መቼ ነው አንድ ቀን ??
===============
ስንጠጋው ሚሸሽ
ስንቀርበው ሚርቀን
ዕድሜያችንን ሁሉ
ስንኖር ሚናፍቀን
በተስፋ ጠቅልለው ይመጣል የሚሉን
መቼ ነው ' አንድ ቀን ' ??
===============
ስንጠጋው ሚሸሽ
ስንቀርበው ሚርቀን
ዕድሜያችንን ሁሉ
ስንኖር ሚናፍቀን
በተስፋ ጠቅልለው ይመጣል የሚሉን
መቼ ነው ' አንድ ቀን ' ??
👏7❤4👍3🔥1
ቤትሽ ግድግዳ ላይ
አስቱ✍️
ለእናታቹ 🥰
ቤትሽ ግድግዳ ላይ
ማርያም ልጇን አቅፋ ምትታየው ምስል
ለምን አንደሆነ እንጃ
ቁርጥ እራስሽን አንቺን ስትመስል
[እርግጥ ነው]
እርግጥ ነው ከአናትሽ
የንግስና ተምሳል ዘውድ አልተደፋም
እርግጥ ነው ፀዳልሽ
እንደ እመቤታችን በፍፁም አልፋፋም
ውብ አለባበሷ
ካንቺ ብጫቂ ጨርቅ እየተጣመረ
ድኩም አምሮዬ
ምስጢር ስጦታሽን አየመረመረ
(እአየመዘመረ)
የመለኮት ሀይልሽ
የቱ ጋር እንዳለ ላይገባኝ ቢቀርም
ቤትሽ ግድግዳ ላይ ያለቺውን ማርያም
ሁሌ እንደምትመስይ አልጠራጠርም
ተመልከቻት እሷን
በሀለት እጆቿ ንጉሱን ታቅፋ
ስለክብሩ ብላ አንገቷን ስትደፋ
ተመልከቺ ልጇን
ከበግ ስር እንዳለ ብላቴና ግልገል
ከጡት አፈትልኮ
ከእናት ስር አምልጦ ለመሮጥ ሲታገል
ሁሌም ልሂድ ሲላት አትሂድ ትላለች
እናቱ ናትና ከሄደ በሗላ
ምን እንደሚገጥመው ቀድማ ታውቀዋለች
(አየሽ እኔም ልጅሽ)
የማይጨብጠው ተስፋዬን ጨበጬ
አትሂድ ከሚለኝ ከእቅፍሽ አምልጬ
ግብሬን ሁሉ ስቼ
አንቺን እረስቼ
ያሰርሺልኝ እውነት ማህተመ ከላላ
ስንት ጊዜ ሆነው ስንት ጊዜ ሞላ
አየሽ እኔ ልጅሽ
በኖርኩት ዘመኔ
ልጄ ሆይ ያለችን እንቴን ያልረዳሁ
እምነት የጎደለኝ
ትንቢቴን የፈራሁ ቤቴን ያልተረዳሁ
እዳዬን ፈርቼ
ስቃዬን ፈርቼ መስቀል እየሸሸሁ
በጉብዝናዬ ወር
ቀሽም ቀን ሳሳልፍ ስንት ግዜ አመሸሁ
አየሽ አይደል እማ
ከንቱነት ነው ለካ
እናቱን ማያምን እናቱን ማይሰማ
እውነትም እኔ ነኝ
መንገድም እኔው ነኝ ለራሴ እንዳላልኩኝ
መሄጃው ሲጠፋኝ
አማላጅ ፍለጋ ከእቅፍሽ ላይ ዋልኩኝ
መገመት የሚከብድ ለሀሳብ የረቀቀ
መፍረድ የማይችል ሆድ ክክፋት የራቀ
በዚህ ሁሉ ሽሽት በዚህ ሁሉ ምሽት
እንዴት አልተቆጣ እንዴት አልረገመኝ
እውነት እማማዬ ማርያምን ነው ምልሽ
እቅፍሽ ገረመኝ
ቤትሽ ግድግዳ ላይ
ማርያም ልጇን አቅፋ ምትታየው ምስል
ለምን አነደሆነ እንጃ
ቁርጥ እራስሽን አንቺን ስትመስል
አስቱ✍️
ለእናታቹ 🥰
ቤትሽ ግድግዳ ላይ
ማርያም ልጇን አቅፋ ምትታየው ምስል
ለምን አንደሆነ እንጃ
ቁርጥ እራስሽን አንቺን ስትመስል
[እርግጥ ነው]
እርግጥ ነው ከአናትሽ
የንግስና ተምሳል ዘውድ አልተደፋም
እርግጥ ነው ፀዳልሽ
እንደ እመቤታችን በፍፁም አልፋፋም
ውብ አለባበሷ
ካንቺ ብጫቂ ጨርቅ እየተጣመረ
ድኩም አምሮዬ
ምስጢር ስጦታሽን አየመረመረ
(እአየመዘመረ)
የመለኮት ሀይልሽ
የቱ ጋር እንዳለ ላይገባኝ ቢቀርም
ቤትሽ ግድግዳ ላይ ያለቺውን ማርያም
ሁሌ እንደምትመስይ አልጠራጠርም
ተመልከቻት እሷን
በሀለት እጆቿ ንጉሱን ታቅፋ
ስለክብሩ ብላ አንገቷን ስትደፋ
ተመልከቺ ልጇን
ከበግ ስር እንዳለ ብላቴና ግልገል
ከጡት አፈትልኮ
ከእናት ስር አምልጦ ለመሮጥ ሲታገል
ሁሌም ልሂድ ሲላት አትሂድ ትላለች
እናቱ ናትና ከሄደ በሗላ
ምን እንደሚገጥመው ቀድማ ታውቀዋለች
(አየሽ እኔም ልጅሽ)
የማይጨብጠው ተስፋዬን ጨበጬ
አትሂድ ከሚለኝ ከእቅፍሽ አምልጬ
ግብሬን ሁሉ ስቼ
አንቺን እረስቼ
ያሰርሺልኝ እውነት ማህተመ ከላላ
ስንት ጊዜ ሆነው ስንት ጊዜ ሞላ
አየሽ እኔ ልጅሽ
በኖርኩት ዘመኔ
ልጄ ሆይ ያለችን እንቴን ያልረዳሁ
እምነት የጎደለኝ
ትንቢቴን የፈራሁ ቤቴን ያልተረዳሁ
እዳዬን ፈርቼ
ስቃዬን ፈርቼ መስቀል እየሸሸሁ
በጉብዝናዬ ወር
ቀሽም ቀን ሳሳልፍ ስንት ግዜ አመሸሁ
አየሽ አይደል እማ
ከንቱነት ነው ለካ
እናቱን ማያምን እናቱን ማይሰማ
እውነትም እኔ ነኝ
መንገድም እኔው ነኝ ለራሴ እንዳላልኩኝ
መሄጃው ሲጠፋኝ
አማላጅ ፍለጋ ከእቅፍሽ ላይ ዋልኩኝ
መገመት የሚከብድ ለሀሳብ የረቀቀ
መፍረድ የማይችል ሆድ ክክፋት የራቀ
በዚህ ሁሉ ሽሽት በዚህ ሁሉ ምሽት
እንዴት አልተቆጣ እንዴት አልረገመኝ
እውነት እማማዬ ማርያምን ነው ምልሽ
እቅፍሽ ገረመኝ
ቤትሽ ግድግዳ ላይ
ማርያም ልጇን አቅፋ ምትታየው ምስል
ለምን አነደሆነ እንጃ
ቁርጥ እራስሽን አንቺን ስትመስል
❤56
አሸን መሰናክል በጫንቃዬ አዝዬ
መቆም እስኪከብደኝ በፈተና ዝዬ
እየዳኹኩ በጉልበት - ስቆም ምስልህ ፊት
ሚካኤል አባቴ
ተልጦ ይረግፋል የውድቀቴ ቅርፊት
በጸሎቴ መሀል የሀሰትን መና
ሽቅብ አንጠልጥሎ ሰቅሎ ከደመና
"ይብቃህ ዳዊት መድገም - ተው ውዳሴ ማርያም
ምስጋና፣ መሻትህ - ደርሷል ከአርያም
ተመልከት ወደ ላይ - አንጋጥጥ በጥብቅ
አየህ በረከትክን አንተን ሲጠብቅ"
እያለ ይጮኻል - ከንቱ ወናፍ ላንቃ
ከመች ጀምሮ ነው
ጸሎት የሚቋረጥ ምስጋናስ ሚበቃ?
እንጃ ግራ ገባኝ
አለማወቅ ጎዳኝ
ሚካኤል ረዳቴ - ዞርኩኝ ወደ ምስልህ
አሳቼን አየኹት ሲንፈራገጥ ከእግርህ
በስምህ ልዘክር - ካለኝ ላይ ቀንሼ
በደስታ እያበራኹ ከደጅህ ደርሼ
ስከፍት ሞሰቤን እጄን እያነቀ
በአዛኝ ከንፈሩ የፌዝ እየሳቀ
የኑሮን ውድነት እየዘረዘረ
"ገነት ለገባ ነፍስ - ጸድቆ ለበረረ
ገንዘብ የሚያባክን ምጽዋት ምን ሊበጅ?
ከሞት አያነቃ ህይወት አያደረጅ"
ይለኛል አስሬ እየዘጋ መንገድ
ከመቼ ወዲህ ነው
ምጽዋት ተለግሶ ውድቀት የሚታጨድ?
እንጃ ግራ ገባኝ
አለማወቅ ጎዳኝ
ሚካኤል አጋዤ ምስልህን ስታቀፍ
ጠላቴን አየሁት ከመኖር ሲቀረፍ
ክብርህ ያልገባቸው ምልጃህን ሊያጎድፉ
ጥቅስ እያጣቀሱ ቃል ሲለፈልፉ
ላስረዳቸው ስጥር ገድልህን አንብቤ
እንድትገልጥላቸው ስጽልይ በልቤ
የኔን እየተው ሊጫኑኝ በጩኸት
አፋቸው ደጋግሞ በውድቀት ሲከፈት
መዳረቅን ሽሽት ስሄድ ጥያቼው
እየተዘባበቱ በጉድፍ ቃላቸው
መክሰሬን ሲገልጹ አንተን በማክበሬ
የፌዝ ሳቅ አንግቤ - ሳያቸው ዞሬ
"ሂድና በላቸው ጥርሳቸውን አርግፍ
እንዴት ዝም ትላለህ - ክብሬ ሲጎድፍ"
የሚል ቁጣ ትዕዛዝ - ገባ ወደ ዕዝኔ
መቼ ይሆን ደግሞ
ስላንተ መምታትን የተማርኩት እኔ?
እንጃ ግራ ገባኝ
አለማወቅ ጎዳኝ
አልመስልህ አለኝ እውን ያንተ ቃል
ለስምህ መሞት እንጂ - መግደል ያጸድቃል?
ሚካኤል አዳኜ
አወጣኹ ምስልህን - ኪሴ ውስጥ መዝዤ
አነቀኝ አንዳች ኃይል - ቀረኹኝ ፈዝዤ
ባጣ መታገያ አቅም - ወረደ እንባዬ
ብቻ ግን ደስ አለኝ - አልሳትኩም ተታልዬ
ልጅህን የማትተው በፈተና ቃርሚያ
አዳንከኝ ሚካኤል ልክ እንደ አፎሚያ
አሸን መሰናክል በጫንቃዬ አዝዬ
መቆም እስኪከብደኝ በፈተና ዝዬ
እየዳኹኩ በጉልበት - ስቆም ምስልህ ፊት
ሚካኤል አባቴ
ተልጦ ይረግፋል የውድቀቴ ቅርፊት
#ኤልዳን
መቆም እስኪከብደኝ በፈተና ዝዬ
እየዳኹኩ በጉልበት - ስቆም ምስልህ ፊት
ሚካኤል አባቴ
ተልጦ ይረግፋል የውድቀቴ ቅርፊት
በጸሎቴ መሀል የሀሰትን መና
ሽቅብ አንጠልጥሎ ሰቅሎ ከደመና
"ይብቃህ ዳዊት መድገም - ተው ውዳሴ ማርያም
ምስጋና፣ መሻትህ - ደርሷል ከአርያም
ተመልከት ወደ ላይ - አንጋጥጥ በጥብቅ
አየህ በረከትክን አንተን ሲጠብቅ"
እያለ ይጮኻል - ከንቱ ወናፍ ላንቃ
ከመች ጀምሮ ነው
ጸሎት የሚቋረጥ ምስጋናስ ሚበቃ?
እንጃ ግራ ገባኝ
አለማወቅ ጎዳኝ
ሚካኤል ረዳቴ - ዞርኩኝ ወደ ምስልህ
አሳቼን አየኹት ሲንፈራገጥ ከእግርህ
በስምህ ልዘክር - ካለኝ ላይ ቀንሼ
በደስታ እያበራኹ ከደጅህ ደርሼ
ስከፍት ሞሰቤን እጄን እያነቀ
በአዛኝ ከንፈሩ የፌዝ እየሳቀ
የኑሮን ውድነት እየዘረዘረ
"ገነት ለገባ ነፍስ - ጸድቆ ለበረረ
ገንዘብ የሚያባክን ምጽዋት ምን ሊበጅ?
ከሞት አያነቃ ህይወት አያደረጅ"
ይለኛል አስሬ እየዘጋ መንገድ
ከመቼ ወዲህ ነው
ምጽዋት ተለግሶ ውድቀት የሚታጨድ?
እንጃ ግራ ገባኝ
አለማወቅ ጎዳኝ
ሚካኤል አጋዤ ምስልህን ስታቀፍ
ጠላቴን አየሁት ከመኖር ሲቀረፍ
ክብርህ ያልገባቸው ምልጃህን ሊያጎድፉ
ጥቅስ እያጣቀሱ ቃል ሲለፈልፉ
ላስረዳቸው ስጥር ገድልህን አንብቤ
እንድትገልጥላቸው ስጽልይ በልቤ
የኔን እየተው ሊጫኑኝ በጩኸት
አፋቸው ደጋግሞ በውድቀት ሲከፈት
መዳረቅን ሽሽት ስሄድ ጥያቼው
እየተዘባበቱ በጉድፍ ቃላቸው
መክሰሬን ሲገልጹ አንተን በማክበሬ
የፌዝ ሳቅ አንግቤ - ሳያቸው ዞሬ
"ሂድና በላቸው ጥርሳቸውን አርግፍ
እንዴት ዝም ትላለህ - ክብሬ ሲጎድፍ"
የሚል ቁጣ ትዕዛዝ - ገባ ወደ ዕዝኔ
መቼ ይሆን ደግሞ
ስላንተ መምታትን የተማርኩት እኔ?
እንጃ ግራ ገባኝ
አለማወቅ ጎዳኝ
አልመስልህ አለኝ እውን ያንተ ቃል
ለስምህ መሞት እንጂ - መግደል ያጸድቃል?
ሚካኤል አዳኜ
አወጣኹ ምስልህን - ኪሴ ውስጥ መዝዤ
አነቀኝ አንዳች ኃይል - ቀረኹኝ ፈዝዤ
ባጣ መታገያ አቅም - ወረደ እንባዬ
ብቻ ግን ደስ አለኝ - አልሳትኩም ተታልዬ
ልጅህን የማትተው በፈተና ቃርሚያ
አዳንከኝ ሚካኤል ልክ እንደ አፎሚያ
አሸን መሰናክል በጫንቃዬ አዝዬ
መቆም እስኪከብደኝ በፈተና ዝዬ
እየዳኹኩ በጉልበት - ስቆም ምስልህ ፊት
ሚካኤል አባቴ
ተልጦ ይረግፋል የውድቀቴ ቅርፊት
#ኤልዳን
❤30
የደሃውን ልመና ችል አትበል፡፡ በነፍሱ የመረረው ነውና ቢረግምህ እግዚአብሔርአቤቱታውን ይሰማዋል ፤ ፈጥኖም ይደርስብሃል፡፡ ስለዚህ ደሃን በድህነቱ ምከንያት አታቃለው፤ አንተንም ይረግምህ ዘንድ ምከንያት አትሁነው፡፡
ልብሶቹ ቢያድፋበት በውኃ እጠብለት፤ አዲስም ልብስ ገዝተህ አልብሰው፤ ደሃው ወደ ቤት የገባ እንደሆነ እግዚአብሔር ወደ ቤትህ ይገባል፤ በመኖሪያህም ያድራል፡፡ ከመከራ ከስቃይ ያላቀቀኸው ያ ድሃ አንተንም ከሚመጣብህ መከራና ስቃይ ያላቅቅሃል።
የእንግዳውን እግር አጠብክን ? የበዛ ኃጢአትህን አጥበህ አስወገድከው፡፡ ለድሃው ይመገብ ዘንድ ማዕድን አቀረብክለትን ? እነሆ እግዚአብሔር አብ ከማዕድህ በላ፤ ክርስቶስም ለደሃው ካቀረብከለት ውኃ ጠጥቶ ረካ፤ መንፈስ ቅዱስም ማደሪያ ቤቱ አደረገህ፡፡
ድሃው ካቀረብክለት በልቶና ጠጥቶ ደስ አለውን? ጌታ ክርስቶስን ደስ አሰኘኸው፤ እርሱ ያደረግህለትን መልካም ችሮታ የሚረሳ አይደለምና በመላእከትና በሰዎች ፊት ያከብርሃል፡፡ ከርሃቡ እንዳሳረፍከው በመጨረሻው ቀን ይመሠክርልሃል፤ ለጥማቱ የሚጠጣ ስላቀረብክለት በመላእክቱ ፊት ያመስግንሃል፡፡
ልጄ ሆይ መልካም ዘርን በደስታና እግዚአብሔርን ተስፋ በማድረግ ዝራ፤ ልፋትህም ፍሬ ይስጥህ፡፡ ገበሬ ዘሩን በተስፋ ይዘራል፣ ነጋዴም በተስፋ አተርፋለሁ ብሎ ባሕር አቋርጦ ይጓዛል፤ አንተም አዝመራ የሚሆን ፍሬን ትፈልጋለህ፣ ስታገኝም በተስፋ ትዘራለህ፤ ምርቱንም በተስፋ ትጠባበቃለህ፡፡
ልጄ ሆይ ማናቸውንም ነገር በምትፈጽምበት ጊዜ ሥራህን በጸሎት ጀምር፡፡ የምትሠራቸውን ሥራዎች ሁሉ በትምህርተ መሰቀል ባርካቸው። በምትበላም፣ በምትጠጣም ጊዜ፣ በምትተኛም በምትነቃም ጊዜ፣ በቤት ውስጥም ሳለህ ይሁን በጎዳና ፣ በዕረፍትም ወቅት ቢሆን፣ ማማተብን አትዘንጋ፡፡ (የጌታህን ስቅለት አስታውሶ) ከክፋት የሚጠብቅህ ይህን የመሰለ ጠባቂ ከቶ አታገኝምና፤ እርሱ ለምታደርጋቸው ድርጊቶችህ ሁሉ እንደ ግንብ ነው (ማስተዋልን ይሰጥሃል)፡፡ ማማተብን በሥርዓት ይፈጽሙት ዘንድ (የከርስቶስ ኢየሱስንም ስቅለት ሁሌም በፊታቸው ይስሉ ዘንድ) ለልጆችህ በጥንቃቄ አስተምራቸው።
በትከክለኛው ትርጉም ነጻ ሰው ትባል ዘንድ ራስህን ከእግዚአብሔር ሕግ ቀንበርበታች አድርግ፡፡ ከእግዚአበሔር ፈቃድ ውጪ የሆነውን የነፍስን ፈቃድ አታድርግ፡፡
ስለአንተ መዳን ምን ያህል ትእዛዛትን ልጻፍልህ? ምን ያህልስ ሕግጋትን ልቅረጽልህ? ነጻነትህን የምትሻት ከሆንህ ሕግጋትን ከሥነፍጥረት የምትማራቸው አይደሉምን? ቅድስናን የምትወድ ከሆነ አንተው ራስህ ይህንን ለሌሎች ማስተማር ትችላለህ፡፡
ተፈጥሮ እንደ መጽሐፍ፤ ፍጥረታት እንደ ጽላት ይሁኑህ፤ ከእነርሱ ሕግጋትን ተማር፡፡ በተመሰጦም ሆነ በመጽሐፍ ያልሰፈሩትን ሕግጋት መርምረህ ተረዳ፡፡ ፀሐይ በመውጣቷና በመግባቷ ለሥራ ዕርፍት አንደሚያስፈልግህ ታስተምርሃለች፡፡ ሌሊትም በጸጥታ ለሥራዎችህ መጨረሻ እንዳላቸው ጮኻ ትነግርሃለች፡፡ በምድር ላይ የሚፈሩ ፍራፍሬዎችም ለሁሉ ነገር ወቅት ወቅት እንዳላቸው ያውጁልሃል። በክረምት የዘራኸውን ዘር በበጋ ትሰበስባዋለህ፤ እንዲሁ በምድር የጽድቅን ዘር የዘራህ ከሆነ በትንሣኤ ፍሬውን ትሰበስባለህ፡፡
(ስብከት ወተግሣጽ ዘቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ገጽ 75-76 በመምህር ሽመልስ መርጊያ የተተረጎመ)

❤34🥰1
እናት አለኝ
በመንገዴ...
ከኔ ቀድማ የምትገኝ
ቀን ሲከዳኝ ሲያሻኝ ማረፍ
ቀሚሷ ነው የኔ መዳፍ
እናት አለኝ
ቃል ኪዷኗ 'ሚደግፈኝ
ክንዴ ሲዝል ለመኖር ስደክም
እኩል ከኔ ታማ ቁስሌን የምታክም
ሳዝን የሚጨንቃት ሲከፋኝ የማትወድ
በሄድኩበት ሁሉ አብራኝ የምትሄድ
እናት አለኝ
በሀዘን ተከብቤ እንዳልታይባት
የኔን ድካም ወስዳ የምትሰጠኝ ብርታት
እናት አለኝ
@MekuanenetM
በመንገዴ...
ከኔ ቀድማ የምትገኝ
ቀን ሲከዳኝ ሲያሻኝ ማረፍ
ቀሚሷ ነው የኔ መዳፍ
እናት አለኝ
ቃል ኪዷኗ 'ሚደግፈኝ
ክንዴ ሲዝል ለመኖር ስደክም
እኩል ከኔ ታማ ቁስሌን የምታክም
ሳዝን የሚጨንቃት ሲከፋኝ የማትወድ
በሄድኩበት ሁሉ አብራኝ የምትሄድ
እናት አለኝ
በሀዘን ተከብቤ እንዳልታይባት
የኔን ድካም ወስዳ የምትሰጠኝ ብርታት
እናት አለኝ
@MekuanenetM
❤41🥰7
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ሲነግሩሽ ሰሚነሽ |@Z_TEWODROS
✞ ያለሽ ልዩ ፀጋ
ያለሽ ልዩ ፀጋ ያለሽ ልዪ ክብር
የሁሉ እመቤት በሰማይ በምድር
አቁራሪተ መዐልት ምራገ ፀሎት
ሲነግሩሽ ሰሚነሽ ኪዳነምህረት
በመከራ ላለው ሁኝለት መፅናኛ
ዕንባውን አብሺው አይዘን ዳግመኛ
ጉድለቱን ሙይለት በፈረሰው ቆመሽ
ስለምታስምሪ በልዩ ኪዳንሽ
ከኪዳንም በላይ ኪዳንሽ ልዩ ነው
እናቴ የሚልሽ አምላክሽ ልጅሽ ነው
አዝ__
ይበጠሰ ከእጁ የወህኒው ሰንሰለት
የሞቱ ደብዳቤ ይቀየር በህይወት
አዲስ ተስፋ ሞልተሽ አዲስ ሰው አድርጊው
መቅበዝበዙ ይርሳ ድንግል አረጋጊው
ከኪዳንም በላይ•••••••••••••
አዝ____
በዕንባ የመጣው ይመለስ በደስታ
መጠማቱ ይቅር ይሞላ በእርካታ
ስለቱ ሰምሮለት ይቁም ለምስጋና
የአብራኩን ክፋይ አሳቅፊውና
ከኪዳንም በላይ••••••••••••
አዝ__
ተይዞ ለሚኖር በአልጋ ቁራኛ
አንቺው እመቤቴ የዴውም ዳኛ
መንገርስ ላንቺ ነው መማፀን ወዳንቺ
ተስፋን ለምትቀጥይ ህልምን ለምትፈቺ
ከኪዳንም በላይ••••••••
ሊቀ-መዘምራን
ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ያለሽ ልዩ ፀጋ ያለሽ ልዪ ክብር
የሁሉ እመቤት በሰማይ በምድር
አቁራሪተ መዐልት ምራገ ፀሎት
ሲነግሩሽ ሰሚነሽ ኪዳነምህረት
በመከራ ላለው ሁኝለት መፅናኛ
ዕንባውን አብሺው አይዘን ዳግመኛ
ጉድለቱን ሙይለት በፈረሰው ቆመሽ
ስለምታስምሪ በልዩ ኪዳንሽ
ከኪዳንም በላይ ኪዳንሽ ልዩ ነው
እናቴ የሚልሽ አምላክሽ ልጅሽ ነው
አዝ__
ይበጠሰ ከእጁ የወህኒው ሰንሰለት
የሞቱ ደብዳቤ ይቀየር በህይወት
አዲስ ተስፋ ሞልተሽ አዲስ ሰው አድርጊው
መቅበዝበዙ ይርሳ ድንግል አረጋጊው
ከኪዳንም በላይ•••••••••••••
አዝ____
በዕንባ የመጣው ይመለስ በደስታ
መጠማቱ ይቅር ይሞላ በእርካታ
ስለቱ ሰምሮለት ይቁም ለምስጋና
የአብራኩን ክፋይ አሳቅፊውና
ከኪዳንም በላይ••••••••••••
አዝ__
ተይዞ ለሚኖር በአልጋ ቁራኛ
አንቺው እመቤቴ የዴውም ዳኛ
መንገርስ ላንቺ ነው መማፀን ወዳንቺ
ተስፋን ለምትቀጥይ ህልምን ለምትፈቺ
ከኪዳንም በላይ••••••••
ሊቀ-መዘምራን
ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
❤39👏3👍1
Forwarded from ነይ ነይ እምዬ ማርያም መዝሙሮች (𝓟𝓲𝓵𝓾𝓟𝓪𝓭𝓮𝓻)
አስደናቂ ተአምር ያለባት እና በአህዛብ የተከበበችዉ በቂልጦዋ ሎዛ ማርያም
ሰኔ 21ን ከጓደኞቼ ጋር በዛ አከበርን
ይሄን video ለማየት
👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/VnnnRBTXaoQ?si=Ib1aPotJjENZUDp0
ሰኔ 21ን ከጓደኞቼ ጋር በዛ አከበርን
ይሄን video ለማየት
👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/VnnnRBTXaoQ?si=Ib1aPotJjENZUDp0
YouTube
ሰኔ 21ን በቂልጦ ማርያም አከበርን | Day 1
Come with me on a peaceful and spiritual journey as I explore one of Ethiopia’s beautiful historic churches. This vlog captures the culture, architecture, and deep traditions of Ethiopian Orthodox Christianity. 🙏🏽⛪️🇪🇹
📍 Location: ቂልጦ ማርያም (ወራቤ)
🎥 Filmed…
📍 Location: ቂልጦ ማርያም (ወራቤ)
🎥 Filmed…
❤10🥰4
Forwarded from የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች (. .)
+ ያላለቀው ሰፌድ +
ዓሥር ብር ላይ የኖረችው የዚህች ሴት ነገር አንጀት ይበላል:: ሰፌድዋን ሠርታ ሳትጨርስ ጊዜዋን ጨረሰች:: ቀና ብዬ ወሬ ልይ ሳትል አቅርቅራ ሥራዋ ላይ እንዳተኮረች ኖረች:: ትዳር ልያዝ ሳትል የየሰዉን ኪስ ለመሙላት እንዳቀረቀረች ኖረች:: አሁን ግን እጅ ለእጅ በተያያዙ አራት ሰዎች ተተክታ ተሰናበተች::
መልእክቱ ይኼ መሰለኝ :-
ወዳጄ ነገሮች መቼ እንደሚለወጡ አታውቅም:: እጅህ ላይ ያለውን ሥራ ሁሉ በቶሎ ጨርስ:: ማንም ሊሠራባት የማይችላት ሌሊት ሳትመጣ በፊት ሥራህን አከናውን::
ብዙዎቻችን ከአጭሩ ዘመናችን ብዙ እናባክናለን:: ምንም ያላደረግንባቸው ባዶ ጊዜያትና ያልተኖሩ ብዙ ቀናት አሉ:: ከገንዘብ በላይ የማይተካው ብክነት የጊዜ ብክነት ነው::
ሰዎች ጊዜያቸውን ተጠቅመው የሠሩትን ክፋት ማውራት ትተን ጊዜያችንን መጠቀም ይኖርብናል::
በጊዜህ በአግባቡ ተጠቀም:: የማትጨርሰው ለዓመታት የማያልቅ ሰፌድ አትጀምር:: ለነገሮች ቅደም ተከተል ሥጣቸው:: አንዱን ሳትጨርስ ሌላ አትጀምር:: ቁምነገሩ በነገሮች መወጣጠርና ቢዚ መሆን አይደለም:: ጉንዳኖችም ቢዚ ናቸው:: ቁምነገሩ ጊዜ የምታጠፋው ምን ላይ ነው የሚለው ላይ ነው:: እነርሱ ቢያንስ ለገብረ ጉንዳን ይተርፋሉ:: ያንተ ቢዚነት ለማን ይተርፋል?
ስልክህ ውስጥ ባለ ጌም ላይ ያሉ ግንቦችን ለማፍረስ አለዚያም ለመገንባት ጊዜ የምታጠፋ ከሆነ ድንገት ብትሞት እንኳን በጣም ታሳዝናለህ:: ምድር ካንተ ብዙ ትጠብቃለች:: ሰዎች ገንዘብ እንዲያገኙ አንተ ገንዘብ የማታገኝበት ነገር ላይ ትሰቃያለህ::
የምትሰፋውን ሰፌድ አሁኑኑ ወስን:: ነገ ዓለም ሳትቀይርህ በፊት ሥራህን ወስን:: ጊዜህን ተጠቀምበት:: ባላስፈላጊ ነገር ላይ ጊዜ አትውሰድ:: መጽሐፍ ቅዱስ "ለሚጠፋ መብል አትሥሩ ለዘላለም ሕይወት ሥሩ" ይልሃል::
ከቻልክ ትውልድ የሚጠቅም ለአንተም ለነፍስህ የሚበጅ ነገር ሥራ:: ብቻ እየሰፋኸው ያለኸውን ሰፌድ ቆም አድርገህ ምን እያደረግኩ ነው? ብለህ ራስህን መጠየቂያህ ጊዜ አሁን ነው:: አለዚያ ግን ድንገት ሕልውናህ አብቅቶ ሰዎች ባዩህ ቁጥር እንደዚህች ሴትዮ "ውይይይይ ይቺ ሴትዮ አሥር ብር ላይ የነበረችው እኮ ናት" እያሉ ከንፈር ይመጡብሃል::
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

❤54🥰2
እኔ እና ገጣሚው
(Desu Fikriel)
ዛሬም ባይገባኝም - እንዴት እንዳመንኩሽ - እንዴት እንዳሳትሽኝ
"ፍቅር ይኑር እንጅ ገንዘብ ምን ያደርጋል" ብለሽ አሳመንሽኝ።
ካመንኩሽ በኋላ...
በቅጡ ሳንኖር ሳምንት ሳይሞላ
"ዋናው ገንዘቡ ነው ፍቅር አይበላ"
ብለሽ ክደሽኛል
ፍቅር ባያውረኝ - እንኳን ለኔ ቀርቶ - ለልጅ አይሳትም
የዘመን ሀቅ ነው - ፍቅር 'በድሀ ደንብ' - አይመሰረትም
ከካድሽኝ በኋላ
ሱራፌል መልአኩን - ከ'ሳት ሰይፉ ጋራ - ልቤ ዳር አቁሜ
ሴት ውስጤ ላትገባ - ዳግም ላላፈቅር - ማልኩኝ ደጋግሜ
የምልሽ ገብቶሻል?
ለነገሩ ተይው
ቢገባሽም እንኳን - ገብቶኛል አትይም - መካድ ለምዶብሻል
በርግጥ አታነቢም (ምናልባት ከሰማሽ)
አንድ ባለቅኔ
ፍቅረኛውን ቀጥሮ - ትንሽ በማርፈዷ - ብዙ የበሸቀ
ምድሩ አልበቃ ብሎት ከጨረቃዋ ጋር በእልህ ተናነቀ
ፍቅረኛውን መክራ ያስቀረች ይመስል ዓለምን ጠልቷታል
የሚቀኝላትን
የሚሳሳላትን ጨረቃዋን እንኳ 'እናቷን' ብሏታል
የምልሽ ገብቶሻል?
ለነገሩ ተይው
ቢገባሽም እንኳን - ገብቶኛል አትይም - መካድ ለምዶብሻል
ይሄን ባለቅኔ
ያረፈደችው ሴት (አንቺ እንዳደረግሽው) ከድታው ቢሆን ኖሮ
ከፈጣሪው ጋራ መሟገቱ አይቀርም ፍጡሩን ተሻግሮ
እያልኩ አስባለሁ
ህመም በወለደው አስታማሚ ቅኔ ቁስሌን አሻሻለሁ
የሚገርምሽ ነገር
ግጥም ልፅፍ ነበር
'ያማል' የሚል ርዕስ ከዚህ ሰው አንስቼ
ግን አስቢው እስኪ የእሱ ሴት አርፍዳ እኔ ተከድቼ
አንድ አይነት ስንቀኝ
ሳስበው ራሱ ብቻየን ቁጭ ብዬ እንደ ጅል አሳቀኝ

❤31👍4
ሚዛኑ ቢያደላ፤ ጊዜ ሆኖ ዳኛ
ቋንቋ ቀለም ሆነ፤ የሰው መመዘኛ።
ትገል እደው ግደል፤ ታድን እንደው አድን
ጠባሳ አይዝም፤ መርቅዞ የሚድን።
ብዬ ባዜምበት ....
ይፈትለው ጀመረ ቃል አጠቃቀሜን
ምንሽር አንስቼ ላላሳየው አቅሜን
ማንስ ገሎ ዳነ ማን ሞቶ ተረሳ ?
ፍጻሜው ሰይፍ ነው፤ ሰይፍ ለሚያነሳ።
***
ስለዚህ፤ ትርጉሙን
"ሀገር" ማለት ብባል?
"ሀገር" ማለት "ሰው ነው" አልልም ደፍሬ።
ሀገር የሚሆን ሰው፤ አታለች ሀገሬ።
ቋንቋ ቀለም ሆነ፤ የሰው መመዘኛ።
ትገል እደው ግደል፤ ታድን እንደው አድን
ጠባሳ አይዝም፤ መርቅዞ የሚድን።
ብዬ ባዜምበት ....
ይፈትለው ጀመረ ቃል አጠቃቀሜን
ምንሽር አንስቼ ላላሳየው አቅሜን
ማንስ ገሎ ዳነ ማን ሞቶ ተረሳ ?
ፍጻሜው ሰይፍ ነው፤ ሰይፍ ለሚያነሳ።
***
ስለዚህ፤ ትርጉሙን
"ሀገር" ማለት ብባል?
"ሀገር" ማለት "ሰው ነው" አልልም ደፍሬ።
ሀገር የሚሆን ሰው፤ አታለች ሀገሬ።
❤27👍2👎1
Forwarded from 💠ኢዮራም ፕሮሞሽን💠
⛪️ የትኛዉን ማግኘት ይፈልጋሉ ⁉️
⇛ኦርቶድክሳዊ ፎቶና ስዕላድኖች...♡
⇛ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮችን...♡
⇛ኦርቶዶክሳዊ መፅሐፍትች...♡
⇛ኦርቶዶክሳዊ ዜናወችን...♡
⇛ኦርቶዶክሳዊ TikTok video ወችን...♡
⇛ኦርቶዶክሳዊ የመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅሶችን..
🎧 እነዚህ ሁሉ ለማግኘት ይቀላቀሉ
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
⇛ኦርቶድክሳዊ ፎቶና ስዕላድኖች...♡
⇛ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮችን...♡
⇛ኦርቶዶክሳዊ መፅሐፍትች...♡
⇛ኦርቶዶክሳዊ ዜናወችን...♡
⇛ኦርቶዶክሳዊ TikTok video ወችን...♡
⇛ኦርቶዶክሳዊ የመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅሶችን..
🎧 እነዚህ ሁሉ ለማግኘት ይቀላቀሉ
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
❤6
Forwarded from ታዚ
አጭር አስተማሪ ታሪክ
ልጅቷ ሥራ የላትም ፣ ከመኖሪያዋ አጠገብ ካለው ቤተክርስቲያን ዘወትር እየተገኘች ልመናዋ ሥራ ስጠኝ ብቻ ከሆነ ሰንብታለች፡፡ በነጋ በጠባ ቁጥር “እባክህን አምላኬ ውዬ የምገባበት ሥራ ስጠኝ እያለች” እያለች ትጸልያለች፡፡ አንድ ቀን ቤተክርስቲያን ደርሳ ወደ ቤቷ ስትመለስ ከአንድ መሥሪያ ቤት አጠገብ ትደርስና የተለጠፈ የሥራ ማስታወቂያ አይታ ቆማ ማንበብ ትጀምራለች፡፡ የሥራው ዓይነት እና የትምህትቱ ደረጃ ሁሉ በዝርዝር ሰፍሯል፡፡
ሁሉም እሷ ልታሟላ የምትችለው መስፈርት ነበር፡፡ ደሞዙም አምስት ሺህ ብር ይላል፡፡የመሥሪያ ቤቱ ለመኖሪያ ቤቷ ቅርብ መሆን፣ የትምህርት ደረጃ መስርቱ ከእርሷ የትምህርት ደረጃ ጋር መመሳሰል፣ የመነሻ ደመወዙም ቢሆን ይህ ሁሉ ተደምሮ የመቀጠር ጉጉቷን ከፍ አደረገው፡፡ ይኹን እንጂ ከሌሎች ተመዝጋቢዎች ጋር መወዳደር ግድ ስለሆነ የማለፍና ያለማለፍ ጉዳይ እንዳለ ስትረዳ በጣም ተጨነቀች፡፡ ስለዚህ ተመዝግባ ስታበቃ ወደ ቤተክርስቲያን አቅንታ አምላኳን “እባክህን ይህን ፈተና አሳልፈኝና የሥራውን እድል ስጠኝ” ስትል ተማጸነች፡፡ ሁሉም አልፎ ውጤት የሚለጠፍበት ቀን ደረሰና በናፍቆትና በጉጉት ታጅባ ታነብ ለማንበብ ሄደች፡፡ውጤቱ ግን የእሷን ማለፍ የሚያረጋግጥ አልነበረም፡፡ የእሷ ስም የለም ያለፉት ሌሎች ናቸው፡፡ ምንም ሳትናገር ወደ ቤተክርስቲያን ሮጠች፡፡ እዚህም እንደደረሰች አምላኳን “ታዘብኩህ” ስትል የምሬት ድምጽ አሰማች፡፡
ይህ በሆነ በሳምንቱ ሌላ ማስታወቂያ በሌላ መ/ቤት ወጣ፡፡ ደመዎዙ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር ነበር፡፡ ይህን ስታይ እንደመጸጸት አለችና “አምላኬ ለካስ ይሄ እንደሚሻል አውቀህ ነው ያኛው እንዲያልፈኝ ያደረከው፣ እባክህን ይቅር በለኝ የአፌን አትቁጠርብኝ ይህን ግን እንዳትከለክለኝ አደራ” ስትል ተማጸነችና ተመዝግባ ውድድሯ ጀመረች፡፡ ሁሉም አልቆ ውጤት ሲለጠፍ አሁንም የእሷ ስም የለም፡፡ ያለፉት ሌሎች ናቸው፡፡ አሁን በጣም አዘነች፡፡ በአምላኳ ላይ ያላት ተስፋ ሲሟሽሽ ተሰማት፡፡ በረዶ እንደወረደበት ሰው ወኔዋ ቀዘቀዘ፡፡ ጊዜ ሳታባክን ወደ ቤተክርስቲያን ሄደችና “አሁንስ በጣም ታዘብኩህ” ስትል እሱ የሰጣትን ምላስ እሱው ላይ ዘረጋችው፡፡
በዚህ ሁለት ሳምንታት አለፉና አንዲት ጓደኛዋ አንድ መሥሪያ ቤት የሥራ ማስታወቂያ መለጠፉን ነግራት አልመዘገብም ብላ በማኩረፏ በብዙ ጉትጎታ ከቦታው ደረሰች ማስታወቂያውን ስታነበው ሁሉም መረጃ ከሷ ጋር የሚሄድ ሲሆን ደሞዙም ከመጀመሪያው በሁለት እጥፍ ጨምሮ አስር ሺህ ብር ይላል፡፡ ከሚቀር እስኪ ልሞክረው ብላ ተመዘገበች፡፡ ተገቢውን ሁሉ አድርጋ የመጨረሻ ውጤት የሚለጠፍበት ቀን ከስፍራው ተገኘች፡፡ አሁን ስሟ አንደኛ ተራ ቁጥር ላይ ተለጥፏል፡፡ በከፍተኛ ብቃት ማለፏን ስታይ ዕንባዋ በዐይኗ ግጥም አለ፣ ሁለቱን ዐይኖቿን ስትጨፍናቸው ቋ ጥረው የያዙትን የደስታ ዕንባ በጉንጮቿ ላይ ከለበሱት፡፡ ቃል ማውጣት አልቻለችም እየበረረች ወደ ቤተክርስቲያን መጣችና፡፡ ውስጧም አምላኳን በዚሁ ቦታ ተገኝታ ታዘብኩህ ስትል እንዳማረረችው አስታወሳት ያኔ “የኔ አምላክ ታዘብከኝ አይደል?” አለች ለራሷ ብቻ በሚሰማ ድምጽ በቀስታ፡፡
እኛስ በህይወት ውጣ ውረድ በማይገባን መዓረግና በሌለን አቅም አምላካችንን ስንት ጊዜ ታዝበነው ይሆን?
✍ታዚ

❤61👍6
Forwarded from የጥበብ እጆች✍️✍️
አስችለኝ
ጌታዬ.....አምላኬ.....እንዴት ብዬ ልጥራህ
አንደበቴ ረክሶ በምን አፌ ላንሳህ
በስድብ በሀሜት ረክሷል ንግግሬ
ከቶ እንዴት ብዬ ላውራ በከንፈሬ
****
አንተ ክቡር ምስጉን ግርማህ የሚያስፈራ
አዛኝ ታጋሽ የዋህ ለህዝብህ የምትራራ
ሆነህ ፍቅር ለሰው ወድቀህ በአደባባይ
ሳይገባህ ወርደህ ከዙፋንህ ሰማይ
በትህትናህ ልቀህ በሰው እጅ ተይዘህ
በጥፊ ተመተህ ተገርፈህ ተሰቅለህ
ስትሰጠኝ ህይወትን እንካ ልጄ ብለህ
እኔ ግን በምላሽ ሸሸው እንደ ባዳ
ነፍሴ ስትታበይ በሀጥያት ተገምዳ
*
ጌታዬ....አምላኬ...እንደው ምኔን አይተህ
ምኔ ይዞህ ከቶ ምህረትን ማብዛትህ
የበደሌ መብዛት የመርከሴ ነገር
የውስጤ መከርፋት የልቤ መታወር
የስጋዬ መዛል ያንደበቴ መምረር
እንደምን የኔ አባት ቻልክበት መታገስ
በሞቱለት ወዳጅ በሀሰት መከሰስ
****
እስከዛሬ ችለህ ታግሰህ ካለፍከኝ
በፍቅርህ ጎብኝተህ ደጋግመህ ከማርከኝ
ከእንግዲህስ ወዲህ አስችለኝ አባቴ
እንድተው አምርሬ ክፉውን ሀጢያቴ
ይብቃህ በቃህ በለኝ አበርታኝ አባቴ
በንስሀ ድኜ ልግባ.....ከዘላለም ቤቴ
✍ብሩክ ተፈራ
ጌታዬ.....አምላኬ.....እንዴት ብዬ ልጥራህ
አንደበቴ ረክሶ በምን አፌ ላንሳህ
በስድብ በሀሜት ረክሷል ንግግሬ
ከቶ እንዴት ብዬ ላውራ በከንፈሬ
****
አንተ ክቡር ምስጉን ግርማህ የሚያስፈራ
አዛኝ ታጋሽ የዋህ ለህዝብህ የምትራራ
ሆነህ ፍቅር ለሰው ወድቀህ በአደባባይ
ሳይገባህ ወርደህ ከዙፋንህ ሰማይ
በትህትናህ ልቀህ በሰው እጅ ተይዘህ
በጥፊ ተመተህ ተገርፈህ ተሰቅለህ
ስትሰጠኝ ህይወትን እንካ ልጄ ብለህ
እኔ ግን በምላሽ ሸሸው እንደ ባዳ
ነፍሴ ስትታበይ በሀጥያት ተገምዳ
*
ጌታዬ....አምላኬ...እንደው ምኔን አይተህ
ምኔ ይዞህ ከቶ ምህረትን ማብዛትህ
የበደሌ መብዛት የመርከሴ ነገር
የውስጤ መከርፋት የልቤ መታወር
የስጋዬ መዛል ያንደበቴ መምረር
እንደምን የኔ አባት ቻልክበት መታገስ
በሞቱለት ወዳጅ በሀሰት መከሰስ
****
እስከዛሬ ችለህ ታግሰህ ካለፍከኝ
በፍቅርህ ጎብኝተህ ደጋግመህ ከማርከኝ
ከእንግዲህስ ወዲህ አስችለኝ አባቴ
እንድተው አምርሬ ክፉውን ሀጢያቴ
ይብቃህ በቃህ በለኝ አበርታኝ አባቴ
በንስሀ ድኜ ልግባ.....ከዘላለም ቤቴ
✍ብሩክ ተፈራ
❤36👏1
ሽራፊ የህይወት ስንቅ
... ... ... ያልቋጠርኩ ለስስ ነፍሴ
በተግባር ያልተሟሸሁ
... ... ... የምጾም በምላሴ
ያልተቃኘሁ እንደ ክራር
... ... ... ያልፀናሁ እንደ ጉንዳን
ሺ ብንገዳገድ እንኳ
... ... ... የማልጣደፍ ለመዳን
አልጋ እንዳነቀ መጻጉዕ
... ... ... ቢያምረኝም መፈወስ
ለአፍታ ጥረት ማላቅ
... ... ... የጽድቅ ጸበል ለመቅመስ
እንዲሁ ለነገሩ ብቻ
... ... ... ደጅህ ምሄድ ምመጣ
ጥፋቴን ጠንቅቄ ባወቅም
... ... ... ራሴን ለለውጥ ማልቀጣ
በአፍ አሞጋሽ አወዳሽ
... ... ... ለምጽአት አፈግፋጊ
ተቀናቃኜን ለመጣል
... ... ... የጸሎት ሽምቅ ተዋጊ
ለምስጋና ለእልልታ
... ... ... መዳፌን የማላቀና
ድፍረት ግን ተጎናጽፌ
... ... ... በስምህ የምጽናና
ብሆንም ደካማ ልጅ
... ... ... ብሆንም እምነተ ገለባ
ገብርኤል አባቴ
አንተን አምኜ አይደል
... ... ... ዘልዬ ከእሳት የምገባ
አፉን ለቅቆ ከፍቶ
... ... ... ማጣት እንደ አንበሳ
ሊውጠኝ በመቋመጥ
... ... ... እልፍ ጊዜ ቢያገሳ
መች እደነብራለሁ
... ... ... መጉደልን በመፍራት
ትደፍነው የለም ወይ
... ... ... በበረከትህ እራት
እንደ ጉድ ቢፍለቀለቅ
... ... ... ፈተና እስኪያነፍር
አልሰጋም ቅንጣት ታክል
... ... ... ሺ ቢጎርፍም ችግር
ቢነድ የጥፋት እሳት
... ... ... ሊያከስመኝ ቢታገል
እየሳቅኩ እገባለሁ
... ... ... አምንኃለው ገብርኤል
ታበርደዋለህ ትኩሱን
... ... ... ትዘጋዋለህ ክፍቱን
ደካማ ብሆንም ልጅህ
... ... ... አትተወኝም ፍጹም
እረታለሁ ባንተ ሰይፍ
... ... ... እበረታለሁ ባንተ ክንፍ
ስንት ጊዜ የዳንኩት
... ... ... ቅዱስ ስምህን ስጽፍ።
ቅዱስ ገብርኤል
መልአከ ብስራት
መልአከ ራማ
አንጻኝ ከኃጢአቴ
ልዳን በእጆችህ በምህረትህ አውድማ!!
#ኤልዳን
... ... ... ያልቋጠርኩ ለስስ ነፍሴ
በተግባር ያልተሟሸሁ
... ... ... የምጾም በምላሴ
ያልተቃኘሁ እንደ ክራር
... ... ... ያልፀናሁ እንደ ጉንዳን
ሺ ብንገዳገድ እንኳ
... ... ... የማልጣደፍ ለመዳን
አልጋ እንዳነቀ መጻጉዕ
... ... ... ቢያምረኝም መፈወስ
ለአፍታ ጥረት ማላቅ
... ... ... የጽድቅ ጸበል ለመቅመስ
እንዲሁ ለነገሩ ብቻ
... ... ... ደጅህ ምሄድ ምመጣ
ጥፋቴን ጠንቅቄ ባወቅም
... ... ... ራሴን ለለውጥ ማልቀጣ
በአፍ አሞጋሽ አወዳሽ
... ... ... ለምጽአት አፈግፋጊ
ተቀናቃኜን ለመጣል
... ... ... የጸሎት ሽምቅ ተዋጊ
ለምስጋና ለእልልታ
... ... ... መዳፌን የማላቀና
ድፍረት ግን ተጎናጽፌ
... ... ... በስምህ የምጽናና
ብሆንም ደካማ ልጅ
... ... ... ብሆንም እምነተ ገለባ
ገብርኤል አባቴ
አንተን አምኜ አይደል
... ... ... ዘልዬ ከእሳት የምገባ
አፉን ለቅቆ ከፍቶ
... ... ... ማጣት እንደ አንበሳ
ሊውጠኝ በመቋመጥ
... ... ... እልፍ ጊዜ ቢያገሳ
መች እደነብራለሁ
... ... ... መጉደልን በመፍራት
ትደፍነው የለም ወይ
... ... ... በበረከትህ እራት
እንደ ጉድ ቢፍለቀለቅ
... ... ... ፈተና እስኪያነፍር
አልሰጋም ቅንጣት ታክል
... ... ... ሺ ቢጎርፍም ችግር
ቢነድ የጥፋት እሳት
... ... ... ሊያከስመኝ ቢታገል
እየሳቅኩ እገባለሁ
... ... ... አምንኃለው ገብርኤል
ታበርደዋለህ ትኩሱን
... ... ... ትዘጋዋለህ ክፍቱን
ደካማ ብሆንም ልጅህ
... ... ... አትተወኝም ፍጹም
እረታለሁ ባንተ ሰይፍ
... ... ... እበረታለሁ ባንተ ክንፍ
ስንት ጊዜ የዳንኩት
... ... ... ቅዱስ ስምህን ስጽፍ።
ቅዱስ ገብርኤል
መልአከ ብስራት
መልአከ ራማ
አንጻኝ ከኃጢአቴ
ልዳን በእጆችህ በምህረትህ አውድማ!!
#ኤልዳን
❤35
አንችን ብቻ ቤተልሔም
ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
አንቺን ብቻ ቤተልሔም
አንቺን ብቻ ቤተልሔም
አንቺን ብቻ በዚያ ግርግም
ዮሀንስን በገሊላ በኤፍራታ አላየንም
አንቺን ብቻ ቀራንዮ አንቺን በኮረብታ
ዮሴፍንምአላየንም ሊቶስጥራ ጎልጎታ❴አዝ❵፪*
አዝ
ገና በማለዳ በናዝሬቷ መቅደስ
ገብርኤል በስራት ይዞ ከገሊላ ሲደርስ
ያን ዜና ስሰሚ ደነገጥሽ በብርቱ
አንቺ ብቻ ነበርሽ ብላቴናይቱ
አዝ
ሕፃኑን ስትወልጅ ግርግም የነበሩ
የሉም በመከራው ቀራንዮን ፈሩ
በልደቱ እንጂ የታሉ በሞቱ
አብረሹ ነበርሽ አንቺ ብቻ እናቱ
አዝ
የግብፅ በረሀ አብረውሽ የወጡ
በቀያፋ ግቢ እንደምን አልመጡ
እርሱ ለሚገረፍ እነሱ እያፈሩ
አንቺን ብቻ ትተው በመንደር ነበሩ
አዝ
ሐሙስ ዕለት ፋሲካን ሲበሉ ያመሹ
አርብ ዕለት ተነሥተው ከቶ ወዴት ሸሹ
ቃል ገብተው ነበር ላይክዱት መሀላ
ድንግል ካንቺ በቀር ማን ነበር ሌላ
አዝ
በሠላሳ ዘመን በሥጋ ወራቱ
መች ነበሩ ከቶ ደቀመዛሙርቱ
የእጆቹን ታምራት ቀን ከሌሊት እያየሽ
በቃሉ በርታት ፊት አንቺ ነበርሽ
አዝ
ቤተልሄም ያሉ ቀራንዮ የሉም
ቀራንዮም ያሉ ግርግም አልነበሩም
በሆነበት ዘመን በመስቀል ሞቱ
አብረሹ ነበርሽ አንቺ ብቻ እናቱ
አንቺን ብቻ ቤተልሔም
አንቺን ብቻ በዚያ ግርግም
ዮሀንስን በገሊላ በኤፍራታ አላየንም
አንቺን ብቻ ቀራንዮ አንቺን በኮረብታ
ዮሴፍንምአላየንም ሊቶስጥራ ጎልጎታ
አንቺን ብቻ ቤተልሔም
አንቺን ብቻ በዚያ ግርግም
ዮሀንስን በገሊላ በኤፍራታ አላየንም
አንቺን ብቻ ቀራንዮ አንቺን በኮረብታ
ዮሴፍንምአላየንም ሊቶስጥራ ጎልጎታ❴አዝ❵፪*
አዝ
ገና በማለዳ በናዝሬቷ መቅደስ
ገብርኤል በስራት ይዞ ከገሊላ ሲደርስ
ያን ዜና ስሰሚ ደነገጥሽ በብርቱ
አንቺ ብቻ ነበርሽ ብላቴናይቱ
አዝ
ሕፃኑን ስትወልጅ ግርግም የነበሩ
የሉም በመከራው ቀራንዮን ፈሩ
በልደቱ እንጂ የታሉ በሞቱ
አብረሹ ነበርሽ አንቺ ብቻ እናቱ
አዝ
የግብፅ በረሀ አብረውሽ የወጡ
በቀያፋ ግቢ እንደምን አልመጡ
እርሱ ለሚገረፍ እነሱ እያፈሩ
አንቺን ብቻ ትተው በመንደር ነበሩ
አዝ
ሐሙስ ዕለት ፋሲካን ሲበሉ ያመሹ
አርብ ዕለት ተነሥተው ከቶ ወዴት ሸሹ
ቃል ገብተው ነበር ላይክዱት መሀላ
ድንግል ካንቺ በቀር ማን ነበር ሌላ
አዝ
በሠላሳ ዘመን በሥጋ ወራቱ
መች ነበሩ ከቶ ደቀመዛሙርቱ
የእጆቹን ታምራት ቀን ከሌሊት እያየሽ
በቃሉ በርታት ፊት አንቺ ነበርሽ
አዝ
ቤተልሄም ያሉ ቀራንዮ የሉም
ቀራንዮም ያሉ ግርግም አልነበሩም
በሆነበት ዘመን በመስቀል ሞቱ
አብረሹ ነበርሽ አንቺ ብቻ እናቱ
አንቺን ብቻ ቤተልሔም
አንቺን ብቻ በዚያ ግርግም
ዮሀንስን በገሊላ በኤፍራታ አላየንም
አንቺን ብቻ ቀራንዮ አንቺን በኮረብታ
ዮሴፍንምአላየንም ሊቶስጥራ ጎልጎታ
❤20
''.....ሰው ሲታመም የምንጠይቀው ከቋጠሮ ሰሐን ጋር ነው... ሰው ሲታሰር ' እግዚአብሔር ያውጣህ ' የምንለው ከፍትፍት አገልግል ጋር ነው ....አራስ የምትጠይቀው ከፔርሙዝ አጥሚት ጋር ነው ... የክርስትና አባታችን ለፋሲካ አክፋዩን የሚጠብቀው ድፎ ዳቦ ና አረቄ ነው ...እዝንተኛ የምናስተዛዝነው ሰባት እንጀራ ከአንድ ሰሐን ወጥ ጋር ነው ...ሟች የምንሸኘው ከገንቦ ጠላና ከለምለም እንጀራ ጋር ነው ...የቅዱሳንና የመልአክታት ተራዳኢነት የሚጎበኘን በስማቸው ከዘከርን ነው...ሰዕለታችን በሬ ወይም በግ ነው ...ሰርጋችን ፣ ልደታችን፣ እርቃችን፣ ሹመታችን፣ አምልኳችን፣ የሚበላ ነገርን ሙጥኝ ያሉ ናቸው ... ...ሌላው ቀርቶ አንድ ሰው ተምሮ ሲመረቅ ይዘን የምንሄደለት ስጦታ ብዕር ወይንም መጽሐፍ አይደለም ፤ ኬክ ፣ ብርቱካን ፣ ሙዝ ...ነው ። በሽተኛ ስትጠይቅ ከብርቱካንና ከሙዝ ይልቅ መጽሐፍ መውሰድ እንደማላገጥ ይቆጠራል ። ጊዜውን ይገፋበት ዘንድ መጽሐፍ ማበርከት በሽተኛው እንዳይድን ከመመኘት እኩል ነው ። ለኛ ለኢትዮጵያውያን መጻሕፍት ከባዶ ገበታችን በስተዚያ የተቀመጡ ትርፍ ነገሮች ናቸው ። መጻሕፍት የሚያስፈልጉት ገበታችን ሞልቶ ከገነፈለ በኃላ ነው ብለን በይነናል። ገበታችንም አይሞላ ፤ መጻሕፍቱም አይነሱም ። ያልተረዳነው ቢኖር ለገበታ መትረፍረፍ ዙሪያ ጥምጥም ጉዞ መጻሕፍት አቋራጭ መንገድ መሆናቸውን ነው ።እንዴት ታዲያ ማንበብ መብላትን ይቅደም ? መቼ ይሆን ከምንኮራባቸው ባህሎቻችን በላይ ማንበብ ባህላችን ሆኖ የምንታወቅበት ናየምንኮራበት?......'''''
❤31👍4