I don’t think anyone is actually busy, it’s all just a matter of priority.
💯5👍1👌1
ስባሪ ሰማይ ላይ በአበባ እግሮቿ እየተራመደች ነበር::
ልእልት ናት- ከሰማይ ላይ የወደቀች ጊዜ እኔነቷ የጠፋት::
ፀይም ፊቷ የክዋክብትን ፀዳል ለበሷል:: ሳቋ በፍንጭቶቿ መሃል ይሾልካል:: እንደ አካይ ከንፈሮቿ ልስልስ ናቸው::
እንዲህ እንዲያ ነው አይልም ተረኳ- ወጥነትን አይለብስም- ሰሞነኛ ሰማይዋ ላይ እንደዘንባባ ከሚውለበለበው ቀሚሷ ወጥታ ራሷን አንድ የድንጋይ ቅልስ ውስጥ አገኘችው::
የታቀፈችው እርጥብ ህፃን- አይኑን በቅጡ ያልገለጠ ነበር:: የመስኮቱ ወገግታ የቀኑን ከስአትነት ይዘግባል:: ከሽንጧ ቢዘረጋ እስከደብረዘይት ተራራ ሚደርሰውን ቀሚሷን አጣችው:: ጠይም ታፋዋ ላይ የጃጀ ቢጫ ቀሚስ ስታይ ግርታ እንጂ ድንጋጤ አልሞላትም::
የሞላት 'ሀሰት' አለ- ጣእሙ እውነትነትን የተቀባ:: ከምታባብለው ጨቅላ ውጭ ጭር ያለ ቤት ውስጥ ናት:: ከሩቅ የ'አምባሰል' ቅኔ ያለው ቅኝት ትሰማለች:: ክልብ ሰማይዋ ይታወሳታል::
'አንቺ... ማነሽ!'
ከአንገቷ መቃናት ያየቻት ሴት በወፍራም ፊቷ ውስጥ አይኖቿ ተቀብረዋል:: ስትናገር እጆቿ እላይ ታች ይወናጨፋሉ::
'አዲሷ ገረድ ነሽ አይደል? በይ ልጁ እኮ ዳይፐሩ የተቀየረ አይመስለኝም... ቶሎ ብለሽ...'
በምትናገራቸው ቃላቶች ልክ ፍዘቷ ይጨምራል:: የተጠራችበት ስም ያወዛግባታል:: የቱ ህይወቷ እውነት እንደሆነ ይጠፋታል:: ስሟ- የሆነችውን ነው ወይስ የተሰጣት?
ከጆሮዋ ላይ የሚያቃጥል እጅ ሲያርፍባት ሴትዩዋ ያረገችው ቀለበት ተሰማት::
'ምን ያፈዛታል? አትሰሚም እንዴ!'
ከድንጋጤዋ ተንስታ ዳይፐር ፍለጋ መዳከር ጀመረች:: አንድ አይኗ እምባ አመለጠው:: ውዝግቡ ፀናባት:: ፀይም ፀዳሏ ሲፈዝ ተሰማት:: የሀሰቱ ግነት አስደነገጣት:: መልሳ መላልሳ ታስባለች:: ምኑ ነው ሀሰትነቱ? የትኛው እውነት እንደሆነ ማን ያረጋግጣል?
በሰባራ ሰማይ ላይ እንደምትራመድ ልእልት ነኝ ብትል ማን ያምናታል? ሚስቅባት አይበዛም? ትፈራለች- አንዳንዴም በልቧ ደብቃ ልትይዝ ትወዳለች:: ልእልትነቷን በኢ-አማኒ ልባቸው እንዳይከልሱባት::
የወደቀችበት ምድር ከንቱ እንደሆነ ገባት:: እውነት ህልመኛ ሚያስብልበት ጠፈር ላይ እግሮቿ እንዳረፉ ታወቃት:: ከሚወረወሩት ኮከቦች ጋር አብራ ልእልትነቷን ወረወረች:: አለም የጋተቻትን ሀሰት በ'አሜን' ተቀበለች::
ያን ለት ጠዋት- የሚሮጡ ደመናዎች ተሰብሰበው አነቡ::
B’Fkr

❤4👌2❤🔥1
ሀምራዊ ሰማይ ላይ የተፈረካከሱ ደመናዎች ይዘራሉ:: ክረምት መቅረቡን በእንባቸው ያውጃሉ:: መተከዝ ሩቅ አይደለም- ምናልባት አሁን ከገፋም ነገ ነው::
እንደ ውልብታ በትዝታዬ ላይ ዳናዋ ይጎላል:: በእርጥብ ለሊት ረጅም የእግር መንገድ ልግዋዝ እወጣለሁ:: እንቁራሪቶች በጭርጭርታ ጨለማውን ያዋክቡታል:: ውሾች በእጅብታ ይጮሃሉ:: የከተማ መስፋፋት የገፋቸው ጅቦች ከጫካቸው ያላዝናሉ:: ሩቅ አይደለም መገናኛችን- ከቀረበ እዚህ- ከራቀም እዚያ ነው::
የራሴው ኮቴ ይከተለኛል:: ከሩቅ 'ያ ባህርዛፍ' ይታየኛል:: ከእድሜው ብዛት አጎንብሷል:: ከቆዳችን አንዱ ቦታ ላይ ስንጥሩ ተሰክቷል:: ህመሙ ሳይቀዘቅዝ ይጠዘጥዛል:: ከሱ እንዳለፍኩ የጎበጠች ላስቲክ ቤት ተተክላለች:: ምን ያህል ዝናብ ተጠለልንባት? ቀዝቃዛ እጆችሽ እጄ ላይ ተሰሙኝ:: *የት ነሽ?
ሀምራዊ አበቦች ወደ ኮከቦች ያርጋሉ:: ምን ያህል እንደምግዋዝ ራሴን ጠይቃለው:: የትዝታ መንገድ መጨረሻው የት ነው?
B’Fkr
*የትዝታ ግነቱ ከምናወሳው ሰው ርቀት ዘንድ አይለካም:: መደብ ላይ ተቃቅፎ ሚነፋፈቅ አለ:: ትዝታ ያጣንው ነገር ህላዌ ነው:: ዛሬ ምናየው ሰው ውስጥ ምንናፍቀው ትናንት የነበሩት ሰው አለ- ያ የትላንቱ ሰው ምን ያህል ሩቅ ነው? ጊዜን በርቀት ሚለውጥልን አለ? ያን ሰው ለማግኘትስ ምን ያህል መግዋዝ አለብን?

❤3
‘It’s unfair, Life, all this, is senseless’
‘The communion of unfair, doesn’t this all make it, like, fair?’
It was a breathless night. The stars seduce our thoughts away. We wonder if the night could stretch and we can age like wine, pretty and complex. Her little movements speak to my being but my entity listens to her eyes. She tries to sneak in a pierced leaf in to my hair. With each moment she gets close to me, I could feel her smelling like home.
I remember those old times, with my grandma standing across the kitchen counter, buttering the slice of bread she bought. I could see the reflection of the knife afar, when she worded her thoughts, saying, ‘It’s never the right time.’
The reflection of the stars, bouncing on her eyes pulls me back to now. I repeat the same words my grandma said in my head, ‘it’s never…’
‘Fair, Unfair… I believe in the poise of our uncertain life’
She says, rolling her eyes on the sky.
‘The happy ending is never universal. Someone is always left behind.‘
Words scratch in me but my tongue wither in my throat from unhappy silence. I wonder through the moment looking at the sky that spread itself.
‘It’s never the right time.’

❤5
'አስቴር- ቡና አለ ?'
'አስቴር አስቴር እያላቹሃት በድምፅዋ ስታደነቁረኝ ነው የዋለችው'
አለ- አንድ የህንፃው ዘበኛ- ቀን ቀን ከጀበናው ዞር አይልም- የማታውንም አንድዬ ና ጨረቃ ነው ሚያቁት::
'የት አግኝተህ እቴ- ዪሄ ድምፅ አይዶል ላይ ሚፈለግ ነው እኮ- ሾካካ'
'አስቴ- ቲ- ገነት- ይሄን ስኳር ቀይሪ አላልኩሽም'
ጠረፔዛ ላይ ያሰፈረቻትን ሲኒ ወደ መሃል ጠጋ አረኩአት:: ኢ-እርግጠኝነት ያመክነኛል:: በየመሃሉ ወደ አንድ ዘፈን ስትሰብር ይሰማኛል:: 'በሰባራ ፎሌ...'
ቡናው ሲፈስ የተዋከበ ስክነት አለው:: ወደ ግራ ወደ ቀኝ ሚተርፉት ነጠብጣቦች የራሳቸውን ክልል ይይዛሉ:: ጥቃቃን አበቦች ገላዋ ላይ የሰፋችው ሲኒ ሞልታ ጥቃቅን እንባዎች ሰውነቷን ታከው ወረዱ:: እንድትቀጥል ፈለኩ:: ከጀበናው ሚወርደው ቡና ወለሉን እንዲሞላው- ጎዳናው እንዲጥለቀለቅ- ሰው ከነልብሱ እንዲነከርበት- እንዲነፃ- እንዲሰክር- ሰማይ ጫፍ ደርሶ የደመናው ጭራ እስኪሰምጥ- አለም ቡኒ እስክትሆን- ሁላችንም *እስክን'ቦንን'...
በሲኒ የተገደበችውን ቡና ፎተትኩ::
አስቴር ስኳር መቀየር አለባት::
በፍ'

👍4😁1
The walking was never actually walking, but the act of spreading oneself in to borderless dimensions, to get lost, to get away from anything that haunts you.
You, intact, needlessly bleed your heart onto the streets where no one will notice it. The slow dancing trees care more about their rhythm than your wrangles. The seeking, the tiring process of nothing but patience, dries your soul arid. Everyday, you cycle back to the same spot, you return to your tears that reflect the golden array of the setting dusk. The sky howls the end of the day, but you are still there, embarking hope on to the night.
You remind yourselves of the words of the Rabbi, the messiah, who said,
You scatter again, pleading peace for your battles, to then find out, you were the constraint, the limit for your answers. The sky speak volume to you, the clouds stretch themselves across the summer, for you to see there actually is nothing of a concept called a new day but a new you, a new wineskin, ready to be poured in life and not burst.

And no one pours new wine into old wineskins. If he does, the wine will burst the skins, and both the wine and the wineskins will be ruined. No, he pours new wine into new wineskins.” Mar 2:22.
You scatter again, pleading peace for your battles, to then find out, you were the constraint, the limit for your answers. The sky speak volume to you, the clouds stretch themselves across the summer, for you to see there actually is nothing of a concept called a new day but a new you, a new wineskin, ready to be poured in life and not burst.
B’Fkr
❤5👌2
እድሜዬን በውል ያወቀ ቀን- አንገቱ ላይ ሚጥላትን ጋቢ እንኳን ዞሮ ሳይፈልጋት ጥሎኝ ወጣ::
ያን ሌት ጋቢውን ይዤ በተፈጥሮዬ አነባው:: ጋቢው ንፁህ የላቡን እትማት ተሸክማለች:: እንደ ሃምሌ ማለዳ አየር መአዛውን ማጉት:: የመጀመሪያ ፍቅሬ አይደለም- በፍቅር የመጨረሻ እድሌ እንጂ::
'የእንትና ልጅ ከአዲስ አበባ መታለች' ሲባል ብዙ ወንድ ከደጃፌ ተከመረ:: ከጡቴ መሃል ጨብጬ የያዝኳት የአስራ አምስት ልፋቴን ወሽቄ በመልኬ እና ጠባዬ እንዲወዱኝ ተራ በተራ ተዋወቅሁአቸው:: ያገባሁት የመጀመሪያ ባሌ የአባቴ ግዋደኛ ልጅ ነበር:: ዝምድናውን ፍለጋ ሁሉም አጣድፈው ዳሩን:: የተጠመቀው ጠጅ እና ጠላ ከጣና የገዘፈ ነበር:: አባቴም የቀሩትን ሁለት በሬዎቹን አረደ:: ዜናው እስከ ተረሮቹ ጫፍ ተዳረሰ::
በተጋባን ባመቱ መሬት በገንዘቤ ገዛን:: ከዚያች ቀን ጀምሮ በመደቡ ላይ ሚነደው ወላፈናችን መደብዘዝ ጀመረች:: መሽቶ ጉበናችን እንደተገረበበ መጨቃጨቅ በዛ:: ብዙም ጀምበሮች ሳይኖግዱ እቃውን ሸክፎ ማለዳ ዶሮ ሳትጮህ ከድንኳናችን ወጣ:: የሽማግሌ ጥረትም ብዙ ሳይፈይድ መሬቱን ለሁለት ሽጠን ተከፋፈልን::
ወራቶች ተንሸራተው ብዙም ሳይርቁ እናቴ እድሜዬን ታስታውሰኝ ጀመረች:: 'ወጉ እንዳይቀርብሽ':: 'የሴቶች መጠቋቀሚያ እንዳትሆኚ(እንዳታረጊኝ)':: 'ቆመሽ እንዳትቀሪ'::
በዚህ ሁሉ ፍርሃት ሰበበ ድርጊት ሆኖ ሌላ ባል ትፈልጋለች ተባለ:: ፀሀይ ስትጠልቅ አንድ ሰው የቤቴን በር ገረበበ:: እምብዛም ፊቱን እንዳላይ ኩራዜ ደክማለች:: ስሜን በቀስታ ጠርቶ አቤቴን ጠበቀ:: በመደቡ ዳር ተቅምጦ በደከም ድምፁ ለስሙ መታወሻ እንደሚፈልግ ነገረኝ:: ፍርሀት አውሮኝ ይሆን ጨለማው ልቤ በዝምታ አመነው:: ብዙም አልቆየም ራሴን በሁለተኛ ትዳር ዳስ ውስጥ አገኘሁት::
አመት ሁለት አመት ሄደ:: ከስራ ሲመጣ እግሮቹን ካጠብኩ በህዋላ ረጃጅም ቅልጥሞቹን አሻለው:: ያሰናዳሁትን ምግብ ወገቤ ሳይቃና እስኪበላ ጠብቃለው:: ወላፈኑን ራቅ አድርጌ ቡና አፈላለታለው:: እሱን በመንከባከብ ውስጥ ህይወትን ዘራው::
አንድ ምሽት ከወትሮ ፀጥ ባለ መንፈስ ተቀምጠን ነበር:: አንገቱን ዝቅ እንዳደረገ የልቤን ሸክላነት የፈተነ ጥያቄ የጠየቀኝ:: 'መሃን ነሽ እንዴ?'
እንባዬ ከሚቀጣጠለው ነበልባል ላይ አረፈ:: የምፈልጋቸው ቃላቶች አፌ ላይ እስኪሰነደሩ ጠበኩ::
'አልሰማሽኝም እንዴ?'
ሰምቼው ነበረ:: በውስጤ ግን ለቤተሰቤ ስል የሰዋሁትን እድሜ እንዴት እንደማስረዳው ጠፋኝ:: በተሰዋው እድሜዬ ውስጥ አብሬ የሸኘሁትን ሴትነቴን እንዴት ልንገረው?
'እድሜሽ ስንት ነው?'
ነገርኩት:: ቆዳዬ ባይጃጅም ያረጀሁ ሚያስመስለኝን የእድሜዬን ቁጥር ነገርኩት:: ተንስቶ ሊወጣ ሲል ክንዱን ይዤ የሆኑ ቃላቶች አነበነብኩኝ:: ለኔም ለሱም ትርጉም አልሰጡንም ነበር::
ራሴን ተጠያቂ ማረግ ፈራው:: ቤተሰቦቼ ላይ: እድሜዬ ላይ: ሴትነቴ ላይ ፈረድኩ::
በጋ ሳይጠባ የራሴን ፀጉር ላጨሁት::
በ'ፍቅ...

👍8❤1