Telegram Web Link
"መጽሐፈ ግንዘት" እና ˝የዮሐንስ ወንጌል በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅጽ ሁለት‌  መጻሕፍት የምረቃ መርሐ ግብር ተከናወነ።

ጥቅምት ፱ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም

ማኅበረ ቅዱሳን ለመጀመሪያ ጊዜ  ያስተረጎመውን "መጽሐፈ ግንዘት" እና  ˝የዮሐንስ ወንጌል በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ  ቅጽ ሁለት‌  መጻሕፍትን በትናትናው ዕለት ጥቅምት 8 ቀን 2018 ዓ.ም  በዋናው ማእከል ሕንጻ 3ተኛ ወለል ንቡረ እድ  ድሜጥሮስ አዳራሽ አስመርቋል።


በመርሐ ግብሩ ላይ ሊቀ ሊቃውንት ዮሴፍ ደሳለኝ የሊቃውንት ጉባኤ አባልና  የአራቱ መጻሕፍት ጉባኤያት የትርጓሜ መምህር "መጽሐፈ ግንዘት" የተሰኘውን እንዲሁ። መምህር ቀሲስ ዐቢይ ሙሉቀን የሐመር መጽሔት ምክትል ዋና አዘጋጅ ˝የዮሐንስ ወንጌል በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ  ቅጽ ሁለት‌"  በተመለከተ የመጽሐፍ ዳስሳ አድርገዋል።

የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ሥራ አስፈጻሚ መምህር ዋሲሁን በላይ በበኩላቸው ማኅበረ ቅዱሳን ከሚሠራቸው ሥራዎች መካከል መጽሐፍትን በማዘጋጀት ለምእመናን ተደራሽ ማድረግ ሲሆን በዚህም በርካታ መጽሐፍት ተጽፈው፣ ተተርጉመው፣ ታትመው ለአገልግሎት መዋላቸውን ገልጸዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለውም መጻሕፍቱ እዚህ እንዲደርሱ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋናን አቅርበዋል።

በመጨረሻም መጽሐፍቱ በአባቶች የተመረቁ ሲሆን  መጻሕፍቱን በመተርጎም ኃላፊነታቸውን ለተወጡ አካላትም የምስክር ወረቀትና የስጦታ መርሐ ግብር ተከናውኗል።
12👍8
የ2018 ዓ.ም የጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በጸሎት ተጀመረ።

የጸሎት መርሐ ግብሩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፣ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተካሂዷል።
1🙏1
“ከአባቶቻችን ለልጆቻችን” በሚል መሪ ቃል ጥቅምት 16 ቀን 2018 ዓ.ም የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር እንደሚካሄድ ዛሬ ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓም በቦናንዛ አዲስ ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተገለጸ።

በመግለጫው የደብረ ታቦር ደብረ ልዑላን መድኃኔ ዓለም የ፬ቱ ጉባኤያት መጻሕፍት ምስክር ጉባኤ ቤት የ72 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።

"በኦርቶዶክሳዊ ትውፊትና ትምህርት ዓለም አቀፍ በጎ ተጽዕኖበመፍጠር ትውልድ አሻጋሪ የልሕቀት ጉባኤ ቤት መሆን" የሚል ታላቅ ርዕይ ያለው ጉባኤ ቤቱ ይህ ርዕይ እውን እንዲሆን ዓለም አቀፍ መንፈሳዊ ትምህርት ማዕከል ግንባታ ለማጠናቀቅ አቅዷል።

የደብረ ታቦር ደብረ ልዑላን መድኃኔ ዓለም የ፬ቱ ጉባኤያት መጻሕፍት ምስክር ጉባኤ ቤት መምህር መምህረ መምህራን በጻሕ ዓለሙ ጥቅምት 16 ቀን 2018 ዓ.ም በግዮን ሆቴል ገቢ መሰብሰብ እንዳቀዱ ገልጸዋል።

በ1851 ዓ.ም በአጼ ቴዎድሮስ አማካኝነት በቅኔ እና መጻሕፍት ጉባኤው እንደተጀመረ ገልጸው በ2011 ዓ.ም አምስተኛ የወንበር መመህር ሁነው መመደባቸውን ተናግረዋል።
2025/10/27 18:00:53
Back to Top
HTML Embed Code: