-------- ላንተ ያለው የትም አይሄድም -------
አርጀንቲናዊ ነው Jorge Mario Bergoglio ይባላል ይህ ወጣት የኬሚስትሪ መምህር ሆኖ ጥቂት ጊዜ ከቆየ በኋላ፣ ይህንን ስራ በመተው በቦነስ አይረስ የምሽት ናይት ክለቦች የበር ላይ ጥበቃ ሆኖ ሰርቷል።
ስራው በቀጥታ ናይት ክለቡን መጠበቅ ሳይሆን፣ ወደ ክለቡ የሚገቡትን ሰወች መፈተሽ፣ እድሜያቸው አጠራጣሪ የሆኑ ወጣቶችን መታወቂያ እያዩ ማስገባት፣አንዳንዴም በናይት ክለቡ ውስጥ ግጭት ሲኖር ጣልቃ በመግባት ማስማማት የመሳሰሉ ስራዎችን ነበር የሚሰራው።
Jorge Mario በሃያ አመት እድሜው ባጋጠመው አደገኛ ህመም ምክንያት አንድ ሳንባው ተቆርጦ እንዲወጣ ሲደረግ ብዙዎች ረጅም እድሜ እንደማይኖር ገምተው ነበር። ሆኖም ያጋጠመው የጤና እክል ተጨማሪ 68 አመታትን ፡ በህይወት እንዳይኖር አላገደውም።
ይህ ከላይ ያነሳነው ታሪክ በ88 አመት እድሜያቸው ከትላንት ወዲያ በሞት የተለዩት የካቶሊኩ ጳጳስ የፖፕ ፍራንሲስ የወጣትነት ታሪክ ነው ።
ከናይት ክለብ ባውንሰርነት ፡ የካቶሊክ ጳጳስ እስከመሆን የደረሰ ስብዕና።
በአንድ ወቅት በምንም ሁኔታ ውስጥ ልታልፍ ትችላለህ ሆኖም አንድ ቀን የዛሬው ማንነትህ ተቀይሮ ታላቅ ደረጃ እንደምትደርስ የእኒ ታላቅ ጳጳስ ህይወት ከተራ ማነቃቂያ ያለፈ የህይወት ምስክርነት ነው።
©via ከፍልስፍና አለም
✍Wasiehun Tesfaye
@mahtot

ዛሬ የምንወዳትን ሪም አል-ካማሊን(reem al-kamali) እያነበብኩ፣ አጋጣሚ ስለ እጣን የጻፈችውን ሳገኝ ቀጨም አደረግኩት። አላውቅም ነበር ሁሌ እጣን እሳት ሲነካው ለምን እንደሚጤስ ....
ድሮ ከብዙ ሺህ አመታት በፊት አንዲት ከመናፍስቱ አለም የሆነች ሴት(jinn) አንድ ወጣት ታፈቅራለች። ይህቺ የተዋሸች ሴት ባለችበት አለም፣ ከራስ ተፈጥሮ ውጪ ያለን ነገር ማፍቀር ነውር ነው። ከነውርም በላይ ወንጀል ነበር። ግን ፍቅር ይሄን ያውቃል? አያቅማ!
በማፍቀሯ አለቀሰች፣ ምርር ብላ ብዙ አነባች፣ ማቀቀች፣ ታሰረች፣ በመጨረሻ ተፈረደባት። በተማጽኖ ሌላ ነገር ከምሆን ዛፍ አድርጉኝ አለች። እሺታ አግኝታ ዛፍ ሆኖ ወደ ምድር ተጣለች። ከዛን ቀን አንስታ ብዙ ሺህ አመታት- ካለፈው የበለጠ እምባ ታነባለች። ሰዎች ሙጃ እያሉ እምባዋን ያጠራቅሙታል። ለፍቅር የምትከፍለው ለቅሶ አንዴ ሙጃ፣ አንዴ መስታወት ሆኖ ከገላዋ ይፈሳል፣ አንዳንዴ ቆዳዋንም ይገፍፉታል።ይሄ ሁሉ ስለ ፍቅር።
ይሄ እምባዋ ግን ለሷ ይምረር እንጂ ለእኛ ግን መልካም ነገርን ልባችን ላይ ያፈሳል፣ እሳት ሲነካው ያ ፍቅሯ መልካም መዐዛ ሆኖ ይሸተናል። ለፍቅር ሩቅ ይኬዳል አይደል? ዛሬ ዛሬ ሰዎች ከቡና ጋር ያቀርቡታል እኛ ቤት፣ መንፈስ ይለውጣል፣ ቤት ያሞቃል፣ ህመም ይፈውሳል። እዛ አረብ ምድር ደግሞ ዕጣን ይታኘካል፣ እንደ ከረሜላ በአፍ ይደረጋል ብዙ ብዙ።
እኔም፣ሪም ይገርመናል- እንዴት ከዚህ ዕጣን ዘይት ወጥቶ አምልኮ ቦታዎች ይቀባ ዘንድ የተገባ እንደሆነ። ሰዎች ወደ ሰማይ የሚያጤሱት መሆኑ ይገርማል።
| A beautiful tree, which suffered as
| a result of love, heroically
| produced a material that healed
| people. Isn’t it love that we seek
| from each other?
- Reem al-kamali-
እና ሪም እንደምትለው ይሄ አፈታሪክ እና ይሄ ዛሬ በዶፋር፣ ኦማን፣ የመን፣ እና መካከለኛው ምስራቅ ባሉ ቤቶች ሁሉ አሉ። ምንም መነሻ ባይኖረው አፈታሪክ፤ ታሪኩ ግን ሃይል እና እውነት አለው። ምክንያቱም ሁላችንም ፍቅርን አይደለ የምንሻው?
✍D/r. Semahel Dagne

ፊታውራሪ ተክለሐዋርያት ተክለማርያም በተዋበው የህይወት ታሪክ መፅሐፋቸው ላይ ያነሱትን ነጥብ
ሩስያውያን ስለ ምዕራባውያን-
ሰው ምንም የተማረ ቢሆን ምዕራባዊ አውሮፓን ካልጎበኘ የአውሮፓን ስልጣኔ በትክክል ለመረዳት አይችልም። ዕውቀቱም ሙሉ አይሆንም። ምዕራባውያን እኛን ሩስያኖችን ከግብዞች፥ ከገልቱዎች ይቆጥሩናል።
ለዚህም ምክንያት ይገኝላቸዋል። እነሱ ከኛ በፊት መሰልጠናቸው በታሪክ ላይ የታመነ ነው። አሁንም ቢሆን ከኛ በፊት መሰልጠናቸው አያጠራጥርም። ነገር ግን እንዴት ነው የሰለጠኑት? አንጎላቸውን፥ አንደበታቸውን፥ እጆቻቸውን፥ አኗኗራቸውን አሰልጥነዋል። ልቡናቸው ግን ወደጨካኝነት ተዛውሯል። ሃይማኖታቸውን፥ ፍቅርን፥ ቁም ነገርን ትተዋል። ነውርን ንቀዋል።
ቅሌተኛነት አያስጠይፋቸውም።
ይህ ሁሉ ያረጀ ፈሊጥ ይመስላቸዋል።
ፈጣሪን ክደዋል፤ ማቴሪያሊስቶች ሆነዋል። እምነታቸውንና ተስፋቸውን በነዋይ ላይ ብቻ አድርገዋል።
ዕውቀት የሚያስፈልጉት ለምድራዊ ኑርዋቸው ማደላደያ የጥበብና የዘዴ ማከናወኛ መስሪያ እንዲሆናቸው ነው እንጂ ለልቡናቸው ነፍሳዊ ሃይል እንዲሰጣቸው አይደለም። ዕውቀታቸው የስሌት፤ የሒሳብ ነው። ጥቅምን ለመፍጠሪያ ነው። ጥቅምን እየፈጠሩ ወዲያውም ችግርን ይፈጥራሉ። ነጋዴዎች ናቸው።
ሁሉንም ለገንዘብ ይለውጡታል። ጥበባቸው ሁሉ ወደ ጥፋት የሚወስድ ነው። ሁሉ ምዕራባውያን የሚገሰግሱት ከሌሎች ሕዝቦች በፊት፥ ለሌላው አጥፊዎች ራሳቸውም ጠፊዎች ለመሆን ነው።
ከዚህ መገንዘብ የምንችለው በነዴካርት የተጀመረው በጭንቅላት የመተማመን ፍልስፍና ከዘመናት በኋላ ያመጣውን አስከፊ መዘዝ ነው። መሰልጠን መሰይጠንን ያስከተለበት አቢይ ምሳሌ በዚህ ተገልጿል።
ስለዚህ ኢትዮጵያውያንም ሆኑ ሌሎች የምዕራቡን ነገር ሁሉ እንደብርቅና ድንቅ አድርገን ከመቀበል ይልቅ እንደ ዘርአ ያዕቆብ ሁሉ በመንፈሳዊ እይታ አስቀድሞ መመርመር እንደሚያስፈልግ ጠቋሚ ትምህርት ነው።

𝑴𝒐𝒓𝒆 𝒊𝒔 𝒍𝒆𝒔𝒔
መሰረታዊ ሃሳቡ ብዙ ምርጫ ሲኖራችሁ ትንሽ ምርጫ ነው ያላችሁ የሚል ነው... Let me explain.
እንደሚታወቀው ብዙ ጫማ አላችሁ ማለት ትንሽ ጫማ አላችሁ ማለት አይደለም፣ ነገር ግን አንዳንድ በማይጨበጡ ነገሮች ዙርያ ብዙ ነገር ሲኖራችሁ፤ ያላችሁ ምርጫም ይቀንሳል።
ለምሳሌ ታውቃላችሁ እንደ አሁኑ ዲሽ፣ ዩቲዩብ ምናምን ሳይመጣ ብዙዎቻችን ቤት የነበረን ቲቪ ብቻ ነው። ግፋ ቢል ማዮታ ዲቪዲ እና ቲቪ ነው። ይሄንን ስል ብዙ ሰው ዘጠናዎቹ ሊመስለው ይችላል። no ይሄ 2007 8 9 አከባቢ ነው። እና ብዙዎቻችን ቲቪ ላይ ምናየው ከ 3 ነገር አይበልጥም። ኢቲቪ፣ ኢቲቪ 2 ከዛ fox movies. እሱም ቀን ቀን fox movies ይሆንና ከ7 ሰአት በኋላ ሌላ የኢቲቪ 3 ሙከራ ስርጭት አይነር ነገር ይሆናል።
በዛ ሰአት ጠብቀን አብረን ሰብሰብ ብለን የምናያቸው ድራማዎች፣ ታለንት ሾው ምናምን ነገሮች ነበሩን። ከዛ ውጪ ተማሪ እያለን የሆነ ሰአት የሚተላለፈውን WWE የሚል ፕሮግራም እናያለን፣ ጠዋት ፊልም እናያለን። ከዛ ትምህርት ቤት ሄደን ያልጨረስነውን ፊልም ከጓደኞቻችን እየሰማን እንጨርሰዋለን። ቁጭ ብለን ሙሉ ፊልም ከ አንድ ሰው የምንሰማበት ጊዜ ነበር እሱም ሩቅ አልነበረም። አናስተውለውም እንጂ እኛ ሃገር ነገሮች የሄዱበት ፍጥነት በጣም የሚገርም ነው። ባንዴ ነው ሁሉንም እርግፍ አድርገን የጣልነው። ዲሽ ሲመጣ ሁሉ ነገር መለወጥ ጀመር። free ነገሮች ማየት ጀመርን። ያኔ በነበረን 3 ቻናል የምናያቸው ነገሮች ዋጋ ነበራቸው፤ ዲሽ ከመጣ በኋላ ግን ዋጋው ወረደ። ያኔም ቢሆን በተወሰነ መልኩ ደህና ነበር ማለት ይቻላል። ማስታወቂያ ጠብቀን እናያለን፣ ማሳለፍ የሚባለው የጥድፊያ ማቀላጠፊያ መሳርያ አልነበረውም ዲሽ።
ከዛ በኋላ ዘመነ ስልክ መጣ።
እና ብዙ ምርጫ ትንሽ ምርጫ ነው ስንል የምናየው ብዙ ነገር፣ ወይ የምናደርገው ብዙ ነገር በፊት በጥቂት ምርጫ የምናደርገውን ያህል እርካታ አይሰጠንም።
ጥያቄ: እስኪ የዩቲዩብ History ውስጥ ግቡና ምን ያህል short video እና ምን ያህል ቪድዮ ጨርሳችሁ እንዳያችሁ check አድርጉ። ከዛ የምታዩት ነገር መልሱን ይሰጣችኋል። የሰው ልጅ በተገደበ ስርዓት ውስጥ ካልሆነ መስተቀር እርካታን ማግኘት ከባድ ይሆንበታል ብዬ አስባለሁ። ሁሉም ገደብ ጥሩ ነው ባይባልም!
አንዳንዴ fox movies ይናፍቀኛል። እዛ ላይ ያየሁት toy story በሃሳቤ ይመጣል። ከሰአት etv2 ላይ የነበሩ የጃፓን ፊልሞችን ያየሁባቸው ጊዜያት ምንኛ rich ነበሩ እላለሁ። ዛሬ ሰብስክራይብ ካደረግኳቸው 1200 የዩትዩብ ቻናል የቱን ማየት እንዳለብኝ ራሱ አላውቅም። ወይም አንድ short ቪድዮ ካየሁ በኋላ ሳላቋርጥ ለሁለት ሰአት ስክሮል ሳደርክ ቆይቼ ሰው ካላነቃኝ እንደማልነቃ ሳስብ ይገርመኛል። ምን ይሁን?
✊etv2 ይመለስ
✊FoxMovies እና Mbc2 ይመለሱ
✊wwe ይመለስ

ትንሽ ቆይቷል-
እኛ ሰፈር አንድ ሰው ነበር(ስሙን መግለጥ አስፈላጊ ባይሆንም)። እና ረጅም ጊዜ ከሚስቱ ጋር በሰላም ነው የኖሩት። ደስ የሚል ፍቅር እንዳላቸው ሁሉም ያውቃል። የሆነው ሆኖ ግን ሚስቱ ልጅ መውለድ አልቻለችም ነበር። ያው በተለምዶ ሳይወልዱ ሲቀሩ፤ ሴቷ ላይ ማሳበቡ የተለመደ አይደለ? እና በወጣች በገባች ቁጥር 'ለምን አትወልዱም' የሚላቸው በዛ። በተለይ ሚስቱን የሚዘባበትባት ብዙ ነው። ቤቷ የሚመጡ ጓደኞች ሁሉ 'ባልሽ ሌላ ጋር ቢሄድብሽስ'፣ 'የሄኔማ አንዷ ጋር ልጅ አለው' ምናምን እያሉ ይጠዘጥዟታል። እኔ ሳያት ሰላም ብቻ ብያት ከማለፍ የዘለለ፣ አውርታኝ ድምጿን ሰምቼ እንኳን አላውቅም ነበር። ነገር ግን አይኗ የሆነ የደፈረሰ ነው በብዛት። ምናልባት የምታለቅስበት ይሆናል። ከጥቂት ጊዜ በኋላ የሆኑ ውሾች ግቢያቸው አምጥተው ማሳደግ ይጀምራሉ። ይሄንን የሰማሁት እኛ ጊቢ(ተከራይተው) ከሚያሽሟጥጡ ሴቶች ነው። 'ልጅ እምቢ ሲላት፣ ውሻ እንኳን ታሳድግ እንጂ ቂ ቂ ቂ' ግማታሞች።
እና አንድ እሮብ ስነሳ ጩኸት ሰምቼ ደንግጬ ወጣሁ። ስወጣ፣ ድንኳን ተጥሎ ሰው እያለቀሰ ነው። በመሃላችን ቢያንስ ስድስት ወይ አምስት ቤት ቢኖር ነው፣ ነገር ግን ፎቶዋ ጥርት ብሎ ታየኝ። ያለ ምንም ጥርጥር ራሷን እንዳጠፋች አወቅኩ። ፊቴን ታጥቤ ድንኳኑ ጋር ስደርስ፣ ስሟን እየጠሩ እያለቀሱ ነው። እውነት ነው ማለት ነው?!
'ይሄ የተረገመ የሰው አፍ ነው የገደላት' እያልኩ ተብሰለሰልኩ። ምን አለ የሃሜተኛው አፍ ሁሉ አንድ ሆኖልኝ በሰይፍ በቆረጥኩት- እያልኩ አለቀስኩላት-የኔ ምስኪን። ቀብሯ እንዳለቀ፣ ፖሊሶች ባለቤቷን አፈፍ አድርገው ሰው ወደ ቤታቸው ሲሄድ፤ እሱን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወሰዱት። ያንን እለት ሳስታውስ እውነት አይመስለኝም። የሰው ግርግር ሃዘኑን ከ ወከባው መለየት እንዲያቅተን አደረገ። የሆነው ሆኖ ባሏ እምባውን እያዘራ በፖሊስ መኪና ተጭኖ ሄደ። ሰዉ ባዶ ቤት እያለቀሰ ዋለ።
ቀናት አለፉ፣ በአራተኛው ቀን ተለቀቀና ወደ ቤቱ ሲመለስ፤ ሰዎች ተሰባስበው እንደ አዲስ አብረው አለቀሱ። ያ ሲያማት የነበረ ህዝቤ 'እንትናዬ' እያለ አለቀሰላት(ወይም አማት)። ለምን እንደሆነ ባላውቅም በባልየው ፊት ላይ ፍጹም ጸጥታ ነበረበት፣ ብዙ አያለቅስም።
ከተረገሙት የጊቢ ተከራዮች: እሱ እንደገደላት ተጠርጥሮ እንደነበር ሰማሁ። እና አሁን ተመርምሮ ነጻ ወጥቷል። እሱ ብቻ ሳይሆን ከመሞቷ አንድ ቀን በፊት የሆነ ሰው አጥራቸውን ዘሎ ገብቶ እንደነበር፣ በነጋታው ሌሊት ደግሞ(አጥራቸውን ዘሎ) ውሾቹን ገድሎ፣ ሚስትየው ስትጮህ በጩቤ ወግቷት፣ ባልየው ላይ ተኩሰው እቃ ተዘረፈ። ባሏ በተአምር ተረፏል። እሷ ካረፈች በኋላ ሁለት ቀን ያህል አይቼዋለሁ። 'እንዴት ነህ ቤቢ' ከሚለው ባለፈ ሌላ ማለቱን አላስታውስም። እናቴ ስትነግረኝ የተባለው ሌሊት ላይ ጩኸት እና ተኩስ ሰምታለች።
እንዲሁ በሌላ ምሽት ሰፈሩ በጩኸት ተደበላለቀ። በግምት 4 ሰዓት ሊሆን ይችላል። ሁላችንም ተገልብጠን ስንወጣ፣ ሰፈሩ በሰማያዊ እና ቀይ መብራት ተደበላልቋል፣ ፖሊሶች ሰፈሩን ውርር አድርገውት ነበር። ዛሬም ባሏን በካቴና አስረው፣በመኪና ጭነው ወሰዱት። 'ምን እየተፈጠረ ነው እዚህ ሰፈር' አልኩ። እስከ እኩለ ሌሊት የሰፈር ሰዎች ጊቢ ውስጥ ቆመው ሲያወሩ፣ ሲያሙ ምናምን አደሩ። ነገሩ እንዲህ ነው(እንዳሉት ከሆነ):
ባሏ ያን እለት ዘረፉ የተባሉትን ሰዎችን ያውቃቸዋል። እዚህ ከታ-ቡራዩ የሚኖሩ ትልቅ ቤተሰብ እና ባለጠጋ ናቸው አሉ። የባልየው ወንድም ቡራዩ ውስጥ የእነዚህን ባለጠጋ ልጅ ገድሎ ይሰወራል። ባለጠጎቹ አረሳስተው ይጠብቁና መጥተው በቀላቸውን ይወጣሉ። እሱን እንገድላለን ብለው መጥተው፤ እሷን ገድለዋት ሄዱ። እንደ ቀልድ!
ከዛ በኋላ የፍርድ ቤቱን ጉዳይ የተከታተለች የቤቱ ሞግዚት ስታወራልን(ቡና ላይ): " ስድስት ሰዎችን ጨምሮ በአልጋ ያሉ አሮጊት በአንድ ቀን ነው የተቀበሩት። ሁለቱ ሰዎች በስለት ተቆራርጠው፣ የቀሩት:ቤት ተዘግቶባቸው- ከነቤቱ ተቃጠሉ። በአግባቡ የተቀበሩት በስለት የተተለተሉት ብቻ ናቸው። ቤቱ የተቃጠለባቸውን መለየት እንኳ አልተቻለም አሉ በስማም! ፊቱ ላይ አንድም ፍርሃት አይታይም ነበር። መጨረሻ ላይ ስለ ሚስቱ ሲነሳ ብቻ ትንሽ እምባ አይቻለሁ" አለች።
ባሏ በህግ ቁጥጥር ስር ይቆይ ተብሎ እስካሁን አልተፈታም።ከዛ በዘለለ ግን ምንም አይነት ማስረጃ በእሱ ላይ አልተገኘም። 'አልገደልኩም' ከሚለው ሌላ ብዙ አይናገርም ይላሉ ያዩት። እንድ ቀን ሄጄ እጠይቀዋለሁ 'ገድለሃቸዋል?' እለዋለው ብዬ አስብና፣ መልሱን ስለማውቀው አስካሁን አልሄድኩም። አንድ አንድ ሃሜተኞች ዛሬም 'ውይይይ እንደው ምን አይነት ጨካኝ ነው እቴ? በስለት እንዲ' ፣' ያቺ ምስኪን ሚስቱ ናት እንጂ እሱስ' እያሉ ከንፈር ይጠቡላታል። እና አስባለሁ- ለምን ይዘገንናቸዋል፣ ፊልም እና መጽሐፍ ላይ የምናነበው የበቀል ታሪክ ይሄ አይደለ? ከተቀመጥንበት ሳንነሳ የምናየው የaction ፊልም ይሄ አይደለ? ለምን እሱ አይዘገንነንም? John wick ይሄ አይደለ ታሪኩ?
ነገር ግን Mark twain እንዳለው ነው "truth is stranger than fiction". እውነት ትንሽ የመዘግነን አዝማምያ አላት። ያኔ ያየሁት የደፈረሰ አይኗ ሲመጣብኝ የእውነት ሰውነቴ ይታመማል። life is not fair እላለሁ። አንድ ቀን ከሰው አፍ ሳታርፍ፣ ከዛም በማያገባት ነገር ህይወቷ ተቀጥፎተቀጥፎ ማለፏ፣ እንደው ለፈጣሪ ምን ብላ ትከሰን ይሁን? በተለይ የዚህን ሰፈር የተረገሙ ሃሜተኞችማ...

• THE BIG SHIT •
ፍሪዳ ካሕሎ | Frida kahlo የምን ጊዜውም ምርጧ ሴት አርቲስት ናት። የሜክሲኮ ገበያ ብትሄዱ በየ ቦርሳ፣ ቲሸርት፣ ደብተር፣ ካፌ ላይ ፎቶዋን ወይም ስሟን አታጡትም። የሜክሲኮዎች ገብረክርስቶስ ደስታ፣ የላቲኑ አለም አፈወርቅ ተክሌ በሏት። ፍሪዳ ካሕሎ ስትወለድ ስሟ frieda kahlo(ፌሬይዳ) ነበር- ልክ እንደ ብዙዎቹ አርቲስቶች ከፍ ስትል፣ አፍ ላይ ለመያዝ ወደሚቀለው ፍሪዳ ለወጠችው። በ1907 ነበር የተወለደችው- ከአለም ጦርነት 7 አመት ቀደም ብላ። ለሚመጣው ጡዘት ትዘጋጅ ዘንድ 7 አመቅ ቀደም ብላ የተወለደች ይመስላል። ዝም ብዬ ሳስበው የፍሪዳ ልጅነት በመጥፎ ወሬ የተሞላ ይመስለኛል። ዛሬ እኮ እገሌ ሞተ፣ ለስራ ሄዱ በቦምብ እንዲ ሆነ የሚል ወሬ እየሰማች ነው ያደገችው።
ያንን ሁሉ አልፋ 18 አመቷ ላይ ባስ ይገጫታል። ተራ ግጭት አይምሰላችሁ: የእጅ ድጋፍ የሆነ ብረት በጎኗ ገብቶ uterusሷን ጎድቶ pelvis በሚባለው የታችኛው ሆዷ ክፍልን በስቶ ወጣ። አለም ለትልቅ ነገር ስታዘጋጅህ እንዲ ነው። አልጋ ላይ ለሞት እያጣጣረች ብዙ ጊዜ ቆየች። ለትልቅ ነገር የታሰበች ነፍስ መቼ በቀላሉ ትሄዳለች? ባትሞትም ግን፣ አካሏን ላይሻር ሰብሯት አልፏል። የጀርባ አጥንቷ ላይ የደረሰው ጉዳት እስከ ወዲያኛው ተከትሏታል።
አካሏ እክል ኖሮት፣ አለም በጦርነት ሰክራ፤ እሷ ግን መኖርን የመረጠች ሰው ናት። ራስህን ሁን ሳይሆን-ፍሪዳን ሁን ነው 'ሚባለው። እዛው አልጋዋ ላይ ሆና አንዳንዴ ትስላለች፣ አንዳንዴ አልኮል ነገር ትቀምሳለች፣ ታጨሳለች፣ ዲዬጎ የሚባለውን ፍቅረኛዋን ትስመዋለች፣ ታነባለች፣ ፎቶ ያነሷታል በቃ የቱንም ያህል ቢያማት መኖርን መረጠች። ላለመኖር ከፍሪዳ በላይ፤ ማን ምክንያት ሊኖረው ይችላል?

ፍሪዳ የምትላት ነገር አላት: ሁሉም ሰው እገሌ is the big shit ይላል እኔ ግን አይመስለኝም፣ ዋናው ነገር ትልቅ ፍላጎት ነው ይላሉ እኔ ግን እብሪቱን እጠላዋለሁ፣ ትልቅ ጉዳይ(the big shit) መሆን ብዙም አይስበኝም..ምናምን ትላለች። ፍሪዳ ከስዕል ሌላ ሲበዛ ፖለቲከኛም ነበረች። ታዋቂ ከሆነች በኋላ ሰዎች በብዛት ያገኟት የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ፣ ወይም የህዝብ ተቃውሞ ሲኖር ስትናገር ነው። ከመሞቷም በፊትም ለመጨረሻ ጊዜ የታየችው መፈንቅለ መንግስቱን የሚደግፍ ተቃውሞ ላይ ነበር።
ብረቱ ማህጸኗ ላይ ባደረሰው ጉዳት ምክንያት ልጅ መውለድ ሳትችል ቀረች፣ ባደረገችው 30+ ቀዶ ጥገና ብዙ ጊዜ በክራንች ወይ ዊልቸር እየተዟዟረች ያላትን ሁሉ አካፍላለች። አንዴ ስለእግሯ "ክንፍ እያለኝ ለምን ታስፈልገኛለክ" ብላለች ይባላል። በብዛት የሳለቻቸው ስዕሎች እንደ እኔ ዝም ብሎ ለሚያይ ሰው ግራ የሚያጋባ ነው። የሚበዙት ራሷን(self portrait) የሳለችው ነው። ሌላው ግን ለምሳሌ የቆመ ብረት እንደ ጀርባ አጥንት አድርጋ የሳለችው ስዕል፣ በአዋቂ ፊት ጡት ስትጠባ..ያሉት ስዕሎች የማይገጥሙ ነገሮች እንዴት ገጠሙ ያስብላል። ያው እንደተለመደው አለም ያወቀቻት ከሞተች በኋላ ነው። ፍሬ ካለቻቸው የተወሰነ ...
At the end of the day, we can endure much more than we think we can
I drank to drown my sorrows, but the damned things learned how to swim.
(የምሰክረው ስቃዬን ለማስጠም ነበር፤ እሱ ግን ዋና ለምዷል)
I hope the exit is joyful and I hope never to return.
I paint flowers so they will not die