Telegram Web Link
ማክሰኞን ከ11:00 ሰዓት ጀምሮ የት ለማሳለፍ አስበዋል?

የአርምሞ ማሰልጠኛ ማዕከል ዋና ስራ አስፈፃሚ፣ ሳይኮቴራፒስት፣ የ5 መጽሐፍት ደራሲ፣ ሃይፕኖቴራፒስት እንዲሁም የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ ማክሰኞ የካቲት 14 ቀን 2015 ዓ.ም ከ11፡00 ሰዓት ጀምሮ በዳዊት ድሪምስ መድረክ ላይ ድንቅ የሆነ የአዕምሮ ማዕድ ሊያጋራን ተዘጋጅቷል። 

ይህን ድንቅ የአዕምሮ ምግብ ለመታደም ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።

መግቢያ በነፃ  VIP REP 200birr

ለበለጠ መረጃ በ +251938252525 ይደውሉ።

@melkam_enaseb
በሐዋሳ እና በአከባቢዋ ለምትገኙ!

ዘፀአት የአዕምሮ ጤና ማማከር አገልግሎት በማንኛውም የአዕምሮ ጤና እክል እንዲሁም የሂዎት ተግዳሮቶች ሙያዊ የሆነ የማማከር እና ህክምና አገልግሎት ይሰጣሉ።

አድራሻ፦ ሐዋሳ ከቲቲሲ ወደ ሪፈራል በሚወስደው መንገድ ኮሜሳ ህንፃ አንደኛ ፎቅ ላይ።

ስልክ: 0943007007

@melkam_enaseb
ስሜታዊ ምክንያት (Emotional Reasoning)

በሳይኮሎጂ ሳይንስ አንዱ የትምህርት ዘርፍ ነገሮችን እንዴት እንደምንረዳና ወደ አእምሮ የሚገቡ መረጃዎች በአስተሳሰብ፣ በስሜትና በባህሪ የሚኖራቸውን ተፅእኖ መመልከት ነው።

የሰው ልጅ ጥሩ ስሜት እንዳይሰማውና ያልተገባ አስተሳሰብ እንዲያስብ ከዛም በዘለለ ተገቢ ያልሆነ ድርጊት እንዲያከናወን ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ በእውነታ ላይ ያለ ነገርን በተዛባ አመለካከት (አስተሳሰብ) መንገድ መረዳት ነው፤ misinterpretation of reality ብንለውም ይገልፀዋል። የሳይኮሎጂ ጠበብቶች Cognitive Distortion ይሉታል።

አንድ ሰው በተደጋጋሚ ነገሮች የሚረዳበት ሁኔታ የተንሸዋረረ ከሆነ፣ አጋኖ የሚመለከት፣ በአንድ እይታ ብቻ የሚያየው ከሆነ፣ ሌላ አማራጭ የለም አይነት አረዳድ ካለው ለተለያዩ የስነልቦና ችግሮች የመጋለጥ እድሉ ሰፊ ነው።

Cognitive Distortion በአይነቱ ብዙ ቢሆንም አንዱን እንኳን ብንጠቅስ Emotional Reasoning የሚል እናገኛለን። ስሜታችን በሚነግረን መልእክት እውነታውን ያላገናዘበ ድምዳሜ ላይ መድረስ ማለት ነው። እየተደረገ ያለውን ነባራዊ እውነታ ትተን የስሜት መርህ መከተል የሚል አንደምታ አለው። ይህ ማለት ማሰብ ትተን በስሜት መነዳት ማለት ነው።

ለምሳሌ፦ አንድ ሰው በውስጡ የቅናት ስሜት ስለተሰማው ብቻ ሚስቱ ከሌላ ወንድ ጋር ትማግጣለች ብሎ ድምዳሜ ላይ ሊደርስ ይችላል። እዚህ ላይ መገንዘብ ያለብን ሚስቱ ለትዳሯ ታማኝ እያለች ነው።

ስለዚህ በEmotional Reasoning እሳቤ መሠረት በነገሮች ላይ የሚኖረን አስተሳሰብ፣ እምነትና አቋም የሚወሰነው በምናስበው ምክንያታዊ አስተሳሰብ ሳይሆን እውነታውን ያላገናዘበ በሚሰማን ስሜት ነው።

#zepsychologist

@melkam_enaseb
ሱስ የሌለባችሁ ሰዎች እስቲ እጃችሁን አውጡ!

ብዙ ሰዎች ሱስ የሚጠቀሙ ሰዎችን እንደ ሰነፍ፣ ዱርዬ፣ የሞራል ውድቀት ውስጥ እንዳሉ አድርገው ሲፈርጁ ይታያል። ሱስ ውስጥ ያሉ ሰዎች ደግሞ ፍረጃውን በመፍራት ወይም ሀፍረት ስለሚሰማቸው ወደ አእምሮ ህክምና ለመምጣት ያንገራግራሉ። አንዳንዶቹ ሼም ስለሚይዛቸው "ከፈለግኩኝ እኮ ማቆም እችላለሁ።" ቢሉም ተመሳሳይ እሽክርክሪት ውስጥ ለአመታት ይቆያሉ። ሱስ ውስብስብ ስነ ልቦናዊ፣ አካላዊና ማህበራዊ ሂደት ነው። ማን ሱስ ውስጥ እንደሚገባ ማወቅ አይቻልም።

ዶ/ር ጋቦር ማቴ የሱስን ፍቺ ሲያስቀምጥ "ማንኛውም ለጊዜያዊ ደስታ ተብሎ የሚወሰድ (የሚደረግ) እና 'አምጣ፣ አምጣ' የሚል ወስዋስ (Craving) የሚፈጥር እና በዘለቄታው ግን በግለሰቡ ወይም በግለሰቡ ዙሪያ ባሉ ሰዎች ላይ ጉዳት የሚያስከትል ለመተው የሚያስቸግር ድርጊት ነው" ብሏል።

በዚህ ትርጓሜ መሰረት የተለያየ ሱስ አምጪ እፆች መጠቀም፣ ፖርኖግራፊ መመልከት፣ ማህበራዊ ሚዲያ ለብዙ ሰአት መጠቀም፣ ከሚገባ መጠን በላይ መመገብ፣ ቁማር መጫወት...ወዘተ ሁሉም በተመሳሳይነት ሱሶች ናቸው።

ሰዎችን "ሱሰኛ" ብሎ ከመፈረጅና ዝቅ አድርጎ ከመመልከት በፊት "ምንም አይነት ሱስ የለብኝም!" የምትሉ ሰዎች እስቲ እጃሁን አውጡ!

ሱሶች ሁሉ የሚያስከትሉት ጉዳት እኩል ነው እያልኩ አይደለም። ሆኖም ሁሉም ሱሶች ተመሳሳይ ሂደት እንዳላቸውና ማንም ሰው ላይ ሊከሰት እንደሚችል እንድንረዳ ነው። ከፍረጃ ይልቅ ርህራሄ፣ አናት ላይ ቆሞ ከመምከር ይልቅ አጠገብ ተቀምጦ ማገዝ ብንችል ብዙ ሰዎች ከሱስ እንዲወጡ ማገዝ እንችላለን።

ሱስ የሚታከም የአእምሮ ህመም ነው። ዘውዲቱ፣ ጳውሎስ ወይም አማኑኤል የሱስ ህክምና ይሰጣል። ጥሩ የግል ህክምና አማራጮችም አሉ።

(ዶ/ር ዮናስ ላቀው)

@melkam_enaseb
⬆️ Life Improvement Training!

13ኛ ዙር የሳይኮሎጂና የሕይወት ክህሎት ስልጠና በዚህ ሳምንት ይጀምራል!

ስልጠናው ላለፉት 4 አመታት ሲሰጥ የነበረና የብዙዎችን የሕይወት መንገድ ያገዘ ስልጠና #የመጨረሻዉ ዙር ነው፡፡

ለመመዝገብ እና ለበለጠ መረጃ በ 0912664084 ይደውሉ፡፡

@melkam_enaseb
#Dailytips

''ለአእምሮ ጤናህ መልካም የሆኑ እና ሰላም እንዲሰማህ ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ግዜህን አሳልፍ''

'ሁለት ነገሮች ብልህ ያደርጉናል። የምናነባቸው መፅሀፎች እና በህይወት መንገድ ላይ የሚገጥሙን ሰዎች።'

ለራስህ የምትነግራቸው ነገሮች ስነ ልቦናህን ይገነባሉ ወይም ይሰብራሉ። 

ትግል ዋጋ አለው። በህይወት ትግል ውስጥ የሚፈልጉትን ነገር ያገኛሉ። ካልታገሉ ለመማር እና ለማደግ ጠቃሚ እድሎች ያመልጦታል።

ሁኔታው ​​የቱንም ያህል መጥፎ ቢመስልም ያልፋል።

እራስዎን ጨምሮ ሌሎች ላይ መፍረድ በእጅጉ ይቀንሱ። መፍረድ ቀላሉ ነገር ነው። በሰው ጫማ ሆኖ ደግሞ ነገሮችን ማየት ከባዱ ነገር ስለሆነ።

ስራ በዝቶቦታል ማለት ውጤታማ ኖት ማለት አይደለም። ወደ ግቦችዎ የሚያንቀሳቅሱ ትክክለኛ ተግባራትን ማከናወን ነው የበለጠ አስፈላጊው ነገር።

''የሰው ልጅ ስለሚፈልጋቸው ነገሮች በራሱ አእምሮ መወሰን ካልቻለ ለሰዎች አላማ መዳረሻ ይሆናል። ህይወትህንና ፍላጎትህን ሌሎች ሰዎች እንዲሾፍሩት በጭራሽ አትፍቀድ።''

በመልካም ሀሳብ የምንሞላበት ብሩህ ቀን ይሁንልን!

@melkam_enaseb
መጋቢት 10

የአለም አቀፍ የዳዉን ሲንድረምን ቀን ''ስለኛ ከእኛ ጋር'' በሚል መሪ ቃል አብረዉን በመጋቢት 10 በወዳጅነት ፖርክ እያከበሩ፣ ግንዛቤ ያስጨብጡ፣ አብረዉን ይስሩ።

Call +251942225838 for t-shirt orders.

(Deborah Foundation)

@melkam_enaseb
የተሰበረው ገጽህ!

አንድ ገጽ ላይ የተሰበረ መጽሐፍ ሁል ጊዜ ስትከፍተው የሚከፈተው እዚያ የተሰበረው ገጽ ላይ ነው፡፡

አንድን መጽሐፍ አንሳና አንድ ገጽ ላይ ከፍተህ ግራና ቀኙን ይዘህ ወደ ኋላ በመለመጥ እዚያ የተከፈተው ገጽ ጋር እስኪላቀቅ ግፊት በማድረግ ስበረው፡፡ 

በሌላ ጊዜ መጽሐፉን ስታነሳው መጀመሪያ ራሱን ከፍቶ የሚቆይህ ይህ የተሰበረ ገጽ ነው፡፡

በሕይወትህ አንድ ደጋግሞ የተሰበረ ክፍል ካለህ ምንም ነገር ሲከናወን የሚከፈትብህ ይህ የተሰበረ ገጽ ነው፡፡

አንድ ገጽ ላይ የተሰበረ መጽሐፍ ሌላ ገጽ ላይ ተከፍቶ እንዲቀመጥ ቢሞከር እንኳን ማንም ሳይጠይቀው ወደዚያ ገጽ የመከፈት ዝንባሌ አለው፡፡ ሕይወትም እንዲሁ ነች፡፡ ደጋግመን የተሰበርንባቸው የሕይወታችን “ገጾች” በሆነ ባልሆነ የመከፈት ባህሪይ አላቸው፡፡ 

ደጋግመህ የተሰበርክበትን የሕይወት “ገጽ” ቀድመህ ካላስተካከልካቸው በሁሉም የሕይወት ዘርፍ ውስጥ እየተከፈተ ያስቸግርሃል፡፡

በተለይ እነዚህን ስብራቶች ይዘህ ወደ ጓደኝነት፣ ወደ ፍቅር ሕይወት ወይም ወደ ትዳር፣ ወደ ስራ ወደ መሳሰሉት ማሕበራዊ ስምሪቶችህ ስትገባ ገጹ እየተከፈተ ያስቸግርሃል።

ምንም ነገር ውስጥ ከመግባትህ በፊት በመጀመሪያ የተሰበረውን “ገጽህን” ጠግን!!!

(ዶ/ር ኢዮብ ማሞ)

መልካም ቀን!

@melkam_enaseb
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ የአዕምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት እና ከሱስና ተያያዥ ችግሮች ጋር በተያያዘ ሰብ ስፔሻሊስት የሆኑት ፕሮፌሰር ሰለሞን ተፈራ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጥናቶችን ዋቢ በማድረግ ስለ ድብርት መንስዔ፣ ምልክቶች፣ ጉዳት እና ሕክምና ሙያዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ድብርት ምንድን ነው? ምልክቶቹስ?

የድብርት (ዲፕሬሽን) ሕመም በሰፊው ከሚታዩ የአዕምሮ ጤና ችግሮች አንዱ ሲሆን÷ የስሜት መውረድን ብሎም የደስታ ስሜት ማጣትን ያሳያል፡፡ እንደ ባለሙያው ገለጻ አንድ ሰው በድብርት ውስጥ ሲሆን በውስጣዊ ስሜቱ እና በውጫዊ ገጽታው እንደሚንጸባረቁ ጠቅሰው÷ ይህም ደስታ ማጣት፣ መከፋት፣ ጥልቅ በሆነ ሀዘን ውስጥ መሆን ናቸው፡፡

ድብርት የስሜት በሽታ በመሆኑ ከስሜት መቃወስ ጋር ተያይዞ የሐሳብ መዛባት ያስከትላል ብለዋል፡፡ በዚህም ሰዎች ለእራሳቸው፣ ለሕይወት እና ለቀጣይ ኑሯቸው ያላቸው አመለካከት ጨለምተኛ የመሆን አዝማሚያ ይታይበታልም ነው የሚሉት።

ከድብርት መገለጫዎች መካከል፦

የስሜት መዛባት፣ በፊት ያስደስቱ በነበሩ ሁኔታዎች አለመደሰትና አለመፈለግ፣ የአስተሳሰብ (የአዕምሮ እና የአካል) ፍጥነት መቀነስ (ዘገምተኝነት)፣ የምግብ ፍላጎት እና ክብደት መቀነስ ይጠቀሳሉ፡፡

በአንጻሩ በአንዳድ ሰዎች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የምግብ ፍላጎት መጨመር፣ ከመጠን ያለፈ ውፍረት፣ ምክንያቱ በግልጽ ያልታወቀ ከፍተኛ ድካም፣ እራስን በከፍተኛ ሁኔታ አሳንሶ ማየት፣ እራስን በከፍተኛ ሁኔታ መውቀስ (የተጋነነ የጥፋተኝት ስሜት)፣ የኃጢያተኝነት ስሜት፣ ሕይወትንና ኑሮን መጥላት፣ ሞትን መመኘት፣ እራስን ለማጥፋት ማሰብ ብሎም ለማጥፋት መሞከር የድብርት መገለጫዎች ናቸው፡፡

የድብርት መንስኤ ይታወቃል?

ድብርት ብዙ ጊዜ እንደማንኛውም የአዕምሮ ህመም ቁርጥ ያለ መንስኤ ባይኖረውም÷ የታወቁ ሥነ ልቦናዊ፣ ማህበራዊ እና አካላዊ አጋላጭ ሁኔታዎች አሉት ይላሉ ባለሙያው፡፡ ጾታዊ ጥቃት፣ ድንገተኛ የኢኮኖሚ ክስረት፣ የተፈጥሮ እና ሰው ሠራሽ አደጋን ተከትሎ የሚፈጠር ማህበራዊ መቃወስ፣ በትዳር ውስጥ የሚያጋጥሙ ከፍተኛ ጫናዎች እና ከሥራ መፈናቀል ለድብርት አጋላጭ የሚባሉ ማህበራዊ ችግሮች መሆናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

ከሥነ-ልቦናዊ ችግሮች መካከል የአዕምሮ ጥቃት ለድብርት አጋላጭ መሆኑ ሲጠቀስ÷ አንዳንድ መድኃኒቶች፣ አደንዛዥ እና አነቃቂ ዕጾች እና ሥር የሰደዱ አካላዊ (ሥነ ሕይወታዊ) ህመሞች በድብርት አጋላጭነታቸው ይነሳሉ፡፡

ድብርት በዘር የመተላለፍ ባህሪ ስላለው በቤተሰባቸው የድብርት ህመም ታሪክ ያላቸው ሰዎች ለድብርት የመጋለጥ ዕድላቸው እንደሚጨምር ተገልጿል። ድብርት በሁሉም የዕድሜ ደረጃ ሊታይ እንደሚችል ቢታመንም በተለይ በጉርምስና እና በ40ዎቹ መጨረሻ የዕድሜ ክልል ላይ በጉልህ ይታያል፡፡

ድብርት ሕክምና አለው?

ድብርት እንደ ሕመሙ ዓይነትና ክብደት በምርመራ ተለይቶ ሥነ-ልቦናዊ (ሳይኮ ቴራፒ) እና የመድኃኒት ሕክምና ይሰጣል፡፡ የድብርቱ ዓይነት ቀላል ከሆነ ሥነ-ልቦናዊ ሕክምና፣ ከባድ ከሆነ ደግሞ የመድኃኒት ሕክምና ይሰጣል።

በተጨማሪም የሕመሙ ተጠቂዎች ሆስፒታል ተኝተው ሊታከሙ የሚችሉበት ሁኔታ እንዳለም ጠቁመዋል፡፡ ሕመሙ ሥር ሰዶ ምግብ መመገብ፣ መናገር ብሎም መድኃኒት ለመውሰድ ፈቃደኛ የማይሆኑበት ጊዜ ከደረሰ አንጎልን በኤሌክትሪክ የማነቃቃት ሕክምና ሊሰጥ ይችላል፡፡

ድብርት ከወንዶች ይልቅ በሴቶች ላይ በእጥፍ ጨምሮ የሚታይበት ሁኔታ በግልፅ ባይታወቅም መላ-ምቶች እንዳሉ ግን ፕሮፌሰር ሰለሞን ተፈራ ያስቀምጣሉ፡፡ በሴቶች ላይ በተፈጥሮ በተለያዩ ሁኔታዎች የሚቀያየሩ የሆርሞን ልዩነቶች (ከወሊድ በኋላ ለሚከሰት ድብርት)፣ እንዲሁም በወንዶች እና በሴቶች መካከል ያሉ የተፈጥሮ ቅመሞችን ለአብነት ጠቅሰዋል። ከሥነ-ልቦና አንጻርም ሴቶች ለድብርት የበለጠ ተጋላጭ መሆናቸውን ያነሳሉ፤ ለምሳሌ ተገዳ የተደፈረች ሴት ለድብርት የመጋለጥ ዕድሏ ሠፊ ሊሆን እንደሚችል በመጥቀስ።

በተመሳሳይ ሴቶች ላይ የቤት ውስጥ ጥቃት መበራከቱ፣ በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሴቶች በማህበራዊ አጋላጭ ምክንያቶች በአብዛኛው ለድብርት ሊጋለጡ እንደሚችሉም መላ-ምቶች መኖራቸውን ፕሮፌሰር ሰለሞን ተፈራ ጠቅሰዋል፡፡

@melkam_enaseb
መልካም ዜና!

የዛሬ አመት አካባቢ በማህበራዊ ሚዲያ ሶስት የአእምሮ ታማሚ ወንድማማቾች በአንድ ቤት ውስጥ ተዘግቶባቸው የሚል ዜና አይተን ነበር። ታዲያ አሁን ላይ ከሶስቱ ወንድማማቾች አንዱ ተሸሎት ተሞሽራል!

የተማረ ነው… ድግሪን በጣጥሷታል፡፡ ያውም በማዕረግ፡፡ መምህር ሆኖ ትውልድን በትምህርት ወልዶ፣ አሳድጎ ለቁም ነገር ያበቃ ተወዳጅ መምህር፡፡ ግን…. ህመም ማንን ሊፈራ? ታመመ፡፡ ንቁ አእምሮው እውኑን እና ምዕናቡን መለየት እስኪያቅጠው ድረስ ታመመ፡፡

አስታማሚ በሌለበት ታመመ፡፡ ራሱን ከማስታመም በላይ ከሱ የባሰ ታመው ከምሰሶ ጋር ለታሰሩ ወንድሞቹ ሀለፊነት መውሰድ ነበረበት፡፡ ረዳት በሌለበት... በባዶ ቤት ውስጥ… ተስፋን ብቻ ይዘው።

ከ10 ዓመት በኋላ… ከዕለታት በአንድ ልዩ ቀን… አንዲት የተባረከች ጋዜጠኛ ብርሀን በሚገባበት በር ገብታ ከፊታቸው ቆመች-- ከአእምሮ ህመም ጋር ለሚታገሉ የተሰጠ  “ስጦታን'' ይዛ፡፡

ስጦታ የአእምሮ ህክምና እና የሱስ ማገገሚያ ማዕከል ሶስቱን ወንድማማቾች ተቀበለ፡፡ ጤናቸውን ስጦታ አድርጎ ሊመልስላቸው፡፡

እነሆ ባለ ምጡቅ አእምሮ መምህር አብዱልቃድር ሰይድ ይኸው ተሞሸረ፡፡

እንኳን ደስ አለህ!

የአእምሮ ታማሚዎች ታክመው ውጤታማ ሂወት መቀጠል እንደሚችሉ ይህ ማሳያ ነው።

@melkam_enaseb
እንኳን ለ127ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ!

ክብርና ሞገስ ከወራሪ ነፃ የሆነች ሀገር ላስረከቡን ጀግኖች አርበኞቻችን።

@melkam_enaseb
Join us for the first episode of our mental health series. You can register through the link below.

Topic: Pathways into a Career in Mental Health.

Date and time: March 04, 2023, 3:00 PM Nairobi Time

Registration link: https://forms.gle/cTS7dLaSdoUkyTuW6

#EMA

@melkam_enaseb
"አልችልምን" መሰረዝ!

ሁላችንም እኛን ለማጥፋት ኃይል ያለውን ቃል ተሸክመን ነው የምነዞረው....ይሄውም ቃል "አልችልም." ነው።

ይህ ቃል ነፍስን ይሰብራል፣ ህልምን ያጨናግፋል።

"አልችልም" ... ብዙዎቻችን ያለንን አቅም እንዳንጠቀም የሚከለክለን ቃል ነው።

በህይወታችን ለውጥን የምንሻ ከሆነ...... "አልችልም" የሚለውን ቃል ከመጠቀም መንፃት አለብን፣ በምትኩም በተሻለ፣ ጠንካራ፣ እና ተስፋን በሚያጭር ቃል መተካት ተገቢ ነው።

"አልችልም"ን በአወንታዊ በሆኑ እንደ "የመቻል አቅም አለኝ"፣ "በሙከራዬ አሳካዋለሁ"፣ "የማሳካት አቅም አለኝ" ወ.ዘ.ተ. በመሳሰሉ ቃላት ስንቀይር..... በመንገዳችን የተጋረጡትን መሰናክሎች ጠርምሰን የማለፍ አቅምን ማካበት እንጀምራለን፣ ከዛም በተጨማሪ ተግዳሮቶችን የምንጋፈጥበትን ዘዴ በጥሞና እናስተካክላለን።

በጥቅሉ "አልችልም" የሚለው ቃል ከንግግራችን ሲጠፋ፣ በምትኩ ችግሮቹን የምንወጣበት ዘዴ የመፈለግ ተነሳሽነታችን ይጨምራል!

ጥበብ እና ማስተዋል ለሰው ልጅ በሙሉ!
 
ሣሙኤል ተክለየሱስ (ዓለመ አቀፉ የህይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)

መልካም ቀን!

@melkam_enaseb
⬆️ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
መጋቢት 23

ሲ ኤፍ ኤስ ኢትዮጵያ ከስለ እናት የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን የዓለም ኦቲዝም ቀንን ለማክበር ቅዳሜ መጋቢት 23፤ 2015 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በስለ እናት የበጎ አድራጎት ድርጅት ቅጥር ግቢ ይገኙ።  

መርሐ ግብሩ ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ እስከ መጋቢት 15፤ 2015 ዓ/ም ድረስ  በ +251-911-619018 የእርስዎን እና የሚጋብዟቸውን እንግዶች ስም ይላኩ!

አድራሻ፡ ሳር ቤት ቫቲካን ኤምባሲ በሚገኘው ስለእናት የበጎ አድራጎት ድርጅት ቅጥር ግቢ።

ስለ ኦቲዝም ማህበረሰባዊ ግንዛቤ በጋራ እንፍጠር!

@melkam_enaseb
ልባችን ከእድሜያችን በላይ ሊያረጅ እንደሚችል ያውቃሉ?

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ልባችን ከእኛ ቀድሞ እንዲያረጅ የሚያደርጉ ናቸውና አስቀድመን ጥንቃቄ ማድረግ ይበጃል።

1. ጭንቀት

ልብን በፍጥነት ከሚያስረጁ ምክንያቶች ቀዳሚው ጭንቀት መሆኑን ጆን ሆፕኪንስ ያወጣው ጥናት ያሳያል። ጭቅጭቅ የበዛበት ትዳር ውስጥ ያሉ እና ፍቺ የተደጋገመባቸው ሰዎች ለልብ ህመም የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ መሆኑንም ነው ጥናቱ ያመላከተው። በጭንቀት ጊዜ ሰውነታችን የሚለቃቸው ኬሚካሎች የደም ግፊት እና የመጥፎ ኮሊስትሮል መጠን እንዲጨምር ማድረጉም የልብ ጤናን እንዲያውክ ያደርገዋል።

2. የእንቅልፍ እጦት

በቂ የእንቅልፍ ጊዜ ማጣትም የደም ዝውውርን በማፍጠን በልብ ላይ ከፍተኛ ጫናን ያሳድራል። ይህም የልብ ጤናን በረጅም ጊዜ ክፉኛ የሚጎዳው ሲሆን ልባችን ያለጊዜው ያስረጀዋል ይላል የሲ ዲ ሲ ጥናት።

3. አካላዊ እንቅስቃሴ አለማድረግ

ማዮ ክሊኒክ በ2019 ባደረገው ጥናት የልብ እርጅናን ለመቀነስ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ትልቅ ድርሻ እንዳለው አመላክቷል። በወር ውስጥ ለ150 ደቂቃዎች የአካል እንቅስቃሴ ማድረግንም የልብ ጤናን ለመጠበቅ ወሳኝ ነው በሚል ይመክራል።

4. ሲጋራ ማጨስ

“ሲጋራ ማጨስ ሳንባን ብቻ ይጎዳል ብላችሁ የምታስቡ ተሳስታችኋል” የሚለው ሲ ዲ ሲ፥ ማጨስ የልብ ጤና ጸር መሆኑን ይገልጻል። በሲጋራ ውስጥ የሚገኙ ኪሚካሎች የደም መርጋትን በማስከተል በልብ ላይ ጫና እንደሚፈጥሩ በጥናት ተረጋግጧል። እናም ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች ልባቸው ከእድሜያቸው በፊት ከማርጀቱ በፊት ማጨስ ያቁሙ ሲልም ያሳስባል ሲ ዲ ሲ።

በአጠቃላይ ጤናማ አመጋገብን መከተል፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግና ከአጉል ሱሶች መራቅ ልባችን ቀድሞን እንዳያረጅ ያደርጋሉ ተብሏል።

(አል-አይን)

@melkam_enaseb
ታላቁ ጥበብ!

በህይወታቹ ውስጥ የሚገጥማችሁን ማንኛውም ችግር ወደ በጎ አጋጣሚ ልትቀይሩት ትችላላቹ።

የአለማችን ዝነኛዋ የሚዲያ ባለሙያ ኦፕራ መልክሽ ለቴሌቪዥን ሾው አይመጥንም ተብላ ከስራዋ ተባራ ነበር። እሷ ግን ያን መጥፎ አጋጣሚ ራሷን ችላ ለመቆምና ውስጧ ያለውን እምቅ ሀይል አውጥታ ለማሳየት ተጠቀመችበት።

አምፖል የኖረው ጨለማ ስላለ እንደሆነ አስታውሱ። አውሮፕላን የተፈጠረው አቀበትና ርቀት እንዲሁም ብዙ ከልካይ ነገሮች ስላሉ እንደሆነ አትርሱ።

ስለዚህ ዋናው ቁም ነገር የችግሮች መኖር አይደለም። ይልቁኑ እነዚህን ችግሮች ወደ መልካም አጋጣሚ ለመቀየር ዝግጁ ናችሁ ወይ የሚለው ነው።

እስኪ ቆም በሉና አሁን ላይ የምትማረሩባቸውን ችግሮች አስቡ። በነዚህ ችግሮች ውስጥ መልካም አጋጣሚም አብሮ እንዳለ ልነግራቹ እወዳለው። እስከ ሕይወታቹ ፍጻሜ ድረስ የተሻለ ህይወት የመኖር እድል አላቹ። ተግዳሮቶቻችን ሊቆሙ አለመቻላቸው ቢያሳዝንም ተግዳሮቶችን ለከፍታችን ልንጠቀምባቸው መቻላችን ደሞ ደስ ያሰኛል።

የሚደርስባችሁን ነገር መምረጥ ባትችሉ የምትሰጡትን ምላሽ ግን መምረጥ ትችላላችሁ።

አስቡ ደግማቹ አስቡ!

ኤርሚያስ ኪሮስ
(Counseling Psychologist)

@melkam_enaseb
2025/07/09 01:25:22
Back to Top
HTML Embed Code: