📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚
ተው ማረኝ
ተው ማረኝ እባክህ በደሌን አጥፍተህ
ሀሰት እና እውነቱን በደንብ አስገንዝበህ
የኔን ነውር ጉድፍ ሸፍነህ ደብቀህ
እንድቆም አድርገኝ አቅፈህ ተንከባክበህ
አውቃለው በደሌ እንኳን እንዲ ሊያስብል ይቅር በለኝ ጭራሽ
ፊትህ ለመቆምም የለኝ እንባን አባሽ
ባንተ የሰራውት በደሌማ በዝቶ
መቆም እንኩዋን ከብዶኝ ፊት ለፊትህ
ከቶ
በሳቄ ስር ሆኖ ሀዘንና እንባዬ
ልደብቀው ስል ነው ያጣውህ ጌታዬ
ለሰው ታይታ ስኖር መንፈሴን ዘንግቼ
ለካስ ጠፍቻለው ቀስ በቀስ ሰንብቼ
ታዲያ በዚ ጥፋት በዚኛው በደሌ
እንዴት ብዬ ልቁም ጉድፌን ተንተርሼ
ግን አንተ አባት ነህ አዳኝ የመንፈሴ
ተረከባት እና ልቤን ከነ ነብሴ
እንድሆን አድርገኝ ጀግና በሀይማኖቴ
✍ Gual Mengesha
ተው ማረኝ
ተው ማረኝ እባክህ በደሌን አጥፍተህ
ሀሰት እና እውነቱን በደንብ አስገንዝበህ
የኔን ነውር ጉድፍ ሸፍነህ ደብቀህ
እንድቆም አድርገኝ አቅፈህ ተንከባክበህ
አውቃለው በደሌ እንኳን እንዲ ሊያስብል ይቅር በለኝ ጭራሽ
ፊትህ ለመቆምም የለኝ እንባን አባሽ
ባንተ የሰራውት በደሌማ በዝቶ
መቆም እንኩዋን ከብዶኝ ፊት ለፊትህ
ከቶ
በሳቄ ስር ሆኖ ሀዘንና እንባዬ
ልደብቀው ስል ነው ያጣውህ ጌታዬ
ለሰው ታይታ ስኖር መንፈሴን ዘንግቼ
ለካስ ጠፍቻለው ቀስ በቀስ ሰንብቼ
ታዲያ በዚ ጥፋት በዚኛው በደሌ
እንዴት ብዬ ልቁም ጉድፌን ተንተርሼ
ግን አንተ አባት ነህ አዳኝ የመንፈሴ
ተረከባት እና ልቤን ከነ ነብሴ
እንድሆን አድርገኝ ጀግና በሀይማኖቴ
✍ Gual Mengesha
🍂📖🍂📖🍂📖🍂📖🍂📖🍂📖🍂📖
( ርዕስ - የንስሐ ግጥም )
አባ ስማ ድምፄን ደጅህ ቆሚያለሁኝ
የጠፋሁት ልጅህ በር እየመታሁኝ
በሀፍረት ታጥሬ እንደተሸማቀቅኩ
በፀፀት ታጅቤ እንደተኮራመትኩ
ከናፈቅኩት ቤትህ አይኔን እያማተርኩ
ቁጭ ብያለሁ ደጅህ አንተን እየጠበኩ
አባ ተመልከተኝ እንዲህ ተጎድቼ
የልጅነት መልኬን ወዜን ሁሉ አጥቼ
ካንተ የተቀበልኩት ጥሪቴን አጥፍቼ
በዚህች ወረተኛ አለም ተከድቼ
አዎን መጥቻለው ጉስቁልቁል እንዳልኩኝ
እርቃኔን ሳልሸፍን እንደተራቆትኩኝ
የህሊና እስረኛ መንገድ የጠፋብኝ
ሆኜ ቀርቻለው አለም ተጫውታብኝ
አባ ያንን ጊዜ ካንተ እንደተለየው
የዝ'ችን አለምን ጉድ ስንት ነገር አየው
ለካንስ እውነት ነው ምድር ከንቱነቷ
አያልቅም ተወርቶ ኮተታኮተቷ
አሳስቃ ወስዳ እያታለለችኝ
ይኸው አንገዋላ ከመንገድ ጣለችኝ
የምሸሸግበት ማርፍበት እስካጣ
ወዳጅ ተለውጦ እስኪሆን ባላንጣ
አይመስለኝም ነበር የጭካኔዋ ጥግ
አላስተዋልኳትም ያሻትን ስታደርግ
በርሀብ እና በጥም እየተሰቃየው
መሄድ እስኪያቅተኝ እየተንገላታው
የችግሬን ዳገት ብቻዬን ስገፋው
አልደረሰልኝም ወዳጅ ያልኩትም ሰው
ግን ጥርሴን ነክሼ ሰው ለመሆን ዳግም
ስቃይ ያደቀቀው ማንነቴን ላክም
በጉልበቴ ድኼ እንዲያ ስፍገመገም
ያን ጊዜ አየሁት ፊት ለፊቴ ሲቆም
ትንሿን ተስፋዬን ድጋሜ ሊያጨልም
ለካን ውሸት ኖሯል ፍቅራችን የይምሰል
ለካን ለጌጥ ሆኗል የለበስነው መስቀል
ይሄኔ ነው ታዲያ ልቤ ቤትህን ናፍቆ
ይቅርታ ሊጠይቅ ከእግሮችህ ስር ወድቆ
የመጣው በድፍረት ተስፋውን ሰንቆ
አባ አደራህን እንዳትጨክንብኝ
በርህን ለመክፈት እንዳትዘገይብኝ
በመከራ ምክር በጣም ስለደከምኩ
መኖር መርጫለው ለአንተ እያገለገልኩ
እንጂማ ከእንግዲህ ሌላም እቅድ የለኝ
አባ ቶሎ መተህ እንዳረከኝ አርገኝ
ወዲህ ወዲያም ሳልል ቆሚያለው በርህ ላይ
በይቅርታ አይኖችህ ዳግም እስከምታይ
ፈራ ተባ እሚለው ልቤን እየሞገትኩ
እስካሁን በርህ ለይ እንደተኮራመትኩ
ቁጭ ብያለው እና አንተን እየጠበኩ
አባ ናልኝ ባክህ ኧረ እኔስ ተጨነኩ
አንዴ ብቻ መተህ በሩን ከፍተህ ካየህ
በልጅህ መሰበር ስንቱን ታስባለህ
ግን አንድ እውነት እወቅ ከመምጣትህ በፊት
በርህን ደብድቤ ብጣራም በድንገት
አጥፍቼው ብመጣም ያንን ሁሉ ንብረት
ገንዘብ የማይገዛው ልብን ገዝቻለው
ከትናንቱ ግብሬ ዛሬ ተሽያለው
ስለዚህ ስትመጣ በሩን ልትከፍትልኝ
በዛሬ እኔነቴ እንድትቀበለኝ
ከቤት አስገብተህ አገልጋይህ አድርገኝ
ልጅህ ልባል እንደው አልሻም ከ'ንግዲህ
አገልጋይህ ሆኜ ልሩጥ ወዲያ ወዲህ
አዎን አባ መጥተህ በሩን ስትከፍትልኝ
አልሻም ድጋሚ
የአባትነት ዋጋን እንድትከፍልልኝ
ከቤታችን ካሉት ከአገልጋዮች ጋራ
እንድትፈቅድልኝ አብሬ እንድሰራ
እለምንሀለው እሺ በለኝ ባክህ
ያንን የትናንቱን ደጉን ቀን አስበህ
እንጂማ እንደግብሬ እንደ'ኔማ ቢሆን
አንተን ባልፈለኩህ ወዳጁ አውሬ ሲሆን
በቃኝ ስልችቶኛል ደክሞኛል እንግልት
በደንብ ገብቶኛል የምድር ከንቱነት
ላልመልሰው ፊቴን እርም ይሁን ብያለው
ቤትህ ነው አለሜ አባ ተምሪያለው!!!
======///========
ለሁላችንም መሃሪ ይቅር ባይ አምላካችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለንስሐ ሞት ያብቃን 🙏
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን !

ፍቅር ሳበው ከአርያም
ወዶን በፈቃዱ ፥ አፍቅሮን በብዙ
ክፋት በዳላችን ፥ ሀጢያት ድንግዝግዙ
ሳይገድበው እራሱን ፥ ዝቅ ብሎ ለእኛ
እራሱን አዋርዶ ፥ ከበረት ቢተኛ
የአለሙ ንጉስ ፥ ቸሩ ደጉ ጌታ
ዕዳችንን ከፍሎ ፥ በፍቅሩ ሊረታ
ሻረው የኛን በደል ፥ በደሙ አንፅቶ
ሀዘናችን ጠፋ ፥ እርሱ ለኛ ሞቶ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••
ፅድቃችን እንደመርገም ፥ ስራችን ከንቱ መድከም
ቢሆንብን ጊዜ ፥ ተስፋችን ቢጨልም
አንዳችም ሳይሻ ፥ ሳይለካ ሳይቆጥር
ተጨነቀ ጌታ ፥ ተንገላታ በምድር
ወዳጆቹን እንዲው ወዶ ካለ ሰበብ
ህማምን ሲቀበል በጉን ለመሰብሰብ
ከቶ ምን ሊጠቅመው ፥ ለእርሱ እኛን ማፍቀር
ነገር ግን ወደደን ፥ በፍፁም ሳይለያይ አንዳችም ሳያስቀር
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አማኑኤል ጌታ ፥ አለምን ቢፈጥር
በቃሉ ቢያፀና ፥ ሰማይ እና ምድር
ምን ግሩም ያሰኛል ፥ እጅግ ያስደንቃል
ሀያል ንጉስ እንዴት ፥ ከመስቀል ይውላል???
ከጥልቁ ተጥለን ፥ መከራን ውስጥ ሳለን
ታስሮልን በምትክ ፥ ተገርፎ ሊያስምረን
በህማም ሲገረፍ ፥ ሰይጣንን ቀጥቅጦ
ህይወትን ሰጠን ፥ ሞትን ውጦ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
እንደ በግ ታስሮ ወረደ
ስለ ፍቅር ተሰደደ
ታሞ ዋለ ተቸንክሮ
በመስቀል ላይ አቀርቅሮ
ፈራጅ ጌታ ቆሞ እርቃኑን
ጎንበስ ብሎ ሲያይ ልጆቹን
ከፍሎ ዋጋ ሰበሰበ
የራቅነውን አቀረበ
ትሁት የዋህ አዛኝ መሪ
ቸር እረኛ ግሩም ሰሪ
ፍቅር ሳበው ከዙፋኑ ፥ ከአርያም ወረደልን
ከበደል ሊያነፃን ፥ ስጋ ደሙን ሰጠን
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አይለካም ቁጥር የለው
አይባልም እስከዚህ ነው
በምህረቱ ይጠብቃል
በፍቅር አይኑ ህዝቡን ያያል
አይቀየር ሁሌም እርሱ
አይቀንስም ፍቅር ከእርሱ
ስለጠሉት የማይጠላ
ስለገፉት የማይገፋ
ስለረሱት የማይረሳ
እየጣሉት የሚያነሳ
እግዚአብሔር ጌታ... ...የፍጥረታት አባት
በፍቅሩ እሳት ይቺን አለም የሚያቆማት
✍✍ ብሩክ ተፈራ

🤲🤲🤲🤲🤲አቤቱ🤲🤲🤲🤲🤲
አምላክ በፍቃዱ በአምሳሉ ፈጠረ
ሰውን ባፈጣጠር ውብ አርጎ አከበረ
ጌታ በፍጥረቱ ሊወደስ ሊቀደስ
ከአፈር አበጃጅቶ ሲባርክ ሲያነግስ
ሁሉን ሙሉ አድርጎ አስተካክሎ ቅድሚያ
ልጁን እፍ ብሎ አስገኘው ከትቢያ
የምስጋና ጣዕም የውዳሴን ዜማ
በከንፈሩ ፍሬ አርጎት እንዲስማማ
ከሁሉ አልቆ አከበረው ሰውን
አደለው ሸለመው ጥበብ ማስተዋልን
ሰው ግን...ሰው ግን ረከሰ ቆሸሸ በስራው
ሀጥያት ክፋት ተንኮል ሆኖት መሸሸጊያው
አካሉ እና መልኩ ግሩም ሆኖ ሳለ
በግብሩ መጠልሸት ተዋርዶ ቀለለ
አቤቱ....አምላኬ.....ምንኛ አጥፍተን አሳዝነን ይሆን
በክፋት በሀጢአት.....አንተን ብዙ በደልን
ነውራችን ገነነ ድካማችን በዛ
ስጋችን ደቀቀ ነፍሳችን ደንዝዛ
ወደቅን....ከሰርን አንተን አጣን ጌታ
ሀዘን ከቦን ወሮን ሸሸ ከኛ ደስታ
አቤቱ...አምላኬ...ገድለናል ሰርቀናል ዋሽተናል በብርቱ
ስራችን ከርፍቶ ሆኖብናል ከንቱ
ዝሙትን ሰርተናል ስምህን አምተናል
ረክሰናል በሀጥያት ቀለናል ገምተናል
ያልበደልነው በደል ያልነካነው ክፋት
ያልሰራነው ሴራ ያልገለጥነው ትዕቢት
ምንም የለም ከቶ....ሁሉን አዳርሰናል
አንዳችም ሳናስቀር ሀጥያትን ሰርተናል
እናም...እናም...አንተ ቸር ፈጣሪ ሁሉን ቻይ ነህና
ክቡር....ቅዱስ ሀያል ነህና ገናና
አንፃን ከስራችን ማረን በይቅርታ
በንስሀ አጥበህ አርገን የበረታ
✍ብሩክ ተፈራ
አምላክ በፍቃዱ በአምሳሉ ፈጠረ
ሰውን ባፈጣጠር ውብ አርጎ አከበረ
ጌታ በፍጥረቱ ሊወደስ ሊቀደስ
ከአፈር አበጃጅቶ ሲባርክ ሲያነግስ
ሁሉን ሙሉ አድርጎ አስተካክሎ ቅድሚያ
ልጁን እፍ ብሎ አስገኘው ከትቢያ
የምስጋና ጣዕም የውዳሴን ዜማ
በከንፈሩ ፍሬ አርጎት እንዲስማማ
ከሁሉ አልቆ አከበረው ሰውን
አደለው ሸለመው ጥበብ ማስተዋልን
ሰው ግን...ሰው ግን ረከሰ ቆሸሸ በስራው
ሀጥያት ክፋት ተንኮል ሆኖት መሸሸጊያው
አካሉ እና መልኩ ግሩም ሆኖ ሳለ
በግብሩ መጠልሸት ተዋርዶ ቀለለ
አቤቱ....አምላኬ.....ምንኛ አጥፍተን አሳዝነን ይሆን
በክፋት በሀጢአት.....አንተን ብዙ በደልን
ነውራችን ገነነ ድካማችን በዛ
ስጋችን ደቀቀ ነፍሳችን ደንዝዛ
ወደቅን....ከሰርን አንተን አጣን ጌታ
ሀዘን ከቦን ወሮን ሸሸ ከኛ ደስታ
አቤቱ...አምላኬ...ገድለናል ሰርቀናል ዋሽተናል በብርቱ
ስራችን ከርፍቶ ሆኖብናል ከንቱ
ዝሙትን ሰርተናል ስምህን አምተናል
ረክሰናል በሀጥያት ቀለናል ገምተናል
ያልበደልነው በደል ያልነካነው ክፋት
ያልሰራነው ሴራ ያልገለጥነው ትዕቢት
ምንም የለም ከቶ....ሁሉን አዳርሰናል
አንዳችም ሳናስቀር ሀጥያትን ሰርተናል
እናም...እናም...አንተ ቸር ፈጣሪ ሁሉን ቻይ ነህና
ክቡር....ቅዱስ ሀያል ነህና ገናና
አንፃን ከስራችን ማረን በይቅርታ
በንስሀ አጥበህ አርገን የበረታ
✍ብሩክ ተፈራ
ሀሰት በከበባት ኢ ፍትሀዊ አለም ተከሳሽ በሙሉ ወንጀለኛ አይደለም
አይገርምም ...?
የሚታዘዙለት ሳርና ንፋሱ ሀጢአት የሌለባት ንፁህ ሳለች ነፍሱ
ወንጀለኛ ተብሎ ፤
ተከሳሽ ነበረ ክርስቶስ እራሱ፡፡
By Eyob Z Mariam
አይገርምም ...?
የሚታዘዙለት ሳርና ንፋሱ ሀጢአት የሌለባት ንፁህ ሳለች ነፍሱ
ወንጀለኛ ተብሎ ፤
ተከሳሽ ነበረ ክርስቶስ እራሱ፡፡
By Eyob Z Mariam
በየሰፈሩ ሰፍረን
በየአጥሩ ተንጠልጠለን
አድዋን ያህል
አድባር ጥለን
ካምና ርቀን
ዛሬን ንቀን
ነገን ናፍቀን
መራመዱ እየጨነቀን
በየጥጉ ተናንቀን
ቀኑን ማሰብ እስኪያስፈራው
የታለ ባለፈረሱ?
የታለ ባለ ባንዴራው?
የታል የትውልድ አደራው?
አድዋን ያህል ትልቅ ጥለት
አድዋን ያህል ህብር ቀለም
ክብሩ ገብቶን
ፍሬው ታይቶን
ሳንደምቅበት ተያይዘን
ሳንኮራበት ታሪክ መዘን
በጊዜ ፊት እንዲህ ፈዘን
ያከበረን ያስከበረን
ኩራት ሆኖ ያዘለቀን
አድዋ ያህል ዘ ላ ለ ም ቀን
ስሙን መጥራት
ድሉን ማሰብ ተናነቀን?!
By Thomas lemma
እንኳን አደረሳቹህ
በየአጥሩ ተንጠልጠለን
አድዋን ያህል
አድባር ጥለን
ካምና ርቀን
ዛሬን ንቀን
ነገን ናፍቀን
መራመዱ እየጨነቀን
በየጥጉ ተናንቀን
ቀኑን ማሰብ እስኪያስፈራው
የታለ ባለፈረሱ?
የታለ ባለ ባንዴራው?
የታል የትውልድ አደራው?
አድዋን ያህል ትልቅ ጥለት
አድዋን ያህል ህብር ቀለም
ክብሩ ገብቶን
ፍሬው ታይቶን
ሳንደምቅበት ተያይዘን
ሳንኮራበት ታሪክ መዘን
በጊዜ ፊት እንዲህ ፈዘን
ያከበረን ያስከበረን
ኩራት ሆኖ ያዘለቀን
አድዋ ያህል ዘ ላ ለ ም ቀን
ስሙን መጥራት
ድሉን ማሰብ ተናነቀን?!
By Thomas lemma
እንኳን አደረሳቹህ
ከዳመናው መሀል ይፈልቃል ኃያል ጢስ
ድል ለሀገሬ ሊሰጥ
በፈረሱ ይነጉዳል የአራዳው ጊዮርጊስ
ይዘምታል በሰማይ አማኝ ህዝቡን ከልሎ
የአምላክ ውብ ምድር
ቅድስት ኢትዮጵያ አትደፈር ብሎ
ይጎርፋል ሰው
ጦር ጋሻውን በእጁ አንጠልጥሎ
ምንሽር አልቤኑን በጀርባው ላይ አዝሎ
በባዶ እግሩ ጋሬጣውን ረቶ
እንዴትስ ይቀራል
ከንጉሱ ከንፈር የማርያም ስም ወጥቶ
ልክ እንደ ጦር እቃ ታቦት ተሸክሞ
ልክ እንደ አዘቦት ቀን በጾም ተሸልሞ
ቅንጣት እህል ሳይጎርስ በእምነቱ ቁሞ
ቅዳሴውን ሳይሽር በሰዓቱ ተገኝቶ
‹‹አሀዱ›› ሲል በህብረት አንድነት ገንብቶ
የዋለ ገበሬ የዋለ ሰራዊት
ድል አፍሶ ቢመለስ ይደንቃል ወይ ጥቂት?
(አይደንቅም)
አቡነ ማቲዎስ እምነትን አግዝፈው
ለሰራዊት ሲባል
‹‹ጾም ይሻር›› የሚል ትእዛዝ ተላልፈው
ከንጉስ ተሟግተው
በመስቀል አሳልመው
ባርከው ተዋጊውን ቢልኩ ወደ ውጊያ
ሰው በእህል ሳይሆን
በእምነት እንደሚረታ
ምስክር ትሆን ዘንድ አሸነፈች ጦቢያ
እኔ ግን
የድል ታሪክ ይዤ
ቆሚያለሁ ፈዝዤ
ተኝቻለሁ ደንዝዤ
አልስራ ጀብድ አልፈጽም ገድል
እንዴት ያቅተኛል
መዘከር እንኳን የአባቶቼን ድል?
ቢገባኝ ኖሮ የነጻነት ክብር
የካቲት ጊዮርጊስ
ስዕለት ባስገባሁ ለመቆሜ ተአምር
በባዶ እግር ሄዶ ጫማ ያለበሰኝ
ከአራቱም አቅጣጫ
ለአንድ አላማ ዘምቶ ሀገር ያወረሰኝ
በዘር ጎጠኝነት
ተከፋፍዬ ቢያይ በእንባው በወቀሰኝ
‹‹ ከአንድነት እርካብ ቁልቁል ተፈጥፍጠህ
በቁንጽል ማንነት ራስክን ለውጠህ
የምትኖር ሁላ አድዋን አስታውሰህ
ሁን እንደ ጥንቱ ፍቅርን ተንተርሰህ
አሻፈረኝ ካልክ ግን
‹‹ማርያምን!›› እፋረድኃለው በሰማይ
በሀገሬ ጀርባ ላይ ፈልተኃል እንደ ተባይ ››
ብሎ ባወጀብኝ
ሽልብታዬን አይቶ
እብደቴን ታዝቦ ከሞቴ ባነቃኝ
ጾም ጸሎትን ትቼ
አርብ ሮብን ረስቼ
ቅዳሴ ሰዓታት
ማህሌት ኪዳንን እኒህን ዘንግቼ
ለሆዴ አድሬ ስኖር እንደ አሳማ
ይደንቃል ወይ እውነት
ተረግጬ ብቀር ልክ እንደ ቄጤማ?
ተንኜ ብቀር ልክ እንደ ጤዛ?
ተሸንፌ ብታይ ወድቄ እንደ ዋዛ?
(አይደንቅም)
ዋ ለእኔ!
ዋ እኔ!
ርግብ ጋር ዘምቼ
ለቀረሁኝ ሞቼ
#ኤልዳን
ድል ለሀገሬ ሊሰጥ
በፈረሱ ይነጉዳል የአራዳው ጊዮርጊስ
ይዘምታል በሰማይ አማኝ ህዝቡን ከልሎ
የአምላክ ውብ ምድር
ቅድስት ኢትዮጵያ አትደፈር ብሎ
ይጎርፋል ሰው
ጦር ጋሻውን በእጁ አንጠልጥሎ
ምንሽር አልቤኑን በጀርባው ላይ አዝሎ
በባዶ እግሩ ጋሬጣውን ረቶ
እንዴትስ ይቀራል
ከንጉሱ ከንፈር የማርያም ስም ወጥቶ
ልክ እንደ ጦር እቃ ታቦት ተሸክሞ
ልክ እንደ አዘቦት ቀን በጾም ተሸልሞ
ቅንጣት እህል ሳይጎርስ በእምነቱ ቁሞ
ቅዳሴውን ሳይሽር በሰዓቱ ተገኝቶ
‹‹አሀዱ›› ሲል በህብረት አንድነት ገንብቶ
የዋለ ገበሬ የዋለ ሰራዊት
ድል አፍሶ ቢመለስ ይደንቃል ወይ ጥቂት?
(አይደንቅም)
አቡነ ማቲዎስ እምነትን አግዝፈው
ለሰራዊት ሲባል
‹‹ጾም ይሻር›› የሚል ትእዛዝ ተላልፈው
ከንጉስ ተሟግተው
በመስቀል አሳልመው
ባርከው ተዋጊውን ቢልኩ ወደ ውጊያ
ሰው በእህል ሳይሆን
በእምነት እንደሚረታ
ምስክር ትሆን ዘንድ አሸነፈች ጦቢያ
እኔ ግን
የድል ታሪክ ይዤ
ቆሚያለሁ ፈዝዤ
ተኝቻለሁ ደንዝዤ
አልስራ ጀብድ አልፈጽም ገድል
እንዴት ያቅተኛል
መዘከር እንኳን የአባቶቼን ድል?
ቢገባኝ ኖሮ የነጻነት ክብር
የካቲት ጊዮርጊስ
ስዕለት ባስገባሁ ለመቆሜ ተአምር
በባዶ እግር ሄዶ ጫማ ያለበሰኝ
ከአራቱም አቅጣጫ
ለአንድ አላማ ዘምቶ ሀገር ያወረሰኝ
በዘር ጎጠኝነት
ተከፋፍዬ ቢያይ በእንባው በወቀሰኝ
‹‹ ከአንድነት እርካብ ቁልቁል ተፈጥፍጠህ
በቁንጽል ማንነት ራስክን ለውጠህ
የምትኖር ሁላ አድዋን አስታውሰህ
ሁን እንደ ጥንቱ ፍቅርን ተንተርሰህ
አሻፈረኝ ካልክ ግን
‹‹ማርያምን!›› እፋረድኃለው በሰማይ
በሀገሬ ጀርባ ላይ ፈልተኃል እንደ ተባይ ››
ብሎ ባወጀብኝ
ሽልብታዬን አይቶ
እብደቴን ታዝቦ ከሞቴ ባነቃኝ
ጾም ጸሎትን ትቼ
አርብ ሮብን ረስቼ
ቅዳሴ ሰዓታት
ማህሌት ኪዳንን እኒህን ዘንግቼ
ለሆዴ አድሬ ስኖር እንደ አሳማ
ይደንቃል ወይ እውነት
ተረግጬ ብቀር ልክ እንደ ቄጤማ?
ተንኜ ብቀር ልክ እንደ ጤዛ?
ተሸንፌ ብታይ ወድቄ እንደ ዋዛ?
(አይደንቅም)
ዋ ለእኔ!
ዋ እኔ!
ርግብ ጋር ዘምቼ
ለቀረሁኝ ሞቼ
#ኤልዳን
፫
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ እውነተኛ ጾም፤ ስለ ሐሜት...በተናገረበት ድርሳኑ እንዲህ አለ፦
....እንኪያስ የነነዌ ሰዎች እንዴት አድርገው እንደ ጾሙና እንዴት ከዚያ [የእግዚአብሔር] ቊጣ ሊድኑ እንደ ቻሉ እንመልከት "ሰዎችና እንስሶች ላሞችና በጎች አንዳችን አይቅመሱ" ይላል ነቢዩ (ዮና.3፥7)፡፡
አንተ ነቢይ! ምን እያልክ ነው? እስኪ ንገረኝ! ግዕዛን የሌላቸው እንስሳት እንኳን ሳይቀሩ ሊጾሙ፣ ፈረሶችና በቅሎዎችም ማቅ ሊለብሱ ግድ ነውን? “አዎ! እነርሱም ቢኾኑ ሊጾሙ ደግሞም ማቅ ሊለብሱ ግድ ነው" ብሎ ይመልሳል፡፡ ምክንያቱም አንዳንድ ባለጸጎች በሞቱ ጊዜ ዘመድ አዝማዱ፣ የወንድም የሴትም አገልጋዮች ብቻ ሳይኾኑ ፈረሶችም ቢኾኑ የኀዘናቸውን ታላቅነት ለማሳየት ሰው ኹሉ እንዲያለቅስ ለማድረግ ማቅ እንዲለብሱ፣ በጋላቢዎቻቸው አማካኝነት የመቃብሩን ሥፍራ እንዲዞሩ ይደረጋሉና፡፡ በመኾኑም የነነዌ ከተማ ልትጠፋ በተቃረበች ጊዜ ግዕዛን የሌላቸው እንስሳትም ቢኾነ ማቅ ለብሰዋል፤ አርዑተ ጾምንም (የጾምን ቀንበር) ተሸክመዋል፤ እንዲህ ለማለት “እነዚህ እንስሳት የእግዚአብሔርን ቊጣ በአመክንዮ ሊረዱት አይችሉም፤ ስለዚህ ይህ ቊጣ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዘ እንደ ኾነ በጾም እንዲገባቸው አድርጉ፡፡ ከተማይቱ ከተገለበጠች መቃብራችን የምትኾነው ለእኛ ለነዋሪዎቿ ብቻ ሳይኾን ለእንስሳቱም ጭምርነውና፡፡ ስለዚህ የቅጣቱ ገፈት ተካፋዮች የሚኾኑ ከኾነ ከጾሙም ተካፋዮች ይኹኑ፡፡" ነቢያቱ ኹልጊዜ ሲፈጽሙት የኖሩና የነነዌ ሰዎች ይህንን ሲያደርጉ ዓላማ ያደረጉት ሌላም ነገር ነበር፡፡
ሰብአ ነነዌ ከሰማያት እጅግ አስፈሪ የኾነ ቍጣ እየመጣ እንደ ኾነ ሲመለከቱ፣ ለራሳቸው ምንም ምን ሳይሉ ሊቀጡ ያሉት እንስሳቱም፡- ማቅ ለብሰው፣ ጥቂት ምሕረት ወይም ይቅርታ እንኳን የማይገባቸው ኾነው፣ ምን እንደሚያደርጉ ወይም ለተግሣጻቸው ረዳትን ከየት ማግኘት እንዳለባቸው ሳያውቁ፥ ግዕዛን የሌላቸው ፍጥረታትን መሸሸጊያ አደረጉ፤ አሟሟታቸው እጅግ አሳዛኝ እንደ ኾነ በመግለጽ በእነርሱ አማካኝነት ምልጃን አቀረቡ፤ ኀዘናቸውንና ጥፋታቸውን እንደ ልመና አቀረቡ፡፡ ስለኾነም በቀደመው ጊዜ እስራኤላውያን ረሀብ በገጠማቸውና አገራቸውንም ትልቅ ድርቅ በመታው ጊዜ እንደዚሁም ኹሉም ነገሮች በወደሙ ሰዓት ከነቢያቶቹ አንዱ እንዲህ አለ፡- “ጊደሮች ከምሳጋቸው ጠፉ፤ ማሰማሪያ የላቸውምና የላምም መንጎች እጅግ ጮኹ፤ እንስሶችም ኹሉ ወደ ላይ ወደ አንተ አንጋጠጡ ፈሳሹ ውኃ ደርቆአልና" (ኢዩ.1፡17)፡፡ ሌላ ነቢይም ከድርቁ የተነሣ እያለቀሰ እንዲህ ብሏል፡- “ዋላ ደግሞ በምድረ በዳ ወለደች፤ ሣርም የለምና ግልገልዋን ተወች፡፡ የሜዳ አህዮችም በወና ኮረብታ ላይ ቆመዋል፤ እንደ ድራጎንም ወደ ነፋስ አለከለኩ፤ ልምላሜም የለምና ዓይኖቻቸው ጠወለጉ” (ኤር.14፡5-6)፡፡ ዳግመኛም ነቢዩ ኢዩኤል ዛሬ እንዲህ ሲል ሰምታችሁታል፡- “ሙሽራው ከእልፍኙ ሙሽራይቱም ከጫጉላዋ ይውጡ፤ ጡት የሚጠቡትን ሕፃናት ሰብስቡ” (ኢዩ.2፡16)፡፡
እንግዲህ እንጠይቅ! እንዲህ ሕፃናት እንዲጸልዩ የሚጠራቸው ስለ ምን ምክንያት ነው? “ለዓቅመ አዳምና ለዓቅመ ሔዋን የደረሱ ሰዎች ኹሉም የእግዚአብሔርን ቍጣ ስለ ቀሰቀሱ፥ እነዚያ በደል በማይሠራበት ዕድሜ ላይ ያሉ ሕፃናት የተቈጣዉን እግዚአብሔርን ይለምኑት” ሲል ነው፡፡
ነገር ግን አስቀድሜ እንደተናገርኩት ይህ ታላቅ የኾነውን የእግዚአብሔርን ቍጣ በምን ምክንያት እንደ ቀረ ማየት አለብን፡፡ እናስ በጾማቸውና ማቅ በመልበሳቸው ብቻ ነበርን? እንዲህስ አንልም፤ ኹለንተናዊ ሕይወታቸው ስለ ተቀየረ ነው እንላለን እንጂ፡፡ ይህስ ከመቼ ጀምሮ ያሳዩት ነው? ገና ነቢዩ ከመናገሩ አንሥቶ! ምክንያቱም ስለ እግዚአብሔር ቍጣ ስለ ጾማቸው የነገረን እርሱ ስለ ዕርቃቸውና የመታረቃቸው ዋናው ምክንያቱ ምን እንደ ኾነ ሲነግረንም እንዲህ ብሏል፡- “እግዚአብሔርም ሥራቸውን አየ” (ዮና.3፡10)፡፡ ምን ዓይነት ሥራቸውን ነው? መጾማቸውን ነውን? [ወይስ] ማቅ መልበሳቸውን ነውን? እግዚአብሔር ያየው ይህንን አይደለም፤ እነዚህን ኹሉ ነጥቦች አልፎ እንዲህ ብሎ ይጨምራልና፡- “ከክፉ መንገዳቸው እንደ ተመለሱ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም፡፡” እንግዲህ ከዚህ ቍጣ ያዳናቸው፣ በእነዚህ አሕዛብ ላይ እንዲራራና ምሕረቱን እንዲሰጣቸው ያደረገው የሕይወታቸው ለውጥ እንጂ ጾማቸው እንዳልኾነ ታያለህን?
እነዚህን ነገሮች የምናገራቸው ግን ጾምን ለማንኳስስ ብዬ አይደለም፤ ጾምን እንድናከብር ነው እንጂ፡፡ ጾምን ማክበር ማለት ከምግበ ሥጋ መከልከል ብቻ ሳይኾን ከምግባረ ኃጢአትም ጭምር ነውና፡፡ ጾምን ይበልጥ የሚያቃልለው ሰው እየጾምኩ ነው ብሎ ራሱን ከምግብ ብቻ የሚከለክል ሰው ነውና፡፡
ይቀጥላል....
(ትምህርት በእንተ ምክንያተ ሐውልታት፣ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ገጽ 79-96 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)

ይነበብ❗️
የነገ ሟች የዛሬ ሟችን ይቀብራል !!
ከ150 ዓመታት በኋላ ዛሬ በህይወት ካለነው ሰዎች አንዳንችም በህይወት አንገኝም፡፡ዛሬ ላይ ከምንታገልላቸው ነገሮች 70 በመቶ የሚሆኑት ከ150 ዓመታት በኋላ አንዳቸውም ለምልክት እንኳ አይገኙም ፈፁመው ይጠፋሉ ይረሳሉ፡፡
እስኪ ወደ ኋላ 150 ዓመታት እንሂድ፡፡ወቅቱ 1872 ገደማ ነው የሚሆነው፡፡ያኔ የሰው ልጅ እንደ እቃ በአደባባይ ተደርድሮ የሚሸጥበት ወቅት ነበር፡፡በወቅቱ ብርቅ የነበረውን የፊት መስታወት ለማግኘት ሲሉ የገዛ ዘመዶቻቸውን የሸጡ ሰዎች ዛሬ የታሉ? መስታወትንስ ዛሬ ላይ እንደ ሀብት የሚያስበው ማን ነው? ማንም፡፡
ጨው ወይም ጌጥ ወይም ሌላ ነገር ለማግኘት ሲሉ የተሻሻጡ ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡ዛሬ ላይ እነዚያ ሰዎች የሞቱላቸው የገደሉላቸው የተካካዱባቸው የተሻሻጡላቸው አብዛኞቹ ነገሮች ይህ ነው የሚባል የረባ ዋጋ ያላቸው አይደሉም፡፡በጊዜው ግን ለሰው ልጅ የሞትና የህይወት ልዩነት ነበሩ፡፡የሰው ልጅ በየጊዜው የሚታገልላቸው አብዛኞቹ ነገሮች ዛሬ ላይ ዞር ተብለው ሲታዩ በጣም የሚያስቁ ናቸው፡፡
አስታውሳለሁ የሀይስኩል ተማሪ እያለሁ የትምህርት ቤቱ ፌመስ ለመሆን ብዙ ነገር አደርግ ነበር፡፡ዛሬ ከጥቂት አመታት በኋላ እንኳን ያኔ የነበረኝን ዝና ቀርቶ በትምህርት ቤቱ መማሬንም የሚያስታውስ ሰው የለም፡፡አስቡት የዛሬ 150 ዓመታት ደግሞ … ጭራሽ ትምህርት ቤቱም ላይኖር ይችላል፡፡
አሁን አሁን ላይ ዘመኑ የኢንተርኔት በመሆኑ ኢንተርኔት ትዝታችንን ያስቀምጥልናል ብለን እናስብ ይሆናል፡፡ግን እስኪ በዚህ ዘመን እንኳ ዝነኛ የሆኑትን እናስታውስ፡፡ማይክል ጃክሰን በጊዜው ዝነኛ ነበር፡፡ነገር ግን ከሞተ ገና ሁለት አስርት አመታት እንኳ ሳይሞላው እየተረሳ ነው፡፡ዛሬ ላይ ካለው ትውልድ ማይክልን የሚያስታውሰው በጣም ጥቂቱ ነው፡፡እሱንም ገና ካወቁት ነው፡፡ ከ150 ዓመታት በኋላ ደግሞ ማይክል ጃክሰን የሚለው ስም ጨርሶ ለማንም የማይታወቅ ይሆናል፡፡
ማጠቃለያው ህይወትን ቀለል አድርገህ ኑር፡፡ምንም ሆነ ምንም ዘላለም የሚኖር የለም፥ ከዚህች ምድር በህይወት የሚወጣ ሰውም የለም፡፡ዛሬ ልትሞትለት እና ልትገድልለት የተዘጋጀኸው መሬት ከዚህ ቀደምም ብዙዎች ተጋድለውለት ሞተው ጭራሽ እንዳልነበሩ ሆነው ተረስተዋል፡፡
ከ150 ዓመታት በኋላ ዛሬ አንተ እንደ ትልቅ ሀብት የምታያቸው አብዛኞቹ ነገሮች ምንም ፋይዳ የሌላቸው ተራ ቁሶች ይሆናሉ፡፡እና ምን ለማለት ነው ፥ ፍቅር ይግዛን ፥ መጠላለፍ ከጀርባ መወጋጋት መቀናናት መፎካከር ይቅርብን፡፡ህይወት ከማንም ጋር የምታደርገው ፉክክር አይደለችም፡፡ቀደምንም ዘገየንም መጨረሻችን መቃብር ነው፡፡ ለዚች ምድር ዘላለማዊ ሳይሆን ተረኛ ነዋሪ ነን፣ነገ የምናልፍ።
(ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ)

የሴትነት ከፍታ እናት ናት።
ብልኽ ናት። አይመስልኽም እንጂ ከእሷ በላይ የሚረዳኽ የለም፤ ሳትናገር ነው የምታውቅኽ። እንጠባይኽ ብላ ያየችውን እንዳላየች ስለምታልፍና ነጻነትኽን ከማንም በላይ ስለምትጠብቅ እንጂ ስለአንተ ከራስኽ በላይ ታውቃለች።
እስከመጨረሻው አብራኽ የምትጓዘው እናትኽ ናት። ካላመንኸኝ በዕለተ ዐርብ እስከመስቀል አብሮት ማን እንደነበር እስከሞት የደረሰውን ጌታ ጠይቀው።
ሴት ልጅ የምትከብረው በመውለድ እንደኾነ ቅዱሱ መጽሐፍም ይነግርኻል። ስትወልድ የሰውነት ኹሉ ልክ ትኾናለች። ከፈጣሪኽ በታች አምላክኽ ትኾናለች።
እናትኽ...
ስትጨልም አብራኽ ትጨልማለች፣ ስትሰንፍ ፍጹም ልታበረታኽ አብራኽ ትሰንፋለች፣ ብርታቷን ልታጋባብኽ በወረት ሳይኾን በፍጹም ፍቅር የምትጥር ናት።
እሷ ጋር የአንተ በሽታ በሽታዋ ነው። ስለአንተ ደኅንነት እንጂ ለበሽታኽ ግድ አይሰጣትም።
እሷ ጋር የአንተ ዝቅተኛነት ሳይኾን መኖርኽ ብቻ ዋጋ አለው።
እሷ ጋር ከአንተ ሐዘን በላይ የሚያሳዝናት የለም።
እሷ ጋር ደሀ ብትኾንም ሀብትዋ እንደኾንኽ ትቆጥራለች።
እሷ ጋር መለዋወጥ፣ በአንተ ተስፋ መቁረጥ የለም።
ሰዎች መልክኽን፣ ዕውቀትኽን፣ ሞራልኽን፣ ሕመምኽን፣ ችግርኽን፣ ስንፍናኽን ተመልክተው ሊሸሹኽ፤ አይረባም ብለው ከሕይወታቸው ሊያስወጡኽና ተስፋ ሊቆርጡብኽ ይችላሉ።
እናትኽ ግን ስትወልድኽ እንደተደሰተችው ኹሉ እስከሕቅታዋ ድረስ ያው በአንተ ደስተኛ ናት።
ስለምታደርግላት አይደለም...በቃ ስላለኻት ስለተወለድኽላት ብቻ ደስተኛ ናት።
ከእሷ ውጪ የአምላክኽ ምድራዊ አምሳል ማን ሊኾን ይችላል?
ማንም የማይተካት የፈጣሪኽ ጸጋ ናት።
ብልኽ ናት። አይመስልኽም እንጂ ከእሷ በላይ የሚረዳኽ የለም፤ ሳትናገር ነው የምታውቅኽ። እንጠባይኽ ብላ ያየችውን እንዳላየች ስለምታልፍና ነጻነትኽን ከማንም በላይ ስለምትጠብቅ እንጂ ስለአንተ ከራስኽ በላይ ታውቃለች።
እስከመጨረሻው አብራኽ የምትጓዘው እናትኽ ናት። ካላመንኸኝ በዕለተ ዐርብ እስከመስቀል አብሮት ማን እንደነበር እስከሞት የደረሰውን ጌታ ጠይቀው።
ሴት ልጅ የምትከብረው በመውለድ እንደኾነ ቅዱሱ መጽሐፍም ይነግርኻል። ስትወልድ የሰውነት ኹሉ ልክ ትኾናለች። ከፈጣሪኽ በታች አምላክኽ ትኾናለች።
እናትኽ...
ስትጨልም አብራኽ ትጨልማለች፣ ስትሰንፍ ፍጹም ልታበረታኽ አብራኽ ትሰንፋለች፣ ብርታቷን ልታጋባብኽ በወረት ሳይኾን በፍጹም ፍቅር የምትጥር ናት።
እሷ ጋር የአንተ በሽታ በሽታዋ ነው። ስለአንተ ደኅንነት እንጂ ለበሽታኽ ግድ አይሰጣትም።
እሷ ጋር የአንተ ዝቅተኛነት ሳይኾን መኖርኽ ብቻ ዋጋ አለው።
እሷ ጋር ከአንተ ሐዘን በላይ የሚያሳዝናት የለም።
እሷ ጋር ደሀ ብትኾንም ሀብትዋ እንደኾንኽ ትቆጥራለች።
እሷ ጋር መለዋወጥ፣ በአንተ ተስፋ መቁረጥ የለም።
ሰዎች መልክኽን፣ ዕውቀትኽን፣ ሞራልኽን፣ ሕመምኽን፣ ችግርኽን፣ ስንፍናኽን ተመልክተው ሊሸሹኽ፤ አይረባም ብለው ከሕይወታቸው ሊያስወጡኽና ተስፋ ሊቆርጡብኽ ይችላሉ።
እናትኽ ግን ስትወልድኽ እንደተደሰተችው ኹሉ እስከሕቅታዋ ድረስ ያው በአንተ ደስተኛ ናት።
ስለምታደርግላት አይደለም...በቃ ስላለኻት ስለተወለድኽላት ብቻ ደስተኛ ናት።
ከእሷ ውጪ የአምላክኽ ምድራዊ አምሳል ማን ሊኾን ይችላል?
ማንም የማይተካት የፈጣሪኽ ጸጋ ናት።
🍂📖🍂📖🍂📖🍂📖🍂📖🍂📖🍂📖
( ርዕስ - የንስሐ ግጥም )
አባ ስማ ድምፄን ደጅህ ቆሚያለሁኝ
የጠፋሁት ልጅህ በር እየመታሁኝ
በሀፍረት ታጥሬ እንደተሸማቀቅኩ
በፀፀት ታጅቤ እንደተኮራመትኩ
ከናፈቅኩት ቤትህ አይኔን እያማተርኩ
ቁጭ ብያለሁ ደጅህ አንተን እየጠበኩ
አባ ተመልከተኝ እንዲህ ተጎድቼ
የልጅነት መልኬን ወዜን ሁሉ አጥቼ
ካንተ የተቀበልኩት ጥሪቴን አጥፍቼ
በዚህች ወረተኛ አለም ተከድቼ
አዎን መጥቻለው ጉስቁልቁል እንዳልኩኝ
እርቃኔን ሳልሸፍን እንደተራቆትኩኝ
የህሊና እስረኛ መንገድ የጠፋብኝ
ሆኜ ቀርቻለው አለም ተጫውታብኝ
አባ ያንን ጊዜ ካንተ እንደተለየው
የዝ'ችን አለምን ጉድ ስንት ነገር አየው
ለካንስ እውነት ነው ምድር ከንቱነቷ
አያልቅም ተወርቶ ኮተታኮተቷ
አሳስቃ ወስዳ እያታለለችኝ
ይኸው አንገዋላ ከመንገድ ጣለችኝ
የምሸሸግበት ማርፍበት እስካጣ
ወዳጅ ተለውጦ እስኪሆን ባላንጣ
አይመስለኝም ነበር የጭካኔዋ ጥግ
አላስተዋልኳትም ያሻትን ስታደርግ
በርሀብ እና በጥም እየተሰቃየው
መሄድ እስኪያቅተኝ እየተንገላታው
የችግሬን ዳገት ብቻዬን ስገፋው
አልደረሰልኝም ወዳጅ ያልኩትም ሰው
ግን ጥርሴን ነክሼ ሰው ለመሆን ዳግም
ስቃይ ያደቀቀው ማንነቴን ላክም
በጉልበቴ ድኼ እንዲያ ስፍገመገም
ያን ጊዜ አየሁት ፊት ለፊቴ ሲቆም
ትንሿን ተስፋዬን ድጋሜ ሊያጨልም
ለካን ውሸት ኖሯል ፍቅራችን የይምሰል
ለካን ለጌጥ ሆኗል የለበስነው መስቀል
ይሄኔ ነው ታዲያ ልቤ ቤትህን ናፍቆ
ይቅርታ ሊጠይቅ ከእግሮችህ ስር ወድቆ
የመጣው በድፍረት ተስፋውን ሰንቆ
አባ አደራህን እንዳትጨክንብኝ
በርህን ለመክፈት እንዳትዘገይብኝ
በመከራ ምክር በጣም ስለደከምኩ
መኖር መርጫለው ለአንተ እያገለገልኩ
እንጂማ ከእንግዲህ ሌላም እቅድ የለኝ
አባ ቶሎ መተህ እንዳረከኝ አርገኝ
ወዲህ ወዲያም ሳልል ቆሚያለው በርህ ላይ
በይቅርታ አይኖችህ ዳግም እስከምታይ
ፈራ ተባ እሚለው ልቤን እየሞገትኩ
እስካሁን በርህ ለይ እንደተኮራመትኩ
ቁጭ ብያለው እና አንተን እየጠበኩ
አባ ናልኝ ባክህ ኧረ እኔስ ተጨነኩ
አንዴ ብቻ መተህ በሩን ከፍተህ ካየህ
በልጅህ መሰበር ስንቱን ታስባለህ
ግን አንድ እውነት እወቅ ከመምጣትህ በፊት
በርህን ደብድቤ ብጣራም በድንገት
አጥፍቼው ብመጣም ያንን ሁሉ ንብረት
ገንዘብ የማይገዛው ልብን ገዝቻለው
ከትናንቱ ግብሬ ዛሬ ተሽያለው
ስለዚህ ስትመጣ በሩን ልትከፍትልኝ
በዛሬ እኔነቴ እንድትቀበለኝ
ከቤት አስገብተህ አገልጋይህ አድርገኝ
ልጅህ ልባል እንደው አልሻም ከ'ንግዲህ
አገልጋይህ ሆኜ ልሩጥ ወዲያ ወዲህ
አዎን አባ መጥተህ በሩን ስትከፍትልኝ
አልሻም ድጋሚ
የአባትነት ዋጋን እንድትከፍልልኝ
ከቤታችን ካሉት ከአገልጋዮች ጋራ
እንድትፈቅድልኝ አብሬ እንድሰራ
እለምንሀለው እሺ በለኝ ባክህ
ያንን የትናንቱን ደጉን ቀን አስበህ
እንጂማ እንደግብሬ እንደ'ኔማ ቢሆን
አንተን ባልፈለኩህ ወዳጁ አውሬ ሲሆን
በቃኝ ስልችቶኛል ደክሞኛል እንግልት
በደንብ ገብቶኛል የምድር ከንቱነት
ላልመልሰው ፊቴን እርም ይሁን ብያለው
ቤትህ ነው አለሜ አባ ተምሪያለው!!!
መልካም ቀን
( ርዕስ - የንስሐ ግጥም )
አባ ስማ ድምፄን ደጅህ ቆሚያለሁኝ
የጠፋሁት ልጅህ በር እየመታሁኝ
በሀፍረት ታጥሬ እንደተሸማቀቅኩ
በፀፀት ታጅቤ እንደተኮራመትኩ
ከናፈቅኩት ቤትህ አይኔን እያማተርኩ
ቁጭ ብያለሁ ደጅህ አንተን እየጠበኩ
አባ ተመልከተኝ እንዲህ ተጎድቼ
የልጅነት መልኬን ወዜን ሁሉ አጥቼ
ካንተ የተቀበልኩት ጥሪቴን አጥፍቼ
በዚህች ወረተኛ አለም ተከድቼ
አዎን መጥቻለው ጉስቁልቁል እንዳልኩኝ
እርቃኔን ሳልሸፍን እንደተራቆትኩኝ
የህሊና እስረኛ መንገድ የጠፋብኝ
ሆኜ ቀርቻለው አለም ተጫውታብኝ
አባ ያንን ጊዜ ካንተ እንደተለየው
የዝ'ችን አለምን ጉድ ስንት ነገር አየው
ለካንስ እውነት ነው ምድር ከንቱነቷ
አያልቅም ተወርቶ ኮተታኮተቷ
አሳስቃ ወስዳ እያታለለችኝ
ይኸው አንገዋላ ከመንገድ ጣለችኝ
የምሸሸግበት ማርፍበት እስካጣ
ወዳጅ ተለውጦ እስኪሆን ባላንጣ
አይመስለኝም ነበር የጭካኔዋ ጥግ
አላስተዋልኳትም ያሻትን ስታደርግ
በርሀብ እና በጥም እየተሰቃየው
መሄድ እስኪያቅተኝ እየተንገላታው
የችግሬን ዳገት ብቻዬን ስገፋው
አልደረሰልኝም ወዳጅ ያልኩትም ሰው
ግን ጥርሴን ነክሼ ሰው ለመሆን ዳግም
ስቃይ ያደቀቀው ማንነቴን ላክም
በጉልበቴ ድኼ እንዲያ ስፍገመገም
ያን ጊዜ አየሁት ፊት ለፊቴ ሲቆም
ትንሿን ተስፋዬን ድጋሜ ሊያጨልም
ለካን ውሸት ኖሯል ፍቅራችን የይምሰል
ለካን ለጌጥ ሆኗል የለበስነው መስቀል
ይሄኔ ነው ታዲያ ልቤ ቤትህን ናፍቆ
ይቅርታ ሊጠይቅ ከእግሮችህ ስር ወድቆ
የመጣው በድፍረት ተስፋውን ሰንቆ
አባ አደራህን እንዳትጨክንብኝ
በርህን ለመክፈት እንዳትዘገይብኝ
በመከራ ምክር በጣም ስለደከምኩ
መኖር መርጫለው ለአንተ እያገለገልኩ
እንጂማ ከእንግዲህ ሌላም እቅድ የለኝ
አባ ቶሎ መተህ እንዳረከኝ አርገኝ
ወዲህ ወዲያም ሳልል ቆሚያለው በርህ ላይ
በይቅርታ አይኖችህ ዳግም እስከምታይ
ፈራ ተባ እሚለው ልቤን እየሞገትኩ
እስካሁን በርህ ለይ እንደተኮራመትኩ
ቁጭ ብያለው እና አንተን እየጠበኩ
አባ ናልኝ ባክህ ኧረ እኔስ ተጨነኩ
አንዴ ብቻ መተህ በሩን ከፍተህ ካየህ
በልጅህ መሰበር ስንቱን ታስባለህ
ግን አንድ እውነት እወቅ ከመምጣትህ በፊት
በርህን ደብድቤ ብጣራም በድንገት
አጥፍቼው ብመጣም ያንን ሁሉ ንብረት
ገንዘብ የማይገዛው ልብን ገዝቻለው
ከትናንቱ ግብሬ ዛሬ ተሽያለው
ስለዚህ ስትመጣ በሩን ልትከፍትልኝ
በዛሬ እኔነቴ እንድትቀበለኝ
ከቤት አስገብተህ አገልጋይህ አድርገኝ
ልጅህ ልባል እንደው አልሻም ከ'ንግዲህ
አገልጋይህ ሆኜ ልሩጥ ወዲያ ወዲህ
አዎን አባ መጥተህ በሩን ስትከፍትልኝ
አልሻም ድጋሚ
የአባትነት ዋጋን እንድትከፍልልኝ
ከቤታችን ካሉት ከአገልጋዮች ጋራ
እንድትፈቅድልኝ አብሬ እንድሰራ
እለምንሀለው እሺ በለኝ ባክህ
ያንን የትናንቱን ደጉን ቀን አስበህ
እንጂማ እንደግብሬ እንደ'ኔማ ቢሆን
አንተን ባልፈለኩህ ወዳጁ አውሬ ሲሆን
በቃኝ ስልችቶኛል ደክሞኛል እንግልት
በደንብ ገብቶኛል የምድር ከንቱነት
ላልመልሰው ፊቴን እርም ይሁን ብያለው
ቤትህ ነው አለሜ አባ ተምሪያለው!!!
መልካም ቀን
በግድ የፈለቀች
ጠብ አደረኩ እምባ
"በቃ ይፍቱኝ አባ"
ይሄ ነው ሀጥያቴ
ከእግሮ ስር ያራቀኝ
ምን ልስራ
ምን ላድርግ
አዚሙ እንዲለቀኝ?
አዩኝ ትክ ብለው
ቀረቡኝ
ቀረብኩኝ
መስቀል ተሳለምኩኝ
ከዛ ግን አላውቅም
ካልቾ .. ጥፊ .. ጨምቧ
".. ያማል እኮ አባ"
"ዝምበል"
"አባ ይፍቱኝ በል"
"አዎን አባ ይፍቱኝ"
አገላብጠው መቱኝ።
"ይኸው የኔ ጎበዝ
መንፈሰ ከርታታው
አንዲህ ነው ሚፈታው"
እስቲ ዝቅ
እስቲ ዝቅ
ከዛ አንዴ ድልቅ!
ወይኔ መድሃኒአለም
እጃቸው እንዴት ያማል፤
"የኔ ልጅ ይሰማል?"
በተዋጠ ልሳን
"አይሰማም አባ"
በድጋሚ ጨምቧ
የጠገበ ልጄን
ሳጠምቅ አልገኝም
እስቲ ከፍ ጨምቧ
ያንተማ አይጠፋኝም
እስቲ ከፍ ጥብስ
እስት ዝቅ ጨምቧ
"ይበቃኛል አባ!"
"ምኑ ነው ሚበቃህ?"
የኔን ትንሽ ዱላ
ከሳር የቀለለ ፤
ንፅህና የታለ?
ድንግልና የታለ?
ከፍ ዝቅ ክልትው
ሸሸሁኝ በዳዴ ፤
አባ ይቅር በሉኝ
ተሳሳትኩኝ አንዴ
"ሰው አይደለው እንዴ?"
እሱማ ሰው ነበርክ
በእግዜር የሚፀና
ክህነቱስ ግና?
ድቁናውስ ግና?
ቀና በል ያዝ ጧ!
አትወራጭ ፡ ድርግም!
"አይለምደኝም ዳግም"
እሱን ለግዜር በለው
ይኸው የኔ ፋንታ ፤
ከፍ ዝቅ ድርግም
"እባኮት የኔታ"
"ይቅር በሉ ይላል
ወንጌሉን አይርሱ
መመለሴን አይደል
ሚፈልገው እሱ?"
"እሱማ መተሃል
ዱላ ለወጉ ነው
ዳግም እንደማትሄድ
.. ለማረጋገጫ ፤
"ይሄ ሁሉ እርግጫ?"
"ዝምበል"
"አባ ይፍቱኝ በል"
"እሺ ይፍቱኝ አባ"
ቀና ሳብ ጨምቧ
ከዛን ተረጋጉ
አየር ሳብ አረጉ
"ይኸውልህ ልጄ
አድገህ አይደል በእጄ
አይንህ ልቤን ወጋው
ከእሳት ሳይህ ሰጋው
ለዛ ነው የተቆጣው
እስኪ እጅህን አምጣው"
"ይኸው" ብዬ አቀበልኩ
"ለበረከት እንጂ
አይሆኑም ለመርገም፤
እንካ ዳዊት ድገም
ይበቃል የስካሁን
አንተን ሳይ ፈራለው
.. ከእቶን ከእሳት፤
ከንግዲህ አትሳሳት"
ብለው አሳለሙኝ
ዝቅ ስል አመመኝ
ለንስሃ ያልወጣ
እምባዬ ቀደመኝ
ዱላ ያጀገነው
ልቤን ብሶት ገፋው
ስብርብር እያልኩኝ
ከእግራቸው ተደፋው
"አሳፈርኮት አባ
አሰደብኮት አባ
አስተምረው መና
አሳደገው መና
አልበሰልኩም ገና
አልበቃውም ገና
ይቅር በሉኝ አባ
አፉ በሉኝ አባ"
ብዬ ጥምጥም አልኩኝ
ጉልበታቸው ግርጌ
ጎትተው አነሱኝ
አቀፉኝ ሳብ አርገው፤
"ይሄን ልጅነት ነው
ጌታ ሚፈልገው"።
አሁን ለርሱ ስጋ
ባለበሰህ ፀጋ
ስለምትበድለው
ግፍን ስትሰበስብ ፤
እኔማ በእጄ ነህ
ለሞተልህ አስብ!።
አልቅስ እዘን እንጂ
ተስፋ ለማይቆርጠው
የምትድንበትን
ምክንያት ሲገጣጥም ፤
የጠገብክ እንደሆን
እናትህ ሆድ እንኳን
እኔን አታመልጥም!።
Guys ስንቶቻችን ነው ንሰሀ ለመግባት ንሰሀ አባታችንጋ ሄደን ሀጥያታችንን ሰምተው ሲቆጡን ጭራሽ እነሱንም ቂም ይዘንባቸው የምንገባው ፈጣሪ ልቦና ይስጠን🙏

ስንቱን ዘመን ጥዬ ፥ በስንቱ ተጥዬ
ስበድል ሳጠፋ ፥ ክፉ ዘር አብቅዬ
በሀጢአት ክምር ፥ ልቤ አንዴ ደንድኗል
የንስሀን እንባ ፥ ማንባት እንዴት ያውቃል???
አንተ ካልመራኸው ፥ አንተ ካልረዳኸው
የመፀፀት ሀይልን፥ አንተ ካላደልከው
አልነፃም ፈፅሞ ፥ አላገኝም ዋጋ
በእጆችህ ጎትተኝ ፥ ወዳንተ ልጠጋ
ፍቅርህን አብራርተህ ፥ በልቤ ፃፍና
አምርሬ ልመለስ ፥ ዕለት ዕለት ልፅና
✍✍ ብሩክ ተፈራ
ስበድል ሳጠፋ ፥ ክፉ ዘር አብቅዬ
በሀጢአት ክምር ፥ ልቤ አንዴ ደንድኗል
የንስሀን እንባ ፥ ማንባት እንዴት ያውቃል???
አንተ ካልመራኸው ፥ አንተ ካልረዳኸው
የመፀፀት ሀይልን፥ አንተ ካላደልከው
አልነፃም ፈፅሞ ፥ አላገኝም ዋጋ
በእጆችህ ጎትተኝ ፥ ወዳንተ ልጠጋ
ፍቅርህን አብራርተህ ፥ በልቤ ፃፍና
አምርሬ ልመለስ ፥ ዕለት ዕለት ልፅና
✍✍ ብሩክ ተፈራ
+ ያልተተከሉ ዛፎች +
አንድ ሩስያዊ የቴዎሎጂ መምህር የተናገሩትን አዝናኝ ወግ ሐበሻዊ ቀለም ሠጥቼ ልተርከው
ባልና ሚስት ከተጋቡ ጥቂት ዓመታት ቢያልፋቸውም ልጅ ግን አልወለዱም ነበር:: ወደ አንድ አባት ይሔዱና እባክዎን ልጅ እንዲሠጠን ይጸልዩልን ይሏቸዋል:: አባም ችግሩን ሰምተው የሚከተለውን ምክር ሠጡ
“እዚያ ተራራ ላይ ያለችው ገዳም ትታያችኁዋለች?" አሉአቸው
"አዎ አየናት" አሉ ባልና ሚስቱ
"ነገ በጠዋት እህል ሳትቀምሱ ሒዱና ገዳሙ ውስጥ የወይራ ዛፍ ተክላችሁ ልጅ ሥጠን ብላችሁ ስእለት ተሳሉ"
ባልና ሚስት በማግሥቱ ወደ ገዳሙ ሔደው የወይራ ዛፉን ተከሉ:: ይህ በሆነ በጥቂት ቀናት ልዩነት ውስጥ አባ ወደ ሌላ ሀገረ ስብከት ተመድበው ከዚያች ትንሽ የገጠር ከተማ ተሰናብተው ሔዱ::
ከሃያ ዓመታት ቆይታ በኁዋላ በአንድ አጋጣሚ አባ ወደዚያች ከተማ ተመልሰው መጡ:: ትንሹ ከተማ ትልቅ ሆኖ ብዙ ነገር ተለውጦ ጠበቃቸው:: የመጡበትን ጉዳይ ከፈጸሙ በኁዋላ የእነዚያ ባልና ሚስት ነገር ትዝ አላቸው:: በከተማው መቀየር ትንሽ ቢቸገሩም ቤቱን ፈልገው አገኙትና በር አንኳኩ::
አንድ የሚያምር ሕፃን የታቀፈች ሴት በሩን ከፈተች:: መካኒቱ ሴት ነበረች:: ከታቀፈችው ልጅ ሌላ እግርዋን ተጠምጥመው የያዙ ሁለት ሕጻናት አባን ሽቅብ እያዩ ይቁለጨለጫሉ:: መስቀል አሳልመው ወደ ውስጥ ሲዘልቁ ሶፋ ላይ ቁጭ ብለው ቴሌቪዥን የሚመለከቱ አራት ሕጻናት ተደርድረዋል::
ታላቆቻቸው የሚሆኑ ሁለት ልጆች ደግሞ ጠረጴዛው ላይ ቁጭ ብለው ያጠናሉ:: ይህ እንግዲህ ቡና የምታፈላውን ሴት ልጅና በሕፃን ልጅ አልጋ ላይ የተኛውን አራስ ልጅ ሳይጨምር ነው::
አባ በደስታም በመደነቅም ፈዝዘው ቀሩ::
"እንኩዋን ለዚህ አበቃችሁ ልጄ" አሏት በደስታ
"በእርስዎ ጸሎት ነው አባታችን" አለች እናት
"ለመሆኑ ባለቤትሽ የት ነው?" አሉ በጉጉት
እናት አንገትዋን ደፋች አባ ደነገጡ
"ምነው ሰላም አይደለም?" አሉ በስጋት
"ኸረ ሰላም ነው ... በጠዋት ወደዛች ተራራ ላይ ወዳለችው ገዳም ሔዶአል" አለች እያፈረች
"ምነው? ለምን ጉዳይ ሔደ?"
"ያኔ የተከልነውን የወይራ ዛፍ ሊቆርጥ"
✍🏽 ✍🏽 ✍🏽. ✍🏽. ✍🏽 ✍🏽 ✍🏽
ሊቁ ተርቱሊያን "የሰማዕታት ደም የክርስቲያኖች ዘር ነው" ብሎ ነበር:: "ክርስቲያን መግደል ክርስቲያን እንዲበቅል መዝራት ነው" እንደማለት ነው:: ከዚያ ውጪ ደግሞ ሌላው የክርስቲያን ዘር መውለድ ነው:: ብዙ ምእመናን የመውለድን ጸጋ ተጎናጽፈው ከመውለድ ይሸሻሉ::
ድሆች ሆነው እንኩዋን በፈጣሪ መግቦት አምነው የሚወልዱ እንዳሉ ሁሉ የኢኮኖሚ አቅም እያላቸው የተማሩ በመሆናቸው መውለድን እንደ ኁዋላ ቀርነት ቆጥረው ከመውለድ ወደ ኁዋላ የሚሉም ብዙዎች ናቸው::
ከላይ እንዳየነው ሰው ያህል እንኩዋን ሳይወልዱ ዛፍ ቆረጣ የሚሮጡ ብዙዎች ናቸው:: የሚወልደውን ኸረ በቃህ በቃሽ እያሉ የሚተቹ "ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉ ሲባል ብቻህን ልትሞላ ነው እንዴ?" ብለው በወለዱ የሚዘብቱ አሉ::
መውለድ ጸጋ በረከት ነው:: የልጅን ጣዕምና ጸጋ የወለዱ ሁሉ ያውቃሉ:: ልጅ መውለድ የወላጆችን መንፈሳዊ ሕይወት ሳይቀር ከፍ ያደርጋል:: ልጅ ፊት አይወራም ሲባል ከሚተው ክፉ ወሬ ጀምሮ አርኣያ ለመሆን ሲባል ከሚደረግ ጥረት ድረስ ልጅ መውለድ ትልቅ በረከት ነው::
ለቤተ ክርስቲያን ደግሞ የልጆች መብዛት በረከት ነው:: አንድ አባትም "በሕፃናት የለቅሶ ጩኸት የማትረበሽ ቤተ ክርስቲያን የነገ ተስፋ የሌላት ቤተ ክርስቲያን ናት" ብለዋል:: ሕፃናት የሚበዙባት ቤተ ክርስቲያን ግን ነገ እንደምትኖር ያረጋገጠች ቤተ ክርስቲያን ናት።
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥር 30/2012 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!
#share

+ የሕፃናት ድንቅ ጥበብ የተሞሉ ንግግሮች +
ነቢዩ "የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል" መዝ 18:7 ይላል:: በእርግጥም ሕፃናት ልክ እንደ ብሂለ አበው ሊጠቀስ የሚችል ብዙ ደስ የሚያሰኝ ትምህርት ያለው ቃል ይናገራሉ:: በጥያቄያቸውም በመልሳቸውም የሚሉት ነገር ትምህርት ሊሆን ይላል:: የሚከተሉት ለዚህ ማሳያ የሚሆኑ ናቸው::
✍🏽 ✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽
እናት ቤት ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ በክብር አስቀምጣለች:: ሕፃን ልጅ ያይና ሊገልጠው ሲል
"ተው አትንካ እሱ የእግዚአብሔር መጽሐፍ ነው" ትለዋለች:: እሺ ብሎ ይተዋል:: ደጋግሞ ይህንን ሊያደርግ ሲል ይህ ማስጠንቀቂያ ይሠጠዋል:: እናቱም ቁጭ ብላ መጽሐፍ ቅዱስ ስታነብ አይቶ አያውቅም:: ስለዚህ ልጅ እንዲህ አላት :-
"እማዬ ይህ መጽሐፍ የእግዚአብሔር መጽሐፍ ነው ብለሽኛል:: እኛ ስለማንጠቀምበት ለምን አንመልስለትም?"
⛪️ የመጽሐፍ ቅዱስ ክብሩ መነበቡ ነው:: ሕይወት የሚሆነን እንዳያቃዠን ትራስ ላይ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ገልጠን ማንበባችን ነው:: ከፈጣሪ የተላከልንን ደብዳቤ ሳናነበው እንዳንሞት አደራ አለብን:: ለዚህም ነው አንድ አባት BIBLE የሚለውን ቃል Basic Information Before Leaving Earth ብለው የተነተኑት::
✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽
አስተማሪው በፈጣሪ መኖር የማያምን ነው:: ለሕፃናቱም ይህንን አስተሳሰቡን ማስተማር ፈለገና በሰሌዳ ላይ
GOD IS NO WHERE (እግዚአብሔር የትም የለም) ብሎ ጻፈ:: አንድዋን ሕፃን አስነሥቶ አንብቢ ሲላት ግን ያነበበችው እንዲህ ነበር::
GOD IS NOW HERE (እግዚአብሔር አሁን እዚህ አለ)
✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽
ማሙሽ ሳንቲም የሚያጠራቅምባት ትንሽ ባንክ አለችው::
አንድ ጠዋት ከወላጆቹ ጋር ቤተ ክርስቲያን አርፍዶ ሲመለስ ባንኩን ዘርግፎ ሳንቲሙን መቁጠር ጀመረ:: ይህንን ሥራውን ያየው አባቱ ምን እያደረገ እንደሆነ ሲጠይቀው እንዲህ ሲል መለሰ :-
"ዛሬ ቤተ ክርስቲያን አባ ሲያስተምሩ ክርስቶስ በቶሎ ይመጣል ብለዋል:: የሚመጣ ከሆነ ደግሞ ይህንን ሁሉ ሳንቲም ደብቄ ይዤ እንዲያገኘኝ ስለማልፈልግ በቶሎ ለድሆች ልሠጠው አስቤ ነው"
✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽
አቡነ ሺኖዳ ይህን ጽፈው ነበር::
በአንድ ሀገር ዝናም ጠፋ:: ሰዎች ሁሉ ተጨነቁ:: በመጨረሻም ምሕላ ለማድረግ ተወሰነ:: ሕዝቡ ሁሉ ወደ ቤተ ክርስቲያን ጉዞ ጀመረ:: አንዲት ሕፃን በጉዞው መካከል ጃንጥላ ይዛ ነበር:: ለምን እንደያዘች ስትጠየቅ እንዲህ አለች :-
"የምንሔደው ዝናም እንዲዘንም ልንለምን አይደል? ታዲያ ስንመለስ በምን እንጠለላለን?"
ስለዚህች ሕፃን እምነት በዚያን ቀን ዝናም ዘነመ::
ሕዝቡ ሲደበደብ እርስዋ ጥላ ይዛ ነበር::
✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽
ፓትርያርክ ታዋድሮስ እንዲህ አሉ
አንድ አስተማሪ ለሕፃናት ለወደፊት በሳይንስ ትምህርታችሁ ምን አዲስ ቴክኖሎጂ መፍጠር ትፈልጋላችሁ? አላቸው::
አንድዋ ሕፃን :- ሕልም ቀርጾ የሚያስቀር ትራስ
ስትል ሌላው ልጅ ደግሞ :- ሰው ሐሰት ሲናገር ውሸቱን ነው ብሎ የሚጮኽ የእጅ ሰዓት አለ::
✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽
አንድ ቅዱስ አባት ሕፃናት እንቆቅልሽ ሲጫወቱ ይሰማል
"እኔ የምወደው እሱ የሚጠላኝ ደሃ
እሱ የሚወደኝ ባለጠጋ ማን ነው?" አለ አንዱ ሕፃን::
የሕፃናቱን መልስ ሳይሰማ ያ አባት ልቡ ተነክቶ ሔደ::
እርሱ የተረጎመው እንዲህ ብሎ ነበር
"እርሱ የሚወደኝ እኔ የምጠላው ባለጠጋ ትዕዛዙን የማልፈጽምለት እግዚአብሔር ነው:: የሚጠላኝ ደሃ ደግሞ የእርሱን ፈቃድ የምፈጽምለት ሰይጣን ነው" ብሎ አዘነ::

( ቆየን አይደል .. )
==============
ቆየን አይደል
:
የማለዳ አአዕዋፍ ድምጽ
ከእርጋታ ጋር ካደመጥን
ጀምበር ቀልታ ጎህ ስትቀድ
በተመስጦ ካደነቅን ...
ቆየን አይደል
:
እናት አባት ሲመርቁ
ከልባችን " አሜን " ካልን
ጨቅላ ሕጻናት በየሜዳው ሲቦርቁ
በመደሰት ካስተዋልን ....
ቆየን አይደል
:
ዝናብ መቶን ጸሐይ ሞቀን
" እፎይ " ካልን
ጨረቃ እና ኮከብ ናፍቀን
ወደ ሰማይ ቀና ካልን ....
ቆየን አይደል ?
==============
ቆየን አይደል
:
የማለዳ አአዕዋፍ ድምጽ
ከእርጋታ ጋር ካደመጥን
ጀምበር ቀልታ ጎህ ስትቀድ
በተመስጦ ካደነቅን ...
ቆየን አይደል
:
እናት አባት ሲመርቁ
ከልባችን " አሜን " ካልን
ጨቅላ ሕጻናት በየሜዳው ሲቦርቁ
በመደሰት ካስተዋልን ....
ቆየን አይደል
:
ዝናብ መቶን ጸሐይ ሞቀን
" እፎይ " ካልን
ጨረቃ እና ኮከብ ናፍቀን
ወደ ሰማይ ቀና ካልን ....
ቆየን አይደል ?
🌹#ማመስገን_ማመስገን🌹
ማመስገን ማመስገን ብቻ ነው ሥራዬ
መዘመር መዘመር ብቻ ነው ተግባሬ
አንተማ አትለይም ከአንደበቴ/2/
አንተማ አትነጥፍም ከከንፈሬ/2/
🌺
አዝ....
🌺
ውለታህ ነው ውዴ የሚቀሰቅሰኝ
ማለዳ ማለዳ አዚመው የሚለኝ
የቀመስኩህ ውዴ ያጣጣምኩት ፍቅር
እንዴት ያስችለኛል በአፌ ሳልናገር
🌸
ልናገር ልናገር የአንተን ነገር
ላምህክህ ላውጅህ በአዲስ መዝሙር
አልጠግብህ አልጠግብህ ባወራህ
አንተማ አንተማ ልዩ ነህ
🌸
#ኢየሱስ_ልዩ_ነህ/4/
#ወዳጄ_ልዩ_ነህ
🌺
አዝ......
🌺
ከቋንቋ ይልቃል ከቃላትም በላይ
ምድር አይወስነዉም አይክልለው ሰማይ
የፍቅርህን መጠን አለካዉምና
ዕፁብ ዕፁብ ብዬ ላብዛልህ ምስጋና
🌺
አዝ....
🌺
በሞገስ ያቆምከኝ በጠላት ከተማ
ጥልቁን ያሻገርከኝ ያን ክፉ ጨለማ
በናቁኝ ሰዎች ፊት ያማረው ነገሬ
ኢየሱስ ሆነኽ ነው አዲሱ መዝሙሬ
🌺
አዝ.....
🌺
ማረፍ ሆኖልኛል ስምህን ስጠራ
አሜን ነው መዝሙሬ ስኖር ካንተ ጋራ
ማጉረምረም አይኖርም ማመስገን ብቻ ነው
ሲሞላም ሲጎልም ኢየሱስ ጌታ ነው
🌸
ልናገር ልናገር የአንተን ነገር
ላምህክህ ላውጅህ በአዲስ መዝሙር
አልጠግብህ አልጠግብህ ባወራህ
አንተማ አንተማ ልዩ ነህ
🌸
ነን ዋማ አን መቃ ኬ
ነን ለብሳ ነን ለብሳ አን ዋኤ ኬ
ሂን ቁፉ ሂን ቁፉ አን ሲፋርሴ
ኢየሱስ ኢየሱስ አደ ከንኬ
🌸
ንዘንጂ ንዘንጂ ያኸ አር
ኖድንኸ ኖድንኸ በገደር መዝሙር
አንጠፎኸ አንጠፎኸ ብንዝረጊኸ
አኽማ አኽማ ልይንኸ
🌸
ክዛረብ ክዛረብ ናትካ ነገር
ከምልኽካ ክእውጅ በሓዱሽ መዝሙር
አይፀግበካን አይፀግበካን ተዛሪበ
ንስኻኮ ንስኻኮ ፍሉይ ኢኻ
🌸
ኦዳና ኦዳና ታኔ ነዋ
ጎኛና ጎኛና አዋጀና ኦራንቲያን መዝሙሪያን
ካሊኬ ካሊኬ ሃሰያዬ
ኔኒ ታው ኔኒ ታው ዱማቴኔ
🌸
ላዋልክ ላዋልክ ያተን መርካ
ሊውዲንከ ሊውዲንከ በአጂሰ አሐት
ኢለውጦፋ ኢለውጦፋ ቢላዋልካ
አተማ አተማ በሬዳንካ
🌸
#ኢየሱስ_ልዩ_ነህ/4/
#ወዳጄ_ልዩ_ነህ
ማመስገን ማመስገን ብቻ ነው ሥራዬ
መዘመር መዘመር ብቻ ነው ተግባሬ
አንተማ አትለይም ከአንደበቴ/2/
አንተማ አትነጥፍም ከከንፈሬ/2/
🌺
አዝ....
🌺
ውለታህ ነው ውዴ የሚቀሰቅሰኝ
ማለዳ ማለዳ አዚመው የሚለኝ
የቀመስኩህ ውዴ ያጣጣምኩት ፍቅር
እንዴት ያስችለኛል በአፌ ሳልናገር
🌸
ልናገር ልናገር የአንተን ነገር
ላምህክህ ላውጅህ በአዲስ መዝሙር
አልጠግብህ አልጠግብህ ባወራህ
አንተማ አንተማ ልዩ ነህ
🌸
#ኢየሱስ_ልዩ_ነህ/4/
#ወዳጄ_ልዩ_ነህ
🌺
አዝ......
🌺
ከቋንቋ ይልቃል ከቃላትም በላይ
ምድር አይወስነዉም አይክልለው ሰማይ
የፍቅርህን መጠን አለካዉምና
ዕፁብ ዕፁብ ብዬ ላብዛልህ ምስጋና
🌺
አዝ....
🌺
በሞገስ ያቆምከኝ በጠላት ከተማ
ጥልቁን ያሻገርከኝ ያን ክፉ ጨለማ
በናቁኝ ሰዎች ፊት ያማረው ነገሬ
ኢየሱስ ሆነኽ ነው አዲሱ መዝሙሬ
🌺
አዝ.....
🌺
ማረፍ ሆኖልኛል ስምህን ስጠራ
አሜን ነው መዝሙሬ ስኖር ካንተ ጋራ
ማጉረምረም አይኖርም ማመስገን ብቻ ነው
ሲሞላም ሲጎልም ኢየሱስ ጌታ ነው
🌸
ልናገር ልናገር የአንተን ነገር
ላምህክህ ላውጅህ በአዲስ መዝሙር
አልጠግብህ አልጠግብህ ባወራህ
አንተማ አንተማ ልዩ ነህ
🌸
ነን ዋማ አን መቃ ኬ
ነን ለብሳ ነን ለብሳ አን ዋኤ ኬ
ሂን ቁፉ ሂን ቁፉ አን ሲፋርሴ
ኢየሱስ ኢየሱስ አደ ከንኬ
🌸
ንዘንጂ ንዘንጂ ያኸ አር
ኖድንኸ ኖድንኸ በገደር መዝሙር
አንጠፎኸ አንጠፎኸ ብንዝረጊኸ
አኽማ አኽማ ልይንኸ
🌸
ክዛረብ ክዛረብ ናትካ ነገር
ከምልኽካ ክእውጅ በሓዱሽ መዝሙር
አይፀግበካን አይፀግበካን ተዛሪበ
ንስኻኮ ንስኻኮ ፍሉይ ኢኻ
🌸
ኦዳና ኦዳና ታኔ ነዋ
ጎኛና ጎኛና አዋጀና ኦራንቲያን መዝሙሪያን
ካሊኬ ካሊኬ ሃሰያዬ
ኔኒ ታው ኔኒ ታው ዱማቴኔ
🌸
ላዋልክ ላዋልክ ያተን መርካ
ሊውዲንከ ሊውዲንከ በአጂሰ አሐት
ኢለውጦፋ ኢለውጦፋ ቢላዋልካ
አተማ አተማ በሬዳንካ
🌸
#ኢየሱስ_ልዩ_ነህ/4/
#ወዳጄ_ልዩ_ነህ