Telegram Web Link
አሰላ ማእከል  ፳፰ኛ ጠቅላላ ጉባኤዉን እያካሄደ እንደሚገኝ አስታወቀ

ሐምሌ ፳፮/፳፻፲፯ ዓ.ም

ማኅበረ ቅዱሳን አሰላ ማእከል  ፳፰ኛ ጠቅላላ ጉባኤዉን እያካሄደ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡


መርሐ ግብሩ የአርሲ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ታምራት ወልዴ ፣ የሀገረ ስብከቱ የክፍል ኃላፊዎች፣ የወረዳ ቤተ ክህነት ሊቃነ ካኅናት ፣ የአሰላ ከተማ አድባራት አስተዳዳሪዎች በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል፡፡


በዋናዉ ማእከል ልዑክ በአቶ አበበ በዳዳ የማኅበረ ቅዱሳን ግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ ኃላፊ የማኅበረ ቅዱሳን መልእክት የቀረበ ሲሆን በአቶ ዉቤ ተሰማ የማእከሉ የጽ/ቤት ኃላፊ የ2017 ዓ.ም የማእከሉን የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

ጉባኤዉ ከትላንት ሐምሌ 25   የጀመረ ሲሆን እስከ እሑድ ሐምሌ 27  እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡
3
27ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አሜሪካ ማእከል አስታወቀ

አሜሪካ ማእከል 27ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በፖርትላንድ ግ/ጣቢያ አስተባባሪነት ከትናንት ምሽት ሐምሌ 25 ቀን መክፈቻውን በፖርትላንድ ደብረ መንክራት ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን በጸሎተ ወንጌል ያደረገው የማእከሉ ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው እለት ሐምሌ 26 ቀን 2017 ዓ.ም. በፖርትላንድ ምስካዬ ኃዙናን መድኃኒ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በኪዳን ጸሎት የተጀመረ ሲሆን በጉባኤው መክፈቻ የእንኳን ደኅና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት የማእከሉ ሰብሳቢ ዶ/ር አይዳ ግርማ  ማእከሉ በዓመቱ ውስጥ በሀገር ቤት እና በአሜሪካ ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

የጉባኤው መረ ቃል በሆነው “ከበጎ ሥራ ወገን ምን ላድርግ?” የሚለውን ቃለ እግዚአብሔር መነሻ በማድረግ ትምህርተ ወንጌል በአባ ፍቅረ ማርያም መኩሪያ ከኢትዮጵያ ተሠጥቷል፡፡በማስቀጠልም የማእከሉ የ2017 ዓ/ም አፈጻጸም ዘገባ፤ የሒሳብና የኦዲት ረፖርት እንዲሁም ዋና ማእከሉም በዓመቱ ውስጥ ያከናወናቸውን አጠቃላይ ሪፖርት በአቶ ታደሰ አሰፋ ቀርቧል፡፡ የቀረቡትንም ረፖርቶች ተከትሎ በጉባኤው የታደሙት የዋሽንግተን ኦሪገን አይዳሆና አካባቢው  ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ባስተላለፉት መልእክት ቤተክርስቲያንን የሚያሻግር ተተኪ ትውልድ ለማፍራት ማኅበረ ቅዱሳን የሚያደርገው ጥረት እጅግ የሚደነቅ መሆኑን ገልጸው አባላቱ በብዙ ፈተናዎች ውስጥ እያለፋችሁ ለምታከናውኑት አገልግሎት ድጋፋችንን አጠንክረን እንቀጥላለን ብለዋል:: ብፁዕነታቸው ሥራህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ ሀሳብህም ይጸናልሃል የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ በማንሳት ማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎቱን ለእግዚአብሔር አደራ ሰጥቶ እንዲሰራም የማትሰሩ መስላችሁ ሥራችሁን ስሩ በማለት አባታዊ መመሪያ ሰጥተዋል ::

ጉባኤው በተቋማዊ ለውጥ አተገባብርና አባላት ተሳትፎ፤ ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮችና የ2018 ዓ/ም እቅዱና ሌሎች አጀንዳዎች መክሮ ውሳኔ የሚያሳልፍ ይሆናል፡፡ ጠቅላላ ጉባኤው ከአባላት በተጨማሪ ለሕጻናትና አዳጊዎች የተለያዩ አስተማሪ ዝግጅቶች  በተጓደኝ እየተከናዎኑ ናቸው፡፡በማእከሉ ተግባራዊ የተደረገውን መዋቅራዊ ለውጥ ተከትሎ 3ቱ ማስተባበሪያዎች በአካል የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን ባለፉት ሳምንታት ሲያካሂዱ ሰንብተዋል ::  የማእከሉ ጠቅላላ ጉባኤ ማስተባባሪያዎቹ በአካል ጠቅላላ ጉባኤ በሚያደርጉበት ዓመት የማእከሉ ጠቅላላ ጉባኤ በዙም እንዲካሄድ በተወሰነው ውሳኔ መሰረት ነው ዘንድሮ በዙም እየተካሄደ ይገኛል:: ዘገባው የአሜሪካ ማእከል ሚዲያ ክፍል ነው::
2
የማኅበረ ቅዱሳን ደሴ ማእከል 30ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ማከናወኑን ገለጸ

ሐምሌ ፳፰/፳፻፲፯ ዓ.ም

ማኀበረ ቅዱሳን ደሴ ማእከል 31ኛ ዓመት 30ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ባለፉት ሁለት ቀናት ሐምሌ 26 ቀን እስከ ሐምሌ 27 ቀን 2017 ዓ.ም የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቆሞስ አባ ለይኩን ወንድይፍራው፤ የሀገረ ስብከቱ መምሪያ ኃላፊዎች ፣ ተጋባዥ እንግዶች፣ የተለያዩ አጋር አካላት ፣ የማእከላትና የወረዳ ማእከላት ተወካዮች በተገኙበት መከናወኑ ተገልጿል።

በጉባኤው የማእከሉ የ2017 ዕቅድ ክንውን የቀረበ ሲሆን 248 አዳዲስ  አማኒያን መጠመቃቸውን ፣በወቅታዊ ጉዳዮች ለተፈናቀሉ ምእመናንና ማኅበራዊ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ከ675 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ መድረጉ በሪፖርቱ ተመላክቷል::

የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት  የኢንቨስትመንትና ሀብት ልማት ቦርድ ወጪን ሳይጨምር ለአገልግሎት ማስፈጸሚያ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ መድረጉን  በሪፖርቱ የቀረበ ሲሆን በተጨማሪም የዋናው ማእከል  ሪፖርት በማኅበረ ቅዱሳን ዋና ሥራ አስፈጻሚ  መ/ር ዋሲሁን በላይ በጽሑፍ ቀርቧል::

በጉባኤው ላይ የ2017 ዓ.ም ዕቅድ የቀረበ ሲሆን አስተያየት ተሰጥቶባቸው መጽደቃቸው ተጠቁሟል::
 
በመጨረሻም የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ  ቆሞስ አባ ለይኩን ወንድይፍራው በ2018 ዓ.ም የበለጠ ተናበን አብረን መሥራት ይጠበቅብናል ሲሉ አሳስበዋል::
1
2025/09/21 04:21:38
Back to Top
HTML Embed Code: