Telegram Web Link
Forwarded from Elohe pictures (Elohe pictures)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Elohe pictures (Elohe pictures)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Elohe pictures (Elohe pictures)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#የጌታ_ስቅለት_በአበው

"አደምን የፈጠሩ እጆቹ በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ የማይሞተው ሞተ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡" #ቅዳሴ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

“እጆቹን እግሮቹን በተቸነከረባቸው ችንካሮች መወጋቱንም እናምናለን፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ እኛን ለማዳን ኃጢአታችንንም ለማሥተሥረይ መከራ ተቀበለ እንዳለ፣ በባሕርዩ ሕማም የሌለበት ሲሆን በሥጋ የታመመ ነው፤ በእርሱ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ድነናል አለ፡፡ በተገረፈና በተቸነከረም ጊዜ በመከራው ሁሉ መለኮትን ሕማም ተሰማው የሚል ሰው ቢኖር የተለየ የተወገዘ ይሁን፡፡” #ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ሊቀ_ጳጳስ

‹‹የሚሠዋ በግ እርሱ ነው፤ የሚሠዋ ካህን እርሱ ነው፡፡ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም መሥዋዕት የሚቀበል እርሱ ነው፡፡ በፈቃዱ መከራን በሥጋው የተቀበለ መከራንም ሁሉ የታገሠ እርሱ ነው፡፡ እንደ በግ ሊሠዋ መጣ፤ በግ በሚሸልተው ሰው ፊት እንዳይናገር አልተናገረም፤ በአንደበቱ ሐሰት አልተገኘበትም፡፡›› #ጎርጎርዮስ_ዘኑሲስ

‹‹ታመመ ሞትን ከተቀበለበት ከሥጋ ጋር ተዋሕዶ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ለሥጋውያን ሞተ፤ ባሕርየ መለኮት ሥጋን ተዋሕዶ በማኅፀን ካደረ ጀምሮ ሥጋ ገንዘቡ እንደመሆኑ በሥጋ ይኸንን ሥርዐት ፈጸመ፡፡ ለማይመረመር ለመለኮቱ ባሕርይ እንደሚገባ ደግሞ እርሱ ኅብስት አበርክቶ ሁሉን ያጠግባል፤ አይራብም፤ አይጠማም፤ አይደክምም፤ አያንቀላፋም፤ አይታመምም፤ አይሞትም፤ ሕይወትን ለሁሉ ይሰጣል፡፡ ዳግመኛ በዛ በሲኦል ተገዝተው ያሉ ነፍሳትን ያድን ዘንድ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወረደ በመለኮቱም ሲኦልን በዘበዘ›› #ቅዱስ_ቄርሎስ_ዘእስክንድርያ
    
‹‹ሙሴም ሞትን ያጠፋ ዘንድ አልቻለም፤ እርሱንም ይዞ ገዛው እንጂ፤ ከእርሱም በኋላ የተነሡ ነቢያትንም ሁሉ ሞት ገዛቸው እንጂ፡፡ ክርስቶስ ግን በቸርነቱ ለሁሉ ሕይወትን ሰጠ››  #ቅዱስ_አቡሊዲስ_ዘሮም

‹‹ምትሐት ያይደለ በእውነት ተራበ፣ ተጠማ እንጂ፡፡ ዳግመኛም ከኃጥአን ከመጸብሐን ጋር በላ ጠጣ፤ ያቀረቡለትንም በላ፡፡ ራሱን አሳልፎ ለመስቀል ሰጠ፤ እጁን እግሩን ተቸነከረ፤ ጎኑን በጦር ተወጋ፤ ከእርሱም ቅዱስ ምሥጢር የተገለጠበት ደምና ውኃ ፈሰሰ /ወጣ/፡፡›› #ቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሳሪያ
"ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት፤ የህያውን አምላክ ልጅ አሠሩት፤ በቁጣ ጎተቱት፤ በፍቅር ተከተላቸው። በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤

ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፥ በመኳንንት የሚፈርደውንም በእርሱ ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የሾህ ዘውድ አቀዳጁት፤ ለኪሩቤል የገርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት፤ ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሰወሩለትን እርሱን ክፉ ባሪያ አሥሮ ፊቱን ጸፋው፤ የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ የሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡

ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው? ይህን ያህል ትእግስት እንደምን ያለ ትእግስት ነው? ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው? ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው? ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው በደል የሌለበትን እንደበደለኛ ሰቀሉት፡፡ ህይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋር ቆጠሩት፤ አዳምን የሠሩ እጆች በመስቀል ቀኖዎት ተቸነከሩ፤  ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ተቸነከሩ፡፡

ወዮ በአዳም ፊት የህይወት እስትንፋስን እፍ ያለ አፍ ከሃሞት ጋር የተቀላቀለ የኮመጠጠ መፃፃን ጠጣ፤... ወዮ የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምንስ አንደበት ነው? የፍቁሩ የጌታ ህማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል፤ ህሊናም ይመታል፤ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች፤ ሥጋም ይደክማል የማይሞተው ሞተ፤ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ፤ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ። የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡"

/ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/
#ኒቆዲሞስ
(የዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት)

ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ በነበረው በኒቆዲሞስ የተሰየመ ሰንበት ነው፡፡ የአይሁድ አለቆች አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን “ምልክት አሳየን” እያሉ ይፈታተኑት ነበር፡፡ ስለሞቱና ትንሣኤው በምሳሌ ቢነግራቸው አልገባቸውም፡፡ ሲያስተምር ብዙዎች ያምኑ ነበር፡፡ ለአይሁድ አለቆች ግን ጭንቅ ነበር፤ የታመሙ ሲፈወሱ ሕጋችን ተሻረ ይሉ ነበር፡፡ በዚህ ሁሉ ተአምራትና ትምህርት የአይሁድ አለቆች ክርስቶስን ለመክሰስ በሚፈልጉበት ወቅት ከአይሁድ አለቆች አንዱ ኒቆዲሞስ በቀን እንዳያደርገው አይሁድን ፈርቶ አንድም ጊዜ አላደርሰው ብሎ እንደ አይሁድ አለቆች ኢየሱስን መቃወሙን ትቶ በሌሊት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ሄደ፡፡ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በነፍስ የታመሙትን በቃሉ በሥጋ የታመሙትን በተአምራቱ ሲፈውስ፤ ኒቆዲሞስ ሰምቶና ተመልክቶ “መምህር ነኝ” ብሎ በመምህርነቱ ሳይኮራ አለቅነቱን መመኪያ ሳያደርግ፡፡ በልቦናው የተሳለውን እውነትን የመፈለግ ስሜት አንግቦ ጌታው መምህሩ ዘንድ በሌሊት ገሠገሠ ዮሐ.3÷1ደርሶም ምስክርነቱን እንዲህ ሲል መስጠት ጀመረ “መምህር ልታስተምር ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን፡፡ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርገውን ተአምራት ሊያደርግ የሚችል የለምና” ዮሐ.9÷24፣ የሐዋ.ሥራ 10÷38 በማለት መመስከር ሲጀምር ጎዶሎን የሚሞላ፡፡ አላዋቂነት በአዋቂነት የሚለውጥ፡፡ ከምድራዊ እውቀት ወደ ሰማያዊ ምስጢር የሚያሸጋግር አምላክ፡፡ “ዳግመኛ ያልተወለደ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማየት አይችልም” ዮሐ.3÷6 ,1ጴጥ.1÷23 በማለት የአይሁድ መምህር ለሆነው ኒቆዲሞስ ቢያስተምረው ስለዳግመኛ መወለድ ከመጽሐፍ ቢያገኘውም ምስጢሩ አልተገለጠለትምና “ሰው ከሸመገለ በኋላ ዳግመኛ መወለድ እንደምን ይቻላል? ዳግመኛ ይወለድ ዘንድ ወደ እናቱ ማኅፀን ተመልሶ መግባት ይችላልን?” በማለት ጥያቄ አቅርቧል፡፡

“እውነት እውነት እልሃለሁ ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደ ወደ እግዝአበሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡ ኤፌ.5÷26 ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፡፡ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነውና፡፡ በማለት አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቢያስረዳው ምስጢሩ ከአቅሙ በላይ የሆነበት ኒቆዲሞስ እንደምን ይቻላል? በማለት ጠይቋል፡፡ አበ ብዙኀን አብርሃም ከአምላኩ ሞገስን አግኝቶ፤ የሰዶምና ገሞራ ጥፋት እንዳይደርስ እያማለደ ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገር እንደ ነበረ፤ ኒቆዲሞስም አላዋቂነቱን አምኖ ያልገባውን ምስጢር አምላኩን የመጠየቅ ዕድል በማግኘቱ ሲጠይቅ፣ ኢየሱስ ክርስቶስም “አንተ የእስራኤል መምህራቸው ነህ ግን ይህን ነገር አታውቅምን? በምድር ያለውን ስንነግራቸው ካላመናችሁ በሰማይ ያለውን ብንነግራችሁ እንደምን ታምናላችሁ? ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፡፡ ሙሴ ምድረ በዳ እባቡን እንደ ሰቀለ የሰው ልጅ እንዲሁ ይሰቀላል፡፡

ያመኑበት ሁሉ ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ እንዲኖር እንጂ እንዲጠፉ አይደለም…..” ዮሐ.3÷14፡፡ እያለ ለድኅነተ ዓለም እንደ መጣ ሰው በመብል፣ አምላኩን ከድቶ ልጅነቱን ትቶ ከእግዚአብሔር ቢለይም የሰው ልጅ ያጣውን ልጅነት ለመመለስ ስመ ግብርና ሀብተ ወልድን ለመስጠት መምጣቱን አስረዳው። “ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ፡፡ አመከርከኒ ወኢተረከ በዓመፃ በላዕሌየ፡፡ ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመሕያው፡፡ ልቤን ፈተንከው በሌሊትም ጎበኘኸኝ ፈተንከኝም ምንም አላገኘህብኝም፡፡ የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው” መዝ.16÷3 እንዳለ ቅዱስ ዳዊት ምስጢረ ሥጋዌን የድኅነት ምስጢር ገልጾለታል፡፡

በሌሊት ከአምላኩ ተምሮ ምስጢሩ የተገለጸለት ኒቆዲሞስ ፍርሃት ርቆለት ቀድሞ በአደባባይ ሄዶ መማርን የፈራ ምስጢሩ ሲገለጽለት አይሁድ በሰቀሉት ዕለት ሳይፈራ ከአርማትያሱ ዮሴፍ ጋር ቅዱስ ሥጋውን ገንዞ ለመቅበር በቃ “ወአልቦ ፍርሃት ውስተ ተፋቅሮትነ፡፡ ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል ማቴ.27÷58፣ 1ዮሐ.4÷18 እንዲል፡፡ ያመነ የተጠመቀ ይድናል፡፡ ያላመነ ያልተጠመቀ ይፈረድበታል ማር.16÷16፡፡ ባለው አማናዊ ቃል ኪዳን መሠረት አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አምላክነቱ አምነን ለመንግሥቱ ዜጋ እንድንሆን ለኒቆዲሞስ ምስጢሩን ጥበቡን የገለጸ አምላክ ለኛም ይግለጽልን፡፡

#የዕለቱ_የሰንበት_መዝሙር_እና_ግጻዌ

#መዝሙር
ሖረ ኀቤሁ ዘስሙ ኒቆዲሞስ ወይቤሎ ለኢየሱስ ረቢ ሊቅ ንሕነ ነአምን ብከ ከመ እምኃበ አብ መጻእከ ከመ ትኩን መምህረ፤ ዕጓለ አንበሳ ሰከብከ ወኖምከ አንሥአኒ በትንሣኤከ፡፡ (ስሙ ኒቆዲሞስ የተባለው ሰው ወደ ጌታችን ኢየሱስ ሄደ፤ መምህር ሆይ ልታስተምር ከእግዚአብሔር አብ ዘንድ እንደመጣህ እናምንብሃለን አለው። የአንበሳ ደቦል ተኛህ፣ አንቀላፋህም፤ በትንሣኤህ አንሣኝ።)

#መልዕክታት
ሮሜ 7÷1-12
"ወንድሞች ሆይ፥ ሕግን ለሚያውቁ እናገራለሁና ሰው ባለበት ዘመን ሁሉ ሕግ እንዲገዛው አታውቁምን? ያገባች ሴት ባልዋ በሕይወት ሲኖር ከእርሱ ጋር በሕግ ታስራለችና፤ ባልዋ ቢሞት ግን ስለ ባል ከሆነው ሕግ ተፈትታለች።...

1ኛ ዮሐ. 4 ÷18 - ፍጻሜ
ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም። .....

የሐዋ.ሥራ 5÷34 - ፍጻሜ
በሕዝብ ሁሉ ዘንድ የከበረ የሕግ መምህር ገማልያል የሚሉት አንድ ፈሪሳዊ በሸንጎ ተነሥቶ ሐዋርያትን ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጉአቸው አዘዘ......

#ምስባክ
መዝ.16፥3
ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ፡፡
አመከርከኒ ወኢተረክበ ዓመፃ በላዕሌየ፡፡
ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመ ሕያው፡፡
ትርጉም፦
በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤ ልቤንም ፈተንኸው÷
ፈተንኸኝ÷ ዐመፅም አልተገኘብኝም፡፡
የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር

#ወንጌል
ዮሐንስ 3፥1-12
"ከፈሪሳውያንም ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ። መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ
የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን አለው።....

ይቆየን
መጋቢት_29_በኩረ_በዓላት

ይህች ቀን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልዩ ናት።

በዚህ ዕለት፦
#ጥንተ_ፍጥረት ነው፦ በዚህች ቀን እግዚአብሔር ፍጥረታትን መፍጠር ጀመረ። "....ሰማይና ምድርን ፈጠረ።" ዘፍ. 1፥1)
#በዓለ_ጽንሰት (#በዓለ_ትስብእት) ነው፦ (ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በብሥራተ ቅዱስ ገብርኤል  በቅድስት ድንግል ማርያም ማኅፀን ተጸነሰ።) ሉቃ. 1፥26
#ጥንተ_ትንሳኤ ነው (የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበት ነው) ማቴ. 28፥1
#ዳግም_ምጽአት በዚህች ዕለት ነው፦ (በዚህች ዕለት ጌታችን ዳግመኛ ለፍርድ በዚህች ቀን ይመጣል።) ማቴ. 24፥1

በእነዚህ በዓላት ምክንያት ዕለቱ "ርዕሰ በዓላት፣ በኩረ በዓላት" ይባላል።
ለምንድን ነው የምንጾመው?

እንደ አንድ ክርስቲያን [በግልም በአዋጅም] በመደበኛነት እንድንጾም ታዝዘናል፡፡ ኾኖም እስኪ ጥያቄ እናንሣ! ለምንድን ነው የምንጾመው? በመራባችን ምክንያት እግዚአብሔር ደስ ይሰኛልን? በየቀኑ እግዚአብሔርን ለማገልገል በቂ ነው የሚባል ምግብ ልናገኝ እንደሚገባን የታ ወቀ የተረዳ ነው፡፡ ታዲያ በዚህ [በመጾማችን - በመራባችን] ውስጥ ያለው ምሥጢርና እግዚአብሔር ከዚያ ውስጥ የሚፈልግብን ፍሬ ምንድን ነው?

በልብ መታሰቡ፣ በቃል መነገሩ፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም መዘከሩ ይክበር ይመስገንና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመጾ ማቸው ምክንያት የሚገበዙትን እጅግ ወቅሷቸዋል፡፡ ጾም የሚያስታብይ አይደለም ሲላቸው ነው፡፡

ስለዚህ እግዚአብሔር እንድንጾም የሚፈልገው ስለ ኹለት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው፡-

አንደኛው፥ ራሳችንን ከዚህ ዓለም ነገሮች - ከእነርሱ ዋናውም ከምግብ - አርቀን ወደ መንፈሳዊ ነገሮች እንድናቀርብ ስለሚፈልግ ነው፡፡ በየጊዜው በየሰዓቱ ስንበላ ሥጋችን ተድላ ደስታ ያደርጋልና፡፡ በመሠረቱ ምግብ በልቶ ደስ መሰኘት በራሱ ነውር ኾኖ አይደለም፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር የአማናዊ ተድላና ደስታ ምንጩ መንፈሳዊ ተግባር እንደ ኾነ እናስብ ዘንድ ይሻል፡፡ ስለዚህ እንድንጾም የሚፈልገ ውና በዚያውም ውስጥ እንድናስተውለው የሚፈልገው የመጀመሪያው ምክንያት ይኸው ነው፡፡

ኹለተኛው ምክንያት ደግሞ ማጣት ዘወትር እንዲራቡ ከሚያደርጋቸ ው ሰዎች ጋር አንድነትና ኅብረት እንዲኖረን ስለሚሻ ነው፡፡ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ተከትለን በየጊዜው ልንጾም እንችላለን፡፡ ይህ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አስገድዶአቸው ሳይኾን እጦት አስገድዶአቸው ያለማቋ ረጥ ዘወትር የሚጾሙ ሰዎች ግን አሉ፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ለእነዚህ ሰዎች እውነተኛ ፍቅር እንድናሳይ ይፈልጋል፡፡ አጥቶ የመራብ ትር ጕሙ ምን ማለት እንደ ኾነ እኛው ራሳችን በተግባር እንድናይ ይሻል፡፡ በጾማችን ውስጥ እንድናፈራው የሚፈልገው አንዱ ፍሬ ይኼ ነው፡፡ ጾም የፍቅረ ቢጽ እናት ነች የምንለውም ለዚህ ነው፡፡

ስለዚህ ጾማችን እግዚአብሔር የሚፈልገውና የሚቀበለው እንዲኾንልን በጾማችን ወቅት ወጪአችንን መቆጠብ ሳይኾን እነዚህን ድኾች እንድ ናስብ ያስፈልጋል፡፡

(አምስቱ የንስሐ መንገዶች፣ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ገጽ 71-72)
በጎ እንደራሴዎች

ያለህን ለሌሎች አካፍላቸው፤ እንዲህ ካላደረግህ ታጣዋለህና፡፡ ያንተ የኾነው ያንተ እንደ ኾነ ይቆይ ዘንድ፥ ለነዳያን ስጣቸው፡፡ ይወሰድብሃልና ያንተ በኾነው ነገር፥ በገንዘብህ ላይ የሙጥኝ ብለህ አትጣበቅ፡፡ እንዳይበሰብስና ዋጋ ቢስ እንዳይኾንብህ ሀብትህን አታከማች፡፡ ከየትኛውም ዓይነት ስርቆት ወይም ጥፋት ይጠበቅልሃልና ብዕልህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፡፡

እነዚህ ትእዛዛት ምን ማለት እንደ ኾኑ ታስተውላለህን? ወይስ ከዚሁ በተቃራኒ እርባና ቢስ እንደ ኾኑ ታስባለህን? እምነት ለሌለው ሰው እነዚህ ነገሮች ምንም ትርጉም የላቸውም፡፡ እምነት ላለው ሰው ግን ጥልቅ ትርጉም ይሰጡታል፡፡ የምንደገፍባቸው ቁሳውያን ነገሮች የሚሰጠን እግዚአብሔር እንደ ኾነ የሚነግረን እምነት ብቻ ነውና፡፡

እግዚአብሔር ለአንዳንዶቹ ከሚያስፈልጋቸው በላይ ሀብት ይሰጣቸዋል። የሚሰጣቸው ግን እንዲቀማጠሉበት አይደለም፡፡ ወላጅ የሌላቸውን ሕፃናት፣ ሕመምተኞችንና አካል ጉዳተኞችን ይረዱበት ዘንድ የእግዚአ ብሔር እንደ ራሴዎች ናቸው እንጂ፡፡ ክፉ እንደራሴዎች ኾነው ሀብቱን ለራሳቸው ካስቀሩት ግን በነፍሳቸው ድኾች ይኾናሉ፣ ልባቸውም ኀዘን የተሞላ ይኾናል፡፡ በጎ እንደ ራሴዎች የኾኑ እንደ ኾነ ግን በነፍሳቸው ባለጸጎች ይኾናሉ፤ ልባቸውም ሐሴት የተሞላ ይኾናል፡፡

(አምስቱ የንስሐ መንገዶች፣ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ገጽ 183)
ጸጋ ክብርን የተመላሽ ቅድስት ድንግል ሆይ በጸሎትሽ ረዳትነት አምኜ ሳለሁ የማቸነፍ ጥሩር እንድለብስ የመለኮትንም ሰይፍ እንድታጠቅ አውቃለሁ፡፡

እርስ በርሳቸውም ይረዳዳሉ፡፡ የኔ ሃይማኖት ያንቺ ጸሎት የልዑል እግዚአብሔር ማዳን ዳግመኛም የኔ መታመን ያንቺ ልመና የልዑል አግዚአብሔር ይቅርታ እርስ በርሳቸው ይረዳዳሉ፡፡ እኔ ባንቺ አምኜ ሳለሁ ግዳጄን የማግኘቴ ተስፋ አንቺ ስለኔ ተግተሽ መለመንሽ እግዚአብሔርም ቸል ሳይልና ሳይነቅፍ ግዳጄን መስጠቱ እርስ በርሳቸው ይረዳዳሉ፡፡

እኔ በስምሽ እለምናለሁ አንቺም ስለኔ ትማልጃለሽ፡፡ ልጅሽም ስላንቺ የልመናዬን ዋጋ ይሰጠኛል እኔ ለፍቅርሽ ካልተጋሁ አንቺ እኔን ለማዳን አትተጊም፡፡ ልጅሽም እኔን ይቅር ለማለት አይተጋም፡፡

እኔ በስምሽ ግዳጄን ሁሉ ማግኘት እመኛለሁ፡፡ አንቺ ለኔ አማላጅ ነሽ፡፡ ልጅሽም ግዳጄን የሚሰጠኝ ነው፡፡ እኔ የተጸማሁ ነኝ፡፡ አንቺ የወርቅ መጥለቂያ ነሽ፡፡ ልጅሽም የሕይወት ውሃ አዘቅት ነው፡፡

የመለኮትን ዕንቁ ለመግዛት እኔ ነጋዴ ነኝ፡፡ አንቺ የሕይወት መርከብ ነሽ፡፡ ልጅሽም የበጎ ነገር ሁሉ ድልብ በውስጡ ያለበት የትርፍ ሥፍራ ነው፡፡

እኔ ገደሉን ለማለፍ ወደ ብርሃን ሥፍራ ለመድረስ የቸኮልሁ ነኝ፡፡ አንቺ የመድኃኒት ድልድይ ነሽ፡፡ ልጅሽም ለተገፉት መጠጊያ የተድላ ደስታ ሥፍራ ነው፡፡

እኔ የመንፈስ ቅዱስን ሀብት የምፈልግ ድሀ ነኝ፡፡ አንቺ የክብር ሁሉ መከማቻ ነሽ፡፡ ልጅሽም ለባለሟልነትና ለክብር ለማሞገስ የሽልማት ጌጽ ነው፡፡

እኔ እለምናለሁ አንቺ ጸሎቴን ታሳርጊያለሽ ልጅሽም ኃጢአቴን ያስተሠርያል፡፡ የልቤን ግዳጅ ይሰጠኛል፡፡ እኔ ቁስለኛ ነኝ አንቺ የመድኃኒት ሙዳይ ነሽ፡፡ ልጅሽም ባለ መድኃኒት ነው፡፡

እኔ ቁስለ ኃጢአቴ የሸተተ፡፡ የቅዱሳንንም መዓዛ ሽቱ የምሻ ነኝ፡፡ አንቺ ያማረ የተወደደ ሽቱ ብልቃጥ ነሽ፡፡ ልጅሽም ከሽቱ ሁሉ ይልቅ ያማረ የተወደደ የመለኮት ቅቤ ነው፡፡

እኔ የታረዝሁ የብርሃን ልብስ የምሻ ነኝ፡፡ አንቺ የሸማኔ ዕቃ ነሽ፡፡ ልጅሽም የማያልቅ የማያረጅ የሃይማኖት ልብስ ነው፡፡

በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ የተመረጥሽ ድንግል እመቤቴ ማርያም ሆይ! ሁልጊዜ በዓይነ ልቡናዬ አይሻለሁ በሃሳቤም በየሥፍራው ሁሉ አገኝሻለሁ በተኛሁ ጊዜ እኔን ለመጠበቅ የነቃሽ ነሽ፡፡ ከመኝታዬም ስነቃ እኔን ለማንሣት የተዘጋጀሽ ነሽ፡፡

ስቀመጥም እኔን ለመምከር ትደርሻለሽ፡፡ በቆምሁም ጊዜ በቀኜ ትቆሚያለሽ በተናገርሁም ጊዜ አንደበቴን ለማጣፈጥ ታከናውኛለሽ፡፡ በዝምታዬም ጊዜ ለመጠበቄ ማሞገሻ ነሽ ኃሴትም ባደረግሁ ጊዜ ተድላ ደስታ ነሽ፡፡

ባዘንሁም በተቆረቆርሁ ጊዜ የኃዘኔ መጽናኛ ነሽ፡፡ ባለቀስሁም ጊዜ የልቅሶዬ መተዊያ ነሽ፡፡ በዘመርሁ ጊዜ ለእጄ እንደ መሰንቆ ለጣቶቼም እንደ በገና ነሽ፡፡

በተራብሁም ጊዜ ለሆዴ ትመግቢኛለሽ በተጸማሁም ጊዜ እኔን ለማርካት የሕይወት ውሃን የተመላሽ ነሽ፡፡ የተፍገምገምሁም ጊዜ እኔን ለመደገፍ እጅሽን ትዘረጊያለሽ፡፡ በወደቅሁም ጊዜ እጅሽን ዘርግተሽ ታነሺኛለሽ፡፡

ተባሕትዎም በያዝሁ ጊዜ እኔን ለመጎብኘት አታቋርጭም፡፡ በማኅበር መካከል ወደኔ ትደርሻለሽ በደከምሁም ጊዜ ድካሜን ታበረቻለሽ፡፡ በታመምሁም ጊዜ ሥጋዬን ከሞት ታድኛለሽ፡፡ በተቸገርሁም ጊዜ ከችግሬ ታድኝኛለሽ፡፡

በተጨነቅሁም ጊዜ ጭንቄን ታርቂያለሽ፡፡ በቆሰልሁም ጊዜ ቁስሌን ታጠጊያለሽ፡፡ በርኩሰቴም ጊዜ ንጹሕ ታደርጊኛለሽ፡፡ በበደልሁም ጊዜ ኃጢአቴን ታቃልያለሽ፡፡ በደኸየሁም ጊዜ ለድህነቴ ባለጸግነት ሀብቴ ነሽ፡፡

(#አርጋኖን #በአባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ)
Forwarded from Elohe pictures (Elohe pictures)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Elohe pictures (Elohe pictures)
ELOHE PICTURE

በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው


መዝ118:26

🅲🅻🅸🅲🅺 🅷🅴🆁🅴
ይህን ይጫኑት

♡ ㅤ  ⎙ㅤ    ⌲        ✉️    Lᶦᵏᵉ   ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
ቶሎ ቶሎ እንድንለቅ ሪያክሽን እንዳይረሳ ❤️
     ➪ ꌗꃅꍏꋪꍟ ꌩꂦꀎꋪ ꎇꋪꀤꍟꈤꀸ

🔻🔻ይቀላቀሉን 🔗🔗
https://www.tg-me.com/+Ci5F1FcleWtlZThk
Forwarded from Elohe pictures (Elohe pictures)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
"አንተ ራስህ ለገዛ ወንድምህ ጨካኝና ይቅር የማትል ኾነህ ሳለስ እግዚአብሔር እንዲራራልህና እንዲምርህ እንዴት መለመን ይቻልሃል?

"ባልንጀራህ ምናልባት ንቆህ ሊኾን ይችላል፡፡ አዎ! አንተ ግን እግዚአብሔርን ኹልጊዜ እንደናቅኸው ነው፡፡ በባልንጀራና በእግዚአብሔር መካከልስ ምን ንጽጽር አለ? ባልንጀራህ ምናልባት ጉዳት ሲደርስበት ሰድቦህ ይኾናል፤ አንተም በዚህ ተበሳጭተህ ይኾናል፡፡ አንተ ግን ምንም ሳይጎዳህና በአንተ ላይ ክፉ ሳያስብ ይልቁንም ዕለት ዕለት በረከቱን እየተቀበልክ እያለ እግዚአብሔርን ሰድበኸዋል፡፡ እንግዲህ ተመልከት! ነቢዩ፡- “እመሰ ኃጢአተኑ ትትዐቀብ እግዚኦ መኑ ይቀውም - አቤቱ ኃጢአትንስ ብትጠባበቅ ማን ይቆማል?” ብሎ እንደ ተናገረ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የምንፈጽመውን በደል ቢመረምር ኖሮ አንዲት ቀንስ እንኳን በሕይወት መቆየት አንችልም ነበር (መዝ.129፡3)፡፡

እያንዳንዱ በደለኛ ሰው ለራሱ የሚያውቀውንና ሌላ ሰው የማይመሰክርበትን እግዚአብሔር ብቻዉን ግን የሚያውቀውንስ ይቅርና የተገለጠውና ሰው ኹሉ የሚያውቀው ኃጢአታችንን እንኳን እግዚአብሔር ቢቈጣጠር ኖሮ ከእነዚህ ኃጢአቶች በኋላ የምንጠብቀው ምንድን ነው? እግዚአብሔር ንዝህላልነታችንንና ጸሎት ስናደርስ የምናሳየው ግድየለሽነታችንን፣ ሠራተኞች ለአሠሪዎቻቸው ወታደሮችም ለአለቆቻቸው ጓደኛሞች ለጓደኞቻቸው የሚያሳዩትን ፍርሐትና ክብር ያህልስ እንኳን ለጸሎትና ለልመና በፊቱ በቆምን ጊዜ አለማሳየታችንን ቢቈጣጠር ኖሮ ምን ነበር የምንኾነው?

አንተ ከጓደኛህ ጋር ስትነጋገር ለምታደርገው ማንኛውም ነገር ትጠነቀቃለህ፡፡ ስለ በደሎችህ እግዚአብሔርን ስትጠብቀው፣ ለብዙ መተላለፎችህ ይቅርታን ስትጠይቀው፣ ሥርየትን ለማግኘት ስታሳስበው ግን [በፊቱ ላይ] ኹልጊዜ ግድየለሽ ትኾናለህ፡፡ ጉልበትህ በምድር ላይ ተንበርክኮ ሳለ ልቡናህ ግን እዚህም እዚያም፣ በገበያ ሥፍራም፣ በቤት ውስጥም ይዋልላል፤ ከንፈርህ በከንቱና እንዲሁ ያነበንባል፤ ይህን የምንፈጽመው ደግሞ አንዴ ወይም ኹለቴ ሳይኾን ኹልጊዜ ነው።

እንግዲህ እግዚአብሔር ይህን ብቻ እንኳን ቢመረምር ይቅርታን ወይም ምሕረትን እንደምናገኝ ታስባለህን? በእውነት አይመስለኝም!"

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ትምህርት በእንተ ምክንያተ ሐውልታት መጽሐፍ)
የሰሙነ ሕማማት ሰኞ

መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው


ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግሥቱም ከቢታኒያ ሲመጡ ተራበ፡፡ (ማር.11፤11-12) ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት። በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባር ናት፤ ከእስራኤል ፍቅርን፤ ሃይማኖትን፤ ምግባርን ፈለገ አላገኘም፤ እስራኤል (ሕዝበ እግዚአብሔር) መባልን እንጂ፤ ደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፤ በመርገሙ ምክንያት እርሱ ከለያቸው በስተቀር ደግ ሰው ጠፋባት፡፡

በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና፤ ፍሬ በአንቺ አይሁን አላት፤ ደኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡

በለስ ኃጢአት ናት፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ደስ ያሰኛል፤ ኋላ ግን ያሳዝናል፤ ወደ እርሷም ሄዶ ማለትም ከኃጥአን ጋር ዋለ፤ ኃጥእ ከመባል በቀር በአንደበቱ ሐሰት፤ በሰውነቱ ክፋት እንዳልተገኘበት ለማመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፤ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፤ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፤ ስትረገም ፈጥና መድረቋም፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ ካሣነት እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡

አንጽሆተ ቤተ መቅደስ የተፈጸመበት ዕለት ነው

ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ቤተ መቅደስ፣ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፤ ገርፎም አስወጣቸው፤ ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡

በዚህ በሰሙነ ሕማማት ካህናትና ምእመናን በቤተክርስቲያን ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስኪል ድረስ በነግህ፤ በሠለስተ፣ በስድስቱ ሰዓት፤ በተሰዓቱ ሰዓትና በሠርክ መላልሰው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ፤ በተለይም ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፤ ምክንያቱም የደረሰብን መከራ ኀዘኑን እና 5ሺ ከ5መቶ ዘመን የሰው ልጅ በጨለማ ይኖር እንደነበረ ለማዘከር ነው፡፡
በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ  የውጭ ቃላት አሉ ቀጥታ ሳይተረጓሙ ከዕብራይስጥ፣ቅብጥ፤ግሪክ ቃላት ይገኛሉ።

ኪርዬ ኤሌይሶን/ኪርያላይሶን/

ኪርዬ ማለት እግዚኦ ሲሆን ኪርያ ሲሆን ግን እግዝእትነ ይሆናል ኪርያላይሶን የምንለው በተለምዶ ነው እንጂ መባል ያለበት ኪርዬ ኤሌይሶን ነው ትርጉሙም አቤቱ ማረን ማለት ነው።

እብኖዲ ማለት አምላክ ማለት ነው።

ናይናን ማለት ማረን ይቅር በለን ማለት ነው።

ታኦስ የግሪክ ቃል ሲሆን ጌታ አምላክ ማለት ነው።

ማስያስ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ መሲሕ ማለት ነው 

ትስቡጣ ማለት ዴስፖታ ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ደግ ገዥ ማለት ነው።

ኢየሱስ ማለት መድኃኒት ማለት ነው።

ክርስቶስ ማለት መሲሕ ማለት ነው።

አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ማለት ነው።

በሰሙነ ሕማማት የሚባሉ ቀለሞች እንደ ሌላው ጊዜ ወጥ ከግዕዝ የመጡ አይደሉም ይልቁንሙ ከዕብራይስጥ ፣ ከሮማይስጥ ፣ ከግሪክ የተውጣጡ ናቸው።

ቅዱስ ያሬድ ይህንን ያደረገበት ምስጢር ጲላጦስ ጌታን ካሰቀለ በኋላ ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሠ አይሁድ የሚለውን ቃል በእነዚህ ቋንቋዎች ጽፎ በትራፈ መስቀሉ ላይ ጠርቆት ነበርና ያንን ለማስታወስ ነው።

                                    
ከማግሥተ ሆሣዕና በኃላ ዕለተ ረቡዕ

ሰሞነ ህማማት

እለተ ረቡዕ
በቅዱስ ማቴዎስና በቅዱስ ማርቆስ ወንጌላት እንደ ተገለጸው በዕለተ ረቡዕ የሚከተሉት ሦስት ተግባራት ተፈጽመዋል፤

አንደኛ የካህናት አለቆች፣ የሕዝብ ሽማግሌዎችና ጸሐፍት ፈሪሳውያን በጌታችን ላይ ተማክረዋል፤
ሁለተኛ ጌታችን በስምዖን ዘለምጽ ቤት ሳለ አንዲት የተጸጸተች ሴት ሽቱ ቀብታዋለች፡፡
ሦስተኛ ከዳተኛው ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ለመስጠት ከጸሐፍት ፈሪሳውያንና ከካህናት አለቆች ዘንድ ሠላሳ ብር ለመቀበል ተስማምቷል፡፡
የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሹማምት በጌታችን ላይ ይሙት በቃ ለመወሰን የሰበሰቡት ሸንጐ ‹‹ሲኒሃ ድርየም›› ይባላል፡፡ በዚህ ሸንጐ ላይ በአብዛኛው የተሰየሙት ሰዱቃውያን ሲኾኑ ሌሎቹ ደግሞ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ነበሩ፡፡ ሸንጐው በአጠቃላይ ሰባ ሁለት አባላት
የነበሩት ሲኾን የሚመራውም በሊቀ ካህናቱ በቀያፋ ነበር፡፡ በዕለቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት እንደሚገድሉት አይሁድ በዚህ ሸንጎ መክረዋል፡፡ ከዳተኛው ይሁዳም ጸሐፍት ፈሪሳውያንና የካህናት አለቆች በጌታን ላይ የነበራቸውን ጥላቻ ያውቅ ስለ ነበር ‹‹ምን ልትሰጡኝ ትወዳላችሁ? እኔም አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤›› በማለት ጌታችን አሳልፎ ሊሰጣቸው እንደሚችል ተስማምቷል፡፡

ጌታችን ያስተምር በነበረበት ወቅት የአስቆሮቱ ይሁዳ ከምእመናን ለሚገባው ገንዘብ ሰብሳቢ (ዐቃቤ ንዋይ) ነበር፡፡ ከሚሰበሰበው ሙዳየ ምጽዋት ለግል ጥቅሙ እየቀረጠ የማስቀረት የእጅ አመል ነበረበት፡፡ ይሁዳ ፍቅረ ንዋይ እንደሚያጠቃው ድብቅ አመሉ ጎልቶ የወጣው ጌታችን በለምጻሙ በስምዖን ቤት ሳለ አንዲት ሴት ዋጋው ውድ የኾነ ሽቱ በቀባችው ጊዜ ነው፡፡ በዚያች ዕለት ይሁዳ የተቃውሞ ድምፅ ካሰሙት አንዱ ነበር፡፡ ‹‹ይህ ሽቱ ተሽጦ ለድሆች ቢሰጥ መልካም ነበር፤›› በማለት ያቀረበው አሳብ ‹‹አዛኝ ቅቤ አንጓች›› እንደሚባለው ነበር፡፡ ይሁዳ፣ ሽቱ ሲሸጥ የሚያገኘው ጥቅም ነበረ፤ ሽቶው በጌታችን እግር ሥር ከፈሰሰ ለእርሱ የሚተርፈው የለም፡፡ ተቆርቋሪ መስሎ ያቀረበው አሳብ ተቀባይነት በማጣቱም በቀጥታ ከካህናት አለቆች ዘንድ ሔዶ ጌታንን በሠላሳ ብር ለመሸጥ ተዋዋለ (ማቴ. ፳፮፥፫-፲፮፤ ማር. ፲፬፥፩-፲፩፤ ሉቃ. ፳፪፥፩፮)፡፡

የአስቆሮቱ ይሁዳ እንደ ሌሎች ሐዋርያት ከጌታችን ተምሯል፡፡ በረከተ ኅብስቱን ተመግቧል፡፡ ልዩ ልዩ ተአምራት በጌታችን እጅ ሲደረጉ ዅሉ ተመልክቷል፡፡ ጌታችንም ከሌሎች ሐዋርያት ሳይለየው እግሩን አጥቦታል፡፡ ከዳተኛው ይሁዳ ግን ለሐዋርያነት የጠራውን፣ ተንበርክኮ እግሩን ያጠበውን ጌታ ለሞት አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ ‹‹የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሔዳል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት!›› ተብሎ እንደ ተጻፈ (ማቴ. ፳፮፥፳፬)፡፡ ሌሎች ሐዋርያት ከጌታችን ዘንድ ፍቅሩን ገንዘብ ሲያደርጉ ይሁዳ ግን እርግማንን ነው ያተረፈው፡፡ ‹‹ገንዘብ የኃጢአት ሥር ነው፤›› ተብሎ አንደ ተነገረ የኃጢአት ሥር የተባለው ገንዘብ የክርስቲያኖችን ሕይወት ያዳክማልና ምእመናን እንደ ይሁዳ በገንዘብ ፍቅር እንዳንወድቅ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ሰው ‹‹ይህን ዓለም ቢያተርፍ ነፍሱን ከጐዳ ምን ይጠቅመዋል?›› ተብሎ የተነገረውን ቃል ልብ ማለት ጠቃሚ ነው፡፡

ክርስቲያን ነን በማለት የክርስትናውን ስም በመያዝ እምነታቸውን፣ የቆሙበትን ዓላማ በመገንዘብ የሚለውጡ ሰዎች ዛሬም እንደ ይሁዳ ጌታችንን እየሸጡት እንደ ኾነ ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ ለድሆች መመጽወት ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው፡፡ ዳሩ ግን በድሆች ስም የሰውን ገንዘብ ለግል ጥቅም ማዋል እጅግ የከፋ ኃጢአት ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ለገንዘብ ብለው ድሆችን ለረኃብ ለችግር ባልንጀራቸውን ለመከራ እና ለሞት አሳልፈው ሲሰጡ ምንም አይጸጽታቸውም፡፡ እውነተኛ ክርስቲያኖች ግን ሕይወታችንን ለገንዘብ ፍቅር ሳይኾን ለእምነታችንና ለባልንጀራችን አሳልፈን መስጠት ይኖርብናል፡፡ በፍቅረ ንዋይ ተጠምደን ሰዎችን አሳልፎ በመስጠት ለአይሁዳዊ ሸንጐ ምቹ ኾነን መገኘት እንደሌለብን መገንዘብ አለብን
2025/06/29 03:57:27
Back to Top
HTML Embed Code: