የስማርት ስልክ ሱሰኛ መሆንዎን በቀላሉ እንዴት ማወቅ ይችላሉ?
በዚሁ አመት የተደረጉ ጥናቶችም የስማርት ስልኮች እና የተጠቃሚዎቻቸውን አስደንጋጭ አሃዛዊ ትስስር አሳይተዋል ስማርት ስልክዎ አጠገብዎ ከሌለ መተኛት ይከብድዎታል? የባትሪው መቀነስስ ጭንቀት ውስጥ ይከትዎታል? ስልክዎ ሳይጠራ የተደወለልዎ፥ መልዕክት ሳይላክልዎ መልዕክት መላኩን የሚያሳውቅ ድምጽ ሰምተው ስልክዎን ደጋግመው አይተዋል? መልስዎ አዎ ከሆነ የስማርት ስልክ ሱስ ተጠቂ ሳይሆኑ አልቀረምና ቆም ብለው ያስበቡብት።
ከተጠቃሚው ቁጥር መጨመር እኩል በስማርት ስልክ ሱስ ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ቁጥርም እያደረ እየጨመረ መሆኑን ፔው የተሰኘው የጥናት ተቋም ያወጣው የዳሰሳ ጥናት ያመለክታል።
በአሜሪካ 47 ከመቶ የስማርት ስልክ ተጠቃሚዎች ስልካቸውን የሙጥኝ ያስባለ ሱስ እንደያዛቸው ያምናሉ።
71 ከመቶው የሚሆኑ የጥናቱ ተሳታፊዎችም ከፍቅር ጓደኛቸው ጋር ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ለስልካቸው ጊዜ እንደሚሰጡ ነው የተናገሩት።
በጥናቱ ምላሽ ከሰጡት ህጻናት ውስጥም ሁለት ሶስተኛው በቀን ከ4 ስአታት በላይ በስልካቸው እንደሚያጠፉ ተመላክቷል።
ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ተሳታፊዎች ስልካቸውን ሳይዙ መንቀሳቃስ ከፍተኛ የመረበሽ ስሜትና ፍርሃት ውስጥ እንደሚከታቸው የተናገሩ ሲሆን፥ ስማርት ስልኮችን እየተጠቀሙ መንዳት ከሚደርሱ አደጋዎች 20 በመቶውን ይሸፍናል ተብሏል።
ቀጣዮቹ አስደንጋጭ ቁጥሮችም የስማርክ ስልክ ተጠቃሚዎች ችላ ብለው ካለፏቸው በያዙት ስልክ ሱስ ተጠልፈው መውደቃቸውን ያሳያል ይላሉ ባለሙያዎች።
ስማርት ስልኮች አሰራራቸው በራሱ ሱስ
ውስጥ የሚከት ነው የሚለው የአሜሪካ አዲክሽን ሴንተር ድረገጽ፥ የየእለት እንቅስቃሴያችን ከስልካችን ጋር የተያያዘ መሆኑን ያወሳል።
መዝናኛው፣ መረጃ መሰብሰቢያው፣ ክፍያ መፈጸሚያው፣ አቅጣጫ ጠቋሚው፣ አማካሪው ስማርት ስልክ አጠቃቀሙ ገደብ ካልተበጀለት ግን ጉዳቱ እያመዘነ መሄዱ አይቀርም።
ከመጠን ያለፈና በሱስ ደረጃ የተቀመጠ የስማርት ስልክ አጠቃቀም የሰነልቦና ባለሙያዎች ከአዳዲስ ስያሜዎች ጋር እንዲያስተዋውቁን አድርጓል። ከነዚህም ውስጥ “ኖሞፎቢያ” (ስልክ የሌለበትን ሁኔታ መፍራት)፣ ቴክስታፍሪኒያ (መልዕክት ሳይገባልን ግን የተላከልን መስሎን የማየት ልማድ) እና ፋንተም ቫይብሬሽን (ስልካችን በስህተት የነዘረን መስሎን አውጥተን የምናይበት) የተሰኙት ይገኙበታል።
እናም እነዚህ ምልክቶችን ደጋግማችሁ ከተመለከታችሁ በስማርት ስልካችሁ ሱስ ውስጥ ተዘፍቃችሁ ሊሆን ስለሚችል ባለሙያዎችን አማክሩ።
የድብርት፣ እንቅልፍ እጦት እና የስራ መጥላት ባህሪ እየተላመደ መሄድም ከማህበራዊ ህይወት ከመራቅ ጋር ተዳምሮ ራስን ወደማጥፋት ሊያመራ ይችላል፤ ጥናቶችም ይህንኑ አሳይተዋል የሚሉት የስነልቦና ባለሙያዎች ጉዳዩን እንደቀላል ነገር መመልከት እንደማይገባም ያሳስባሉ።
Via: Alain Amharic
@melkam_enaseb

#ገጽ26
የደረሰብን መከራ ባለንበት የሚያስቀረን፣ እኛ ላይ ብቻ እንደሆነ በመስበክ ነው። እኛ ብቻ ተለይተን ተጋላጮች እንደሆንን በመንገር ነው። በገጠመህ እክል ልብህ አዝኖ ጥግህን ይዘህ ቁጭ ብለህ ሳለህ በዚህ መንገድ እኮ የወደቅከው አንተ ብቻ ነህ ይልሃል።
ኩርምት ካልክበት ስፍራ ይቀርብህና ስማኝማ ይልሃል፡፡ እንደምንም ብሎ ቀልብህን እንደሳበም ጆሮህንም እንዳገኘ "ሰነፍ ነህ አትጠቅምም! ከመንገዱ ማብቂያም አትደርስም" ይልሃል። አንተም ተሽመድምደህ ባለህበት ተጣጥፈህ እስከቆየህለት ድረስ የነገረህ ሁሉ እውነት፣ አለምም ባንተ የውድቀት ዜና ዙሪያ ብቻ የምትዞር ይመስልሃል።
እውነት ነው እኮ! የወደቅ ቀን ሁሉም ጭልም ብሎ ነው የሚታይህ። ሰው ትፈራለህ፣ መዝናናትን ትፈራለህ፣ ህብረት ማድረግን ትሸሻለህ፣ ላንተ መፍትሄው ቤትህ ውስጥ መደበቅ ብቻ ይመስልሃል። ትንሽ እንኳ መስኮቴን ገርበብ አድርጌ አካባቢዬን ልይ ብትል እንኳ ዓይንህ ራሱ መርጦ የሚያይልህ ተሰብረው የቀሩትን ብቻ ነው፡፡ ጆሮህም ሳይቀር የሚሰማው ድምፅ የከሸፈ ጥይት፣ የከሸፈ ሰው ራዕይና ፅንስ ሲጨነግፍ የሚሰማውን ብቻ ነው።
በተዘጋ ክፍል ውስጥ መሆን አንድ ነገር ነው፡፡ እኔ ግን መውጫ በር እንኳ ከሌለው ጉድጓድ ውስጥ ገብቻለሁ ትላለህ።
ይህ ሁሉ ግን እመነኝ- እምቢ ብለህ ብድግ እስክትል ድረስ ብቻ ነው። ስትነሳ መንገዱን በሙሉ እየወደቁ የሚነሱ ተነስተውም የሚሮጡ ሞልተውት እንዳሉ ይታዩሃል። ወደኋላ የቀሩበትን መንገድ እንደቀስት ለመወንጨፍ የሚጠቀሙበትን ዘዴ ታስተውላለህ። ውድቀታቸውን በበጎ እይታ የሚመለከቱትንም ልብ ትላለህ።
ያኔ ማንም ያልወደቀበት ጉዞ ቢሆን እንኳ እኔን አይቶ ለመነሻ ይሆነዋል ትላለህ። የከበበህንም ጭጋግ ትበትናለህ ከአንገትህም ቀና ትላለህ።
(ዶ/ር በጸሎት ከበደ)
#Hakim

"አንድ ነገር ይሳካል ብለህ ስታምን አዕምሮህ ማሳካት የምትችልበትን መንገድ ይፈልጋል። በአንጻሩ ደግሞ እንደማይሳካ ስታምን አዕምሮህ ሊሳካ የማይችልባቸውን ምክንያቶች ይደረድርልሃል።"
(የሐሳብ ኃይል መጽሐፍ)
መልካም የሥራ ሳምንት!
@melkam_enaseb
(የሐሳብ ኃይል መጽሐፍ)
መልካም የሥራ ሳምንት!
@melkam_enaseb
ልጆቻችሁን በጥብቅ ተከታተሉ!
ለወላጆች. . .
የልጆቻችሁን ጥሩ መሆን፣ የፍቅር ልጆች መሆንና ታዛዥ መሆን በድብቅ ሊያደርጉትና ሊደረግባቸው ከሚችሉት ነገሮች ጋር በፍጹም አታምታቱ፡፡ በሌላ አገላለጽ ልጆቻችሁ ከላይ የተጠቀሱትንና መሰል መልካም ባህሪያት እየገለጹ ሳለ በስውር ግን አጥፊ ሁኔታ ውስጥ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የሚከተሉትን ሃሳቦች እንደመንደርደሪያ በመውሰድ አስቡበት፡፡
ልጆቻችሁ ላይ መልካምነትን፣ ፍቅርንና ታዛዥነትን እያያችሁ . . .
1. መጥፎ ልማድ ሊያዳብሩ ይችላሉ፡፡
የፖርኖግራፊ፣ የአደንዛዥ እጽና የመሳሰሉት ነገሮችን እየተለማመዱ ከእናንተ ጋር ግን እንደቀድሞው “በጨዋነት”፣ “በፍቅርና” እና “በታዛዠነት” ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ፣ ካለማቋረጥ የልጆችን ስልክ አጠቃቀም ተቆጣጠሩ፣ የባህሪይ ለውጥ ሲያሳዩ በሚገባ ተከታተሉ፣ ለብቻቸው መሆንን የመፈለግን ሁኔታ በቅርብ አጢኑ. . . ፡፡
2. በመጥፎ ጓደኛ ተጽእኖ ስር ሊወድቁ ይችላሉ፡፡
ቀስ በቀስ ባህሪያቸውን ለመጥፎ ከሚለውጡ ልጆች ጋር እያሳለፉ ከእናንተ ጋር ግን እንደቀድሞው “በጨዋነት”፣ “በፍቅርና” እና “በታዛዠነት” ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ፣ ጓደኞቻቸው ማን እንደሆኑ ለይታችሁ እወቁ፣ አዲስ ጓደኛን ሲይዙ እንዲያሳውቋችሁ አድርጉ፣ ከጓደኞቻቸው የሚመጡ ግፊቶችን እንዲያሳውቋችሁ መንገድን ጥረጉ፣ አውሯቸው. . . ፡፡
3. የተለያዩ ጥቃቶች ከሰዎች ሊደርስባቸውና ላይነግሯችሁ ይችላሉ፡፡
በትምህርት ቤት ጉልበተኛ የአካል ጥቃት፣ በዘመድና በቅርብ ሰው የወሲብ-ነክ ጥቃት፣ በአስተማሪና በሌላ “ባለስልጣን” የስነ-ልቦና ጥቃትና የመሳሰሉትን እያስተናገዱ ለእናንተ ሳይነግሯችሁ ከእናንተ ጋር ግን እንደቀድሞው “በጨዋነት”፣ “በፍቅርና” እና “በታዛዠነት” ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ፣ እቤት ከሰው ጋር ትታችሁ የምትወጡትን የልጆች ሁኔታ በሚገባ አስቡበት፣ ማንም ሰው ተገቢ ያልሆነ ቦታ ሲነኳቸውም ሆነ ተገቢ የልሆነ ሃሳብ ሲያቀርቡላቸው በግልጽ መንገር እንዳለባቸው አሳስቧቸው፡፡
በልጆቻችሁ ላይ የስነ-ልቦናም ሆነ የአካል ጥቃት አታድርሱ፡፡ መሰረታዊና አስፈላጊ ነገሮችንም በመከልከል አትጉዷቸው፡፡ ነገር ግን ተገቢ ያልሆነን ነገር እንዳያደርጉ በመከልከልና ተገቢውን ነገር እንዲያደርጉ በመጫን ብትጎዷቸው ጉዳቱ ጤናማና ለውጤት የሆነ ጉዳት እንደሆነ አስቡ፡፡
ትምህርት ቤት፣ ጓደኛም ሆነ ማሕበራዊ ሚዲያ በእነሱ ላይ ከሚያመጣው ተጽእኖ ይልቅ በበለጠ ሁኔታ እናንተ ተጽእኖን ማድረግ እንደሚገባችሁ አትዘንጉ፡፡ አለበለዚያ መቼ እንዳመለጧችሁ ሳታውቁ ታጧቸዋላችሁ፡፡
(በዶ/ር ኢዮብ ማሞ)

እንደዚህ ባሉ ስሜቶች ውስጥ እራስህን አግኝተኸው ታውቃለህ? መከፋት፣ ቁጡ መሆን፣ በቀላሉ መነጫነጭ፣ ረዳት የለሽ መሆን እና የተጣልክ አይነት ስሜት፣ ፍርሀት፣ የጥፋተኝነት ስሜት?
ድንዛዜ እና ነገሮች ትረጉም አልሰጥህ ያሉበት ደረጃ ደርሰሀል? ለሌሎች ራስህን ማስረዳት ተራራ እንደ መውጣት ስለሚከብድህ ብቻህን መሆን መርጠሀል?
ምን ጭንቀት እና ድባቴ ውስጥ እንዳስገባህ ስለማታውቅ ወይንም እንዲህ ለመሆን በቂ ምክንያት የለኝም ብለህ ራስህን ጥፋተኛ ታደርጋለህ? በእራስህ ላይ ትናደዳለህ?
የመንፈስ ጭንቀት ምን ያክል እንደሚከብድ ከአንተ ውጪ ማንም ሊረዳው አይችልም ኣ? "ይገባኛል" ቢሉም "አይ አይገባችሁም! ይህ ከእናንተ ደባሪ ቀናት ውስጥ እንደ አንዱ አይደለም። ከዚያም በላይ...
....ልክ እንደዚህ:- ደስታን ማግኘት አለመቻል፣ ለመኖር ጉጉት ማጣት እመኑኝ ጠዋት ከአልጋ መነሳት፣ ፊትን መታጠብ እስኪከብዳችሁ ድረስ ህይወት አታካች ትሆናለች። ፍላጎት፣ ተነሳሽነት ሚባሉ ነገሮች የሉም በቃ አለም ላይ ምንም የሚያስገርማችሁ ነገር አይኖርም። (አስቡት!) አሁንስ ተረዳችሁኝ?"
ሚገርመው ሠዎች ከዚህ የስሜት ጭንቀት እና ድባቴ እንዳትወጣ የሚያደርግህ ድክመትህ ነው ብለው ያስባሉ። "የምራችሁን ነው? ማለቴ መደበርን አልመረጥኩትም። ማንም የመንፈስ ጭንቀት ውሰጥ መግባትንም ሆነ መቆየትን አይመርጥም። በዘር፣ የእድገት ሁኔታ፣ የህይወት ውጣውረድ፣ ለአሰቃቂ አደጋ መጋለጥ ሌላም የአእምሮ ጭንቀትን ሊያመጣ ይችላል።"
No one is immuned for mental illness 💫
Explore your mentality ✨️
Fetlework Abate (Psychiatry nurse)
Via: Hakim

#አዲስጥናት
ሲጋራ ማጨስ በመካከለኛ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ አጫሾች ላይ የማስታወስ ችሎታቸውን እንደሚቀንስ እና ግራ መጋባት እንደሚያስከትል አዲስ ጥናት አመላክቷል።
ኮሎምበስ በሚገኘው የኦሃዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የተመራው ጥናት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር በJournal of Alzheimer's Disease የታተመው።
በጥናቱ የአጫሽ ሰዎች የማስታወስ ችሎታ ከማያጨሱ ሰዎች በ1.9 እጥፍ ገደማ ያነሰ እንደሆነ ተመራማሪዎቹ አረጋግጠዋል።
ከ10 ዓመት በፊት ሲጋራ ማጨስ ያቆሙ ሰዎች ከማያጨሱ ሰዎች 1.5 እጥፍ የማስታወስ ችሎታቸው ያነሰ መሆኑም በጥናቱ ተመላክቷል።
የጥናቱ ከፍተኛ ባለሞያ እና የኦሃዮ ዩኒቨርስቲ ኤፒዲሚዮሎጂ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ጄፍሪ ዊንግ ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች ከ45-59 ዕድሜ ክልል ውስጥ ማጨስ ቢያቆሙ የሚፈጠረውን የማስታወስ ችሎታ መቀነስ መጠን ማሳነስ ይቻላል ብለዋል፡፡
ሲጋራ ማጨስን እድሜ ከመግፋቱ በፊት ማቆም ለጤና የበለጠ ጥቅም እንደሚያስገኝም ጥናቱ መጠቆሙን ዩ.ፒ.አይ ድረገጽ አስነብቧል።

ለሌላው ኑር!
#ድባቴ ውስጥ ያለ ሰው እንዲህ ያስባል፡-
"በሄድኩበት ሁሉ ችግር ይገጥመኛል፣ ከዚህም ማምለጫ የለኝም፣ ወዴት እንደምጓዝ አላውቅም።"
ይህ ነው ሰዎች ራሳቸውን እንዲያጠፉ የሚገፋቸው። ተስፋን ይቆርጣሉ፣ ከዚህም የተሻለ ቀን እንደሚመጣ አያስቡም።
"በየትም አቅጣጫ ብዞር ማምለጫ የለኝም፣ ስቃዩን አልቻልኩትም፣ የማልረባ ነኝ ለማንም አልጠቅምም፤ ለሁሉም የሚሻለው እኔ ባልኖር ነው" ብለው ያስባሉ።
ለሌላው መኖር አንተ ምክንያት መሆን አለብህ፡፡ ለማንም አልጠቅምም የሚለውን ሰው የምታድነው አንተ ነህ፡፡ ለአንተ ጠቃሚ መሆኑን በማሳየት፣ ግራ ለገባው መንገድ በመሆን፣ ተስፋ ለቆረጠ ተስፋ በመስጠት ለሌላው መኖር ምክንያት መሆን አለብህ፡፡
ለአንተም… ምክንያት የሆንክለት እሱ አለ፡፡ ሁላችንም ተስፋን በመሰጣጠት፣ የተሻለ ቀን እንዳለ በማሳየት አንዳችን ለሌላችን መኖር አለብን፡፡
(የሕይወት ቀመሮች መጽሐፍ)
(12 RULES FOR LIFE)
መልካም ቀን!

የራስ-እንግድነት (depersonalization) and ከባቢ-እንግድነት (derealization)
የራስ-እንግድነት (depersonalization) ለራሳችን እና አካላችን የሚሰማን የሆነ ግራ የሚያጋባ፣ ሰመመን ውሰጥ ያለን የሚመስል፤ አውነት ያለመሆን ወይም የእንግድነት ስሜት ነው፡፡
ይህ ስሜት በዙሪያችን ስላለው ነገር ከሆነ ከባቢ-እንግድነት (derealization) እንለዋለን፡፡
✍ ጋሻው አወቀ (የስነ-አእምሮ ባለሙያ)
ያንብቡ: https://telegra.ph/የራስ-እንግድነት-depersonalization-and-ከባቢ-እንግድነት-derealization-12-29

Telegraph
የራስ-እንግድነት (depersonalization) and ከባቢ-እንግድነት (derealization)
ወይዘሪት ሰናይት የ27 ዓመት የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪ ናት፡፡ ጭንቀት ሊያስነሱ በሚችሉ አከባቢዎች ስትሆን በመቸገሯ ወደ ክሊኒክ መጣች፡፡ በቅርብ ጊዜ የተሰማትን ስታወራ “እያወራሁ ነበር ነገር ግን እኔ እንደማወራ ሆኖ አይሰማኝም። በጣም ግራ የሚያጋባ ነበር። ‘ማን ነው የሚያወራው?’ የሚል ስሜት ተሰማኝ፣ የሆነ ዝም ብዬ ተመልካች የሆንኩ ነገር ነው ሚሰማኝ- የሆነ ሌላ ሰው ሲያወራ እንደማየት አይነት።…
የድብርት/ድባቴ ህመም (Depressive disorders)
- ስርጭቱ ምን ይመስላል?
- ምክንያቶቹ ምንድናቸው?
- ስነ-ልቦናዊ ቀውሶቹ ምንድናቸው?
- ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ምንድናቸው?
- ምልክቶቹ ምንድናቸው?
- ህክምናው ምንድነው?
✍ ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው (የስነ-አእምሮ ሬዚደንት ሃኪም)
ዝርዝሩን ያንብቡ: https://telegra.ph/የድብርትድባቴ-ህመም-Depressive-disorders-12-30

የድብርት ህመም ሲባል በስሩ የተለያዩ አይነት ህመሞችን ያቀፈ ነው። እነዚህም - ከባድ የድብርት ህመም (Major depressive disorder) - ከ2 አመት በላይ የቆየ የድብርት ህመም (persistent depressive disorder) - በመድሃኒት (እንደ steroid) ምክንያት የሚመጡ - በእጾች (እንደ አልኮል) ምክንያት የሚመጡ - በሌላ ህመም ምክንያት የሚመጡ (የውስጥ ደዌዎች፣ እጢዎች፣…
ዳውን ሲንድሮም ምንድነው?
ዳውን ሲንድሮም Trisomy 21 ተብሎም ይጠራል።
ዳውን ሲንድሮም አንድ ሰው ከተጨማሪ 21ኛው ክሮሞዞም ጋር የሚወለድበት ሁኔታ ነው።
ክሮሞሶም በመቶዎች አልፎ ተርፎም በሺዎች የሚቆጠሩ ጂኖችን ይዘዋል። ጂኖች የእርስዎን ባህሪዎች (ከወላጆችዎ የተላለፉ ባህሪዎች) የሚወስን መረጃ ይይዛሉ፡፡
የዳውን ሲንድሮም መንስኤዎች፦
- የሰው ሴሎች በተለምዶ 23 ጥንድ ክሮሞዞም ይይዛሉ፡፡ በእያንዳንዱ ጥንድ ውስጥ አንዱ ክሮሞሶም ከአባት፣ ሁለተኛው ከእናት ነው፡፡
- ዳውን ሲንድሮም የሚከሰተው 21ኛውን ክሮሞዞም በተመለከተ ያልተለመደ የሕዋስ ክፍፍል ሲከሰት ነው፡፡
- እነዚህ የሕዋስ ክፍልፋዮች ያልተለመዱ ተጨማሪ ክፍሎች ወይም ሙሉ ክሮሞዞም 21 ያስከትላሉ፡፡ ይህ ተጨማሪ ክሮሞዞም ንጥር ለዳውን ሲንድሮም ሲንድሮም ባህርይ እና የእድገት ችግሮች ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡
- ሦስቱ የጄኔቲክ ወይም ዘር ልዩነቶች ዳውን ሲንድሮም መንስዔ ሊሆኑ ይችላል፦
1.Trisomy 21.
- ከ95 ከመቶው ያህል ዳውን ሲንድሮም የሚከሰተው በትሪሶሚ 21 ነው።
- ልጆች በሁሉም የሕዋሳት ክፍል ከተለመደው ሁለት ቅጂዎች ይልቅ ሶስት የክሮሞሶም 21 ቅጅዎች አሉት። ይህ የሆነው የወንድ የዘር ህዋስ ወይም የእንቁላል ህዋስ በሚፈጠርበት ጊዜ ባልተለመደ የሕዋስ ክፍል ነው።
2. የሙሴ ዳውን ሲንድሮም
(Mosaic Down syndrome)
- ከባድ ዳውን ሲንድሮም በሚባለው በዚህ ያልተለመደ ሁኔታ አንድ ሰው ክሮሞሶም 21 ተጨማሪ ቅጂ ያላቸው ሴሎች ብቻ ይኖሩታል።
- ይህ የመደበኛ እና ያልተለመዱ ሴሎች ሞዛይክ ከእርግዝና በኋላ በተለመደው ሴል ክፍፍል ምክንያት ነው።
3. ትራንስሎኬሽን ዳውን ሲንድሮም
- ዳውን ሲንድሮም እንዲሁ የክሮሞሶም 21 የተወሰነ ክፍል ወደ ሌላ ክሮሞሶም ይያያዛል ወይም ፅንስ በሚተላለፍበት ጊዜ ሊከሰት ይችላል፡፡
- እነዚህ ልጆች የተለመደው ሁለት ክሮሞሶም 21 ቅጂዎች አሏቸው፣ ግን ደግሞ ክሮሞዞም 21 ከሌላው ክሮሞሶም ጋር ከተያያዘ ተጨማሪ የዘረመል ይዘት አላቸው።
ዳውን ሲንድሮም የሚያስከትሉ የታወቁ ባህሪዎች ወይም አካባቢያዊ ምክንያቶች የሉም።
ምልክቶች፦
- ዳውን ሲንድሮም ያጋጠማቸው ሰዎች የእያንዳንዳቸው ሰዎች የአዕምሮ እና የእድገት ችግሮች መለስተኛ፣ መካከለኛ ወይም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
- አንዳንድ ሰዎች ጤናማ ናቸው ሌሎቹ ደግሞ እንደ ከባድ የልብ ጉድለት ያሉ የጤና ችግሮች አሉባቸው፡፡
- ዳውን ሲንድሮም ያለባቸው ልጆች እና ጎልማሶች የተለያዩ የፊት ገጽታዎች አሏቸው፡፡
- ዳውን ሲንድሮም ያለባቸው ሁሉም ሰዎች ተመሳሳይ ባህሪዎች ባይሆኑም፣ በጣም የተለመዱ ባህሪዎች የሚከተሉትን ያጠቃልላል፦
- ጠፍጣፋ ፊት
- ትንሽ ጭንቅላት
- አጭር አንገት
- ምላስን ያስወግዳል
- ወደ ላይ የሚያንፀባርቁ የዓይን ሽፋኖች (palpebral fissures)
- ያልተለመደ ቅርፅ ወይም ትንሽ ጆሮዎች
- ደካማ ጡንቻ
- ሰፊ፣ አጭር እጆች በአንድ መዳፍ ውስጥ
- በአንጻራዊ ሁኔታ አጫጭር ጣቶች እና ትናንሽ እጆች እና እግሮች
- ከልክ ያለፈ ተለዋዋጭነት
- ብሩሽፊልድስ ስፖትስ በሚባሉት የዓይን ክፍል በቀለማት ክፍል (አይሪስ) ላይ ትናንሽ ነጠብጣቦች
- አጭር ቁመትና የመሣሠሉት ናቸው።
በተጨማሪ፦
- የዳውን ሲንድሮም ምርመራ ልጅዎ ዳውን ሲንድሮም ካለበት ለይቶ ማወቅ ወይም መመርመር ይችላል።
- ዳውን ሲንድሮም ያለበት እያንዳንዱ ልጅ ልዩ ስለሆነ ሕክምናው በግለሰቦች ፍላጎት ላይ የተመሠረተ ነው።
- በልጅዎ ልዩ ፍላጎቶች ላይ በማተኮር የዳውን ሲንድሮም ህክምና የሚከተሉትን የተወሰኑ ባለሙያዎችን ሊያካትት ይችላል፦
- የሕፃናት የልብ ሐኪም
- የሕፃናት የጨጓራ ባለሙያ ሀኪም
- የሕፃናት ኢንዶክሪኖሎጂስት
- የሕፃናት እድገት ሐኪም
- የሕፃናት የነርቭ ሐኪም
- የሕፃናት ጆሮ, አፍንጫ እና ጉሮሮ (ENT) ስፔሻሊስት
- የሕፃናት የዓይን ሐኪም
- ኦዲዮሎጂስት
- የንግግርና ቋንቋ ፓቶሎጂስት
- የፊዚዮቴራፒስት
- የሙያ ቴራፒስት
በማሕሌት አዘነ
(Speech & Language Therapist)

ሊሞቱ የደረሱ ሰዎች የሚቆጫቸው 10 ነገሮች!
ዶ/ር ወዳጄነህ ማህረነ Dawit Dreams ላይ ከተናገረው የተወሰደ።
በተለያየ ህመም ምክኒያት በህይወት ጥቂት ጊዜ የቀራቸው ሰዎች ቀሪ ጊዜያቸውን ያለ ስቃይ እንዲያሳልፉ ህክምና የሚያገኙበት ቦታ Hospice ይባላል። ሆስፒስ ውስጥ የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች እነዚህን ከጥቂት ሳምንታት እስከ ጥቂት ወራት የቀራቸው ሰዎች በህይወታቸው ምን እንደሚቆጫቸው ጠይቀዋቸው የሚከተሉትን 10 ነጥቦች አግኝተዋል።
1) ደስተኛ አልነበርኩም- ህይወቴን በሚገባ enjoy አላደረግሁም።
2) በእውቀት ራሴን አላሳደግሁም። ለመማር ብዙ እድል ነበረኝ ግን አልተማርኩም።
3) እራሴን አልተንከባከብኩም- ጥሩ እንቅልፍ አልተኛሁም፤ ስፖርት አልሰራሁም፤ አመጋገቤ ላይ አልተጠነቀቅኩም፤ የጤና ምርመራ በሰአቱ አላደረግሁም።
4) የኖርኩት በቂምና በጥላቻ ነው- ሁሉም ነገር እንደዚህ ማለፉ ለማይቀር ለምን በቂምና በጥላቻ ራሴንም ሰዎችንም ጎዳሁ?
5) ለቤተሰቤ ጊዜ አልሰጠሁም- ላይ ታች ስል ከልጆቼ ጋር አልተጫወትኩም፤ ወላጆቼን እንደምወዳቸው አልነገርኳቸውም። አብሬያቸው ጊዜ አላሳለፍኩም።
6) ሰዎችን አልረዳሁም- ብዙ የእኔን እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎች ነበሩ። አቅሙ እያለኝ እኔ ግን 'ቢዚ' ስለነበርኩ አልደረስኩላቸውም።
7) ህልሜን አልኖርኩም- ለብዙ አመታት ለአንድ መስሪያቤት ተቀጥሬ ነው የሰራሁት እንጂ የራሴን ህልም አልኖርኩም።
8) ያለምክኒያት ነው የለፋሁት- በማይጠቅሙኝ ነገሮች ተጠምጄ በጣም ስለፋ ነበር።
9) ለሰዎች ፍቅሬን አልገለፅኩም- ለምወዳቸው ሰዎች 'እወድሀለሁ' ወይም 'እወድሻለሁ' አላልኩም። ፍቅሬን ከመግለፅ ይልቅ እኮሳተራለሁ።
10) ሀይማኖትን እንቅ ነበረ- መንፈሳዊነትን እጠላ ነበር። አሁን መጨረሻዬ ላይ እስከምደርስ ወደ አምላኬ ዞር አላልኩም ነበር።
ሞት መቼ እንደሚመጣ አይታወቅም። በየሰአቱ በአለማችን 7500 ሰዎች ይሞታሉ። በየቀኑ በአለም አቀፍ ደረጃ 180ሺ ሰዎች ይሞታሉ። ሞት ማን ጋር መቼ እንደሚመጣ አይታወቅም። ደስተኛ ሆነን፣ ህልማችንን እየኖርን፣ ራሳችንን እየተንከባከብን፣ ብዙም ኮስታራ ሳንሆን፣ ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር ጊዜ እያሳለፍን በይቅርታ ልብ እንዲሁም በመንፈሳዊነት መኖር ሞት ሲመጣ እዳንፀፀት የሚያግዙ ነጥቦች ይመስሉኛል።
Via ዶ/ር ዮናስ ላቀው

⬆️ ስጦታ የአእምሮ ጤና እንክብካቤ ማዕክል!
ስልክ: +251113692818/ +251113692774
🔗 https://sitotapsy.com
📥 [email protected]
@melkam_enaseb
ስልክ: +251113692818/ +251113692774
🔗 https://sitotapsy.com
📥 [email protected]
@melkam_enaseb
የማነብ ኃይል (The power of visualization)
አእምሯችን በገሃድ ዕውነታና በምናባችን ውስጥ በምንፈጥረው ዕውነታ መካከል ያለውን ልዩነት አይረዳም። ይህ ማለት አንድን ያልተፈጠረ ነገር ወይም በትውስታችን የነበረን ነገር በምናባችን ውስጥ ጥርት አድርገን ማየት ከቻልን አእምሯችን ያ ምናባዊ ዕውነት ገሃዳዊ ዕውነት እንደሆነ ያስባል።
ከዚህ የተነሳ በአእምሯችን በፈጠርነው ምናባዊ ምስል ምክንያት የሚሰሙን ስሜቶችና የምናሳያቸው ባህርያት ለዕውነተኛው ክስተት የምናሳየውን ዐይነት ይሆናሉ።
ስኬታማ ሰዎች እንዲህ ያለውን የማነብ ስልት አውቀውትም ሆነ ሳያውቁት በመጠቀም የሚፈልጉትን ውጤት ያሳካሉ።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የማይክል ፌልፕስ (Michael Phelps) የዋና አሰልጣኝ (ቦብ ቦውማን Bob Bowman) ውጤታማ የሚያደርግ የማነብ ስራ ለመስራት የመጀመሪያው ደረጃ ሰውነትን ፈፅሞ ማዝናናት (body relaxation) እንደሆነ ይናገራል።
ከዚያም ማይክል ወደፊት የሚፈልገውን የማሸነፍ ሂደትና ውጤት በአእምሮው ውስጥ በጣም ጥርት ባለና ዕውነት በሚመስል መልኩ በመመልከት በምናቡ ውስጥ እየደጋገመ ይለማመዳል።
ማይክል ይህን የማነብ ሂደት ከውድድር ቀን በፊት በየለቱ በመስራት አእምሮውን ብቻ ሳይሆን ሙሉ ማንነቱና ሰውነቱን ጥርጥር የሌለው ፍፁም የሆነ ማሸነፍ ስሜት ውስጥ ይዘፍቃል።
እንዲህ ያለ የማነብ ሂደት ለማይክል ፌልፕስ ከሃያ ስምንት በላይ የዋና ኦሎምፒክ ሜዳሊያዎችን እንዲያገኝና ሌሎች ብዙ እውቅናዎችን እንዲጎናፀፍ ረድቶታል።
ይህን በተፈጥሮ የተሰጠንን የማነብ ፀጋ እየተጠቀምንበት ነው ወይስ እሱ እየተጠቀመብን? (ልባም ሕይወት)

ስሜ ሃኒም ይባላል በሙያ ጤና መኮንን አና የመንግስት ሰራተኛ ስሆን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ማስተርስ እማራለው ... ነገር ግን ADHD (Attention Deficit Hyperactivity Disorder) የተባለ ችግር ተጠቂ ነኝ።
3 ጊዜ ባለሙያ ፊት ቀርቤ መዳኒት የታዘዘልኝ ቢሆንም መዳኒቱ አገር ውስጥ በጭራሽ የለም። ከውጪ ለማግኘት ብሞክርም ከአንድ አመት በላይ ባፈላልግም አላገኘውም። ከሁሉም በላይ ያሉኝ ህልሞች እንቅልፍ ይነሱኛል። ለሃገሬ ብዙ የመስራት ህልም እና ፍላጎት አለኝ... ነገር ግን በማይታይ ስውር ሰንሰለት ጥፍር አርጌ አንደታሰርኩ ይሰማኛል።
ወይ ሚታይ ነገር አይደል ነገር ሰው አይቶ አይደርስልኝ፣ ይረዱኛል ብዬ ያወራሁዋቸው ሰዎች ራሱ የባህሪ ችግር ስልሚመስላቸው በምክርና በወቀሳ ይመልሱልኛል። ለነገሩ እኔ ራሱ ህመም መሆኑን ማመን ይከብደኛል። ስለዚም ራስን መውቀስ እና ራስን ከሊሎች ጋር እያወዳደሩ መናደድ የቀን ልምዴ ነው።
በዚ የሩጫና የፉክክር አለም ታትሮ መስራትን እየፈለጉ በቀላሉ መስተካከል በሚችል ህመም መቸገር ያሳዝናል። ችግሬ ሳይታወቅልኝ በፈጣሪ እገዛ እዚ ብደርስም ከዚ በላይ በዙ የመስራት አቅም ነበርኝ። አሁን ግን ከብዶኛል!!!
የሚመለከታቸው አካላት መዳኒቱ ወደ ሀገር መግባት የሚችልበትን መንገድ ቢፈልጉ፣ እንዲሁም የግል መዳኒት አስመጪዎችም ቢያስገቡልን ትልቅ እርዳታ ነው።
በተጨማሪም መዳኒቱን ማግኘት ምትችሉ (ከሃገር ውጪ) ያላችው ሰዎች ብታግዙን። እዚው ያላችሁም ብታካፍሉን... ከምንም በላይ ደሞ ወላጆች እና መምህራን ልጆቻችሁን በደንብ እንድትከታተሉ እና የተለየ ባህሪ ካላቸው ወደ ባልሙያ በመውሰድ እንድታማክሩ በጊዜ የታወቀ ነገር መፍትሄው ይቀላልና አደራ እላለው።
ትላልቅ ሰዎችም ብኖን ስለጤናችን መከታትልና ሃኪም ማየት ብዙ የብቻ ትግልን ይቀንሳል ብዬ አስባለው። በመጨረሻም ለብቻችሁ በተለያየ ችግር ውስጥ ያላችው ሰዎች ደፍራችው እንድቶጡ እና እርዳታ ጠይቁ ..... ለመምህራን፣ ለስራ ባልደረባ፣ ለቤተሰብ፣ ለሃኪም መናገር ወሳኝ ነገር ነው ሰዎች ከምናስበው በላይ ደግ እና ሚረዱን ናቸው። አየዞን፣ በርታ፣ ትችያለሽ፣ ጎበዝ..... መባል ራሱ ትልቅ ተስፋ ነው። የህመም ነውር የለውም፣ መቀበል ደሞ ትልቁ መፍትሄ ነው!!!
ያለ አእምሮ ጤና፣ ጤና የለም!
#ADHD #WENEEDMEDS #STIMULANTS #MOH #EFDA #MENTALWELLNES #AWARENESS #Hakim

YETENA WEG CLUBHOUSE DISCUSSION!
Topic: EXERCISE & MENTAL HEALTH
LET'S DISCUSS THE EFFECT OF EXERCISE ON MENTAL HEALTH WITH EXPERTS ON SPORT SCIENCE AND MENTAL HEALTH.
Sunday, Jan 08 at 6:00pm - 8:00 (EAT)
ከምሽቱ 12:00 - 2:00 ሰዓት (በኢትዮጵያ)
Join with this link ⬇️
https://t.co/myOtm2CETO