Telegram Web Link
❤️ይቅናሽ ብየሻለሁ 💏


ሳይገባኝ ነገሩ ከኔ የጎደለው
ቀርቦ መለየቱን ከቶ ምን አመጣው
ይቅናሽ ብዬሻለሁ
በሄድሽበት ሁሉ ሰላሙን እመኝልሻለሁ
ለኔማ ለኔማ
ለኔ የምትሆን የአምላክ ስጦታ
ትመጣልኛለች በጊዜው በቦታ
ይብላኝ ላንች እንጅ
በነገር በውሸት ሰውን ምታፋጅ
መቻሌ ሳይገባሽ በኔ ላይ ፈራጅ
አይ የኔ ዳኛ የኔዋ ጠበቃ
አሁንማ አለቀ ነገሩ አበቃ
ፍርድሽ ካልፀደቀ
መንግስት ካለወቀ
ያገር ሽማግሌ የቀበሌ ፊርማ ቡውል ካልረቀቀ
ይጅ በቃ ዞረሽ አትመለሽ
ችሎቱ ተዘግቷል ካሰብሽበት ድረሽ


Join Share
@loverzonn
@loverzonn
ባይልልህ እንጂ ከኔ ኗሪ😒
ሆኜልክ ነበረ ቃል አክባሪ☀️. . .

የማይከርም ገላን አባብዬ 😕
እንዴት እኖራለው ቃልን ብዬ😞

የ አሁን ግዜ ፍቅር የግዜ ገደብ ስላለው"እወድሀለው" ለሚልህ"እስከመቼ "በለው...😒

Join Share

@loverzonn
@loverzonn
❤️ምርጥ አጭር የፍቅር ታሪክ❤️


ወጣቱ ሲዲ ሊገዛ ወደ አንድ ሱፐርማርኬት ዘው ብሎ እንደገባ ነበር ዓይኑ
አንዲት ልጅ ላይ ያረፈው😍፡፡ ደስ የምትል የምታምር ልጅ! ልጅቱ ሱፐርማርኬቱ
ውስጥ ካሉት ሻጮች መሃከል አንዷ ነች፡፡ ለረጅም ጊዜ የሚያውቃት ያህል ነው
የተሰማው፡፡ አንዳች ደስ የሚል ስሜት ሲስበው፣ ሄደህ አናግራት፣ አዋራት፣
አብረሃት ሁን ሲለው ይሰማዋል፡፡ ልጅቷን ወዷታል😍❤️፡፡ ግን ደግሞ እሱ እንኳንስ
እንዲህ በአጋጣሚ አይቶ የወደዳትን የማያውቃትን ልጅ ይቅርና፣ በወጉ
የተዋወቃቸው ልጆች አጠገብም ዓይናፋር ብጤ ነው፡፡
እና የልቡን በልቡ ይዞ በእፍረት እንዳቀረቀረ የልጅቷን ፊት ሰረቅ አድርጎ
እየተመለከተ ወደ ልጅቷ ቀርቦ ሲዲ እንደሚፈልግ ተናገረ፡፡
ልጅቱ በፈገግታ ተቀበለችው፡፡
“ሲዲውን ልጠቅልልህ…” አለችው፡፡
“እሺ !” ከእሷጋ የሚያቆየውን የትኛውንም አጋጣሚ እጅጉን ይፈልገዋል፡፡ ልጅቷ
ሲዲውን አሽጋ ሰጠችው፡፡
ሂሳቡን ከፍሎ ሊወጣ ነው፡፡ ቢችል ትንሽ ጊዜ አብሯት ለመቆየት አንድ
ተጨማሪ ዕቃ ቢገዛ ተመኘ፡፡ ግን ደግሞ ሌላ ሊገዛ የሚፈልገው ዕቃም ሆነ
አንዳችም ተጨማሪ ሳንቲም ኪሱ ውስጥ የለም፡፡
እናም ሳይወድ በግድ የሲዲውን ጥቅል በእጁ የልጅቷን ፍቅር በልቡ እንደያዘ
ወደ ቤቱ አመራ፡፡ ከዛን ቀን በኋላ የልጁ የዘወትር ተግባር የዐይን ረሃብ
የሆነችበትን ይህቺን ልጅ ለማየት ወደ ሱፐር ማርኬቱ እየሄደ ሲዲ መግዛት
ሆነ፡፡
በቃ ሁልጊዜ እንደዚሁ ነው፡፡
ማለዳውን የልጅቷን ፍቅር እያሰበ፣ መውደዱን እሽሩሩ ሲል አርፍዶ፤ የዐይን
ረሃቡ ሲበረታበት የአንድ ሲዲ መግዢያ ጥቂት ብሮች ከየትም ፈላልጎ ወደ
ሱፐር ማርኬቱ ይፈጥናል፡፡
አዎን፣ እዛ ሱፐርማርኬት ውስጥ ያ ምትሃተኛ ፊት በፈገግታ ተጥለቅልቆ
ያገኘዋል፡፡ ይሄ ሲታሰበው እንዳች ፍርሃት የተቀላቀለበት ለሰስ ያለ ደስታ
በውስጡ ሲያልፍ ተሰማው፡፡ ሱፐር ማርኬቱ ሲደርስ አንድ ደቂቃ እንኳ
የማይሞላው የዘወትር፣ የተለመደው የሲዲ ግብይት ይካሄዳል፡፡
“ሲዲ ፈልጌ ነበር” ይላል፡፡
“ልጠቅልልልህ … ?” ትለዋለች፡፡
“አዎ”
ሲዲውን ይዛ ወደ አንድ ጥግ ትሄድና የሲዲውን ጥቅል አምጥታ ትሰጠዋለች፡፡
ሂሳቡን ይከፍላል፡፡
ይወጣል፡፡
በቃ ይሄው ነው የዘወትር የዐይን ረሃቡ ማስታገሻ፡፡ በዚህች ቅፅበት በስርቆሽ
ያየውን መልክ ቀኑን ሙሉ በናፍቆት ሲያመነዥገው ይውልና፣
ደግሞ ነገ ሲመጣ…
በዚህ መልኩ አንዳችም የልቡን ስሜት የሚገልፅ ቃል ሳይተነፍስ፣ ፍቅሩን
ሳይገልፅላት፣ ሰርክ ሲዲ እንዳስጠቀለለ ወራት ተቆጠሩ፡፡
ልጁ ከቀን ቀን ትካዜና ብቸኝነት አመጣ፡፡ ጉዳዩ ግራ ያጋባት እጅጉን
የሚቀራረቡት የአክስቱ ልጅ ‘ምን ሆነሃል ?’ ስትል ጠየቀችው፡፡ ብዙም
ሳያንገራግር ጉዳዩን አጫወታት፡፡ ሳይፈራ ቀርቦ እንዲያናግራትና የልቡን
እንዲነግራት አደፋፈረችው፡፡
ግን የልጁ ዓይናፋርነት በየት በኩል ! እንኳንስ ቀርቦ ማፍቀሩን ሊገልፅላት
ይቅርና እንዲሁም ራሱ እንደ አንዳች ነው የሚፈራት፡፡
በስተመጨረሻ ግን ከብዙ ውትወታ በኋላ ሲዲውን ገዝቶ ሲወጣ የስልክ
ቁጥሩን አስቀምጦላት እንዲወጣ የአክስቱ ልጅ ባቀረበችለት ሀሳብ ተስማማ፡፡
‘አዎን፣ ቢያንስ ልጅቷ አንዳች ስሜት ላንተ ካላት መደወሏ አይቀርም፡፡ ያኔ
ልታወሩ ትችላላችሁ፡፡ ከፈለግክ የልብህን ትነግራታለህ፡፡ አለበለዚያ
መቀራረባችሁም ቢሆን አንድ ነገር ነው፡፡ ቀስ በቀስ የሚሆነው ይታያል፡፡
ካልደወለችልህም ይቀራል’ አለችው፡፡
ተስማማ፡፡
በቀጣዩ ቀን እንደተለመደው ሲዲ እንደሚፈልግ ተናገረ፡፡
“ልጠቅልልህ…” አለችው፡፡
አዎን !
ሲዲውን ልትጠቀልልለት ዞር እንዳለች ቀስ ብሎ የስልክ ቁጥሩ ያለበትን
ብጣሽ ወረቀት አስቀመጠላት፡፡
የተጠቀለለውን ሲዲ ይዛ ስትመጣ ሂሳቡን ከፍሎ በፍጥነት ሱፐርማርኬቱን
ጥሎ ወጣ፡፡
ከሱፐርማርኬቱ እንደወጣ ባከናወነው ድርጊት ረክቶ እፎይ አለ፡፡ ካልደወለችለት
ግን ከእንግዲህ ዓይኗን የሚያይበት ድፍረት እንደማይኖረው ተገነዘበ፡፡ ሀዘን
ተጫጫነው፡፡ ትካዜው በረታ፡፡ ባትደውልልኝስ ሲል ፈራ፡፡ አዎን፣ በዕርግጥም
እኔ ተራ ደምበኛ ነኝ እንጂ ምኗ ነኝ ሲል አሰበ፡፡ እና ምን ልሁን ብላ ነው
የምትደውልልኝ ! ፈፅሞ አታደርገውም፡፡ አትደውልልኝም ሲል ደመደመ፡፡
አለመደወልም ብቻም አይደል - ጉዳዩ ከዚህም የሚከፋበት ሁኔታ አለ፡፡ ጉዳዩን
የሱፐርማርኬቱ ሰራተኞች ሲያውቁበት፣ ‘ውይ ለካንስ ለዚህ ነውና በየቀኑ ሲዲ
የሚገዛው’ እያሉ ሲሳለቁበት ታየው፡፡
አፈረ፡፡
በቀን አንዴ ሳይሳለማት የማይውለውን የልቡን ንግሥት መቼም ቢሆን ላያያት
ነው ማለት ነው፡፡ ይሄ ሲታሰበው እዛው በዛው ናፍቆቱ በርትቶ ሀዘን
ተቀራመተው፡፡ በሀሳብ እንደተዋጠ ደመነፍሱን ወደ አውራ ጎዳናው ወጣ፡፡
በቀጣዩ ቀን ረፋድ ላይ የልጁ ቤት ስልክ ጮኸ፡፡ ደዋይዋ ተፈቃሪዋ ልጅ ነች፡፡
ትላንት ልጁ በሰጣት ስልክ መደወሏ ነው፡፡
የባለታሪኩ የአክስት ልጅ ስልኩን አነሳች፡፡ በስልኩ በዛኛው ጫፍ ያለው
ልስልስ ያለ የሴት ድምፅ ልጁን እንደሚፈልግ ተናገረ፡፡
ምላሹ ግን ልብ ሰባሪ አሳዛኝ ዜና ሆነ፡፡
ልጁ በትላንትናው ዕለት በደረሰበት የመኪና አደጋ ለዘለዓለሙ አሸልቧል፡፡
ሞቷል…፡፡ ትላንት ሀዘን እንደተጫነው፣ በሀሳብ ተውጦ መንገድ ሲያቋርጥ ነበር
የመኪና አደጋው የደረሰበት፡፡
ልጅቷ ጆሮዋን ማመን አልቻለችም፡፡ አንዳች ክፉ ቀልድ ነው የመሰላት፡፡
ከልጅቷጋ የነበረውን ግንኙነት ጠንቅቃ የምታውቀው የልጁ የአክስት ልጅ
ልጅቷን ወደ ቤታቸው ጠራቻት፡፡
አንድም ሀዘንን መካፈል ነው፡፡ አንድም…
ልጅቷ እንደመጣች ሀዘን እንደደቆሳቸው ጥቂት ተጨዋወቱ፡፡ አልበሙን ከፍታ
አሳየቻት፡፡ ሁለት ልቦቻቸው የተሰበሩ እንስቶች! በስተመጨረሻ የልጁን ትዝታ
ለማደስ፣ ለዘለዓለም ያሸለበውን ልጅ ለማስታወስ ወደ ልጁ መኝታ ቤት ይዛት
ሄደች፡፡ ‘ይሄ መኝታ ክፍሉ ነበር፡፡ ሁልጊዜ እዚህ መስኮቱጋ ነበር ተቀምጦ
የሚያነበው እዚህጋ ደግሞ…’ እያለች አስጎበኘቻትና፣ በስተመጨረሻ፣
ቁምሳጥኑን ስትከፍት … ስፍር ቁጥር የሌለው የታሸጉ ሲዲዎች ክምር
ፊታቸው ተገጠገጠ፡፡ ልጅቷ በድንጋጤ ክው አለች፡፡ እነዛ በየቀኑ እየመጣ
የሚገዛቸው ሲዲዎች መሆናቸው ነው፡፡ ሁሉም እንደታሸጉ ናቸው፡፡ ከመሃከላቸው
አንዱም ከታሸገበት አልተፈታም፡፡
ልጅቷ በቀስታ አንዱን የታሸገ ሲዲ አንስታ እሽጉን ስትፈታ ከውስጡ አንድ
ብጣሽ ወረቀት ወደቀ፡፡ ወረቀቱ ላይ እንዲህ የሚል ተጽፏል፡፡ ‘…አንተ ልጅ…
በጣም ደስ ትለኛለህ❤️….ላገኝህ እፈልጋለሁ፡፡ በዚህ ስልክ ቁጥር ልትደውልልኝ
ትችላለህ…..?’ ይልና ከሥሩ ስልክ ቁጥር ሰፍሯል፡፡ ሲዲውን ስትጠቀልልለት
ይሄን ማስታወሻ ፅፋ ውስጡ ያስገባችለት ልጅቷ ራሷው ነች፡፡
የሲዲውን እሽግ ከፍቶ ማስታወሻውን እንዳላየው ስታውቅ እንባዋ ፊቷን
አጠበው፡፡ አሁንም ሌላ የሲዲ እሽግ አንስታ ከፈተች፡፡ አሁንም ሌላ
ማስታወሻ…
‘…እባክህን አንተ ልጅ…ላገኝህ እፈልጋለሁ፡፡ በዚህ ስልክ ቁጥር ደውልልኝ’
እንባዋ ፊቷን እያጠበው የሲዲዎቹን ጥቅል አንድ በአንድ ፈታቻቸው፡፡
ሁሉም የልጅቷን መልዕክት ይዘዋል፡፡
እባክህን አንተ ልጅ…በጣም ደስ ትለኛለህ❤️…ላናግርህ እፈልጋለሁ፡፡ በዚህ ስልክ
ቁጥር ደውልልኝ
እንባዋ አይኗን ጋረደው፡፡
አነባች፡፡
😭😭😭😢😭😭😭
@loverzonn
share share share
🌺የኔ ይበልጥሃል🌺

እጅጉን ብቶደኝ እንደ ነፍስህ አርገህ
ብትቆጥረኝም እንኳን እንደ ሙሉ አለምህ
እንደ ድማቅ ኮኮብ ብትመስለኝም
ከኔ አይወዳደርም...
አንተን የምወድህ ይበልጣል ከኔ ነፍስ
ሙሉ አለም አይበቃም ፍቅሬን ለመተንፈስ
ኮከብ ለምኔ ነው ጨረቃዬ ሆነሃል
ስለዚ ውድዬ የኔ ይበልጥሃል

🍃@loverzonn🍃
#አታፍቅሪኝ



ተኝቸም ቁጭ ብየም በቁሜም ሳስብሽ፤
ለእኔ ሚሆን ቦታ ባይኖርም በልብሽ ፤
ወረተኛ ሁነሽ ለፍቅር ባትሞች፤
ባክሽ እኔ ላፍቅር አታፍቅሪኝ አንች፡፡
መለየት አቅቶኝ ቀን መሽቶ መንጋቱን፤
አንገቴን ደፍቸ ስገፋ ጊዜያቱን፤
በሳቅ በጨዋታ ሰፈሩ ሲቦርቅ፤
ፍቅርሽ ፍቅሬን ሰብሮት ከህል ውሃሽ ስርቅ፤
ሊያጽናናኝ የሚያስብ ባገር ቢሞላም ሰው፤
የፍቅርሽን ስቃይ ብቻየን ልቅመሰው፡፡
የሚያስተሳስረን ያ ቀን እስኪመጣ፤
አንች ሰላም ሁኝ እኔ ሰላም ልጣ፡፡
እስከማገኝ ድረስ ከእንግዲህ አቻየን፡
ባክሽ አታፍቅሪኝ ላፍቅርሽ ብቻየን፡፡



Join Share

@loverzonn
@loverzonn
................... ( #አደራ ) ..................
.
.
ስስ ልቤን አስፍቼ ላይሽ ተንሰፍስፌ፣
ናፍቆት መተንፈሻ፤
ፍቅርሽን ማፈሻ፤
ቃላቶች መርጬ አበባ ታቅፌ።
መሰንበቴን ላክም ናፍቆቴን ልወጣ፣
በቀጠርሽኝ ስፍራ ማልጄ ስመጣ።
ኦና ጎጆ አየሁ ቤትሽ ተቆልፏል፣
ትዝታችን ብቻ፤
በርሽ ላይ ተጥሎ ከዘመን ተኳርፏል።

ያፈቀረሽ ልቤ አንገቱ ቢደፋም፣
ማልዶ የጨለመው ውብ ቀኔ ቢከፋም።
ምንም አልልሽም፣
በክፉ አልስልሽም።
ብቻ..................
አንድም እግር ጥሎሽ፣
ወይ ልብሽ ተሽሎሽ።
ካኮረፈው ጎጆ ከቤትሽ ከመጣሽ፣
ጎንበስ ብለሽ እዪው፤
በርሽ ላይ ያኖርኩት ጠውልጓል አበባሽ።
እናም የኔ ፍቅር፤
የናፍቆት ስጦታ የሞተው አበባ፣
ገለባ ቢሰኝም የፍቅራችን መባ።
እዘኚለት እንጂ አደራ እንዳትንቂው፣
እንባዬን ስላየ፤
እህ ብለሽ ስሚ ህመሜን ጠይቂው።

Joint Share
@loverzonn
@loverzonn
★★★★ወንድሜ ብለሽ ቀርበሽኝ★★★★★★
ወንድሜ ብለሽ ቀርበሽኝ
ቀልደሽ ተጫውተሽ ስቀሽ እያሳቅሽኝ
ሳታውቂው ሄደሻል ፍቅር አሲዘሽኝ
ለካ አንቺ ልብሽን አሳምነሽዋል
ንፁህ ወንድሜ ነው ብለሽ ነግረሽዋል
አልሰማ አለኝሳ የኔን ልብ ብነግረው
አንቺን እንደ እህትህ ውደድልኝ ብለው
ልቤን ብጠይቀው አጫወተኝ ብዙ
በመውደድ መስከሩን በፍቅርሽ መያዙ
ከዚያን ቀን ጀምሮ
ውስጤ ይፈራ ጀመር አንቺን ሲያይ አይኔ
ልቤ ሲሄድ ታየኝ ተለይቶኝ ከኔ
ጠየቁኝ ጓዶቼ
የኔ እንደዚ መሆን ግራ ቢገባቸው
የት እንሂድ ሲሉ አንቺ ጋር ስላቸው
ስለወደድኳት ነው ብዬ ነገርኳቸው
ስቀውብኝ ነበር ምቀልድ መስሏቸው
ጨዋታዬ ጠፍቶ በዝቶ መጨነቄ
ሲገባቸው ዛሬ በፍቅርሽ መውደቄ
ንገራት እያሉኝ እያለፍኩኝ ስቄ
ዘገየሁ
መሄጃሽ ደረሰ ካይኖቼ ልትርቂ
ስታወሪ ላልሰማ ላላይሽ ስትስቂ
ሳልነግርሽ ማፍቀሬን ዛሬ ነገ እያልኩኝ
ሄደሽብኝ አዘንኩ በሀሳብ ባከንኩኝ
ጨዋታሽ ሳይበቃኝ ሳልጠግብሽ አይቼ
ማፍቀሬ ሳይገባሽ ሳልነግርሽ ፈርቼ
መውደዴን ማስረጃ አንደበት አጥቼ
አዘንኩኝ በራሴ ሄደች ያሉኝ ለታ
ጨለመብኝ በቃ ቀኑም እንደማታ
አስጠላኝ ሰፈሩ አንቺ የሌለሽበት
ልቤ ሀዘን ገባው ሄደሽ ቀርተሽበት
ልነግርሽ ወስኜ
ጠይቄ ጓዶቼን ምን ልበላት ብዬ
ብነግርሽ ደፍሬ ፍራቻን ገድዬ
መውደዴን ጠላሽው ማፍቀሬን ገፋሽው
ለስንት የታሰበው በአጭር ቋጨሽው
እኔኮ ሆዴ
አልጠላም ነበረ ባይሽ እንደ እህቴ
ሳላስበው ገብተሽ ባትበይው አንጀቴ
አንቺን መርሳት አልቻልኩ አቃተኝ ሞክሬ
ከሀሳቤ አትጠፊም ትላንት ሲያልፍ ዛሬ
በሀሳብ አይሻለሁ ላይኔ ስትርቂብኝ
ትዝታሽን ብቻ ጥለሽ ሄደሽብኝ
ተጎዳሁኝ ውዴ አንቺን ስል ቀን ማታ
በአካል ነይልኝ በትዝታሽ ፈንታ



Join Share
@loverzonn
@loverzonn
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Alekm eyalegn yeyazegn abaze
Yamelalsegnal beru hul gize
Mknyat felge👀layh emetalew
👀kalayehuma basab maleke new😞😞

Yene lyu lante new tegabezlgn
.......🥰🥰🥰
@loverzonn
@loverzonn
@loverzonn
#ከፍቅር_በላይ
:
:
አፍቅሮኛል እያልሽ ያወጋሽው ወሬ፣
ስንት ጆሮ አልፎ ከኔም ደርሷል ዛሬ።
በኔ መውደድ ታስሮ መላወስ ከብዶታል፣
ያልሺውም ንግግር ከጆሮዬ ገብቷል።
ከራሴው ሳትሰሚ ሳታውቂው እርግጡን፣
የብብትሽን ጣልሽ ስታልሚ ቆጡን።
ሁሉን ሰምቻለው ማን ምንስ እንዳለኝ፣
አንቺ አፍ እንዳለሽ እኔም ጆሮ አለኝ።
:
:
ምንም ይሁን ምንም፣
ስሜን ስላጠፋሽ አላዘንኩብሽም፣
እውነቱ ግን ይህ ነው እኔ አላፈቅርሽም፣
እኔስ አልወድሽም።
:
:
እርግጥ ነው አልክድም...
ከቤትሽ ፊት ለፊት ከዋርካው ጥላ ስር ሁሌ እቀመጣለው፣
ዕድል ያልቀናኝ ለት ያላየውሽ እንደው ጭንቄን አምጣለው፣
ያየውሽም ከሆን እንደ ረጋ ወተት በደስታ እናጣለው።
:
:
እርግጥ ነው አልክድም...
ያ የሰፈራችን ጠብደሉ ጎረምሳ በጨዋታ መሀል ሲሰድብሽ ስሰማ፣
በጣም ተናድጄ ፈንክቼው ሮጬያለው ጠብቄ ጨለማ።
ደግሞም የሆነ ጊዜ በመንገድ እያለፍሽ አንዱ ጓደኛችን የለከፈሽ ለታ፣
ደም ፋላቴ መቶ አዝንቤበታለው የቡጢ ጋጋታ።
:
:
እርግጥ ነው አልክድም...
ሳገኝሽ ስቄያለው ሳጣሽም ከፍቶኛል፣
አንቺን ብቻ እያየው በመንገድ ሳቀናም ስልክ እንጨት ገጭቶኛል፣
ትረፍ ሲለኝ ከላይ መኪናም ስቶኛል።
:
:
እርግጥ ነው አልክድም...
ጎኔና ፍራሼ የገጠሙ ጊዜም በህልሜ አይሻለው፣
ስምሽን ሲጠሩት የጠሩኝም መስሎኝ ስንቴ አቤት ብያለው፣
አዝነሽ ያየው ቀንም ደም እንባ አልቅሻለው።
:
:
ይህንም አልክድም...
ምንም ቢሆን ምንም፣
እኔ አንቺን አልወድም።
:
:
አፍቅሮኛል ብለሽ ስሜን ስላጠፋሽ አላዘንኩብሽም፣
እውነት እውነት ስሚኝ አላፈቀርኩሽም።
:
:
ይህ ፍቅር አይደለም፣
ይህ መውደድ አይደለም፣
ለጓደኞችሽም ዳግም ስታወጊ፣
ከዚህ የተሻለ ሌላ ቃል ፈልጊ።
አፍቅሮኛል ብለሽ ፍቅሬን አትግደዪ፣
ከፍቅር በላይ ነው ያፈቀረኝ በዪ፣
ከመውደድ በላይ ነው የወደደኝ በዪ።
#እኔን_የገረመኝ

ስትፈልጊኝ ነበርኩ ከጊዜዬ በልጠሽ
ቀርቼ አላውቅም አንቺ እኔን ቀጥረሽ
ሰጠሁሽ ያለኝን ከፈልኩ ጊዜና ልብ
ብትንትን አልኩልሽ እስኪርቀኝ ቀልብ
ሁን ያልሽኝን ሆንኩኝ መሆን መች ተሳነኝ
ምን መሰለሽ ታዲያ እኔን የገረመኝ?

ስፈልግሽ ጠፋሽ አለቀብሽ ናፍቆት
ከብሩህ ፊትሽ ላይ ይታይ ጀመር ወረት
አለቀብሽ መውደድ ልብሽ እፎይ አለ
ያንቺስ ተመለሰ የኔ ልብ የታለ?
መሄድሽ አይደለም ህመም ላይ የጣለኝ
ምን መሰለሽ ውዴ እኔን የገረመኝ?

ከመምጣትሽ በላይ አካሄድሽ ግሩም
እንኳንስ ስንብት ሄጃለሁ የለውም
ስለዚህ በይ ይብቃኝ ተውኩኝ መጠበቄን
ሄደሽ አልታመም እሻለሁ መዳኔን

ድሮስ...

ስሜት ነዳን እንጂ መቼ ተፈቃቀርን
ተፋቅረን ቢሆንማ ስንቀር ባልቀረን
ፍርድን እፈርዳለሁ አልሻም የሚዳኝ
መሄድሽ አይደለም እኔንስ የጎዳኝ
ነይ ሳልልሽ መጥተሽ ሂጅ ሳልልሽ መሄድሽ
እምልልሻለሁ ውዴ ልክ ነበርሽ
የመራቅሽ ነገር ምኑ ያስገርማል
ሳይጠሩት የመጣ ሂድ ሳይሉት ይሄዳል

እየሄዳችሁ🧎🚶🏃

yohanes zekarias(የጥቁር ፈርጥ)
🌹🍃🕊...ትመስክር ጨረቃ!

እንዴት እንደምወድሽ ትናገር ጨረቃ
ጠብቀሽ ጠይቂያት ስትወጣ ደምቃ

የሆዴን ሁሉ አንዳችም ሳልደብቅ
አዋያት ነበረ ጠብቂአት በድብቅ

እሷም አታሳፍር ታዳምጠኛለች
ከክዋክብት ጋራ ተገርማ እያየች

ደመናው አይሎ እንዲያው የቀረች ቀን
አይሻልም ምሽቱ ከ ልቤ ሰቀቀን

አሁን አሁንማ........
ክረምቱም ደረሰ ደመናው አየለ
የእኔ ና የእሷም ነገር ከንግዲህ ተለየ

እንዲው ግን ሰሞኑን አንዳች ግር ብሎኛል
ላንቺ ከነበረኝ ጥልቁ ፍቅርሽ ግን የሷ በልጧብኛል።

Join Share
@loverzonn
​​​​♥️••ያልወደደ አበደ••♥️

በሰው የደረሰ. . .
በእኔ ላይ እንዳይደርስ ፣ ስፈራና ስቸር
ወድዴሽ እንዳላብድ ፣ ስጠነቀቅ ነበር !
ታዲያ ምን ያደርጋል ፣
በከንቱ ፍርሀት ፣ ባክኖ መጠንቀቄ
ዋናው እብደት ነበር ፣ ከመውደድ መራቄ።

#yabu

Join & Share

@loverzonn
@loverzonn
​​​​ ┈••◉❖◉●••┈
ላንቺ ስል🌺
:¨·....................:¨:


አፈቀርኩሽ ስልሽ እሺ ባትዪኝም
አቅም ኖሮኝ እኔ ልጠላሽ አልቻልኩም
ባላገኝሽ እንኳን ተጣመሩ ባይለን
መዉደዴን ያሳይሽ ብዬ በመወሰን
"ያንቺ የሆነውን ሁሉን እወዳለሁ"
ብዬ ድሮ ያኔ ቃሌን ሰጥቻለሁ፡፡
እናም ቃል አክብሬ በልቤ አንግቤው
ምትወጂውን ሁሉ ስወድ እኖራለው፡፡
ያፈቀርሽውን ሰው እኔም አፈቀርኩት
ወደሽ ስታገቢው ላንቺ ስል ወደድኩት
የወለድሽውን ልጅ እንዳንቺ አየሁት
ከነጭቃው እኔም እንዳንቺው አቀፍኩት
ይበቃል ሲልልኝ
በጣም ምትወጂያትን ቆንጆ ጓደኛሽን
ላንቺ ስል ወድጂያት ከሷ ፍቅር ያዘኝ
ላንቺ ስል ባፈቅራት ከሷ አጣመረኝ፡

Join & Share

@loverzonn
@loverzonn
👉ፍቅር የለም ከማለትህ በፊት፣ እኔ ውስጥ ፍቅር አለ
ወይ? ብለህ ፈትሽ!
👉ሚስት የምትሆን ሴት የለችም ፣ ከማለትህ በፊት እኔ ባል
መሆን ችላለሁ ወይ? ብለህ ራስህን መርምር!
👉ወንድ እንጂ ባል የለም ከማለትሽ በፊት፣ እኔ ጥሩ ሚስት
መሆን ችላለሁ ወይ? ብለሽ ራስሽን ጠይቂ!
👉ጥሩ ጉዋደኛ የለም ከማለትሽ በፊት እኔ ጥሩ ጉዋደኛ
መሆን ችላለሁ ወይ? ብለሽ አስቢ!
👉ማንም ሰው ጥሩ ከሆነ፣ ጥሩ ነገሮች ሁሉ ከሱ አይርቁም
https://www.tg-me.com/loverzonn keep on sharing
❤️ውዶችዬ ❤️ እስቲ እቺን ተጋበዙልን😍😍

♨️♨️♨️ሴቶች ከወንዶች የሚጠብቋቸዉ ሰባት መገለጫዎች♨️♨️♨️

1💝የትም ብትሆን ሁሌም ያማረ አለባበስ ይኑርህ::

2💝ጠብ አጫሪ አለመሆንህን-የፍቅር ሰው መሆንህን አሳይ::

3💝ተረጋጋ ፣ ዘና ብለህ አሽኮርምማት

4💝ከማዉራት ባሻገር ማድመጥም እንደምትችል አሳያት

5💝ድምፅህን ዝግ አድርገህ ተናገር (ድምፅህ የማማለል ዋነኛ መሳሪያ መሆኑን
አትርሳ)

6💝ስሜቷን ጠብቅላት (እንደሙዳቸዉ ሁን)

7💝ሙሉ ትኩረትህን እሷ ላይ አድርግ (በተለይ እሷ እያወራች ከሆነ ዐይኗን መሸሽ የለብህም)

Join us https://www.tg-me.com/loverzonn
Writer @yaddiii
ወንዶች ደስተኛ ሚሆኑባቸው ሴቶች💑

1/ ❤️ደስታ ልትሰጥክ ከምትችል ሴት ጋር ሁን፡፡

2/ ❤️ትኩረት ከምትሰጥክ ሴት ጋር ሁን

3/ ❤️ስላንተ ከምትጨነቅ ሴት ጋር ሁን

4/ ❤️ከልቧ ከምትወድክ ሴት ጋር ሁን

5/ ❤️ፍፁም ከምትታመንልክ ሴት ጋር ሁን

6/ በመጀመሪያ ግን እነዚ ከላይ ያሉት 5ሴቶች እርስ በእርሳቸው እንደማይተዋወቁ እርግጠኛ ሁን፡፡😂😂😂

@loverzonn
ቃሌን የምሰጥህ ለፌሽታህ ብቻ አልነበረም ህመምህን ልታመምልህ እንጂ……

ቃል የምገባልህ ለፈገግታህ ብቻ አልነበረም እንባህን ላነባልህ እንጂ……

ግን አይገባህም ነበር💔
@loverzonn
2025/07/04 07:19:35
Back to Top
HTML Embed Code: