Telegram Web Link
31 ደቀ መዛሙርት መመረቃቸው ተገለጸ

ሐምሌ ፳፰/፳፻፲፯ ዓ.ም

የጀሞ ደብረ ሰላም  መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፈለገ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ከሰበካ ጉባኤውና ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በመተባበር ከወላይታና ዳውሮ ሀገረ ስብከት ለተወጣጡ 31 ደቀ መዛሙርት  ለአንድ ወር በማሠልጠን በትናንትናው ዕለት ሐምሌ 27  ቀን 2017 ዓ.ም  ጀሞ ደብረ ሰላም  መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ማስመረቁን ተገልጿል።

በምረቃት መርሐ ግብሩ የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ አርያም ዓለማየው ዘውዴ፣ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የስብከተ ወንጌል ኃላፊ በትረ ትጉሃን ደምመላሽ ቶጋ፣ የደብሩ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ስዩማን ኃይለ ሚካኤል ወሰኔ፣ የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቀ መንበር ወ/ሮ ፀሐይ አሻግሬ፣ የማኅበረ ቅዱሳን ተወካዮች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና ምእመናን ተገኝተዋል።

ተተኪ መምህራኑ  በነበራቸው የአንድ ወር ቆይታ ትምህርተ ሃይማኖት፣ ነገረ ድኅነት፣ ክርስቲያናው ሥነ ምግባር፣ የቤተ ክርስቲያን ምሥጢራትና ሥርዓት፣ ነገረ ቅዱሳን፣ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና ሌሎችም ሥልጠናዎችን መውሰዳቸው ተጠቅሷል።

አቶ ኃይለ መስቀል ጋሻው የፈለገ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ሊቀ መንበር  ተመራቂ ተማሪዎችን እንኳን ደስ አላቹ በማለት መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ለሥልጠናው የበኩላቸውን ድርሻ ለተወጡ አጋርና ባለድርሻ አካላት ምስጋናን ችረዋል።

የጀሞ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ  መልአከ አርያም ዓለማየሁ ዘውዴ እንደተናገሩት ከገጠራናው ና ከጠረፋማው አካባቢ ተተኪ ሰባኪያነ ወንጌልን አምጥቶ ማሠልጠን መልካም ምግባር መሆኑን ገልጸው ሠልጣኞች አካባቢያቸውን በቋንቋ እንዲያገለግሉ አደራ ብለዋል።
3
ሠልጣኞች  በበኩላቸው  በቆይታቸው ለተደረገላቸው ነገር በሙሉ ምስጋናን ያቀረቡ ሲሆን በኃላፊነት የድርሻቸውን ለመወጣት ቃል ገብተዋል።

የማኅበረ ቅዱሳን ተወካይ የሆኑት መምህር አምባቸው ጸጋዬ እንደገለጹት ማኅበረ ቅዱሳን ስብከተ ወንጌልን ከገጠራማው አካባቢ ተደራሽ ለማድረግ ከአጋርና ባለድርሻ አካላት ጋር እየሠራ መሆኑን ገልጸው ለተመራቂ ሰባኪያነ ወንጌል የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

  አክለውም   የሥልጠና ውጤት የሚለካው በቆይታው ብቻ ሳይሆን በምትሰማሩበት የሐዋርያዊና የእረኝነት አገልግሎት የመድከምና የመሰልቸት ስሜት ሳይሰማችሁ ስታገለግሉና ነፍሳትን ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስትመልሱ ነው በማለት መልእክት አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም የሥልጠናው ተሳታፊዎች በአንዲት ቤተ ክርስቲያን በፍጹም አምናችሁ፣ የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር አክብራችሁ አገልግሎታችሁን እንድትፈጽሙ በማለት ያሳሰቡ ሲሆን በሥልጠናው  የተሳተፉ አካላትን በሙሉ አመስግነዋል።👇👇👇👇👇👇👇
የማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች ይቀላቀሉ
ቴሌግራም፡- http://www.tg-me.com/mkpublicrelation
የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት፡- http://www.facebook.com/eotcmkidusan/
ድረገጽ፡- http://www.eotcmk.org
ዩ ቲዩብ፡- http://www.youtube.com/user/EOTCMK
:- https://www.youtube.com/@-zemawetibebzmk7905
በማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማእከል ሲያካሂድ የሰነበተውን 27ኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጠናቋል፡፡

"ዘመኑን የዋጀ አገልግሎታችሁን ቀጥሉ በቻልንው ሁሉ እንተባበራለን " ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የዋሽንግተን ኦሪገን አይዳሆ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

የዋሽንግተን ኦሪገን አይዳሆ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ በጉባኤው 2ተኛ ቀን ላይ ባደረጉት ንግግር ማኅበሩ በውጭ ሀገር ላለችው ቤተክርስቲያን ተረካቢ ትውልድ በማፍራት ረገድ እየሰራ ያለው ሥራ የሚደነቅ እና ዘመኑን የዋጀ በመሆኑ በመግለፅ የበለጠ እንድትገፉበት አሳስባለሁ ሲሉ  አባታዊ መመሪያ ሰጥተዋል ::

የማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ተወካይ ሁነው በጉባኤው ሲሳተፉ የሰነበቱት መጋቢ ሀብታት ታደሠ አሰፋ በበኩላቸው ማኅበሩ በተገባደደው በጀት ዓመት ያከናወናቸውን ዋና ዋና ጉዳዮች ለጉባኤተኛው አቅርበዋል :: በተለይም የአሜሪካ ማእከል ድጋፍ ጉልህ ድርሻ የነበረባቸው የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎት : ገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶች ድጋፍ እና በተለያያ ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን መርዳት የሚሉት የሪፖርቱ ዋና ዋና ትኩረቶች ነበሩ ::

የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ አቶ ካሳሁን ኅይለማርያም እና ዋና ሥራ አስፈፃሚው መምህር ዋሲሁን በላይም በጉባኤው ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ማእከሉ ማኅበረ ቅዱሳን ለሚያስገነባው የልኅቀት ማእከል እያደረገ ያለውን ድጋፍ እንስተው ምስጋና አቅርበዋል :: በቀጣይም ግንባታው እስኪጠናቀቀ አባላቱ የተቻለውን ሁሉ እንዲያደርጉም የሥራ ኅላፊዎቹ ጠይቀዋል ::

ለ3 ተከታታይ ቀናት በተካሄደው የማእከሉ ጠቅላላ ጉባኤ የ2017 ዓ.ም የዋና ክፍላት፣የፋይናንስና የኦዲት ሪፖርት እና እቅዶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል ::

የቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ፈተናዎች : የአባላት የአገልግሎት ሁኔታና ሌሎችም ጥናታዊ ጽሑፎችም በጉባኤው ተዳሰዋል ::

የ27ኛው የማእከሉ የዙም ጠቅላላ ጉባኤ አስተናጋጅ የነበረው የፖርት ላንድ ግንኙነት ጣቢያም ጉባኤውን ከመክፈቻው እስከመዝጊያው ባማረ እና ሰላማዊ በሆነ መልኩ ያስተባበረው ሲሆን በአካባቢው ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ላበረከቱለት ድጋፍ ምስጋና አቅርቧል ::

የአሜሪካ ማእከል ቀጣይ ዓመት 28ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በአትላንታ ንዑስ ማእከል አዘጋጅነት በአካል እንደሚካሄድ ቀጠሮ ተይዞለታል::

መረጃው:- የአሜሪካ ማእከል ሚዲያ ክፍል ነው
3
ማኅበረ ቅዱሳን በዳሰነች ወረዳ በውኃ ሙላት ለተፈናቀሉ ወገኖች የምግብ ግብዓት ድጋፍ አደረገ

ሐምሌ ፳፰/፳፻፲፯ ዓ.ም

የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት በሀገራችን እያጋጠሙ ያሉ ሰፊ ማኅበራዊ ቀውሶች በማኅበረሰብ ክፍሎች፣ በገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ላይ እያስከተሉት ያለውን ችግር ለማቅለል ባለፉት ተከታታይ ዓመታት ሁለገብ ማኅበራዊ ድጋፍ አድርጓል።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህም በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች  ወረዳ  በተደጋጋሚ  እየተከሰተ ባለው የኦሞ ወንዝና ቱርካና ሐይቅ መሙላት ሳቢያ በ6 ቀበሌዎች የሚገኙ ከ26 ሺ በላይ ወገኖች ለከፍተኛ ማኅበራዊ ቀውስ መዳረጋቸውን የተገኙ መረጃዎች ያሳያል።

ስለሆነም ማኅበሩ እነዚህ ወገኖች በተጠለሉባቸው ጊዜያዊ ጣቢያዎች በመገኘት ከ960 ለሚደርሱ ተፈናቃይ አባወራዎችና እማወራዎች ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የሆነበት የምግብ ግብዓቶች ድጋፍ አድርጓል። በዚህ የድጋፍ ርክክብ ወቅትም የማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል ልዑካን፣ የማኅበረ ቅዱሳን ጅንካ ማእከል ተወካዮች፣ የአካባቢው የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችና የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በመገኘት ድጋፉን ለተጎጅዎች አስረክበዋል። 

ድጋፎቹ የተደረጉት የዘወትር አጋራችን ከሆነው በሀገረ አሜሪካ ከሚገኘው ከሜሪላንድ ኆኅተ ምሥራቅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ምእመናን በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ሲሁን በተመሳሳይ ሜሪላንድ ኆኅተ ምሥራቅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በመፈናቀልና በድርቅ ለተጎዱ በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ ወገኖች ተደጋጋሚ ድጋፍ እንድናደርግ ከፍተኛ ድርሻ የተወጣ በመሆኑ ማኅበረ ቅዱሳን ከፍ ያለ ምሥጋናውን ያቀርባል። 
3🙏2
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ባለፉት 10 ወራት ብቻ በማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች 12 በላይ ተመሳሳይ ማኅበራዊ ድጋፍ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን መሰል የነፍስ አድን ድጋፎችን ለማድረስ በሚደረገው የሰብአዊነት ሥራ ምእመናን የተለመደ ድጋፍ እንድታደርጉልን ሲል ማኅበሩ ጥሪውን ያቀርባል።
ድጋፍ ለማድረግ፡-
#በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400 
6. በወገን ፈንድ ፡- https://Www.wegenfund.com/mknu መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
16
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
✝️ከአንድ ቤተሰብ፣ ለአንድ ተማሪ✝️
++++
ማኅበረ ቅዱሳን በየዓመቱ እንደሚያደርገው በማኅበራዊ ቀውስ ጉዳት የተነሣ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ በገንዘብና በዓይነት እያሰባሰሰበ ይገኛል።
ድጋፍ ለማድረግም፡-
  #በገንዘብ
በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000309803648
2. በአቢሲኒያ ባንክ 37235458
3. በወጋገን ባንክ 0837331610101                                                 
4. በአዋሽ ባንክ 01329817420400
  #በዓይነት
ደብተር፣እስክርቢቶ፣ እርሳስና ቦርሳ                                                                                                                               ለበለጠ መረጃ
•  09 84 18 15 44
•  ማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ 1ኛ ወለል
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት
6
የነሐሴ ወር ሐመር #መጽሔት #በውስጧ ምን ይዛለች ?

የነሐሴ ወር ፳፻፲፯ ዓ.ም መልእክት ዘማኅበረ ቅዱሳን "#ሁሉም ወገን ለቤተክርስቲያን ተገቢውን ክብር ይስጥ ! . ›› በሚል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለሀገር ሉዓላዊነት እንዲሁም ልማትና ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበራት ሲባል ለኦርቶዶክሳውያን ብቻ የሚጠቅም ማለት አይደለም፤ መላውን የሀገር ዜጋ በአንድም በሌላም መንገድ የሚጠቅም እንጂ በማለት  በመልእክቱ ዐምድ ይዛለች።
       .#ዐውደ ስብከት ሥር” ጾምና ፈተናዎቹ" የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን በልዩ መንፈሳዊ ዝግጅትና ሙቀተ መንፈስ ቅዱስ ባልተለየው መንፈሳዊነት እንዲፈጽሟቸው ከተሠሩት የመንፈሳዊ ተጋድሎ መንገዶች መካከል አንዱ ጾም እንደሆነ በስፋት በመጋቤ ምሥጢር ቀሲስ ስንታየሁ አባተ  የቅዱሳት መጻሕፍትና የሊቃውንቱን አስተምህሮ  መሠረት በማደረግ ትምህርት ይዛለች፡፡
  አጠቃላይ ጾም ፈቃደ ሥጋን ለፈቃደ ነፍስ የምናስገዛበት፣ ጠላት ዲያብሎስን ድል የምናደርግበት፣ ከእግዚአብሔር በረከትን የምንቀበልበት መንፈሳዊ ተጋድሎ ጾም እንደሆነ ሐመር መጽሔት ታስነብባለች፡፡

#በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር” ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ሀገረ እግዚአብሔር "በሚል ርእስ ይህንን ቅዱስ ቃል ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የራቀውን አቅርቦለት የቀረበውንም አጉልቶለት በትንቢት መነጸር ከሩቅ ሆኖ አይቶ የተናገረው ልዑል እግዚአብሔር እንደ ልቤ ያለው ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት  የተናገረውን  ግሩም ጹሑፍ በትምህርተ ሃይማኖት ይዛለች።
3
#ዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ሥር ደግሞ “#የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተዋፅኦ ለሀገር ግንባታ  " በሚል ርእስ   የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ታሪክ ሥልጣኔና ዕድገት፣ የሞራልና የሥነ ምግባር ግንባታ ውስጥ ታላቅ ድርሻ ያላት መንፈሳዊት መንግሥት ፣ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በረጅም ጊዜ ታሪኳ ውስጥ ከመንፈሳዊ አገልግሎቷ ባሻገር ሞልቶ በተረፈ አስተዋፅኦዋ በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ ዘርፈ ብዙ ሚና ተጫውታለች የሚል ዐቢይ ትምህርት  ይዟል።
"#ክርስትና በማኀበራዊ ኑሮ፦ ኦርቶዶክሳዊነትን በማኅበረሰቡ ውስጥ በማጽናት ቦታችን የት ነው? ክ ፍል አራት  ? በማለት በመጨረሻው በክፍል አራት ደግሞ ለነፍስ ተስፋዋ የሆነችውን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን በእሳቤ፣ በእይታ፣ እና በተግባር በማኅበረሰባችን ውስጥ ከመትከል፣ ከማለምለም፣ ከማስፋትና ከማጽናት አንጻር ቦታችንን  ያሳያል ።

#በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “#፲፪ ዓመታትን በባሕር ውስጥ የጸለየች እናት  "በሚል ርእስ የተጋድሎ ሕይወቷ  ፣ትውልድና ልደት ፣ የምናኔ ሕይወት፣ የአማላጅነት ጸጋ፣የተሰጣት ቃል ኪዳን፣ ዕረፍቷ ላይ  ሰፊ ትምህርት ይሰጣል ።
#በነገዋ ቤተ ክርስቲያን ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነት "በሚል የወጣትነትና መገለጫዎቹ፣ የወጣትነት ፈተናና መፍትሔው ፣ አጠቃላይ ወጣትነት እግዚአብሔርን የምናስብበት ዕድሜ፣ ለሽምግልና ዘመን ለጭንቅ ወራት ድጋፍ የሚሆነንን የጽድቅ ዛፍ አስቀድመን የምንተክልበት ዘመን መሆኑን   ሐመር  መጽሔት  ታስነብባለች።
#በኪነ ጥበብ ዐምድ #ሲሳይ -ክፍል ሁለት "ውድ አንባቢያን ከወርኃ ሐምሌ ዕትም ‹‹ሲሳይ›› በሚል ክፍል አንድ አስነብበናል ክፍል ሁለት ታስነብባለች ።
#የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ "#ዘመነ ክረምት " ውድ አንባብያን ዘመነ ክረምትን መሠረት አድርገው የሚነሡ ጥያቄዎችን በሐምሌ ወር ክፍል አንድን ማስነበባችን ይታወቃል። ክፍል ሁለትንና የመጨረሻውን    ላይ የሚነሡ ጥያቄዎችን መሠረት አድርገን፣ክረምት የምን ምሳሌ ነው?፣ ዘመነ ክረምትን ከሥነ ፍጥረትና ከነገረ ድኅነት ጋር በማያያዝ   ምላሽ  ይዛለች  ።
ሐመር መጽሔት #፴፪ ኛ ዓመት ቁጥር ፰ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !
Magazine @eotcmk.org #ሐመር #መጽሔት ዝግጅት ክፍል
1👍1🙏1
2025/09/21 06:20:51
Back to Top
HTML Embed Code: