Telegram Web Link
ዳውን ሲንድረም (Down Syndrome) ምንድነው?

March 21: የአለም የዳውን ሲንድርም የግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ነው።

በአለም ላይ ከሚወለዱ 800 ህፃናት በአንዱ ህፃን ላይ ዳውን ሲንድረም ሊከሰት ይችላል።

ማንኛዉም ሰዉ ገና በማህፀን ዉስጥ ሲፀነስ 23 ዘረመል ከእናቱ 23 ዘረመል ከአባቱ ወስዶ ሰዉ እንደሚሆን ያውቃሉ?

በሰውነታችን ዉስጥ ያሉ እያንዳንዱ ህዋሶች 23 ዘረመል ከእናት ተጨማሪ 23 ዘረመል ከአባት ወስደው ይሰራሉ። ስለዚህ ባጠቃላይ አንድ ሰዉ 46 ዘረመሎች በእያንዳንዱ ህዋስ ዉስጥ አሉት ማለት ነው።

ሆኖም አልፎ አልፎ ይህ ተፈጥሯዊ ሂደት በተለያየ ምክንያት ሳይሳካ ሲቀር አንደኛ ዘረመል ቦታ (ላይ ሁለት ከመሆን ይልቅ ሶስት ዘረመሎች ይሆናሉ።

ከ 46ቱ ዘረመሎች በ 21ኛው ዘረመል ቦታ ላይ ሁለት ዘረመል መሆን የነበረበት ቦታ ላይ ሶስት ዘረመል ሆኖ ሲገኝ ዳውን ሲንድሮም (Down syndrome) ያለው ልጅ ሊፈጠር ይቺላል።

ስለዚህ በ አጭሩ ዳውን ሲንድረም ማለት የዘረመል አፈጣጠር ችግር ሲሆን ዘላቂ የሆነ የተለያዩ የጤና እክሎች ሊያመጣ የሚቺል ተፈጥሮ ነው።

ከዚህም ጋር ተያይዞ ከቀላል እሰከ ከባድ ተጓዳኝ የጤና ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል። ለምሳሌ፦

- የአይምሮ የእድገት ዉስንነት
- የአየር ቱቦ እና አተነፋፈስ ችግር
- የልብ አፈጣጠር ችግር
- የሆርሞን ችግሮች
- የደም ችግሮች
- የአንጀት ችግሮች

Down syndrome ምልክቶቹ ምንድናችው?

ዳውን ሲንድረም ያለበት/ባት ህፃን የሚከተሉት አካላዊ ምልክቶች ይታዩባቸዋል። ለምሳሌ፦

- ጠፍጣፋ እና ለየት ያለ የፊት ገፅታ
- ከፈት ያለ አፍ እና ተለቅ ብሎ የሚታይ ምላስ
- አጭር አንገት
- ዝቅ ያለ ጆሮ
- የአይን ቅድ (አከፋፈት) አቀማመጥ ወደ ላይ ከፍ ማለት
- የአይን ሽፋሺፍት ቆዳ መብዛት
- ደካማ/የላላ ሰውነት ጡንቻ
- አጭር እና ትንሽ መዳፍ
- አጫጭር ጣቶች
- አንድ ወጥ የሆነ የመዳፍ መስመር እና የመሳሰሉት ሊኖሩት ይችላሉ።

አዘጋጅ: ዶ/ር ፋሲል መንበረ (በቅዱስ ጳዑሎስ ሆስፒታል የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር)

@melkam_enaseb
ይቅርታ እንዴት እንጠይቅ?

ምን ያህሎቻችን ነን ይቅርታ ባለማረግ እና ይቅርታ ባለመጠየቅ ደስታችንን እየቀነስን ያለን?

ይቅርታ እንዴት እንጠይቃለን በሚለው ዙሪያ ትንሽ ለማለት ዳዳው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ሌላውን ሰው አስቀይመው ወይም ጥፋት አጥፍተው ይጸጸታሉ፡፡ ነገር ግን መጸጸትና ይቅርታ መጠየቅ ይለያያሉ፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ይቅርታቸውን ከአንገት በላይ ያደርጉና ተበዳዩን አዛኝ መስለው በከንፈር መጠጣ (lips service) ይሸነግሉታል፡፡ አልያም መልሰው እንደሚያጠፉ እርግጠኛ እየሆኑ እንኳን የይስሙላ ይቅርታ ይጠይቃሉ፡፡

ሺህ ግዜ እያጠፋ ከስህተቱ ለማይማር ሰው ይቅርታ ትርጉም የለውም፡፡ እንዲሁም ይቅርታን ለጥፋቱ መሸሸጊያ የመጨረሻ ምሽግ ያደርገዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የሌላውን ሰው ልብ ያደማል፡፡ ይቅርታው በተግባር ለውጥ ስለማይታጀብ ከአፍ አይዘልም፡፡ የዚህ ስሜት በእራሳችን ደርሶ ካላየነው በስተቀር ህመሙ አይሰማንም፡፡ ታዲያ አሳማኝ ይቅርታ እንዴት መጠየቅ ይቻላል?

አንድሪያ ብራንድ የተባለች ሳይኮሎጂስት የሚከተሉት ስድስት ነጥቦች ይቅርታን ለመጠየቅ ጠቃሚዎች ናቸው በማለት ትመክራለች፡-

1. ከልብ የመነጨ ይቅርታ መጠየቅ፡- 

የተበዳይ የመንፈስ ስብራት እኛም በግለሰቡ ቦታ ብንሆን ምን ያህል እንደሚሰማን በማሰብ ከውስጥ በመነጨ ስሜት ይቅርታን መጠየቅ፡፡

2. ስለበደሉት ነገር ዕውቅና መስጠትና ዳግመኛ ላለመበደል ኃላፊነትን መውሰድ፡- 

ስለአጠፉት ጥፋት እቅጩን መናገር “አውቃለሁ እንዲህ ማድረግ አልነበረብኝም፤ እኔ በእንተ ቦታ ብሆን ምን ያህል እንደሚሰማኝ እረዳለሁ፡፡ እባክህን ይቅር በለኝ!” በማለት ጥፋትን ለማረም ዝግጁ መሆንን ማሳየት፡፡

3. ዳግመኛ ላለመበደል ቁርጠኛ መሆን፡- 

የበደላችሁት ሰው ከጥፋታችሁ እንደተማራችሁ እንዲያውቅ ማድረግ፡፡ ይህንንም ዕለት ተዕለት በሚደረግ አግባቦትና ተግባር በግልጽ ማሳየትና ምንም ለውጥ ያላሳየን እንደሆን ወዳጆቻችን በግልጽ ቅሬታቸውን እንዲገልጹ ማድረግ፡፡

4. ይቅርታ የምትጠይቁት ሰው ለእናንተ ምን ያህል እንደሆነ መግለጽ፡-

ከበደላችሁት ሰው ጋር ያላችሁ ግንኙነት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ በማድነቅ መግለጽ፡፡

5. ይቅርታ መጠየቅ፡- 

ይቅርታ መጠየቅ በሁለታችሁ መሃል ስላለው ግንኙነት አስፈላጊነት የሚያስረዳ ሲሆን፤ በምላሹ ተበዳይ ይቅርታ ለማድረግ ጊዜን ይፈልግ ይሆናል እንደ ጉዳቱ መጠን፡፡ ምክንያቱም አንዳንድ ሁኔታዎች ይቅር የሚባሉ ነገር ግን በደሉ ሊረሳ የማይችል ስለሚሆን፡፡ “Forgiven but never forgotten” እንዲል የባህር ማዶ ሰው፡፡

6. ለውጥን በተግባር ማሳየት፡-

“የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ”  እንደሚባለው በአገረኛው ዘይቤ፤ ያጠፉትን ጥፋት ዳግመኛ ላለመተግበር ለእራስ ቃል ታማኝ መሆን፡፡ ይህም የአእምሮ ደውል በመውስጣችን በማቃጨል “እንዲህ ላለማድረግ እኮ እንዲህ ብለህ ቃል ገብተሃል” በተግባር ቃልህን አሳይ ማለት፡፡

በደል ያቆስላል ልብንም ይሰብራል፤ ይቅርታ ግን ቁስልን ይሽራል የተሰበረ ልብንም ይጠግናል፡፡ ይቅርታ እንታረቅ!

መልካም ጊዜ!

(አንቶኒዮ ሙላቱ)
#zepsychologist

@melkam_enaseb
⬆️ የጤናወግ በክለብሐውስ!

የአልኮል መጠጦች በጤና ላይ የሚያመጡትን ችግሮች ያውቃሉ?

እሁድ (መጋቢት 17) በ Clubhouse ላይ  የአልኮል መጠጦች በጤና ላይ ስለሚያስከትሉት ችግሮች በምናደርገው ውይይት ይቀላቀሉን።

ተጋባዥ እንግዶች፡

ዶ/ር ኃይለሚካኤል ደሳለኝ (የጨጓራ አንጀት እና የጉበት ህክምና ስፔሻሊስት)

ዶ/ር ዮናስ ላቀው (የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት)


ከምሽቱ 12:00 - 2:00 ሰዓት

ውይይቱን ለመቀላቀል እዚህ ይጫኑ

ክለብሐውስ ከሌሎዎት ለማውረድ እዚህ ይጫኑ

@melkam_enaseb
ጥልቅ ግንኙነት!

ከሰዎች ጋር ብሎም ከ አካባቢያችን ጋር ያለን ግንኙነት ምን ይመስላል?

ውጤታማ በሆኑና ውጤታማ ባልሆኑ ሰዎች መካከል ያለውን ልዩነት እንዲፈጠር ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል አንዱ ከሰዎች ብሎም ከ አካባቢያችን ጋር ያለን ግንኙነት ነው።

የውጤታማ ሰዎች መገለጫዎችና መታወቂያዎች ከሆኑት ነገሮች መካከል ጥልቅ ግንኙነት አንዱና ዋንኛው ነው።

ውጤታማ የሆኑ ሰዎች በግል ህይወታቸው፣ በማህበራዊ ግንኙነታቸው እንዲሁም በስራ ቦታቸው ሰዎችንና አካባቢያቸውን በተሻለ ሁኔታ የመረዳትና የማወቅ አቅምና ጥልቅ መሻት ያላቸው ናቸው።

በዚህም የተነሳ በቀላሉ ከሰዎች ጋር የሚግባቡና የተሻለ ምቹ፣ መተማመን የሞላበት የስራ ሁኔታን በስራ ቦታ እንዲሁም ጥሩ ማህበራዊ ግንኙነቶችን መፍጠር የሚችሉ ናቸው።

ብሎም በግል ህይወታቸው ማሳካትና ማድረግ የሚፈልጓቸውን ነገሮች በቀላሉ እንዲሳኩና ዕውን እንዲሆን በሚደረገው ሂደት ላይ አካባቢያቸውና በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች ደጋፊዎቻቸውና አጋዦቻቸው  ይሆናሉ።

ታዲያ በዙሪአያችን ካሉ ቤተሰቦች ጋር፣ ከስራ ቦታ ባልደረቦቻችን ብሎም በማህበራዊ ህይወታችን ከሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት ምን ይመስላል?

(ዳንኤል አያሌው)

@melkam_enaseb
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!

"ጥራት ያለው አካቶ ትምህርት ከኦቲዝም ጋር ለሚኖሩ ሁሉም ህፃናት እና ወጣቶች"

16ተኛው ዓለምአቀፍ የኦቲዝም ግንዛቤ ቀን በድምቀት ይከበራል! ቀኑ በኢትዮጵያ ለ21ኛ ጊዜ በጆይ ኦቲዝም ማዕከል ይከበራል።

ቀን፦ እሁድ መጋቢት 24፥ 2015 ዓ.ም
ሰዓት፦ ከጠዋቱ 3:00- 8፡30 ድረስ፣
ቦታ፦ ሳፋሪ ት/ቤት አካባቢ በሚገኘው ጆይ ኦቲዝሞ ልህቀት ማዕከል ግንባታ ሳይት ላይ።

ስለ ኦቲዝም ያገባኛል!

@melkam_enaseb
ከመናገርህ በፊት ሁለቴ አስብ!

ምላስ አጥንት የላትም አጥንት ትሰብራለች የሚለው ንግግር እውነት ነው። ሁሌም ቢሆን ከመናገርህ በፊት አስብ። የምትናገራቸው ቃላት ከድንጋይ በላይ ሰዎችን የማቁሰል አቅም አላቸው። በመናገርህ ተጸጽተህ ይቅርታ ብትጠይቅ ህመማቸውን ትቀንሰዋለህ እንጂ ጠባሳውን አታጠፋውም።

ስለዚህ፦

1ኛ. ስሜታዊ ስትሆን ላለመናገር ሞክር፦

ምክንያቱም ስሜታዊ ስትሆን ምክንያታዊ መሆን አትችልም። ይሄ የአዕምሮህ አሰራር (function) ነው። ስለዚህ ስሜታዊ ስትሆን ለብቻህ ጊዜ ለመውሰድና ራስህን ለማረጋጋት ሞክር። የምትናገረውን ነገር ብታዘገየው የሚፈጠር ተአምር የለም። ከተረጋጋህ በኃላ በችግሩ ላይ ታወራለህ።

2ኛ. የመሰለህ ሁሉ እውነት እንደሆነ አታስብ፦

ስሜት ሀሳባችን የሚፈጥረው ነገር ነው። ሰዎች የበደሉህ ስለመሰለህ በድለውሀል፣ ያጠፋ ስለመሰለህ አጥፍተዋል ማለት አይደለም። ስለዚህ የመሰለህ ሁሉ እውነት እንደሆነ ደምድመህ ከሰዎች ጋር ካወራህ ስሜታዊ ትሆናለህ። ስለዚህ ሁሌም ልክ ነኝ ከሚል መርህ ውጣና ልክ ላልሆን እችላለሁ ብለህ እያሰብክ በመረጋጋት እውነቱን ለማወቅ በሚፈልግ ልብ ጥያቄ ለመጠየቅና ሰዎችን ለመረዳት ሞክር።

ስሜታዊ አለመሆን አትችል ይሆናል። ከስሜት ተነስተህ አለመመለስ (react አለማድረግ) ግን ትችላለህ። ከስሜት ተነስቶ መመለስ ጊዜያዊ ሲሆን መዘዙ ግን የረጅም ጊዜ ነው። አስብበት።

ኤርሚያስ ኪሮስ (ካውንስሊንግ ሳይኮሎጂስት)

@melkam_enaseb
አማራጭ የአእምሮ ህክምና ተቋም- ሴሬኒቲ የአእምሮ ጤና!

ዶ/ር ቢንያም እና ዶ/ር እንግዳ የስነ ልቦና ህክምና ላይ የሚያተኩሩ (Psychologically inclined) የአእምሮ ህክምና ስፔሻሊስቶች ናቸው።

በሴሬኒቲ የአእምሮ ጤና አገልግሎት ማእከል የሚሰጠው የስነ ልቦና ህክምና ሰዎች የተሻለ የአእምሮ ጤንነት እንዲኖራቸው ከማገዝ ባሻገር ትርጉም ያለው እና ደስተኛ ህይወት እንዲመሩ ያግዛል።

በሴሬኒቲ የሚሰጡት አገልግሎቶች፦

- የአእምሮ ምርመራ (Diagnostic evaluation)
- የአስተሳሰብ መግራት ህክምና (Cognitive Behavioural Therapy)
- በስልክ የሚሰጥ የማማከር አገልግሎት (Tele psychiatry)
- በአእምሮ ጤና ዙሪያ ለድርጅቶች የማማከር አገልግሎት (Mental health Consultancy)

አድራሻ: ሽመክት የገበያ ማእከል 10ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 ብስራተ ገብርኤል።

ስልክ ቁጥር፡ +251946841200

#Mentalwellness

@melkam_enaseb
ከጎደለን ይልቅ የተሰጠን ይበልጣል!

በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ፖል ሪቻርድ አሌክሳንደር ይባላል። የተወለደው በ1946 ሲሆን በ6 አመቱ በፖሊዮ በሽታ ይያዛል። እንደ ፈረንሳዮች ከ 1952 ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በ "ብረት ሳንባ" ማሽን ውስጥ ይኖራል።

ከአንገቱ የላይኛው ክፍል በስተቀር መላ ሰውነቱ ፓራላይዝድ ነዉ። በምስሉ ላይ የምትመለከቱት የመተንፈሻ ማሽን ውስጥ ከገባ ዛሬ 71 አመት ሆኖታል። በዚህ ማሽን ምክንያት ነው በሕይወት ያለው። ከዚያ ለደቂቃ ከወጣ መተንፈስ ስለማይችል በህይወት አይቆይም። የሚያስገርመዉ ግን የህግ ትምህርትን ከታወቀ ዩንቨርስቲ ተመርቆ በህግ ሙያ ያስተምራል።

አንዳንድ ጊዜ የጤንነታችንን እና የሰላማችንን ዋጋ አንረዳዉም። እጅ እግር እያለን በሚረባዉ እና በማይረባዉ ነገር እናማርራለን። ይህ ሰዉ ግን ሁሌም በህይወት በመኖሩ ያመሰግናል።

ከጎደለን ይልቅ የተሰጠን ይበልጣል እና ሁሌም በህይወት በመኖራችን እናመስግን።

(ዶ/ር ኃይለልዑል)

@melkam_enaseb
April 2: አለምአቀፍ የኦቲዝም የግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ነው!
ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር
(Autism Spectrum Disorder)

የኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር የአንድን ሰው ማህበራዊ መስተጋብር፣ ተግባቦት እና ባህሪ የሚጎዳ እክል ነው።

እነዚህ እክሎች መለስተኛ፣ ከባድ፣ ወይም መካከለኛ ሊሆኑ ይችላሉ። ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር የቡድን ስም ሲሆን በውስጡ አምስት እክሎችን የያዘ ነው።

እስከ ቅርብ ጊዜ ባለሙያዎች የሚጠቅሷቸው የኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር አይነቶች አሉ። እነዚህም፦

1.አስፐርገርስ ሲንድሮም (Asperger's Syndrome)
2.ፐርቫሲቭ ዴቨሎፕመንታል ዲስኦርደር (Pervasive developmental Disorder)
3.ኦቲስቲክ ዲስኦርደር (Autistic Disorder)
4.ቻይልድሁድ ዲስኢንተግሬቲቭ ዲስኦርደር (childhood disintergrative disorder)
5. ሬት ሲንድሮም (Rett syndrome) ናቸው።

1. አስፐርገርስ ሲንድሮም
(Asperger's Syndrome)


ይህ የኦቲዝም አይነት ቀለል ያለ የሚባለው ነው። አስፐርገርስ የሆኑ ልጆች በጣም አስተዋይ እና የዕለት ተዕለት ሕይወታቸውን በተገቢው መንገድ ማስተናገድ የሚችሉ ይሆናሉ፡፡

- እነርሱ በሚወዷቸው ወይም በተሳቡባቸው ነገሮች ላይ የሚያተኩሩ ናቸው።
 
- እነዚህ ልጆች ማኅበራዊ ክህሎታቸው ላይ ተግዳሮት ይገጥማቸዋል።

- በተጨማሪም የንግግር እና ቋንቋ ክህሎታቸው ላይ እምብዛም እክል አይታይባቸውም።
 
2. ፐርቫሲቭ ዴቨሎፕመንታል ዲስኦርደር (Pervasive developmental Disorder)

- ይህ እክል ከአስፐርገርስ ሲንድሮም ካጋጠማቸው ልጆች የከፋ ሲሆን ነገር ግን ኦቲስቲክ ዲስኦርደር ካላቸው ልጆች የከፋ አይደለም፡፡

3. ኦቲስቲክ ዲስኦርደር (Autistic Disorder)

- ይህ የቆየ ቃል ያለው ከአስፐርገርስ እና ፐርቫሲቭ ዴቨሎፕመንታል ዲስኦርደር የበለጠ እክል ነው፡፡

- ይህም ተመሳሳይ የሕመም ምልክቶችን ያጠቃልላል ግን በጣም ኃይለኛ ደረጃ ላይ ይቀመጣል።

- ይህም የልጆችን ማህበራዊ መስተጋብር፣ ተግባቦት፣ ባህርይ፣ ስሜት እና ጨዋታ የሚጎዳ እክል ነው።

4. ቻይልድሁድ ዲስኢንተግሬቲቭ ዲስኦርደር (childhood disintergrative disorder)

ይህ እክል እጅግ በጣም ከባዱ እና እጅግ የከፋው የስፔክትረም ክፍል እንደሆነ ይገለፃል።

- ይህ እክል ያጋጠማቸው ልጆች በመደበኛነት የሚያድጉ እና ከዚያም ዕድሜያቸው ከ2 እስከ 4 ባለው መካከል ሲሆን ብዙ ማህበራዊ፣ ቋንቋ እና አእምሯዊ ክህሎቶችን በፍጥነት የሚያጡ ልጆች ናቸው።

- አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ልጆች የሚጥል ህመም ሊያጋጥማቸው ይችላል።

5. ሬት ሲንድሮም (Rett syndrome)
 
ሬት ሲንድሮም ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር ነው?

ሬት ሲንድሮም ያለባቸው ሕፃናት ብዙውን ጊዜ ከአቲዝም ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ባሕሪዎች አሏቸው። ባለሙያዎቹም ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር መካከል ካሉት ቡድኖች ውስጥ ይመድቡት ነበር፤ አሁን ግን በጄኔቲክ ሚውቴሽን ምክንያት እንደሚከሰት ስለታወቀ በማለት እንደ ASD አይቆጠርም፡፡

በማሕሌት አዘነ
(Speech & Language Therapist)

@melkam_enaseb
April 2: አለምአቀፍ የኦቲዝም የግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ነው!

በኦቲዝም ጥላ ስር የሚኖሩ ልጆች እንድናውቅላቸው የሚፈልጓቸው 10 ነገሮች፦

1. ካለብኝ ኦቲዝም ይልቅ ትኩረታችሁ እንደማንኛውም ልጅ/ሰው መሆኔ ላይ ይሁን።

2. በስሜት ህዋሳት አማካኝነት የማገኛቸው መረጃዎች ከአብዛኛዎቻችሁ በተለየ ሊረብሹኝ ይችላሉ።

3. አንዳንድ ነገሮች እንደተነገሩኝ ወዲያውኑ ላልረዳቸው እና ምላሽ ላልሰጥ እችላለሁ።

4. በየእለቱ በድግግሞሽ የሚደረጉ ነገሮችን መረዳት ይቀለኛል። ድግግሞሽ የምማርበት መንገድ መሆኑን እወቁልኝ።

5. ከሌሎች ልጆች ጋር አታነፃፅሩኝ።

6. እጃችሁን እየጎተትኩ የምፈልገውን የማሳያችሁ በቃላት ሀሳብን እንዴት እንደምገልፅ ስለማላውቅ ነው።

7. ስታስተምሩኝ በቃላት ብቻ ከምትነግሩኝ ይልቅ ብታሳዩኝ እና ብታስነኩኝ በቀላሉ ነገሮችን መረዳት እችላለሁ።

8. ከሚያቅተኝ ነገር ይልቅ የምችለው ላይ አተኩሩ።

9. ከሌሎች ጋር መሆን እፈልጋለሁ ግን እንዴት ማድረግ እንዳለብኝ አስተምሩኝ።

10. ያለምክንያት ውደዱኝ ይገባኛልና።

በመአዛ መንክር (ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት)

@melkam_enaseb
የጆሀሪ መስኮቶች: የማንነታችን አራቱ ክፍሎች!

የጆሀሪ መስኮቶች ከሰው ጋር እንዲሁም ከራሳችን ጋር ያለንን ግንኙነት በተሻለ ለመረደት የሚያግዝ ንድፍ ነው፡፡ ጆሀሪ ስያሜውን ያገኘው ንድፉን በጋራ ከፈጠሩት የስነ ልቦና ባለሞያዎቹ ጆሴፍ ለፍት እና ሀሪንግተን ኢንግሀምን ስም በማቀናጀት ነው፡፡ ማንነታችን በአራት ሊከፈል ይችላል፦ ግልፅ፣ ድብቅ፣ የተሰወረ እና ጨለማ፡፡

ግልፁ ማንነት፦

ይሄኛው ስለራሳችን እኛም ሌላውም ሰው የሚያውቀው ሲሆን ድርጊቶችን፣ እውቀትን፣ ክህሎትን ያጠቃልላል፡፡ ስለዚህኛው ማንነታችን ከሰዎች ጋር ለመነጋገር ችግር የለብንም በተጨማሪም ሰዎች ስለዚህ የማንነታችን ክፍል በሚሰጡት አስተያየት በብዛት እንስማማለን፡፡

ድብቁ ማንነት፦

ይህ ማንነት ራሳችን የምናውቀው ሲሆን ከሌሎች የተደበቀ ነው፡፡ በዚህ መስኮት ውስጥ ያሉ ማንነቶቻችንን ስለምናፍርባቸው ወይም የግል ህይወታችን ስለሆኑ ተጋላጭ እንዳንሆን ከሌሎች እንደብቃቸዋለን፡፡ በተመሳሳይ በትህትና ምክኒያት ሰዎች እንዲያውቁ የማንፈልጋቸው ችሎታዎቻችን እውቀታችንንም ያካትታል፡፡

የተሰወረ ማንነት፦

ይሄኛው ሌሎች ሰዎች የሚያዩት ከኛ ግን የተሰወረው ማንነት ነው፡፡ ምክኒያታዊ እንደሆንን እናስብ ይሆናል ሰዎች ግን ግትር እንደሆንን ነው የሚያውቁት፡፡ ወይም ራሳችንን 'ምንም እንደማያውቅ' ልናስብ እንችላለን ሰዎች ግን በጣም ብልህና አስተዋይ እንደሆንን ሊረዱ ይችላሉ፡፡ በዚህ መስኮት ውስጥ ነው ሰዎች ቃላችን እና ድርጊታችን እንደሚለያይ የሚያስተውሉት፡፡

ጨለማ (የማይታወቀው) ማንነት፦

ይህ ማንነት በራሳችንም ሆነ በሌሎች የማይታወቅ ክፍል ነው፡፡ ጥሩም ጥሩ ያልሆኑ ሀሳቦች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡

በአጠቃላይ የ ጆሀሪ መስኮቶቸ ራሳችንን ለመረዳት ከዚያም ለማገጎልበት እንዲሁም ከሌሎች ሰዎች ጋር የሚኖረንን ግንኙነት ለማሻሻል የሚያግዝ ንድፍ ነው፡፡

ዶ/ር ዮናስ ላቀው (የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት)

@melkam_enaseb
የለውጥ ሂደቶች!

ሰዎች በህይወት ዘመናቸው በተለያዩ የለውጥ ሂደቶች ያልፋሉ። ለውጥ በአንድ ጀምበር አይመጣም ሂደት ነው። ብዙ መውደቅና መነሳቶች፣ ብዙ ተስፋ ሰጪና ተስፋ አስቆራጭ ጊዜያቶች ታልፈው ነው ስኬት ላይ የሚደረሰው። ምናልባት አንዳንዶቹ እድል፣ ብርታት ወይንም ብልጠት በታከለበት ሁኔታ ነገሮች ቶሎ ተፈጽመውላቸው ይሆናል።

እንደ Prochaska እና DiClemente እይታ ከሆነ መለወጥ በሽክርክሪት ይመሰላል።

ለዛሬ ለዚህ ጽንሰ ሃሳብ አስረጂ እንዲሆነን ሱስ የማቆም ሂደትን እንመለከታለን፦

Pre-contemplation/ቅድመ ውጥን:-

በዚህ የለውጥ ሂደት ላይ ያሉ ሰዎች ስለችግሮቻቸው ያላቸው ግንዛቤ እምብዛም ነው።

ብዙ ሱስ አስያዥ እጾችን የሚጠቀሙ ግለሰቦች፣ ሱሱ በሚታይ ሁኔታ አሉታዊ ተጽዕኖ እያደረሰባቸው ቢሆን እንኳን፡ ችግሩን አምኖ ከመቀበል ይልቅ፡ ምንም ችግር እንዳልተከሰተባቸው በመካድ (denial) እና ሱሰኛ እንዳልሆኑና ማቆም ከፈለጉ በየትኛውም ጊዜ ማቆም እንደሚችሉ ሲናገሩ ይስተዋላል። በዚህ ወቅት የባለሙያው ሚና እነዚህን ጉዳቶች እንዲያስተውሏቸው (impact assessment) እጽ ተጠቃሚ መሆናቸው የጠቀማቸውንና የጎዳቸውን ነገር (pros and cons) እንዲዘረዝሩ በማድረግ ነገሮችን እንዲያሰላስሉ መፍቀድ ይሆናል።

Contemplation/ውጥን-

በዚህ የለውጥ ሂደት ላይ ያሉ ሰዎች ስለ ችግሩ እውቅና ይኖራቸዋል። ንግግሮቻቸው በመለወጥና ባለመለወጥ ሃሳቦች መሃል ይዋልላሉ።

'እጹን መጠቀሜ ከባለቤቴ ጋር እንዳጋጨኝ አውቃለሁ: ግን ደሞ ጓደኞቼን ሳገኝ መጠቀሜ አይቀርም: የክፋ ቀን ወዳጆቼን ማጣት ደሞ አልፈልግም' አይነት ንግግሮች ይስተዋላሉ።

ብዙዎቹ የዕጽ ተጠቃሚዎች እዚህኛው ደረጃ ሲደርሱ ወደ ባለሙያ እርዳታን ለማግኘት የማቅናት እድላቸው ይጨምራል።

በዚህ ወቅት የባለሙያው ሚና ወደ መለወጥ ሃሳቦች እንዲዘነብሉ ማበረታታት ይሆናል።

የችግሩን ግዝፈት እንዲረዱ እና ለውጥ ለማምጣት ብቁ እንደሆኑ እንዲገነዘቡ በማድረግ ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ማሻገር ይቻላል።

Preparation/ የዝግጅት ምዕራፍ

በዚህ ደረጃ ላይ ሲደርሱ የመለወጥ ውጥናቸው ሚዛን መድፋት ይጀምራል።

Action/ ተግባራዊ የመለወጥ ስራዎች

የለውጥ ስራዎቻቸው መታየት ይጀምራሉ። የሚጠቀሙትን ሱስ መጠን ሲቀንሱ: ከፍ ሲልም ሲያቆሙት ይስተዋላል።

በዚህ ሂደት ውስጥ ያሉ ሰዎች: የለውጥ ሂደቱን የሚያሳልጡ መሰረታዊ ክህሎቶችን እንዲማሩ ይደረጋል።

Maintenance/ ለውጥን ማስቀጠል

በዚህ ሂደት ላይ ያሉ ሰዎች: የቀድሞ ባህርያቸው እንዳያገረሽ ስራን ይፈልጋል።

Relapse/ ወደ ቀደመ ባህርይ መመለስ

ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች ወደቀደመ ባህርያቸው ሊመለሱ ይችላሉ። እነዚህ ምክንያቶችን መለየትና መስራት መቋቋምያ መንገዶችን መፈለግ ያሻል።

የሱስ ማቆም ህክምናዎች እነዚህን የለውጥ ሂደቶቾን መሰረት አድርገው ይካሄዳሉ።

- በግል ወይንም በቡድን ሊሰጡ ይችላሉ።
- የሱስ ማቆም ህክምናን ለማግኘት የተለያዩ የህክምና ተቋም አማራጮች በመዲናችን ይገኛሉ።

Reference
- Curriculum based motivational group by Ann Fields and Internet

ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው
(የአእምሮ ህክምና ሬዚደንት ሃኪም)

@melkam_enaseb
የስራ እና ድርጅታዊ ሳይኮሎጂ ስልጠና!

Certificate Course on Work and Organizational Psychology!

For further details and registration, use the link below! ⬇️

https://forms.gle/L8ghqgECiBp6nQeS9

+25111662437/ +251940200454

(Aha Psychological Services)

@melkam_enaseb
ይቻላል!

የይቻላል አዎንታዊ አስተሳሰብን ማዳበር ይቻላል፡፡ የ Positive psychology ባለሙያዎች ይህንን ሂደት “Learned Optimism” የሚል ስያሜ ሰጥተውታል፡፡

ያለፈ ጊዜያችን መጪውን ጊዜ እንዳይወስን መወሰን አስፈላጊ ነው፡፡ ውድቀታችሁ የወደፊት ስኬታችሁን እንዳይወስን መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው፡፡ “ምን እባክህ ከዚህ በፊትም እኮ ሞክሬ አልሆነልኝም! አሁን ምን የተለየ ነገር ይኖራል ብለህ ነው?” የምትሉ ከሆነ ያለፈ ውድቃታችሁ እስር ቤት ውስጥ አሁንም በገዛ ፈቃዳችሁ ለመኖር ወስናችኋል ማለት ነው፡፡

ጥቂት እውን መሆን ያላቻሉ ህልሞቻችሁን ብቻ መሠረት አድርጋችሁ ዓላማ ያለው ሕይወት ከመጓዝ ወደ ኋላ አትበሉ፡፡ ዓለም በብዙ አዳጋች ሁኔታዎች የተሞላች ነች፡፡ እነዚህ እንቅፋቶች መንገድ ላይ ሲያጋጥሟችሁ ወድቃችሁ አትቅሩ፡፡ በክረምት ወራት ጭቃ በየቦታው ይኖራል፡፡ አንድ እና ሁለት ቀን ወድቃችሁ ስለቆሸሻችሁ ወይም ስለተጎዳችሁ ወይም ሰው ስለሳቀባችሁ “ከዚህ በኋላ ከቤቴ ንቅንቅ አልልም” አትሉም መቼም፡፡ ቁም ነገሩ ከዚህ በፊት የወደቃችሁበትን ምክንያት ማወቅ እና ዳግመኛ ላለመውደቅ ጥንቃቄ አድርጎ ጉዞን ወደፊት መቀጠል ነው፡፡

ሴሊግማን አዎንታዊ መሆንም ሆነ አዎንታዊ የሆኑ ነገሮችን ማግኘት ሕይወትን ከምንረዳበት ዘዴ (Explanatory Style) ጋር የተያያዘ ነው ይላል፡፡ ይህ ዘዴ ራሳችንን እና ዓለምን አእምሮአችን ውስጥ የምንተረጉምበት መንገድ ነው፡፡ ይህንን እይታችንን፣ አረዳዳችንን፣ አተረጓጎማችንን አወንታዊ ማድረግ መቻል በየትኛውም ዘርፍ ቢሆን አንድ የስኬት መንደርደሪያ ነው፡፡

ነጋሽ አበበ (ሳይኮሎጂስት እና ፀኃፊ)

@melkam_enaseb
የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተጽእኖ!

የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በአግባቡ ጥቅም ላይ ከዋሉ፣ ለመማር፣ ለመግባባት እና ለመዝናናት ጥሩ መድረኮች ናቸው።

ነገር ግን የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በልጆች ላይ የሚያመጡት አሉታዊ ተፅዕኖ በቀላሉ የሚታይ አልሆነም። ምክንያቱም እነዚህ መድረኮች ከልክ በላይ ጥቅም ላይ ከዋሉ ለሳይበር ጉልበተኞች ጥቃት/cyberbulling/፣ ለጭንቀት፣ ለድብርት እና የእንቅልፍ መዛባትን ለመሳሰሉ የጤና ችግሮች ሊጋለጡ ይችላሉ።

ልጆች ተፅዕኖውን የሚረዱበት የአዕምሮ ብስለት ደረጃ ላይ ባለመሆናቸው ችግሩ በእነሱ ላይ የበረታ ይሆናል። የኒውዮርክ፣ የቨርጂኒያ፣ የሳን ዲዬጎ ዩኒቨርሲቲዎች እና ደብሊው ብራድፎርድ ዊልኮክስ የቤተሰብ ጥናት ተቋም ከማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አጠቃቀም ጋር በተገናኘ ባደረጉት ጥናትም መድረኮቹ በልጆች የአእምሮ ጤና ላይ ከፍ ያለ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን አመልክተዋል። ጉዳቱ በተለይም በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ባሉ ልጃገረዶች ከፍተኛ ነው ተብሏል።

ተመራማሪዎቹ ማህበራዊ መነጠል እና ብቸኝነት፣ ድብርት፣ ከፍ ያለ ጭንቀት እና ራስን የማጥፋት ሀሳቦችን እና ሌሎች ከማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ጋር የተገናኙ ተፅዕኖዎችንም ጠቁመዋል። ራስን ከሌሎች ጋር ማወዳደር፣ በራስ ስራ ላይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ በዲጅታሉ ዓለም ባልተጨበጡ ነገሮች መጠመድም ሌላው ችግር ነው።

በመሆኑም ልጆች ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን እንዲጠቀሙ ወላጆች ከመፍቀዳቸው በፊት ተግባራቶቹን፣ የግላዊነት መመሪያዎችን እንዲሁም የእድሜ ገደቦችን ማወቅ አለባቸው። በአጠቃቀም ወቅትም የወላጆች ቁጥጥር ወሳኝ ነው። ከልጆች ጋር ጥብቅ ትስስር መፍጠር እና አንዳንዴም አብሮ በመሳተፍ አቅጣጫ ማሳየት እና ማስተማር በባለሙያዎች የሚመከር ነው። (DW)

@melkam_enaseb
ጥንካሬን ማወቅ!

በዚህ ርዕስ ላይ ስልጠና ስሰጥ እስካሁን የተረዳሁት አንድ ነገር አለ፡፡ ብዙዎቻችን ስለ ጥንካሬያችን ሳይሆን ስለ ድክመታችን ብዙ እንደምናውቅ ነው፡፡ ይኸም ደግሞ ደካማ፣ የማንችልና የበታች እንደሆንን እዲሰማን አድርጎናል፡፡

ህይወታችንን ከፍ አድርገን ለመኖር ድክመቶቻችን ላይ ትኩረት ማድረግ እንደ መፍትሄ እንጠቀመዋለን፡፡ ይህም ብዙ ውጤት የማያመጣ መፍትሄ ነው፡፡

ስለ ድክመቶቻችን ብቻ በማሰብና ለማሻሻል በመሞከር ብዙ ጊዜያችንን ማጥፋት ውጤት የማያመጣ ከሆነ፤ ታዲያ ውጤት የሚያመጣው ምንድን ነው?

1. ስለ ድክመታችን የምናውቀውን ያህል ስለጥንካሬያችን ማወቅ አለብን፦

ምን ተሰጥኦ አለኝ? ምን ችሎታዎች አሉኝ? ምን ማድረግ ያስደስተኛል? ምን ነገሮች ላይ ሃላፊነት እወስዳለሁ? ራሳችንን ጠይቀን ጥንካሬዎቻችንን ማወቅ የመጀመሪያው መፍትሄ ነው፡፡

2. ድክመቶቻችንን መቀበል አለብን፦

ድክመቶቻችንን ለመቀየር ከመታገል ይልቅ መቀበልና ማወቅ በቂ ነው፡፡ ለመቀየር ስንታገል አቅማችንን ወደታች እያወረደብን ይመጣል፡፡

3. ጥንካሬዎችንን ካወቅን በኋላ በየቀኑ መጠቀም መቻል፦

ጥንካሬዎቻችንን የሚያድጉት በየቀኑ ስንጠቀምባችው ነው፡፡ ዛሬ የትኛውን ጥንካሬዬን ተጠቀምኩበት? ራስን መጠየቅ።

4. አዳዲስ ጥንካሬያችንን መፈለግ፦

በየጊዜ የማናውቀውን ጥንካሬ እናገኛለን፡፡ ይህም የሚሆነው አዲስ ነገሮችን ስንሞክር፣ ከአዲስ ሰዎች ጋር ስንገናኝ፣ ስንወስን ወዘተ. ነው፡፡

ጥንካሬዎቻችንን ላይ ትኩረት አደርገን መስራት ከቻልን ድክመቶቻችንን ማሸነፍ እንችላለን፡፡

ተመስገን አብይ (የስነልቦና ባለሙያ)

@melkam_enaseb
2025/07/08 12:32:31
Back to Top
HTML Embed Code: