Telegram Web Link
--አቤቱ--
------------
ደግ ሰው አለቀ፤
ሁሉ ክንድህ ስር ወደቀ።
ልጆችህ ተጨንቀናል፤
ከእግርህ በታች ወድቀናል።
እምነታችን አልፀና፤
ማእበል በረታና።
አለም መአት ወረደባት፤
መርከባችንን ምጥ ያዛት።
አቤቱ....
በደቃቃ ደዌ፥ ትውልድ ረገፈ፤
አንም አልተገኘ ፥መከራን ያለፈ።
ጌታ ካላቆምከው፥ በቃችሁ ካላልከን፤
በሰማይ በምድር፥ ረዳት ማን አለን።
የቤትህ ግርግዳ፥ በሳት የተሰራ፤
ይበቃሻል በላት፥ ያለምን መከራ።
መፍረስ የሌለብህ፥ የመድሀኒት ደጃፍ።
አንተ ትችላለህ፥ መከራን ማሳለፍ፤
እማማ ኢትዮጵያ፥ ይቺ ቅድስት ሀገር፤
እናቴ ኢትዮጵያ፥ ይቺ ታላቅ ሀገር።
በዘመናት ችግር፥ ትከሻዋ ጎብጧል፤
በሸክሟ ጽናት፥ ጀርባዋ ተልጧል፤
አትችልም ጌታዬ፥ እናቴ ደክማለች።
ቀና ካላረካት፥ ጎብጣ ትቀራለች፤
አትችልም ሀገሬ፥ መከራ በቅቷታል።
ችግር በየአይነቱ፥
ጦርነት ባይነቱ፥ ተፈራርቆባታል።
አትችልም ጌታዬ፥ እናቴ ደክማለች፤
ይበቃል ካላልካት፥ ጎብጣ ትቀራለች።
አንድ ጻድቅ ጠፍቶ፥ ከቶም በምድሪቱ፤
ከፈርኦን መከራ፥ ጨከነ መአቱ።
ቸነፈር ፀናብን፥ ቀባሪ እስኪጠፋ፤
ዋኔ ዋኔ ሆኗል፥ የእንባችን ተስፋ።
ክንድህን የቻለ፥ የምድር ሀይል የለም፤
ሀያል ነህ ዘላለም ጌታ መድሀኔአለም።
አንድም ሶስትም ፥ሆነህ አለምን የገዛህ፤
ዛሬም ለዘላለም፥ የምትኖር አንተ ነህ።
የመጻጉን አልጋ፥ በራሱ ያሸከምክ፤
የጣቢታን ትንፋሽ፥ በቃልህ የመለስክ።
በልብሶችህ ቁጨት፥ የደም ምንጭ ያደረክ፤
በምራቅህ ስለህ አይን፥ የፈጠርክ አምላክ።
ታምራትህ ብዙ፥ ፍቅርህ ለዘላለም፤
ምረትህን ስጠን፥ ጌታ መድሀኔ አለም።
++++++++++++++++++++
#ElmestoAgya #እልመስጦአግያ #Share

——ዳግም ትንሳኤ——

በተዘጉ ደጆች፣ ገባ አምላካችን፤
ሰላም ለናንተ ይሁን፣ አለን ሰላማችን፡፡
ቶማስ ሆይ አስገባ፣ ጣትህን በጎኑ፤
እጅግ ብፁዓን ናቸው፣ ሳያዩ የሚያምኑ።
Guys ዛሬ አንድ ምርጥ ቻናል ልጋብዛቹህ ሁላቹም ይህን ቻናል እየገባቹ join አድርጉ እና ትወዱታላቹህ

https://www.tg-me.com/Apostolic_Answers
♡ ሁሉም ያልፋል ♡
✞ የመዝሙር ግጥሞች ✞
♡ ሁሉም ያልፋል ♡

ሁሉም ያልፋል እግዚአብሔር ያሳልፋል /2/
ልጆቹን መቼ ይረሳል

ብርሃን ይመጣል ጨለመው ተገፎ
ደስታ ይሆናል መከራው አልፎ
የምስራች ቃል ይሞላል በአፋችን
ሀዘናችን ጠፍቶ ይፈካል ፊታችን/2/

በትር ነው ምርኩዝ ነው እሱን ላመኑበት
ባህር ውቅያኖሱን ከፍለው የሚያልፉበት
በእሳት መካከል በግፍ ለተጣሉ
ውሃ እየሆናቸው በድል ይወጣሉ /2/

ማስተዋል ጥሩ ነው ትዕዛዛቱን ማክበር
ያኖራል በሕይወት በሰማይ በምድር
የማያልፍ ቀን የለም ታሪክ የማይሆን
በአምላክ አንድ ቀን ነው አንድ ሺ ዘመን /2/

ይቅርታ እንዲሰጠን በደልን ሳይቆጥር
ማረን እንበለው ስለሆነ ፍቅር
ነገ ቀን ሲመጣ ብርሀኑ ሲያበራ
ፊታችን እንዳይዞር ወደ ክፉ ስራ /2/
ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒 pinned «Guys ዛሬ አንድ ምርጥ ቻናል ልጋብዛቹህ ሁላቹም ይህን ቻናል እየገባቹ join አድርጉ እና ትወዱታላቹህ https://www.tg-me.com/Apostolic_Answers»
#ኧረ_አልሆንልኝም_አለ

/ድንቅ የንስሐ መነባንብ/

ኧር አልሆንልኝም አለ መንፈሴ አልገዛም አለ፤
የጭንቅ አማላጅቱ አንድ ብትዪኝ ምን አለ?

ጸሎት ምህላ አቃተኝ መንፈሴ ለንሰሐ ሸፈተ፤
መንጸፈ ደይን ወደቅኩኝ ነፍሴ በኃጢአት ሸፈተ።
እምቢ አለኝ ፆም ጸሎት እምቢኝ አለኝ ንስሐ፤
ስጋ መንፈሴ ኮብልሎ እየዋኘ ከዓለም ውሃ።

ኧር አንድ በይኝ እመቤቴ ወለላይቱ ተማለጂኝ፤
ጨርሶ ዓለም ሳይነጥቀኝ ከወደኩበት አንሺኝ።

ነጭ ነጠላ አጣፍቼ ከቤተ መቅደስ ስወጣ፤
መጽሐፍ ቅዱስ ዘርግቼ ለስብከት መድረክ ስወጣ፤
ልብሰ ተክህኖ ለብሼ ንፍቅ ገባሬ ሰናይ ስሆን፤
ጥቅስ በቃሌ ስደረድር ለዜማ ቅኔ ስቀኝ፤
አካሌ እዚህ ሆኖ መንፈሴ እየሸፈተ፤
ነፍሴን በኃጢአት ገንዞ ስጋዬ ነፍሴን ጎተተ።

ኧር አንድ በይኝ እመብርሃን ወለላይቱ ተማለጂኝ፤
ጨርሶ ዓለም ሳይነጥቀኝ ከወደኩበት አንሺኝ።

ማለዳ ኪዳን አድርሼ ቅዳሴ ጸሎት ጨርሼ፤
ከቤተክርስቲያን ወጥቼ ወደ ስጋ ገቢያ ተመልሼ፤
በኃጢአት ባህር ስዋኝ የግፍ ዳንኪራ ስረግጥ እውላለሁ፤
የልጅነት ፀጋዬን አውጥቼ ብኩርናዬን እሸጣለሁ።
እዚህ መልአክ መስዬ ላዬ በቅድስና በርቶ፤
ውጪ ከክፋት ከፍቼ ኃጢአት በጽድቄ ተተክቶ፤

በሀሜት የሰው ስጋ ስበላ በወንድሜ ሸር ስሸርብ፤
ስዋሽ ስቀጥፍ ውዬ ስሰርቅ ሳሽሟጥጥ ስሳደብ፤
ነጠላ ስለብስ ግን ወደ ቤተ እግዚአብሔር ስገባ፤
ሰዓሊለነ ቅድስት ስል ያለ ንስሐ እንባ፤
የመውደቂያዬ ጉድጓድ ጥልቀቱ ወሰን ዳርቻ የለውም፤
እዝነ ህሊናዬ ለዓለም እንጂ ለጽድቅ ቦታ የለውም፤

መሃረነ ክርስቶስ እንዳልል ተዘከረነ ፈጣሪዬ፤
ኃጢአት በደሌ አፈነኝ በሀፍረት ነደደ ህሊናዬ፤
ምን ብዬ ልጥራው ጌታዬን ተዘከረነ ብዬ።
ስለእኔ መገረፉን የመስቀሉን ፍቅር አቃልዬ፤
እንዴት ማረኝ ልበለው ስለ ስጋ ጣዕም ተቃጥዬ።

ምን ብዬ ልጥራው ጌታዬን?

ዓይኔን ወደ ፀፍፀፈ ሰማይ ወደ ሥላሴ መንበር፤
አንስቼ ማየት አቃተኝ ማረኝ ብዬ ለመናገር።
ለሰው ጻድቅ መስዬ የኃጢአት ጎተራ ሆኛለሁ፤
እንዴት አባቴ ቀና ብዬ መንበረ ጸባኦትን አያለሁ።
እባክሽን እናቴ ወለላይቱ ተማለጂኝ፤
እንደቃና ዘገሊላ ባዶ ማድጋዬን ሙዪልኝ።
ከፊቱ እንዳላፍር ከአማኑኤል ጋር አስታርቂኝ፤
ለተጠማ ውሻ እንዳዘንሽ ለመጻተኛው እዘኚልኝ።

አንቺ የትሁታን ትሁት ርህሪይተ ልብ እናቴ፤
ከልጅሽ ከኢየሱስ አማልጂኝ እዘኚ ለእኔም እመቤቴ።
አንቺ ውዳሴሽ የነፍስ ስንቅ ስምሽ ከማር የጣፈጠ፤
በላኤሰብዕ በእፍኝ ውሃ በምልጃሽ ከሞት ያመለጠ።

አንቺ መላእክት የሚጎበኙሽ የካህናት አለቆች ምስጋናቸው፤
በመወሰን የማይወሰን እሳተ መለኮትን የቻልሽው።
አንቺ ከገነት በተሰደደ ጊዜ ለአዳም ተስፋ የሆንሺው፤
ዛሬም ለእኔም ተስፋ ሁኚኝ ለነፍሴ ስለነፍሴ ተዋሺው።

እንጂ እኔማ አልቻልኩም የልቤ ንጽህና ጠፍቷል፤
ለጸሎት እንኳን ስቆም ልቤ ለሁለት ተከፍሏል፡፡

ኧረ አልሆንልኝም አለ መንፈሴ አልገዛም አለ፡፡
የጭንቅ አማላጂቱ አንድ ብትዪኝ ምን አለ?
እምቢ አለኝ ፆም ጸሎት እምቢኝ አለኝ ንስሐ፤
ስጋ መንፈሴ ኮብልሎ እየዋኘ ከዓለም ውሃ።

የልቤን መወላወል የነፍሴን ድካም አበርቺ፤
በአማላጅነትሽ ስር ነኝ እና ከልጅሽ አስታርቂኝ አንቺ።
ለሰው ዓይን ባይገለጥም ሰውሬ የሰራሁት ኃጢአት፤
አምላክን አሳዝኖታል የምኖርበት ሕይወት፤
ይኸው የምናገረው አይሰምር የወረወረኩት አይመታም፤
ስጋዬ አልተቀደሰ ገበታዬ በረከት የለውም፤
ዕውቀት ምርምር አይዘልቀኝም ህሊናዬ ፍሬ አይቋጥር፤
ዝርው ሆኖብኝ ቀርቶ የነፍስ የስጋዬ ምስጢር።

ይኸው የማወራው ለሰው አይጥም ፍቅር ከእኔ ቤት ርቋል፤
መቆም መቀመጤ አያምርም ሰው በስራዬ ይማረራል፤

የኃጢአት ምንዳዬ ይኸው የኃጢአት ደሞዜ ይኸው ስቃዬ ውስጤን በልቶታል፤
ለአንድነት የተናገርኩት ዛሬም ጉባኤ ይበትናል።

እና አዛኝቱ ታረቂኝ ከልጅሽ ከአማኑኤል አማልጂኝ፤
ከሰው የሸሸግኩት ኃጢአት ጨርሶ በልቶ ሳይውጠኝ።
የበላኤሰብዕ እመቤት እባክሽን ተማለጂኝ፤
አንቺ ሕይወቴን ዳብሺው ነፍሴ ዕረፍት እንድታገኝ።

ኧረ አልሆንልኝም አለ መንፈሴ አልገዛም አለ፤
የጭንቅ አማላጅቱ አንድ ብትዪኝ ምን አለ?

መልካም ቀን
እመቤታችን በአንቺ ምልጃ
@ney_ney_emye_maryam
#እመቤታችን_በአንቺ_ምልጃ (በማየ ቃና)

እመቤታችን በአንቺ ምልጃ (2)
ድንግል ማርያም በአንቺ ምልጃ (2)
መድኃኔዓለም ተአምር ሠራ በማየ ቃና(2)

ለጌታችን ተአምር >>> በማየ ቃና
ተመርጣ ታድላ >>> በማየ ቃና
መጀመሪያ ኾነች >>> በማየ ቃና
ቃና ዘገሊላ >>> በማየ ቃና

ቃናን ሊያደርጋት የተአምሩ ቀዳሚ ስፍራ
የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ

አዝ ---------------

ታውቋት ስላለችው >>> በማየ ቃና
ወይንኬ አልቦሙ >>> በማየ ቃና
ውኃ ወይን ሲሆን >>> በማየ ቃና
ኹሉ ዓዩ ሰሙ >>> በማየ ቃና

ቃናን ሊያደርጋት የተአምሩ ቀዳሚ ስፍራ
የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ

አዝ -------------

አሳላፊዎቹ >>> በማየ ቃና
ግራ ቢገባቸው >>> በማየ ቃና
የድንግል ማርያም ልጅ >>> በማየ ቃና
ከጭንቅ አወጣቸው >>> በማየ ቃና

ቃናን ሊያደርጋት የተአምሩ ቀዳሚ ስፍራ
የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ

አዝ --------------

እኛም እናምናለን >>> በማየ ቃና
በርሷ ትንብልና >>> በማየ ቃና
ስለ ቃልኪዳኗ >>> በማየ ቃና
ሁሉ እንደሚቀና >>> በማየ ቃና

ቃናን ሊያደርጋት የተአምሩ ቀዳሚ ስፍራ
የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ


መዝሙር: ቀሲስ እስክንድር ወ/ማርያም

Guys ሰሞኑን ለማግባት ያሰባቹት አልያም ሚንዜ የሆናቹ ካላቹ እቺን መዝሙር ሸምድዷት ትጠቅማቹሀለች😂😂😂
መልካም ምሽት
ሰላም👋 እንዴት አመሻቹህ

ውድ የዚህ ቻናል ብተሰቦች የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችን የመዝሙር lyrics የተለያዩ የኪነ ጥበብ ስራዎችን በዚ ቻናል በየጊዜው post በማድረግ ሌሎችን ማስተማር የምትፈልጉ ካላችሁ admin ይሰጣቹሀል ከዚህ በታች ባለው username አናግሩኝ
👇👇👇👇👇
@abrex_1
አረገ በክብር
የሰማያት ጌታ ፥ አለምን የሰራ
ጨለማን አርቆ ፥ ብርሀንን ያበራ
ቀድሞ በትንሳኤው ፥ ታይቶ እንደነበረ
እነሆ በሞገስ ፥ በስብሀት አረገ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ተምሳሌት ሊሆነን ፥ መንግስቱን ሊያወርሰን
ስፍራን አዘጋጅቶ ፥ ወደርሱ ሊወስደን
አረገ በክብር ፥ ሀያል ንጉስ ጌታ
ይገባል ምስጋና ፥ በሆታ በእልልታ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የማዳኑን ስራ ፥ ለእኛ እንደገለጠ
በፍርዱ ዘፋን ላይ ፥   በላይ ተቀመጠ
ወደ ሰማይ ወጣ ፥ ከሰማይ የመጣው
በአባቱ ቀኝ ሆኖ ፥ አለሙን ሊገዛው
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
እንደ በፊት ላይሞት ፥ ላይታይ ተገርፎ
ፍፁም በሚያስፈራ ፥ ግርማን ተጎናፅፎ
እልፉን መላዕክቱን ፥ ዙሪያው በመሰብሰብ
ለመምጣት ዳግመኛ ፥ ያ ጊዜ ሲቃረብ
አረገ በክብር ፥ ሀያል ንጉስ ጌታ
ይገባል ምሰጋና ፥ በሆታ በእልልታ

ብሩክ ተፈራ
የእግዚአብሔር ጥበቃ !

ትላንትና ማታ ቤተክርስትያን ቁጭ ብለን አባትና ልጅ አጠገባችን መጥተዉ ገና ቁጭ እንዳሉ ልጅ አባቷ እቅፍ ዉስጥ ሆና “አባዬ ወክ እንዉጣ” እያለች ታስቸግራለች

አባት ማስቸገሯን መቀጠሏ ስለረበሸዉ እዛዉ አካባቢ እንድትንቀሳቀስ ይለቃታል ልጅ ገና ከመለቀቋ ፊት ለፊቷ ወዳገኘችው መንገድ ሩጫዋን ቀጠለች

ይሄንን ያየ አባት ልጁ ሳታየዉ ከኃላዋ ይከተላት ጀመረ እንዳትወድቅበት ሊይዛት ፣ እንዳትጠፋ ሊጠብቃት ፣ ፍላጐቷን ሳይነፍጋት እንድትራመድ ፈቅዶ እያደረግኩልሽ ነዉ ሳይል በሚችለዉ ሁሉ አለላት

በጣም ርቃ ባይደርስባት እንኳን ፊት ለፊቷ ያሉትን ሰዎች ያዙልኝ ይላል እንጂ ተስፋ ቆርጦ አይተዋትም

ታድያ የፈጠረን ለእኛ ሲል ራሱን መስዋዕት ያደረገልን የሰማዩ አባታችን እማ እንዴት እየጠበቀን ይሆን ?

እንኳን አደረሳችሁ !

ስላልተዉከን ተመስገን 🙏
ያ_ውሻ ...


ሰዎች ያባረሩት
ከመንደር ያስወጡት የሌለው መድረሻ
አቻውን ፍለጋ ሚንከራተት ዘውትር
በጫካ በጥሻ ....
የጭንቅ አማላጇ
ምህረት ተጠምቶ ጫማሽን ሚናፍቅ
እኔ ነኝ ያ ውሻ .....
:
መቼ ትመጫለሽ
መች ታልፍያለሽ በዚያ በተጣልኩበት በር
መባዘን መድከሜ ፊትሽን አይቼ
መቼ ነው የሚቀር  ???
ረዘመ ቀኑ ....
መላው ጠፋ ሀሳቤ አላልቅ አለኝ ሌቱ
ጉልበቴ ሲደክም .....
ወዜ ሲንጠፈጠፍ በረታ እንግልቱ
ከወርቁ ጫማሽ ላይ
ውሃ ምታጠጭኝ
መች ነው አዛኝቱ  ?

መከረኛው ልጅሽ ጥቂት ቅድስና
ወይ ምግባር የሌለኝ
ባውቅም እንደ ግብሬ
ጫማሽን ልነካ አቅም እንደሌለኝ
አምናለሁ ስጠራሽ አልፈሽኝ አትሄጂም
አትጨክኚብኝም
ለውሻ ሚራራ እንስፍስፍ አንጀትሽ
ጥርኝ አይነሳኝም !
ግን ደግሞ ከብዶኛል
ግን ደግሞ ጠምቶኛል
ውሃ ልታጠጪኝ መቼ ትመጫለሽ
ያ ጫማሽ ናፍቆኛል 😔
የሰጠኸኝ ሴት
@Mekre_Abew_Orthodox

እግዚአብሔር አዳምን "አትብላ ካልሁህ ዛፍ በላህን?" ብሎ ጠየቀው። አዳምም:- ከእኔ ጋር እንድትሆን የሠጠኸኝ ሴት ከዛፉ ሠጠችኝና በላሁ አለ።

የሰጠኸኝ ሴት! በጣም ይገርማል። ሚስቴ አላለም። አዳምና ሔዋን የተገናኙ ቀን አዳም ያለውን አስታውሱ "ይህች አጥንት ከአጥንቴ ይህች ሥጋ ከሥጋዬ" ብሎአት ነበር:: ምንም እንክዋን አዳም ወላጆች ባይኖሩትም ሰው እናትና አባቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ብሎም ነበር። ራቁታቸውን ቢሆኑም አይተፋፈሩም ነበር::

አሁን በራቁቱ ብቻ ሳይሆን በሔዋንም አፈረባት:: እናትና አባቱን ይተዋል እንዳላለ ሔዋንን ራስዋን ተዋት። ከሚስቱ ጋር መተባበር ቀርቶ ክስ ጀመረ።

አካሌ አጥንቴ ሥጋዬ ማለቱ ቀረና የሠጠኸኝ ሴት አለ:: የጫጉላው ጊዜ አለፈና ከሚስትነትዋ ሴትነትዋ ብቻ ታየው።

በጋብቻ ብቻ አይደለም እግዚአብሔር የሠጠንን ነገር ሁሉ ቀድመን የራሳችን እናደርጋለን ነገሮች ሲበላሹ ግን ባለቤትነቱን ወደ እርሱ እንመልሰዋለን::

የሠጠኸኝ ሥራ
የሠጠኸኝ ወላጆች
የሠጠኸኝ ሰፈር
የሠጠኸኝ ሀገር
የሠጠኸኝ መሪ
የሠጠኸኝ ጉዋደኞች
የሠጠኸኝ ደካማ ሥጋ
የሠጠኸኝ ዓይን

ትናንት ሲሠጠን ዘምረን የተቀበልነውን ሥጦታ ዛሬ ለምሬት እንጠቅሰዋለን። የሠጠኸኝ የሠጠኸኝ .... ሠጠኝና በላሁ ብለን ቀርጥፈን ለበላነው ዕፀ በለስ ፈጣሪን እንከስሰዋለን::

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ የግዮን ወንዝ
Audio
Waadaa Araaraa Maryaam
@ORTHO_mezmure

Waadaa Araaraa Maryaam Waadaa Araaraa*2
Nuuf Kennamtee Waaqayyoo irraa *2

Waaqayyo Abbaan kan filatamtee
Afuura Qulqulluun at kan guutamtee
Qulqulleetiidhaa waadaa fayyinaa
Yaa hadha waaqaa nut si faarsinaa

Fannoo jalattii kan nuuf kennamtee
Yohannisiif kan nuuf laatamtee
Haadha hundaafuu taatee argamtee
Dhaloota maraaaf kennaa kenamtee

Mana cidhaatti qaanaa galilaatti
Rakkina dokimaas durbeen kan hubattee
Wayiniin dumachuusaa laalteetoo diinqasaa
Ilmasheetti himtee guuteef wayinii isaa

Mirga ilmakee at kan dhaabatuu
Waa'ee cubbuu keenyaaf at kan kadhattuu
Rakina namaa daftee hubattaa
Araarsuummaa keen dhifama kenisifttaa

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
የዛሬው ዉሎ አንዴት ነበር?

በሰላም እደሩልን የያዕቆብ ሌሊት ያድርግልን አብሮነታችሁን
🥰👍 ግለፁልን
እወዳችኋለሁ
የተሻለ ነገር 
ዘማሪት መስከረም ወልዴ|@yemezmurgetemoche|
የተሻለ ነገር
@ORTHO_mezmure

የተሻለ ነገር አስበህልኝ ነው
ፈተናው የበዛው
ነገ መልካሙን ቀን አያለሁ
በዚህም አምናለሁ

  ሰው ነኝ መቼም እቸኩላለሁ
  የሀሳቤን ቶሎ እሻለሁ
   አዳዴማ በቃ እረስቶኛል
   እላለሁኝ እኔን ትቶኛል
        አተ ግን ስጦታህ ብዙ ነው
        ታደርግልኛለህ በጊዜው
        አንተኮ አትፈልግም ውድቀቴን
        ሁል ጊዜ በጭንቀት ማንባቴን

አንዱን ቺግር ሳልሻገረው
ይደረባል ገዝፎ ሌላኛው
የሕይወትን ውጣ ውረድ
አይቻለሁ ስንቱን መንገድ
        ጨለማው ቢረዝም ሌሊቱ
        አይኔ አይቀርም ብርሃን ማየቱ
        እሩቅ የመሰለው ይቀርባል
        ሰላም ወደ ቤቴ ይገባል

ፈተናዬ ቢበዛብኝም
የሀዘኔ ማብቂያው ቢርቅ
አምላክ ባንተ ታሪክ ይሆናል
የደስታ ቀን ለኔም ይመጣል
      አንተ አትሳሳትም በስራህ
      ፍፁምና መልካም አባት ነህ
      እስከሚሆን ድረስ ተራዬ
      እጠብቅሃለሁ ጌታዬ

አለፈኮ ዘመኔ እያልኩኝ
በማጉረምረም ይሄው አለሁኝ
ፅናት ጎሎት ልቤ ቢያማርም
ያሰብክልኝ ያልከው አይቀርም
      አንተ ግን ስጦታህ ብዙ ነው
      ታደርግልኛለህ በጊዜው
      አንተኮ አትፈልግም ውድቀቴን
      ሁል ጊዜ በጭንቀት ማንባቴን

ዘማሪት መስከረም ወልዴ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ጠፍቼ ሳለው...
  @ort_poem   @ort_poem
°
°
በለመለመው መስክ ላይ
እኛ በጎቹ ፥ ነበርን አንድ-ላይ
ስንግጥ ባንድ ላይ
ስንጠጣ ባንድ ላይ
የማይነጥፈው ሳለ ፥ ሳለ ተንዠርግጎ
ለወዲያ ማዶ ፥ አንገቴ አስግጎ
አረሙ ናፍቆኝ ፥ ካንተ አመለጥኩኝ።
°
°
አረሙ ናፍቆኝ
መግደሉ ናፍቆኝ
ዝሙቱ ናፍቆኝ
ስርቆቱ ናፍቆኝ
ይኸው ጠገብኩኝ ፥ ካይነት ካይነቱ
ጣዕሙ አልሆነኝ ፥ እንደ ትላንቱ።
°
°
ጣዕሙ አልሆነኝ
አንገዳገደኝ
እንዴት ልመለስ...
አስሬ እያነሳ ፥ አስሬ እየጣለኝ
ወደ በጎችህ...
የማት[ቀላቅለኝ] ፥ እየመሰለኝ
ከደጅህ  እመለሳለሁ።
በኩነኔ  አፍሬያለሁ።
°
°
ከደጅህ እመለሳለሁ።
በምን አይኔ አይሃለሁ።
ውቅያኖስ ያህል ፥ ሀጥያት ነበረኝ
ባንዲት ዕንባዬ ፥ ሞገዱ ሲጠራኝ
ወደ ኩሬ ስትቀይረኝ...
አቤት ማለት ፥ አፌ አስፈራኝ።
°
°
ወደ ኩሬ ስትቀይረኝ
መጣኽና አጠለልከኝ።
አንተ  ጠባቂዬ
አንተ  ከለላዬ
አንተ  እረኛዬ
አቅፈኸ ነው ፥ የሳምከኝ
ከበጎችህ ፥ የ--ቀላቀል--ከኝ።

✍️@Diriba_16
Like 👍 አድርጉ ቤተሰብ 👍
1000046143
<unknown>
ይህ ግጥም ብዙ Like ካገኘ በድምፅ እና በፅሑፍ እንቀጥላለን

ኪዳነ ምህረት
@ort_poem

ያከበረሽ ሊከብር፥ኪዳን አለሽና፤
አይቆምም ለስምሽ፥እልልታ ምስጋና።
የጠሩሽ ቢበዙ፥አንቺ ባርከሻቸው፤
የወደዱሽ ሁሉ፥ቀና መንገዳቸው።
   
ልጆችሽ ስለሆን፥እናቴ እንላለን፤
እስከ ዘላአለም፥ገና እንወድሻለን።
ከወዴት ይገኛል፥እንዳንቺ ያለ እናት፤
ዘወትር እንላለን፥ኪዳነምህረት።
    
ከአምላክ መታረቅ፥የምህረት ኪዳን ነሽ፤
እንኳን ለወደደሽ፥ለጠላሽ እናትነሽ።
ኪዳነምህረት፥ኪዳንኪ ኮነ፤
በልጅሽ ቤዛነት፥ፍጥረት ሁሉ ዳነ።

ወስብሀት ለእግዚአብሄር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር ይቆየን
        
         

ግጥሙን ከወደዳችሁት ላይክ እና ሼር እንዳይረሳ🙏
ከመፅሐፍ ቅዱስ የቅዱሳን መንፈሳዊ ታሪኮችን በYoutubeቻናላችን ጀምረናል
SUBSCRIBE SHARE እና LIKE
በማድረግ አበረታቱን🙏


1, የታላቁ ንጉስ ዳዊት  ታሪክ
               👇👇👇
https://youtu.be/mX9dYS0NGis?si=Rnz7MY8a1kPZ1EtK

2, የነብዩ ዳንኤል ታሪክ
          👇👇👇
https://youtu.be/nuklogb2uw8?si=1gV2W8JutcN3Q4z1

3, የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ታሪክ
                  👇👇👇
https://youtu.be/CPJ_gMQEoIM?si=F84PWERsb27ZZXYg

4,  የአብርሐም ሙሉ ታሪክ
             👇👇👇
https://youtu.be/yK1N81Xrclg?si=QXHNvk0tMXInjzf8

5, የበለዓም ታሪክ
         👇👇👇
https://youtu.be/0tHmJPHCzp4?si=kOYo58_kSrcAelYK

6,  ከባህር ዳርቻ
          👇👇👇
https://youtu.be/WIk3jWI2qpU?si=Fu50kEG_Xa0XDsQ8
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2025/06/27 05:51:48
Back to Top
HTML Embed Code: