠላኋት አልልም መልሼ 😔



Join & Share

@loverzonn
@loverzonn
​​❤️እወድሻለሁ❤️

ዘመኑ ቢራቀቅ እሳቱ ቢጨመር
ፈታኞች ቢበዙም ቃልኪዳን ቢሰበር
ትውልድ ቢዘምን ቢጨልምም ፍቅር
ሁሉም ነገር ረክሶ ቢቀየር ወደ አፈር
ቆርቤያለው ባንቺ በውስጥሽ ልቀበር
❤️እወድሻለሁ❤️

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌Join & Share
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
@loverzonn
@loverzonn
ምን ያክል ባጠፋ ነው ምን ያክል ባስቀይምሽ
አይኔን አንክዋን ለማየት አንዲ እስኪደ ብርሽ

#yabu


@loverzonn 💔
@loverzonn 💔
ፍቅርን በእውነት እፈራው ነበር ዳግም እንዳልጎዳ ግን አንቺ መጣሽ እና ድፍረትን አስትማርሽኝ ግን ምን ዋጋ አለው ትተሽኝ ስትሄጅ ይባሱኑ እምነቴን አጠፋሽው 💔

#yabu



@loverzonn 💔
@loverzonn 💔
……?
😢
የሆነ ቀን እመኚኝ ዝም ብዬ እሄዳለው…ቻው እና ወደዚህ ነው የሄድኩት ሳልልሽ በአንቺም ተስፋ ማድረግ አቁሜ እሄዳለው…እዛኔ ግን ለዘላለም ነው…ለዘላለም…እመቤቴን ያኔ እኔ ተመልሼ አልመጣም…ብትደውይልኝ እና ብትፈልጊኝም አታገኚኝም…ያ ቀን መቼ ነው?…ምን አልባት ነገ…ወይ ከነገ ወዲያ…አልያም የሆነ ቀን…



Join & Share

@loverzonn
@loverzonn
🌹❤️....
መሄድሽ ቢከፋኝ ቢላወስ አንጀቴ
አቲጂ አልልሽም እኔስ ባንደበቴ
አይከፋኝ ማጣቴ አልልም ያቅታል
ሲተውት መተውን ልቤ ያቅበታል

Join & Share

@loverzonn
@loverzonn
​​. 💔🤷‍♂#ፍቅሬን በምን #ቋንቋ💞
---------------------
ለአይኔ እንኳን ለአፍታ እንዳላጣሽ፤
እፈልግ ነበረ ፍቅሬ እንዲገባሽ።
ግን እንዴት ልናገር እንዴት ስ ላውራ፤
ወደ ሌላ እንዳትሄድ እያለ ልቤ ሲፈራ።
ስሜቱ ከባድ ህመሙ አይቻልም፤
ፍቅርሽ ከብዶኛል ያዢልኝ አልቻልኩም
እንዴትስ ልናገር እንዴት ላውጣው፤
እያሰቃየኝ ነው ፍቅርሽ በእጣው።
ፍቅር ሠው ይገላል ሲሉ እሰማለሁ፤
እኔ ግን ስላንቺ ስንቴ ሞቼ ተነስቻለሁ።
ቃል ሲሰማ ከአንደበትሽ፤
በውበት ፍክትክት ይላል ፊትሽ።
በምንስ ልግለፀው ፍቅርሽን በቃላት፤
እኔ ግን እፈራለሁ አይንሽን ለማየት።

ሁሌም 😔#እወድሻለው😔

Join & Share

@loverzonn
@loverzonn
አፍቅሮ መፈቀር❤️ መታደል ነበረ
ግን ይሆናል ያልኩት ሳይሆንልኝ ቀረ🥺
ብዙም አልተከፋሁ☺️ ብዙም አልተጨነኩ😌
ሰው ሁሉ ወረተኛ መሆኑን ግን አወቅኩ😏
አውቄ ፈተሽኩት😞 እራሴን ቀርቤ
ለዚ ዘመን ፍቅር ለካ አይሆንም ልቤ😔

Join & Share

@loverzonn
@loverzonn
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​
ተደመሰሰ
__________

በቃ ተደመሰሰ
ልቦናችን ተቆረሰ
አይኖቼ አንችን ሲሹ
ይህ ነበር ምላሹ
ከምኔው እጅሽ ተጋ
ስለትሽ ጎኔን ወጋ
በጄ ነበር እኮ አልቢን
ብተኩሰው እሚበትን
በማስመሰል ከእቅፌ ገብተሽ
ስለምን በደሜ መራስሽ
... በቃ ...
በቃ ተደመሰሰ
ጥላቻችን ነገሰ
የኔና አንች ፍቅር
በቃ.. ለዚህ ነበር ።


@loverzonn
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​
ማፍቀር ....

ልጁን ላየው እጓጓለው
እንዳልይዘው እፈራላው
እማፈቅረው ከቃል በላይ
ከሱ ውጪ ከቶ እማላይ
እሱ ሁኖ የኔ አማላይ
ከሌላ ጋር እንዴት ልታይ
እሱን በሱ የሚተካ
ሠው አለ ወይ የሚረካ
ካገኛቹ ወዲ በሉኝ
መረጃዋን ጣል አርጉልኝ
ትንሽ እንኳ አናድጄው
ምን አለበት ፍቅር ቢገባው
እኔ በጣም እሚገርመኝ
ሰድቦኝ እንኳ ከሱ ስር ነኝ
ታዲያ ይሄ ፍቅር ነው ወይ.....?
ያጋጠመው እስኪ ይንገረኝ
ማበዴ ነው እኔ ጨነቀኝ 😔

✍️✍️ሐና ይመር




━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
@loverzonn
​​🌺#ፍቅር እስከ መቃብር#🌺

ያጥንቴ ፍላጭ 🌺
የስጋየ ቁራጭ
የደሜ ጠብታ🌺
የህይወቴ እፎይታ
ዘላለም ኑርልኝ🌺
እንዳትንገላታ
የህይወቴ ህይወት
የነፍሴ ባለቤት
የመኖሬ ትርጉም
ለቅሶህን አልሻም
ዘላለም ተደሰት 🌺
አትኑር በፀፀት
ለቅሶህ ለቅሶየ ነው ሀዘንህ ሀዘኔ...🌺
የስጋየ ቁራጭ የአይን ብሌኔ
ስለዚ ተደሰት እኔም ደስ ይበለኝ...
ለምን ይክፋኝ እኔስ ያላንተ ማን አለኝ.!!!!!
.......................



❤️
,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌https://www.tg-me.com/loverzonn
https://www.tg-me.com/loverzonn
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔@loverzonn 💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔
😘የቆንጆዋ ጦስ😘

🔥ክፍል 17

#የመጨረሻው_ክፍል


.
.
.
ከባህርዳር ከተመለስን ከሁለት ቀን በዃላ ደብር ዘይት ያለው የሀኒ አባት ከብዙ ደጅ ማስጠናት በዃላ ውሀ አጣጭህ የምትሆነውን ሴት እንዳገኜ እና ለእሷና ለእህቷ ሊያስተዋውቃቼው ቀን ቆርጦ እንደጨረሰ በደስታ ፈንድቆ ይነግራታል ሀኒም በአባቷ ደስታ እጅግ በጣም ተደስታለች ለብቻው በመሆኑ እና እንደጓደኞቹ ጎኑ ሁና የምታደምጠው እና ጎጆውን ሞቅ ሞቅ አድርጋ በጊዜ እቤቱ እንዲገባ የምታደርገው ሴት ባለ መኖሯ በጣም ያሳዝናት ነበር የምትሆነውን አግኝቶም ተረጋግቶ እንዲቀመጥላት የዘወትር ምኞቷ ነበር ዛሬ የምኞቷን መሳካት በአንድ የስልክ ጥሪ አጎቷ አበሰራት እኔም ሀኒ ልትሄድ በመሆኑ እጅጉን ብከፍም እንዲህ ፈክታ ሳያት ግን ለእሷ መደሰቴ አልቀርም። በሚቀጥሉት ቀናት ከዚህ በፊት እንዳደርግነው የሚገዛዙ ነገሮችን ገዛዝተን የሀኒ ጓደኛ እናት ጋር ሄድን
ከመመለሶ በፊት እንደምታያቼው ቃል ስለገባች እና በዛውም የአባቷን የብስራት ዜና ለሳቼውም ለመናገር ነበር የሄደችው ሴትየዋ የአባቷን ሊያገባ መሆን ሲሰሙ የቤተሰብ ያህል በጣም ነበር የተደሰቱት እንደው እንዴትና ከወዴት አገኜዃት አለሽ ሲሉ ሀኒን ጠየቋት ሀኒም ምንም የተጨበጠ ነገር እንዳልነገራት ሁሉንም የሚያጫውታት ስትመጣ እንደሆነ ነገረቻቼው ያው ከዚህ በፊት ስለግንኙነቱ መጀመር እና
ሴቷ ያለችው አዲስ አበባ እንደሆነ ጫፍ ጫፉን ታቃለች እንኳንም ተሳካለት እንኳንም አንችም ከሀሳብ እና ጭንቀት አረፍሽ አሉ ሴትዮዋ በእናትነት ለዛ ።
ከዛ በዃላ ነበር ሀኒ ጓዟን ጠቅልላ ከደሴ ወደ ደብረዘይት አባቷ ጋር የሄደችው ያን ቀን አብረን አድረን ነበር የሼኜዃት እሷን ሼኝቼ ስመለስ የተሰማኝን የብቼኝነት ስሜት እና ባዶነት እንዲህ በቀላሉ በቃል የምገልፅበት ቃልም አልነበረኝም ዳግም የምንገናኝ ሁላ አልመስልህ እስኪለኝ ሆዴ ተላወሰ ለካ ኤርፖርት ላይ ሰው ተቃቅፎ እንደዛ የሚላቀሰው ወዶ አይደለም ከሚወዱት ለቀናትም ቢሆን መለየት ምን ያክል እንደሆነ ስሜቱ የገባኝ በዛን ሰሞን ነበር ። ከሀኒ ጋር ወዲያው ወዲያው ብንደዋወልም በቃ ደርሳ ትናፍቀኛለች ያ ሳቋ ፊቴ ላይ ድቅን ይልብኛል ።
አንድ ምሽት ከሀኒ ጋር ተደዋውለን እያወራን አዲሷን እናቴን እኮ የምተዋወቅበት ቀን ነገ ነው ደስ አይልም ደሞ ሳልነግርህ ድርሰቱ ወደ ፊልም እስክሪፕት ተቀይሮ በቅርብ ግዜ ቀረፃው እንደሚጀመርም አጎቴ ነገረኝ ስትል ፍፁም በሚያስታውቅ ደስታ ፍልቅልቅ እያለች አወራችልኝ እኔም የደስታዋ ተካፋይ ለመሆን የአባቷ ትውውቅ ላይ ባልገኝ እንኳ ፊልሙ ሲመረቅ ግን በአካል ቦታው ድረስ እንደምገኝ ቃል ገባሁላት በጣም ደስ ይለኛል ነገ በጧት ለስራ ተነስቼ ጉድ ጉድ ማለት ስላለብኝ በግዜ ልተኛልህ እወድሀለሁ ብላኝ ተሰነባብተን ስልኩ ተዘጋ
በሚቀጥለው ቀን እህቴና ሀዩ ባሉበት ቁጭ ብለን ቡና እየጠጣን ነው እህቴና ሀዩ ሀኒ ከሄደች በዃላ እኔ ላይ በሚያዩት ድብርት መቀለድ እና መጠቋቆም ከጀመሩ ቆይተዋል የዚች የቆንጆ ጦስ መቼም ሂዳም አለቀቀህማ ትለኛለች እህቴ ሀዩ ግን እህቴ ጋር ስትሆን አብራ ብትቀልድም ለብቻዋ ስትሆን ግን በቻለችው ሁላ ፈታ እንድል የማታደርገው ጥረት አልነበረም በቀልዳቼው መሀል የስልኬ መጥሪያ አቃጨለ ሀኒ ነበረች የአባቷን ሚስት በአካል የምትተዋወቅበት ቀን ዛሬ ስለሆነ አይመቻትም ብየ አልደወልኩላትም ነበር አነሳሁትና እንደሁልግዜው ቆንጆዋ አልኳት ድምፆ የቀዘቀዘ ነበር ምንድነው ድምፅሽ ደህና አይደለሽም እንዴ ሀኒ ስል ጠየኳት ምንም ሳትመልስልኝ የእናትህ ስም ማን ነበር ያልከኝ ስታስተዋውቀኝ የሚል ደረቅ ጥያቄ አስከተለች ከምናወራው ጋር ምን አገናኘው እያልኩ በውስጤ የእናቴን ስም ነገርኳት በዛው በቀዘቀዘ ድምፆ እሺ ብቻ ብላኝ ስልኩን ዘጋችው ግራ እየተጋባሁ ደወልኩላት አይነሳም ደገምኩት ቴክስትም ላኩኝ ምንም ምላሽ የለም ይባስ ብሎ ስልኳ ጠፍ በእህቴ ስልክም ሞከርኩ ጥሪ አይቀበልም ነው የሚለው ከቀን ጀምሮ ምሽት ስድስት ሰአት እስከሚሆን እየቆየሁ ብሞክርም ስልኳ ግን አሁንም ያው ነው አሁንም አይሰራም ያን ሌት እንዲሁ ስገላበጥ ሀሳብ ሳወጣና ሳወርድ እንቅልፍ የሚባል በአይኔ ሳይዞር ነጋ ከአልጋየ እንደተነሳሁም የመጀመሪያ ስራየ ምን አልባት ከሰራ በሚል ወደ ሀኒ መደወል ነበር ምን ዋጋ አለው እንደማታው ነው ጥሪ አይቀበልም ። አንዳንዴ ከሆነው አልያም ከደረሰብን ነገር በላይ እጅጉን ሰላም የሚነሳን እና ውስጣችንን እረፍት የሚነሳው ለምን እና እንዴት ሆነ የሚለው ነገር ነው እኔም አሁን ያ ስሜት ነው የሚሰማኝ ስልኩን ስለዘጋችብኝ ወይ ስላጠፋችው ብቻ ሳይሆን ለምን ያ ሆነ ? እንዴት የእናቴን ስም ጠየቀችኝ ? በቃ ውዝግብግብ ያለ ነገር ሆነብኝ በመሀል ደሞ አንዳች ነገር ገጥሟት ይሆን እንዴ እያልኩ እጨነቃለሁ በደስታዋ ቀን ላይ እንደዛ የመቀዛቀዟ የመረበሿ ነገር ደግሞ ሌላ ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው ። እህቴ ቁርስ ሰርታ እኔን እየጠበቀች ነው እኔ ደግሞ ምንም የመብላት ፍላጎት አልነበረኝም እኔ እቆያለሁ ብያት ከቤት ወጣሁ ወደየት እንደምሄድ ግን አላውቅም እንደ እብድ ብቻየን አወራለሁ በእህቷ ስልክ እንኳ እንዳልደውል የእህቷን ስልክ አላውቀውም አንዲህ ባለ ሁኔታ ነገር እያብሰለሰልኩ ከእንቅልፍ እንደተጣላሁ የሀኒ ስልክም እንደተዘጋ ሶስት ቀን ሞላኝ ከዚ በላይ ግን የውስጤን ጥያቄ ሳልመልስ የሀኒንም ሁኔታ ሳላቅ ታግሶ መቆየት አልቻልኩም የሆነ ነገር መፍጠር እንዳለብኝ ወስኜ ከአልጋየ ተነሳሁ የሰሞኑ ሁኔታየ ከወትሮው የተለየባት እህቴ ከመኝታ ቤቴ መውጣቴን ጠብቃ ምንድነው የሆንከው አንተ ልጅ ስትል አስቁማ አፋጠጠችኝ ምንም እንዳልሆንኩ ላስመስል ብሞክርም በዛ ሁኔታ አልችልም ነበር የግዴን ያለውን ነገር አንድ በአንድ ከሄደችበት ምክኒያት አንስቶ ደውላ የእናታችንን ስም ጠይቃኝ ስልኩ እስከተዘጋበት ደረስ ያለውን ነገርኳት ለአፍታ አንገቷን አቀርቅራ ከቆየች በዃላ ከሰመመን እንደነቃ ሰው አይነት ብንን ብላ አባቷ ሚኖረው ደብረዘይት ነዋ ያልከኝ አለች አዎ ምነው አልኳት ፊቷ ላይ የተወሰነ ግራ የመጋባት አይነት ድንጋጤ አስተውያለሁ አይ ምንም ቆይ ታዲያ በሷ በኩል የምታቀው ሌላ ሰው የለም አንዴ ምን አልባት ያለችበትን ሁኔታ የሚነግርህ አልያም ሌላ ስልክ ካላት የሚሰጥህ አለችኝ እህቷን እና አንድ ጓደኛዋን ብቻ ነው የማቀው የሁለቱም ስልክ ደግሞ የለኝም የኔ መልስ ነበር ይሄን እያወራን ሀዩ እንዴት አደራችሁ ብላ ወደቤት ገባች ሁለታችንም ፊት ላይ መረበሽ ስላየች ምንድነው በጧቱ ቆዝማችዃልሳ ብላ ከእህቴ ጎን ተቀመጠች እኔ ካለሁበት ተነሳሁና የተጫጫነኝ ትንሽ ለቀቅ ቢያደርገኝ ብየ ወደሻወር ቤት ገባሁ እህቴና ሀዩና እዛው በተቀመጡበት ይንሾካሾካሉ የሻወር ቆይታየን ጨርሼ ስወጣ ቁርስ ቀርቦ ነበር ካልበላሁ ስለምትጨናነቅ ለእህቴ ስል እንደነገሩ ቀማመስኩና አንዳች ፊንጭ ባገኝ እንኳ እዛው እቤታቼው ድረስ መሄድ እንዳለብኝ ቁርጥ ሀሳብ ላይ ደርሼ ከቤት ወጣሁ
ከቤት ወጥቼ ትንሽ እንደሄድኩ እስኪ ቢሰራ ደውየ እድሌን ልሞክር ብየ ስልኬን ላወጣ ከኪሴ ስገባ ስልኬ የለም ትዝ ሲለኝ ሻወር ከመውሰዴ በፊት የለበስኩት የቱታየ ኪስ ውስጥ እንዳስቀመጥኩት ነበር ሱሪ ስቀይር የረሳሁት ከነበርኩበት በጥድፊያ ወደ ቤት ተመለስኩ በሩ ጋር ደርሼ ልገባ ስል ይልቅ ሰአቱ ሳይረፍድ ሁሉንም ብትነግሪው ይሻላል የሚለው የሀዩ ድምፅ ከውስጥ ወደ ውጭ ጆሮየ ላይ ጥልቅ አለ ባለሁበት ቀጥ ብየ ቆምኩና መላ አካሌን ጆሮ አድርጌ የሚያወሩትን ለመስማት ተዘጋጀሁ እህቴ ቀጠለች እኔኮ በስመ ደብረዘይት ዝምብየ ያልተጨበጠ ነገር ይዤ ከማወራው
መጀመሪያ ማሚ ጋር ልደውልላትና ስሙን ልጠይቃት ከዛም የሀኒን የአባት ስም እሱን ጠይቄ አንድ አይነት ከሆነ በቃ ምንም ማድረግ አልችልም እሱም እንደዚህ ከሚሆን ነግረዋለሁ የእህቴን መልስ የሰማችው ሀዩ ደግሞ እንዲህ ስትል ወሬዋን ቀጠለች እኔም የወሬያቼውን ፍንጭ እና መጨረሻ ለመስማት በቆምኩበት ቋምጫለሁ ግን አንቺ እንዳልሽው የሀኒ አባት በሚስትነት የተዋወቀው የእናንተን እናት ከሆነኮ በጣም ከባድ ነው አስበሽዋል ከአንቺና እናት እና ከልጅቱ አባት ልጅ ቢወለድ እኮ ለሁለቱም ወንድም ወይም እህት ነው የሚሆነው ይሄን ስሰማ ባለሁበት ጉልበቴ ተንቀጠቀጠ ሰውነቴ ድንዝዝ አለ ምኑ ከምኑ ጋር ተገናኝቶ ነው ያ ሊሆን የቻለው እህቴስ ይሄን ከማን እና እንዴት ሰምታው ነው ? በድን ሰውነቴን አንደምንም አንቀሳቅሼ በሩን አልፌ ወደ ውስጥ ገባሁ የሁለቱም አይን በድንጋጤ ፈጦ እኔ ላይ አረፈ ምንም ሳልናገር ፊት ለፊታቼው ሂጄ ተቀመጥኩ ምን ሁነህ ነው አለችኝ እህቴ በመመለሴና በወሬያቸው መሀል ድንገት በመገኜቴ ግማሽ ግርምት ግማሽ ድንጋጤ ውስጥ ሁና ሀዩ እንደፈዘዘች ናት እያወራችሁት የነበረውን በር ላይ ሁኜ ስሰማ ነበር እና አሁን ምንም ሳትደብቂ ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ነገሪኝ አልኳት በጣም ተቆጥቼ ነበር እህቴ ደሞ አደለም በዚህ መልኩ ተናድጄ ይቅርና ድምፄ ትንሽ ለወጥ ካለ ድንብርብር ነው የምትለው ድምፇ ቁርጥቁርጥ እያለ እንዲህ አለችኝ ማሚ ባለፈው ደውላልኝ ነበር እናታችንን ማሚ እያልን ነው የምንጠራት እናም በስራ ምክኒያት ከሆነ ሰው ጋር ትውውቅ ጀምራ ነገሩ ወደ ትዳር እያመራ እንደሆነና አሁን ደሞ ልጆቹን ሊያስተዋውቃት ቀጠሮ እንደያዙ አውርታልኝ ነበር ይሄን ነገር ለኔ ብቻ ነው የነገረችኝ ለእናንተ አሁን ላይ እንዳልነግራችሁ እና አሷ ራሷ በሁኔታው ወስና ከጨረሰች በዃላ እንደምትነግራችሁ ጨምራ ነግራኛለች እናም የተዋወቀችው ሰው ነዋሪነቱ ደብረዘይት እንደሆነ ስለነገረችኝ ቀኑም ሀኒ ከሄደችበት ጋር ስለተመሳሰለብኝ በቃ ይሄን አሰብኩ አለችኝ የእናቴ ይሄን ነገር ለእህቴ ብቻ መንገሯ ምንም አላስገረመኝም ምክኒያቱም ከዚ በፊትም ቢሆን በእናቴ ዙሪያ ምንም አይነት ጉዳይ ሲኖር ከሁላችንም ቀድማ የምትሰማው እህቴ ናት ከሁሉም በፊት የቅርብ አማካሪዋ እሷና እሷ ብቻ ናት ሌሎቻችን ከረፈደ ነው የምንሰማው ያን ስለማቅ አልደነቀኝም አደንዝዞ ያስቀረኝ የነገሩ መገጣጠም ነው የፈለገ እውነቱ ቢመርም አንዴ ቁርጤን ማወቅ ግን ፈልጊያለሁ የሀኒን የአባት ስም አቀው ስለነበር ያን ለማረጋገጥ እህቴ ምንም እንዳልተፈጠረ በመሆን እናቴ ጋር ደውላ ስለትውውቃቼው ወሬ በማንሳት በሆነ መንገድ ስሙን ምናውቅበትን ሀሳብ አወራን ቁርጤን ማወቁ ቢያጓጓኝም ነገሩ እውነት እኛ እንዳሰብነው ቢሆንስ የሚለው ፍርሀቴና ጭንቀቴ ግን አያድርስ ነበር ምንም እንኳ በብቼኝነት ሌትና ቀን የምትገፋው እናቴ ሰምሮላት ለአዲስ ጎጆ የጀመረችው መንገድ እፎይታ ቢሰጠኝም ወዲህ ግን ጅምሩ ፍቅሬ፣ አዲሱ ፍቅሬ፣ ወደማላቀው ደስታ ያስገባኝ ፍቅሬ ብዙ ያሰብኩለት ፍቅሬ መና ሁኖ ሊቀር

መሆኑ ሲታሰበኝ ባለሁበት የሀዘን ጭልመት ከበበኝ በመጨረሻም እህቴ እናቴ ጋር ደውላ እያሳሳቀች ነገሩን መውጣጣት ጀምራለች እኔ መቁነጥነጤን ቀጥያለሁ ካፍታ የስልኩ ቆይታ ቡሀላ መራራው እውነት ፈረጠ እናቴ የተዋወቀችው አዲሱ እንጀራ አባቴ የሀኒ አባት ሁኖ አረፈው ምን ይባላል አሁን በማንስ ይፈረዳል ግዜ እኛ ላይ ሲፈርድ ይሄን የግጥምጥሞሽ ዳስ እኛ ላይ ደፋብን ቤቱ በአንዳች የዝምታ መንፈስ ተዋጠ በዚ መሀል የስልኬ መጥሪያ አቃጨለ እህቴ ከኔ ቀድማ ብድግ ብላ ወደስልኬ በመሄድ አነሳችውና እስክሪኑ ላይ አፈጠጠች ወዲያው የፊቷ ገፅ ቅይር አለና ሀኒ ደወለች አለችኝ ወደኔ ስልኩን እየዘረጋች እጄ እየተርበተበተ ተቀበልኳትና ትንፋሼን ሳብ አድርጌ ለመረጋጋት እየሞከርኩ ስልኩን አነሳሁት ከሷ እስከሚመጣ ድረስ ምንም እንዳልሰማ ሁኜ መቀጠልን መርጫለሁ ።ድምፇ ለመጨረሻ ግዜ እንደሰማሁት አሁንም ቀዝቃዛ ነው ምን ሁነሽ ነው ምን ተፈጥሮ ነው? ይሄን ያክል ቀን ስልክሽን አጥፍተሽ ስታስጨንቂኝ የነበረው ስል ጠየኳት ፀጥ ብላ ቆየችና በቃ ምንብየ እንደምነግርህም አላቅም ከአቅሜ በላይ የሆነ ነገር ሆነብኝ ያሰለፍኳቼውን የስቃይ ቀናት እኔ ብቻ ነኝ የማቀው ወድጄም አይደለም ስልኬን ያጠፋሁት ድምፇ እየተቆራረጠ ወደ ለቅሶ ቃና ተቀየረ ምንም እንኳ ሁኔታውን ቀደም ብየ ብሰማውም አሁን ይበልጥ ህመሙ ወደ ውስጤ ዘልቆ ሲገባ ታወቀኝ አይኖቼ እንባ ቋጠሩ ሀኒ ሳግ እየተናነቃት ወሬዋን ስትቀጥል የእኔም እንባዎች እየተንኳሉሉ መውረድ ጀመሩ እንደዛ አስቦርቆኝ የነበረው የአባቴ ዜና ተገልብጦ የመርዶ ያክል የሚከብድ ዱብዳ ሀነብኝ አባቴ ሚስት ብሎ ያስተዋወቀኝ የአንተን እናት ነው ብላ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች የሷ ለቅሶ እኔንም ከነጭራሹ አሳጣኝ ከዛ በዃላ ምንም እንዲህ ነው ብየ የምናገረው ቃልም አልነበረኝ ልናገርም ብል አፌ ተያይዞል ደሞስ በዛ ሰአት እኔ ለራሴ አፅናኝ በሚያስፈልግብኝ ከየት አቅም አገኝቼስ ሀኒን አፅናናለሁ እሷ ድምፅ አውጥታ እያለቀሰች እኔ ደግሞ በዝምታ ወደ ውስጥ እያነባሁ በተገተርኩበት እህቴ ጆሮየ ላይ ያለውን ስልክ ተቀብላኝ ሀሎ ሀኒ እያለች ወደውጭ ወጣች ምን እንደምታወራትም አላቅም ብቻ ብዙ ቆይታለች ።ቤቱ ውስጥ እኔና ሀዩ ቀርተናል ወደተቀመጥኩበት መጥታ ጎኔ አረፍ አለች በክሪሟ ጫፍ ከጉንጮቼ ላይ እንደመጥረግ እያደረገች በቃ አይዞህ እንደዚህ አትሁን እራሳህን አረጋጋ እስከመጨረሻውኮ አላጣሀትም ምንድነው እንደዚህ ባንዴ ተስፋ መቁረጥ አንተ ላይ ሳቅና ጨዋታ እንጂ መቆዘም አያምርብህም ለሰው መካሪ እንዳልነበርክ ዛሬ ምከሩኝ ልትል ነው እንዴ ቀጠለች ሀዩ በስስት እያየችኝ ደሞ ታውቃለሀ ሁሉም ሰው በራሱ ርእስ የተፃፈ መፅሀፍ አለው የገፃችን ብዛት ግን የት ጋር እንደሚቆም ማናችንም አናቀውም ። እና ደሞ የሂወታችን መፅሀፍ ውስጥ እያንዳንዱ ገፆች ላይ የተፃፈው ነገር ይለያያል የደስታ የሀዘን ፣ የመገናኜት የመለያየት፣የመሳቅ የማልቀስ፣ የማግኛት የማጣት፣ የመውደድ የመጥላት ፣ የመውደቅ የመነሳት የጠብ የመታረቅ ፣ የመሄድ የመምጣት ፣ የፈታ የድብርት ፣ የማትረፍ የመክሰር ፣ የመውደቅ የስኬት ብቻ ብዙ አይነት የሂወት ውጣ ውረዶች በገፆቹ ውስጥ ተፅፈውበታል። እናም በመኖር ሂደት ውስጥ ድንገት አንዱ ገፅ ሊበላሽብህ አልያም አንተ እንደጠበከው ሁኖ ላታገኛው ትችላለህ ነገር ግን ያ ሆነ ብለህ ቶሎ ብለህ ተስፋ መቁረጥ የለብህም ራስህንም እንደ እድለ ቢስ ማየትም ደሞ ይሄን አትርሳ ሁሉም የሚሆነው በምክኒያት ነው ሳይደግስ አይጣላም ሲበል አልሰማህም ይልቅ በርታ ብለህ በትእግስት እለፍና ቀጣዩን የሂዎትህን ገፅ ለመግለፅ ሞክር ማን ያቃል አዲስ የምትገልጠው የሂወት ገፅ የተሻለና አንተ የምትፈልገው አይነት ብቻ ሳይሆን ለአንተ የሚያስፈልግህ
አይነት ሁኖ ያለፈውን መጥፎ ገፅ ቢያስረሳህስ, ,, አየህ ሂወት ይቀጥላል ስለዚህ አንድ ገፅ ተበላሸ ብለህ አትቁም አንተ ገልጠህ ያላያሀቸው ብዙ መልካም ገፆች ይኖራሉኮ ማን ያውቃል በዛ ላይ አሁንም ወደ አንድ ቤተሰብ ልተሰበሰቡ ሆነ እንጂ ጭርሱን አላጣሀት እስኪ ቆይ ያኔ መጀመሪያ ስትገናኙ ሹራቧ ውስጥ ያገኜኸው ደብዳቤ የሷ ሁኖ በነበር ዛሬ በሂዎት ትኖር ነበር እንዴ ?? ንገረኛ አለች እኔ አንገቴን እንዳቀረቀርኩ ነው ሀዩ በዝምታየ ላይ ቀጠለች አየህ ሁሉም የሚሆነው በምክኒያት ነው የደረሰብህን እያሰብክ ከማማር ይልቅ ሊደርሰብህ ብሎ በፈጣሪ እዝነት ያልደረሰብህን ነገር አመዛዝነው በተናገረችው ነገር በጣም ተገርሜ እውነትም ያኔ ሙታ በነበር ሀዘኑ ምን ያክል ይጎዳኝ ነበር ስል እራሴን ጠየኩት ሀዩ እውነትም ልክም ነበረች ሁሉም ነገር የሚሆነው በምክኒያት ነው በዝምታየ ውስጥ እንዳለሁ ጥምጥም አድርጌ አቀፍኳት ካለሁበት ጭንቀት ውስጥ በሷ ውስጥ ልደበቅ እሷም በምላሹ እንደኔው አቀፈችኝ ቤቱ በአንዴ ፀጥ ረጭ ያለ ድባብ ወረሰው እኔም የሀዩ እቅፍ ውስጥ እንዳለሁ ይችን ግጥም በውስጤ አነበነብኩ
ብ ናስብም እኛ የሩቁን የማዶ
የጋራችን ፍቅር ላያድግ ተወልዶ
የጧት ጤዛ ሁኖ ውሎ የማያመሽ
ላፍታ ብቅ ብሎ ተኖ እንደሚሸሽ
በወጉ ሳንጠግብ ያብሮነትን ደስታ
የትናንት ፍቅራችን በግዜ ተረታ
የዘራነው መውደድ ይበቅላል በማለት
እንቡጡ ተቀጨ ፍሬው ሆነ ዘበት
እጣ ፈንታ ሆነ አልታደልንም በቃ
ያሁሉ ፍቅራችን ነበር ለደቂቃ
የህሉሀችን ገመድ ልኬቱ ሲሰመር
መርዘም ተገድቦ ተፅፎ ለማጠር
ይብቃችሁ እዚ ላይ በሉ ተለያዩ
ሲል አስቆመን ግዜ ጎጇችህን ለዩ
አንቺም አላጠፋሽ ምን አድርጌስ እኔ
ማንስ ይወቀሳል ምን ሰርቶ ኩነኔ
አባትሽም አይደል ወይንም እናቴ
በቃ የድል ፍርጃ አረገሽ እህቴ ።

.
.
.

°°°°°°\\°°°°°°°\\°°°°°°^^
🔥ታሪኩ ተፈፀመ የህይወታችን ሌላኛው ገፅ ግን ተገለጠ🔥
......//......//.....//...//.....

እናንተ እራሳችሁን የታሪኩ ባለቤት አድርጉና ሴቶቹ ሀኒን ብትሆኑ ወንዶቹ ደግሞ እኔን ብትሆኑ ምን ታደርጉ ነበር...? እዉነተኛ ስሜታችሁን እና በታሪኩ ዙሪያ ያላችሁን አስተያየት @wiz_sami @feva_19
2025/07/13 22:36:16
Back to Top
HTML Embed Code: