ዛሬ ማታ በአሏህ ፍቃድ ይለቀቃል
አዲስ ታሪክ ''ሀ'' ብለን መጀመራችን የታወቀ ነው።
ርዕሱ ''መጅኑን ለይላ''
ክፍል 12
ዛሬ ማታ በጊዜ 4:00
ቻናላችንን join & share ያድርጉ
👇👇👇
@mahbubil
አዲስ ታሪክ ''ሀ'' ብለን መጀመራችን የታወቀ ነው።
ርዕሱ ''መጅኑን ለይላ''
ክፍል 12
ዛሬ ማታ በጊዜ 4:00
ቻናላችንን join & share ያድርጉ
👇👇👇
@mahbubil
❤4
(መጅኑነ ለይላ)
ክፍል 12
✍መሊኩ [ MAJNUN ]
ኸሊለየ ማአርጁ ሚነል አይሺ በእደ ማ
አራ ሀጀቲ ቱሽራ ወላ ቱሽተራ ሊያ
ፈቀዷሀ ሊገይሪ ወብተላኒ ቢሁቢሀ
ፈሀላ ቢሸይኢን ገይሪ ለይላ ኢብተላኒያ
፡
አንተ ጓደኛዬ ሆይ የኔ ህይወት ካሁን በኀላ ምን ዋጋ አለው? ህይወቴን አልፈልገውም፡፡ ምክነያቱም የኔ ፍላጎት እየተሸጠ ነው፡፡ እኔ ደግሞ ፍላጎቴን ማሟላት አልችልም፡፡ ለይላን ለሌላ ሰው ሊድሯት ነው፡፡
:
አላህ እኮ ለይላን የሌላ ሰው ስጦታ አደረጋት፡፡ ለኔ አላደረጋትም፡፡ ነገር ግን የፍቅርሯ ፈተና የተሰጠው ለኔ ነው፡፡ ጌታዬ ሆይ????? ምናለ በሷ ፍቅር ባትፈትነኝ፡፡ ምናለ ከለይላ ፍቅር ውጭ በሆነ ነገር ብትፈትነኝ"፡፡ እያለ ሳግ በሚተናነቀው ሰላላ ድምፁ ሲያነበንብ ለይላ ደረሰች፡፡ አሊ እና ጓደኞቹም ለይላ እንደመጣች ሲመለከቱ እንደሚታረድ በሬ ከመሬት አጋድመው የያዙት ጓደኛቸውን ለቀቁት፡፡ ለይላዬ መጣሽ? ተመልከች... ሁሉም ለኔና አንቺ አጥር እያበጀ ሊለያየን ይታትራል፡፡ ይሄው አሁን ደግሞ ጭራሽ አንቺን ለሌላ ሰው ሊድሩሽ እንደሆነ ሰማሁ፡፡ እውነት ነው የምሰማው? እባክሽ ውሸት ነው በይኝ፡፡ አለ መጅኑን፡፡ ለይላም እንባ እያነቃተሸ ጭንቅላቷን ወደላይ ወደታች ነቅንቃ አዎንታዊ መልስ ባንገቷ መለሰችለት፡፡ እና ምን እንጠብቃለን እንጥፋ ፣ እንሽሽ! በጀበሉ ሰውባን ያለምነውን ህይወት ከምንኖርበት የኔና አንቺ አለም እንሂዳ! ሁሉንም እዚህ ትተን አንጥፋ! ተከተይኝ ብሏት ከትቢያው ላይ ተነሳ፡፡ ለይላ በሚያነቡ አይኖቿ ቡዝዝ ብላ አስተዋለችው፡፡ ጥያቄውን ተቀብላ አብራው ብትኮበልል የሁለቱም እጣ ፋንታ ምን ሊሆን እንደሚችል አሰበችው፡፡ አባቷ ሰእድ በሄዱበት ሁሉ ዳናቸውን ተከትሎ ሰላም እንደማይሰጣቸውና በህይወት እንዲኖሩ በፍፁም እንደማይፈቅድላቸው ታውቃለች፡፡ ስለዚህ "አይ አይሆንም! አሁን እኔ ላገባ ነው፡፡ ይህን እውነት ተቀበል፡፡ በቃ እርሳኝ!" ብላ ለመጨረሻ ልትሰናበተው ቆርጣለች፡፡ በርግጥ ውሳኔዋ ምስቅልቅል ህይወታቸው ባይባጀውም ግና ከነፍሷ በላይ የምትወደው እሱን በህይወት ያቆይልኛል ብላ አስባ እየከበዳትም ቢሆን ልትነግረው ወስናለች፡፡ ግን ደግሞ ቃሉ ከጉሮሮዋ ተሰንቅሮ አውጥታ ልትናገረው አቃታት፡፡ ምን ያክል መጅኑንን ሊጎዳው እንደሚችል ታውቃለችና ከበዳት፡፡ ባንድ በኩል ያለው ውሳኔዋ ደግሞ እስከ መጨረሻ የሚገድለው ነውና ልትሰናበተው ቆረጠች፡፡ መጅኑንም በያ ተከተይኝ እያለ እጁን ዘርግቶ ወደ መንገዱ ጋበዛት፡፡ በመጨረሻ የሞት ሞቷን "አይ ፣ አይ አይሆንም"! እያለች ጭንቅላቷን ወዘወዘች፡፡
መጅኑን የለይላን እምቢታ በሰማበት ቅፅበት በፍላፃ እንደተወጋ ሰው በቁሙ ተዝለፍልፎ በንብርክኩ ፈገመ፡፡ እሬት እንደቀመሰ ብላቴና ፊቱ በቅፅበት ተገለባብጦ ከንፈሩ እየተንቀጠቀጠ ማ....ማ...ማለት? መንገዴ መንገድሽ አይደለም? እውነትም እንደሚሉት እሱ በልጦብሻል? ለይላዬ እውነት የሌላን ሰው ቃል ኪዳን ልታጠልቂ በልብሽ የነበረን የኔን ኪዳን ፋቅሽው? አላት፡፡ ለይላም የሚንቀጠቀጥ እጇን አፏ ላይ ጭና ከማልቀስ ውጭ መልስ አጣችለት፡፡ አንደበቷ ሲዋሽ አይኖቿ ያንደበቷን ውሸት አስተባብለው ያንጀቷን እውነት ሊናገሩ ያነባሉ፡፡ ምነው ለይላዬ አነስኩብሽ? እብድ ነው አሉሽ አይደል? ግን እኮ ሁሉም ስላንቺ ነበር፡፡ ግን እኮ ቃል ተገባብተን ነበር? ውላችን እኮ እስከ ወዲያኛው ጀነት ድረስ ነበር! በቃ? ታዳ ይህ ነው መጨረሻው? መልሺልኛ!!!!! ላንቺ ጀነቱ ይህ ነው? ላንቺ ይሄን ያክል ቀላል ነው ወይይይይይ? እያለ ከመሬት እራሱን እያላተመ ጮኸ ፣ ሰከረ፡፡ ለይላም እንዲያ ሲሆን ማየት ተስኗት ከግቢ ወጥታ እሮጠች፡፡ ሰው እንደገደለ ሰው እያንዘፈዘፋት በመከራ ቤቷ ደረሰች፡፡ ከዛን ጊዜ በኀላ መጅኑንም ላይመለስ ነጅድን ለቆ ወደ ሂጃዝ ጫካ አቀና፡፡ ከለይላ ያለውን ተስፋ በለይላ ቃል አሟጦ ገደፈ፡፡ ዘላለሙን ላያገኛት ግና ዘላለሙን እንዲያፈቅራት የተፈረደበትን እጣፋንታውን ተቀበሎ ከነጅድ ኮበለለ፡፡ እንደዋዛ ሳምንታቶችም ነጎዱ የለይላ ቤተሰቦች እና የወርድ ቤተሰቦች የልጆቻቸውን የሰርግ ቀን ቆርጠው የሰርጉ ሽርንጉድ በሁለቱም በኩል ተጧጡፏል፡፡ ለይላ የሰርጓን ቀን ምድር እንደምትጠፋበት የመጨረሻው ቀን በፍርሀት እየራደች ስትጠብቀው ቀኑ ደርሶ ከወርድ ጋር ተሞሸረች፡፡ ህይወቷን ሙሉ ያለመችው ከመጅኑን ጋር የመኖር ህልሟ ጨነገፈ፡፡ ልቧን ሌላ ሰው ጋር ገላዋን ሌላኛው ጋር እንድታሳድር ህይወት ፈረደችባት፡፡ ቀን በቀን መጅኑንን እያሰበች ብታነባም አንዴ የወሰነችውን ውሳኔ መልሳ ሽራ ነገሮችን መመለስ አትችልም፡፡ በዚህም ምክነያት ህይወቷን አምርራ ጠላችው፡፡ መጅኑን የሌለበት አለሟ ውስጥ መተንፈስ ቀፈፋት፡፡ ከምግብም ከውሀም ተከልክላ እራሷን ቀጣች፡፡ በየ ቀኑ ስለ መጅኑን እያብሰለሰለች ሰለለች፡፡ ከነጅድ የሚመጣን የነጅድ ነዋሪ ባገኘች ጊዜ ስለሱ ከመጠየቅ ቦዝና አታውቅም፡፡ አንድ ጊዜ ዲመሽቅ የሚመላለሰው ነጋዴው አሊን አግኝታ ለመጅኑን ደብዳቤ ያደርስላት ዘንድ ከአደራ ጋር ሰጠችው፡፡ አሊም ወደ ነጅድ እንደተመለሰ በሂጃዝ ጫካዎች መጅኑንን አፈላልጎ በአደራ የተሰጠውን ደብዳቤ ሰጠው፡፡
መጅኑን የደብዳቤውን አምቦልክ እየተጣደፈ ከፍቶ ከቆዳ ተልጎ በተሰራው ወረቀት ላይ የሰፈሩት የለይላ ቃላቶች ለይ አይኑን ቀሰረ፡፡ ለመጅኑን ከቃላትነት ባሻገር ጥልቅ ስሜት አላቸው፡፡
፡
<<ሀቢቢ ካለህበት ሁነህ የአላህ እዝነት ያካብህ ዘንድ ምኞቴ ነው፡፡ መቼም 😱😢 .......
ይቀጥላል .....
www.tg-me.com//mahbubil

Telegram
የዓለሙ ሹም ሙሀመድﷺ 👏👏👏tube
#የጥንት መንዙማዎች
#ታሪኮች [ ቂሳ ]
#ሙሀደራዎች
#የኡለማዎች አስደናቂ ንግግር
.
.channel created july 19
.
የዓለሙ ሹም ሙሀመድ ﷺ ቻናል
ለአስታየት ለ ሼር ስራ @maganhadra
#More Info ......
https://www.youtube.com/channel/UC3NmNDSUYHCMWyUKocMaSYw
https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAEs2TwF_VmEBGeGaDw

❤1👍1
በአልጄሪያ መስጂድ ፊት ለፊት ስርአት አልበኞች ሆን ብለው ሙስሊሞችን
ለመተንኮስ ያደረጉት የሙዚቃ ኮንሰርት ከፍተኛ ቁጣን ቀሰቀሰ። የመስጂዱ
ኢማም በስፒከር ባደረጉት ንግግር ድርጊታቸውን ከማውገዝም አልፈው ኃይለ
ቃል የተናገሩ መሆኑም ተዘግቧል።
እኛ በመልካም ማዘዝ ከመጥፎ ነገር መከልከል በተሳነን ጊዜ ስርዓት አልበኛና
ጋጠወጦች እኛን ከመልካም ነገር ሊከለክሉን ደጃፋችን ድረስ መጡ።
ሐስቡነላህ

አሰላሙ ዐለይኩም ውድ ተመልካቾቼ እሁድ ለት በተጠናቀቀው ውድድር አሸናፊዎች ሁሉም በህጉ መሰረት ትላንት ምሽት ካርዱ ተልኮላቸዋል። በአሏህ ፍቃድ አልሀምዱሊላህ 🥰
በአሏህ ፍቃድ በቀጣይ የውድድር ፕሮግራም አሏህ ያገናኘን 🤲
ሙዕሚን ቃሉን አክባሪ ነው ! ይህ ደሞ ስብእናችን ነው ።
ሀሳባቹን አጋሩኝ @maganhadra
T.me//mahbubil
በአሏህ ፍቃድ በቀጣይ የውድድር ፕሮግራም አሏህ ያገናኘን 🤲
ሙዕሚን ቃሉን አክባሪ ነው ! ይህ ደሞ ስብእናችን ነው ።
ሀሳባቹን አጋሩኝ @maganhadra
T.me//mahbubil
❤4👏1
ዛሬ ማታ በአሏህ ፍቃድ ይለቀቃል
አዲስ ታሪክ ''ሀ'' ብለን መጀመራችን የታወቀ ነው።
ርዕሱ ''መጅኑን ለይላ''
ክፍል 13
ዛሬ ማታ በጊዜ 4:00
ቻናላችንን join & share ያድርጉ
👇👇👇
@mahbubil
አዲስ ታሪክ ''ሀ'' ብለን መጀመራችን የታወቀ ነው።
ርዕሱ ''መጅኑን ለይላ''
ክፍል 13
ዛሬ ማታ በጊዜ 4:00
ቻናላችንን join & share ያድርጉ
👇👇👇
@mahbubil
መጅኑን ለይላ
ከክፍል 12 የቀጠለ .....
መቼም እንደምን አለህ? አልልህም፡፡ ደህና እንደማትሆን አውቃለሁና፡፡ አሁን ላይ ዋጋ ባይኖረውም ያኔ እጅህን ዘርግተህ ስትማፀነኝ የእምቢታዬ ፍቺ ገብቶት ይሆን? ስል እስካሁን እብሰለሰላለሁ፡፡ ልጅነቴን ፣ ወጣትነቴን ፣ እድሜዬን በሙሉ የማውቀው ፍቅርህን ባንድ ጀምበር የምረሳ ከንቱ ከሀዲ መስዬህ ከልብህ ፍቅከኝ ይሆን ስል አነባለሁ፡፡ ግን ያደረኩትን ሁሉ ያደረኩት ስላንተ ፈርቼ እንደነበር አውቀህ ከልብ የሆነ ይቅርታህን ትሰጠኝ ዘንድ እለምንሀለሁ፡፡ ትሞትብኛለህ ፣ አጣሀለሁ ብዬ ፈርቼ ነበር፡፡ በርግጥም አባቴ እንድንተነፍስ አይፈቅድልንም ነበር፡፡ ሀቢቢ ግና ከዛን ጊዜ ጀምሮ መተንፈስ ተቸግሬአለሁ፡፡ ከአለም የከበደ የፀፀት አሎሎ ከደረቴ ላይ እንዳለ ይሰማኛል፡፡ ለካ ሞት የሚባለው ጉድ ፈርጁ ብዙ ነው፡፡ አንተንም ሆነ እራሴን ከስጋ ሞት ስከላከል ወደከፋው ሞት ነበር ለካ የሸሸሁት፡፡ በህይወት እየተነፈሱ መሞት ለካ ይቀፋል፡፡ አሁን ግን ሁሉም ነገር ደክሞኛል፡፡ በህይወቴ የቀሩኝ ውብ ነገሮች ያንተ ትዝታዎች ነበሩ እነሱም በራሴ ጥፋት አድፈዋል፡፡ ግን አስታውስ ለከንቱዋ ለይላ ከነፍሷም በላይ ነበርክ፡፡ ደህና ሁን! ያንተው ለይላ፡፡ ይላል..... ደብዳቤዋ የሞት ኑዛዜም ይመስላል፡፡ መጅኑን አንብቦ እንደጨረሰ ደብዳቤውን በደረቱ ጭምቅ አድርጎ ከመሬት ላይ ኩርትም ብሎ ተንሰቀሰቀ፡፡
ለይላም በምግብ እጦት ለከፋ ህመም ተዳርጋ ከሀልጋ ውላለች፡፡ በዚ ሁኔታ ወራቶች ነጎዱ የምትወደውን ፍቅሯን በህይወት ለማቆየት እሷ ላትነቃ አይኗን ጨፈነች፡፡
ይቀጥላል ......

ባለፈው አመት ረመዳን ሲጠናቀቅብህ የተፀፀትክባቸው በርካታ ጉዳዮች ይኖራሉ። ከነዚሀም ውስጥ...
🛑 ቁርአን ያከተምከው ትንሽ ጊዜ መሆኑ
🛑 የሌሊት ሶላት ላይ የነበረብህ ክፍተት
🛑 የሰጠኸው ሰደቃ አናሳ መሆን
🛑 ሰዎችን አለማስፈጠርህ
🛑 ያልተፈቀዱ ነገራቶችን መመልከትህና ማድመጥህ
🛑 ከቤተሰብና ጓደኛ ጋር የነበረህ ጥሩ ያልሆነ ግንኙነት
🛑 ዚክር ላይ የነበረህ ድክመት
🛑 ሶላትን በጀመዓ ያለመስገድህ ሊሆን ይችላል።
ታዲያ አላህ አድሎህ ለዚህ ረመዳን ካደረሰህ፤ የዘንድሮውን ረመዳን ከአምናው ረመዳን በምን ልትለየው አስበሃል? ወይስ ሃሳብህ ተመሳሳይ ረመዳንን ለማሳለፍ ነው ?
✏️አብዱልአዚዝ (የገነቴው)

👍1
💫💫
ለ አሽረል አዋኺር መረሳት የሌለባቸው 3 ነገሮች
💞💞
-ለመስራት ቀላል
-ቦታ የማይመርጡ
-ጊዜ የማይወስዱ
-ትልቅ አጅር የሚያስገኙ
💞💞
💌በየቀኑ ከኢሻዕ ቡሃላ ቢያንስ 1ብር ሰደቃ ላገኘነው ድሀ መስጠት
💮1ዱ ለሊት ለይለቱል ቀድር ላይ ስለምንሰጥ 84 ዓመት ሙሉ ሰደቃ የሰጠን ያህል ይፃፍልናል
💌ሁለት ረከዐ በየለሊቱ መስገድ
💮ለይለቱል ቀድር ላይ 84 ዓመት ሙሉ ለይል እንደቆምን ይፃፍልናል
💌ሱረቱል ኢኽሏስ 3 ጊዜ መቅራት
💮ሱረቱል ኢኽላስ 3 ጊዜ የቀራ ሰው ቁርአን ሙሉ እንደቀራ ይቆጠራል፡ ለይለቱል ቀድር ላይ ስንቀራ 84 ዓመት ቁርዓን እንዳከተምን ይፃፍልናል
💥ሱብሀነላህ!!
ይሄን ፅሁፍ ቢያንስ ለ30 በመላክ ተጠቃሚ አንዲሆኑ አድርጉ
Share

Watch "ዘይኑ ነቢዬ - አዲስ የመንዙማ ክሊፕ - Al burda Tube አል ቡርዳ ትዩብ | በቅርብ ቀን" on YouTube
https://youtu.be/pS5JLEvtD00
https://youtu.be/pS5JLEvtD00
YouTube
ዘይኑ ነቢዬ - አዲስ የመንዙማ ክሊፕ - Al burda Tube አል ቡርዳ ትዩብ | በቅርብ ቀን
ዘይኑ ነቢዬ - አዲስ የመንዙማ ክሊፕ - አል ቡርዳ ጀማዓ | በቅርብ ቀን
#አል_ቡርዳ_ትዩብ #Alburda_Tube
------------
👇👇👇👇👇👇👇👇👇chanal link
https://youtube.com/channel/UCk2Gt7wPtM-IsSuw3HFQ1hw

👍2
በዛሬው ተመሳሳይ ቀን ማለትም በሂጅራ አቆጣጠር በ9ነኛው አመት በረመዷን 23ተኛው ቀን ላይ ነበር ... ሱሓቢዩ "ሙጊራ ኢብኑ ሹዕባ" ሙሽሪኮች የሚገዙትን "አል-ላት" የተባለን ጣኦት ያፈረሰው።
:¨·.·¨: ❀
`·. አሏህ አሏህ
T.me/mahbubil
:¨·.·¨: ❀
`·. አሏህ አሏህ
T.me/mahbubil
ዛሬ ማታ በአሏህ ፍቃድ ይለቀቃል
አዲስ ታሪክ ''ሀ'' ብለን መጀመራችን የታወቀ ነው።
ርዕሱ ''መጅኑን ለይላ''
ክፍል 13
ዛሬ ማታ በጊዜ 4:00
ቻናላችንን join & share ያድርጉ
👇👇👇
@mahbubil
አዲስ ታሪክ ''ሀ'' ብለን መጀመራችን የታወቀ ነው።
ርዕሱ ''መጅኑን ለይላ''
ክፍል 13
ዛሬ ማታ በጊዜ 4:00
ቻናላችንን join & share ያድርጉ
👇👇👇
@mahbubil
መጅኑን ለይላ
ክፍል 13
ፀሀፊ ✍️ መሊኩ (majnun)
ካይኖቹ የሚሰፈው እምባ ባንገቱ ላይ ቁልቁል ወደ ደረቱ ይወርዳል፡፡ በፊቱ ላይ እንደ ሀረግ የተጋደሙት የደም ስሮቹ ተወጣጥረዋል፡፡ ጨርቁን የጣለላትን ለይላ በሞት ያጣው መጅኑን አቅሉን ስቶ ይጮሀል....ለይላላላላላ ለይላዬ እባክሽን ጥለሺኝ አትሂጂ እባክሽ! ... ስንት ጊዜ ነው ብቻዬን ጥለሺኝ የምትሄጂው? ለምንስ እንደዚህ አምርረሽ መሄድን ወደድሽ??? ለይላ..... እያለ ይንሰቀሰቃል፡፡ ሙሉ የሷ ዘመዶች የመጅኑን ቤተሰቦች ጨምር ከነጅድ በለይላ ሞት ምክነያት ዲመሽቅ ተገኝተዋል፡፡ እናትና አባቷ ሙሽራዋ ልጃቸውን ድንገት ሞት ነጥኳቸው ድንዝዝ ብለው ለበድንነት ቀርበዋል፡፡ መጅኑን ክፉኛ ልቡ ተሰብሮ እስከምትቀበር ድረስ ያለ ሟቋረጥ ሲጮህ ለቀስተኛው ሁሉ ልቡ ፈንድቶ እንዳይሞት ፈርተው ስጋት ገብቷቸው ነበር፡፡
ለይላ ተቀብራ ከሳምንት በኀላ ቤተሰቦቹ ሁሉ ወደ ነጅድ ሲመለሱ መጅኑን ግን ዲመሽቅ ከለይላ መቃብር ቦታ ቀረ፡፡ ቀሪ ህይወቱን ከሷ ዘንድ መቆየትን ወደደ፡፡ ቀኑንም ሌሊቱንም መቃብሯን እየዞረ ያለቅሳል፡፡ ሲሻው ወደ መኖሪያ ቤቷ ሂዶ ሙሾውን ያወርዳል፡፡
፡
አሙሩ አለዲያሪ ዲያሪ ለይላ
ኡቁቢሉ ዘልጂዳራ ወዘልጂዳራ
ወማሁቡ ዲያሪ ሸገፍነ ቀልቢ
ወላኪን ሁቡ መን ሰከነ ዲያራ
፡
እግሮቼ በለይላ መኖሪያ አካባቢ ይጓዛሉ በዛ መንገድ በምጓዝ ጊዜ ቤቷን ሳየው ከቤቷ ውስጥ ባትኖርም ጎራ ብዬ ፈልጋታለሁ፡፡ የቤቷንም ግድግዳ እስመዋለሁ ፣ ምሶሶውን አቅፈዋለሁ፡፡ ነገር ግን ቤቱን የምስመው እንጨት የመሳም ፍቅር ኖሮብኝ ሳይሆን ይህ ቤት አንድ ወቅት ለይላን ይዞ የነበር ቤት ስለሆነ ነው፡፡ እሱ ከንጨትነትም በላይ ለኔ ትርጉም አለውና ነው፡፡ እያለ ያለማቋረጥ ያነባል፡፡
በዚህ ሁኔታ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ብዙ ቀን እና ምሽቶች ተፈራረቁ፡፡ ከሷ ሞት በኀላ እንደሷው ሁሉ ከምግብ እና ከውሀ እርቆ የሞት አፋፍ ላይ ደርሷል፡፡ እሷ የሌለችበት ህይወቱ ለሱ ምንም ነውና የሞቱን ቀን በናፍቆት ይጠባበቃል፡፡ በዛለ ሰውነቱ ወደ መቃብሯ ያዘግማል፡፡ በአንዱ ቀን ካለበት ጫካ ወደሷ ዘንድ ሲሄድ አቅም አጥቶ ካንድ ዲንጋ ስር አረፍ አለ፡፡ በርሀቡ ላይ ህመም ተጫጭኖታል፡፡ እንደዛም ሁኖ ለይላ ጋር ለመድረስ ይፍጨረጨራል ሆኖም ግን ከተቀመጠበት እንኳን መነሳት ተሳነው፡፡ መጅኑን እየሞተ እንደሆነ ተሰምቶታል፡፡ እዛው የተደገፈው ዲንጋይ ላይ እንዳለ ከኮሮጆው ውስጥ መድ እና ቀሰሙን አውጥቶ በወረቀት ላይ ግጥሞቹን እየሞነጫጨረ ሳለ በሰመመን አይኑን ከደነ፡፡
፡
ተወሰደ አህጃረል መሀሚሂ ወልቀፍሪ
ወማተ ጀሪሀል ቀልቢ መንደሚለ ሶድሪ
ፈያልይተ ሀዘል ሁበ ዩእሸቁ መረተን
ፈዩእለም ማ የልቀል ሙሂቡ ሚን ሀጅሪ
፡
ይህ ባካኝ የለይላ አፍቃሪ በዚህ በረሀማ ጫካዎች ዲንጋዮችን ተንተራሰ፡፡ ልቦናው ቆስሏል ፣ ከደረቱም ላይ የስቃይ ደም ይንቆረቆራል፡፡ እንዲህ እያደረገ የሚያሰቃይ ፍቅር ካሁን በኀላ እንዴት ነው ሊወደድ የሚገባው? ያፈቀረ ሰው እኮ ምን ያክል መንገላታት እና መከልከል እንደሚደርስበት መታወቅ አለበት! ያፈቀሩትን ሰዉ የማጣት መሪርነቱ ሊታወቅ ይገባል! እኔ በጣም ተጎድቻለሁ ፣ የማፈቅራትን ለይላ አጥቼ ስሰቃይ በዚህ መልኩ ነው እየሞትኩኝ ያለሁት፡፡ የሚል ግጥሙን ሞነጫጭሮ የሞተችው ፍቅሩን ተከትሏት ይቺን አለም ተሰናበተ፡፡ በህመም እና በስቃይ የተሞላው ፍቅራቸው በሞት ተቋጨ፡፡🥺😔 በመጨረሻም በህይወት ሳሉ የሚመኙትን አብሮነት መጅኑንን ከለይላ አጠገብ በመቅበር በሞታቸው ጊዜ ሞሉላቸው፡፡
ተፈፀመ!
For any comment 👉 @maganhadra
https://www.tg-me.com/mahbubil

😢4👍1