Telegram Web Link
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም በዓል!

@melkam_enaseb
ጤና ይስጥልኝ፤ ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው አደረሳችሁ!

በአሉን ስናከብር ከዚህ የሚከተሉትን በማስታወስ ይሁን፤

1. ነብሰ ጡር ሴቶች በቤት ውስጥ የሚዘጋጁም (ጠላ፣ ጠጅ፣ አረቄ) ሆነ በፋብሪካ የሚመረቱ (ቢራ፣ ወይን፣ ውስኪ የመሳሰሉት) የአልኮል ይዘት ያላቸውን መጠጦች መጠቀም በፅንሱ አዕምሮ ላይ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ መጠጣት የለባቸውም።

2. የሀገራችን ህግ እድሜያቸው ከ 21 አመት በታች ለሆኑ የአልኮል ይዘት ያላቸውን መጠጦች መጠጣት እንደሚከለክል ያውቃሉ?

3. ጠጥቶ ማሽከርከር የአዕምሮ እና የአካል ቅንጅትን (coordination) በማዛባት እና የመወሰን ፍጥነትን (reaction time) በማዘግየት ለከባድ የተሽከርካሪ አደጋ ስለሚዳርግ ጠጥቶ ከማሽከርከር ይታቀቡ!

በአሉ የሰላም፣ የደስታ፣ የጤና ይሁንላችሁ!

ፕ/ር ሰለሞን ተፈራ (አዲክሽን ሳይካትሪስት፤ የሬናሰንት ሪሃብ ሴንተር መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ)

@melkam_enaseb
በወጣቶች ላይ ሱስ የሚያደርሰው ተጽዕኖ!

አንድ ወጣት በጉርምስና ዕድሜ ላይ እያለ ባዮሎጅካዊ (ስነህይወታዊ) እና ሥነ ልቦናዊ ለውጦች ይኖሩታል።

በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶች አንጎል እያደገ መሄዱን የሚጠቁሙ አካላዊ ለውጦች ብቻ ሳይሆኑ ይበልጥ ውጤታማ በሆነ መንገድ መሥራት የሚችሉባቸውን መንገዶችም እያዳበረ ነው። ይህ ዘዴ በተለያዩ የአንጎል ክፍሎች መካከል አላስፈላጊ የሆኑ ሲናፕሶችንና እርስ በርስ የሚገናኙትን ነገሮች ማስወገድ ነው።

እንዲህ ዓይነቱ የአእምሮ መገረዝ ለአካለ መጠን የደረሰ አንጎል ይበልጥ ትኩረት ሰጥቶ ውጤታማ እንዲሆን ያስችለዋል፡፡ በጉርምስና ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶች ትልቅ ሰው ሲሆኑ ለጤናማ አዕምሮ አሰራር በጣም አስፈላጊ ናቸው። 

በመሆኑም በእነዚህ ዓመታት የጤናማነት ደረጃን ጠብቆ መቀጠል አስፈላጊ ነው። አደገኛ መድኃኒቶችንና ዕፆችን አላግባብ መጠቀም አንጎል በአጭር ጊዜ ውስጥ ሥራውን ለማከናወን ባለው ችሎታ ላይ ተጽዕኖ ከማሳደሩም በላይ ለረጅም ጊዜ ተገቢውን እድገት እንዳይኖር ሊያደርግ ይችላል።

የጉርምስና ወቅት በነርቭ ልማት ውስጥ ልዩ ጊዜ ነው። በዚህ ወቅት ወጣቶች አልኮል እና ማሪዋና መጠቀም የተለመደ ነው። በቅርብ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በጉርምስና ዕድሜ ላይ ያሉ ንጥረ ነገሮችን ተጠቃሚዎች የአንጎል አሠራር መለኪያዎች ላይ ያልተለመዱ ነገሮችን ያሳያሉ ይህም ከጊዜ ወደ ጊዜ በነርቭ ሴሎች ውስጥ ካለው ለውጥ ጋር የተያያዘ ነው፡፡

በማደግ ላይ ያለው አንጎል ለኒውሮቶክሲክ ተጽእኖዎች የበለጠ የመቋቋም ችሎታ ሊኖረው ይችላል፡፡ በወሳኝ የነርቭ እድገት ወቅት ለአልኮል እና ለአደንዛዥ እጾች መጋለጥ የአዕምሮ ብስለት ተፈጥሯዊ ሂደትን እና የአዕምሮ እድገት ቁልፍ ሂደቶችን ሊያቋርጥ ይችላል፡፡ 

እንደ እውነቱ ከሆነ የጉርምስና ዕድሜ በአንጎል ላይ ለአልኮል ተጽእኖ የተጋለጠበት ወቅት ሊሆን ይችላል፡፡ ከእነዚህ አልኮል እና አደንዛዥ እጾች ጋር የተያያዙ በነርቭ ላይ የሚከሰቱ የግንዛቤ ጉድለቶች በቀጣይ እውቀት፣ ሙያ እና ማህበራዊ ተግባራት ላይ እስከ ጎልማሳነት የሚዘልቅ ጎጂ አንድምታ አላቸው።

ከአልኮል እና አደንዛዥ እጾች ጋር የተያያዙ በነርቭ ላይ የሚከሰቱ የግንዛቤ ጉድለቶች በቀጣይ አካዳሚያዊ፣ ሙያዊ እና ማህበራዊ ተግባራት ላይ እስከ ጎልማሳነት የሚዘልቅ ጎጂ አንድምታዎች አሏቸው።

ስለዚህ ከመጠን በላይ የመጠጣት እና የአደንዛዥ ዕፅ አጠቃቀም የኒውሮኮግኒቲቭ /የአስተሳሰብ/ አሉታዊ ተጽእኖ ያስከትላል፡፡ አሁን ላይ ያሉት ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በጉርምስና ወቅት ከመጠን በላይ መጠጣት በጉርምስና ዕድሜ ላይ ባሉ ወጣቶች አስተሳሳብ ተግባር ላይ ስውር፣ ግን ጉልህ፣ ጎጂ ውጤት መኖሩን ነው፡፡

ጥናቶች እንዳረጋገጡት በጉርምስና ዕድሜ ላይ የሚገኙ አልኮል ጠጪዎች የማስታወስ ትኩረት መቀነስ እና ፈጣን የመረጃ አያያዝ እና የቋንቋ ብቃት ጉድለቶች እና የአካዳሚክ ስኬት ጉድለቶች በተለይም የወደፊት እቅድ፣ ህይወት የመምራት ላይ ከፍተኛ ተጽኖ አለው (SF Tapert • 2004/ &/Cortés Pascual • 2019)፡፡

በቅርብ ጊዜ በተደረገ የማሪዋና አጠቃቀምን በተመለከተ ከአራት ሳምንታት መታቀብ በኋላም ቢሆን በመደበኛነት ማሪዋና የሚያጨሱ  በትምህርት አፈጻጸም ፈተናዎች፣ በግንዛቤ መለዋወጥ፣ በእይታ ቅኝት፣ ስህተት በመስራት ትውስታ ላይ ደካማ አፈጻጸም አሳይተዋል። ይህ የሚያሳየው አደንዛዥ እጾችን ተጠቅመን ስናቆም እንኳ በአእምሮአችን ላይ ተጽእኖ መኖሩን ነው፡፡

(ዶ/ር ቤተል ጥበቡ)
#AMSH

@melkam_enaseb
"ስለ አእምሮ ጤና ያገባኛል" የፖናል ውይይት!

አካላዊ ጤንነታችንን መንከባከብ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን፤ አካላዊ ጤናችንን ስንንከባከብ ስለ አእምሮአዊ ጤንነታችንም ትኩረት መስጠት አለብን!

ውመን ኢኮኖሚክ ኢምፖወርመንት አፍሪቃ ስለእምሮ ጤና ያገባኛል በሚል መፈክር በUS Embassy Satchmo Center April 26, 2023 የውይይት መድርክን አዘጋጅተናል::

በኢትዮጵያ የአእምሮ ደህንነት ላይ ያተኮረ የውይይት እና የኔትወርክ ዝግጅት ለመቀላቀል በምስሉ ላይ ባለው Qr Code የመዝገቡ እና ይቀላቀሉን።

ያሉን ቦታዎች እጅግ ውስን በመሆናቸው ለመሳተፍ ከፈለጉ እባክዎን ቀድመው ይመዝገቡ እና በውስጥ መስመር ያናግሩን::

በውይይት መድረኩም ከአእምሮ ጤና ባለሞያዎች፣ የማህበራዊ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና ከሁሉም በላይ መልካም አስተሳሰብ ካላቸው ግለሰቦች ጋር ለመማማር እና ለመተዋወቅ ጥሩ መድረክ መሆኑን እናምናለን::

N.B; መመዝገቦን ማረጋገጥዎን ያስታውሱ:: የመሳተፊያ ቦታ እንደተያዘሎ በእጅ ስልኮ መልእክት እንደደረሶ ማረጋገጥ ይችላሉ:: በእለቱም መታወቂያዎን ይዘው መምጣትዎን አይርሱ።

ለአእምሮ ጤናችን ቅድሚያ እንስጥ እና ጤናማ እና ደስተኛ የሆነች ኢትዮጵያን በጋራ እንስራ!

(WOMEN’S ECONOMIC EMPOWERMENT AFRICA)

@melkam_enaseb
አጋጣሚን የመጠቀም ቁልፍ!

1. ጨለምተኝነትን አስወግድ

“ጨለምተኛው በፊቱ ባገኘው እድል ሁሉ ውስጥ ያለውን አስቸጋሪ ነገር ያያል፤ አዎንታዊው በገጠመው ችግር ሁሉ ውስጥ ያለውን እድል ይመለከታል” - Winston Churchhill

የገጠመህን ሁኔታ ሁሉ በምን እይታ እንደምታየው የመምረጥ ሙሉ መብት አለህ፡፡ ጨለምተኝነትን ከመረጥክ እይታህን ሁሉ የማደብዘዝ ተጽእኖ ያስከትልብሃል፡፡ ምርጫህ ሁሉ ጤና ቢስ ይሆናል፡፡ አዎንታዊነትን ስትሞላ ግን ከክፉ ነገር ውስጥ እንኳ ሳይቀር መልካም ነገርን ጨምቆ ለማውጣት የሚያስችልን ብሩህ እይታ ታገኛለህ፡፡

2. ሁኔታዎችን ወደ መኖር አምጣቸው

“አንዳንድ ሰዎች ነገሮችን ወደመኖር ያመጣሉ፣ ሌሎች ነገሮች ወደመኖር ሲመጡ ዝም ብለው ያያሉ፣ ሌሎች ደግሞ በሚከናወነው ነገር ከመደነቅ ያለፈ ነገር የላቸውም” –Unknown Source

ከየትኛው ወገን ነህ? ሰዎች ባላቸው ብቃት ተጠቅመው ከስኬት ወደ ስኬት ሲዘልቁ የእነሱን ነገር እንደ ድራማ ከሚያዩት ነህ? ሰዎች ከአንዱ ክንዋኔ ወደሌላኛው ሲሻገሩና ጊዜአቸውን ለመልካም ስኬት ሲያውሉት ከሚያደንቁትና ከሚያወሩት ነህ? ወይስ ጨዋታው መካከል ነህ? አሁን ላነሳሳህ፣ ጨዋታው መካከል ግባ! በመጀመሪያ ራስህን አነሳሳ፤ በመቀጠልም ነገሮችን ቀስቅሰ፡፡ የሌለው ነገር በአንተ ምክንያት ወደመኖር ይምጣ፡፡ ያለው ነገር በአንተ ምክንያት ወደ ተሻለ ደረጃ ይደግ፡፡ 

3. እጥረትን ወደ ገቢ ምንጭ ቀይር

“ችግራችን የችግር መኖር አይደለም፡፡ ችግራችን፣ ችግር በፍጹም መከሰት የለበትም ብለን አስበን ችግር መኖሩን እንደችግር መቁጠራችን ነው” – Theodore Rubin

አንድ ችግር እስካሁን ሊለወጥ ካልቻለና መፍትሄ የሚሰጠው ሰው ስላልተገኘ ነው፡፡ መፍትሄ ሰጪ የማይገኝበት ምክንያት ደግሞ ችሎታው ያለው ሰው ሲጠፋ ወይም ደግሞ ችሎታው እያለው ፈቃደኝነቱ ያለው ሰው ሲታጣ ነው፡፡ ሁኔታው ግን ምን አይነት እድል ሊሰጥህ እንደሚችል አስበው፡፡ መፍትሄ ፍጠርለትና አንድ ነገር አድርግ፡፡

(“25 የስኬት ቁልፎች” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

@melkam_enaseb
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1444’ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ዒድ ሙባረክ!

@melkam_enaseb
''እችላለሁም አልክ አልችልም ትክክል ነህ'' ሄንሪ ፎርድ

ሰዎች ስለራሳችን፣ ስለሌሎች፣ ስለ አለም፣ ስላለፈው፣ ስለመጪው የተለያዩ ሃሳቦችን እናስባለን።

ከሁሉም በላይ ግን ስለራሳችን የምናስባቸውና የምናሰላስላቸው ሃሳቦች ወሳኝና መሰረታዊ ናቸው።

ማንኛውም በህይወት የምናገኛቸው ነገሮች የሃሳቦቻችንና የአመለካከቶቻችን ውጤቶች ናቸው።

የምንጎዳው፣ የምንሰበረው፣ የምንፈራው፣ የምናጣው፣ መጥፎ የሚባሉት ስሜቶች፣ በአጠቃላይ የሚፈጠሩት በሀሳባችን ነው።

ሃሳቦቻችን ውስጣችን በሚፈጠረው የእርግጠኝነት ስሜት ልክ ተራም ጠንካራም ሊሆኑ ይችላሉ።

ሃሳባችን በጠንካራ ስሜት ሲደገፍ እምነት ሆኖ በተግባር ስለነገሮች ያለንን አቋም እንድናጸባርቅ ያደርጋል።

ስለራሳችን፣ ስለሌሎችና ስለ አለም ያሉን እምነቶችና አመለካከቶች ፍላጎቶቻችንንና ግቦቻችንን እንድናሳካ የሚያስችሉ፣ ከምንፈልገው ቦታ የሚያደርሱ ናቸው ወይስ ከግብና ፍላጎቶቻችን ጋር የሚቃረኑና ጎታች ናቸው?

(ዳንኤል አያሌው)

መልካም ቀን!

@melkam_enaseb
ከመሸነፍ ሃሳብ ለመውጣት!

Reframing /የሃሳብ ምህዳርን ማስፋት/ የሚል ጸንሰ ሃሳብ “አልችልም፣ ደካማ ነኝ’’ የሚልን የሽንፈት ሃስብ ለመግታት በዶ/ር ቦሪሴንኮ /D.R Borysenko/ የምትባል ከፈተኛ የአዕምሮ ሳይንስ ተመራማሪ እና የህክምና ባለሙያ እንደሚከተለው አብራርታዋለች።

የሀሳብን ምህዳርን ማስፋት/Reframing/ ማለት እንድን ነገር የምናይበት እይታን በተለየ /Frame/ ማየት ማለት ነው፤ በአጭሩ.. አንድ ሰው አለምን የሚያይበት መንገድ ከአስተዳደጉ፣ ከእምነቱ፣ ከተሞክሮው የሚመነጭ መሆኑ አይካድም፣ ነገር ግን የአለማችን ምህዳር ከአንድ ሰው እንደሚሰፋም የማይካድ እውነታ ነው። ልክ መኪና ዉስጥ ቁጭ ብለን በተለያዩ መስኮቶች ጭንቅላታችንን እያዟዟርን አካባቢያችንን እንደምንቃኝ ሁሉ ከሽንፈት ሃሳባችን ለመውጣት ሃሳባችንን እንደገና ማቀናበር ይረዳል።

ዋናው ነገር በአንዷ /Frame/ ብቻ ማየትን ማቆም ነው፤ “ለመኪና የጎን መስታወት የተገጠመለት አደጋን ለመከላከል ስለሚያግዝ አይደል፤” ለችግራችንም በተላያዩ አንግሎች ማየት ስንጀምር በርካት ውሳኔዎች መወሰን እንችላለን፤ እንደ ምሳሌ... “እህቴ በኔ ህይወት ውስጥ በተደጋጋሚ ጣልቃ ትገባለች...... “የሚለውን ሃሳብ በአዉናታዊ ብንቀይረው..“እህቴ እኔን ለመጠበቅ ብዙ ትጥራለች.....” ቢሆን፤ ሁለቱ ጽንሰ ሃሳቦች በስሜት እጅግ የተለያዩ ይሆናሉ። ለዚህ መለያየት ዋነኛውን ሚና የሚጫወተው እኛ ለድርጊቱ የምንሰጠው አስተያየት/Perception/ ነው። በሀብታም እና ድሃ፣ በደፋር እና ፈሪ መሃል ያለውም ይህ ነው፤ የሃሳብ ምህዳር ልዩነት።

“አልችልም፣ ደካም ነኝ” የሚል ሃሳብ ውስጥ እንደንቆይ የሚያረገን ምንድን ነው?

1. ግትርነት| stubbornness

እኔ ያልኩት ካልሆነ፣ መንገዱ በዚህ ብቻ ነው የሚሉ መሰል አስተሳሰቦች፣ ሂስን ለመቀባል ፈቃደኛ አለመሆን ወይም መፍራት ምህዳርን የሚያጠብ መሆኑን እንረዳለን። እድሚያችን እይገፋ ሲመጣ ሃሳባችን ከእውነታው ጋር እንደሚጋጭ እነረዳለን። ይህ እንዳይሆን ግትርነታችንን ተገንዝበን ለመለውጥ መዘጋጀት ተገቢ ነው።

2. ምቾት| Comfort

ማንም ሰው ቢሆን ካላበት ምቾት መውጣት አይፈለግም፣ ሰዋዊ ባህርያችን ስለሆነ። ነገር ግን በሁሉም ህይወታችን ውስጥ ምቾታችንን የሚጻረር ሁኔታዎች አሉ። እንደምሳሌ አትሌት ሀይሌ ገ/ስላሴ ለሊት 11 ሰዐት ተነስቶ ይሮጥ ነበር.... /ለማሸነፍ ሲል/፣ አንድ ተማሪ ረጅም ሰዐት ማጥናአት አለበት ..../ በፈተና ጥሩ ዉጤት ለማምጣት ሲል/፣ ወዘተ...። መተኛትም ሆነ አለማጥናት መቾት ዉስጥ የሚከቱን ተግባራት ናቸው፣ በዚህም የአላማችንን ምህዳር ያሳጥራሉ።

የሃሳብ ምህዳራችንን እንዴት እናስፋ?

እንዚህን 2 ነገሮች ብንጀምር ከላይ የተገለጹትን መሰናክሎች ለመበታተን ይረዳናል፦

1. የጨዋታ ለዛን ማብዛት /Use of Humor/

በህይወታችን ውስጥ ጨዋታ ለዛ ካስገባን፣ የሃስብ ምህዳራችንን በተሻለ መንገድ እንድናሰፋ ያግዘናል። ውጥረትን ለመቋቋም መጽናኛ የሆነናል፣ ከሰዎች ጋር ያለንን ግንኙነት ያጠናክርልናል፣ የህይወት ተሞኩሮዎችንን ኖርማል ያረግልናል።

2. አዉንታዊ ማረጋገጫ ለራስ መስጠት/ Positive affirmation/

በራስ ለመተማመን ከተፈለገ ሁልጊዜ አዉንታዊ ማረጋገጫ መስጠት ይገባል። አልችለም የሚለዉን የሽንፈት ሃሳብ የሚቃወመው ይህ ሰለሆን፣ በዚህ ለይ ደግሞ ከሌሎች ጋር የምናደርገውን አጉል ውድድር ይቀርፍልናል፣ ውድድሩ ከራስ ጋር ስለሆነ። በራሱ የሚተማመን ሰው ፈተና አይፈራም፣ ደፋር ይሆናል፣ የፈጠራ ሃሳብ ይኖረዋል።

“ስለዚህ ለዉጤት ስትል የህይወት ጌምን አሸንፋት”

ዶ/ር መሀመድ ንጉሴ (Psychiatrist)

@melkam_enaseb
የአማኑኤል አዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የስነ አዕምሮ ህክምና መስጫ መምሪያ አስመረቀ።
  
ሆስፒታሉ ለሁለት ዓመታት በዘርፉ የተሰማሩ ታዋቂ የስነ አዕምሮ ባለሙያዎችን በማቀናጀትና በማስተባበር ሲያዘጋጅ የቆየውን የስነ አዕምሮ የህክምና መስጫ መምሪያ (Standard Treatment Guideline for Psychiatric Disorders) የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት አስመርቋል።

የዚህ መምሪያ ዝግጅት አላማው በስነ-አእምሮ ህክምና ዘርፍ የሚስተዋለውን የእውቀትና ክህሎት ክፍተት ለማረምና የህክምና አገልግሎት አሰጣጡ ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ ለማድረግ ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።

#AMSH

@melkam_enaseb
እነዚህን 7ቱን አድርግ!

1. የሌሎችን ልብ ከመጉዳት ተቆጠብ። የህመሙ መርዝ ወደ አንተ ይመለሳል።

2. ሁልጊዜ ታማኝ እና እውነተኛ ሁን።

3. ራስህን ሚዛናዊ አድርግ። የአንተ አእምሯዊ እራስህ፣ መንፈሳዊ እራስህ፣ ስሜታዊ እራስህ እና አካላዊ እራስህ - ሁሉም ጠንካራ፣ ንጹህ እና ጤናማ መሆን አለባቸው።

4. ማን እንደሆንክ እና ምን ምላሽ እንደምትሰጥ በማስተዋል ውሳኔ አድርግ። ለድርጊትህ ተጠያቂ ሁን።

5. የሌሎችን ግላዊነት እና የግል ቦታ አክብር።

6. መጀመሪያ ለራስህ ታማኝ ሁን። መጀመሪያ እራስህን ማሳደግ እና መርዳት ካልቻልክ ሌሎችን መንከባከብ እና መርዳት አትችልም።

7. መልካም እድልህን ለሌሎች አካፍል። በበጎ አድራጎት ውስጥ ተሳተፍ።

(በራስ መተማመን መጽሐፍ)

መልካም ቀን!

@melkam_enaseb
⬆️ YETENA WEG CLUBHOUSE DISCUSSION!

Topic: Work place Mental Health!

Sunday| April 30
6:00-2:00 (EAT)

Here is the Clubhouse link to join ⬇️

https://www.clubhouse.com/house/yetena-weg-%E1%8B%A8%E1%8C%A4%E1%8A%93-%E1%8B%88%E1%8C%8D

@melkam_enaseb
ውጥረት (Stress) እና ሱስ ያላቸው ግንኙነት!

ውጥረት የሚከሰተው አንድ ሰው ማቅረብ ወይም መስራት የሚጠበቅበት (demand የሚደረገው) ካለው አቅም ወይም መስራት ከሚችለው (ካለው resource, capacity) በልጦ ሲገኝ ነው። ውጥረት ሲከሰት ያስጨንቃል፤ ይህም አዕምሮን የሚለውጡ ኬሚካሎችን (ለምሳሌ፦ አልኮል፣ አደንዛዥና አነቃቂ እፆችን) ለመጠቀም ይዳርጋል። ምክንያቱ ወይ ተጨማሪ ጉልበት ለማግኘት፣ የአዕምሮ ፍጥነትን ለመጨመር ወይም ችግሩን ለመርሳት ነው። ይህ ሁኔታ ጊዜያዊ መፍትሄ የሰጠ ቢመስልም ድግግሞሽ ውስጥ በመክተት ሳያስቡት ለሱሰኝነት ይዳርጋል።

ለምሳሌ:- ተማሪዎች ከስር ከስር ማጥናት ሲገባቸው ፈተና እስኪደርስ ይጠብቁና ማጥናት የሚገባቸው ካላቸው ጊዜ ጋር የማይመጣጠን ይሆንና ውጥረት ውስጥ ይገባሉ፤ በዚህ ጊዜ አዕምሮን የሚያነቃቃ ነገር (ጫት) ወደ መጠቀም ይገባሉ፤ ይህ ነገር ሲደጋገም ለሱሰኝነት ይዳርጋል። ስለዚህ፤ በተቻለ መጠን ውጥረት የሚቀንሱ ተግባራትን መፈፀም፤

ለምሳሌ፦ ተማሪዎች ፈተና እስከሚደርስ ሳይጠብቁ ከስር ከስር ማጥናት፣ ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት ቀድሞ መከላከል፣ ጤናማ የአቅም መጨመሪያ ዘዴዎችን መጠቀም፣ ችግሮችን የመፍታት ክህሎትን ማዳበር፣ እንዲሁም ውጥረት ለመቀነስ የሚረዱ ዘዴዎችን መጠቀም (የአተነፋፈስ ስርአትን በመጠቀም፣ በሜዲቴሽን ወይም ፀሎት ራስን ማረጋጋት፣ ጤናማ የመዝናኛ አማራጮችን መጠቀም እንዲሁም የሌሎችን እገዛ መጠየቅ) ውጥረትን ለመቀነስ ይረዳል። ውጥረት አቅማችንን እንዳንጠቀም ሊያደርገን ይችላል። ውጥረት ሲደጋገም እና እየቆየ ሲሄድ ለአዕምሮ ህመም ይዳርጋል። ውጥረትን መከላከል ሱስ እንዳይከሰት ከመከላከያ መንገዶች አንዱ ነው።

ፕ/ር ሰለሞን ተፈራ (አዲክሽን ሳይካትሪስት)

@melkam_enaseb
ሜንታል ሄልዝ አዲስ ሚያዚያ 28/2015 ቅዳሜ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዶር አዲስ ሆቴል "እውን የአዕምሮ ህመም መርገምት ነው?! በዘርስ ይተላለፋል?" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ዶ/ር ዮናስ ባህረጥበብን ጋብዟል፡፡

መግቢያ:- ነፃ
ለመታደም: በ0933616212 ሙሉ ስሞትን ይላኩ ወይንም በዚህ መስፈንጠሪያ ይመዝገቡ: https://docs.google.com/forms/d/1JcXN5wU_CItM93fUVZgpFNXUq7xK0ZjBWa1ddxwfEww/edit?usp=drivesdk

የሆቴሉን አድራሻ በዚህ መስፈንጠሪያ ማግኘት ይቻላል: https://goo.gl/maps/SG2wDmdyAz52bPL2A

@melkam_enaseb
ጭንቀት

አንዳንድ ሰዎች በየምክንያቱ ይጨናነቃሉ፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን አብዛኛዎቹ የምንጨነቅባቸው ነገሮች ቀድሞውኑ መሰረት የሌላቸው ናቸው፡፡ ለምሳሌነት የሚከተለውን የአንድ ጥናት ውጤት እንመልከት፡፡ የምንጨነቅባቸው ነገሮች . . .

1. 40% በፍጹም ለማይደርስብን ነገር

2. 30% ምንም ልንለውጠው ስለማንችለው ስላለፈው ነገር

3. 12% ሰዎች ስለእኛ ስለሚናገሩብን ፍርድ፣ ወሬና ሃሜት

4. 10% ስለጤንነታችን (ስለተጨነቅን የሚብስ)

5. 8% ስለእውነተኛ ልናስብበት ስለሚገባ ሁኔታ

በፍጹም ለማይደርስብን ነገር ከተጨነቅን . . . ያለን አማራጭ ምክንያታዊነትን ማዳበር ነው፡፡ ሁኔታው ሊደርስብንና ላይደርስብን የሚችልበትን የእድል መጠን አመዛዝነን ያለመድረሱ ሁኔታ ካመዘነ፣ መጨናነቅን የማቆምን ሂደት መጀመርና እየተዉ መሄድ የግድ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ግን እንዲሁ ምክንያት ፈልገው የመጨነቅ “ሱስ” አለባቸው፡፡  ይህ ዝንባሌ የሚመጣው ለረጅም ጊዜ በአጣብቂኝ ሁኔታ ከማሳለፍና ስሜታችን የጭንቀት ሰለባ ሆኖ ከመክረሙም የተነሳ ሊሆን ይችላል፡፡ ያም ሆነ ይህ ፍጹም የማይደርስ ነገር ተለይቶ ሊታወቅና ከስሜታችን የደም ዝውውር ውስጥ ሊወገድ ይገባዋል፡፡ 

ምንም ልንለውጠው ስለማንችለው ስላለፈው ነገር ከተጨነቅን . . . ያለን አማራጭ ፈጽሞ አንዴ የሆነ ነገር መሆኑንና ምንም ብናደርግ ልንለውጠው እንደማንችል በመቀበል አእምሮን በአዳዲስ ነገሮች መሙላት ነው፡፡ ይህን ማድረግ ካልፈለግን ግን እስቲ አንዴ የሆነውንና ያለፈውን ነገር ለመለወጥ የአንድ ወር ጊዜ እንስጠውና የምንችለውን ያህል እንሞክርና ካልቻልን ነገሩን ለመተው ለራሳችን እድል እንስጠው፡፡

ሰዎች ስለእኛ ስለሚናገሩብን ፍርድ፣ ወሬና ሃሜት ከተጨነቅን . . . ያለን አማራጭ መቆጣጠር የማንችለውን የሰውን ባህሪይ ለመቆጣጠር ከመጦዝ ይልቅ መቆጣጠር የምንችለውን የራሳችንን በሆነ ባልሆነው የመጨነቅ ዝንባሌ ለመቆጣጠር መስራቱ ይመረጣል፡፡ ሰዎች ስለአንተና በአንተ ላይ የሚሉት ነገር አንተ ካልፈቀድክለት በስተቀር ምንም ሊያደርግህም እንደማይችል አትዘንጋ፡፡ ብትችል ወሬው አንተ ጋር የማይደርስበትን መንገድ ፍጠር፡፡ ካልቻልክ ደግሞ ወሬው ወደ ስሜትህ የማይደርስበትን ጥንካሬ አዳብር፡፡

ስለጤንነታችን (ስለተጨነቅን የሚብስ) ከተጨነቅን . . . ያለን አማራጭ ስለጤነታችን የሚያሳስበን ሁኔታ ካለ ያንን ለማስቀረት ወይም ለመቀልበስ የምንችለውን ያህል መሞከር ነው፡፡ ጭንቀታችን ግን “ምናልባት እታመም ይሆን” የሚል ከሆነ፣ ይህ የራስ በራስ ትንበያ እንደሚፈጸም አትጠራጠር፡፡ ጭንቀት በሽታን የመሳብ ባህሪይ አለውና፡፡ 

ስለእውነተኛ ልናስብበት ስለሚገባ ሁኔታ ከተጨነቅን . . . ያለን አማራጭ በቅድሚያ፣ ሁኔታው በትክክልም የሚያሳስብና በቅጡ ካልያዝነውም የሚስጨንቅ ጉዳይ ስለሆነ ማሰባችንና በመጠኑም ቢሆን መጨነቃችን ትክክለኛው መሆኑን አምኖ መቀበል አስፈላጊ ነው፡፡ ሲቀጥል ያሳሰበንን ሁኔታ በምን መልኩ ብንጋፈጠው ልናሸንፈው እንደምንችል በሚገባ ማሰብን ይጠይቃል፡፡ አእምሮን በጭንቀት ከመሙላት ይልቅ ትክክለኛውን ምላሽ በማሰብ መሙላት በብዙ እጥፍ ይመረጣል፡፡ በጉዳዩም ላይ ሰውን ማማከሩም አንዱ መንገድ ነው፡፡

(ዶ/ር ኢዮብ ማሞ)

@melkam_enaseb
ዝግጅታችን ላይ በአክብሮት ጋብዘንዋታል!

ዓብርሆት ስፔሻላይዝድ የሳይኮሎጂ ማዕከል የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር በማስመልከት የመዝግያ ፕሮግራም አዘጋጅተናል በዝግጅቱ ወላጆች፣ መምህራኖች፣ የሳይኮሎጂ እና የህፃናት ህክምና ባለሙያዎች ይገናኛሉ።

ሚያዚያ 27፣ 2015 ከቀኑ 8:30

ለመመዝገብ ማስፈንጠሪያውን ይጠቀሙ: https://bit.ly/3ViKKQc

ለተጨማሪ መረጃ: +251989737372  

ድረገፅ: http://www.abrihot.com/

@melkam_enaseb
2025/07/08 02:13:29
Back to Top
HTML Embed Code: