ሥራህን ሥራ
ሌሎች ሰዎችን ከማያድን ክርስቲያን በላይ የከፋ ምንም የለም፡፡ አንተ ሰው! ድኻ ነኝ የምትለኝ ለምንድን ነው? ኹለት ዲናር የጣለችዋ ሴት ትፋረድባሃለች፡፡ ከምናምንቴ ቤተሰብ እንደ ተወለድክ የምትነግረኝስ ለምንድን ነው? ሐዋርያትም ምናምንቴዎች ነበሩ፤ ነገር ግን ታላላቅ መኾን ተችሏቸዋል፡፡ አለመማርህን ሰበብ አድርገህ አትንገረኝ፤ ሐዋርያትም ያልተማሩ ነበሩና፡፡
ባሪያ ብትኾንም እንኳ፣ ስደተኛ ብትኾንም እንኳ ሥራህን መሥራት ይቻልሃል፤ ሌሎችን መርዳት ይቻልሃል፤ ሰዎችን ማዳን ይቻልሃል፥ አናሲሞስም እንደ አንተ ዓይነት ሰው ነበርና (ፊልሞ.1፥10-11)፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ጳውሎስ እንደ ምን ወዳለ ማዕረግ ከፍ እንዳደረገውና ምን ብሎ እንደ ጠራው አድምጥ፡- “በእስራቴ ስለ ወለድሁት፡፡”
ወዳጄ ሆይ! እኔ እንኳን ሕመምተኛ ነኝ ብለህ አትንገረኝ፤ ጢሞቴዎስም እንደ አንተ ዘወትር ይታመም ነበር፡፡
ፍሬ የማያፈሩ ዛፎች እንደ ምን ብርቱዎችና ተወዳጆች፣ ግዙፋንና ሐመልማላውያን እንደዚሁም ረጃጅም እንደ ኾኑ አላየህምን? የፍራፍሬ ቦታ ቢኖረን ግን ፍሬ የሚያፈሩት ሮማንንና ወይራን እንተክላለን እንጂ እነዚህ ፍሬ የማይሰጡንን ዛፎች አንተክልም፡፡ ምክንያቱም እንዲሁ ለዓይን ማረፊያ ለማየት ካልኾነ በስተቀር ሌላ ጥቅም የላቸውምና፡፡
የራሳቸውን ጥቅም ብቻ የሚመለከቱ፣ ሌሎች ሰዎችንም የማይረዱ ክርስቲያኖችም እንደ እነዚህ ዛፎች ናቸው፡፡ እንዲያውም ከእነዚህ ዛፎችም የባሱ ናቸው፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች የሚቆረጡት ለእሳተ ገሃነም ነው፡፡ ዛፎቹ ግን ቢያንስ ቢያንስ ጠረጴዛም ወንበርም ለመሥራት ይጠቅማሉ፡፡ ለቤት መሥሪያ ይጠቅማሉ፡፡ አጥር ቅጥር ኾነው ያገለግላሉ፡፡
እነዚያ አምስቱ ደናግል እንደዚህ ነበሩ (ማቴ.25፥1)፡፡ ርግጥ ነው ንጽህናቸውን የጠበቁ ነበሩ፡፡ ለሚያያቸው ኹሉ ግሩም የኾነ ጠባይ የነበራቸው ነበሩ፡፡ ሥርዓት ያላቸው ነበሩ፡፡ ይህ ኹሉ ግን ምንም አልጠቀማቸውም፡፡ ወደ እሳተ ገሃነም ከመጣ’ል አልታደጋቸውም፤ ዘይት የተባለው ምጽዋት አልነበራቸው’ማ! ክርስቶስን በነዳያን አማካኝነት የማይመግቡትም ዕጣ ፈንታቸው ጽዋ ተርታቸው ይኸው ነው የሰነፎቹ ደናግል ዕጣ!
አንተ ሰው ልብ ብለህ አስተውል! እነዚህ ደናግል በግል ኃጢአታቸው አልተነቀፉም፡፡ በዝሙት ወይም በሐሰት ምስክርነት አልተወቀሱም፡፡ በፍጹም! ይልቁንም የተነቀፉትና የተወቀሱት ሌሎች ሰዎችን ባለመጥቀማቸው ነው፡፡
እንደዚህ ከኾነ ታዲያ ሰዎች ክርስቲያን ተብለው ሊጠሩ የሚችሉት በምን መመዘኛ ነው? እኮ በምን መስፈርት? አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ! በሊጥ ውስጥ የተጨመረ እርሾ ሊጡን እንዲቦካ ካላደረገው እንዲሁ እርሾ ተብሎ መጠራት ብቻውን ምን ይረባዋል? ዳግመኛም ወደ እርሱ የቀረቡትን ሰዎች መዓዛው ካልሸተታቸውና ቤቱን ካላወደው በቀር ከርቤ በከርቤነቱ ምን በቁዔት አለው?
ሌሎች ሰዎችን መርዳት አይቻለኝም ብለህ አትንገረኝ፡፡ እንዲያውም ልንገርህ፤ አንተም ስማኝ፡- አንተ በእውነት ክርስቲያን ከኾንክ ሌሎች ሰዎችን አለመርዳት የማይቻል ነው፡፡ ዕጣን መዓዛ እንዲኖረው፣ እርሾም ሊጥን እንዲያቦካ ተፈጥሮው እንደ ኾነ ኹሉ፥ አንድ ክርስቲያንም በስም ክርስቲያን ከመባል አልፎ በእውነት ያለ ሐሰት ክርስቲያን ከኾነ ሌሎች ሰዎችን መርዳት መቻሉ፣ ሌሎችን የሚጠቅም ሥራ መሥራቱ ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነው፡፡
ስለዚህ አይኾንልኝም፤ አይቻለኝም በማለት እግዚአብሔርን አታማርር፡፡ ፀሐይ ብርሃኗን በእኔ ላይ ማብራት አይቻላትም ካልክ ፀሐይን እየሰደብካት ነው፡፡ ልክ እንደዚሁ አንድ ክርስቲያንም ሌሎች ሰዎችን ሊጠቅማቸው አይችልም የምትል ከኾነ እግዚአብሔርን እየሰደብክ [ሎቱ ስብሐትና] ሐሰተኛም እያደረግኸው ነው፡፡ ምክንያቱም አንድ ክርስቲያን ሌሎች ሰዎችን ካለመርዳትና ካለመጥቀም ይልቅ ፀሐይ ሙቀትና ብርሃን ባትሰጥ ይቀላል፡፡ እንደዚህ ከሚኾን ብርሃን ወደ ጨለማ መቀየር ይቀላል፡፡
እናስ? እና’ማ አይቻለኝም አትበለኝ፡፡ የማይቻለው መርዳት አለመቻል ነውና፡፡ አይኾንልኝም እያልክ በከንቱ እግዚአብሔርን አታማርር፡፡
ሕይወታችንን በአግባቡና በሥርዓቱ የምንመራ ከኾነ እነዚህን ነገሮች ኹሉ በቀላሉ ማድረግ ይቻለናል፤ እነዚህ ነገሮች ሊደረጉ ግድ ነው፡፡ በመቅረዝ ላይ የተቀመጠ ሻማ ብርሃኑን መደበቅ እንደማይቻለው ኹሉ ክርስቲያንም የእውነት ክርስቲያን ከኾነ ብርሃኑም መሸሸግ አይቻለውም፡፡ ስለዚህ እውነተኞች ክርስቲያኖች ከኾንን ሌሎች ሰዎችን መርዳት መጥቀምም ችላ አንበል፡፡
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - የክርስቲያን መከራና ሌሎች ገጽ 72-75)

Telegram
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
በዚህ ቻናል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡
በቤትህ ያለው ዳቦ ለተራበው ሰው የሚውል(ንብረቱ) ነው፥ በልብስ ማስቀመጫህ ውስጥ ያለው የማትጠቀመው ኮት የችግረኛው ገንዘቡ ነው፥ በጫማ ማስቀመጫህ ውስጥ አልፈልገውም ብለህ ሊበላሽብህ የሆነው ጫማ የደሃው ጫማ (ጫማ ለሌለው ገንዘቡ) ነው ፥ ያከማቸኸው ገንዘብ ለድሃው የሚገባው ነው....
ዛፍ በፍሬው ይታወቃል፥ ሰውም በድርጊቱ፡፡ መልካም ስራ መቼም አይጠፋም፡፡ መልካም እርዳታን የሚዘራ፥ ወዳጅነትን ያጭዳል፡፡ ደግነትን የሚተክል ፍቅርን ይሰበስባል፡፡
"ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ብቻ የለብንም፥ ነገር ግን ካነበብነው ተምረን ማደግ አለብን፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ምንም የማይጠቅም ነገር እንዳልተጻፈ ተገንዘብ፡፡
አሁንም ለጥንካሬ፣ ለመታገስ፣ ለመዳን፣ ለመለወጥ ጊዜ አለህ! ተኝተሃልን? ንቃ! ኃጢአት ሰርተሃልን? እንግዲያውስ መስራቱን አቁም፡፡
(ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ)

Forwarded from ማኅቶት Wave
♦⛪️የኢኦተቤክ አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ የትኞቹን መዝሙራት ማግኝት ይፈልጋሉ⁉️
👏 የቸብቸቦ መዝሙራት
📖▓⇨→vido ⇨ግጥም
🎻 የበገና መዝሙራት
📖▓⇨→vido ⇨ግጥም
👑 የቅዱሳን መዝሙራት
📖▓⇨→vido ⇨ግጥም
⛪️ የንግስ መዝሙራት
📖▓⇨→vido ⇨ግጥም
🤲 የምስጋና መዝሙራት
📖▓⇨→vido ⇨ግጥም
🙏 የንስሐ መዝሙራት
📖▓⇨→vido ⇨ግጥም
💍 የሠርግ መዝሙራት
📖▓⇨→avido ⇨ግጥም
🌦 ወቅታዊ መዝሙራት
📖▓⇨→vido ⇨ግጥም
🇪🇹 ለአገር የተዘመሩ
📖▓⇨→vido ⇨ግጥም
👇👇
https://www.tg-me.com/+lVXHSARuil5kZDU0
👇🏽ከእስልምና ወደ ክርስትና በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ በYOUTUBE👇🏽
👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽

ማኅቶት ፕሮሞሽን💓
You’ve been invited to add the folder “ማኅቶት ፕሮሞሽን💓”, which includes 100 chats.
#ደብረ_ዘይት
(የዐቢይ ጾም አምሥተኛ ሳምንት)
የዐቢይ ጾም የአምስተኛው ሳምንት ደብረ ዘይት ይባላል፡፡ ጌታ በደብረ ዘይት የዳግም ምጽአቱን ነገር ማስተማሩ ይነገርበታል፡፡ ደብረዘይት የስሙ ትርጓሜ የዘይት ተራራ ማለት ነው ስያሜ የተሰጠው በቦታው ብዙ ወይራ ተክል ይበቅልበት ስለ ነበር ነው፡፡
እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ ደቀመዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው ንገረን ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድን ነው?›› አሉት (ማቴ. 24፥3፣ ዘካ. 14፥5 ፤ ሐዋ. 1፥11 ፤ 1ኛ ተሰ. 4፥16 ፤ ራዕ. 22፥7)
#አመጣጡስ_እንዴት_ነው?
ጌታ ይህንን ዓለም ለማሳለፍ ለሁሉም እንደ ሥራው ለመክፈል በግርማ መለኮቱ በክበብ ትስብዕቱ ይመጣል፡፡ ጊዜው ዘመነ ዮሐንስ ወርሃ መጋቢት ዕለት እሑድ መንፈቀ ሌሊት እንደሆነ ሊቃውንት ተናግረዋል፡፡ ምነው የሚያውቀው የለም ይባል የለምን? ቢሉ እውነት ነው የሚያውቀው የለም ብዙ የዮሐንስ ዘመን፤ ብዙ የመጋቢት ወር፤ ብዙ የእሑድ ዕለት አለና ለይቶ የሚያውቅ የለም፡፡ ሞት ለማን አይቀርምና ሁሉም ይሞታል፡፡ ዘፍ. 3፥19 በዕለተ ምጽአት ቅዱስ ገብርኤል ስምንቱን ነፋሳተ መዓት ከየመዛግብታቸው ያወጣቸዋል፡፡ ዛፏን ነቅለው ደንጊያውን ፈንቅለው ምድርን እንደ ብራና ይዳምጧታል፡፡ ቅዱስ ሚካኤል መለኸት ይነፋል፡፡ 1ኛ መቃ. 9፥8 ቅዱስ እግዚአብሔር ዘያነቅሖሙ ለሙታን ሲል በዱር በገደል በባሕር በየብስ በመቃብር ውስጥ ያሉት በአውሬ ሆድ ውስጥ ያሉ ሁሉ ይሰበሰባሉ፡፡ በሁለተኛው ነጋሪት ሲመታ አጥንትና ሥጋ አንድ ሆነው ፍጹም በድን ይሆናሉ፡፡ ሦስተኛው ነጋሪቱን መቶ (ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ህያው ዘኢይመውት) ንቃሕ መዋቲ ዘትነውም ባለ ጊዜ መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ደጉ ደጉነቱን ክፉውም ክፋቱን ይዞ ይነሳል፡፡
ወንዱ የ30 ዓመት ሴቲቱ የ15 ዓመት ሆነው ጻድቃን ብርሃን ለብሰው ብርሃን ተጎናጽፈው ከፀሐይ 7 እጅ አብርተው ማቴ.13፥43 ኃጥአን ጨለማ ለብሰው ፍጹም ዲያቢሎስን መስለው ይነሳሉ፡፡ ጻድቃን ስለሠሩት መልካም ሥራ ኑ የአባቴ ቡሩካን ብሎ መንግሥተ ሰማያትን ያወርሳቸዋል፡፡ ኃጥአንን ስለ ክፉ ሥራቸው (ከኔ ሂዱ) ገሃነም ይሰዳቸዋል፡፡ ጻድቃን ደስ ይላቸዋል ኃጥአን ግን ያዝናሉ፤ ዋይ ዋይ ይላሉ፤ ደረት ይደቃሉ እንባቸው ያፈሳሉ፡፡ የማይጠቅም ለቅሶ የማይጠቅም ሐዘን ሰቅለው የገደሉትም አይሁድ ክብሩን አይተው ላይጠቀሙ ይጸጸታሉ፡፡
#ምልክቱስ_ምንድን_ነው? ብለው ጌታን ሲጠይቁ ‹‹ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፡- ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፡፡ ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ፤ ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ አትደንግጡ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው፡፡ ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሳል፤ ረሃብም ቸነፈርም መናወጥም በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው፡፡ በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል ይገድሉአችሁማል፤ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ›› አላቸው፡፡ በዳግም ምጽአቱ ጊዜ ከቅዱሳኑና ከሰማዕታቱ ጋር ለመቆም ያብቃን፡፡
#የዕለተ_ሰንበት_መዝሙር_ከጾመ_ድጓ
እንዘ ይነብር እግዚእነ ውስተ ደብረ ዘይት ወይቤሎሙ ለአርዳኢሁ ዑቁኬ ኢያስሕቱክሙ ወንበሩ ድልዋኒክሙ ብዙኃን ይመጽኡ በስምየ እንዘ ይብሉ አነ ውእቱ ክርስቶስ ወዘአዝለፈ ትዕግሥቶ ውእቱ ይድኅን ወአመ ምጽአቱሰ....
(ጌታችን በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ ለደቀ መዛሙርቱ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፤ ተዘጋጅታችሁም ኑሩ፤ ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ እስከ መጨረሻው የጸና እርሱ ይድናል፡፡....)
#የዕለቱ_ምንባባት
1ኛ ተሰሎንቄ 4÷13-ፍጻ፡-
ወንድሞቻችን ሆይ÷ ስለ ሞቱ ሰዎች÷ ተስፋ እንደሌላቸው ሰዎች እንዳታዝኑ ልታውቁ እንወዳለን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞቶ እንደ ተነሣ ካመንን እንዲሁ እግዚአብሔር ሙታንን በኢየሱስ ያስነሣቸዋል ከእርሱም ጋር ያመጣቸዋል፡፡.....
2ኛ ጴጥ.3÷7-14፡-
አሁንም ሰማይና ምድር በዚያ ቃል ለእሳት ተዘጋጅተዋል፤ ኃጥኣን ሰዎች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀንም ተጠብቀዋል፡፡ነገር ግን ወንድሞቻችን ሆይ÷ ይህን አትርሱ፤ በእግዚአብሔር ዘንድ አንዲት ቀን እንደ አንድ ሺህ ዓመት÷ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን ነውና፡፡.....
ሐዋ. 24÷1-21፡-
በአምስተኛውም ቀን ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ከመምህራኑና ጠርጠሉስ ከሚባል አንድ ጠበቃ ጋር ወረደ፤ ጳውሎስንም በአገረ ገዢው ዘንድ ከሰሱት፡፡..... (ተጨማሪ ያንብቡ)
#የዕለቱ_ምስባክ
መዝ. 49÷2
እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ
ወአምላክነሂ ኢያረምም
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ፡፡
ትርጉም፦
እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል፡፡
አምላካችንም ዝም እይልም፤
እሳት በፊቱ ይነድዳል በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ አለ፡፡
#የዕለቱ_ወንጌል
ማቴ. 24÷1-25፡-
ጌታችን ኢየሱስም ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ሄደ፤ ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው የቤተ መቅደሱን የሕንጻ አሠራር አሳዩት፡፡ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው÷ “ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፤ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም፡፡.....” (ተጨማሪ ያንብቡ)
#የዕለቱ_ቅዳሴ፦ ቅዳሴ አትናቴዎስ
ምንጭ፡-
(የማቴዎስ ወንጌል 24፥1 ትርጓሜ፣ መዝገበ ታሪክ ቁጥር 2፣ ግጻዌ)

ተግሣፅ ዘቅዱስ ኤፍሬም
ሕይወትህን በአግባቡ መምራት ትፈልጋለህን? እንግዲያውስ ትሕትናን ተለማመድ፤ ያለ ትሕትና ተገቢውን ሕይወት መምራት አይቻልም፡፡ ሥራህን ሁሉ በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ጀምር፡፡ ያን ጊዜ ፍሬዎችህ ወደ መንግሥተ ሰማያት ይደርሳሉ።
ሰው ከትሕትና ከራቀ ከትክክለኛው መንገድ ርቋል ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔርን የተወ ሰውን ርኵስ መንፈስ እንደ ሳውል ያስጨንቀዋል። የጠላት ወጥመድ በማር የተቀባ ነው፡፡ በማር ጣዕም የሚማረክ ሰው ሐዘንን ሁሉ በያዘ ወጥመድ ይያዛል። ትሕትናን ውደዱ፤ ያን ጊዜ ከሰይጣን ወጥመድ ውስጥ አትወድቁም፡፡ በትሕትና ክንፍ በበረራችሁ ቁጥር ሁል ጊዜ ከጠላት ወጥመድ በላይ ትሆናላችሁ።
ግልፍተኝነት እንደ በሰበሰ ረጅም ዛፍ ነው፤ ቅርጫፎቹ ሁሉ በቀላሉ የሚሰበሩ ናቸው᎓᎓ አንድ ሰው በወጣባቸው ጊዜ ከወጣበት ከፍታ ወዲያውኑ ይወድቃል፡፡ በመልካም ሐሳብ ልቡናው የበራ ሰው ግን ምስጉን ነው፤ ክብሩም ታላቅና ዘላለማዊ ነው።
እንግዲህ ራሳችንን ለመቆጣጠር እንጣር ያን ጊዜ ኃጢአታችንን እንረዳለን፡፡ ያን ጊዜም ሁል ጊዜ ራሳችንን ዝቅ እናደርጋለን፤ እንደ እባብ በእብሪት መወጠርን እና ራሳችንን ከፍ ከፍ ከማድረግ እንቆጠባለን፡፡ እንግዲህ ራሳችንን ዝቅ ዝቅ ማድረግን እንውደድ፤ በንጹሕ ልቡና ሆነን ምናልባት የተሰጠንን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በኃጢአት ከማቆሸሽ እንታደግ ይሆናል።
መልካም ጸሎት በሳግ እና በዕንባ የታጀበ ነው፤ በተለይ ደግሞ በምሥጢር የሚፈስ ዕንባ፣ በልቡናው ከፍታ ሆኖ የሚጸልይ ጌታውን በፊቱ ያያል። እኛ የምንኖረውና የምንሔደው በእርሱ ፈቃድ ነውና። ልቡናችሁ ከጠነከረ በጌታችን ፊት አልቅሱ እርሱ የዕውቀትን ብርሃን ይገልጥላችኋል፤ ወደ እርሱ የሚወስዳችሁ አዲስ ልብንም ይሰጣችኋል።
ንስሓ የገቡና ምሕረት የለመኑ ሰዎች ዕዳቸው ተሰረዘላቸው፤ ነገር ግን ለሠራኸው በደል ምሕረት ስትለምን ወንጀልን እና በደልን፤ በወንድምህም ላይ ቂም መያዝን መተው ይገባሃል። ፍቅር ሳይኖርህ ወደ እግዚአብሔር የምታደርገው ልመና ከተዘጋው በር ውጭ ይቀራል፡፡ የጸሎትን በር የሚከፍት ፍቅር ብቻ ነው፡፡
ወንድምህን ብታስቀይም እግዚአብሐርን ታሳዝናለህ፤ ካንተ ጋር ካለው ከወንድምህ ጋር ሰላምን ከፈጠርህ ግን በሰማይ ካለው ከእግዚአብሔር ጋር ትታረቃለህ፡፡ ወንድምህን በፍቅር ብትቀበለው፣ በደሉንም ይቅር ካልከው እግዚአብሔርን ተቀበልክ፡፡
ስለዚህ በተናደዱ ሰዎች በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ታረቅ፤ እንግዲህ የተበሳጩትን በማስደሰት እግዚአብሔርን አስደስተው፣ በታሰሩት ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን ጎብኘው፣ በተራቡት ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን አብላው፤ በታረዙ ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን አልብሰው፣ መንገደኛን በመቀበል እግዚአብሔርን በአልጋህ ላይ አስተኛው፤ እግሮቹንም እጠበው፣ በማዕድህም አስቀምጠው፣ እንጀራህንም ከእርሱ ጋር ተካፈል፤ ጽዋህንም ስጠው᎓᎓ እርሱ ታላቅ ፍቅሩን አሳይቶሃልና፤ እርሱ ስለ አንተ ብሎ ትበላው ዘንድ ሥጋውን ቆርሶልሃል፣ ትጠጣው ዘንድም ደሙን አፍስሷል።

እንደ ኃጢአት አዋራጅ የለም
እንደ ኃጢአት አዋራጅ የለም፡፡ ኃጢአትን የሚያደርግ ሰው በሐፍረት ካባ ብቻ የሚከናነብ አይደለም፤ አስቀድሞ ከነበረው ማስተዋልና ማገናዘብም ይዋረዳል እንጂ፡፡ ይህንንም ለመረዳት የአዳም የቀድሞ ክብሩን ማሰብ እንቸችላለን፡፡
ዳግመኛም ኃጢአትን ከሠራ በኋላ ያገኘውን ውርደት እንመልከተው፡፡ “በሰርክ ጊዜ ጌታ በገነት ውስጥ ድምፀ ሰናኮ ብእሲ እያሰማ ወደነርሱ ሲመጣ በሰሙ ጊዜ አዳምና ሔዋን ከእግዚአብሔር ፊት በገነት ዕንጨት መካከል ተሰወሩ” (ዘፍ.3፥8)፡፡ በዚህስ አዳም እንደ ምን ባለ ውርደት እንደ ተያዘ ታስተውላላችሁን? ምሉእ በኩለሄ ከኾነው፣ ፍጥረታትን ካለ መኖር ወደ መኖር ካመጣው፤ የተሰወረውን ኹሉ ከሚያውቀው፤ የሰውን ልቡና የፈጠረና በኀልዮ የሠሩትን ዐውቆ ከሚፈርደው (መዝ.33፥15)፤ ልብ ያሰበውን ኩላሊት ያጤሰውን መርምሮ ከሚያውቀው (መዝ.7፥9)፤ ልቡናችን ያሰበውን ከሚያውቀው (መዝ.44፥21) ከእግዚአብሔር ሊሸሸግ መውደዱ ከማወቅ ወደ ድንቁርና ከክብር ወደ ኃሣር እንደ ኼደ ያመለክታል፡፡
እኛም ኃጢአት ስንሠራ እንደዚህ ነው፡፡ መሸሸግ ባንችል እንኳን መሰወርን እንሻለን፡፡ ይህን ማድረጋችንም በኃጢአታችን ምክንያት ክብራችን እንደ ምን እንዳጣን፤ ሐፍረታችንን መሸፈንም እንደ ምን እንዳቃተን ያስረዳል፡፡ ነገር ግን ኃጢአትን የሠራ ሰው እንኳንስ በረኻ በኾነች በዚህች ምድር በገነት መካከልም መደበቅ አይችልም፡፡
("የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች" በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 81 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)

Forwarded from Elohe pictures (几ㄖᐯ卂ᵘᶜʰⁱʰᵃ)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Elohe pictures (几ㄖᐯ卂ᵘᶜʰⁱʰᵃ)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ማኅቶት Wave
✅❤️የተወለዱበትን ወር በመምረጥ የሚደርሶትን መንፈሳዊ ቻናል በመቀላቀል ዕውቀቶችን ያግኙ
መልካም ዕድል!!!
https://www.tg-me.com/addlist/hVsJ5h6oKyk1NDRk

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በእናንተው ደጋፍ የተጀመረው እዚህ ደርሷል አሁንም ድጋፋችሁ አይለየን 🙏🙏🙏
የቤተክርስቲያኑ የባንክ አካውንት
💰 👉 1000265718063 👈
ገላን ቅዱስ ሚካኤል
ሁላችንም 100 ብር ብናስገባ ብዙ ነገር መሸፈን እንችላለን የቅዱስ ሚካኤል ምልጃው እና ጥበቃው አይለየን 🙏🙏🙏
ለበለጠ መረጃ የደብሩ ስልክ
+251950008283
የቅዱስ ሚካኤል ወዳጅ የሆናችሁ
የአቅማችሁን ሼር በማድረግ ማገዝ ለሚችሉ እናድርስ
T.me/Elohe_picture

Forwarded from Elohe pictures
ቻናሉ ላይ ምን እንዲጨመር ትፈልጋላችሁ???
ከዚህ ውጭ ካለ ኮሜንት ላይ ይፃፉልን ከፍተኛ ብልጫ ያለውን 1 / 2 ጭማሪ እናደርጋለን መልካም ዕለተ ሰንበት ።☦️ ማኅበራችንን መቀላቀል ለምትፈልጉ @Elohe_picture_robot ልታገኙን ትችላላችሁ

Anonymous Poll
36%
መዝሙር/ የመዝሙር ግጥሞች
28%
የእለቱ ማኅሌት እና ምስባክ
43%
ኮርስ
27%
ዕለታቱን የጠበቁ ግጥሞች
18%
የጉዞ አገልግሎት
37%
የአብነት ትምህርት ከቁጥር - አቋቋም
26%
ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ዜናዎች
47%
ኦርቶዶክሳዊ መጻህፍት በPDF
Forwarded from Elohe pictures
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ለማመን የሚከብዱ ታሪኮች አሉበት፡፡ እባብ ከሰው ጋር ሲነጋገር ፣ አህያ ጌታዋን ስትመክር ፣ ኤልያስ ዝናብን እንደ ቧንቧ ውኃ ሲከፍትና ሲዘጋ ፣ ቁራ አስተናጋጅ ሲሆን ፣ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ሲሳፈር ፣ ዮናስ በአሳ አንበሪ ሆድ ውስጥ ሲጸልይ ፣ የኤልሳዕ አጥንት ሙት ሲያስነሳ ፣ የኤልያስ ልብስ ባሕር ሲከፍል ፣ የሙሴ በትር እባብ ሲሆን ፣ ጌታ በምራቁ ዓይን ሲፈጥር ፣ የአራት ቀን ሬሳ በስም ተጠርቶ ሲወጣ ፣ የጴጥሮስ ጥላ ሲፈውስ ፣ የጳውሎስ ጨርቅ ሙት ሲያስነሣ ተጽፎ ታገኛለህ፡፡ ይሄንን ሁሉ እግዚአብሔር ሁሉን ማድረግ ይችላል ብለህ በእምነት ካልተቀበልከው በስተቀር እንዴት ታደርገዋለህ?
ሔዋን ከእባብ ጋር ተነጋገረች የሚለውን አምነህ አቡነ አረጋዊ በእባብ ተራራ ወጡ ሲባል ከቀለድህ ፣ ኤልያስን ቁራ መገበው ሲባል ተቀብለህ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቁራውን መገቡት ሲባል ከዘበትህ ፣ ዳንኤል ከአንበሶች ጋር አደረ ሲባል አምነህ አቡዬ አንበሶች ጋር ነበሩ ሲባል ካጣጣልክ መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ ያለቀበት ቀን ለአንተ የዓለም ፍጻሜ መስሎሃል ማለት ነው::
አንድ አባት 'ዮናስን አሣ አንበሪ ዋጠው የሚለውን ታሪክ እንዴት ማመን ይቻላል?' ተብለው ሲጠየቁ 'የምናወራው ስለ እግዚአብሔር ከሆነ እንኳንስ ዓሣ አንበሪው ዮናስን ዋጠው ተብሎ ይቅርና ዮናስ ዓሣ አንበሪውን ዋጠው ቢባልም አምናለሁ' ብለዋል፡፡ 'አይ ይኼ እኮ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጻፈ ነው' ካልከኝ እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ ሲጠናቀቅ ሥራ አቁሞአል ማለት ነው? 'እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ከእናንተ ጋር ነኝ' ሲል አብረን አልሰማነውም? (ማቴ. 28፡19)

ኃጥእ በደለኛ ነህን? ተስፋ አትቁረጥ! ወደ ቤተክርስቲያን መጥተህም ንስሓ ግባ፡፡ ኃጢአት ሠርተሃልን? እግዚአብሔርን “በድያለሁ” በለው፡፡ “በድያለሁ” ብለህ ለመናዘዝ የሚጠይቅህ ድካምና ጥረት እንደ ምን ያለ ነው? “በድያለሁ [ይቅር በለኝ]” ለማለት የሚጠይቅህ ዓይነት የሕይወት መንገድ ወይም እንደ ምን ያለ መከራ ነው? “በድያለሁ” ብሎ አንዲት ቃል ለመናገር ክብደቱ ምኑ ላይ ነው? ምናልባት ኃጥእ ነኝ ብለህ ራስህን ባትጠራ፥ ዲያብሎስ በዚህ እንደማይነቅፍህ አስበህ ነውን?
በፍጹም! እንዲያውም ንስሓ ባትገባ ይህን ከዲያብሎስ የሚመጣ ነቀፋ እንደሚኖር ጠብቅ፡፡ የከሳሽ ግብሩ ንስሓ እንዳትገባ መከልከል በዚያ ንስሓ ባልገባህበት በደልም አንተን መውቀስ ነውና ንስሓ ባትገባ ይህን ጠብቅ፡፡ ስለዚህ ለቅጽበት ያህልስ እንኳን የማይተኛ ከሳሽ እንዳለህ ዐውቀህ ለምን እንዳይወቅስህ አትከለክለውም? ለምን በደልህን ተናዝዘሃት አታስወግዳትም?
ኃጢአት ሠርተሃልን? ወደ ቤተ ክርስቲያን ና፡፡ “በድያለሁ” ብለህ ለእግዚአብሔር ንገረው፡፡ እኔ ከዚህ ውጪ ከአንተ የምፈልገው ሌላ ምንም ነገር የለኝም፡፡ መጽሐፍ ሲናገር፡- “ትከብር ዘንድ አንተ አስቀድመህ ኃጢአትህን ተናገር” ይላል (ኢሳ.43፡26)፡፡ ስለዚህ ኃጢአትህን ታስወግዳት ዘንድ ተናዘዛት፡፡ ይህን ለማድረግ ድካም ጥረት አይጠይቅህም፡፡ አንደበተ ርቱዕ መኾን አያሻህም፡፡ ገንዘብ መክፈል አያስፈልግህም፡፡ ወይም እነዚህን የመሰሉ ሌሎች ነገሮች አያስፈልጉህም። አስቀድመህ በደልህን በሰቂለ ሕሊና በነቂሐ ልቡና ኾነህ አስባትና አንዲት ቃል ተናገር፡- “በድያለሁ” ብለህ ተናዘዛት፡፡
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ "ንስሐና ምጽዋት" ገጽ 28 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)
በፍጹም! እንዲያውም ንስሓ ባትገባ ይህን ከዲያብሎስ የሚመጣ ነቀፋ እንደሚኖር ጠብቅ፡፡ የከሳሽ ግብሩ ንስሓ እንዳትገባ መከልከል በዚያ ንስሓ ባልገባህበት በደልም አንተን መውቀስ ነውና ንስሓ ባትገባ ይህን ጠብቅ፡፡ ስለዚህ ለቅጽበት ያህልስ እንኳን የማይተኛ ከሳሽ እንዳለህ ዐውቀህ ለምን እንዳይወቅስህ አትከለክለውም? ለምን በደልህን ተናዝዘሃት አታስወግዳትም?
ኃጢአት ሠርተሃልን? ወደ ቤተ ክርስቲያን ና፡፡ “በድያለሁ” ብለህ ለእግዚአብሔር ንገረው፡፡ እኔ ከዚህ ውጪ ከአንተ የምፈልገው ሌላ ምንም ነገር የለኝም፡፡ መጽሐፍ ሲናገር፡- “ትከብር ዘንድ አንተ አስቀድመህ ኃጢአትህን ተናገር” ይላል (ኢሳ.43፡26)፡፡ ስለዚህ ኃጢአትህን ታስወግዳት ዘንድ ተናዘዛት፡፡ ይህን ለማድረግ ድካም ጥረት አይጠይቅህም፡፡ አንደበተ ርቱዕ መኾን አያሻህም፡፡ ገንዘብ መክፈል አያስፈልግህም፡፡ ወይም እነዚህን የመሰሉ ሌሎች ነገሮች አያስፈልጉህም። አስቀድመህ በደልህን በሰቂለ ሕሊና በነቂሐ ልቡና ኾነህ አስባትና አንዲት ቃል ተናገር፡- “በድያለሁ” ብለህ ተናዘዛት፡፡
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ "ንስሐና ምጽዋት" ገጽ 28 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)
Telegram
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
በዚህ ቻናል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡
....ወዳጆቼ ሆይ በመጽሐፍ ቅዱስ «ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ…የሚያሳፍር ነገርም የስንፍና ንግግርም ወይም ዋዛ የማይገቡ ናቸውና።» (ኤፌ. 4፥29፣ ኤፌ. 5፥4) የሚል ቃል ስለ ተጻፈ እንዲህ ካሉ ከንቱ ንግግሮችና ተራ አባባሎች ራሳችንን እናርቅ፡ እንደዚህ ያሉትን አባባሎች እኛ አለማለት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሲሏቸው ብንሰማም ዝም እንዲሉ እንንገራቸው፡፡ በብርቱ እየተቃወምናቸውም አሳፋሪ አንደበታቸውን እንዲገቱ እናድርጋቸው፡፡
እስቲ ንገሩኝ! በመንገድ ዳር እያደባ የሚተላለፉ መንገደኞችን የሚጠባበቅ የቀማኞች አለቃ እየሰረቀ የሚያገኘውን ወርቅና ብር በዋሻና በጉድጓድ እየደበቀ፣ ብዛት ያላቸው ከብቶችን በሰዋራ ስፍራ እያጎረ፣ በዘረፈው ሀብት ብዙ ልብሶችንና ባሮችን ሲያፈራ ብታይ፤ እስቲ እባክህን ንገረኝ! ይህንን ስው ስላከማቸው ሀብት ስትል የታደለ ትለዋለህ ወይስ ከሚጠብቀው ቅጣት አንጻር ዕድለ ቢስ ትለዋለህ? በእርግጥም እጁ ተይዞ በሚፈርድበት ዳኛ ፊት አልቆመም፡፡ ወደ እስር ቤትም ቢሆን አልተወረወረም፡፡ ከሳሽ ስለሌለው ወይም ጉዳዩ በድምፅ ብልጫ እንዲወሰን ስላልቀረበ በአባካኝነት እየበላና እየጠጣ በታላቅ ድሎት ሐሴት ያደርጋል፡፡ እንዲህ ስላደረገ አሁን ስላሉትና ስለሚታዩት ንብረቶቹ የታደለ ነው ብለን አንጠራውም፤ ይልቁንም ስለሚጠብቁት መከራዎቹ መከረኛ ብለን እንጠራዋለን እንጂ።
ባለጸጋና ስስታም ስለሆኑት ሰዎችም በተመሳሳይ መልኩ ልትገነዘቡ ይገባችኋል፡፡ እነዚህም ሰዎች ልክ በመንገድ ላይ አድብተው አላፊ አግዳሚውን በሚዘርፉት ቀማኞች ይመሰላሉ፡፡ ቀማኞች የዘረፉትን በዋሻና በጉድጓድ ውስጥ ሲቀብሩ እነዚህ ደግሞ የሌሎችን ሀብት በቤታቸው ውስጥ ያኖራሉ፡፡ ይህ ስለሆነም ስላላቸው ነገር ዕድለኞች ብለን አንጥራቸው፡፡ ይልቁንም ስለሚመጣው አስፈሪ ችሎት፣ ሊቋቋሙት ስለማይችሉት ፍርድና ስለሚጠብቃቸው በውጪ ስላለው ጨለማ መከረኞች ስንል አንጥራቸው፡፡ በእርግጥ ቀማኞች አብዛኛውን ጊዜ ከሰዎች እጅ ያመልጣሉ፡፡ ይህንን ብናውቅም እንዲህ ያለው በበደል የተከማቸ ሀብት የሞላበትን ሕይወት እንዲያርቅልን ለእኛም ሆነ ለጠላቶቻችን እንጸልያለን፡፡ ማንም ከእርሱ ፍርድ የሚያመልጥ ስለሌለ ይህ ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ እንደዚህ አይደለም፡፡ በማጭበርበርና በስርቆት የሚኖሩ ሁሉ ልክ እንደዚህ ባለጸጋ ሰው ያንን ዘላለማዊና መጨረሻ የሌለው ቅጣት በራሳቸው ላይ እንደሚያመጡ እርግጥ ነው፡፡
ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ! እነዚህን ሁሉ ጕዳዮች በሕሊናችሁ ከያዛችሁ ባለጸጋውን ሳይሆን ድሀውን የታደለ ብለን እንጥራው፤ ደግሞም ክፉውን እንጂ ድሀውን መከረኛ ብለን አንጥራው:: «አሁን ያለውን ጊዜ መመልከት ሳይሆን የሚመጣውን ጊዜ መገንዘብ ያስፈልጋል» የሚለውን አባባል ለማጉላት ሶሎን (Solon) የሚባለው የግሪክ ህግ አዋቂ «ማንንም ሰው እስካልሞተ ድረስ ደስተኛ ብለህ አትጥራው፡፡» በማለት ተናግሯል፡፡
እያንዳንዱን ስው መመልከት ያለብን ውጪያዊው አለባበሱን ሳይሆን ውሳጣዊ አመለካከቱን ወይም አስተሳሰቡን ነው፡፡ ጽድቅን በመሥራት የሚገኘውን ደስታና ቅንነት እንከተል፡፡ ሀብታምም ሆንን ድሀ አልዓዛርን በጽናቱ እንምስለው:: ምክንያቱም ይህ ሰው የተፈተነው በአንድ ወይም በሁለት ወይም በሦስት መልካም ሥራዎቹ ብቻ ሳይሆን ብዛት ባላቸው የጽድቅ ሥራዎቹ ነው፡፡ ይህንንም ስል ድህነት በሽታና ረዳት ማጣት ዋና ዋናዎቹ ነበሩ። ወድቆ የከረመው መከራዎቹን ሁሉ ሊያቃልልለት በሚችል ሰው ቤት ደጃፍ ላይ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ አንዲት የመጽናኛ ቃል እንኳ አላገኘም፡፡ ያላዘነለትን ሰው በደስታ ሲቀማጠል አይቶታል:: በደስታ መቀማጠል ብቻ ሳይሆን መጥፎ ቀንና መከራ ሳያጋጥሙት በክፋት ውስጥ ሲኖርም ተመልክቶታል፡፡ ሌላ እርሱን የመሰለ ሰው አይቶ ካለመጽናናቱ በተጨማሪ ራሱን የሚያረጋጋበት ምንም ዓይነት የዳግም ትንሣኤ እውቀት አልነበረውም፡፡ ቀደም ሲል ከጠቀስኳቸው መከራዎች ሌላ ስለ ገጠመው ከባድ ሕይወት በአብዛኛው ሕዝብ መካከል ጥሩ ስም አልነበረውም፡፡ ለሁለት ወይም ለሦስት ቀናት ብቻ ሳይሆን ዕድሜውን ሙሉ እንዲህ ባለው ሁኔታ መኖሩን ሲመለከት ባለጸጋውን ግን የዚህ ተቃራኒ በሆነ ሕይወት ውስጥ ተመልክቶታል:: እኛ የዚህን ሰው የመከራውን እኩሌታ እንኳ ሳንሸከም እርሱ እነዚህን ሁሉ ክፉ ቀኖቹን በድፍረት ሲጋፈጥ እኛ ምን ዓይነት ይቅርታ ልናገኝ እንችላለን? እንደዚህ ያሉ ታላላቅ ክፉ ቀናትን የታገሠ ወይም የተቋቋመ ሰው ልታሳዩኝ ወይም ልትጠሩልኝ አትችሉም፡፡ በአልዓዛር ያለውን ታላቅ የመከራ መጠን በመመልከት ምንም ዓይነት መከራ ቢገጥመን በትዕግሥቱና በቻይነቱ በቂ መረጋጋትና መጽናናትን እንድናገኝ ክርስቶስ እርሱን በፊታችን አኖረልን፡፡ በዓለም ዙሪያ በክፉ ቀኖችም ሆነ በሌሎች መከራዎች ለተጠቁ ወደፊትም ብቸኛ መምህር ሆኖ ይቆማል። በደረሱበት መከራዎች ብዛትም ሁሉንም መብለጡ በሁሉም ይታይ ዘንድ ራሱን አቅርቧል፡፡
ለዚህ የሰው ልጆችን ለሚወደው ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ምስጋናን እናቅርብ፡፡ ከዚህም ጽሑፍ የሚረዳንን ነገር እንቅስም፡፡ በጉባኤያት፣ በቤታችን፤ በገበያ ቦታና በማንኛውም ሥፍራ ስለ አልዓዛር ያለመሰልቸት እንነጋገር፡፡ አሁን ካሉብን መከራዎች ያለ ሀዘን እንድናልፍና ወደፊት ሊመጡ ካላቸው መልካም ነገሮች ሁሉ እንድንሳተፍ ከዚህ ጥቅስ የሚገኘውን ሀብት ሁሉ በጥንቃቄ እንድንመረምር ይሁን፡፡
ለዚህም ከአባቱና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ክብርና ምስጋና ሁሉ ዛሬም ዘወትርም እስከ ዘላለሙ ድረስ ለእርሱ የሚሆን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጸጋና በፍቅሩ መንግስተ ሰማያትን ለመውረስ እንድንበቃ ያድርገን፤አሜን፡፡
(ሀብታምና ደሀ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደሰበከው -ገጽ 36-40 አያሌው ዘኢየሱስ እንደተረጎመው)

#መጋቢት_27
#መድኃኔዓለም (#ጥንተ_ስቅለት)
መጋቢት ሃያ ሰባት በዚችም ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ድኅነት በሥጋ ተሰቀለ። ፈጣሪዋ በዕንጨት መስቀል ላይ ተዘርግቶ ተሰቅሎ በአየችው ጊዜ ፀሐይ ጨለመች እርሱም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የነሣትን ለባዊት ነባቢት የሆነች ነፍሱን ከሥጋው ለያት ሐዋርያ ጴጥሮስ በሥጋ ምውት ሲሆን በመለኮት ሕያው ነው እንዳለ ነፍሱ ከመለኮት ሳትለይ ከሥጋ ተለየች በዚያ ጊዜ ሥጋ ከመለኮት ሳትለይ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ነበር። እንዲሁም ነፍስ ከመለኮት ጋራ አንድ ሁና እሥረኞች ነፍሳትን ትፈታቸው ዘንድ ወደሲኦል ወረደች።
መድኃኔዓለም ክርስቶስ ስለ ዓለም ሁሉ ድኅነት በሥጋ ተሰቅሏልና ሞቱን በአንክሮ እናዘክር ዘንድ የልቡናችን ዐይን ወደ ቀራንዮ እናንሳ! እነሆ ክፉዎች አይሁድ ሰይጣን ልባቸውን አስቶታልና እንደ ወረንጦና እንደ ወስፌ እንደመርፌም ያለ 300 እሾህ ያለው ስረወጽ አድርገው አክሊል ሠርተው ከፍላት አግብተው በጉጠት አንስተው ‹ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሥ ነህ ዘውድ ይገባሃል› ብለው በራሱ ላይ ደፉበት፡፡ ለአክሊለ ሦኩም 73 ስቁረት ነበረው፡፡ እራሳቸው እንደ መሮ፣ ወርዳቸው እንደ ሞረድ 4 ማዕዘን አሠርተው ቁመታቸውን ክንድ ከስንዝር፣ ስለታቸውን እንደ ወስፌ አድርገው 73 ችንካር ሠርተው በ73ቱ ስቁረት አግብተው በጌታችን በራሱ ላይ ቢመቱበት ሥጋ ለሥጋ ገብቶ መሐል ልቡን ወጋው፡፡ አክሊለ ሦኩን በራሱ ላይ አድርገው ሲያበቁ ከቤት ወደ አደባባይ እያመላለሱ ‹‹ንጉሥ ሆይ!...›› እያሉ ምራቃቸውን እየተፉበት ተዘባበቱበት፡፡ መስቀል አሸክመው ከሊቶስጥራ እስከ ቀራኒዮ ድረስ እያዳፉ ሲወስዱት 136 ጊዜ በምድር ላይ ጣሉት፡፡ ከኋላ ያሉት ‹‹ፍጠን›› እያሉ ገፍትረው ይጥሉታል፣ ከፊት ያሉት ደግሞ ‹‹ምን ያስቸኩልሃል?›› እያሉ መልሰው ገፍትረው ይጥሉታል፡፡ ከዚህ በኋላ ክፉዎች አይሁድ ቁመታቸውን ክንድ ከስንዝር ስለታቸው ደግሞ እንደ ወስፌ የሆኑ 5 ችንካሮችን ሠርተው ሳዶር በሚባለው ችንካር ቀኝ እጁን፣ በአላዶር ግራ እጁን፣ በዳናት ሁለት እግሮቹን፣ በአዴራ መሐል ልቡንና በሮዳስ ደረቱን ቸንክረው የአዳም ራስ ቅል ባለበት ቀራኒዮ አደባባይ ላይ ሰቅለውታል፡፡
ክፉዎች አይሁድ መድኃኔዓለም ክርስቶስን እንደያዙት የኋሊት አስረው አፍንጫውን 25 ጊዜ ቢመቱት ደሙ በመሬት ላይ እንደ ውኃ ፈሰሰ፡፡ ከጌቴሴማኒ እስከ ሐና ቤት ድረስ አስረው የፊተኞቹ ሲጎትቱት የኋለኞቹ እየለቀቁት የኋለኞቹም በተራቸው ሲጎትቱት የፊተኞቹ ይለቁታል፡፤ እንዲህ እያደረጉ 65 ጊዜ ከመሬት ጋር አጋጭተውታል፡፡ ሳውል በእግሩ ሲረግጠው ጌታችን ‹‹መመለስህ ላይቀር ለምን ትረግጠኛለህ?›› ቢለው ስለዚህ ንግግርህ ብሎ ሳውል 440 ጊዜ አስገረፈው፡፡
ክፉዎች አይሁድ መድኃኒታችንን በሁለት ግንዶች መካከል አድርገው 65 ጊዜ ከግንዱ ጋር አጋጩት፡፡ ቀያፋ በሚመረምረው ጊዜ ጌታችን ‹‹አምላነቴን አንተው ራስህ ተናገርኽ›› ቢለው አይሁድ በእጃቸው ሲመቱት እጃቸውን ቢያማቸው ድንጋይ ጨብጠው 120 ጊዜ ፊቱን ጸፉት፡፡ አይሁድ ወደ ጲላጦስ ዘንድ ሲወስዱት ‹‹ምናልባት ጲላጦስ ባይፈርድበት እንኳ እንዳይቆጨን›› ብለው 305 ጊዜ በሽመል ደብድበውታል፡፡ በአምላክነቱ ቻለው እንጂ የአንዱ ምት ብቻ በገደለው ነበር፡፡ በርባን የይሁዳ የሚስቱ ወንድም (አማቹ) ስለነበር እርሱ እንደፊታለትም ከዋጋው ከ30ው ብር ጋር አብሮ ተደራድሮበት ነበር፡፡
ሰይጣን ልባቸውን ለክፋት ያስጨከናቸው ክፉዎች አይሁድ በጲላጦስ አደባባይ የጌታችንን ፂሙን 80 ጊዜ ነጭተውታል፡፡ ጲላጦስ እንደ ሕጋቸው 41 ብቻ ገርፈው እንዲለቁት ቢያዝም ክፉዎች አይሁድ ግን ጌታችንን ሲገርፉት ‹‹አሠቃቂ ግርፋቱን አይተን ልባችን እንዳይራራ›› ብለው ሰንጠረዥ ገበጣ ሰርተው ሲጫወቱ አንዱ ተነስቶ እስከ 60 እና 70 ድረስ ይገርፍና ሲደክመው ‹‹ቆጠራችሁን?›› ብሎ ይጠይቃል፡፡ ‹‹አልቆጠርንም›› ሲሉት ከድካሙ የተነሣ ‹‹እኔው ልግረፍ እንደገና እኔው ልቁጠር›› ብሎ ትቶት ሲቀመጥ ሌላኛው ይነሣና እንደዛኛው ሁሉ በተራው 60 እና 70 ይገርፈዋል፡፡ ሁሉም እንዲህ እያሳሳቱ የራሳቸውን ሕግ እየተላለፉ አይሁድ ጌታችንን ሥጋው አልቆ አጥንቱ እንደበረዶ ነጭ ሆኖ እስኪታይ ድረስ 6666 ጊዜ ጽኑ ግርፋትን ገረፉት፡፡ በእነዚህ ሁሉ ግርፋቱ ወቅት 366 ጊዜ ሥጋው ተቆርሶ መሬት ላይ ወድቋል፡፡
የመድኃኔዓለም ወገኖች ሆይ! የጌታችን ሞቱ በፈቃዱ መሆኑንና የትዕግሥቱን ብዛት አይተን እናደንቅ ዘንድ ከመጻሕፍት ጠቅሰን እንነግራችኋለን፡፡ አይሁድ ጌታችን አብርሃም ሳይወለድ በፊት እርሱ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገን አምላክ መሆኑን ቢነግራቸው ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፡፡ እሱ ግን ጊዜው ገና ነበርና ተሰውሮአቸው በመካከላቸው አልፎ ሲሄድ በፍጹም አላዩትም ነበር፡፡ በቅዱስ ወንጌል ላይ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፡- ‹‹አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው። አይሁድም:- ገና አምሳ ዓመት ያልሆነህ አብርሃምን አይተሃልን? አሉት። ኢየሱስም:- እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው። ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ፡፡›› ዮሐ 8፡56-59፡፡
ዳግመኛም በዮሐንስ ወንጌል ላይ እንደተጻፈው አይሁድ መድኃኔዓለምን ሊይዙት የጦር መሣሪያቸውን ሰብስበው ወደ ጌቴሴማኒ በመጡ ጊዜ ‹‹ማንን ትፈለጋላችሁ?›› ቢላቸው ‹‹የናዝሬቱን ኢየሱስን እንፈልጋለን›› ሲሉት ‹‹እኔ ነኝ›› ቢላቸው ከአንደበቱ የወጣውን መለኮታዊ ቃል ብቻ መቋቋም አቅቷቸው መሬት ላይ ወድቀው ተዘርረዋል፡፡ ይህም ክስተት በተደጋጋሚ ተከስቷል፡፡ (ዮሐንስ ወንጌል ላይ ምዕራፍ 18 ከቁጥር አንድ ጀምሮ ይመለከቷል፡፡) እናም የጌታችን ሞቱ በፍጹም ፈቃዱ ባይሆን ኖሮ በጌቴሴማኒ ሊይዙት የመጡት ክፉዎች አይሁድን እንደመጀመሪያው ሁሉ በተሠወራቸው ነበር አሊያም ከአንደበቱ በሚወጣው አምላካዊ ቃሉ ብቻ ባጠፋቸው ነበር፡፡ በመጨረሻ ግን ጌታችን ወደዚህች ምድር የመጣበትን ዓላማ ይፈጽም ዘንድ እንዲገድሉት በፈቃዱ ራሱን አሳልፎ ቢሰጣቸው ያን ሁሉ እጅግ አሠቃቂ መከራ አደረሱበትና ለመስቀል ሞት አበቁት፡፡
ወዮ ለዚህ ለመድኃኒዓለም ፍጹም ትዕግስት አንክሮ ይገባል! ዓለምን በመዳፉ የያዘ አምላክ በአይሁድ እጅ እንደሌባ ተያዘ፡፡ ሠራዊተ መላእክት ለምሥጋና በፊቱ የሚቆሙለት መድኃኔዓለም እርሱ ሊፈረድበት በፍርድ አደባባይ ቆመ፡፡ በእስራት ያሉትን የሚፈታ እርሱ በብረት ችንካር ተቸነከረ፡፡ ሰማይን በከዋክብት ምድርም በአበባ ያስጌጠ እርሱ ግን የእሾህ አክሊል በራሱ ላይ ደፋ፡፡ ዓለሙን ሁሉ በቸርነቱ የሚመግብ እርሱ ተጠማሁ አለ፡፡ ወዮ የመድኃኔዓለም የማዳኑ ምሥጢር ምንኛ ድንቅ ነው!!! ለዚህ ባሕርይው አንክሮ ይገባል፡፡
በመድኃኔዓለም ክርስቶስ ሞት በአንድነት እናለቅስ ዘንድ ቅዱሳን ሁላችሁ ኑ! መድኃኒታችን ሙቷልና ፍጥረታት ሁሉ ያለቅሳሉ፤ መያዝንና መታሠርን የተቀበለ መድኃኒታችን ሙቷልና፡፡ ጥፊንና ግርፋትን የተቀበለ መድኃኒታችን ሞተ፡፡ መደብደብንና መመታትን የታገሰ መድኃኒታችን ሞተ፡፡ ሄኖክ እግዚአብሔር ‹‹በሴም ቤት ይደር›› ብሎ አብ ስለራሱ የተናገረለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ አብርሃም ቃልኪዳን የገባልህን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ይስሐቅ ከሰይፍ ቤዛ የሆነህን

የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ያዕቆብ በበረሃ የታገለህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኢዮብ በደመና የታየህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ሙሴ ስለ እርሱ ‹እንደእኔ ያለ ነቢይ ይነሣል› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዳዊት ‹‹እነሆ በኤፍራታ ሰማነው፣ በበረሃ ዛፍም አገኘነው›› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኤርሚያስ ‹‹የክቡሩን ዋጋ ሠላሳ ብር ተቀበሉ›› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡
ኢሳይያስ ‹‹ወልድ ሰው ለመሆን ተገለጠልን፣ ሕፃን ተወለደልን፣ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ›› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ሕዝቅኤል ‹‹አምላክ ወደ ተዘጋች ደጃፍ ገባ፣ ከተዘጋች በርም ወጣ›› ብለህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዳንኤል ነጭ ሐር ለብሶ ያየኸውን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኤልያስ ከሞት በፊት የሰወረህ በእሳት ፈረሶች ያሳረገህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ሕዝቅያስ የፀሐይ መግባቱን ያሳየህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ምናሴ ችንካሮችህን ከእግር ብረት የፈታ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኢዮስያስ ፋሲካውን ያደረግህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ አናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤል ከእሳት ምድጃ ያዳናች የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ኑ፡፡ አብያና ሲላ ፌንቶስ ከመወለዱ አስቀድሞ ያመናችሁበት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ኑ፡፡ የቀድሞ አባቶች ነቢያት ሁላችሁ ከፋራን ተራራና ከቴማን ይመጣል ያላችሁት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ኑ፡፡ አሞፅ በአድማስ ቅጥር ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዘካርያስ በተራራዎች መካከል ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዕዝራ በአርፋድ በረሃ ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡
ስምዖን በክንድህ የታቀፍከውን ሕፃን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዮሴፍ እንደ አንተ የተሸጠ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ጠራቢ ዮሴፍ በትከሻህ ያዘልከው በክንድህ የተሸከምከው ሕፃን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ ከሕፃንነትህ ጀምሮ በበረሃ ያለ እናት ያለ አባት ያሳደገህ መንገዱንም እንድትጠርግለት ያዘጋጀህና መለኮትን እንድታጠምቅ የመረጠህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡
ኢያቄምና ሐና ሆይ የልጃችሁን ልቅሶዋን የልቧንም መዘንጋት ታዩ ዘንድ ኑ፡፡ ከሔዋን እስከ ፋኑኤል ልጅ እስከ ሐና ያላችሁ ሁላችሁ ቅዱሳት ሴቶች የድንግልን ልቅሶዋን ታዩ ዘንድ ኑ፣ አንድ ልጇ ሙቷልና፡፡ የለመለመ የሥጋ ሞት ሕንፃ የተጀመረበት የአቤል ተከታዩ፣ ከጎኑ የፈሰሰው ደም ሔዋንን ከጥፋት ያዳናት የተገደለ መድኃኒታችን ነው፡፡ የናቡቴ ጓደኛው የተገፋው መድኃኒታችን ነው፡፡ አቤል ስለሚስቱ ሞተ፡፡ ናቡቴም ስለ ወይኑ ቦታ ሞተ፡፡ መድኃኒታችን ግን በቀኙ ያነጻት ዘንድ ስለቤተክርስቲያን ሞተ፡፡ ነፍሳችሁን ይወስዷታልና መውረዱንም አላወቁምና ስለ ወገኖቹ ኃጢአት እስከ ሞት ደረሰ ብሎ ስለ እርሱ የተናገረ አባቱን እንስማው፡፡ ሙሴም እርሱን ያውቁት ዘንድ አላሰቡትም፣ በሚመጣበት ቀንም አላወቁትም አለ፡፡ ዕዝራ በባሕር ጥልቅ ያለውን ማወቅ እንዳይችሉ ወልድንም ማወቅ እንዲሁ ሆነባቸው አለ፡፡ ጳውሎስም ብታውቁትስ ኖሮ የክብርን ጌታ እግዚአብሔርን ባልሰቀላችሁት ነበር አለ፡፡
በመሰደድ፣ ያለምንም በደልም በፍርድ አደባባይ በመቆም መከራ መስቀልን በመሸከም አብነት የሆናችሁ ሰማዕታት ሁላችሁ ኑ የመድኃኔዓለምን የሞቱን ዕለት አስባችሁ በጋራ አልቅሱለት፡፡ ሁሉ የእርሱ ከእርሱ ለእርሱ ተፈጥሮ ሳለ በምድር ላይ ምንም ሳይኖረው ራሱን እንኳን የሚያስጠጋበት ቤት ሳይኖረው አብነት የሆናችሁ ባሕታውያንና መነኮሳት ሁላችሁ ኑ በዛሬዋ ዕለት ስለሞተው አምላካችሁ መሪር ዕንባን አልቅሱለት፡፡ ሕግ ጠብቆ፣ ሥርዓት አክብሮ፣ ነዳያንን በመመገብና ያዘኑትን በማጽናናት 33 ዓመት በምድር ላይ ኖሮ አብነት የሆናችሁ እናንት በዓለም ሆናችሁ ሕግ ጠብቃችሁ፣ አሥራት በኩራቱን አውጥታችሁ፣ ድሆችን በመርዳት የምትኖሩ ክርስቲያኖች ሁላችሁ የመድኃኔዓለምን የሞቱን ዕለት ታስቡ ኑ፡፡
‹‹የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና›› ብሎ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደጻፈልን (1ኛ ጴጥ 2፡21) እርሱ ንጹሕ ባሕርይ ሲሆን ወደ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ ወደ ዮርዳኖስ በመሄድ ለተጠመቅን ለእኛ ለተነሣሕያን ለሁላችን አብነት የሆነን መድኃኒታችን ስለእኛ ሞቷልና ሞቱን እናስብ ዘንድ ኑ በቤቱ ተሰብስበን እናልቅስለት፡፡ መታሰያውንም እናድርግለት፡፡ ጌታችን ሞቶ ተቀብሮ ካረገ በኋላ ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለቅዱሳን አባቶቻችን ለእነ አቡነ መባዓ ጽዮን፣ ለእነ አቡነ ዘርዐ ቡሩክ እንደነገራቸው የሞቱን መታሰቢያ የሚያደርግ ኃጠአተኛ እንኳ ቢሆን ሲኦልን አያያትም፡፡ የመድኃኔዓለምን የሞቱን መታሰቢያ የሚያድርግ ቢኖር ሲኦል ራሷ አፍ አውጥታ ‹‹ይህችን ነፍስ ወደኔ አታምጡብኝ›› ብላ ትጮሃለች እንጂ ችላ አትቀበለውም፡፡
የጌታችን ወዳጆቹ ዮሴፍ ኒቆዲሞስ በድርብ በፍታና በመቶ ወቄት ሽቱ ገንዘው በሐዲስ መቃብር ሊቀብሩት ቢሉ ጌታችን ያን ጊዜ ዐይኑን ክፍቶ ‹‹በሰውነቴ መዋቲ ብሆን በመለኮቴ ሕያው ነኝ እንጂ ምነው እንደ እሩቅ ብእሲ ዝም ብላችሁ ትገንዙኛላችሁን?›› አላቸው፡፡ ይህን ጊዜም ዮሴፍ ኒቆዲሞስ በታላቅ ድንዳጤ ሆነው ‹‹አቤቱ ጌታችን ሆይ! እንግዲያስ ምን እያልን እንገንዝህ?›› አሉት፡፡ መድኃኒታችንም እንዲህ እያላችሁ ገንዙኝ አላቸው፡- ‹‹ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል ተሣሃለነ እግዚኦ፡፡ ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተጠምቀ በዮርዳኖስ ወተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል ተሣሃለነ እግዚኦ፡፡ ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተንሥአ እሙታን አመ ሣልስት ዕለት ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት ወነበረ በየማነ አቡሁ ዳግመ ይመጽእ በስብሐት ይኰንን ሕያዋነ ወሙታነ ተሣሃለነ እግዚኦ› እያላችሁ ገንዛችሁ ቅበሩኝ አላቸው፡፡›› ከዚህም በኋላ መድኃኒታችን ለወዳጆቹ ለ12ቱ ሐዋርያት፣ ለ72ቱ አርድእት፣ ለ36ቱ ቅዱሳት አንስት ‹‹እስከ ሦስት ቀን እነሣላችኋለሁ እዘኑ አልቅሱ፣ እህል ውኃ አትቅመሱ በሏቸው›› ብሎ ለዮሴፍና ለኒቆዲሞስ አክፍሎት አስተማራቸው፡፡
ዳግመኛም መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከዕርገቱ በኋላ ለቅዱሳን ሐዋርያት የሞቱን መታሰቢያ እንዲያደርጉ ነግሯቸዋልና፡፡ ሕማሙንና ሞቱንም እንዲዘክሩ አዟቸዋልና አሁንም ያንን ሁሉ የመድኃኔዓለምን ሞቱን ያላሰበና የሞቱን መታሰቢያ በዓል ያላከበረና እርሱንም የማይወደው ቢኖር ዕድል ፈንታው ጽዋ ተርታው ከአይሁድ ጋር ነው፡፡
የአምላካችንን የመድኃኔዓለምን ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ተባብረን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ከእርሱ ለመተባበር ያብቃን!
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መጋቢት እና #ከገድላት_አንደበት)