ንዴትሽን እወደዋለሁ
እሳት ነው እሳት ይለብሳል፤
ግን እመኚኝ ከዛ በላይ
ናፍቆትሽ እጥፍ ያከሳል፤
ምን አለው አይገናኝም
መስታወት ላይ ቃልን ማራገፍ፤
የስላሴን ልጅ መውደዴን
ፊደል ቆጣጥሮ ማሰለፍ፤
ተፈጥሮ ትንሽ ብትገፋኝ
እንደምንም ቢቻለኝም፤
እወዱሻለሁ ካልኩሽ በቀር
የቀረ ቅኔ የለኝም፤
አቃለሁ ሰነፍ ነኝ እኮ
ከኔ ጋር መሆን ይከብዳል፤
ልቤ ግን እውነት ሀቅ አለው
ከራሱ ሰውን ይወዳል፤
እወድሽ እወድሻለሁ
የሰማ ይሰንጠቅ አለት፤
በአካል እያየሽ ብታውቂኝ
እስቲ ግን ምንነበረበት ?
ተፈጥሮ ትንሽ ብትገፋኝ
እንደምንም ቢቻለኝም፤
እወድሻለሁ ካልኩሽ በቀር
የቀረ ቅኔ የለኝም፤
ሁሌ ነው በቀን በቀኑ
የሚጨምረው ግፊቱ፤
የተሳለበት ይመስል
የፊትሽ ግማሽ ከፊቱ ፤ ፤
እኔ ሳልሆን የሚወድሽ ልቤ ነው የፃፈው
@dagi1u
እሳት ነው እሳት ይለብሳል፤
ግን እመኚኝ ከዛ በላይ
ናፍቆትሽ እጥፍ ያከሳል፤
ምን አለው አይገናኝም
መስታወት ላይ ቃልን ማራገፍ፤
የስላሴን ልጅ መውደዴን
ፊደል ቆጣጥሮ ማሰለፍ፤
ተፈጥሮ ትንሽ ብትገፋኝ
እንደምንም ቢቻለኝም፤
እወዱሻለሁ ካልኩሽ በቀር
የቀረ ቅኔ የለኝም፤
አቃለሁ ሰነፍ ነኝ እኮ
ከኔ ጋር መሆን ይከብዳል፤
ልቤ ግን እውነት ሀቅ አለው
ከራሱ ሰውን ይወዳል፤
እወድሽ እወድሻለሁ
የሰማ ይሰንጠቅ አለት፤
በአካል እያየሽ ብታውቂኝ
እስቲ ግን ምንነበረበት ?
ተፈጥሮ ትንሽ ብትገፋኝ
እንደምንም ቢቻለኝም፤
እወድሻለሁ ካልኩሽ በቀር
የቀረ ቅኔ የለኝም፤
ሁሌ ነው በቀን በቀኑ
የሚጨምረው ግፊቱ፤
የተሳለበት ይመስል
የፊትሽ ግማሽ ከፊቱ ፤ ፤
እኔ ሳልሆን የሚወድሽ ልቤ ነው የፃፈው
@dagi1u
❤13🥰4
🤲🤲🤲🤲🤲አቤቱ🤲🤲🤲🤲🤲
አምላክ በፍቃዱ በአምሳሉ ፈጠረ
ሰውን ባፈጣጠር ውብ አርጎ አከበረ
ጌታ በፍጥረቱ ሊወደስ ሊቀደስ
ከአፈር አበጃጅቶ ሲባርክ ሲያነግስ
ሁሉን ሙሉ አድርጎ አስተካክሎ ቅድሚያ
ልጁን እፍ ብሎ አስገኘው ከትቢያ
የምስጋና ጣዕም የውዳሴን ዜማ
በከንፈሩ ፍሬ አርጎት እንዲስማማ
ከሁሉ አልቆ አከበረው ሰውን
አደለው ሸለመው ጥበብ ማስተዋልን
ሰው ግን...ሰው ግን ረከሰ ቆሸሸ በስራው
ሀጥያት ክፋት ተንኮል ሆኖት መሸሸጊያው
አካሉ እና መልኩ ግሩም ሆኖ ሳለ
በግብሩ መጠልሸት ተዋርዶ ቀለለ
አቤቱ....አምላኬ.....ምንኛ አጥፍተን አሳዝነን ይሆን
የበደል ማርከሻ እስኪታጣ በደልን
ነውራችን ገነነ ድካማችን በዛ
ስጋችን ደቀቀ ነፍሳችን ደንዝዛ
ወደቅን....ከሰርን አንተን አጣን ጌታ
ሀዘን ከቦን ወሮን ሸሸ ከኛ ደስታ
አቤቱ...አምላኬ...ገድለናል ሰርቀናል ዋሽተናል በብርቱ
ስራችን ከርፍቶ ሆኖብናል ከንቱ
ዝሙትን ሰርተናል ስምህን አምተናል
ረክሰናል በሀጥያት ቀለናል ገምተናል
ያልበደልነው በደል ያልነካነው ክፋት
ያልሰራነው ሴራ ያልገለጥነው ትዕቢት
ምንም የለም ከቶ....ሁሉን አዳርሰናል
አንዳችም ሳናስቀር ሀጥያትን ሰርተናል
እናም...እናም...አንተ ቸር ፈጣሪ ሁሉን ቻይ ነህና
ክቡር....ቅዱስ ሀያል ነህና ገናና
አንፃን ከስራችን ማረን በይቅርታ
በንስሀ አጥበህ አርገን የበረታ
✍ብሩክ ተፈራ
አምላክ በፍቃዱ በአምሳሉ ፈጠረ
ሰውን ባፈጣጠር ውብ አርጎ አከበረ
ጌታ በፍጥረቱ ሊወደስ ሊቀደስ
ከአፈር አበጃጅቶ ሲባርክ ሲያነግስ
ሁሉን ሙሉ አድርጎ አስተካክሎ ቅድሚያ
ልጁን እፍ ብሎ አስገኘው ከትቢያ
የምስጋና ጣዕም የውዳሴን ዜማ
በከንፈሩ ፍሬ አርጎት እንዲስማማ
ከሁሉ አልቆ አከበረው ሰውን
አደለው ሸለመው ጥበብ ማስተዋልን
ሰው ግን...ሰው ግን ረከሰ ቆሸሸ በስራው
ሀጥያት ክፋት ተንኮል ሆኖት መሸሸጊያው
አካሉ እና መልኩ ግሩም ሆኖ ሳለ
በግብሩ መጠልሸት ተዋርዶ ቀለለ
አቤቱ....አምላኬ.....ምንኛ አጥፍተን አሳዝነን ይሆን
የበደል ማርከሻ እስኪታጣ በደልን
ነውራችን ገነነ ድካማችን በዛ
ስጋችን ደቀቀ ነፍሳችን ደንዝዛ
ወደቅን....ከሰርን አንተን አጣን ጌታ
ሀዘን ከቦን ወሮን ሸሸ ከኛ ደስታ
አቤቱ...አምላኬ...ገድለናል ሰርቀናል ዋሽተናል በብርቱ
ስራችን ከርፍቶ ሆኖብናል ከንቱ
ዝሙትን ሰርተናል ስምህን አምተናል
ረክሰናል በሀጥያት ቀለናል ገምተናል
ያልበደልነው በደል ያልነካነው ክፋት
ያልሰራነው ሴራ ያልገለጥነው ትዕቢት
ምንም የለም ከቶ....ሁሉን አዳርሰናል
አንዳችም ሳናስቀር ሀጥያትን ሰርተናል
እናም...እናም...አንተ ቸር ፈጣሪ ሁሉን ቻይ ነህና
ክቡር....ቅዱስ ሀያል ነህና ገናና
አንፃን ከስራችን ማረን በይቅርታ
በንስሀ አጥበህ አርገን የበረታ
✍ብሩክ ተፈራ
❤35👍3👏1
የሰወች ህይወት ውስጥ መጥፎ ክምሮችን አትክተት ።
ኢሄን የምልህ አለመክተት ስለምትችል ነው...
የተናደደ ሰው ላይ እሳት አታርከፍክፍበት...
ውሀ ሁንለት በግዱ ይቀዘቅዛል
የተከፋውንም ከልብህ አፅናናው ...
ያለቀሰውን እጅህን ሰደህ ከጉንቾቹ እምባውን
በመዳፍህ አብስለት ...
የተደሰተውንም ደስታው የክፋት ካልሆነ አመፀኛ ምላስህን በገዛ ፍቃድህ ያዝለት ደስ ይበለው..
በወንድምህ ደስታ ተደሰት...
መልካም ማሰብህ ዋጋው ከእግዚአብሔር ስለሆነ
ከባንክ ቤት ወይም ከሰው ኪስ ውስጥ መጠበቅህን ተወው...
እንደ ሰው ኑር....
@dagi1u
ኢሄን የምልህ አለመክተት ስለምትችል ነው...
የተናደደ ሰው ላይ እሳት አታርከፍክፍበት...
ውሀ ሁንለት በግዱ ይቀዘቅዛል
የተከፋውንም ከልብህ አፅናናው ...
ያለቀሰውን እጅህን ሰደህ ከጉንቾቹ እምባውን
በመዳፍህ አብስለት ...
የተደሰተውንም ደስታው የክፋት ካልሆነ አመፀኛ ምላስህን በገዛ ፍቃድህ ያዝለት ደስ ይበለው..
በወንድምህ ደስታ ተደሰት...
መልካም ማሰብህ ዋጋው ከእግዚአብሔር ስለሆነ
ከባንክ ቤት ወይም ከሰው ኪስ ውስጥ መጠበቅህን ተወው...
እንደ ሰው ኑር....
@dagi1u
❤11
አሻግሬ አየሁት
.
.
በግርግር መሐል ጨርቄን ጥዬ ስበር፣
አሻግሬ አየሁት ከቀራንዮ ጫፍ ከጎለጎታ ስር።
መንገዱን በማያዉቅ እልፍ መንገደኛ መንደሩ ታዉኮ፣
አንዱ ካንዱ ሲጋጭ ከሌላኛዉ ተጓዥ ሳይተያይ ታክኮ፣
አላፊ አግዳሚውን ወጪና ወራጁን ቆሜ ስመለከት፣
ደምግባቱን ያጣ የተራቆተ ሰው አየሁኝ በድንገት፣
በደም ረስርሶ በወዝ የረጠበ ቀይ ከለሜዳ፣
በሀሰት ተከሶ ፍርዱን የሚጠብቅ ከጲላጦስ ዘንዳ፣
ይታየኛል አንድ ሰው........
በአይሁድ ሊቀ ካህናት ግራና ቀኙን ተከቦ፣
በህዝብ መካከል የቆመ በእነ ቀያፋ ተዋክቦ፣
ሲንጠበብ ወዙ ሲነሳ ሲወድቅ፣
በጥፊ ሲመቱት እጅጉን ሲሳቀቅ፣
ይታየኛል ንፁህ ሰው......
በቁርጥራጭ ብረት፣
በተሰበረ አጥንት፣
እረፍት በሌለው በወንበዴ ጅራፍ ጀርባውን ተገርፎ፣
አልባስ ተለይቶት እርቃኑን የዋለ ቀሚሱን ተገፎ፣
ስጋዉ ሲቦጫጨቅ፣
ፅሂሙም ሲነጫጭ፣
ቁጥር በማይቆጥረዉ በአይሁድ ግርፋት ቆዳዉ ተገሽልጦ፣
እዡን እያነባ ህማም አይሎበት ፊቱ ተላልጦ፣
በድካም ሲያጣጥር፣
ይታወቀኝ ጀመር፣
ከአይኔ ተንከባሎ ጉንጩን እያራሰ እንባዬ ሲወርድ፣
ላብ እያጠመቀኝ እግሬ ተብረክርኮ ሰዉነቴ ሲርድ፣
አሻግሬ አየሁት.........
በተሳለ ቅንዋት ለአዳም ሲቸነከር፣
በደሙ ቤዛነት ብድራትን ሲቸር፣
በመስቀሉ ካሳ አርአያ ሊሆነን እንባችንን ሊያብስ፣
ለዘላለም ፍቅሩ ለታመነ ቃሉ እስከመሞት ሲደርስ።
✍ኤደን
.
.
በግርግር መሐል ጨርቄን ጥዬ ስበር፣
አሻግሬ አየሁት ከቀራንዮ ጫፍ ከጎለጎታ ስር።
መንገዱን በማያዉቅ እልፍ መንገደኛ መንደሩ ታዉኮ፣
አንዱ ካንዱ ሲጋጭ ከሌላኛዉ ተጓዥ ሳይተያይ ታክኮ፣
አላፊ አግዳሚውን ወጪና ወራጁን ቆሜ ስመለከት፣
ደምግባቱን ያጣ የተራቆተ ሰው አየሁኝ በድንገት፣
በደም ረስርሶ በወዝ የረጠበ ቀይ ከለሜዳ፣
በሀሰት ተከሶ ፍርዱን የሚጠብቅ ከጲላጦስ ዘንዳ፣
ይታየኛል አንድ ሰው........
በአይሁድ ሊቀ ካህናት ግራና ቀኙን ተከቦ፣
በህዝብ መካከል የቆመ በእነ ቀያፋ ተዋክቦ፣
ሲንጠበብ ወዙ ሲነሳ ሲወድቅ፣
በጥፊ ሲመቱት እጅጉን ሲሳቀቅ፣
ይታየኛል ንፁህ ሰው......
በቁርጥራጭ ብረት፣
በተሰበረ አጥንት፣
እረፍት በሌለው በወንበዴ ጅራፍ ጀርባውን ተገርፎ፣
አልባስ ተለይቶት እርቃኑን የዋለ ቀሚሱን ተገፎ፣
ስጋዉ ሲቦጫጨቅ፣
ፅሂሙም ሲነጫጭ፣
ቁጥር በማይቆጥረዉ በአይሁድ ግርፋት ቆዳዉ ተገሽልጦ፣
እዡን እያነባ ህማም አይሎበት ፊቱ ተላልጦ፣
በድካም ሲያጣጥር፣
ይታወቀኝ ጀመር፣
ከአይኔ ተንከባሎ ጉንጩን እያራሰ እንባዬ ሲወርድ፣
ላብ እያጠመቀኝ እግሬ ተብረክርኮ ሰዉነቴ ሲርድ፣
አሻግሬ አየሁት.........
በተሳለ ቅንዋት ለአዳም ሲቸነከር፣
በደሙ ቤዛነት ብድራትን ሲቸር፣
በመስቀሉ ካሳ አርአያ ሊሆነን እንባችንን ሊያብስ፣
ለዘላለም ፍቅሩ ለታመነ ቃሉ እስከመሞት ሲደርስ።
✍ኤደን
❤27👍1
፡ስቃለሁ እንደተመቸኝ፡
እራስን ማጣት ቀለለ
ዘመኔ ቦግ እልም ሆነ፤
አለማወቅ መጋጋጫው
ድድብና እንኳን ዘመነ፤
ከንቱነት መኪና አስገዛ
ደረጃ ነው ሰው ይረገጣል፤
ሁለት ልብ ግራገቡ
ማገር ጠፍቶ የት ይቀመጣል ?
ሰወች ላይ ሰውን ደራርቦ
እሳት ላይ እሳት ለኮሰ፤
ማርያምን ቃል አጣሁ እኮ
ከመሬት ህይወት አነሰ ??😭
አፈር መሆኔን ባውቅም
ግድ የለም ማለት ሰለቸኝ፤
ውስጤ ቢተራመስም
እስቃለሁ እንደተመቸኝ ።
✍@dagi1u ግርማዊ ዳግም
እራስን ማጣት ቀለለ
ዘመኔ ቦግ እልም ሆነ፤
አለማወቅ መጋጋጫው
ድድብና እንኳን ዘመነ፤
ከንቱነት መኪና አስገዛ
ደረጃ ነው ሰው ይረገጣል፤
ሁለት ልብ ግራገቡ
ማገር ጠፍቶ የት ይቀመጣል ?
ሰወች ላይ ሰውን ደራርቦ
እሳት ላይ እሳት ለኮሰ፤
ማርያምን ቃል አጣሁ እኮ
ከመሬት ህይወት አነሰ ??😭
አፈር መሆኔን ባውቅም
ግድ የለም ማለት ሰለቸኝ፤
ውስጤ ቢተራመስም
እስቃለሁ እንደተመቸኝ ።
✍@dagi1u ግርማዊ ዳግም
❤13🔥1
ማን ይውደደኝ
ዝም አልኳቸው
ሄዱ ጥለውኝ
፡
አያስመስልም ብለውኝ
መግለፄን አወቁ
ገፉኝ ተደበቁ
፡
አርጉልኝ ከማለት
ላድርገው አልኳቸው
፡
ስሜ ከሚጠፋ
ባዶ ልቅር ደስስስ እስከሚላቸው
ንቃ ስጥ ሰጪ ከሆንክ መስጠት
፡
ሁሉም ይለያያል
አንተን መሳይ ካጣህ
ዝም ብለህ ግፋበት ...
✍@dagi1u ግርማዊ ዳግም
ዝም አልኳቸው
ሄዱ ጥለውኝ
፡
አያስመስልም ብለውኝ
መግለፄን አወቁ
ገፉኝ ተደበቁ
፡
አርጉልኝ ከማለት
ላድርገው አልኳቸው
፡
ስሜ ከሚጠፋ
ባዶ ልቅር ደስስስ እስከሚላቸው
ንቃ ስጥ ሰጪ ከሆንክ መስጠት
፡
ሁሉም ይለያያል
አንተን መሳይ ካጣህ
ዝም ብለህ ግፋበት ...
✍@dagi1u ግርማዊ ዳግም
❤14👍2
ገና ያኔ ድሮሮ
ከሩቅ ዘመን በፊት፣
አማኝ በሞላበት
ፈላስፎችም አሉ ብቻ ትንሽ ጥቂት፤
ታድያ በዛ ዘመን
መሬት ክብ ነበረች
ምጣድ ምትመስል፣
ለጥ ብላ ምትኖር
የማትዞር ማትዋልል፥
ያችኛዋ መሬት
አሁን ከነበረው በጣም ትለያለች፣
ምንም አድሎ የለም
ሁሉን ታበቅላለች፤
ታድያ እነዛ ጥቂት
የሚፈላሰፉ፣
ከንቱ ሀሰበቸውን
በሰው ውስጥ አስፋፉ፤
መሬት ክብ ሳትሆን
ሰማይ የምታክል፣
እንቁላል ነገር ነች
አሎሎ ምትመስል፤
ብለው ማይሆን ወሬ
ምድር ላይ በተኑ፣
ደበራት መሰለኝ
እንደዚ ሲሆኑ፤
አሁን በኛ ዘመን
ትንሽ መረጋጋት ያለ ከመሰላት፣
ለስሟ ነዉ መሰል
ድርቅና ቸነፈር
ጦርነት አይቀራት።
ከሩቅ ዘመን በፊት፣
አማኝ በሞላበት
ፈላስፎችም አሉ ብቻ ትንሽ ጥቂት፤
ታድያ በዛ ዘመን
መሬት ክብ ነበረች
ምጣድ ምትመስል፣
ለጥ ብላ ምትኖር
የማትዞር ማትዋልል፥
ያችኛዋ መሬት
አሁን ከነበረው በጣም ትለያለች፣
ምንም አድሎ የለም
ሁሉን ታበቅላለች፤
ታድያ እነዛ ጥቂት
የሚፈላሰፉ፣
ከንቱ ሀሰበቸውን
በሰው ውስጥ አስፋፉ፤
መሬት ክብ ሳትሆን
ሰማይ የምታክል፣
እንቁላል ነገር ነች
አሎሎ ምትመስል፤
ብለው ማይሆን ወሬ
ምድር ላይ በተኑ፣
ደበራት መሰለኝ
እንደዚ ሲሆኑ፤
አሁን በኛ ዘመን
ትንሽ መረጋጋት ያለ ከመሰላት፣
ለስሟ ነዉ መሰል
ድርቅና ቸነፈር
ጦርነት አይቀራት።
❤22👍5
እኔም እንደ አዳም . . .
በገነት ገዳም
ሁሉ ተሟልቶ ፥ ኑሮ ሲመቻች
አድርጎኝ ታካች
ማለት ሲዳዳኝ "ከፀሐይ በታች..."
የዛኔ መጣች !
መጣች ...
"ንቃ" አለችኝ
ጎኔን እየወጋች ፥ ተፈታተነችኝ
ዝም አልኩኝ በግብሯ
ታገስኳት እንዴትም ፤
ለካ እንደመሳሳቅ ፥ ይጥማል ንዴትም ።
( ምቾት ብቻውን መች ያስደስታል ?
መስኩ ለምለም ነው
አፀዱ ሙሉ
ምግቡ ፥ መጠጡ በገነት ሞልቷል
ምስኪኑ አዳም ግን ትቶት ተኝቷል ።
ሳይጠፋበት ጥፋት ፥ ሳይጎበኘው ሐጥያት
ለካስ ይሰለቻል ፥ መንግስተ - ሰማያት ። )
እሷ ግን በቃ
እግዜር ያስተኛኝ በገነት አልጋ
እንዳልነቃበት ስለሚሰጋ
መሆኑን አውቃ
ህይወት ሰጠችኝ ፥ ምቾቴን ነጥቃ ።
By Habtamu Hadera
በገነት ገዳም
ሁሉ ተሟልቶ ፥ ኑሮ ሲመቻች
አድርጎኝ ታካች
ማለት ሲዳዳኝ "ከፀሐይ በታች..."
የዛኔ መጣች !
መጣች ...
"ንቃ" አለችኝ
ጎኔን እየወጋች ፥ ተፈታተነችኝ
ዝም አልኩኝ በግብሯ
ታገስኳት እንዴትም ፤
ለካ እንደመሳሳቅ ፥ ይጥማል ንዴትም ።
( ምቾት ብቻውን መች ያስደስታል ?
መስኩ ለምለም ነው
አፀዱ ሙሉ
ምግቡ ፥ መጠጡ በገነት ሞልቷል
ምስኪኑ አዳም ግን ትቶት ተኝቷል ።
ሳይጠፋበት ጥፋት ፥ ሳይጎበኘው ሐጥያት
ለካስ ይሰለቻል ፥ መንግስተ - ሰማያት ። )
እሷ ግን በቃ
እግዜር ያስተኛኝ በገነት አልጋ
እንዳልነቃበት ስለሚሰጋ
መሆኑን አውቃ
ህይወት ሰጠችኝ ፥ ምቾቴን ነጥቃ ።
By Habtamu Hadera
❤10
መልስ አጣለሁ
ልቤ ይደነግጣል
እንደ ሰው ለመሳቅ
:
አይኔ ተመልክቷል
አፍቃሪ ሲናናቅ
ከሆነ ጥፋቴ
አጋር መፈለጉ
:
ይሻላል መሰለኝ
ቢቀርብኝ ወጉ
እኔ መከረኛ
ስንቴ ስፈልጋት
:
የሚቆራረጠው
ተስፋዬ አልቆ ነው
ከጨለማ መሀል
የሚደባብሳት
:
ያገኛት ይመስል
ልቤ ሲኮታትን
:
አላገኘም በቃ
አልፏል አመታትን....
✍@dagi1u ግርማዊ ዳግም
ልቤ ይደነግጣል
እንደ ሰው ለመሳቅ
:
አይኔ ተመልክቷል
አፍቃሪ ሲናናቅ
ከሆነ ጥፋቴ
አጋር መፈለጉ
:
ይሻላል መሰለኝ
ቢቀርብኝ ወጉ
እኔ መከረኛ
ስንቴ ስፈልጋት
:
የሚቆራረጠው
ተስፋዬ አልቆ ነው
ከጨለማ መሀል
የሚደባብሳት
:
ያገኛት ይመስል
ልቤ ሲኮታትን
:
አላገኘም በቃ
አልፏል አመታትን....
✍@dagi1u ግርማዊ ዳግም
❤7👍1
አላውቅም
አላቅም ምን እንደልሽ
ጠፋብኝ ምን እንደሚባል
:
መናፈቅ አለመናፈቅ
መንጠልጠል በጣም ያባባል
ዝም ልበል ላውራ ?
አሟሙተኝ ተብሎ
ማንም አይጠራ
:
ያልገባሽ ያልገባኝ
መስመር ሲዘረጋ
ለኔ እንደጨለመ
ላንቺ ብቻ ነጋ......
✍@dagi1u ግርማዊ ዳግም
አላቅም ምን እንደልሽ
ጠፋብኝ ምን እንደሚባል
:
መናፈቅ አለመናፈቅ
መንጠልጠል በጣም ያባባል
ዝም ልበል ላውራ ?
አሟሙተኝ ተብሎ
ማንም አይጠራ
:
ያልገባሽ ያልገባኝ
መስመር ሲዘረጋ
ለኔ እንደጨለመ
ላንቺ ብቻ ነጋ......
✍@dagi1u ግርማዊ ዳግም
❤9
Forwarded from Biruk Tefera
በዚህ ምድር ስትኖር
አስብ የሰው ድካም
ማንንም እስከ ጥግ
አትመነው በጣም
ቤተሰብ ጓደኛ
ፍቅረኛ ወዳጄ
አጋር መከታዬ
ብለህ ያልከው ቀኝ እጄ
ሁሉም በየጊዜው
ያልፋል ሆኖ ሽታ
አምላክህን ያዘው
አድርገህ አለኝታ
✍ብሩክ ተፈራ
አስብ የሰው ድካም
ማንንም እስከ ጥግ
አትመነው በጣም
ቤተሰብ ጓደኛ
ፍቅረኛ ወዳጄ
አጋር መከታዬ
ብለህ ያልከው ቀኝ እጄ
ሁሉም በየጊዜው
ያልፋል ሆኖ ሽታ
አምላክህን ያዘው
አድርገህ አለኝታ
✍ብሩክ ተፈራ
❤16
መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒
መልስ አጣለሁ ልቤ ይደነግጣል እንደ ሰው ለመሳቅ : አይኔ ተመልክቷል አፍቃሪ ሲናናቅ ከሆነ ጥፋቴ አጋር መፈለጉ : ይሻላል መሰለኝ ቢቀርብኝ ወጉ እኔ መከረኛ ስንቴ ስፈልጋት : የሚቆራረጠው ተስፋዬ አልቆ ነው…
ቻናሉ መንፈሳዊ ፅሁፎችን የምንጋራበት በመሆኑ መንፈሳዊ ይዘት ያላቸውን ነገሮች ብቻ ብናጋራ።
❤4👍4👏3
ላልችል አልኩኝ
እርግጥ ነው
ንዴት መሀል ስራ አጣሁ
:
ግን አልቆየም
ሀሳቤን ስቆጣው
ማለት የፈለኩትን
ላስረዳሽ ጊዜ ጠላኝ
:
ሄደሽ የለም ማንነቴ
ሳቄን ነው የቀማኝ....
ልልሽ የፈለኩት
እኔ እወድሻለሁ
:
ሁሌም መጨረሻ
ነብስ ትጎዳለች
አፍ በቀባጠረው...
እኔም ልክ እንደዛው
አፌ ሲፈጣጥን
እጣዬን ቀድጄ
:
ምን ይባላል አሁን
እራሴን ጠልቼ
ካንቺ ተዋድጄ ...😁
ማሽላ እያረረ ነው የሚስቀው
✍@dagi1u ግርማዊ ዳግም
እርግጥ ነው
ንዴት መሀል ስራ አጣሁ
:
ግን አልቆየም
ሀሳቤን ስቆጣው
ማለት የፈለኩትን
ላስረዳሽ ጊዜ ጠላኝ
:
ሄደሽ የለም ማንነቴ
ሳቄን ነው የቀማኝ....
ልልሽ የፈለኩት
እኔ እወድሻለሁ
:
ሁሌም መጨረሻ
ነብስ ትጎዳለች
አፍ በቀባጠረው...
እኔም ልክ እንደዛው
አፌ ሲፈጣጥን
እጣዬን ቀድጄ
:
ምን ይባላል አሁን
እራሴን ጠልቼ
ካንቺ ተዋድጄ ...😁
ማሽላ እያረረ ነው የሚስቀው
✍@dagi1u ግርማዊ ዳግም
❤3
ለሳቸው ለማዘን
ሰው መሆኔ ይበቃኛል
:
የፍቅራቸው ሰንሰለቱ
ያስለቅሳል አወ አስሮኛል
"ተመስገን ታቦታችን ገባ"
አሉ "ሀጂ ሙፊታ" በቃላቸው....
እግዜር ያከበረውን
ማክበር ነውና ስራቸው😭
ትልቁ ዋርካ ሲወድቅ
እልፍ ሰው ይበታተናል
:
ከሀሩር የተጠለለ
ከሽሽት ብዛት ይተናል...
ሰው ሰው ለሚሸት አባት
ማን ልሁን እሺ ለማልቀስ ?
:
ክርስቲያን ነኝ ሁሉም ያቃል
ለሳቸው ይሁን ብከሰስ
ሀገሬ ግንዷ ተነካ
አፈር ነው የሰው ልጅ ልብሱ
:
ሀጂ ግን እንዴት ቻሉበት
መሆንን ለወጣት ሱሱ...
አጣኖት አወ አባታችን
በመቃብሮ ቀናንባት
እርሶን ይዛለች እና
ማን መልሽ ማን አውጪ ይበላት😭😭
ሀጂ ሙፍቲ እንድሪስ የኢትዮጲያዊያን ሁሉ አባት ነበሩ 😭😭😭 እግዚአብሔር ነብሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑርልን
✍@dagi1u ግርማዊ ዳግም
ሰው መሆኔ ይበቃኛል
:
የፍቅራቸው ሰንሰለቱ
ያስለቅሳል አወ አስሮኛል
"ተመስገን ታቦታችን ገባ"
አሉ "ሀጂ ሙፊታ" በቃላቸው....
እግዜር ያከበረውን
ማክበር ነውና ስራቸው😭
ትልቁ ዋርካ ሲወድቅ
እልፍ ሰው ይበታተናል
:
ከሀሩር የተጠለለ
ከሽሽት ብዛት ይተናል...
ሰው ሰው ለሚሸት አባት
ማን ልሁን እሺ ለማልቀስ ?
:
ክርስቲያን ነኝ ሁሉም ያቃል
ለሳቸው ይሁን ብከሰስ
ሀገሬ ግንዷ ተነካ
አፈር ነው የሰው ልጅ ልብሱ
:
ሀጂ ግን እንዴት ቻሉበት
መሆንን ለወጣት ሱሱ...
አጣኖት አወ አባታችን
በመቃብሮ ቀናንባት
እርሶን ይዛለች እና
ማን መልሽ ማን አውጪ ይበላት😭😭
ሀጂ ሙፍቲ እንድሪስ የኢትዮጲያዊያን ሁሉ አባት ነበሩ 😭😭😭 እግዚአብሔር ነብሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑርልን
✍@dagi1u ግርማዊ ዳግም
❤22👎2👏2
ገበሬው ሞፈሩን ጥሎ ቢተምም
እንደምን ይሆናል ለሀገሩ ሀኪም
እንጂነሩም ትቶ ሀገር መገንባት
ሼፍ ሁን ብለው ቢያዙት ሽንኩርቱን ከአናት
ተማሪው ቀርቶበት ትምህርቱን አቋርጦ
ወታደር ሁን ቢሉት ይሮጣል አምልጦ
የቅኔው ዘራፊ ጥበቡን ዘንግቶ
ይገኛል ከሰፈር የሰው ኪስ ውስጥ ገብቶ
ስለዚህ ወዳጄ ቦታህን እወቀው
ያንተ ማንነትህ ስሪትህ እርሱ ነው
እንጂማ ጎበዜ ሁሉም ያለ ቦታ
ነውና መሆኑ ሚዶ ለመላጣ
✍ ብሩክ ተፈራ
እንደምን ይሆናል ለሀገሩ ሀኪም
እንጂነሩም ትቶ ሀገር መገንባት
ሼፍ ሁን ብለው ቢያዙት ሽንኩርቱን ከአናት
ተማሪው ቀርቶበት ትምህርቱን አቋርጦ
ወታደር ሁን ቢሉት ይሮጣል አምልጦ
የቅኔው ዘራፊ ጥበቡን ዘንግቶ
ይገኛል ከሰፈር የሰው ኪስ ውስጥ ገብቶ
ስለዚህ ወዳጄ ቦታህን እወቀው
ያንተ ማንነትህ ስሪትህ እርሱ ነው
እንጂማ ጎበዜ ሁሉም ያለ ቦታ
ነውና መሆኑ ሚዶ ለመላጣ
✍ ብሩክ ተፈራ
👍4❤2
ይቅር በል (ዳኒ ከአርባምንጭ)
--------------
ከቶ እንዳትመጻደቅ!!
ባንተ ሲሆን ድንገት, አንተ ስትጠየቅ
ሊከብድ እንደሚችል ቀድሞዉኑ ጠብቅ
ከከበደህ ደግሞ ምትለዉን አታዉቅ
ስለዚህ ተጠንቀቅ
ማለት ያለብህን አስቀድመህ እወቅ
.
.
.
ወጥነኸዉ ሳይሆን
ሳታስበዉ ጭራሽ
ወይ ተጠያቂ ልትሆን
ወይ ይቅርታህን አድራሽ
ባንዱ ትገኛለህ
ከሆንክ ስጋ ለባሽ!!!
.
.
.
ይቅርባዩ መምህር
እራሱ ሲያስተምር
ሰባት ጊዜ ሳይሆን ሰባሰባቴ እንድንምር
አስቦ ይሆናል እኛ እንድንማር
.
.
.
ምንም ሆኖ ቢሆን ምንም እንዳልሆነ
ረስቶት ይቅር ብሎ ደግሞ ካልኮነነ
በቃ አዉቆበታል እሱ ነዉ ይቅር-ባይ
አምላክ የሚምረዉ ኃጢአቱ ሚሰረይ
------------------------------
Jul. 6, 2013...
--------------
ከቶ እንዳትመጻደቅ!!
ባንተ ሲሆን ድንገት, አንተ ስትጠየቅ
ሊከብድ እንደሚችል ቀድሞዉኑ ጠብቅ
ከከበደህ ደግሞ ምትለዉን አታዉቅ
ስለዚህ ተጠንቀቅ
ማለት ያለብህን አስቀድመህ እወቅ
.
.
.
ወጥነኸዉ ሳይሆን
ሳታስበዉ ጭራሽ
ወይ ተጠያቂ ልትሆን
ወይ ይቅርታህን አድራሽ
ባንዱ ትገኛለህ
ከሆንክ ስጋ ለባሽ!!!
.
.
.
ይቅርባዩ መምህር
እራሱ ሲያስተምር
ሰባት ጊዜ ሳይሆን ሰባሰባቴ እንድንምር
አስቦ ይሆናል እኛ እንድንማር
.
.
.
ምንም ሆኖ ቢሆን ምንም እንዳልሆነ
ረስቶት ይቅር ብሎ ደግሞ ካልኮነነ
በቃ አዉቆበታል እሱ ነዉ ይቅር-ባይ
አምላክ የሚምረዉ ኃጢአቱ ሚሰረይ
------------------------------
Jul. 6, 2013...
❤2
Forwarded from 🟢ኦርቶዶክስ ተዋህዶ🟢
💍ከጋብቻ በፊት ሩካቤ (sex) መፈጸም ምን ችግር አለው⁉️
💁♂ከትዳር በፊት መሳም (ከንፈር ወዳጅ /kiss) ይቻላልን⁉️
👨🦱🧑🦳ፍቅረኛሞቹ እጅግ በጣም ስለሚውዋደዱ (ሩካቤ/sex) ቢፈጽሙ ምን ችግር አለው⁉️
⛪️በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ከተዋደዱ በኋላ ስሜታቸው ይገደባል⁉️
🤵♂የስሜት መግለጫዎች መፈጸም ይቻላል⁉️
በነዚህ ትምህርቶች ዙሪያ እየተማርን እንገኛለን
እርሶም እውቀቱ እዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን ማስፈንጠሪያ Link ጠቅ ያድርጉት
👇👇👇
@EOTC_-OPEN_channel
@EOTC_-OPEN_channel
@EOTC_-OPEN_channel
@EOTC_-OPEN_channel
👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
የይቱብ ቻናላችን
🔔
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺
❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
👇🏽👇🏽
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyjDUcNXW
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyjDUcNXW
💁♂ከትዳር በፊት መሳም (ከንፈር ወዳጅ /kiss) ይቻላልን⁉️
👨🦱🧑🦳ፍቅረኛሞቹ እጅግ በጣም ስለሚውዋደዱ (ሩካቤ/sex) ቢፈጽሙ ምን ችግር አለው⁉️
⛪️በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ከተዋደዱ በኋላ ስሜታቸው ይገደባል⁉️
🤵♂የስሜት መግለጫዎች መፈጸም ይቻላል⁉️
በነዚህ ትምህርቶች ዙሪያ እየተማርን እንገኛለን
እርሶም እውቀቱ እዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን ማስፈንጠሪያ Link ጠቅ ያድርጉት
👇👇👇
@EOTC_-OPEN_channel
@EOTC_-OPEN_channel
@EOTC_-OPEN_channel
@EOTC_-OPEN_channel
👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
የይቱብ ቻናላችን
🔔
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺
❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
👇🏽👇🏽
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyjDUcNXW
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyjDUcNXW
❤1
