Telegram Web Link
#አርመላ -በጎ -አድራጎት- ጀመአ
የረመዳን -ድምቀት
# ረመዷን 21
#የጎዳና ላይ ኢፍጣር በቀን 100 ሰው የማስፈተር መርሀግብር

አዳማ ፖስታ ቤት አከባቢ

#ረመዳን
#1443/2014

@Armala_charity2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
4
#eman abdulaziz instagram የተወሰደ

@mahbubil
👍1
(ፍትህ ለጎንደር ሙስሊሞች )
ዲነል ኢስላም በማንም ሴራ የሚጠፋ እና የሚደናቀፍ አይደለም ሙስሊሞችም የካሀዲያን ሴራ አይበግራቸዉም ሁሌም ዲነል ኢስላም አሸናፊ እና የበላይ ነዉ አሏህ እንዲህ ይላል :-
وَمَكَرُواْ وَمَكَرَ ٱللَّهُ ۖ وَٱللَّهُ خَيْرُ ٱلْمَٰكِرِينَ ...

ከሀዲያን ሴራን አሴሩ አሏህም የሴራቸዉን ጀዛ ሰጣቸዉ አድማቸዉን መለሰባቸዉ አሏህም ከሴረኞቹ ሁሉ በላጭ ነዉ .
.اللهم انصر الإسلام والمسلمين وأذل الشرك والمشركين ودمر أعداءك أعداء الدين
ጌታየ ሆይ የጎንደር ሙስለሞችን ፣መሳጂዶችንእና ንብረታቸዉን ለአንተ አደራ ሰጠናል ሁሉም የአንተ ነዉና
ለአማፂያን ጀዛቸዉን በአሳማሚ ሁኔታ አስከፍልልን የካሀዲያን በላእ በራሳቸዉ ላይ ይዝነብልን
አሚን አሚን አሚን 🤲🤲🤲

@mahbubil
#ኡስታዝ_ሰኢድ_አህመድ በብዕራቸው ተቃውመዋል!

የወንዶቹ ቁና ያ የዲኑ ማገር
ዑመር የሉም ተብሎ
ኢማም አህመድ ጋዚ አልፈዋል ተብሎ
በጎንደር ሙስሊሞች ስቃይ ቢበረታ
አለላቸው ጀሊል
ፍፁም የማይሞተው የነ ዑመር ጌታ


ታምኖ፣ ችሎ፣ ትቶ፣ ታግሶ ቸልቶ
ገራገሩ ሙስሊም ባለ ልዋል ልደር
መስጂዱ ተቃጥሎ ሰጋጁ ሲገደል
ምን አርጎሽ ነው ብልሽ
መልስ አለሽ ወይ ጎንደር??!!

ይቅር ብሎ አልፎ፣ ሰላምን አንግሶ
ሲነፍጉት ለግሶ፣ ለችግርሽ ደርሶ
የሚኖርን ሙስሊም ሲገደል እያየሽ
በዋዛ አሳለፍሽው ጆሮ ዳባ ብለሽ?!!
እንዴት አይባባስ የኔማ ችግሬ
ሰምታ እንዳልሰማች አይታም እንዳላየች
ሆናብኝ አገሬ።

ሙስሊም የተገፋ የተነካ ለታ
ሚዲያሽ ካለወትሮው
ደንቁሮ ታውሮ
ወሬ ነጋሪሽም አፉ ዱዳ ሆኖ
የመዋሉን ምስጢር አውቃ ዝም አለችኝ
ይህ ነው ወይ ምላሼ አገር እያለችኝ

ያውም በረመዷን
ፆም ውለው ፆም ሟቾች
እጣቸው ያስቀናል እንደ በድር ዘማቾች


አይተሽ እንዳላየሽ ዝም ያልሽው አገሬ
ንገሪው ለዛ ሰው
ከጠጣበት ጉድጓድ አፈር ለመለሰው
የንፁሃንን ደም በግፍ ላፈሰሰው
ያጎረሰውን እጅ ጅሎ ለነከሰው
ንገሪው ለዚያ ሰው
ያን ቀቢፅ ተስፋውን ካፎት ይመልሰው
አለዚያ ሙስሊሙ
ልክ እንደ ቀስት ናቸው ኋሊት ሲሸሽቱ
ሃይ ብለው ተነስተው ከተወነጨፉ
እንኳን የደፈሩት ያሰቡም አይተርፉ
መስጂድ በማቃጠል፣ ሙእሚንን በመግደል
ብትፍረመረሙም ለቀቢፀ_ግዛት
ኢስላም ልማዱ ነው
ሲነቅሉት አፍርቶ ሲቀንሱት መብዛት

ግንስ ያስለቅሳል ከእንባም አልፎ ደም
ያንች አውቆ ዝምታ ለፍትህ መግደርደር
የሰላም ነዋሪን ሰላም ነስቶ ማደር
እንዲያ መጨከኑ በሙስሊሙ መንደር
ምን አርጎ ነው ብልሽ
መልስ አለሽ ወይ ጎንደር
።።።
@mahbubil
እዉነተኛ ታሪክ
 😢 #አስለቃሽ #የቴሌግራም
#ፕሮፋይል

🌀 #Part 1⃣




ሂክማ እባላለሁ ተወልጀ ያደኩት በመዲናችን አዲስ አበባ ገርጂ አካባቢ በሚባለዉ ሰፈር ሲሆን ለቤተሰቦቼ ብቸኛ ሴት ልጃቸው ነኝ፡፡ ቤተሰቦቼ ለኔ ያላቸው ፍቅርና ስስት በቃል የሚገለፅ አይደለም! ፍላጎቴ ሳይዛነፍ አቀማጥለው ነው ያሳደጉኝ፡፡ በጥሩ ስነምግባር በኢስላም ተርብያ ዲኔን እያስተማሩ የአንድ ብቁ እና ንቁ እሆንላቸው ዘንድ ተንከባክበው አሳደጉኝ፡፡ የኔም የዋዛ አልነበርኩም በትምህርቴም ሆነ በቂርአቴ ስለጉብዝናየ ኡስታዞቼ እና መምህራኖቼ ምስክር ናቸው፡፡ ቦሌ መድሀኒያለም preparatory school የ12ኛ ክፍል ተማሪ ነኝ፡፡ ጓደኞቼ ስለኔ መልካምነት አውርተው አይጠግቡም፡፡
     መምህራኖቼ ገና በዛ የአፍላነት እድሜ 1 ብሎ በሚጀምርበት fire age ተብሎ በሚጠራው እድሜ ክልል ውሰጥ ሆኜ የባህሪ ለውጥ ያለማሳየቴ ለመምህሮቸ ትንግርት ሆኖባቸውም ነበር፡፡ ከዛም በኃላ ለኔ ያላቸው ውዴታም ክብርም ከፍ ያለ ነው! እንደ ትልቅ ሰው ጓደኛቸው አርገው ያዩኛል፡፡
       አባቴ የመንግስት ሰራተኛ ሲሆን  ሸዋሮቢት በምትባለዉ ከተማ  ነበር የሚሰራው ብዙ ጊዜ ፊልድ ስለሚበዛበት ከሸዋሮቤትም ወደ ሌላ ሀገር ይሄድ ነበር እቤትም  እማ ብዙ ጊዜዋን ከኔ ጋር ታሳልፍለች፡፡ አሁን ላይ ሰወች ለሚወዱት ማንነቴ ግንባታ ኡሚ ከፍተኛውን ድርሻ ትወስዳለች! ወደ መልካም ነገር የምታመላክተኝ መንገድ መሪየ ኡሚ ናት፡፡  አባቢ ለእማ ልዩ ፍቅርና ክብር አለው መልካምነቷና ብልህነቷን ያደንቃል፡፡ በተለይ ደግሞ የአይኑ ማረፊያ የሆነችውን አንድ ልጅን ዲኗን እንድታውቅ መንገድ መሪ ሆናት ልጅም በሰወች ዘንድ ተወዳጅ እንድትሆንለት ከፍተኛውን ድርሻ ለወሰደቾው እናቴ አድናቆቱ ከልብ ነው፡፡

    እኔም "አላህ ኸይርን ሽቶልኝ ዲኔን አስገንዝቦኛል! አንድ ስህተት እንዳለኝ አቀዋለሁ የሰዉ ልጅ ነኝ እና መሳሳቴ አይቀርም ጓደኞቼ ሁሉም profile pictur የራሳቸዉን ፎቶ ስለሚያረጉ በጓደኞቼ ግፊት እኔም profile የራሴን ማረግ ከጀመርኩ ሰነባበትኩ፡፡ ፎቶ መነሳቱ ሀራም መሆኑን እያወኩ ግን ጓደኞቼ ጋር ሰርግ በሚኖረን ሰአት ትምህርት ስንሄድ የማስታወሻ ፎቶ እየተባለ እየተነሳን profile ለማረግ እንቸኩል ነበር፡፡
       በዛም ላይ የማላቀዉን ለማወቅ በተለያዩ social media ላይ የዳእዋ ጥሪ የሚያረጉ ግሩፓች ላይ ተሳታፊ ሆንኩኝ፡፡ whatsap እና telegram የኔ የዳእዋ ጥሪ መገልገያ ከሆኑ ሰነበቱ፡፡ ብዙ group ላይ እኔን add ያረጉኛልበትምህርት ቤት የሚከፈቱ የሰፈር ልጆች የሚከፍቱት group ላይ ብዙ group ገብቻለሁ አገለግላለሁ፡፡ በቦሌ priparatory scholl አንዱ ልጅ group ከፍቶ በጣም ብዙ ተከታታይ ያለዉ ኢስላሚክ group ሁኖ ነበር ከዛም ዉጭ ሌላ group ነበሩኝ፡፡ ፎቶየን እቀያይር ነበር የትዳረ ጥያቄ በቤተሰቦቼ እየመጣ ትምህርቴን ልጨርስ እያልኩኝ አሳልፊያለሁ፡፡
      እናቴም ግን የዩኒቨርስቲ ዉጤት ቢመጣልሽ አትማርም ወደ ትዳር ነዉ የምገቢዉ ልጅ ወልደሽ ማየት እፈልጋለሁ እንጂ ዩኒቨርስቲ ገብተሽ ጊዜ እንድፈጂ አልፈልግም ብቻ ትምህርት እንደጨረሽ ከተቻለ አንቺ ያመጣሽዉን ባል እቀበላለሁ ግን ኢማን የሌለዉ ከሆነ እኔ የጠየቁኝ ያዘጋጀሁልሽ ትምህርቷን ትጨርስ ብየ የመለስኳቸዉ ስላለ እኔ የወደድኩትን እንደምወጂ እርግጠኛ ነኝ አለችኝ፡፡
...እናት ወልይ ናት አይደል የሚባለዉ እኔም እሺ ማሚ ነበር መልሴ፡፡እኔም ተፈትኜ ዉጤት ቢመጣም ዩኒቨርስቲ ላልገባ ወስኛለሁ፡፡
ብዙ  የሚያወሩኝ የማላቃቸዉ ልጆች ቁጥሬን ከየት አገኛችሁ ብየ ስጠይቅ ከGroup አድራሻሽ ነዉ ቁጠርሽ የለንም ይሉኝ ነበር ከዛ በblock አሰናብት ነበር፡፡
     
    ከእለታት አንድ ቀን ግን ከወትሮው ለየት ያለ ነገር አጋጠመኝ፡፡ ከማላውቀው ሰው በእኔ በtelegram ቁጥር የድምፅ መልእክት ተልኮልኝ አየሁ፡፡ መልእክቱን ስሰማ ቀጥታ ወደ ፕሮፍይሉ በመሄድ ስለሱ ማንነት ለማወቅ እንዲረዳኝ ማየት ጀመርኩኝ በጠቅላላ ኢስላማዊ ፎቶወች እና ዱአ ይበዛበታል፡፡፡ እኔም ለማጣራት ያህል ነበር ፕሮፍይሉን የፈተሽኩት፡  የድምፅ መልእክቱ ከአምስት ደቂቃ የበለጠ ሲሆን profile ባረኩት ፎቶ አላህን እንድፈራ ፎቶ ሀራም መሆኑን የካተተ record ነበር አነጋገሩ በጣም አስተማሪ ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ እሱ ነበር ተይ ያለኝ የማላቀዉ ቁጥሮች profile እያዩ ቆንጂት ሀይ የማይለኝ የለም telegram ስገባ የማላቀዉ ቁጥር ይበዛብኝ ነበር እኔ ግን አጂ ነብይ ጋር አላወራም ብየ ማንንም አላወራም ግን ምን ዋጋ አለዉ profile ከgroup እያዩት መሆኑን የተረዳሁት ዘንግቼ ነበር፡፡

     በፁሁፍም ከሀዲስ ከቁርአን ማስረጃ እያቀረበ ብዙ ትምህርቶችን ላከልኝ እኔም ጀዛ ከሏህ ብየ ፎቶየን profile ያረኩትን እንዳለ አጠፋሁ፡፡
ከዛም ግን ጎበዝ ዲነኛ እንደሆንሽ አቃለሁ profile ፎቶዉ የአንቺ መሆኑን ሳይ በጣም ነዉ የገረመኝ ሂክማ መቼ ጀምራ እንደዚህ ሁነች ብየ ግራ ገብቶኝ ነዉ አለኝ
....እኔም በመደንገጥ እንዴ ከአሁን በፊት ታቀኛለህ እንዴ ????? አልኩት
እሱም........

#part 2⃣

,,,,,,,,ይ
,,,,,,,,,,,,,,,,,ቀ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,ጥ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,ላ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,ል

https://www.tg-me.com/mahbubil
👍8
አሰላሙ ዐይኩም
ውድ የተከበራቹህ እናት አባቴ እህት ወንድሜ የሆናቹህ ሙስሊሞች እንኳን ለዒድ አልፈጥር በአል በሰላም በራህመቱ በደስታ እና በፍቅር አደረሳቹህ አደረሰን።

@mahbubil
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
📼 360p, 💾 116.6MB,

ተክቢራ በትላልቆቹ አሊሞች
በቪድዮ ተምትፈልጉ እንኳቹህ ብያለሁ

@mahbubil
Eid tekbira ethiopia // ...
ABRET PRO MENZUMA
ተክቢራ በትላልቆቹ አሊሞች
በአውዲዮ ተምትፈልጉ እንኳቹህ ብያለሁ

@mahbubil
👍1
ዒድ ሙባረክ! 🥳

تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال
كل عام وأنتم بخير
@amuwa_records
2025/07/08 19:32:01
Back to Top
HTML Embed Code: