አውቃለሁ ህይወት ምን ያክል እየከበደችህ እንደሆነ። አንድ ነገር እንዲለወጥ ትፈልጋለህ ግን ምን እንደሆነ አታውቅም። ምን እየሆነክ እንደሆነ፣ በአንተ ላይ ምን እየተፈጠረ እንዳለ አልገባህም፤ ብቻ ጭንቅላትህ ሊፈነዳ እንደደረሰ ይሠማሃል። በጣም ብዙ ጨለማ ሃሳቦች፣ የስሜት ለውጦች ይጎበኙሃል።
ምን አልባትም "እንደ ሌሎች ሰዎች ሆኜ አልተፈጠርኩ ይሆን?" ብለሃል።
ምንም እንኳን በሙሉ አቅምህ ብትሞክርም እዚህ ምድር ላይ "መኖርን" በራሱ መቋቋም አልቻልክም፤ ምክንያቱም ደህና እደለህም! ሁልጊዜ ህመም ውስጥ ነህ። ሁልጊዜ በህመም ውስጥ መሆን ደግሞ ያሰለቻል! ያደክማል!
ግን...ልብ ብለህ ስማኝ...ደህና አለመሆን የአንተ ጥፋት አይደለም፤ ይህ ማለት እረዳታ ያስፈልግሃል ማለት ነው። በመሆኑም በቅርብህ ላሉ ሰዎች ግልፅ በመሆን አማክራቸው። ብቻህን መታገል የለብህም! ምን አልባት በውስጥህ ያሉ ትርጉም የማይሰጡ ነገሮችን የሚጋራህ እና የሚረዳህ ሰው ታገኛለህ፤ ይህ ነገሮችን ያቀላል።
ይህን ማድረግ ከከበደህ ወደ አእምሮ ህክምና መስጫ ማዕከል በመሄድ የስነ አእምሮ ወይንም የስነ ልቦና ባለሙያዎችን አማክር።
No one is immuned for mental illness
Explore your mentality.
Fetlework abate (psychiatry nurse)
#Hakim
@melkam_enaseb

ከቀዳዳ ጀልባ ላይ ውሀ በማንኪያ!
አማኑኤል ሆስፒታል በሀገራችን ብቸኛው የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነው። ወደ ሁለት መቶ የሚጠጉ አልጋዎች አሉት። በተመላላሽ ህክምና አገልግሎት የሚሰጡ ወደ አርባ ክፍሎች አሉት።
የአእምሮ ህመም ከ5 ሰው 1 ሰው ላይ ይከሰታል። በሀገራችን ያለው የአእምሮ ህመም ስርጭት (Life time prevalence) 27% ነው። የሀገራችን ህዝብ 120 ሚልየን ይገመታል። ያ ማለት 30 ሚሊዮን ህዝብ በአንድ ወይም በሌላ ወቅት የአእምሮ ህመም ያጋጥመዋል ማለት ነው። በሚያሳዝን መልኩ አብዛኞቻችን የአእምሮ ህመም የሚመስለን ልብሱን አውልቆ ጎዳና የወጣ ሰው ነው። የአእምሮ ህመም ማለት ህፃናት ላይ የሚከሰት ትኩረት ያለማድረግ ችግር (ADHD)፣ መኮላተፍ (Fluency disorders)፣ ከ5አመት በኋላ አልጋ ላይ መሽናት (enuresis)፣ በአስራዎቸ እድሜ የሚከሰቱ የስሜት መዋዠቅ፣ የድብርት ህመም (Depression)፣ ሱስ፣ የእንቅልፍ ችግር (Insomnia)፣ የወሲብ ፍላጎት አለመኖር (Hypoactive sexual desire disorder)፣ በእድሜ ማምሻ ላይ የሚከሰት የመርሳት ህመም (Dementias) .....ወዘተ ማለት ነው።
የአእምሮ ህመም በሁሉም ክልሎች ይከሰታል። ገጠርና ከተማ፣ ብሄርና ሀይማኖት አይለይም። ከአእምሮ ህመም ስርጭት አንፃር አንድ አማኑኤል የሚሰጥ አገልግሎት ከቀዳዳ ጀልባ ላይ የሞላውን ውሀ በማንኪያ እንደመድፋት ነው። ትልልቅ የአእምሮ ህክምና ተቋማት ቢቻል በየዞኑ ባይሆን በየክልሎች ያስፈልጋል። 27% ማለት ሁላችንም ቤት ያለ ጉዳይ ማለት ነው።
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

#Dailytips
"ሳይገለፁ የቀሩ ስሜቶች አይሞቱም። በህይወት እንዳሉ ተዳፍነው ይከርሙና በአስቀያሚ መልክ ይገለፃሉ።" - ሲግመን ፍሮይድ

"ለምን እኔ ብቻ?" እያልክ ትጠይቅ ይሆን?
እኩዮቼ አግብተዋል።
እኩዮቼ ልጆች አፍርተዋል።
እኩዮቼ ጥሩ ሥራ ይዘዋል።
እኩዮቼ ስኬት ተጎናጽፈዋል።
እኩዮቼ ውድ ቤትና መኪና አሏቸው።
እኩዮቼ በማኅበረሰቡ የተከበሩ ናቸው።
እኩዮቼ እንዲህ ናቸው፤ እንዲያ ናቸው...
እያልክ ይሆናል።
ትክክል ብለሃል። ይሁንና ጨርሰህ መርሳት የሌለብህ...
ከሚታየው ምቾት ባሻገር የማይታዩ ብዙ ሸክሞች። ከሚማርኩ ፈገግታዎች ጀርባ ብዙ የልብ ቁስልና ህመሞች እንዳሉ እወቅ።
ከሩቅ ያማረ ኑሮ ሁሉ የስኬት ምልክት፣ ከውጭ የሚታይ አንጸባራቂ ነገር ሁሉ ወርቅ አይደለምና። ስለዚህ ያወቅነው 'ደስታውን' ሲሆን ያላወቅነው ደግሞ 'ጉድለቱን/ችግሩንና ድካሙን/' ነው።
እኩዮችህ ሆነው በህይወት የሌሉትን።
እኩዮችህ ሆነው በህመም የሚሰቃዩትን።
እኩዮችህ ሆነው በአእምሮ መታወክ በማህበረሰቡ እንደ እብድ የተቆጠሩትን።
እኩዮችህ ሆነው መንገድ ዳር የሚያድሩትን።
እኩዮችህ ሆነው ወላጅ አልባ የሆኑትን።
እኩዮችህ ሆነው የለት ጉርስ ያጡትን።
እኩዮችህ ሆነው አንተ የምትኖረውን ኑሮ የሚናፍቁና ባንተ ህይወት የሚቀኑ መሰል የሰው ዘርን...ረስተሃል።
ምናልባት የምትፈልገው ስፍራ ላይ አልተቀመጥክ ወይም የምትመኘውን ነገር አላገኘህ ይሆናል። ይሁን እንጂ ከብዙዎች በላይ ደስተኛ ነህ። ስለዚህም ፈጣሪህን ባለህ ነገር አመስግን።
አንተ ለብቻህ የሆነብህ ነገር የለም። አንተ ጋር የጎደለህን ሌላው ጋር ስታይ 'ሁሉ የሞላለት' መስሎህ ነው። ባወቅኸው ልክ የሰውን ህይወት አትመዝን፣ የራስህንም አታቃል። ያወቅክ የመሰለህ ያላወቅኸው ብዙ አለና። ስለዚህ በምንም አይነት የህይወት ትግል ውስጥ ብትሆን ደስታን ምርጫህ አድርግ። ሰላምንም ውደዳት። ሁልጊዜም በፈጣሪህ ደስ ይበልህ!
(Samuel Geda)

#ባለውለታ
"ሰውነት አልሞተም"
በዚህ ግዜ እኛ ኢትዮጵያውያን ብሎም በአለም ላይ የሚታየው የሚሰማው ሁሉ ሰው ሰውነቱን በቃ አጣ? ዓለም ለመኖር አስፈሪ እየሆነች ይሆን? የሚያስብሉ ሰው የሰው ስጋት እየሆነ የመጣበት አስከፊ ነገሮች ተከስተዋል እየተከሰቱም ሰብዓዊነትም እየተሸረሸረ የመጣበት ጊዜ ነው።
ነገር ግን አሁንም በጨለማ ውስጥ ብርሃን የሆኑ እና ለመኖር እንድንጓጓ የሚያደርጉን ጥቂት የማይባሉ ለነብሳቸው ያደሩ ልበ ብሩሃን መልካም ሰዎች ዛሬም አሉ።
ለአብነት ያህል ከሰሞኑ በልበ ብሩሁ ቢኒያም አማካኝነት ለተቋቋመው መቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የማስፋፊያ ህንፃ ግንባታው ተጠናቆ ነገር ግን ያላለቁ የበር እና የመስኮት እንዲሁም አንዳንድ የፊኒሺንግ ስራዎች ለማጠናቀቅ የሚውል ገንዘብ አሰባስቤ ሳልጨርስ ከዚች ወንበር ንቅንቅ አልልም ብሎ ራሱን ለመልካምነት አሳልፎ የሰጠውን በበጎ ስራዎቹ የምናውቀው ኮሜድያን ዕሸቱ መለሰን መጥቀስ ይቻላል። እንደዚህ ያሉ መልካም ሰዎች ያብዛልን እያልን፤ ለዚህ በጎ ዓላማ መሳካት ከጎኑ የሆኑ ቅን ልብ ያላቸው መልካም ሰዎች ሁሉ ክብር ይገባቸዋል።
የሀገር ባለውለታው ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ ላደረከው፤ እያደረክ ላለኸው እና ወደፊት ለምታደርገው ሁሉ ክብር ይገባሃል!
"ሰውነት! ሰብዐዊነት አሁንም አልሞተም"
#Bookforall

ስብዕና!
"ከህመሞች ሁሉ ትልቁ ህመም ካንሰር ወይም ኤድስ ሊመስለን ይችላል። እውነቱ ግን ከስብዕና መዛባት የከፋ ህመም የለም። ውጫዊ መልክ የሠው የገጽ ሽፋን ነው። ስብዕና ግን የሠው እውነተኛ መልክ ነው። በየዕለቱ አብረን የምንኖረው ሰው ቢኖር፣ እውነተኛና የማያረጅ ዘላቂ ማንነታችን ሰብዕናችን ነው። በዓይናችን የማናየው እውነተኛ መልካችን በውስጥ ማንነታችን ውስጥ ተቀብሮ ያለው ሰብዕናችን ነው። የሰብዕና ስንኩልነት፣ ጠባሳዎችና መዛባቶች ቤት ያፈርሳሉ፣ አገር ይንዳሉ፣ ግንኙነትን ይመርዛሉ። ለማከም ለማዳን ብቻ ሳይሆን ለማየትና ህመሙን ለመረዳትም አዳጋች ነው።
ሰብዕና በልጅነት እንደ ተቦካ ሲሚንቶ፣ በአዋቂነት ደግሞ እንደ ደረቀ አርማታ ነው። የብዙ ሠው ሰብዕና እንደ ተቦካ ሲሚንቶ በልጅነት ጊዜ በትክክል የሚቀርፀው ካለገኘ ተንሻፎና ተዛብቶ ያድጋል። ዕድሜው ከገፋ በኋላ ደርቆ ስለሚጠነክር፣ ብዙ ጊዜ ለመከራ መዶሻና ለምክር መጥረቢያ አዳግቶት አገር ያጠፋል። የልጅ ውበቱ በቀላሉ መሰራቱ... ያዋቂ ክፋቱ ለመለወጥ አስቸጋሪ የሆነ ክፉ እውቀቱ ነውና።"
(''ሌላ ሰው'' መጽሐፍ በዶ/ር ምህረት ደበበ)

ስኬታማ ሴት ልጆችን ለማሳደግ የወላጆች ድርሻ!
በመጀመሪያ ስኬታማ ሴት ማለት ምን ማለት ነው?
- በራሷ የምትተማመን፣ ውሳኔዎች የመወሰን አቅም ያላት፣
- ምርጫዋን የምታውቅና የሌሎችን ምርጫ የምታከብር፣
- ጊዜዋን በዋዛ ፈዛዛ የማታሳልፍ፣ ችግሮችን ለመፍታት የራሷን አስተዋፆ የምታበረክት፣
- ስሜትና ሀሳቧን የምትገልፅ፣ እችላለሁ የሚል አመለካከት ያላት፣
- ራሷን እና ሌሎችን የምታከብር፣ ሌሎችን ለመርዳት ዝግጁ የሆነች፣
- ችግር ባጋጠማት ጊዜ ከችግሩ ይልቅ መፍትሔው ላይ የምታተኩር፣
- ለፈጣሪዋ፣ ለባሏ እና ለቤተሰቧ ታማኝ የሆነች፣
- የሴቶች የሆነውን ርህራሄ እና ደግነት ያላት፣
- ራስ በመቻል የምታምን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የሌሎችን እርዳታ የምትጠይቅ፣
- ሂወትን እና ዙሪያዋን በአግባቡ የምትረዳ እና ሌሌችን ለመምሰል ጊዜ የማታባክን፣
- በጥላቻ፣ ክፋት እና ሃሜት የሚወረወርባትን ድንጋይ ለውድቀት ምክንያት ሳይሆን ወደከፍታ ለመውጣት ድልድይ የምታደርግ እና ለልጆቿ መልካም አርአያ የሆነች ናት።
ታዲያ እንዲህ አይነት ሴት ለማፍራት ሴት ልጆችን እንዴት እናሳድግ?
1. በዕለት-ተዕለት እንቅስቃሴዋ እኛ እናውቅልሻለን ብለን ለሷ ከመወሰን ይልቅ ራሷ እንድትወስን እድል እንስጣት።
2. በውስጧ ጠቃሚ ነገር እንዳለ ተረድተን እናድምጣት።
3. ብዙ የህይወት እንቅስቃሴዎች ውስጥ እንድትሳተፍ በማድረግ ከሚያጋጥሟት ችግሮች እንድትማር እና ከስኬቷ እችላለሁ የሚል መንፈስ እንዲኖራት እናግዛት።
4. ሴት ልጅ ማድረግ የምትችለው እና የማትችለው በማለት አንገድባት።
5. ሀላፊነቶች የመወጣት አቅሟ እንዲዳብር ሃላፊነት እንስጣት።
6. ብዙ ለውጪ አለም ሚድያ በተለይ በለጋ እድሜ አናጋልጣት ማለትም ስኬት ውበት እና የአርቲፍሻል ጋጋታ እንደሆነ ለማሳየት ስለሚሞክሩ።
7. እንደ ቤተሰብ ያላችሁን ቤተሰባዊ ባህል አስተምሯት።
8. ራሷን እንድትወድ እና እንድትቀበል እንርዳት ማለትም ውብ እና አስፈላጊ እንደሆነች በፍቅር እንግለፅላት።
9. ከሌሎች ጋር አናወዳድራት፤ ለሌሎች ቀና አመለካከት እንዲኖራት አርገን እናሳድጋት።
10. ያላት ዝንባሌ እንዲያድግ እድል እናመቻችላት።
በመጨረሻም: ችግር ሲያጋጥማት ችግሮቿን እንዴት መፍታት እንደምትችል እናሰልጥናት እንጂ ችግር አጋጠመን ማለት ወድቀናል ማለት እንዳልሆነ ይልቁንም የምንማርበት እድል እንደሆነ እንንገራት።
ሴት ልጆቻችንን እንውደዳቸው፣ እንንከባከባቸው፣ አስፈላጊውን ስልጠና እና ትምህርት እንስጣቸው ደግሞም በነሱ እንደሰት።
መአዛ መንክር (ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት)
#March8
መልካም አለም አቀፍ የሴቶች ቀን!

⬆️ You are invited to join a Zoom webinar!
When: Wed, march 15, 2023 at 12:00 Pm.
Topic: Management of Schizophrenia especially on the newly imported drug Paliperidone.
Join Zoom Meeting: https://us05web.zoom.us/j/4284924927?pwd=QjV1aWhxUnV1REQrcUJqdjdrUzFXZz09
Meeting ID: 428 492 4927
Passcode: sitota

የ CBT ስልጠና!
ለተጨማሪ መረጃ እንዲሁም ምዝገባ ከታች የተቀመጠውን ሊንክ ይጠቀሙ።
Certificate Course on Cognitive Behavioral Therapy!
For further details and registration, use the link below!
https://forms.gle/XBxigR7BG2EeDc3m6
(Aha Psychological Services)

ውድቀታችን የኑሮችን መጨረሻ አይደለም!
ሁሉንም ነገር ከልብ ከፈለግነው ያደክመናል እንጂ አናጣውም። ከልቡ የፈለገ ሰው የልቡን አያጣም።
ሽንፈቶቻችን ሁሉ በጥረቶቻችን ይሸነፋሉ። ድክመቶቻችንም በጥንካሬአችን ይደመሰሳሉ። በማይቆም ጥረት ውስጥ ስንኖር ለማይቀር ድል እንታጫለን።
የምንኖረው መሆን እና አለመሆን በሚፈራረቁባት ምድር ላይ በመሆኑ ለደቂቃም ቢሆን ጥሮና ግሮ ከመኖር አንታቀብ። ብዙ ነገር ሊያጥረን ይችላል ነገር ግን የሁሉም እጥረቶች ማጥፊያ ራሱ ጥረት ብቻ መሆኑን አንርሳ።
ከተጋን እየፈካን እንኖራለን። ትጋታችን ምኞታችንን ከተረትነት ይታደገዋል። ሳንሰለች ከታገልን የፈለግነው ሁሉ እኛን ይፈልገናል።
በከፈለኝ ዘለለው ['አሞዛ']
መልካም ቀን!

የማይቀርበት ድንቅ ፕሮግራም!
መጋቢት 9/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ በካፒታል ሆቴል 'እንዴት ይቅር ልበል' በሚል ርዕስ ተግባራዊ የይቅርታ ህይወት ላይ ያተኮረ ዝግጅት ተዘጋጅቷል::
የእለቱ እንግዶች፦
ዶ/ር ወዳጄነህ መሀረነ
አቶ በኃይሉ ገብረመድኀን
ዶ/ር ተወልደ ገብረእግዚአብሔር (በልጃቸው ሮማን ተወልደ በኩል)
መግቢያ 2ዐዐ ብር
🎯 ዳግማዊ አሰፋ
ስልክ: +251-909-888857

ከአምስቱ የስብዕና ሞዴሎች (The Big Five Model) ከሚባሉት የትኛው አይነት ስብዕና ነው ያሎት?
#OCEAN
የመጀመሪያው ተቀባይነት (Openness) የምንለው ነው። ይህ መገለጫ የሚያመለክተው የአንድን ሰው ለአዲስ ሀሳብም ሆነ ክስተቶችን ለመጋፈጥ ያለንን ተቀባይነት ነው። ይህን ስብዕና ለመለካት አንድ ሰው አዲስ ቦታ ላይ በሚሆንበት ጊዜ የሚያሳየውን ምላሽ እና የአዕምሮ አቀባበል ተመልክተን መወሰን እንችላለን።
ጥንቁቅነት (Conscientiousness) የምንለው ሌላኛው የስብዕና አይነት ሲሆን በዋነኝነት ጥንቃቄን ይገልፅልናል። ይህ የሚያመለክተው የአንድን ሰው ድንገታዊ ውሳኔዎችን እና ሀሳቦችን የመቆጣጠር ችሎታ ሲሆን ይህን አድርጎ ምክንያታዊ የሆነ እርምጃን የመውሰድ እና ለስራ ሀላፊነትን የመውሰድ ችሎታን ያመላክታል።
Extraversion የምንለው የአንድን ሰው ከውጫዊው አለም ጋር ወይም ከሰዎች ጋር ያለውን ግንኙነት መንገድ እና መጠን የምንገልጽበት ሌላኛው የስብዕና አይነት ነው። ከሰዎች ጋር የመቀላቀል ችሎታን እንዲሁም ፍላጎትን እና ከውጪው አለም ጋር ለመገናኘት ያለን ተነሳሽነት በመመልከት ይህን መገለጫ ልናስቀምጥ እንችላለን።
አራተኛው የስብዕና አይነት ተስማሚነት (Agreeableness) የምንለው ነው። ይህ መገለጫ ሌላን ሰው ለመረዳትም ሆነ ለሰዎች ከምናሳየው አክብሮት አንፃር የሚብራራ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ሰውን የማመን አቅማችን እና ርህራሄን አጠቃሎ የሚይዝ ነው።
የመጨረሻው የስብዕና አይነት Neuroticism የምንለው ሲሆን እስካሁን ከተነሱት በተለየ መልኩ
አሉታዊ የሆነን ስብዕና የሚያሳይ ነው። ይህን የባህሪ አይነት የተላበሱ ሰዎች እንደ ጭንቀት እና ድባቴ ያሉ አዕምሮን የሚረብሹ ስሜቶች በቀላሉ እና ከፍ ባለ መጠን ይሰሟቸዋል። #APS

⬆️ የአዕምሮ ጤና ምንድን ነው?
ለምንስ ስለ አዕምር ጤና መነጋገር ያስፈልጋል?
አቅራቢ: ፕሮፌሰር አታላይ አለም (MD, PHD)
መቼ: ቅዳሜ መጋቢት 23፣ 2015፣ ከሰዓት 10:00-12:00
የት: አዶር አዲስ ሆቴል
ቦታ ለመያዝ ስምዎትን በጽሁፍ ምልዕክት ይላኩ: 0933616212

ነጻነት ያለው አእምሯችን ውስጥ ነው!
በምስሉ ላይ የምትመለከቱት Ricky Jackson ይባላል። Cleveland, Ohio ነዋሪ ሲሆን ገና በ18 አመቱ በለጋ እድሜው ባልሰራው ወንጀል የሞት ፍርድ ተፍርዶበት 39 አመት ከታሰረ በኋላ (አብዛኛውን ግዜ የሞት ፍርድ የሀገሪቱ ርዕሰ ብሄር ካላፀደቁት ወደ እድሜ ልክ ይለወጣል)፣ ትክክለኛው ወንጀል ፈጻሚ በመገኘቱ ዳጎስ ያለ ካሳ ተከፍሎት በነፃ የተለቀቀ ሰው ነው።
እናም ልክ ከእስር ቤት ተለቆ ሲወጣ ያሳሰረውን ሰው አገኘውና... «ይቅር ብዬሃለሁ» ....ብሎ አቀፈው።
ቃለ መጠይቅ ላደረጉለት ጋዜጠኞች ደግሞ እንዲ ሲል ተናገረ:-
«እስር ቤት ውስጥ ነህ ማለት እስረኛ ነህ ማለት አይደለም»
ነጻነት ያለው ያላችሁበት ስፍራ ላይ ሳይሆን አእምሯችሁ ውስጥ ነው። የቂምና የጥላቻ እስረኛ እንዳትሆኑ ይቅር በሉ!
ይቅር በሉ፣ መራመድ አታቁሙ፣ ጉዳታችሁ ላይ አትቆዩ! ህይወት ሰፊና ብዙ ጠርዝ ያላት የጉዞ ሃዲድ ናት!
ይቅርታ ለራስ የሚሰጥ ድንቅ ስጦታ ነው። ሰው ይቅር ማለት ሲጀምር ህይወት ይጀምራል።
የበደሉንን ይቅር ማለት መሸነፍ ሣይሆን ፍቅርን ማስተማር፣ ቀናነትን መዝራት፣ ህይወትን ማደስ ነው። #Abrsh

💥ስለ ዳውን ሲንድሮም ማወቅ ይፈልጋሉ?
👉 ዳውን ሲንድሮም ምን ማለት ነው?
👉 ምልክቶቹስ ምንድን ናቸው?
👉 ተጠቂዎቹን እንዴት መደገፍ እንችላለን?
🗓 በዛሬው እለት ቅዳሜ መጋቢት 9/2015 ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በዳውን ሲንድሮም ላይ በ Clubhouse የምናደርገውን ውይይት ይከታተሉ።
እንግዶቻችን፦
- ዶ/ር ኤርሚያስ ደመቀ
- ዶ/ር ዮሃንስ ግዛው
"ለእኛ ሳይሆን ከእኛ ጋር"
ውይይቱን ለመቀላቀል እዚህ ይጫኑ
ክለብሐውስ ከሌሎዎት ለማውረድ👉 እዚህ ይጫኑ

ባህሪ!
''ባህሪ ሁሉም ሰው የራሱን ምስል የሚያሳይበት መስታወት ነው'' ይለናል ታዋቂው ጀርመናዊው ደራሲና ጸሓፊ ጆሃን ዎልፍ ጋንግ ቮን ጎተ
ከፍላጎቶቻችን አንጻር ምን አይነት ባህሪ ነው በተለያየ ጊዜና ቦታ የምናሳየው?
ባህሪያችን ለሚሰሙን ስሜቶች፣ ለምናስባቸው ሃሳቦች እንዲሁም በአካባቢያችን ለሚፈጠሩ ነገሮችና ሁነቶች በምንሰጠው ምላሽ የተነሳ በዕውን የሚታይና የተገልፀ ማንነታችን ነው።
ታዲያ በሕይወት መንገዳችን ከግቦቻችንና ከዓላማዎቻችን አንጻር ምን አይነት ባህሪ እናሳያለን፣ እናጸባርቃለን?
ግቦቻችንንና ዓላማዎቻችንን ለማሳካት በልበሙሉነት መተግበር የሚገባንን ተግባር መተግበር፣ መክፈል ያለብንን መሰዋትነት በመክፈል ወደ ከፍታው ወደ ግባችን እየተጠጋን ነው ወይስ ከግባችንንና ከዓላማዎቻችን ተቃራኒ የሆኑ ባህሪያትን በማሳየት ፍላጎቶቻችንን እንዳይሳኩ ባለማስተዋል እያጨናገፍናቸው ነው?
ማናችንም ብንሆን በህይወት ሂደት ውስጥ ማሳካት የምንፈልጋቸውን ግቦች ብቻ ማስቀመጥ በቂ አይደለም።
ልናሳካቸው የምንፈልጋቸውን ግቦችና ፍላጎቶች እውን እንዲሆኑ በሂደቱ ላይ የምናሳያቸው ባህሪያት ወሳኝና መሰረታዊ ናቸው።
(ዳንኤል አያሌው)