እርሱ ሚካኤል ነው
@menfesawi_getem_ena_menebanb

ወደ ፅድቅ መንገድ ፤ እኛን እየመራ
እግዜር እንዳይቆርጠን ፤ ፍሬ ሳናፈራ
እርሱ ሚካኤል ነው ፤ የመላእክት አለቃ
ባማላጅነቱ ፤ የሆነን ጠበቃ።
ለባሕራን የሞቱን ፤ ደብዳቤ የቀየረ
ሰይጣን ዳቢሎስን ፤ በሲኦል ያሰረ
እስራኤልን ከግብፅ ፤ መርቶ ያሻገረ
እርሱ ሚካኤል ነው ፤ ሀያል የከበረ ።
የሰናክሬም ጦሮች ፤ ቢሆኑ ብዙሃን
ሳይዋጋ የፈጃቸው ፤ በሰይፉ ብርሃን
አዛኝና የውሃ ፤ ከጥፋት ታዳጊ
እርሱ ሚካኤል ነው ፤ የእኛ አሳዳጊ ።

አቤል ታደለ

@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb

ለአስተያየት : @abeltadele
🔥2
#አሻግረን_ባህሩን
@menfesawi_getem_ena_menebanb


ለነፃነት ያልነዉ፣ የግብፅ ህልም እንጀራ ፣ ባርነት ሆኖብን፤
የሸጥነዉም ዮሴፍ፣ በሕሊና ወንበር ፣ እየፈረደብን፤
በባዕድ ሀገር በዝተን ፣ የበረከት ፈንታዉ ፣ ጥሎን ከሥጋቱ፥
የወለድነዉን ልጅ ፣ መልሰን ከጭቃዉ ፣ ረግጦ መጫወቱ፥
ያኘክነዉም ጮማ ፣ ከጥርሳችን ሳይወርድ ፣ የመርገም ሞት ጠርቶ፥
የመኖር ህግ ሲጎድል፣ በሞት ተጠግቶ…ሞትን ተመክቶ፤
ከአስሩ መቅሰፍት፣ ቸነፈር ረሃቡ ፣ ተዓምር ድንቃ ድንቁ፤
አንድ አማኝን አጥተዉ ፣ በኩረ ሞት እስኪደርስ፣ ድንጋን ላይ ሲወድቁ፤
የምፅዓት ምልክት፣ በበሮቹ መቃን፣ ቢቀባ በበግ ደም፤
የግብፃዉያን ዓይን- የጡቡን ግንብ እንጂ ፣ ይህን ማየት አይወድም።
የተፈራዉ ደርሷል፣ ሞት ገብቷል በየቤት ፣ ሀገር ተሸብራል፤
የመቅሰፍት ወላፈን ፣ መጥቶ ሲጥል እንጂ፣ ሲሄድ ተሰዉሯል፤
ለእምነት የሚሆን ፣ የበግ ደም ያለበት ፣ የእምነት ፍሪዳ፥
አንሶ ዋይታ ሆኗል፣ በፈረኦን ቤትም ፣ በእስራኤልም ጓዳ፤
ለነፃነት ብለን ፣ ሌሊት የተጓዝነዉ፣ ሌሊቱ ረዝሞብን፥
ከቀመስነዉ መና ፣ የለመድነዉ ሽንኩርት ፣ ያምናዉ አይሎብን፥
የጨረቃዉ ድምቀት፣ የኮከቡ ምሪት ፣ የሌሊቱ መንገድ፥
አንተ ካላበራህ ፣ ለመቆም አይሆንም፣ እንኳንስ ለመሄድ፤
የጪንጫ ላይ ወሃ፣ አይፈልቅም ያለ አንተ ፣ ለጥማችን አይሆን፤
የበረሃ ልብሳችን ፣ ለቀን አይበረክት፣ አያረካ ለዓይን፤
የገመጥነዉ ሥጋ ፣ ከጉሮሮ ሳይወርድ ፣ ሆኖብን ሞት ጠሪ፤
በሄድንበት ጉዞ፣ ያለ ሩኅሩኅ መልአክ ፣ ያለ መንገድ መሪ።
ከፊታችን ቆሟል ፣ የኤርትራ ባህር ፣ ግንብ ሆኖ በመፍሰስ፤
ከኋላችን መጥቷል ፣ የፈረኦን ሠራዊት ፣ ጦር ሰብቆ በፈረስ፤
ከሁለቱም በፊት ፣ ከሙሴ በትር ጋር ፣ ሚካኤል ሆይ ድረስ።
በጦርም በባህርም ፣ የኢትዮጵያ ድንኳን፣ አይተህ መሸበሩን፤
ልንሰጥም ነዉና፣ መልአከ ምህረት ሆይ ፣ አሻግረን ባህሩን።

@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb

https://www.tg-me.com/menfesawi_getem_ena_menebanb
5
የፀጋው ግምጃ ቤት

@menfesawi_getem_ena_menebanb


ከፀጋ ቀንሶ ፤ ልጇ መድሀኒአለም
ከድንግል ማርያም ፤ ያስቀረባት የለም።
ለሚካኤል ምህረት ፤ ለገብርኤል ብሥራት
ሰፍሮ እንደሰጣቸው ፤ አላጎደለባት
የሰማይ ሀብት ሁሉ ፤ ለማርያም ተሰጣት።
አላት ልዩ ግርማ ፤ የሚወደድ ጠባይ
ከኪሩቤል እና ፤ ከሱራፌል በላይ።
የቅዱሳን ሁሉ ፤ የሐዋርያትም
ፀጋ ቢሰበሰብ ፤ ከማርያም አይበልጥም ።
ክብር የምታሰጥ ፤ የፀጋው ግምጃ ቤት
ለሰው ልጆች ሁሉ ፤ አርጓታል ተምሳሌት።
ለደናግል ቢሉ ፤ በአላማ ፅኑነት
ከእርሷ የተሻለ ፤ ማን አለ አብነት ።
ለወላጅም ቢሉ ፤ ከእርሷ ማነው በልጦስ
እናት ቢሉ እናት ፤ ያውም የክርስቶስ ።
ለጠቢባን ቢሉ ፤ እንደ እርሷ አዋቂ
ማን አለ መላእክን ፤ መርማሪ ጠያቂ።
እንደ አባ ጊዮርጊስ ፤ እንደ ቅዱስ ኤፍሬም
የለመናት ዛሬም ፤
ከእርሷ የተጠጋ ፤
ፈልጎ አያጣም ፤ የእግዚአብሔርን ጸጋ።

አቤል ታደለ


@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb

https://www.tg-me.com/menfesawi_getem_ena_menebanb

ለአስተያየት : @abeltadele
1
አባ ለትጹንም ስለዚህ ኃጥእ ሰው ነፍስ ክብር ይግባውና ጌታችንን እየለመነ አምስት ጊዜ እስከሚሞት ሰውነቱን ሊአሠቃያት ጀመረ ።

13 (፲፫) የመላእክት አለቃ ሚካኤልም መጥቶ አስነሣውና እንዲህ አለው ስለዚያ ኃጢአተኛ ነፍስ ንፍስህን አትግደል ምሕረት አይገባውምና እግዚአብሔር ዕውነት ፈራጅ ስለሆነ በደሉ አይሠረይለትም አባ ለትጹን ግን መሐሪ ይቅር ባይ ወደ ሆነ እግዚአብሔር ስለዚያ ኃጢአተኛ እየለመነ ራሱን ማሠቃየት አልተወም ።

ከዚህም በኋላ ራሱን በባሕር አስጥሞ ሞተ ያን ጊዜም ታላቅ ነጐድጓድ ሆነ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ በባሕሩ ዳር ተቀመጠ ከባሕርም አውጥቶ ከሞት ያድነው ዘንድ ሚካኤልን አዘዘው እርሱም አድኖ ክብር ይግባውና በጌታችን ፊት አቆመው ።

ጌታችንም የመረጥሁህ ለትጹን ሆይ ኃጢአቱ እጅግ ብዙ ስለ ሆነ ከኃጢአተኞች ሁሉ በደል ስለሚከፋ ምሕረት ስለማይገባው ስለዚያ ኃጢአተኛ ብዙ ጊዜ ነፍስህን ለምን ትገድላለህ አለው ። አባ ለትጹንም እንዲህ ብሎ መለሰ መሐሪና ይቅር ባይ ጌታዬ ፈጣሪዬ ሆይ ያን ኃጢአተኛ ትምረው ዘንድ እለምንሃለሁ ያለዚያ ነፍሴን ከእርሱ ጋራ ወደ ሥቃይ ውሰዳት ።

ከዚህም በኋላ ጌታችን የዚያን ኃጥእ ነፍስ ያመጣት ዘንድ ሚካኤልን አዘዘውና አመጣት በከበሩ እጆቹም ዳሠሣት እንዳልተፈጠረችም አደረጋት ። ይቺ ነፍስ አፈር ትሁን እንጂ ለሥቃይ ወይም ለሕይወት አትሁን አለ ። አባ ለትጹንም ስለ ይቅርታውና ቸርነቱ ገናናነት መድኃኒታችንን ፈጽሞ አመሰገነው ።

በረከቱ ይደርብን!
__
@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb
4👏1
አይደለም ገብታን
@menfesawi_getem_ena_menebanb


ከእውቀት ባሻገር ፤ ከቃል ማብራሪያም
ዕፁብ ድንቅ ነው ፤ ነገረ ማርያም።
ቀለም ቢቀዳ ፤ ተጨልፎ ባህር
በየብስ ወረቀት ፤ በውሃ ብእር
አይበቃም ሥፍራ ፤ እስካለም አጽናፍ
ድንግልናዋ ብቻውን ቢፃፍ ።
የእርሷን ከፍታ ፤ የእርሷን ልዕልና
ቃል ሊሸከመው ፤ አይችልምና
ብንናገርም ፤ ገናንነቷን
ከፍቅር እንጂ ፤ አይደለም ገብታን።

✍️ አቤል ታደለ

@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_meneban
ለአስተያየት : @abeltadele
3🔥1
#አያልቅብህ_ትህትናህ
@menfesawi_getem_ena_menebanb

ትሻው ነፍሴን ... እንዴት ልግለጥ፤
ከምቀዳው  ....  እንዴት ልብለጥ።
ከምኔ ላይ ምኔን ጥዬ፤
ላቅርብልህ ውሃ ብዬ።
የለመንከኝ ፍጥረትህን ..
                 የለመንከኝ የጋን ውሃ፤
ማቅረቢያዬ አዳፋ ልብ ..
                    ያልታጠበ በንስሐ።
ታውቀው የለ  ..... ታሪክ ግብሬን፤
ያልኖርኩትን ቡሩክ ኑሮ ..
                በአደባባይ መናገሬን።
ታውቀኝ የለ እድፍ እንዳልኩ ..
     ምን እንዳጣሁ ምን እንዳለኝ፤
በኃጢአት ነትባ ያለች ነፍሴን ..
             የምሰጥህ እኔ ማን ነኝ።
አንካሳ ነኝ ልበ ስንኩል..
      ዛሬ ነገ የምቃጠር ..
       ለማፍቀርህ መልስ የማጣ፤
ና ስትለኝ ልብ የለኝም ..
      በምን ጽድቄስ ችዬ ልምጣ።
ዳሩ አንተ ግን መናፈቅህ፤
የጠማህን የነፍሴን ማይ ..
        እስካጠጣህ  መጠበቅህ፤

አያልቅብህ ትህትናህ!!!

@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_meneban
5
ከልጅሽ በፊት አንቺን ልታረቅሽ
@menfesawi_getem_ena_menebanb

እንድታስታርቂኝ ከልጅሽ ፊት ቀርበሽ
ከልጅሽ በፊት አንቺን ልታረቅሽ
ስለ ኃጥያት በደሌ እንድታማልጂኝ
ስደክም አቅም ሆነሽ እንድታበረቺኝ
የጌታዬ እናት እመአምላክ
አለው በይኝ ከደጅሽ ስንበረከክ

ሀጢያት በዝቶ እንዲያው ብከረፋም
እመቤቴ ማርያም ስምሽን አልረሳም
ብሄድም ከየትኛው የአለም ጫፍ
እንዳንቺ ፀሎትን አሳርጎ የለም የሚያሳረፍ
ስለ እናቱ ብሎ ልጅሽ እንዲምረኝ
ከልጅሽ በፊት ማርያም ሆይ ታረቂኝ
ያገኘሁሽ ከከበረው ጎልጎታ
ልጅሽ የሰጠኝ ከዛ ከመከራው ቦታ
እኔ ልጅሽ በሃጢአት ቆሽሼ ከደጅሽ
ስወድቅ
ህይወት ከብዳብኝ ሳለቅስ ስጨነቅ
እናቴ ስለ አንቺ ብሎ ልጅሽ እንዲምረኝ
ከልጅሽ በፊት እመብርሃን አንቺ ታረቂኝ

@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_meneban
5
አይኔ ናት
@menfesawi_getem_ena_menebanb

እያፈነገጥኩ ሌላ ነገር ሳይ ብውልም ሳትከፋብኝ ፍካትን የምትለግሰኝ
በድክመቴ ወቅት ሁሉ ለይታ ብርታት የሚያላብሰኝን ውብ ነገር የምታመላክተኝ
በጽልመት ህይወቴ ውስጥ የማያቋርጥ የተስፋ ብርሃንን የምትመግበኝ
አይኔ ናት

እኔ ግን
ዝለት የሚመግቡ እንቅልፍ ሊያሸክሙ የሚንደረደሩ ዱካካም ምስለ ኩነኔዎች መጥተው ሲጫኑኝ በዝምታ እሾፋቸዋለሁ
ውድቀቴን የሚያጣድፉ ተልከስካሽ አቧራና ንፋሳም ሀሳቦች እየቦነኑ ሊሞጀሩ ሲከጅሉ በቸልታ አሳልፋቸዋለሁ
ክስመትን የሚያሸክሙ እንደ ፀሐይ የሚያጥበረብሩ ጨረራም ኹነቶች ተምዘግዝገው ሲወተፉ ባላየ ትቻቸው እጓዛለሁ

አይኔ ናት (የነፍሴ)
ግን የስጋ አይኔን ቅንጣት ታህል እንክብካቤ አላደርግላትም። ከንቱነቴን አግዝፌ እንዲሁ ለአፍ ብቻ አይኔ ናት እላለሁ እንጂ ለክብሯ ለግብሯ ልብ ብዬ ዋጋ ሰጥቼ አላውቅም። በብርሃኗ ለመድመቅ እቋምጣለህ እንጂ ተገቢውን ነገር በፍጹም ልቤ ልከውን እጄን አላነሳም።

ለስጋ አይኔ
ትንኝ ገባ፣ ፀጉር ተቆርጦ ተወተፈ ብዬ በፍጥነት በልብሴ እጀታ መንቅሬ ለማስወጣት የምጣደፈውን ሲሶ ታህል ህመም ሲያንቀኝ፣ ችግር ሲለጠፍብኝ መች ተሽቀዳድሜ በጸሎት ለማስወገድ ምስሏ ፊት እቆማለሁ

ደፍርሶ እይታዬ እንዳይከስም እለት ተለት በውሃ አይኔን ለማጥራት የማጥበውን ኢምንት ታህል በኃጢያት ያደፍኩ ጊዜ መች በጸበሏ ለመንጻት ደጇ እመጣለሁ

የፀሐይ ጨረር፣ የኮምፒተር ብርሃን አይኔን እየጠበሰቀ አስቸገረኝ ብዬ ከኪሴ ያለኝን መዥርጬ መነጸር ለመግዛት የማኮበክበውን ሲሶ ታህል ለገጠመኝ ፈተና አንቺ ፍቺልኝ እንጂ ይህን ያህል ለክብርሽ ስለት አስገባለሁ ለመናገር መች አፌ ይፈታል።

አይኔ ናትና ሺ ጊዜ ባጠፋም ማየትን አትነፍገኝም
ብርሃኔ ናትና ሺ ጊዜ ብሳሳትም ለጽልመት አትተወኝም

አይኔ ነሽና ብርሃኔ አይኔ ነሽና ብርሃኔ
#እመቤቴ_ማርያም አብሶማ ለእኔ

አይኔ ሆይ
እናቴ ሆይ
ብርሃኔ ሆይ
እመቤቴ ሆይ
ደካማ ልጅሽን
በአግባቡ ማየትና አንቺን ማክበር አስለምጂኝ
እንዳልሰናከል
እንዳልቀጠፍ
እንዳልረግፍ እንደ ሁልጊዜው እርጂኝ

#ኤልዳን

@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb
5🥰2
አይኔ ናት
@menfesawi_getem_ena_menebanb


እያፈነገጥኩ ሌላ ነገር ሳይ ብውልም ሳትከፋብኝ ፍካትን የምትለግሰኝ
በድክመቴ ወቅት ሁሉ ለይታ ብርታት የሚያላብሰኝን ውብ ነገር የምታመላክተኝ
በጽልመት ህይወቴ ውስጥ የማያቋርጥ የተስፋ ብርሃንን የምትመግበኝ
አይኔ ናት

እኔ ግን
ዝለት የሚመግቡ እንቅልፍ ሊያሸክሙ የሚንደረደሩ ዱካካም ምስለ ኩነኔዎች መጥተው ሲጫኑኝ በዝምታ እሾፋቸዋለሁ
ውድቀቴን የሚያጣድፉ ተልከስካሽ አቧራና ንፋሳም ሀሳቦች እየቦነኑ ሊሞጀሩ ሲከጅሉ በቸልታ አሳልፋቸዋለሁ
ክስመትን የሚያሸክሙ እንደ ፀሐይ የሚያጥበረብሩ ጨረራም ኹነቶች ተምዘግዝገው ሲወተፉ ባላየ ትቻቸው እጓዛለሁ

አይኔ ናት (የነፍሴ)
ግን የስጋ አይኔን ቅንጣት ታህል እንክብካቤ አላደርግላትም። ከንቱነቴን አግዝፌ እንዲሁ ለአፍ ብቻ አይኔ ናት እላለሁ እንጂ ለክብሯ ለግብሯ ልብ ብዬ ዋጋ ሰጥቼ አላውቅም። በብርሃኗ ለመድመቅ እቋምጣለህ እንጂ ተገቢውን ነገር በፍጹም ልቤ ልከውን እጄን አላነሳም።

ለስጋ አይኔ
ትንኝ ገባ፣ ፀጉር ተቆርጦ ተወተፈ ብዬ በፍጥነት በልብሴ እጀታ መንቅሬ ለማስወጣት የምጣደፈውን ሲሶ ታህል ህመም ሲያንቀኝ፣ ችግር ሲለጠፍብኝ መች ተሽቀዳድሜ በጸሎት ለማስወገድ ምስሏ ፊት እቆማለሁ

ደፍርሶ እይታዬ እንዳይከስም እለት ተለት በውሃ አይኔን ለማጥራት የማጥበውን ኢምንት ታህል በኃጢያት ያደፍኩ ጊዜ መች በጸበሏ ለመንጻት ደጇ እመጣለሁ

የፀሐይ ጨረር፣ የኮምፒተር ብርሃን አይኔን እየጠበሰቀ አስቸገረኝ ብዬ ከኪሴ ያለኝን መዥርጬ መነጸር ለመግዛት የማኮበክበውን ሲሶ ታህል ለገጠመኝ ፈተና አንቺ ፍቺልኝ እንጂ ይህን ያህል ለክብርሽ ስለት አስገባለሁ ለመናገር መች አፌ ይፈታል።

አይኔ ናትና ሺ ጊዜ ባጠፋም ማየትን አትነፍገኝም
ብርሃኔ ናትና ሺ ጊዜ ብሳሳትም ለጽልመት አትተወኝም

አይኔ ነሽና ብርሃኔ አይኔ ነሽና ብርሃኔ
#እመቤቴ_ማርያም አብሶማ ለእኔ

አይኔ ሆይ
እናቴ ሆይ
ብርሃኔ ሆይ
እመቤቴ ሆይ
ደካማ ልጅሽን
በአግባቡ ማየትና አንቺን ማክበር አስለምጂኝ
እንዳልሰናከል
እንዳልቀጠፍ
እንዳልረግፍ እንደ ሁልጊዜው እርጂኝ

#ኤልዳን

@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb
5
ሙሴ ጸሊም ኢትዮጵያዊ

1 (፩) አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሃያ አራት በዚች ቀን አባ ሙሴ ጸሊም በሰማዕትነት ሞተ ።

2 (፪) ሰዎች ከገድሉ የተነሣ ይህን ቅዱስ ያደንቁታል እርሱ አስቀድሞ መንግሥተ ሰማያትን ገፍቷት ነበረና እርሱ በሥጋው ጠንካራ በሥራውም ኃይለኛ ነበር ይበላና ይጠጣ ይቀማና ያመነዝር ነበር ይገድልም ነበር ማንም ሊቋቋመው አይችልም ነበር ።

3 (፫) አንድ በግ በአንድ ጊዜ ጨርሶ እንደሚበላና አንድ ፊቀን ወይን ጠጅ እንደሚጠጣ ስለ እርሱ ተነግሮአል ።

4 (፬) እርሱም ፀሐይን ለሚያመልኩ ሰዎች አገልጋይ ነበረ ብዙ ጊዜም ወደ ፀሐይ እያንጋጠጠ ፀሐይ ሆይ አንተ አምላክ ከሆንክ አነጋግረኝ ይል ነበር ደግሞም በልቡ የማላውቅህ ሆይ ራስህን አሳውቀኝ ይል ነበር ።

5 (፭) ከዚህም በኋላ በአስቄጥስ ገዳም ያሉ መነኰሳት እግዚአብሔርን ያውቁታል ያዩታልም እያሉ ሲነጋገሩ ሰዎችን ሰማቸው ።

6 (፮) ያን ጊዜም ተነሣ ሰይፉንም ታጥቆ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ በደረሰም ጊዜ አባ ኤስድሮስን አገኘው ። አባ ኤስድሮስም ፈራው....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇
------------------
@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb
ወድቄያለሁ
@menfesawi_getem_ena_menebanb


ስለቆሸሽኩ ስለሆንኩ የማልረባ
ከደጅሽ መጣሁኝ ስለ ሀጢያቴ ላነባ
አትጨክኚም ሩሩ ነሽ እመቤቴ
ከጎኔ ትሆኛለሽ ሲጨልም ህይወቴ
ምን እሆን ነበር አንቺን ባይሰጠኝ አምላኬ
እናቴ የጭንቄ ተካፋይ የሀዘኔ መርሻ
ስምሽ ብርታቴ ነው የጠላት ድል መንሻ
ስምሽ ምርኩዝ ነው የጨለማ ፋኖስ
ለኔስ መታደል ነው አንቺን ማወደስ
እመቤቴ የኔ አለኝታ የጭንቄ አማላጅ
አምላክ ሲባርከኝ አረገኝ የአንቺ ልጅ
ግን እኔ ደካማው ይህን ሁሉ ረስቼ
በሃጢአት በስብሼ በሠው ሁሉ ተረስቼ
አምላኬን ናኩት በሰይጣን አሰራር ተገዝቼ
የአምላኬን ፍቅር ውለታውን ዘንግቼ
ለቁርባን ቅዳሴ ጥቂት ሰአት አጥቼ
ደከመኝ ሳልል ለበደል ራሴን አፅንቼ
ዛሬ አመሻሽ ላይ ስራዬ ቢያፀይፈኝ
አሁን ከረፈደ ቤቴ ቢናፍቀኝ
እንዴት ብዬ ልምጣ መንገዱ ባይጠፋኝ
ምን ሰአቱ እና ስርአቱ ባየረሳኝ
የነጠላዬ ንጣት ባየው አሳፈረኝ
የልጅነት መልኬን ድሮን አስታወሰኝ
እንደዛሬ ሳልርቅ ሳልጠፋ ከቤቱ
ነጠላ ለብሼ እገኝ ነበር በየሰንበቱ
ዛሬ ግን የለሁም የልጅነት ልምዴ ጠፍቷል
የልጅነት ልቤ በክፋት ጠልሽቷል
እናቴ ዛሬ ግን መዳንን ናፍቄ ከደጅሽ ወድቅያለው
ልጅሽን ለምነሽ እንድታሰምሪኝ ቅድስት ሆይ ብዬ እለምንሻለው

@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb
7
የደረቁ ዓይኖች
@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb

እሷ
ከቤተመቅደሱ በር ላይ ቆማለች፣
ፊት ለፊቷ ካለዉ የጌታ ስዕል ላይ ዐይኖቿን ተክላለች፣
እጆቿን ዘርግታ ፡
የማይቆም እምባዋን ቁልቁል ታፈሳለች፡፡

እኔ
በኃጢአት ደክሜ
ካንዱ አፀድ አጠገብ ታክቶኝ ቁጭ ብያለሁ፣
እንባን ባልታደሉ በደከሙ ዓይኖቼ
ዝም ብዬ አያታለሁ፡፡

ይፈሳል እምባዋ ይወርዳል አይቆምም፣
አሷም ልክ እንደኔ በዓለም ስትሸነፍ
ያዳናትን ጌታ ሳትክደው አትቀርም፡፡
 
እምባ ጥቁር እምባ ፀፀት ያከሰለው፣
እምባ ትኩስ እምባ ሀጢያት ያቃጠለው፣
እምባ መንታ እምባ ከአይኖቿ ይወርዳል፣
ምህረትን ፍለጋ ይጮሀል ይጣራል፡፡
 
ተቸገረች መሠል አልቻለችም መሠል እንባዋን ለመግታት፣
ፀፀቷ ገብቶኛል፡
እልፍ ሀዘኗ ፊት ስንት ቃል ደርድሬ ምን ብዬ ላበርታት፡፡

እንዴት ቀናሁባት እንዴት ታድላለች፣
የበዛ በደሏን በበዛ እምባዋ ታጥባ ትነፃለች፡፡
ይብላኝ እንጂ ለኔ ዓይኔ ለደረቀ፣
ልቤ ደንድኖብኝ
በኃጢአት በርኩሰት ነፍሴ ለደቀቀ፡፡
ይብላኝ እንጂ ለኔ ፀፀት ላላደለኝ፣
ካባቴ ቤት ርቄ መንገድ ለጠፋብኝ፡፡
ይብላኝ እንጂ ለኔ
ልጄ ነሽ እያለኝ ልጁ ላልሆንኩለት፣
ለፈወሰኝ አምላክ ጥፊ የመለስኩለት፣
ባፌ ማረኝ እንዳልልህ ልቤ መቼ አለቀሰ፣
ከንቱ ሆኜ ቀረሁብህ ነፍሴ ባለም እያነከሰ፡፡

ያዳንከኝ ሆይ...

እምባ ስጠኝ የጴጥሮስን ተፀፅቼ ማረኝ እንድል፣
እምባ ስጠኝ የጳውሎስን ማሳደዴን ትቼ እንድድን፣
የሚፈውስ ስጠኝ እምባ፣
የዓይኖቼን መባ አቅርቤልህ፡
የምህረት ደጅህ እንድገባ፡፡

ገጣሚ እሌኒ መኮነን

ሼር እያደረጋችሁ

@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb
5
መድኃኔዓለም ወይስ የግል አዳኝ
@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb

መዳን እንደ ቀለብ ፤ መዋጀት እንደ እህል፤
በቁና ተሰፍሮ የተሰጠ ይመስል፤
መሲሑን ለብቻ ፤ ኢየሱስን የግል፤
አ’ርገህ ምትቀበል፤
አድራሻህ ከየት ነው ስምህን ማን ልበል?

በእንተዝ ነገር ስምዐ ኮነ መልአክ፤
በጊዜ ልደቱ ወደ እረኞች ሲላክ።
መድኃኒት ክርስቶስ ግርግም መወለዱ ፤ በጨርቅ መጠቅለሉ፤
ለእረኞች በግል የተሰጠ ሳይሆን ለዓለሙ ሁሉ፤
እነሆ ሲታወቅ በምሥራች ቃሉ፤
አልሰማህም አሉ።

ራሱ ባለቤቱ፤
በወንጌል ትምህርቱ፤
“ለድኅነተ ዓለም በመልዕልተ መስቀል
ከምድር ከፍ ብዬ ዕርቃኔን ስሰቀል”
አንድ ሁለት ሰው ሳይሆን “ሁሉን እስባለሁ”
ሲል እየሰማነው፤
ጆሮ ነሳህ ምነው?

ደግሞስ ሳምራዊቷ፤
“ብፍርስንያ” ‘ሚሏት ውሃ ቀጂ ሴቷ፤
ውሃ አጠጭኝ ብሎ ፤ በፍቅር ጎብኝቷት ፤ እሷን ብቻ መርጦ፤
ሕይወት ሆኗት ሲሄድ ታሪኳን ለውጦ፤
አዳኝ ፣ መሲሕ የግል፤
መቼ ሰማን ስትል?
እንስራዋን ጥላ ገሰገሰች እንጂ ሰማርያ መንደር፤
የጠበቅነው አምላክ ተገለጠ ብላ ላ’ለም ልትናገር።
ከዚያማ፤
ድኅነት በሷ ሳይቀር፤
ለሃያ አምስት ምዕት ወገኖቹ መጣ፤
ከዓለት ክርስቶስ ማየ ሕይወት ፈልቆ ሁለት ቀን ተጠጣ።

መጣፍ ባለማወቅ ልቡናህ የሳተ፤
ዝንጕ ‘ምትሆን አንተ፤
“በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደሆነ አውቀናል።”
ስትል ሰማርያ ፤ በአልሰሜነትህ በጣም ተደንቀናል።

ከእንግዲህስ ስማ የተዋሕዶን አዋጅ፤

“ቤዛ ኵሉ እንጂ ነው ዓለሙን የሚዋጅ፤
የብቻዬም አይደል፤
የብቻህም አይደል፤
ፋሲካን ልታከብር በደመ ክርስቶስ ፤ ነጽታ ምትታጠብ፤
የምድር ሐሴት እንጂ ፤ የምድር ሁሉ ገንዘብ።
እናም፤
“መ ድ ኃ ኔ ዓ ለ ም”
ያለሚለው ቀለም፤
ትድግናውን ገላጭ ምሉዕ ፊደል የለም።”

እያለች ስትጠራው ስማት በየዕለቱ፤
እያት ስታነግሠው በስመ መንግሥቱ፤
በጥንተ ስቅለቱ።

መድኃኔዓለም!
መድኃኔዓለም!
መድኃኔዓለም!

ዲ/ን ዶ/ር ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ

በድምፅ ለመስማት 👇
https://youtu.be/2T9kWYsC7w0

@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb
6
አንቺ ካለሺኝ
@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb

ማርያም ብዬ ፤ ማንን እፈራለሁ
አባ ጊዮርጊስ ፤ ሲቀኝ እንዳለው ።
እኔን ለመፍጨት፤
ምድርም ወፍጮ ፤ ሰማይ መጅ ቢሆን
አንቺ ካለሺኝ ፤ ከቶ ምን ልሆን።
የጥፋት ውሃን ፤ ዛሬም ለማውረድ
እንደ ኖኅ ዘመን ፤ ሰማይ ቢቀደድ
በቅድስናሽ መርከብ ተርፌ
እሻገራለሁ ሞትን አልፌ።
በሰዶምና በገሞራ ላይ
እንደ ዘነበው ፤ እሳት ከሰማይ
ቢዘንብብኝስ ፤ ምን እሆናለሁ
ባንቺ ልመና ፤ አምኜ ሳለሁ።

✍️ አቤል ታደለ


@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb
ለአስተያየት : @abeltadele
3
መነነ ዮሐንስ
@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb

የድንግሊቱን ድምፅ ፤
ከእናቱ ማፀህን ፤ ከጠባቡ አልጋው
ዮሐነስ ሲሰማ ፤ ለመውጣት አጓጓው።
ወደ እኔ እንድትመጪ ፤ የጌታዬ እናቱ
እኔ ማነኝ ማለት ፤ ባይችል ባንደበቱ ።
ወቶም ሊቀበላት ፤ ባይታደል እንኳ
የእናቱን ማህፀን ፤ ከውስጥ ሆኖ አንኳኳ።
በእግዚአብሔር መንፈስ ፤ ልቡናው ተቃኝቶ
ደስታውን ለመግለፅ ፤ ባይችል ቃል አውቶ።
በአማናዊት ታቦት ፤ በድንግል ማርያም ፊት
በእናቱ ማህፀን ፤ ዘለለ እንደ ዳዊት።
የድንግሊቱን ድምፅ ፤ ከሰማ ጀምሮ
አስጠላው የአለም ፤ ጩኸት አምባኋሮ።
ተወልዶም አልቆየ ፤ ሌላ አልሰማም ብሎ
መነነ ዮሐንስ ፤ ይህን አለም ጥሎ ።
ዘወትር ሃጢያትን ፤ ለጊዜያዊ ደስታ
እኛም እንደ ውሃ ፤ ጠዋትና ማታ
ከዚህ አለም ጉድጓድ ፤ መቅዳት እንዲበቃን
ድምጿን እንሰማ ዘንድ ፤ ድንግሊቱ ታብቃን።

አቤል ታደለ

@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb

ለአስተያየት : @abeltadele
7👍1
ማርያም ሠማይ
@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb

ከ ቀናት መካከል...
ካምላኬ ጋር ተጣልቼ
ኃጢአት በደል ተቀብቼ፣
ወድቃ ረክሳ ነፍሴን ባያት
ካለም ተንኮል ልታደጋት
ካምላኳ ጋር ላስታርቃት፣
አስታራቂ አማላጅ ብሻ...
 
ከ ወንጌል ሃገር ወርጄ የመዳን እውነት ልጋራ
ከ ብሉይ ሰፈር ገብቼ ከ ነቢያት አፍ ሳጣራ
ጽልመቴን ላሸንፍ ስጥር ጨለማ ህይወቴን ላበራ፣
ሃዲስ ላይ ሰማይ አየሁኝ፣
በ ብርሃኗ ተደንቄ አስታርቂኝ ልላት ወሰንኩኝ፡፡
 
ሰማይ የኔ እመቤት
ሰማይ የ እምነቴ ቤት
ሰማይ የ ጽድቅ ሃገር
ሰማይ የ አምላክ መንበር
አስታርቂኝ ከ አንድያ ልጅሽ ልታረቅ ከነፍሴ ጋራ
መኖሬ መች መኖር ሆነ ሳይኖረኝ የልጅሽ ጮራ፡፡
 
አስታርቂኝ ደግሞ ከራሴ ጠላቴ  ከሆነኝ ስጋ፣
ከንቱ መሻቴን ስከተል ወድቄ እንዳልቀር ከአለም ጋ፡፡
የውነትሽ ምስጢር ቢገርመኝ
የልጅሽ ስራ ቢደንቀኝ
አምላክሽን ስትወልጂ አይቼ
ንጽህናሽን ሰምቼ
ክብርሽን ልገልጠው  ብጥር ከ ማይም ልቤ ጠልቄ
ድንግል ነሽ ወይስ እናት ነሽ ጠበበኝ  አለማወቄ፡፡
 
ከራቅሽኝ ምን እሆናለሁ ከተውሽኝ የት እሄዳለሁ
እናቱን አንቺን ሳልጠራ ልጅሽን ምን እለዋለሁ
አትፈትኝ ጠማማ ልቤን አትይው የ ኃጢአቴን ካባ
ላረኩት እልፍ በደሌ
ካዘኔ ከምባዬ በቀር የለኝም  ማቀርበው መባ፡፡
 
ሰማይ የኔ እመቤት
ሰማይ የእምነቴ ቤት
ሰማይ የ ጽድቅ ሃገር
ሰማይ የ አምላክ መንበር
መድኃኒት ያለው ካንቺው ነው
ለስንኩል ነፍሴ መዳኛ
ያላንቺ ሰላምም የለኝ እልፍ ስቃዬን መሸኛ
ይሁነኝ ምልጃሽ መብራቴ ከ ጨለማዬ ያድነኝ
የ ዓለም ብርሃን የሆነው ፀሐይሽ ልቤን ያብራልኝ፡፡

ገጣሚ ዕሌኒ መኮነን
@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb
16🤔1
የአብርሃም ድንኳን
@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb

እግዚአብሔር አምላክ ፤ ከቀን በቀትሩ
በአንድነትና ፤ በሦስትነት ክብሩ
ወደ አብርሃም ድንኳን ፤ እንደ ገባ ዅሉ ።
እግዚአብሔር አብ ለአጽንዖ፤
መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፤
በሰው አካል ለመወለድ ፤
ሥጋ ሊለብስ ፤ እግዚአብሔር ወልድ ።
የተገለጠባት ፤ ዓለሙን ለማዳን
የሐዲስ ኪዳኗ ፤ የአብርሃም ድንኳን
እግዚአብሔር አምላክ ፤ በዘመኑ ቀትር
ድንግል ማርያም ናት ፤ ያረፈባት ቅጥር ።
ምሥጢረ ሥላሴ ፤ ነገረ መለኮት
የጽድቅን ብርሃን ፤ ያየንባት መስኮት።
እንደ አብርሃምና ፤ እንደ ሣራ ጓዳ
ገብቶ ያደረባት ፤ የሰማይ እንግዳ።
የማያስጠማውን ፤ የማያስርበውን
በቀራንዮ ላይ ፤ አርብ የታረደውን
አማናዊ በጉን ፤ የተመገብንባት
በአማላጅነቷ ፤ ፍጥረት ያረፈባት
የአብርሃም ድንኳን ፤ ድንግል ማርያም ናት።

✍️ አቤል ታደለ

@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb

ለአስተያየት : @abeltadele
16🔥2
ሊያዩ የናፈቁት
@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb

ከተራራው ግርጌ ፤ ሌሎቹን አስቀምጦ
የምስጢር ተካፋይ ፤ የሆኑትን መርጦ።
በብርሃን ግርማ ፤ በአስፈሪ ነጎድጓድ
ምስጢረ መንግስቱን ፤ ጌታችን በገሐድ።
በታቦር ተራራ ፤ በአርሞንኤም ቀላያት
አሳያቸው ገልጦ ፤ ለሦስቱ ሐዋርያት።
ፊቱ እንደ ፀሀይ ፤ በራ በፊታቸው
እውነተኛ ብርሃን ፤ እኔ ነኝ ሲላቸው።
ቀሚሱ ነጭ ሆነ ፤ እንደ ጸዳል እንቁ
ንፁሃ በሃሪ ፤ መሆኑን እንዲያውቁ።
ኤልያስን ጠራው ፤ ከሕያዋን ወገን
ሙሴንም አመጣው ፤ ከምድር ማህፀን ።
አንተም ነብይ ነህ ፤ ለሚሉ ሳያቁት
ነቢያት እራሱ ፤ ሊያዩ የናፈቁት ።
የሕያዋን አምላክ ፤ የሙታንም ጌታ
እርሱ እንደሆነ ፤ ታየ የዛን ለታ።
በእርሱ ደስ የሚለኝ ፤ ልጄ ይህ ነውና
እርሱን ስሙት አለ ፤ አብም በደመና ።
ለዘመነ ሐዲስ ፤ ሦስቱ እንደራሴ
ተገለጠላቸው ፤ ምስጢረ ሥላሴ ።
የብርሃን ማዕዶት ፤ ሸፈነው ፅልመቱን
እስከሚዘነጉ ፤ እረኞች መምሸቱን።
ልዕልናው ታየ ፤ በታቦር ተራራ
ጴጥሮስ እስከሚል ፤ ሶስት ዳስ እንስራ።

✍️ አቤል ታደለ

@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb
ለአስተያየት : @abeltadele
10👍2
⭐️ማርያም ቂም አታውቅም⭐️

@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb

ፈጣሪን በድለን ፤
በሃጢአት ጎስቁለን ፤
በአለም ጉራንጉር ፤ ከርመን ብንመጣም
ከእመብርሃን ደጃፍ ፤ ተገፍተን አንወጣም።
አይጨክንም ልቧ ፤ እንደ በደላችን
ትቀበለናለች ፤ ከነ ሸክማችን።
ምንም ብንበድል ፤ ምንም ብንፈጽም
ሁሌም ሰርክ አዲስ ነው ፤ ፍቅሯ አይቀንስም።
ቢከብዳትም እንኳን ፤ በልጇ መጨከን
የእናትም ትእግስት ፤ ያበቃል አንድ ቀን።
ሊያስወድድ የሚችል ፤ ምግባር ባይኖረውም
ድንግል ማርያም ግን ፤ ልጇን አትተውም።
የዳቢሎስን ድምፅ ፤ አይስማ ጆሮአችን
በሯን እናንኳኳ ፤ ከነ ጉድፋችን።
እንደ ጴጥሮስ እንኳን ፤ በክህደት ብንወድቅም
ትቀበለናለች ፤ ማርያም ቂም አታውቅም።

✍️ አቤል ታደለ


⬇️⬇️⬇️🔖🔖

@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb

ለአስተያየት : @abeltadele
2
​​​​🌼የሩፋኤል ጠበል ከልጅነት እስከ ጅልነት🌼

በዲ/ን ከሣቴ ብርሃን ገብረኢየሱስ

በመዋዕለ  ንጽሕ ..
ልጅ ሳለሁ ፤ እንደ ልጅ፤
ጤና ሆኜ ሳለ..
በንዕማን ልማድ፤በውሃ ተጠምቄ፤ ጤንነቴን ሳውጅ፤
በርኅወተ ሰማይ፤
ሲዘንም የምሕረት ማይ፤
በሩፋኤል ጠበል በ“አሳድገኝ” ጬኸት፤
በጋን እንድባጀው እንደ ከረምኩ ክረምት፤
ከልቤ ለምኜ፤
ስብራት ሳይኖረኝ በወግ ተጠግኜ፤
ፀአዳ ብራና ሳልዳመጥ ዳግም፤
በጥምቀት ሳልሸኘው ዘመን አልፎ አያውቅም::

እነሆ ልጅነት እንደ ጥላ አለፈ፤
በዚያ ብራና ገጽ እልፍ ኃጢአት ተጻፈ፤
ሰውነት ይሁዳ ከድቶ ሽፍታ ኖሮ፤
ባበቀለው ጫካ ጠብ መንጃ ሰውሮ፤
ጠብ ክብሪት ሲላኮስ፤
ከጽድቅ ሲታኮስ፤
እኔ ሕመምተኛ፤ የጦር ቁስለኛ፤ መፈወሻ ጠበል የምፈልግ ሳለሁ፤
ጥግ ይዤ ቆሜያለሁ::

ያ ጠለ በረከት፤
የንስሐ እጥበት ዓመቱን ጠብቆ ይኸው ዛሬ መጣ፤
የከተማው ደቂቅ ልብሱን አወላልቆ በነቂስ ሲወጣ፤
እኔ ግን ከቤቴ በለበስኩት ቁምጣ፤
በለበስኩት ሱሬ ፤
በሥራዬ ሳይሆን በኃፍረቴ አፍሬ ፤
ራቁት ከኃጢአት ልጅነቴን ሽሬ:: 
 
ጳጉሜን 3 ፣ 2008 ዓ.ም።

___

@menfesawi_getem_ena_menebanb
@menfesawi_getem_ena_menebanb
10🥰1
2025/10/27 05:38:34
Back to Top
HTML Embed Code: