ስንቱን ዘመን ጥዬ ፥ በስንቱ ተጥዬ
ስበድል ሳጠፋ ፥ ክፉ ዘር አብቅዬ
በሀጢአት ክምር ፥ ልቤ አንዴ ደንድኗል
የንስሀን እንባ ፥ ማንባት እንዴት ያውቃል???
አንተ ካልመራኸው ፥ አንተ ካልረዳኸው
የመፀፀት ሀይልን፥ አንተ ካላደልከው
አልነፃም ፈፅሞ ፥ አላገኝም ዋጋ
በእጆችህ ጎትተኝ ፥ ወዳንተ ልጠጋ
ፍቅርህን አብራርተህ ፥ በልቤ ፃፍና
አምርሬ ልመለስ ፥ ዕለት ዕለት ልፅና
✍✍ ብሩክ ተፈራ
ስበድል ሳጠፋ ፥ ክፉ ዘር አብቅዬ
በሀጢአት ክምር ፥ ልቤ አንዴ ደንድኗል
የንስሀን እንባ ፥ ማንባት እንዴት ያውቃል???
አንተ ካልመራኸው ፥ አንተ ካልረዳኸው
የመፀፀት ሀይልን፥ አንተ ካላደልከው
አልነፃም ፈፅሞ ፥ አላገኝም ዋጋ
በእጆችህ ጎትተኝ ፥ ወዳንተ ልጠጋ
ፍቅርህን አብራርተህ ፥ በልቤ ፃፍና
አምርሬ ልመለስ ፥ ዕለት ዕለት ልፅና
✍✍ ብሩክ ተፈራ
👍38❤26🔥3👏2
+ ያልተተከሉ ዛፎች +
አንድ ሩስያዊ የቴዎሎጂ መምህር የተናገሩትን አዝናኝ ወግ ሐበሻዊ ቀለም ሠጥቼ ልተርከው
ባልና ሚስት ከተጋቡ ጥቂት ዓመታት ቢያልፋቸውም ልጅ ግን አልወለዱም ነበር:: ወደ አንድ አባት ይሔዱና እባክዎን ልጅ እንዲሠጠን ይጸልዩልን ይሏቸዋል:: አባም ችግሩን ሰምተው የሚከተለውን ምክር ሠጡ
“እዚያ ተራራ ላይ ያለችው ገዳም ትታያችኁዋለች?" አሉአቸው
"አዎ አየናት" አሉ ባልና ሚስቱ
"ነገ በጠዋት እህል ሳትቀምሱ ሒዱና ገዳሙ ውስጥ የወይራ ዛፍ ተክላችሁ ልጅ ሥጠን ብላችሁ ስእለት ተሳሉ"
ባልና ሚስት በማግሥቱ ወደ ገዳሙ ሔደው የወይራ ዛፉን ተከሉ:: ይህ በሆነ በጥቂት ቀናት ልዩነት ውስጥ አባ ወደ ሌላ ሀገረ ስብከት ተመድበው ከዚያች ትንሽ የገጠር ከተማ ተሰናብተው ሔዱ::
ከሃያ ዓመታት ቆይታ በኁዋላ በአንድ አጋጣሚ አባ ወደዚያች ከተማ ተመልሰው መጡ:: ትንሹ ከተማ ትልቅ ሆኖ ብዙ ነገር ተለውጦ ጠበቃቸው:: የመጡበትን ጉዳይ ከፈጸሙ በኁዋላ የእነዚያ ባልና ሚስት ነገር ትዝ አላቸው:: በከተማው መቀየር ትንሽ ቢቸገሩም ቤቱን ፈልገው አገኙትና በር አንኳኩ::
አንድ የሚያምር ሕፃን የታቀፈች ሴት በሩን ከፈተች:: መካኒቱ ሴት ነበረች:: ከታቀፈችው ልጅ ሌላ እግርዋን ተጠምጥመው የያዙ ሁለት ሕጻናት አባን ሽቅብ እያዩ ይቁለጨለጫሉ:: መስቀል አሳልመው ወደ ውስጥ ሲዘልቁ ሶፋ ላይ ቁጭ ብለው ቴሌቪዥን የሚመለከቱ አራት ሕጻናት ተደርድረዋል::
ታላቆቻቸው የሚሆኑ ሁለት ልጆች ደግሞ ጠረጴዛው ላይ ቁጭ ብለው ያጠናሉ:: ይህ እንግዲህ ቡና የምታፈላውን ሴት ልጅና በሕፃን ልጅ አልጋ ላይ የተኛውን አራስ ልጅ ሳይጨምር ነው::
አባ በደስታም በመደነቅም ፈዝዘው ቀሩ::
"እንኩዋን ለዚህ አበቃችሁ ልጄ" አሏት በደስታ
"በእርስዎ ጸሎት ነው አባታችን" አለች እናት
"ለመሆኑ ባለቤትሽ የት ነው?" አሉ በጉጉት
እናት አንገትዋን ደፋች አባ ደነገጡ
"ምነው ሰላም አይደለም?" አሉ በስጋት
"ኸረ ሰላም ነው ... በጠዋት ወደዛች ተራራ ላይ ወዳለችው ገዳም ሔዶአል" አለች እያፈረች
"ምነው? ለምን ጉዳይ ሔደ?"
"ያኔ የተከልነውን የወይራ ዛፍ ሊቆርጥ"
✍🏽 ✍🏽 ✍🏽. ✍🏽. ✍🏽 ✍🏽 ✍🏽
ሊቁ ተርቱሊያን "የሰማዕታት ደም የክርስቲያኖች ዘር ነው" ብሎ ነበር:: "ክርስቲያን መግደል ክርስቲያን እንዲበቅል መዝራት ነው" እንደማለት ነው:: ከዚያ ውጪ ደግሞ ሌላው የክርስቲያን ዘር መውለድ ነው:: ብዙ ምእመናን የመውለድን ጸጋ ተጎናጽፈው ከመውለድ ይሸሻሉ::
ድሆች ሆነው እንኩዋን በፈጣሪ መግቦት አምነው የሚወልዱ እንዳሉ ሁሉ የኢኮኖሚ አቅም እያላቸው የተማሩ በመሆናቸው መውለድን እንደ ኁዋላ ቀርነት ቆጥረው ከመውለድ ወደ ኁዋላ የሚሉም ብዙዎች ናቸው::
ከላይ እንዳየነው ሰው ያህል እንኩዋን ሳይወልዱ ዛፍ ቆረጣ የሚሮጡ ብዙዎች ናቸው:: የሚወልደውን ኸረ በቃህ በቃሽ እያሉ የሚተቹ "ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉ ሲባል ብቻህን ልትሞላ ነው እንዴ?" ብለው በወለዱ የሚዘብቱ አሉ::
መውለድ ጸጋ በረከት ነው:: የልጅን ጣዕምና ጸጋ የወለዱ ሁሉ ያውቃሉ:: ልጅ መውለድ የወላጆችን መንፈሳዊ ሕይወት ሳይቀር ከፍ ያደርጋል:: ልጅ ፊት አይወራም ሲባል ከሚተው ክፉ ወሬ ጀምሮ አርኣያ ለመሆን ሲባል ከሚደረግ ጥረት ድረስ ልጅ መውለድ ትልቅ በረከት ነው::
ለቤተ ክርስቲያን ደግሞ የልጆች መብዛት በረከት ነው:: አንድ አባትም "በሕፃናት የለቅሶ ጩኸት የማትረበሽ ቤተ ክርስቲያን የነገ ተስፋ የሌላት ቤተ ክርስቲያን ናት" ብለዋል:: ሕፃናት የሚበዙባት ቤተ ክርስቲያን ግን ነገ እንደምትኖር ያረጋገጠች ቤተ ክርስቲያን ናት።
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥር 30/2012 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!
#share

👍24❤12
+ የሕፃናት ድንቅ ጥበብ የተሞሉ ንግግሮች +
ነቢዩ "የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል" መዝ 18:7 ይላል:: በእርግጥም ሕፃናት ልክ እንደ ብሂለ አበው ሊጠቀስ የሚችል ብዙ ደስ የሚያሰኝ ትምህርት ያለው ቃል ይናገራሉ:: በጥያቄያቸውም በመልሳቸውም የሚሉት ነገር ትምህርት ሊሆን ይላል:: የሚከተሉት ለዚህ ማሳያ የሚሆኑ ናቸው::
✍🏽 ✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽
እናት ቤት ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ በክብር አስቀምጣለች:: ሕፃን ልጅ ያይና ሊገልጠው ሲል
"ተው አትንካ እሱ የእግዚአብሔር መጽሐፍ ነው" ትለዋለች:: እሺ ብሎ ይተዋል:: ደጋግሞ ይህንን ሊያደርግ ሲል ይህ ማስጠንቀቂያ ይሠጠዋል:: እናቱም ቁጭ ብላ መጽሐፍ ቅዱስ ስታነብ አይቶ አያውቅም:: ስለዚህ ልጅ እንዲህ አላት :-
"እማዬ ይህ መጽሐፍ የእግዚአብሔር መጽሐፍ ነው ብለሽኛል:: እኛ ስለማንጠቀምበት ለምን አንመልስለትም?"
⛪️ የመጽሐፍ ቅዱስ ክብሩ መነበቡ ነው:: ሕይወት የሚሆነን እንዳያቃዠን ትራስ ላይ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ገልጠን ማንበባችን ነው:: ከፈጣሪ የተላከልንን ደብዳቤ ሳናነበው እንዳንሞት አደራ አለብን:: ለዚህም ነው አንድ አባት BIBLE የሚለውን ቃል Basic Information Before Leaving Earth ብለው የተነተኑት::
✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽
አስተማሪው በፈጣሪ መኖር የማያምን ነው:: ለሕፃናቱም ይህንን አስተሳሰቡን ማስተማር ፈለገና በሰሌዳ ላይ
GOD IS NO WHERE (እግዚአብሔር የትም የለም) ብሎ ጻፈ:: አንድዋን ሕፃን አስነሥቶ አንብቢ ሲላት ግን ያነበበችው እንዲህ ነበር::
GOD IS NOW HERE (እግዚአብሔር አሁን እዚህ አለ)
✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽
ማሙሽ ሳንቲም የሚያጠራቅምባት ትንሽ ባንክ አለችው::
አንድ ጠዋት ከወላጆቹ ጋር ቤተ ክርስቲያን አርፍዶ ሲመለስ ባንኩን ዘርግፎ ሳንቲሙን መቁጠር ጀመረ:: ይህንን ሥራውን ያየው አባቱ ምን እያደረገ እንደሆነ ሲጠይቀው እንዲህ ሲል መለሰ :-
"ዛሬ ቤተ ክርስቲያን አባ ሲያስተምሩ ክርስቶስ በቶሎ ይመጣል ብለዋል:: የሚመጣ ከሆነ ደግሞ ይህንን ሁሉ ሳንቲም ደብቄ ይዤ እንዲያገኘኝ ስለማልፈልግ በቶሎ ለድሆች ልሠጠው አስቤ ነው"
✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽
አቡነ ሺኖዳ ይህን ጽፈው ነበር::
በአንድ ሀገር ዝናም ጠፋ:: ሰዎች ሁሉ ተጨነቁ:: በመጨረሻም ምሕላ ለማድረግ ተወሰነ:: ሕዝቡ ሁሉ ወደ ቤተ ክርስቲያን ጉዞ ጀመረ:: አንዲት ሕፃን በጉዞው መካከል ጃንጥላ ይዛ ነበር:: ለምን እንደያዘች ስትጠየቅ እንዲህ አለች :-
"የምንሔደው ዝናም እንዲዘንም ልንለምን አይደል? ታዲያ ስንመለስ በምን እንጠለላለን?"
ስለዚህች ሕፃን እምነት በዚያን ቀን ዝናም ዘነመ::
ሕዝቡ ሲደበደብ እርስዋ ጥላ ይዛ ነበር::
✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽
ፓትርያርክ ታዋድሮስ እንዲህ አሉ
አንድ አስተማሪ ለሕፃናት ለወደፊት በሳይንስ ትምህርታችሁ ምን አዲስ ቴክኖሎጂ መፍጠር ትፈልጋላችሁ? አላቸው::
አንድዋ ሕፃን :- ሕልም ቀርጾ የሚያስቀር ትራስ
ስትል ሌላው ልጅ ደግሞ :- ሰው ሐሰት ሲናገር ውሸቱን ነው ብሎ የሚጮኽ የእጅ ሰዓት አለ::
✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽
አንድ ቅዱስ አባት ሕፃናት እንቆቅልሽ ሲጫወቱ ይሰማል
"እኔ የምወደው እሱ የሚጠላኝ ደሃ
እሱ የሚወደኝ ባለጠጋ ማን ነው?" አለ አንዱ ሕፃን::
የሕፃናቱን መልስ ሳይሰማ ያ አባት ልቡ ተነክቶ ሔደ::
እርሱ የተረጎመው እንዲህ ብሎ ነበር
"እርሱ የሚወደኝ እኔ የምጠላው ባለጠጋ ትዕዛዙን የማልፈጽምለት እግዚአብሔር ነው:: የሚጠላኝ ደሃ ደግሞ የእርሱን ፈቃድ የምፈጽምለት ሰይጣን ነው" ብሎ አዘነ::

👍27❤18
( ቆየን አይደል .. )
==============
ቆየን አይደል
:
የማለዳ አአዕዋፍ ድምጽ
ከእርጋታ ጋር ካደመጥን
ጀምበር ቀልታ ጎህ ስትቀድ
በተመስጦ ካደነቅን ...
ቆየን አይደል
:
እናት አባት ሲመርቁ
ከልባችን " አሜን " ካልን
ጨቅላ ሕጻናት በየሜዳው ሲቦርቁ
በመደሰት ካስተዋልን ....
ቆየን አይደል
:
ዝናብ መቶን ጸሐይ ሞቀን
" እፎይ " ካልን
ጨረቃ እና ኮከብ ናፍቀን
ወደ ሰማይ ቀና ካልን ....
ቆየን አይደል ?
==============
ቆየን አይደል
:
የማለዳ አአዕዋፍ ድምጽ
ከእርጋታ ጋር ካደመጥን
ጀምበር ቀልታ ጎህ ስትቀድ
በተመስጦ ካደነቅን ...
ቆየን አይደል
:
እናት አባት ሲመርቁ
ከልባችን " አሜን " ካልን
ጨቅላ ሕጻናት በየሜዳው ሲቦርቁ
በመደሰት ካስተዋልን ....
ቆየን አይደል
:
ዝናብ መቶን ጸሐይ ሞቀን
" እፎይ " ካልን
ጨረቃ እና ኮከብ ናፍቀን
ወደ ሰማይ ቀና ካልን ....
ቆየን አይደል ?
🔥18👍11🥰5❤4
🌹#ማመስገን_ማመስገን🌹
ማመስገን ማመስገን ብቻ ነው ሥራዬ
መዘመር መዘመር ብቻ ነው ተግባሬ
አንተማ አትለይም ከአንደበቴ/2/
አንተማ አትነጥፍም ከከንፈሬ/2/
🌺
አዝ....
🌺
ውለታህ ነው ውዴ የሚቀሰቅሰኝ
ማለዳ ማለዳ አዚመው የሚለኝ
የቀመስኩህ ውዴ ያጣጣምኩት ፍቅር
እንዴት ያስችለኛል በአፌ ሳልናገር
🌸
ልናገር ልናገር የአንተን ነገር
ላምህክህ ላውጅህ በአዲስ መዝሙር
አልጠግብህ አልጠግብህ ባወራህ
አንተማ አንተማ ልዩ ነህ
🌸
#ኢየሱስ_ልዩ_ነህ/4/
#ወዳጄ_ልዩ_ነህ
🌺
አዝ......
🌺
ከቋንቋ ይልቃል ከቃላትም በላይ
ምድር አይወስነዉም አይክልለው ሰማይ
የፍቅርህን መጠን አለካዉምና
ዕፁብ ዕፁብ ብዬ ላብዛልህ ምስጋና
🌺
አዝ....
🌺
በሞገስ ያቆምከኝ በጠላት ከተማ
ጥልቁን ያሻገርከኝ ያን ክፉ ጨለማ
በናቁኝ ሰዎች ፊት ያማረው ነገሬ
ኢየሱስ ሆነኽ ነው አዲሱ መዝሙሬ
🌺
አዝ.....
🌺
ማረፍ ሆኖልኛል ስምህን ስጠራ
አሜን ነው መዝሙሬ ስኖር ካንተ ጋራ
ማጉረምረም አይኖርም ማመስገን ብቻ ነው
ሲሞላም ሲጎልም ኢየሱስ ጌታ ነው
🌸
ልናገር ልናገር የአንተን ነገር
ላምህክህ ላውጅህ በአዲስ መዝሙር
አልጠግብህ አልጠግብህ ባወራህ
አንተማ አንተማ ልዩ ነህ
🌸
ነን ዋማ አን መቃ ኬ
ነን ለብሳ ነን ለብሳ አን ዋኤ ኬ
ሂን ቁፉ ሂን ቁፉ አን ሲፋርሴ
ኢየሱስ ኢየሱስ አደ ከንኬ
🌸
ንዘንጂ ንዘንጂ ያኸ አር
ኖድንኸ ኖድንኸ በገደር መዝሙር
አንጠፎኸ አንጠፎኸ ብንዝረጊኸ
አኽማ አኽማ ልይንኸ
🌸
ክዛረብ ክዛረብ ናትካ ነገር
ከምልኽካ ክእውጅ በሓዱሽ መዝሙር
አይፀግበካን አይፀግበካን ተዛሪበ
ንስኻኮ ንስኻኮ ፍሉይ ኢኻ
🌸
ኦዳና ኦዳና ታኔ ነዋ
ጎኛና ጎኛና አዋጀና ኦራንቲያን መዝሙሪያን
ካሊኬ ካሊኬ ሃሰያዬ
ኔኒ ታው ኔኒ ታው ዱማቴኔ
🌸
ላዋልክ ላዋልክ ያተን መርካ
ሊውዲንከ ሊውዲንከ በአጂሰ አሐት
ኢለውጦፋ ኢለውጦፋ ቢላዋልካ
አተማ አተማ በሬዳንካ
🌸
#ኢየሱስ_ልዩ_ነህ/4/
#ወዳጄ_ልዩ_ነህ
ማመስገን ማመስገን ብቻ ነው ሥራዬ
መዘመር መዘመር ብቻ ነው ተግባሬ
አንተማ አትለይም ከአንደበቴ/2/
አንተማ አትነጥፍም ከከንፈሬ/2/
🌺
አዝ....
🌺
ውለታህ ነው ውዴ የሚቀሰቅሰኝ
ማለዳ ማለዳ አዚመው የሚለኝ
የቀመስኩህ ውዴ ያጣጣምኩት ፍቅር
እንዴት ያስችለኛል በአፌ ሳልናገር
🌸
ልናገር ልናገር የአንተን ነገር
ላምህክህ ላውጅህ በአዲስ መዝሙር
አልጠግብህ አልጠግብህ ባወራህ
አንተማ አንተማ ልዩ ነህ
🌸
#ኢየሱስ_ልዩ_ነህ/4/
#ወዳጄ_ልዩ_ነህ
🌺
አዝ......
🌺
ከቋንቋ ይልቃል ከቃላትም በላይ
ምድር አይወስነዉም አይክልለው ሰማይ
የፍቅርህን መጠን አለካዉምና
ዕፁብ ዕፁብ ብዬ ላብዛልህ ምስጋና
🌺
አዝ....
🌺
በሞገስ ያቆምከኝ በጠላት ከተማ
ጥልቁን ያሻገርከኝ ያን ክፉ ጨለማ
በናቁኝ ሰዎች ፊት ያማረው ነገሬ
ኢየሱስ ሆነኽ ነው አዲሱ መዝሙሬ
🌺
አዝ.....
🌺
ማረፍ ሆኖልኛል ስምህን ስጠራ
አሜን ነው መዝሙሬ ስኖር ካንተ ጋራ
ማጉረምረም አይኖርም ማመስገን ብቻ ነው
ሲሞላም ሲጎልም ኢየሱስ ጌታ ነው
🌸
ልናገር ልናገር የአንተን ነገር
ላምህክህ ላውጅህ በአዲስ መዝሙር
አልጠግብህ አልጠግብህ ባወራህ
አንተማ አንተማ ልዩ ነህ
🌸
ነን ዋማ አን መቃ ኬ
ነን ለብሳ ነን ለብሳ አን ዋኤ ኬ
ሂን ቁፉ ሂን ቁፉ አን ሲፋርሴ
ኢየሱስ ኢየሱስ አደ ከንኬ
🌸
ንዘንጂ ንዘንጂ ያኸ አር
ኖድንኸ ኖድንኸ በገደር መዝሙር
አንጠፎኸ አንጠፎኸ ብንዝረጊኸ
አኽማ አኽማ ልይንኸ
🌸
ክዛረብ ክዛረብ ናትካ ነገር
ከምልኽካ ክእውጅ በሓዱሽ መዝሙር
አይፀግበካን አይፀግበካን ተዛሪበ
ንስኻኮ ንስኻኮ ፍሉይ ኢኻ
🌸
ኦዳና ኦዳና ታኔ ነዋ
ጎኛና ጎኛና አዋጀና ኦራንቲያን መዝሙሪያን
ካሊኬ ካሊኬ ሃሰያዬ
ኔኒ ታው ኔኒ ታው ዱማቴኔ
🌸
ላዋልክ ላዋልክ ያተን መርካ
ሊውዲንከ ሊውዲንከ በአጂሰ አሐት
ኢለውጦፋ ኢለውጦፋ ቢላዋልካ
አተማ አተማ በሬዳንካ
🌸
#ኢየሱስ_ልዩ_ነህ/4/
#ወዳጄ_ልዩ_ነህ
👍12❤8🥰5
ናና አማኑኤል
Orthodox Mezmur Channel
ናና አማኑኤል | ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ (የአእላፋት ዝማሬ)
ናና አማኑኤል ና መድኃኒቴ
ጽድቅህን አልብሰኝ ይቅር መራቆቴ /2/
ናና አማኑኤል ና መድኀኒቴ
ፍቅርህን አልብሰኝ ይቅር መራቆቴ /2/
አዝ
የምሕረት አባት አማኑኤል
የቸርነት ጌታ ''
ፊትህ የተመላ ''
ሁሌ በይቅርታ ''
ካለው ፍቅር በላይ ''
አባት ለአንድ ልጁ ''
አምላክ ይወደናል ''
አይጥለንም ከእጁ ''
አዝ
መድኃኒቴ ልበል አማኑኤል
ድኛለው በሞትህ ''
ቁስሌ ተፈውሷል ''
በቁስልህ በሞትህ ''
ስሸጥህ አቀፍከኝ ''
ስወጋህ አይኔ በራ ''
በፍቅርህ አወጣኽኝ ''
ከዚያ ከመከራ ''
አዝ
አንተ ከኔ ጋር ነህ አማኑኤል
አዎ ከኔ ጋራ ''
ድል አርገህልኛል ''
የጭንቄን ተራራ ''
በጉባኤ መሀል ''
አፌ አንተን አወጀ ''
የከበረ ደምህ ''
ነፍሴን ስለዋጀ ''
አዝ
የድንግሏ ፍሬ አማኑኤል
የበላቴናዋ ''
የቤቴ ምሰሶ ''
የነፍሴ ቤዛዋ ''
መሠረቴ አንተ ነህ ''
ያሳደገኝ እጅህ ''
አተወኝም አንተ ''
ስለሆንኩኝ ልጅህ ''
ናና አማኑኤል ና መድኃኒቴ
ጽድቅህን አልብሰኝ ይቅር መራቆቴ /2/
ናና አማኑኤል ና መድኀኒቴ
ፍቅርህን አልብሰኝ ይቅር መራቆቴ /2/
አዝ
የምሕረት አባት አማኑኤል
የቸርነት ጌታ ''
ፊትህ የተመላ ''
ሁሌ በይቅርታ ''
ካለው ፍቅር በላይ ''
አባት ለአንድ ልጁ ''
አምላክ ይወደናል ''
አይጥለንም ከእጁ ''
አዝ
መድኃኒቴ ልበል አማኑኤል
ድኛለው በሞትህ ''
ቁስሌ ተፈውሷል ''
በቁስልህ በሞትህ ''
ስሸጥህ አቀፍከኝ ''
ስወጋህ አይኔ በራ ''
በፍቅርህ አወጣኽኝ ''
ከዚያ ከመከራ ''
አዝ
አንተ ከኔ ጋር ነህ አማኑኤል
አዎ ከኔ ጋራ ''
ድል አርገህልኛል ''
የጭንቄን ተራራ ''
በጉባኤ መሀል ''
አፌ አንተን አወጀ ''
የከበረ ደምህ ''
ነፍሴን ስለዋጀ ''
አዝ
የድንግሏ ፍሬ አማኑኤል
የበላቴናዋ ''
የቤቴ ምሰሶ ''
የነፍሴ ቤዛዋ ''
መሠረቴ አንተ ነህ ''
ያሳደገኝ እጅህ ''
አተወኝም አንተ ''
ስለሆንኩኝ ልጅህ ''
👍13❤12
ገብርኄር
.
የክርስቲያን ወጉ ፤
የክርስቲያን ህጉ፤
ነፍስን በዘራበት በአምላኩ አምኖ፤
መክሊቱን አትርፎ በጥቂቱ ታምኖ፤
ሞገስን አግኝቶ በብዙ መሾም ነው፤
ከሀጢአት ርቆ በፅድቅ መኖር ነው።
ይህ ነው ክርስትና
በአፍ እያወራ ድኛለው አይልም
ተግባር የሌለው ቃል ከቶ ፅድቅ አይሆንም
.
የክርስቲያን ወጉ ፤
የክርስቲያን ህጉ፤
ነፍስን በዘራበት በአምላኩ አምኖ፤
መክሊቱን አትርፎ በጥቂቱ ታምኖ፤
ሞገስን አግኝቶ በብዙ መሾም ነው፤
ከሀጢአት ርቆ በፅድቅ መኖር ነው።
ይህ ነው ክርስትና
በአፍ እያወራ ድኛለው አይልም
ተግባር የሌለው ቃል ከቶ ፅድቅ አይሆንም
🥰17❤15👍7
ቅጽርህ የእናት እቅፍ
ሸክምን የሚያራግፍ
አልተነፍስ ጸሎት አይወጣ ቃል ከአፌ
ይተናል ጭንቀቴ ስመለስ አርፌ
እመጣለሁ ደጅህ ሀሳብ አንጠልጥዬ
እገባለሁ ቅጽርህ አንገቴን ደፍቼ
መች ታዝንብኛለህ
መች ትወቅሰኛለህ በሽቅጬ ከርፍቼ
አይነድህ ድፍረቴ
አይቆጨኝ ስንፈቴ
አይበሽቅህ ስህተቴ
አይገደኝ ዝለቴ
በኦና ተግባሬ
ውድቀት አንከርፍፌ ስቆም ከነእድፌ
ምን አድርጌልህ ነው?
አክመህ ምትልከኝ በምህረት መርፌ
ከመቀመጥ በቀር
ኢምንት ታህል ድርጊት ፈጽሜ የማላውቅ
አንዲት ዘለላ እንባ
በጉንጬ ሳልሰድ እንዴት ደመቅኩ በሳቅ?
እንዴት ቻልኩ መፍገግ?
እንዴት ቻልኩ ማማር?
እሬት ህይወት ይዤ
አጣፍጥልኝ ሳልል ሳልጠይቅ የሀሴት ማር
ትዕቢት አይሉት ጥጋብ
ፍርሃት አይሉት ስጋት
ስም ያላገኘሁለት
አንዳች አሳሪ ኃይል ወርሮኝ እንደ ውጋት
አላልኩኝ እግዚኦታ አልቆምኩኝ ሰዓታት
ፈውስ አሰኝቶኝ አላደረስኩ ኪዳን
ስለረገጥኩ ብቻ
ስላረፍኩ በቤትህ ይገባኝ ነበር መዳን?
እንጃ!
ብቻ እመጣለሁ ሀሳብ አንጠልጥዬ
ደጅህ እገኛለሁ ማረኝ ቃልን ጥዬ
አርፋለሁ ካንዱ ጥግ አንገቴን ደፍቼ
መች ትቆጣኛለህ
ሰማዕቱ ጊዮርጊስ ከነእድፌ ተኝቼ
ቆይቼ
ቆይቼ
.
.
.
ቆይቼ ስነሳ
ተጋድሞ አየዋለሁ ሸክሜ እንደ ሬሳ
አልጸለየም ሳትል
አልለመነም ሳትል
አላነባም ሳትል
ይገርመኛል እኮ
ጊዮርጊስ አባቴ ጭንቀቴን ስትጥል
ይገርመኛል ቅጽርህ...
ልክ እንደ እናት እቅፍ
ደስታን 'ሚያሳቅፍ!
አባብሎ 'ሚያሳርፍ!
ሸክምን 'ሚያራግፍ!
.
.
.
እርፍ!
#ኤልዳን
ሸክምን የሚያራግፍ
አልተነፍስ ጸሎት አይወጣ ቃል ከአፌ
ይተናል ጭንቀቴ ስመለስ አርፌ
እመጣለሁ ደጅህ ሀሳብ አንጠልጥዬ
እገባለሁ ቅጽርህ አንገቴን ደፍቼ
መች ታዝንብኛለህ
መች ትወቅሰኛለህ በሽቅጬ ከርፍቼ
አይነድህ ድፍረቴ
አይቆጨኝ ስንፈቴ
አይበሽቅህ ስህተቴ
አይገደኝ ዝለቴ
በኦና ተግባሬ
ውድቀት አንከርፍፌ ስቆም ከነእድፌ
ምን አድርጌልህ ነው?
አክመህ ምትልከኝ በምህረት መርፌ
ከመቀመጥ በቀር
ኢምንት ታህል ድርጊት ፈጽሜ የማላውቅ
አንዲት ዘለላ እንባ
በጉንጬ ሳልሰድ እንዴት ደመቅኩ በሳቅ?
እንዴት ቻልኩ መፍገግ?
እንዴት ቻልኩ ማማር?
እሬት ህይወት ይዤ
አጣፍጥልኝ ሳልል ሳልጠይቅ የሀሴት ማር
ትዕቢት አይሉት ጥጋብ
ፍርሃት አይሉት ስጋት
ስም ያላገኘሁለት
አንዳች አሳሪ ኃይል ወርሮኝ እንደ ውጋት
አላልኩኝ እግዚኦታ አልቆምኩኝ ሰዓታት
ፈውስ አሰኝቶኝ አላደረስኩ ኪዳን
ስለረገጥኩ ብቻ
ስላረፍኩ በቤትህ ይገባኝ ነበር መዳን?
እንጃ!
ብቻ እመጣለሁ ሀሳብ አንጠልጥዬ
ደጅህ እገኛለሁ ማረኝ ቃልን ጥዬ
አርፋለሁ ካንዱ ጥግ አንገቴን ደፍቼ
መች ትቆጣኛለህ
ሰማዕቱ ጊዮርጊስ ከነእድፌ ተኝቼ
ቆይቼ
ቆይቼ
.
.
.
ቆይቼ ስነሳ
ተጋድሞ አየዋለሁ ሸክሜ እንደ ሬሳ
አልጸለየም ሳትል
አልለመነም ሳትል
አላነባም ሳትል
ይገርመኛል እኮ
ጊዮርጊስ አባቴ ጭንቀቴን ስትጥል
ይገርመኛል ቅጽርህ...
ልክ እንደ እናት እቅፍ
ደስታን 'ሚያሳቅፍ!
አባብሎ 'ሚያሳርፍ!
ሸክምን 'ሚያራግፍ!
.
.
.
እርፍ!
#ኤልዳን
❤38👍19
🔴 አዲስ ዝማሬ "ማርያም ማርያም" ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ.mp3
ማርያም ማርያም
ማርያም ማርያም ልበል
እረፍቴ ሆይ በስምሽ ልጠለል
የቃል እናት ያድናል ቃልሽ
ታምር ይሰራል ስምሽ
አዝ
ማር ልበል በምድር ያም ልበል በሰማይ
የማይጠግቡት መና የማይጨርሱት ሲሳይ
መንፈስ ቅዱስ ቃኝቶ ሰርቶ በሚስጥሩ
አፌ ላይ ጣፈጠኝ ስምሽ አጠራሩ (2)
አዝ
መዳኒት ታቅፈሽ የአለሙን ጌታ
ከቤተልሄም ደጅ እስከ ጎለጎታ
የዓለሙን ህምም የዓለሙን በሽታ
ታክሚው ነበረ ድንግል በዝምታ (2)
አዝ
በምን እንመስልሽ የለሽም ምሳሌ
አንጠግብም ብንጠራሽ ብንዘምርልሽ ሁሌ
ምስክር አያሻም ያንቺ ልእልና
የአለሙን ንጉሥ ወልደሺዋልና (2)
አዝ
የወርቅ ማእጠንት እሳት የታቀፍሽ
የአዲስ ኪዳን ኪሩብ ማርያም አንቺ ነሽ
የአርያም እጣን ነሽ መአዛሽ ያማረ
ዘላለም አይወድቅም አንቺን ያከበረ (2)
ማርያም ማርያም ልበል
እረፍቴ ሆይ በስምሽ ልጠለል
የቃል እናት ያድናል ቃልሽ
ታምር ይሰራል ስምሽ
አዝ
ማር ልበል በምድር ያም ልበል በሰማይ
የማይጠግቡት መና የማይጨርሱት ሲሳይ
መንፈስ ቅዱስ ቃኝቶ ሰርቶ በሚስጥሩ
አፌ ላይ ጣፈጠኝ ስምሽ አጠራሩ (2)
አዝ
መዳኒት ታቅፈሽ የአለሙን ጌታ
ከቤተልሄም ደጅ እስከ ጎለጎታ
የዓለሙን ህምም የዓለሙን በሽታ
ታክሚው ነበረ ድንግል በዝምታ (2)
አዝ
በምን እንመስልሽ የለሽም ምሳሌ
አንጠግብም ብንጠራሽ ብንዘምርልሽ ሁሌ
ምስክር አያሻም ያንቺ ልእልና
የአለሙን ንጉሥ ወልደሺዋልና (2)
አዝ
የወርቅ ማእጠንት እሳት የታቀፍሽ
የአዲስ ኪዳን ኪሩብ ማርያም አንቺ ነሽ
የአርያም እጣን ነሽ መአዛሽ ያማረ
ዘላለም አይወድቅም አንቺን ያከበረ (2)
❤8👍7
ኃያል ነው እግዚአብሔር
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
ኃያል ነው እግዚአብሔር
ኃያል ነው እግዚአብሔር
ኃያል ነው ቅዱሱ /2/
አይቻለሁ በዓይኔ ሲቆም ማዕበሉ
አይቻለሁ በዓይኔ ሲታዘዝ ነፋሱ
አዝ
ሰረገላውን በእሳት ሠርቶታል
በደመና ላይ ይረማመዳል
በብርሃን ድንኳን በሰማይ ያለው
እርሱ ነው ጌታ የምናመልከው /2/
አዝ
እውነት በፊቱ ፍትሕ በእጁ
ሲኦልም ገነት አሉ በደጁ
ሥልጣን የእርሱ ነው አለቅነት
ማን እንደ ጌታ ከአማልክት /2/
አዝ
ታቦር ተራራ ተንቀጠቀጠ
ግርማው ሲገለጥ ሁሉ ቀለጠ
ድንቅን አድራጊ ተአምረኛ
ከማዳኑ ጋር ይምጣ ወደ እኛ /2/
አዝ
ምድር ጠፈሩ ታዟል ለእርሱ
እሳት ተፈትሎ ሆኗል ቀሚሱ
የክብርህ ብርሃን ይብራ በልቤ
አንተ ነህ ለእኔ ውድ ገንዘቤ /2/
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
እርሱ ነው ጌታ የምናመልከው
Guys ለዛሬ ይሄን መዝሙር ተጋበዙልኝ😘😘😘
ኃያል ነው እግዚአብሔር
ኃያል ነው ቅዱሱ /2/
አይቻለሁ በዓይኔ ሲቆም ማዕበሉ
አይቻለሁ በዓይኔ ሲታዘዝ ነፋሱ
አዝ
ሰረገላውን በእሳት ሠርቶታል
በደመና ላይ ይረማመዳል
በብርሃን ድንኳን በሰማይ ያለው
እርሱ ነው ጌታ የምናመልከው /2/
አዝ
እውነት በፊቱ ፍትሕ በእጁ
ሲኦልም ገነት አሉ በደጁ
ሥልጣን የእርሱ ነው አለቅነት
ማን እንደ ጌታ ከአማልክት /2/
አዝ
ታቦር ተራራ ተንቀጠቀጠ
ግርማው ሲገለጥ ሁሉ ቀለጠ
ድንቅን አድራጊ ተአምረኛ
ከማዳኑ ጋር ይምጣ ወደ እኛ /2/
አዝ
ምድር ጠፈሩ ታዟል ለእርሱ
እሳት ተፈትሎ ሆኗል ቀሚሱ
የክብርህ ብርሃን ይብራ በልቤ
አንተ ነህ ለእኔ ውድ ገንዘቤ /2/
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
እርሱ ነው ጌታ የምናመልከው
Guys ለዛሬ ይሄን መዝሙር ተጋበዙልኝ😘😘😘
❤16👍5
፨አህያዋ፨
ከእንስሳት ተለይታ
ልትቆም በሰው ተርታ
ሊቀመጥባት ጌታዋ
ሊታወቅላት ዋጋዋ
ላይጠፋባት አደራዋ
ሰው የማገልገል ስራዋ
ሲመጣላት ፈጣሪዋ
ደስ አላት አህያዋ
ሲቀመጥባት በጀርባዋ።
ውርንጭላነቷ ቀርቶ
የታሰረችበት ገመድ ተፈቶ
መናቅ መሰደቧ ጠፍቶ
የዋሁ የጺዮን ልጅ ትህትናን ተመልቶ
አስገባት ከተማ በህዝቡ ፊት መርቶ።
አፋቸው ተለጉሞ
ሃሳባቸው ከፍቶ ጠሞ
አዋቂ ነን ባዮቹ
የአይሁድ ካህናት ግብዞቹ
ዝም ቢሉ ለምስጋና
ለመራቸው በደመና
ለመገባቸው ከሰማይ መና
መመስገኑ መቼ ቀረና
እየተባለ ሆሳእና።
በሴቶች በወንዶቹ
በአዛውንት በልጆቹ
በህጻናት ጡት ጠቢዎቹ።
የዘኪዮስ ምኞት
መቼ ተረሳ በእጥረቱ
ዛፍ ላይ ብቻ በመታየቱ
አለቀረም ፍላጎቱ
ለመዘመር መጓጓቱ
ገብቶለታል ወደ ቤቱ
የጺዮን ልጅ ያትሁቱ
ሊበላ አብሮት ከፍትፍቱ።
መቅደስ ገብቶ ዞሮ ሲቃኝ
ሲመለከት ጊዜ አባካኝ
ጽሎት ትቶ ሲቸረችር
ከሌባ ጋር ሲደራደር
አልቻለም ስለ ቤቱ
ሲያቃጥለው ቅንአቱ
ጅራፍ ሰራ ለትምህርቱ
ቤቱን ሊያጠራ ከጠላቱ።
ከእንስሳት ተለይታ
ልትቆም በሰው ተርታ
ሊቀመጥባት ጌታዋ
ሊታወቅላት ዋጋዋ
ላይጠፋባት አደራዋ
ሰው የማገልገል ስራዋ
ሲመጣላት ፈጣሪዋ
ደስ አላት አህያዋ
ሲቀመጥባት በጀርባዋ።
ውርንጭላነቷ ቀርቶ
የታሰረችበት ገመድ ተፈቶ
መናቅ መሰደቧ ጠፍቶ
የዋሁ የጺዮን ልጅ ትህትናን ተመልቶ
አስገባት ከተማ በህዝቡ ፊት መርቶ።
አፋቸው ተለጉሞ
ሃሳባቸው ከፍቶ ጠሞ
አዋቂ ነን ባዮቹ
የአይሁድ ካህናት ግብዞቹ
ዝም ቢሉ ለምስጋና
ለመራቸው በደመና
ለመገባቸው ከሰማይ መና
መመስገኑ መቼ ቀረና
እየተባለ ሆሳእና።
በሴቶች በወንዶቹ
በአዛውንት በልጆቹ
በህጻናት ጡት ጠቢዎቹ።
የዘኪዮስ ምኞት
መቼ ተረሳ በእጥረቱ
ዛፍ ላይ ብቻ በመታየቱ
አለቀረም ፍላጎቱ
ለመዘመር መጓጓቱ
ገብቶለታል ወደ ቤቱ
የጺዮን ልጅ ያትሁቱ
ሊበላ አብሮት ከፍትፍቱ።
መቅደስ ገብቶ ዞሮ ሲቃኝ
ሲመለከት ጊዜ አባካኝ
ጽሎት ትቶ ሲቸረችር
ከሌባ ጋር ሲደራደር
አልቻለም ስለ ቤቱ
ሲያቃጥለው ቅንአቱ
ጅራፍ ሰራ ለትምህርቱ
ቤቱን ሊያጠራ ከጠላቱ።
👍24❤6👎1
ሆሳዕና
.
.
ዘንባባን አንጥፈዉ አንተን ያከበሩ፤
ሆሳዕና ብለዉ ትናንት የዘመሩ፤
ቀን ቢጨልምብህ.......
በጲላጦስ ጊቢ አቁመዉ ከሰሱህ፤
ቀራንዮ ወስደዉ ጌታዬ ሰቀሉህ
.......................................።..
በዔደን ታደሰ
.
.
ዘንባባን አንጥፈዉ አንተን ያከበሩ፤
ሆሳዕና ብለዉ ትናንት የዘመሩ፤
ቀን ቢጨልምብህ.......
በጲላጦስ ጊቢ አቁመዉ ከሰሱህ፤
ቀራንዮ ወስደዉ ጌታዬ ሰቀሉህ
.......................................።..
በዔደን ታደሰ
👍22
Forwarded from Ab
ያወጣው አዲስ መዝሙር
ሁላቺንም ገብታችሁ ስሙት
ለመስማት
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍7❤4👏2
ንሴብሆ ለእግዚአብሔር
❤️ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬ❤️
✞ ንሴብሆ ✞
ንሴብሆ /2/ለእግዚአብሔር /2/
ስቡሐ ዘተሰብሐ /4
እናመስግነው/2/ እግዚአብሔርን/2/
ምስጉን ነው የተመሰገነ /4/
አዝ-----
ባህሩን ተሻግረን ወንዙ ደረቅ ሆነ
በጠላታችን ላይ ድሉ የኛ ሆነ
ከባርነት ቀንበር ፍፁም ነፃ ወጣን
ሕይወት የሚሰጥ መና ነው ምግባችን
አዝ-----
አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል መከራ ቢበዛ
ኃይላችን ጌታ ነው የዓለሙ ቤዛ
አዝ-----
ከአለት ላይ ውሃ ፈልን ጠጣን
ይህን ታላቅ ጌታ ኑ እናመስግን
ሰዎች ደስ ይበለን ሕይወታችን ድኗል
ሰይጣን ጠላታችን አፍሮ ተመልሷል
አዝ-----
አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል ፈተና ቢበዛ
ኃይላችን ጌታ ነው የዓለሙ ቤዛ
ንሴብሆ /2/ለእግዚአብሔር /2/
ስቡሐ ዘተሰብሐ /4
እናመስግነው/2/ እግዚአብሔርን/2/
ምስጉን ነው የተመሰገነ /4/
አዝ-----
ባህሩን ተሻግረን ወንዙ ደረቅ ሆነ
በጠላታችን ላይ ድሉ የኛ ሆነ
ከባርነት ቀንበር ፍፁም ነፃ ወጣን
ሕይወት የሚሰጥ መና ነው ምግባችን
አዝ-----
አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል መከራ ቢበዛ
ኃይላችን ጌታ ነው የዓለሙ ቤዛ
አዝ-----
ከአለት ላይ ውሃ ፈልን ጠጣን
ይህን ታላቅ ጌታ ኑ እናመስግን
ሰዎች ደስ ይበለን ሕይወታችን ድኗል
ሰይጣን ጠላታችን አፍሮ ተመልሷል
አዝ-----
አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል ፈተና ቢበዛ
ኃይላችን ጌታ ነው የዓለሙ ቤዛ
👍9❤6