Telegram Web Link
የሰጠኸኝ ሴት
@Mekre_Abew_Orthodox

እግዚአብሔር አዳምን "አትብላ ካልሁህ ዛፍ በላህን?" ብሎ ጠየቀው። አዳምም:- ከእኔ ጋር እንድትሆን የሠጠኸኝ ሴት ከዛፉ ሠጠችኝና በላሁ አለ።

የሰጠኸኝ ሴት! በጣም ይገርማል። ሚስቴ አላለም። አዳምና ሔዋን የተገናኙ ቀን አዳም ያለውን አስታውሱ "ይህች አጥንት ከአጥንቴ ይህች ሥጋ ከሥጋዬ" ብሎአት ነበር:: ምንም እንክዋን አዳም ወላጆች ባይኖሩትም ሰው እናትና አባቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ብሎም ነበር። ራቁታቸውን ቢሆኑም አይተፋፈሩም ነበር::

አሁን በራቁቱ ብቻ ሳይሆን በሔዋንም አፈረባት:: እናትና አባቱን ይተዋል እንዳላለ ሔዋንን ራስዋን ተዋት። ከሚስቱ ጋር መተባበር ቀርቶ ክስ ጀመረ።

አካሌ አጥንቴ ሥጋዬ ማለቱ ቀረና የሠጠኸኝ ሴት አለ:: የጫጉላው ጊዜ አለፈና ከሚስትነትዋ ሴትነትዋ ብቻ ታየው።

በጋብቻ ብቻ አይደለም እግዚአብሔር የሠጠንን ነገር ሁሉ ቀድመን የራሳችን እናደርጋለን ነገሮች ሲበላሹ ግን ባለቤትነቱን ወደ እርሱ እንመልሰዋለን::

የሠጠኸኝ ሥራ
የሠጠኸኝ ወላጆች
የሠጠኸኝ ሰፈር
የሠጠኸኝ ሀገር
የሠጠኸኝ መሪ
የሠጠኸኝ ጉዋደኞች
የሠጠኸኝ ደካማ ሥጋ
የሠጠኸኝ ዓይን

ትናንት ሲሠጠን ዘምረን የተቀበልነውን ሥጦታ ዛሬ ለምሬት እንጠቅሰዋለን። የሠጠኸኝ የሠጠኸኝ .... ሠጠኝና በላሁ ብለን ቀርጥፈን ለበላነው ዕፀ በለስ ፈጣሪን እንከስሰዋለን::

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ የግዮን ወንዝ
🥰135👍5
Audio
Waadaa Araaraa Maryaam
@ORTHO_mezmure

Waadaa Araaraa Maryaam Waadaa Araaraa*2
Nuuf Kennamtee Waaqayyoo irraa *2

Waaqayyo Abbaan kan filatamtee
Afuura Qulqulluun at kan guutamtee
Qulqulleetiidhaa waadaa fayyinaa
Yaa hadha waaqaa nut si faarsinaa

Fannoo jalattii kan nuuf kennamtee
Yohannisiif kan nuuf laatamtee
Haadha hundaafuu taatee argamtee
Dhaloota maraaaf kennaa kenamtee

Mana cidhaatti qaanaa galilaatti
Rakkina dokimaas durbeen kan hubattee
Wayiniin dumachuusaa laalteetoo diinqasaa
Ilmasheetti himtee guuteef wayinii isaa

Mirga ilmakee at kan dhaabatuu
Waa'ee cubbuu keenyaaf at kan kadhattuu
Rakina namaa daftee hubattaa
Araarsuummaa keen dhifama kenisifttaa

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
7👍3
የዛሬው ዉሎ አንዴት ነበር?

በሰላም እደሩልን የያዕቆብ ሌሊት ያድርግልን አብሮነታችሁን
🥰👍 ግለፁልን
እወዳችኋለሁ
🥰1413👍2
የተሻለ ነገር 
ዘማሪት መስከረም ወልዴ|@yemezmurgetemoche|
የተሻለ ነገር
@ORTHO_mezmure

የተሻለ ነገር አስበህልኝ ነው
ፈተናው የበዛው
ነገ መልካሙን ቀን አያለሁ
በዚህም አምናለሁ

  ሰው ነኝ መቼም እቸኩላለሁ
  የሀሳቤን ቶሎ እሻለሁ
   አዳዴማ በቃ እረስቶኛል
   እላለሁኝ እኔን ትቶኛል
        አተ ግን ስጦታህ ብዙ ነው
        ታደርግልኛለህ በጊዜው
        አንተኮ አትፈልግም ውድቀቴን
        ሁል ጊዜ በጭንቀት ማንባቴን

አንዱን ቺግር ሳልሻገረው
ይደረባል ገዝፎ ሌላኛው
የሕይወትን ውጣ ውረድ
አይቻለሁ ስንቱን መንገድ
        ጨለማው ቢረዝም ሌሊቱ
        አይኔ አይቀርም ብርሃን ማየቱ
        እሩቅ የመሰለው ይቀርባል
        ሰላም ወደ ቤቴ ይገባል

ፈተናዬ ቢበዛብኝም
የሀዘኔ ማብቂያው ቢርቅ
አምላክ ባንተ ታሪክ ይሆናል
የደስታ ቀን ለኔም ይመጣል
      አንተ አትሳሳትም በስራህ
      ፍፁምና መልካም አባት ነህ
      እስከሚሆን ድረስ ተራዬ
      እጠብቅሃለሁ ጌታዬ

አለፈኮ ዘመኔ እያልኩኝ
በማጉረምረም ይሄው አለሁኝ
ፅናት ጎሎት ልቤ ቢያማርም
ያሰብክልኝ ያልከው አይቀርም
      አንተ ግን ስጦታህ ብዙ ነው
      ታደርግልኛለህ በጊዜው
      አንተኮ አትፈልግም ውድቀቴን
      ሁል ጊዜ በጭንቀት ማንባቴን

ዘማሪት መስከረም ወልዴ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
20👍4👏3
ጠፍቼ ሳለው...
  @ort_poem   @ort_poem
°
°
በለመለመው መስክ ላይ
እኛ በጎቹ ፥ ነበርን አንድ-ላይ
ስንግጥ ባንድ ላይ
ስንጠጣ ባንድ ላይ
የማይነጥፈው ሳለ ፥ ሳለ ተንዠርግጎ
ለወዲያ ማዶ ፥ አንገቴ አስግጎ
አረሙ ናፍቆኝ ፥ ካንተ አመለጥኩኝ።
°
°
አረሙ ናፍቆኝ
መግደሉ ናፍቆኝ
ዝሙቱ ናፍቆኝ
ስርቆቱ ናፍቆኝ
ይኸው ጠገብኩኝ ፥ ካይነት ካይነቱ
ጣዕሙ አልሆነኝ ፥ እንደ ትላንቱ።
°
°
ጣዕሙ አልሆነኝ
አንገዳገደኝ
እንዴት ልመለስ...
አስሬ እያነሳ ፥ አስሬ እየጣለኝ
ወደ በጎችህ...
የማት[ቀላቅለኝ] ፥ እየመሰለኝ
ከደጅህ  እመለሳለሁ።
በኩነኔ  አፍሬያለሁ።
°
°
ከደጅህ እመለሳለሁ።
በምን አይኔ አይሃለሁ።
ውቅያኖስ ያህል ፥ ሀጥያት ነበረኝ
ባንዲት ዕንባዬ ፥ ሞገዱ ሲጠራኝ
ወደ ኩሬ ስትቀይረኝ...
አቤት ማለት ፥ አፌ አስፈራኝ።
°
°
ወደ ኩሬ ስትቀይረኝ
መጣኽና አጠለልከኝ።
አንተ  ጠባቂዬ
አንተ  ከለላዬ
አንተ  እረኛዬ
አቅፈኸ ነው ፥ የሳምከኝ
ከበጎችህ ፥ የ--ቀላቀል--ከኝ።

✍️@Diriba_16
Like 👍 አድርጉ ቤተሰብ 👍
25👍8
1000046143
<unknown>
ይህ ግጥም ብዙ Like ካገኘ በድምፅ እና በፅሑፍ እንቀጥላለን

ኪዳነ ምህረት
@ort_poem

ያከበረሽ ሊከብር፥ኪዳን አለሽና፤
አይቆምም ለስምሽ፥እልልታ ምስጋና።
የጠሩሽ ቢበዙ፥አንቺ ባርከሻቸው፤
የወደዱሽ ሁሉ፥ቀና መንገዳቸው።
   
ልጆችሽ ስለሆን፥እናቴ እንላለን፤
እስከ ዘላአለም፥ገና እንወድሻለን።
ከወዴት ይገኛል፥እንዳንቺ ያለ እናት፤
ዘወትር እንላለን፥ኪዳነምህረት።
    
ከአምላክ መታረቅ፥የምህረት ኪዳን ነሽ፤
እንኳን ለወደደሽ፥ለጠላሽ እናትነሽ።
ኪዳነምህረት፥ኪዳንኪ ኮነ፤
በልጅሽ ቤዛነት፥ፍጥረት ሁሉ ዳነ።

ወስብሀት ለእግዚአብሄር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር ይቆየን
        
         

ግጥሙን ከወደዳችሁት ላይክ እና ሼር እንዳይረሳ🙏
51👍28🥰6👏4
ከመፅሐፍ ቅዱስ የቅዱሳን መንፈሳዊ ታሪኮችን በYoutubeቻናላችን ጀምረናል
SUBSCRIBE SHARE እና LIKE
በማድረግ አበረታቱን🙏


1, የታላቁ ንጉስ ዳዊት  ታሪክ
               👇👇👇
https://youtu.be/mX9dYS0NGis?si=Rnz7MY8a1kPZ1EtK

2, የነብዩ ዳንኤል ታሪክ
          👇👇👇
https://youtu.be/nuklogb2uw8?si=1gV2W8JutcN3Q4z1

3, የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ታሪክ
                  👇👇👇
https://youtu.be/CPJ_gMQEoIM?si=F84PWERsb27ZZXYg

4,  የአብርሐም ሙሉ ታሪክ
             👇👇👇
https://youtu.be/yK1N81Xrclg?si=QXHNvk0tMXInjzf8

5, የበለዓም ታሪክ
         👇👇👇
https://youtu.be/0tHmJPHCzp4?si=kOYo58_kSrcAelYK

6,  ከባህር ዳርቻ
          👇👇👇
https://youtu.be/WIk3jWI2qpU?si=Fu50kEG_Xa0XDsQ8
16
በንፁህ ደሙ
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
በንፁህ ደሙ
@ORTHO_mezmure

በንፁህ ደሙ ያዳነን
ከወደቅንበት ያነሳን/2/
ብዙ ነዉ የእርሱ ዉለታ
እንዘምራለን ለጌታ
አዝ

ቀና ብለናል በክብር
አንገቱን ደፍቶ በፍቅር
ስለኛ ብዙ ሆነልን
የብርሃን አክሊል ደፋልን
የዓለም መድሃኒት ጌታ ነዉ
ጠላታችንን ያሰረዉ/2/
አዝ

እርቃኑን ሆኖ ሸለመን
እየደከመ አቆመን
እርሱ በመስቀል ሲሞት
እኛ ተፃፍን በህይወት
የዓለም መድሃኒት ጌታ ነዉ
ጠላታችንን ያሰረዉ/2/
አዝ

እስከ ሺ ትዉልድ ይምራል
ፍቅር ነዉና ይራራል
አይዝልም የርሱ ትከሻ
መጨረሻ ነዉ መድረሻ
የዓለም መድሃኒት ጌታ ነዉ
ጠላታችንን ያሰረዉ/2/
አዝ

በደም ያጌጠ ልብስ አለዉ
ከአማልክት ማንም አይመስለዉ
ትዉልዱ ማዳኑን ይስማ
ነግሷል በጽዮን ከተማ
የዓለም መድሃኒት ጌታ ነዉ
ጠላታችንን ያሰረዉ/2/

ዘማሪ ገብረአምላክ ደሳለኝ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
14👎3
1000046305
<unknown>
ይህ ግጥም ብዙ Like ካገኘ በድምፅ እና በፅሑፍ እንቀጥላለን

ችላ_አትበለኝ
.
@ort_poem @ort_poem

አስተምረኝ መታዘዝን
ታጋሽ አርገኝ አይቶ አላፊ፣
ለታናሽም ለታላቅም
ፅኑ አገልጋይ ልበ ሰፊ።
.
ልከተልህ በስተኋላህ
ልሸከመው ያንተን መስቀል፣
አንድም፡ ፍቅርህ እንዲገባኝ
አንድም፡ የሀጢያት ሸክሜ እንዲቀል።
.
ችላ አትበለኝ የኔ ጌታ
ደካማ ነኝ አቅም አልባ፣
ሁሌም ፊትህ ምበረከክ
ለምህረትህ የማነባ።

Like 👍 አድርጉ ቤተሰብ 👍
48🥰11👍1
ግንቦት ፳፯ /27/

@Mekre_Abew_Orthodox

በዚችም ዕለት የማርያና የማርታ ወንድም ጻድቅ አልዓዛር አረፈ። ይህንንም ጻድቅ ሰው በአራተኛ ቀን ከመቃብር ከአስነሣው በኋላ በዚሁ ሳምንት ውስጥ መድኃኒታችን መከራ ተቀብሎ ተሰቅሎ ሞተ። ከትንሣኤውም በኋላ አልዓዛር ከሐዋርያት ጋራ አንድ ሆነ።

አጽናኝ መንፈስ ቅዱስም በወረደ ጊዜ ከሐዋርያት ጋራ ጸጋውን ተቀበለ። ሐዋርያትም በቆጵሮስ አገር ላይ በአንብሮተ እድ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት። መንጋውንም በመልካም አጠባበቅ ጠበቀ። በሹመቱም አርባ ዓመት ኑሮ በሰላም በፍቅር አረፈ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
3👍1🥰1
1000046304
<unknown>
ይህ ግጥም ብዙ Like ካገኘ በድምፅ እና በፅሑፍ እንቀጥላለን

ነበርኩ_መች_ያድናል
@ort_poem @ort_poem

ሀጢያትን ስትሰራ አምላክን እረስተህ
ቅዱሱን ሰውነት በሀጢያት አርክሰህ
ትእዛዝን ሳትፈጽም መልካምን ሳትሰራ
ዘይት ሳታዘጋጅ መብራትህ ሳይበራ

በተጠራህ ጊዜ መላከሞት ሲመጣ
ለማያልፈው አለም ሲወጣልህ እጣ
ለሚዛን ስትቀርብ አገልጋይ ነበርኩኝ እያልክ መናገሩ
መዝሙር ዘምሬያለው ሄጃለው ከበሩ

ብሎ መከራከር ያኔ መች ይጠቅማል
ይዞ መገኘት ነው ነበርኩ መች ያድናል!!!


Like 👍 አድርጉ ቤተሰብ 👍
👍74🥰1716
ግንቦት ፳፰ /28/

@Mekre_Abew_Orthodox

በዚችም ዕለት የቅዱስ ኤጲፋንዮስ ሥጋ ወደ ቆጵሮስ ደረሰ። ይህም እንዲህ ነው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ወደ መንበረ ሢመቱ እንደማይደርስ ትንቢት እንደተናገረበት ወደ ቆጵሮስ ሳይደርስ በመርከብ ውስጥ ሳለ ግንቦት ዐሥራ ስድስት ቀን አረፈ።

በአረፈም ጊዜም በመርከብ ጭነው ወደ ቆጵሮስ ከተማ አደረሱት። ካህናቱና ሕዝቡ ሁሉ መጡ ከሳቸውም ጋር ወንጌሎች መስቀሎች መብራቶችና ማዕጠንቶችም ይዘው ነበር የሐዋርያት ጉባኤ ከታላቂቱ ቤተ ክርስቲያን እስኪያደርሱት በዝማሬና በማኅሌት በሚገቡት ጸሎቶች ሁሉ እያመሰገኑ ሥጋውን ተሸከሙ። ካህናቱም መቃብሩን በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ሊያዘጋጁ ወደዱ። ቀድሞ ስለ ክፉ ሥራቸው ቅዱስ ኤጲፋንዮስ አውግዞአቸው የነበሩ ሁለት ዲያቆናት ተቃወሟቸው።

ስለዚህም አርባ ቀን ተቀመጠ ነገር ግን ሽታው እንደ ሙታኖች ሽታ አልተለወጠም እንደ አንቀላፋ ሰው ሆነ እንጂ። ከዚህም በኋላ አንድ ደግ ዲያቆን ወደ ቅዱሱ ሥጋ ቀርቦ አባቴ ሆይ በእግዚአብሔር ዘንድ አንተ ባለሟልነት እንዳለህ እኔ አውቃለሁ። ብትፈቅድስ ክፉዎች ተቃዋሚዎችን ልታሸንፋቸው ትችላለህ አለ። የቅዱስ ኤጲፉንዮስንም እጅ ይዞ ምድሩን መታባት በዚያንም ጊዜ ሁለቱ ዲያቆናት በግምባራቸው ተደፉ። ለመሞትም ደረሱ ወደ ቤታቸውም ወስደዋቸው ሞቱ።

ቅዱስ ኤጲፋንዮስንም ካህናቱ በሚጣፍጡ ሽቱዎች ገነዙት። በከበሩ ልብሶችም ጠቅልለው ከከበረ ደንጊያ በተሠራ ሣጥን ውስጥ ጨምረው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቀበሩት። ቀድሞ በሕይወቱ ሳለ እንደሚሠራው ከሥጋው ድንቆች ተአምራት ተገለጡ ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑርለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
7
1000046993
<unknown>
ይህ ግጥም ብዙ Like ካገኘ በድምፅ እና በፅሑፍ እንቀጥላለን

ምስክር ነኝ አኔ
@ort_poem

ምስክር ነኝ አኔስ ሳለሁ በህይወቴ
ኦርቶዶክስ ነችና አንዲቷ እምነቴ
ከጥንት አባቶቼ የዘረስኳት ማንነቴ
ተዋህዶ ነችና የዘለዓለም ቤቴ

ሀጢያትን ሰርቼ ብዙ በድያለሁ
ትዕዛዙንም ጥሼ ሰውንም ንቄያለሁ
አንድ ተስፋ እንዳለኝ አሁን አውቄያለሁ

ስታመም ድኜበት ስቸገር አግኝቼ ሳዝንም ተደስቼ መጥቻለሁና ሁሉንም አግኝቼ
የጎደለው ሞልቷል ወደ አንቺ መጥቼ
ዛሬን መስክሬያለው ሁሉንም አይቼ

ነፅቻለሁና ንስሀ ገብቼ
ለስጋ ወደሙ ክብርም በቃሁኝ
ሰላም የሞላበት ህይወትን አየሁኝ
በተዋህዶ ዕምነቴ ክብር አገኘሁኝ።
     🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
Like 👍 አድርጉ ቤተሰብ 👍

✍️@Diriba_16
85👍16🥰7
ግንቦት ፳፱/29/

❤️@Mekre_Abew_Orthodox❤️

በዚችም ዕለት ከአንጾኪያ ገዳም አባ ስምዖን አረፈ። የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም ዮሐንስ የእናቱ ስም ማርታ ነው ስለ ርሱም ድንቆች ተአምራት ሆኑ። ይኸውም እናቱ ገና ሳትፀንሰው መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ እርሷ መጥቶ የዚህን የቅዱስ ስምዖንን መወለድ ነገራት ከእርሱም የሚሆነውን ገለጠላት።

ተወልዶም ሰባት ዓመት በሆነው ጊዜ በአንጾኪያ ወደአለ ገዳም ሔደ። ራሱንም ወደ ምንኵስና ቀንበር ውስጥ አስገብቶ ታላቅ ገድልን ተጋደለ። መላእክትም አባ ጳኵሚስን እንደ አስተማሩት በየሌሊቱ ሁሉ እየተገለጡለት የምንኵስናን ገድል አስተማሩት።

የማይጠፋ የምንኵስናንም የገድል አሠራር ገለጡለት። እርሱም አጽንቶ ሥጋ ከለበሱ ሁሉ አብዝቶ ተጋደለ መላእክትም ሁልጊዜ መንፈሳዊ ምግብ ያመጡለት ነበረና። ብዙ ከመጋደሉ የተነሣ ከደንጊያ ምሰሶ ላይ ወጥቶ በላይዋ ሰባት ዓመት ቆመ። ከዚህም ወደሌላ ተራራ ሒዶ በሠራው የደንጊያ በዓት ውስጥ እስከ ሃያ ዓመት ፍጻሜ ከእርሷ ሳይወጣ ሃያ ዓመት ኖረ።

ከዚህ በኋላም ደግሞ ከታላቅ ተራራ ራስ ላይ ወጥቶ በላዩ አርባ አምስት ዓመት ኖረ። መላው ዕድሜውም ሰማንያ ስምንት ዓመታት ነው። ይኸውም በአባቱ ቤት ሰባት በአንጾኪያ ገዳም ዘጠኝ ዓመት በምሰሶ ላይ ሰባት ዓመት በደንጊያ ውስጥ ሃያ ዓመት ደግሞ በተራራ ላይ ቁሞ የኖረበት አርባ አምስት ዓመት በጠቅላላ ሰማንያ ስምንት ነው።

ተአምራቱን ግን መቁጠር የሚችል የለም ከእርሳቸውም በገድሉ ተጽፎ አለ። ብዙ የሆኑ ድርሳናትንና ተግሣጽን ደረሰ እነርሱም ለሁሉ የሚጠቅሙ ናቸው። ይልቁንም ለመነኰሳት ከቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትም ብዙዎቹን ተረጐመ። ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
11👍2
Audio
AudioLab
🎤 Feben Nebiyu

👇👇👇👇👇👇
✍️@Diriba_16
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
     @ort_poem @ort_poem
     @ort_poem @ort_poem
     @ort_poem @ort_poem
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧

       ♡ ㅤ  ⎙ㅤ  ⌲        ✉️   
   ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
Like አይቆጥርም ኧረ ተጫኑት👍


           ለሌሎቹም ለመንፈሳዊ ግጥም አፍቃሪያን ይማሩ ዘንድ ቻናሉን Share በማድረግ እንዲቀላቀሉ አድርጓቸው።
👍255🥰5
የተሻለ ነገር መዝሙር በክራር
የተዘመረ ግቡና አዳምጡልኝ

👇👇👇
https://youtu.be/yIOg6qmdKtw?si=z_fiR5RhRgKGSQZ_
6
Audio
እርሱ ብቻ የማይሞተው ነው
@ORTHO_mezmure

እርሱ ብቻ የማይሞት ነው
በብርሃን የሚኖር ነው
በአባቱ ቀኝ አለ ነግሦ
አማኑኤል ክብርን ለብሶ(*2)
አዝ<><>
ትላንትናን ዛሬን ውጧል
ሁሉም ነገር ይለወጣል
ሳይደበዝዝ የሚያበራ
ሁሌም ጽኑ የእርሱ ስራ
አዝ<><>
የአይሁድ ትግል ያልነቀለው
ክፋታቸው ያልሸፈነው
የደም ሐውልት ምሰሷችን
በእርሱ ጸንቷል ከፍታችን
አዝ<><>
የዓለም ጀግኖች ተቀብረዋል
የበረቱ ተሰብረዋል
ገዳዩን ሞት የገደለ
እንደ ጌታ ወዴት አለ?
አዝ<><>
መቃብርን የቀበረ
ኃይለኛውን የሰበረ
ኢየሱስ ነው ጽኑ ጌታ
ማይሸነፍ ማይረታ
19👍4
​​​​ጾመ ሐዋርያት/የሰኔ ጾም

ጾመ ሐዋርያት ሐዋርያት በጽራሐ ጽዮን መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ወደ አገልግሎት ከመግባታቸውና ወደ ሀገረ ስብከታቸው ከመበተናቸው በፊት የጾሙት ጾም ነው፡፡ የጾሙበትም ምክንያት በማርቆስ ፪፥፳ እና በማቴወስ ፱፥፲፬ ላይ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን መሰረት በማድረግ ነው፡፡

ይኸውም የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው እኛና ፈሪሳዊያን ብዙ ጊዜ የምንጾመው ደቀመዛሙርትህ ግን የማይጾሙት ስለ ምንድን ነው? አሉት፡፡ ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፡-ሚዜወች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን ? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል ያን ጊዜ ይጾማሉ፡፡››ብሎ እንደመለሰላቸው፡፡

በዚህ ምሳሌያዊ አነጋገር ሙሽራ የተባለው ካባ በመደረብ ፈንታ ዕርቃኑን ሆኖ በአክሊል ፈንታ የእሾህ አክሊል ደፍቶ በሚዜወቹ ፈንታ በጠላት ተከቦ በመዝሙርና በደስታ ፈንታ በልቅሶና በዋይታ ታጂቦ በክብር ዙፋን መቀመጥ ፈንታ በመስቀል ተሰቅሎ በጭንካር ተወጥሮ በቀራንይዎ አደባባይ ስለ እኛ የተሞሸረው/የተሰቀለው/ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡

ሚዜዎቹ የተባሉት ደግሞ ምንም እንኳን በሰርጉ እለት ከአንዱ በቀር (ከወንጌላዊ ዮሐንስ/ ከጎኑ ባይገኙም ኋላ መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው በሕይወትም በሞትም ሙሽራውን/ኢየሱስ ክርስቶስን/ የመሰሉ ሐዋርያት ናቸው፡፡

ይወሰዳል መባሉም እርገቱን ለመናገር ሲሆን ከዚያ በኋላ ይጾማሉ መባላቸው ደግሞ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ለማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ኢየሱስ ሲያርግ መንፈስ ቅዱስ ይመጣልና፡፡ በዚህ ላይ ልብ ልንል የሚገባን ጉዳይ  ጾም በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበረ በሐዲስ ኪዳንም የቀጠለ ሥርዓት መሆኑን ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን የነበረ ስለመሆኑ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት እና አይሁድ ብዙ ጊዜ ይጾሙ እንደነበረ ተጽፏል፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት"እናንተና አይሀድ የጾማችሁት ባለማወቅ ወይም  በስህተት ስለሆነ ደቀ መዛሙርቴ አይጾሙም" አላለም፡፡  ነገር ግን ለጊዜው ከእኔ ጋር ናቸው ደስ ሊላቸው ይገባል፡፡ ከሄድኩ በኋላ ግን ይጾማሉ ብሏል፡፡ ይኸውም ጾም  ከአዳም ጀምሮ እስከ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እና ደቀ መዛሙርቱ  ከዚያም በክርስቶስ ታድሶና ተቀድሶ ለደቀ መዛሙርቱ የተሰጠ ከዚያም ለእኛ ለተከታይዮቻቸው የተላለፈ ሥርዓት መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ 

ለጊዜው ሐዋርያት ሊጾሙበት ያልቻሉበት ምክንት ሊቃውንት ሲያብራሩ ፡-አንደኛ ጾም ሐዘን ነውና ሐዘኑም ኃላፊነትን ከመሸከም ጋር ተያያዥነት ያለው ነውና፡፡ ምክናያቱም መጾም አላማው ንስሐ እንደመሆኑ እንደ ቅዱስ ዳዊት ለግል ኃጢያት አሊያም እንደነነዌ ሰዎች ስለሀገር ጥፋት የሚያለቅሱበት የሚያዝኑበት ሁኔታ አለው፡፡ ክርስቶስ ደግሞ በስጋው ወራት ከአምላክነቱና ከሁሉ አባትነቱ ባሻገር ለሐዋርይት እንደ ሥጋ አባትም ወንድምም በመሆን የእነርሱን ኃላፊነት ተሸክሞላቸዋልና እርሱ በአካለ ሥጋ በአጠገባቸው እስካለ ድረስ ማዘን አልተገባቸውም፡፡ 

በሁለተኛነት ደግሞ ጾም ኃላፊነት ነው፡፡ኃላፊነቱን ለመሸከም ደግሞ ኃይል የሚሆናቸው መንፈስ ቅዱስ ያስፈልጋቸው ነበርና መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ እንዲጾሙ ጊዜ ሰጣቸው፡፡  ሦስተኛው ምክነያት  አይሁድ ይጾሙት የነበረው በብሉይ ኪዳን ስርዓት ውስጥ ሆነው ነበር፡፡ ሐዋርያት ደግሞ የሐዲስ ኪዳን ልጆች ስለሆኑ መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው አሊያም አዲሱ ሰው በተባለው በክርስቶስ ደም ተጽናንተውና ሥጋውንና ደሙን ተቀብለው አዲሱን ሰው ለብሰው በአዲስ መንፈስና ኃይል በአዲስ ስርዓት መጾም ስለነበረባቸው በጊዜው አልጾሙም ነበር፡፡/ማቴ ፱፥፲፮-፲፯/

ይቀጥላል
24👍2🔥1🥰1
ብዙ ሳይጣጣር
እምብዛም ሳይለፋ
ከዓይን የራቀ
ከምናብ የሰፋ
ይህን ዓለም ሠራ
ያለ ጭንቀት ጥበት
ሆነለት “ሁን” ሲለው
እንዲሁ በዘበት

ሕዋውን በሙሉ
ግዑዙን ተፈጥሮ
በቃሉ ትዕዛዝ
እንዲህ አሳምሮ
ለድንጋዩ ራርቶ
የንብ መንጋ መርቶ
አበባን አፍክቶ
ወፊቱን አብልቶ

እኔ ትንሽ ነገር
ከሕይወት ቢጨንቀኝ
አደራህን ብለው
“እሺ ቆይ” እያለ
ይህን ሁሉ ዓመት
የሚያጠባብቀኝ
እንዴት ብከብደው ነው
ወይ እንዴት ቢንቀኝ ?
….

By henok bekele
22🥰4👍2
---

የአብስራ ሳሙኤል 
*・꙳・꙳・꙳・꙳・・*

እጠራሀለው 
በስምህ አቤት በለኝ ከሰማኀው
"ጠይቁ?" ብለህ አልነበር 
እጠይቃለሁ አንተ እንዳልከው 

ከፀሀይ ጀርባ  ምን አለ?
ከህይወት አድማስ ባሻገር 
ሞት የህይወት ፍጻሜ ነው? 
ወይስ ድልድይ የሚሻገር? 
አላዛር ያኔ ቢጠየቅ 
የሞተ ግዜ የት ነበር? 

ወዴት ነው 
የመኖር ማብቂያው? 
ወዴት ነው መጠናቀቂያው? 
ነፍሴን የማጽናናበት 
ምኞቴን የምዳኝበት 
ምን አለ ከጸሀይ ጀርባ? 
ወዴት ነው ነፍሴ የምትሸሸው? 

ይብቃህ እረፍ ተብዬ 
የስቃይ ቀኔ የሚያመሸው 
አውቃለሁ እንደ ነገርከኝ 
ብረዳም ከድርሳን ቅጽህ 
ማ? በለኝና ማን ልመን 
ብዙ ነው ስምና ገጽህ 

*"ጠይቁ?" ብለህ አልነበር・・・ራባይ* 
―☾―

አየሁኝ 
እውር አንበሣን 
አንካሳ ነብር ሲመራው 
እንዲህ ነው መንግስት የሚዘልቅ 
እንዲህ ነው ፍጡር የሚመራው 

ካልተማመነ 
መንገዱን በነብር አይን ተረድቶ 
መጠራጠር ይገላል 
አንዱን ከአንዱ አባልቶ 
ይኀው ነው የነፍሴ ጣሯ 
አታምነኝ ወይም አላምናት 
ማ? በለኝና ማን ልበል 
በየቱ ቃልህ ላባብላት 

ማመን ነው 
የተስፋ ምርኩዝ 
መከተል የአይኑ ብርሀን 
ወዴት ነው የመኖር ማብቂያው? 
ወዴት ይሆን የመራኀን? 
―✦―

እጠራሀለው 
በስም አቤት በለኝ  ከሰማኀው
ጠይቁ ብለህ አልነበር 
እጠይቃለሁ አንተ እንዳልኀው 

ከጸሀይ ጀርባ  ምን አለ?
ኦና'ነት ወይ ፍጻሜ 
የት ይሆን ጅምር መቋጫው? 
ስንት ይሆን የመኖር እድሜ? 
ወዴት ነው የመኖር ማብቂያው? 
ወዴት ነው መጠናቀቂያው? 

አውቃለሁ 
እንደ ነገርከኝ 
ብረዳም ከድርሳን ቅጽህ 
ማ? በለኝና ማን ልመን 
ብዙ ነው ስምና ገጽህ 
29🥰5
2025/10/24 10:56:08
Back to Top
HTML Embed Code: