ቀን እንደ ናና ከረሜላ ሳይጠገብ ሚሟሟበት ከተማ ውስጥ እንኖራለን:: ሊስትሮው ዝናቡ የቀደሰለትን የእለት እንጀራ ያጭዳል:: ተላካፊ ረዳት የሰፈር ስም ይጠራል:: የመሸበት ሰራተኛ በዝለት ይራመዳል:: በወፍራም ሽቶ የታጠነ ነጠላ የጠመጠሙ አዛውንቶች ብርድን ያማሉ:: ያለፈው ጥር ያንቀላፉ ነፍሳት ጥር ሲደግም ይነቃሉ:: ሶስት ሰዎች ፣ የልብሳቸው ቀለም እንደ ባንዲራ ተዛንፎ የተሳከረ ፣ ቆመው ይሳሳቃሉ:: የህይወት ሀቅ መንገደኛ መሆኑን ይረሳሉ:: ዛሬ ቢያልፍ ነገ ይቀጥላል:: አስፋልቱ መሃል ከደመና የተፀነሰ ኩሬ ይተኛል:: የሹፌር እርግማን ይጠጣል:: ተሻጋሪ መልኩን ያይበታል:: አውቶብስ እንደ እባብ ይርመሰመሳል:: የመንገድ አምፖሎች ፈዛዛ ብርሃን ይለግሳሉ:: ፀሀይ በልዝብ ስንብት ይጠልቃል:: የጨለማ ወጋገን እንደወረርሽኝ ሰማይ ይሞላል:: ሽፍታ ዝንጉ ሰው በአይኑ ያስሳል:: ችኩል እርምጃዎች ይበረታሉ:: ተገናኝተው የቆዩ ሰዎች ባልጠበቁት ጎዳና ላይ ይገጣጠማሉ:: ታክሲ ሰው ይደርባል:: የታሪፍ ዋጋ ያሰዳድባል:: ሹፌር ትራፊክ ሲያይ ሃይማኖቱ ይታወሰዋል:: ቀኑ አራት ነጥቡ ላይ ይደርሳል:: ጭለማው ሁሉንም ያመሳስላል:: ወዳጆች በ'ቻው' 'ቻው' ይለያያሉ::
ዛሬም ትናንት ይሆናል::
ዛሬም ትናንት ይሆናል::
👌5
ሃብሏ ደረቴ ላይ ተኝቷል:: ወርቃማ መስቀል::
'ሞተሽ አልነበር እንዴ?'
አይኗን አሸች::
'ከሞት በህዋላ ምን ያለ ይመስልሃል'
መሽቷል:: ደቃቃ ኮከቦች ፀይም ሰማይ ላይ እንደ ጨው ተበትነዋል::
'እምነት'
አይኗን አሸች::
'ለምን?'
'ምርጫ አለን?'
ጥርሷ የሐምሌ ጨረቃ:: ያፅናናል::
'አንቺስ'
'ትነት'
በአይኔ አይኗን ፈልጋለው:: ትኩስ እስትንፈሷ አንገቴን በስሱ ይገርፋል::
'እንደተረሳች ውሃ ጠብታ... ምተን ይመስለኛል'
ለደቂቃዎች የልቤ ምት ብቻ ይሰማል:: ትከሻዬ ላይ ሚፋጅ እንባ ከጉንጯ ያርፋል:: አንድ ጠብታ... የጉንጯን እጥፋት የሚከተል ዳና::
'አለአ... ስተን ግን የተለያየ ቦታ ምበተን ይመስለኛል:: የቡና ሃሜት ላይ- የስካር ታሪኮች ሲወዙ- ቡኒ ቀለም ሲነሳ- በደበዘዙ ጠባሳዎች ውስጥ... አላቅም... ምታወስ ይመስለኛል:: የትውስታው እድሜ ግን እንደ ትነት ነው:: ስሜ በተጠራ በዛው ቅፅበት ይረሳል::'
የተናገረችውን ሁለታችንም በፀጥታ ለመዋጥ እንታገላለን:: ጣራው ከወትሮው በላይ የቀረበ ይመስላል::
'መች ኖረህ ነው ግን ሞት ሚያስጨንቅህ?'
ምናልባት ልክ ነች:: ደክሞኛል:: አይኖቼን በስሱ ለመክደን እታገላለው:: የሰጠችኝን ሃብል በጣቶቼ ፈልጋለው::
...

❤2
በቆሎ ሻጯ ትዝ ትልሃለች? ያቺ ምስኪን ጠይም እናት የጨሰች ቢጫ ካኔቴራ ምታዘወትር ልጇ ከጡቷ ማይጠፋ? እንዴት ትረሳታላህ? ጭምት ፊት እና ችግሯን ሚክድ ፈገግታ ነበራት:: ልጇ አድጎ መንገድ ላይ አመድ ልሶ ሲሯሯጥ አገኘሁት:: እሷን አይመስልም:: ጠርቼው እናትህስ? ስለው ማናባህ ነህ ብሎኝ ሮጠ:: ጀርባ ጀርባውን እየሰጠኝ እየተከተልኩት እንዳልሆነ ለማየት አስሬ ወደ እኔ እያየ ሲሮጥ አድጦት ገኒ ሱቅ ፊት ያለው ቱቦ ውስጥ ፈረጠ:: ሮጬ ስደርስ ወጥቶ ለማምለጥ ይታገላል:: ግማሽ ሰውነቱ ተለውሷል:: ደህና ነህ? ስለው ግራ ትከሻውን ይዞ እያነከሰ ለመሮጥ ሞከረ:: እዛው ከገኒ ሱቅ አቦለድ ገዛሁለት:: ትንሽ ፍርሃቱ ለቀቀው:: እኔ ፊት መብላት አልፈለገም:: እናትህን ሰላም በላት ብዬው ወደ ቤቴ ገባሁ:: አንዳንዴ ሁሉም ታሪክ እንዳለው ይዘነጋኛል:: ማን የማን እንደሚበልጥ እድል ፈራጅ ነች:: በነጋታው በቆሎ በምትሸጥበት መንገድ ከስራ ተመለስኩ:: ልጇ ከጎኗ ተደግፏት ከሰል ያርገበግባል:: ቀና ብሎ አየት አድርጎኝ አንገቱን ደፋ:: በቆሎ ተወዷል:: ትኩስ ካለ ስጠይቃት እዛው እሳቱ ላይ ከነበረው ጠቅልላ ሰጠችኝ:: ጭምት መልኳ አልፈዘዘም:: ሁለት ጨምሪልኝ አልኳት:: እሳቱ ላይ የቀሩትን ሁለት ጠቅላላ ልትሰጠኝ ስትል አንዱን ለእሷ እና አንዱ ለእሱ እንድታደርግ ነገርኳት:: ፈገግታዋ ሲያምር:: አጠገባቸው ያለ ድንጋይ ላይ ተመቻቼ ተቀመጥኩ:: ብዙ አታወራም:: ከልጇ ጋር ስለኳስ አወራን:: በቆሎዬ ሲያልቅ ተነሳው:: በደንብ ሲጨልም ታወቀኝ:: ሰፈሩ አይታመንም:: ቤት ገብቼ ጥሩ እንቅልፍ ተኛው:: እድል ፈራጅ ብትሆንም ማቅለያ አንቀፅ ግን ለሰው- ሰው ነው::
👌8❤1👍1🤯1
በስሱ ክርኑን ተደግፋ ወደ ጆሮው ትጠጋለች::
'ይሄ ጫማ ሊገለኝ ነው- መኪና ውስጥ ሌላ ጫማ ይዣለው'
ተደጋግፈው ይሄዳሉ:: የአዳራሹ እንፋሎት ግንባራቸው ላይ ተቸፍችፏል::
'ምግቡ ተስማማሽ?'
'መች በላው በናትህ... አስሬ እዚህ እዚያ ሲያዋክቡኝ ታቲ ካጎረሰችኝ በቀር አልቀመስኩም'
'ታቲ አምሮባታል'
'ሁሉን ድራ ጨረሰች... ከእኔ ውጭ'
የመኪናውን በር ይከፍትላታል:: ለጥቂት ደቂቃዎች በዝምታ ይቀመጣሉ::
'ጫማሽን አቀይሪም እንዴ?'
'ከጀርባ ነው መሰለኝ'
ቢጫ ፌስታል ይዞ ይመለሳል::
'ወገቤ እየተንቀጠቀጠ ነው'
ጫማዋን ለመቀየር ታጎነብሳለች:: እህቷ ደወለች:: በዝምታ ከሰማቻት በህዋላ 'እሺ- በቃ ባይ' ብላ ትዘጋዋለች::
'ለእሷም ተቀያሪ ጫማ ትፈልጋለች... በዛውም ለዚህ እግሬ አልኮል ነገር ቤት ሄደን እናድርግበት'
እግሯ አግድሞሽ ላይ ቀይ የቁስል ሰንሰለት ተኝቷል:: ቤቷ ቅርብ ነው:: መኪናውን ያስነሳል:: የአምስት ደቂቃ መንገድ ብትሆንም ዝምታቸው ደቂቃውን ይለጥጠዋል:: በቅጡ ማይሰማ የሬዲዮ ድምፅ ይንሾካሾካል:: ቤቷ ሲደርሱ የጠዋቱ የሽቶ ጠአም አልፈዘዘም:: ለቤቷ ባዳ አይደለም::
'አልኮል የት ነው ምታረጊው?'
'ሳሎን ያለውን ባለአምስት መሳቢያ ቼክ አርግ'
'የለም?'
'እ?'
ከመኝታ ቤት ሚሰማው ድምፅዋ ይዋጣል::
'አምስቱም ውስጥ የለም?'
'አዎ... እኔ ቤት first aid አለኝ'
'እሺ በቃ'
በነጭ ፌስታል ጫማ ጠቅልላ ይወጣሉ:: ቤቱ ጥቂት ደቂቃዎች ቢርቅ ነው:: ማይተነትኑት ዝምታ እንደ መልህቅ ይዘፍቃቸዋል:: ያልፈቱት ቋት አለ:: ቃላት ማይበትኑት:: ቤቱ ሲደርሱ ወፍራም የቀለም ሽታ ይቀበላቸዋል:: ግራጫ ሶፋው ላይ በቀስታ ትቀመጣለች:: ከመታጠቢያ ቤት አልኮል እና ጥጥ ይዞ ይመጣል:: ሶፋው ላይ እንደተቀመጠች በስሱ ተንበርክኮ ጫማዋን ያወልቃል::
'መች ነው ይህን ስእል የሳልከው?'
ክፍሉ ጥግ ላይ በጀርባው የተደገፈውን ስእል በአገጯ እየጠቆመች:: ዞሮ ያየዋል::
'ትናንት ማታ'
'ያምራል'
በዝምታ የቁስሏን መስመር ቀስ ብሎ ያክማል::
'ምን ማለት ነው?'
ስእሉ ሁለት ጥንዶች አጠገብ ለአጠገብ ሆኖ ሲራመዱ የተቀዳ ነው:: ፊታቸው ላይ ሚነበብ የተራቆተ ስሜት አለ::
እግሯን ቀስ ብሎ ምንጣፉ ላይ ያሳርፋል::
'ሃሙስ የሆነ ፊልም እያየው የሳልኩት ነው... እስካሁን ስም ብቻ ነው የሰጠሁት'
'The illusion of parallel points’
ድምፅዋ ቀዝቅዟል::
'መች ነው ግን እንደዚህ ባዳ የሆንነው?'
ቀና ብሎ አይኗን ይፈልጋል:: መልስ ያጣል:: ቃላት የይሁዳ ለምዳቸውን ይለብሳሉ:: አይኗን ማየት ይቀጥላል:: መራራቅ ድንኳኑን በመሃላቸው ተክሏል:: ለእርስ በእርሳቸው ብቻ ሳይሆን ለስሜታቸው ባዳ ሆነዋል:: በዝምታ ዘላለምን የመሰሉ ደቂቃዎች እንደገና ይፈሳሉ::
'ለህክምናው አመሰግናለው'
ለመነሳት ስትጥር ያልደረቀው ቁስሏ ጠዝጥዟት ወደ ሶፋው ቀስ ብላ ተመለሰች:: አጠገቧ ከምንጣፉ ላይ ተነስቶ ተቀመጠ:: የላባቸው እና የሽቶ ድቃይ በመካከላቸው ይሰፋል:: ጭንቅላቷን ትከሻው ላይ ዘረረች:: ሁለቱም ጀርባውን ከክሬሙ ግድግዳ ላይ ከተደገፈው ስእል ጋር ይፋጠጣሉ:: የስሜት ትግሉ አዝሏቸዋል:: ቃል ቢሰጡት የተሳሳተ ትርጉም እንዳያለብሱት ይፈራሉ:: ጣቶቻቸው ይፈላለጋሉ::
'ፊልሙን ሳየው ይህ ቅፅበት ለምን እንደሆነ አላውቅም... ከበደኝ:: አንድ ላይ ሚሄዱ ሰዎች... ፊት ለፊት ስታያቸው እንድ ላይ እየተራመዱ ያለ ይመስላል:: ከጎን ሆነሽ ስታዪው ግን ወይ ሴቷ ወይ ወንዱ ቀደም ብለው እየተራመዱ ይሆናል:: ማን ያቃል? አብዛኛው ትዳር እንደዛ ይሆናል ሚያበቃው:: እስከሆነ ጊዜ ድረስ አንድ ላይ የሆኑ ይመስልና ግን በመካከላቸው የተሰወረ ክፍተት ይኖራል'
ለደቂቃዎች ሲያወራ በዝምታ አይኑን እና ከንፈሩን እየቀያየረች ትመለከታለች::
'እና...'
'ምን?'
'እኔ ነኝ ወይስ አንተ ... ቀደም ያልንው?'

❤🔥3👍1