ጾም
ዔደን ታደሰ
❤3
Forwarded from ✞ የመዝሙር ግጥሞች ✞ (✞ የመዝሙር ግጥሞች ✞)
🌹 ፍልሰታ ምን ማለት ነው⁉️
-----------------🌹-------------------
➮ ‹ፍልሰት› ማለት ደግሞ የተለያየ ትርጕም ቢሰጠውም ‹ፍልሰታ ለማርያም› ተብሎ ሲገለጽ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሚያልፈው ወደ ማያልፈው ዓለም ከመቃብር የወጣችበት (የተነሣችበት) ቀን ማለት ነው፡፡ ወይም ደግሞ ከሥጋዊው ዓለም ወደ መንፈሳዊው ዓለም የተሸጋገረችበት ማለት ነው፡፡››
➮ ‹ፍልሰታ ለማርያም› የሚለው የግእዝ ቃል ሲኾን ‹ፍልሰታ› ማለት ደግሞ ‹ፈለሰ› ከሚል ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ‹ፍልሰት› ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መሔድን (መፍለስን) ያመለክታል፡፡ እመቤታችን ካረፈች በኋላ የሥጋዋን መፍለስ አስመልክቶ ሐዋርያት የእመቤታችን ሥጋ የት እንደ ተቀበረ አላወቁም ነበርና እግዚአብሔር የእመቤታችንን ሥጋ እንዲገልጥላቸው የጾሙት ጾም ነው፡፡
ሐዋርያት ሁለት ሱባዔ ጾመው የእመቤታችንን ሥጋዋን ሰጥቷቸው ትንሣኤዋንና ዕርገቷን በማየት በረከት ያገኙበት ጾም ነው፡፡ ስለኾነም ምእመናን ፍልሰታ ለማርያምን ከልጅ እስከ አዋቂው በጾም በጸሎትና በመቍረብ በጋራ በፍቅር፣ በሰላም ያሳልፉታል፡፡››
በዚህ ጊዜ ሐዋርያት እመቤታችን ከመቃብር መነሣቷንና ማረጓን ማየት አለብን፤ እንዴት ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ እንቀራለን ብለው በመንፈሳዊ ቅናት በመነሣሣት ነሐሴ አንድ ቀን በዕለተ ሰኞ ሁለት ሰባት ሱባዔ ያዙ፡፡ በዐሥራ አራተኛው ቀን ጌታችን የእመቤታችንን ሥጋ አንሥቶ ሰጣቸውና በጌቴሴማኒ ቀበሯት፡፡ እመቤታችን በ፷፬ ዓመቷ ጥር ፳፩ ቀን ዐርፋ ነሐሴ ፲፬ ቀን ተቀብራለች፡፡
ይኹንና ሐዋርያት ቢቀብሯትም ትንሣኤዋንና ዕርገቷን አላዩም ነበር፡፡ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያየው ሲቀብሯት ያላየው ሐዋርያው ቶማስ ነው፡፡ ቶማስ እንዲያስተምር ሕንድ አገር ዕጣ ደርሶት አስተምሮ በደመና ሲመለስ ነሐሴ ፲፮ ቀን እመቤታችን ስታርግ ሕዋ ላይ ተገናኙ በማለት ሊቀ ማእምራን ደጉ ያስረዳሉ፡፡
እንደ እርሳቸው አገላለጽ ምእመናን ጾመ ፍልሰታ የእመቤታችን ዕረፍት፣ ትንሣኤና ዕርገቷ የሚዘከርበት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ የኾነ ጾም ነው፡፡ በየዓመቱ ሕፃን አዋቂው ሳይቀር የእመቤታችን ፍቅር አድሮባቸው ጾሙን ይጾማሉ፣ ያስቀድሳሉ፤ ይቈርባሉ፡፡
➮ የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ ሊቀ ማእምራን ደጉ ምላሽ ሲሰጡም. "ኢትዮጵያ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የዐስራት ሀገር በመሆኗ እና ሕዝበ ክርስትያኑ ለእመቤታችን ልዩ ፍቅር ስላላቸው መሬት ላይ እየተኙ፣ ጥሬ እየበሉ በሰላም በፍቅር ይጾሙታል፡፡
ምእመናን ፍልሰታን ከሌሎች አጽዋማት በተለየ መልኩ መሬት ላይ እየተኙ ይጾሙታል፡፡
ይህ ደግሞ የእመቤታችን ፍቅር ስለሳባቸው ነው ፍቅር›› በማለት ያብራራሉ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
-----------------🌹-------------------
➮ ሊቀ ማእምራን ደጉ ዓለም ለዚህ ጥያቄ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተዋል፤ "ፍልሰታ ማለት ፈለሰ ተሰደደ ከሚለው ግስ የወጣ ነው።"
➮ ‹ፍልሰት› ማለት ደግሞ የተለያየ ትርጕም ቢሰጠውም ‹ፍልሰታ ለማርያም› ተብሎ ሲገለጽ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሚያልፈው ወደ ማያልፈው ዓለም ከመቃብር የወጣችበት (የተነሣችበት) ቀን ማለት ነው፡፡ ወይም ደግሞ ከሥጋዊው ዓለም ወደ መንፈሳዊው ዓለም የተሸጋገረችበት ማለት ነው፡፡››
➮ ቀሲስ ስንታየሁ አባተም በተመሳሳይ መልኩ ስለ ፍልሰታ እንዲህ በማለት ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡
➮ ‹ፍልሰታ ለማርያም› የሚለው የግእዝ ቃል ሲኾን ‹ፍልሰታ› ማለት ደግሞ ‹ፈለሰ› ከሚል ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ‹ፍልሰት› ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መሔድን (መፍለስን) ያመለክታል፡፡ እመቤታችን ካረፈች በኋላ የሥጋዋን መፍለስ አስመልክቶ ሐዋርያት የእመቤታችን ሥጋ የት እንደ ተቀበረ አላወቁም ነበርና እግዚአብሔር የእመቤታችንን ሥጋ እንዲገልጥላቸው የጾሙት ጾም ነው፡፡
ሐዋርያት ሁለት ሱባዔ ጾመው የእመቤታችንን ሥጋዋን ሰጥቷቸው ትንሣኤዋንና ዕርገቷን በማየት በረከት ያገኙበት ጾም ነው፡፡ ስለኾነም ምእመናን ፍልሰታ ለማርያምን ከልጅ እስከ አዋቂው በጾም በጸሎትና በመቍረብ በጋራ በፍቅር፣ በሰላም ያሳልፉታል፡፡››
➮ ሊቀ ማእምራን ደጉ ዓለም ካሣ እንዳብራሩት ቅዱስ ዮሐንስ እመቤታችንን እንዲጠብቃት ከተደረገ በኋላ ሐዋርያት ‹‹የእመቤታችን ነገር እንዴት ነው?›› ብለው በጠየቁት ጊዜ ‹‹እመቤታችንማ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ናት›› ብሎ ነገራቸው፡፡
በዚህ ጊዜ ሐዋርያት እመቤታችን ከመቃብር መነሣቷንና ማረጓን ማየት አለብን፤ እንዴት ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ እንቀራለን ብለው በመንፈሳዊ ቅናት በመነሣሣት ነሐሴ አንድ ቀን በዕለተ ሰኞ ሁለት ሰባት ሱባዔ ያዙ፡፡ በዐሥራ አራተኛው ቀን ጌታችን የእመቤታችንን ሥጋ አንሥቶ ሰጣቸውና በጌቴሴማኒ ቀበሯት፡፡ እመቤታችን በ፷፬ ዓመቷ ጥር ፳፩ ቀን ዐርፋ ነሐሴ ፲፬ ቀን ተቀብራለች፡፡
ይኹንና ሐዋርያት ቢቀብሯትም ትንሣኤዋንና ዕርገቷን አላዩም ነበር፡፡ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያየው ሲቀብሯት ያላየው ሐዋርያው ቶማስ ነው፡፡ ቶማስ እንዲያስተምር ሕንድ አገር ዕጣ ደርሶት አስተምሮ በደመና ሲመለስ ነሐሴ ፲፮ ቀን እመቤታችን ስታርግ ሕዋ ላይ ተገናኙ በማለት ሊቀ ማእምራን ደጉ ያስረዳሉ፡፡
እንደ እርሳቸው አገላለጽ ምእመናን ጾመ ፍልሰታ የእመቤታችን ዕረፍት፣ ትንሣኤና ዕርገቷ የሚዘከርበት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ የኾነ ጾም ነው፡፡ በየዓመቱ ሕፃን አዋቂው ሳይቀር የእመቤታችን ፍቅር አድሮባቸው ጾሙን ይጾማሉ፣ ያስቀድሳሉ፤ ይቈርባሉ፡፡
➮ የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው⁉️
➮ የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ ሊቀ ማእምራን ደጉ ምላሽ ሲሰጡም. "ኢትዮጵያ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የዐስራት ሀገር በመሆኗ እና ሕዝበ ክርስትያኑ ለእመቤታችን ልዩ ፍቅር ስላላቸው መሬት ላይ እየተኙ፣ ጥሬ እየበሉ በሰላም በፍቅር ይጾሙታል፡፡
ምእመናን ፍልሰታን ከሌሎች አጽዋማት በተለየ መልኩ መሬት ላይ እየተኙ ይጾሙታል፡፡
ይህ ደግሞ የእመቤታችን ፍቅር ስለሳባቸው ነው ፍቅር›› በማለት ያብራራሉ
🤗ወስብሐት ለእግዚአብሔር🤗
እመቤታችን በረከቷ አማላጅነቷ ከሁላችንም ጋር ይሁን እናትነቷ ይብዛብን አሜን መልካም የፍልሰታ ጾም ይሁንልን ሀገራችንን ሰላም ታድርግልን አሜን
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
❤13🥰2
😔🥹ወዮ የሰው ድካም ወዮ የሰው ክፋት😔🥹
ውቧን ቤተመቅደስ ቆሽሾ አረከሳት
ሀሜታም በመሆን አፉን አቆሸሸ
በመናገር ብዛት ከንፈሩ ጠለሸ
እጁ ደም ደም አለ ስርቆትን ለመደ
በምግባር ጠልሽቶ ክፋትን ወደደ
እግሩ ወደ ሌላ የአምላኩን ቤት ረሳ
ከመባዘን ብዛት ሰውነቱ ከሳ
የሚብሰው ነገር ከሁሉም ከሁሉ
ህሊናው ከረፋ አደፈበት መሉ😭😭😭
እግዚዮ ይቅር በለን አዎ በድለናል
ተደብቀን መስሎን ነውራችን ጎድቶናል
በቃቹ ይብቃቹ በለን አምላካችን
ምህረት ይቅርታህን አብዝተህ ላክልን
ማረን እነደ ገና ደጃፍህ ወድቀናል
በመረረ ለቅሶ አንተን ተማፅነናል😭😭😭
ማረን ማረን እንደገና
ልጆችህ ነንና
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
✍ብሩክ ተፈራ
ውቧን ቤተመቅደስ ቆሽሾ አረከሳት
ሀሜታም በመሆን አፉን አቆሸሸ
በመናገር ብዛት ከንፈሩ ጠለሸ
እጁ ደም ደም አለ ስርቆትን ለመደ
በምግባር ጠልሽቶ ክፋትን ወደደ
እግሩ ወደ ሌላ የአምላኩን ቤት ረሳ
ከመባዘን ብዛት ሰውነቱ ከሳ
የሚብሰው ነገር ከሁሉም ከሁሉ
ህሊናው ከረፋ አደፈበት መሉ😭😭😭
እግዚዮ ይቅር በለን አዎ በድለናል
ተደብቀን መስሎን ነውራችን ጎድቶናል
በቃቹ ይብቃቹ በለን አምላካችን
ምህረት ይቅርታህን አብዝተህ ላክልን
ማረን እነደ ገና ደጃፍህ ወድቀናል
በመረረ ለቅሶ አንተን ተማፅነናል😭😭😭
ማረን ማረን እንደገና
ልጆችህ ነንና
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
✍ብሩክ ተፈራ
❤45
. . .
ባይፈካ - ንጋት ለአመሉ
ያምፃል ዝም ያለው ሁሉ
አይደለ? ወትሮስ ተረቱ
ይረጋል ? የፍጥረት ሞቱ?
ሰው ልቡ ቢያስበው ደጉን
ያመልጣል ስብራት ህጉን?
ይሸሻል ከሞት ድለቃ
ከመከራ ዶፍ ከዕድል ሰበቃ?
ይሸሻል በስሟ ምሎ
እንደእኔ ልብ ይስጣት ብሎ?
ከሸሸም ይሁን ይሸሻል!
እኔ ግን ምን ያጓጓኛል?
ከመኖር ፍቅር አውድማ
ቢነግሩት ጆሮ ካልሰማ
ቢጠሩት እግር ከዛለ
መተውን ያህል ምን አለ?
By Sirak Wondemu
ባይፈካ - ንጋት ለአመሉ
ያምፃል ዝም ያለው ሁሉ
አይደለ? ወትሮስ ተረቱ
ይረጋል ? የፍጥረት ሞቱ?
ሰው ልቡ ቢያስበው ደጉን
ያመልጣል ስብራት ህጉን?
ይሸሻል ከሞት ድለቃ
ከመከራ ዶፍ ከዕድል ሰበቃ?
ይሸሻል በስሟ ምሎ
እንደእኔ ልብ ይስጣት ብሎ?
ከሸሸም ይሁን ይሸሻል!
እኔ ግን ምን ያጓጓኛል?
ከመኖር ፍቅር አውድማ
ቢነግሩት ጆሮ ካልሰማ
ቢጠሩት እግር ከዛለ
መተውን ያህል ምን አለ?
By Sirak Wondemu
❤19👍3🔥3👏2
ጋይስ 50k ገብተናል በጣም ነው ደስ ያልኝ እና እስኪ ባገልግሎቱ ላይ እንዲስተካከል የምትፈልጉትን ነገር comment sectionኑ ላይ ማስቀመጣቹን እንዳትረሱ በዛውም ቻናሉ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ የተለያዩ ኪነጥበብ ስራዎችን መልቀቅ የምትፈልጉ ከታች ባለው username አናግሩኝ
@abrex_1
@abrex_1
❤11
መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒 pinned «ጋይስ 50k ገብተናል በጣም ነው ደስ ያልኝ እና እስኪ ባገልግሎቱ ላይ እንዲስተካከል የምትፈልጉትን ነገር comment sectionኑ ላይ ማስቀመጣቹን እንዳትረሱ በዛውም ቻናሉ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ የተለያዩ ኪነጥበብ ስራዎችን መልቀቅ የምትፈልጉ ከታች ባለው username አናግሩኝ @abrex_1»
#ምስጋና_ቢስ_ፀሎት!
እዛ ጎዳናው ላይ ...
ስንኩል ሽባነቱን ለሰማይ የሚያሳይ
"እጅ ከሰጠኸኝ ልመና አቆማለሁ" ብሎ እየማለ
አብዝቶ የሚያለቅስ ፥ አንድ ለማኝ አለ።
እናም የዛ ለማኝ!
የኔ ቢጤን ፀሎት...
እግዜር ኖሮ ሰምቶት...
በጥልቅ እንቅልፍ ጥሎ እጅ አበጃጀለት
ላፈሰሰው እንባ ፣ ለጠለየው ፀሎት መልሱ ተላከለት።
ግን እርሱ ሲነቃ...
እጅ አገኘሁ ብሎ አላመሰገነም
ለገባው ቃልኪዳን
ለተሳለው ስለት ምላሽ አላኖረም
ዛሬም እንደ ፊቱ...
ዛሬም እንደ ትናንት ማልቀሱን አልተውም።
እንዲህ ሲል ቀጠለ...
"መንገድ ላይ ወድቄ
ተዘከሩኝ እያልሁ በስምህ ስጣራ
ጤነኛ ነው ብለው...
ፈራንካ ለመስጠት ሰው እንዳይኮራ
ይህን አስብበት ጌታ ሆይ አደራ!!
🔘ሚካኤል አስጨናቂ🔘
አመስጋኝ እንሁን ለማለት ነው
እዛ ጎዳናው ላይ ...
ስንኩል ሽባነቱን ለሰማይ የሚያሳይ
"እጅ ከሰጠኸኝ ልመና አቆማለሁ" ብሎ እየማለ
አብዝቶ የሚያለቅስ ፥ አንድ ለማኝ አለ።
እናም የዛ ለማኝ!
የኔ ቢጤን ፀሎት...
እግዜር ኖሮ ሰምቶት...
በጥልቅ እንቅልፍ ጥሎ እጅ አበጃጀለት
ላፈሰሰው እንባ ፣ ለጠለየው ፀሎት መልሱ ተላከለት።
ግን እርሱ ሲነቃ...
እጅ አገኘሁ ብሎ አላመሰገነም
ለገባው ቃልኪዳን
ለተሳለው ስለት ምላሽ አላኖረም
ዛሬም እንደ ፊቱ...
ዛሬም እንደ ትናንት ማልቀሱን አልተውም።
እንዲህ ሲል ቀጠለ...
"መንገድ ላይ ወድቄ
ተዘከሩኝ እያልሁ በስምህ ስጣራ
ጤነኛ ነው ብለው...
ፈራንካ ለመስጠት ሰው እንዳይኮራ
ይህን አስብበት ጌታ ሆይ አደራ!!
🔘ሚካኤል አስጨናቂ🔘
አመስጋኝ እንሁን ለማለት ነው
❤33👍4👏1
Forwarded from ፀዊረ መስቀል
05/12/2017
ሉቃስ 15:1-11
👉ቅዳሴ ዘእግዝእትነ አው ግሩም
ወትሠይመኒ ውስተ ርእሰ ሕዝብ
ሕዝብ ዘኢየአምር ተቀንየ ሊተ
ውስተ ምስማዐ ዕዝን ተሠጥዉኒ
የአሕዛብም ራስ አድርገህ ትሾመኛለህ
የማላቀው ሕዝብም ይገዛልኛል
በጆሮ ሰምተው ተገዙልኝ
ሉቃስ 15:1-11
ቀራጮችና ኀጢኣተኞችም ሊሰሙት ወደ እርሱ ይቀርቡ ነበር። ጻፎችና ፈሪሳውያንም፥ “ይህስ ኀጢኣተኞችን ይቀበላል፤ አብሮአቸውም ይበላል” ብለው አንጐራጐሩ። 'እንዲህም ብሎ መሰለላቸው። “ከእናንተ መካከል መቶ በጎች ያሉት ሰው ቢኖር፥ ከእነርሱ አንዲቱ ብትጠፋው ዘጠና ዘጠኙን በምድረ በዳ ትቶ እስኪ ያገኛት ድረስ ይፈልጋት ዘንድ ወደ ጠፋችው ይሄድ የለምን? በአገኛትም ጊዜ ደስ ብሎት በትከሻው ላይ ይሸከማታል። ወደ ቤቱም በገባ ጊዜ፥ ወዳጆቹንና ጎረቤቶቹን ጠርቶ፦ የጠፋችኝን በጌን አግኝቼአታለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ይላቸዋል። እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሓ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኙ ጻድቃን ይልቅ ንስሓ ስለሚገባ ስለ አንድ ኀጢኣተኛ በሰማያት ፍጹም ደስታ ይሆናል።
"ዐሥር ድሪም ያላት ሴት ብትኖር፥ አንዲቱ ብትጠፋባት መብራት አብርታ በቤቷ ያለውን ሁሉ እየፈነቀለች እስክታገኛት ድረስ ተግታ ትፈልግ የለምን? 'ያገኘቻት እንደሆነ ወዳጆችዋንና ጎረቤቶችዋን ጠርታ የጠፋችብኝን ድሪሜን አግኝቼአታለሁና፥ ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ትላቸዋለች። እላችኋለሁ፣ እንዲሁ ንስሓ ስለሚገባ ስለ አንድ ኀጢኣተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት በሰማያት፥ ደስታ ይሆናል........
2 ቆሮንጦስ 12:10-17
1 ዮሐንስ 5:14-ፍጻሜ
ሐዋ.ሥራ 15:1-13
👉ቅዳሴ ዘእግዝእትነ አው ግሩም
ምስባክ
መዝሙር ፲፯ :፵፫ – ፵፬
ወትሠይመኒ ውስተ ርእሰ ሕዝብ
ሕዝብ ዘኢየአምር ተቀንየ ሊተ
ውስተ ምስማዐ ዕዝን ተሠጥዉኒ
ትርጉም
የአሕዛብም ራስ አድርገህ ትሾመኛለህ
የማላቀው ሕዝብም ይገዛልኛል
በጆሮ ሰምተው ተገዙልኝ
❤8
Forwarded from ፀዊረ መስቀል
6/12/2017
ማርቆስ 16:9-19
👉ቅዳሴ ዘእግዝእትነ (ጐሥዐ) አው ዘ፫፻ (ግሩም)
ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ
ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር
ኵሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን
የጢሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መንሻን ይዘው ይሰግዱለታል
የምድር ባለጠጎች አሕዛብ ሁሉ በፊትሽ ይማለላሉ
ለሐሴቦን ንጉሥ ሴት ልጅ ሁሉ ክብርዋ ነው
ማርቆስ 16:9-19
በእሑድ ሰንበትም ማለዳ ተነሥቶ ሰባት አጋንንትን ላወጣላት ለማርያም መግደላዊት አስቀድሞ ታያት።
እርስዋም ሄዳ ከእርሱ ጋር ለነበሩት ሲያዝኑና ሲያለቅሱ ሳሉ ነገረቻቸው። እነርሱ ግን ሕያው እንደ ሆነ፥ ለእርስዋም እንደ ተገለጠላት በሰሙ ጊዜ አላመንዋትም።
"ከዚህም በኋላ፥ ከእነርሱ ለሁለቱ ወደ ገጠር ሲሄዱ በሌላ መልክ ተገለጠላቸው። "እነርሱም ደግሞ ሄደው ለባልንጀሮቻቸው ነገሩ፤ አነርሱንም ቢሆን አላመኑአቸውም። "ከዚህም በኋላ፥ ደግሞ ዐሥራ አንዱ በማዕድ ተቀምጠው ሳለ ተገለጠላቸው፤ እንደ ተነሣ ያዩትን አላመኑአቸውምና ስለ ሃይማኖታቸው ጕድለት ገሠጻቸው፤ የልባቸውንም ጽናት ነቀፈ።
እንዲህም አላቸው፥ “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ለፍጥረትም ሁሉ ወንጌልን ስበኩ። ያመነ የተጠመቀም ይድናል፤ ያላመነ ግን ይፈረድበታል። ” ይህችም ምልክት በስሜ የሚያምኑትን ትከተላቸዋለች፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋም ይናገራሉ። "እባቦችንም በእጃቸው ይይዛሉ፤ የሚጎዳቸውም ነገር የለም፤ የሚገድል መርዝ ቢጠጡም የሚጐዳቸው የለም፣ በድውያን ላይም እጃቸውን ይጭናሉ፤ ድውያኑም ይፈወሳሉ.....
1 ቆሮንጦስ 3:10-22
1 ጴጥሮስ 3:1-7
ሐዋ.ሥራ 16:13-19
👉ቅዳሴ ዘእግዝእትነ (ጐሥዐ) አው ዘ፫፻ (ግሩም)
ምስባክ
መዝሙር 44:12-13
ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ
ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር
ኵሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን
ትርጉም
የጢሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መንሻን ይዘው ይሰግዱለታል
የምድር ባለጠጎች አሕዛብ ሁሉ በፊትሽ ይማለላሉ
ለሐሴቦን ንጉሥ ሴት ልጅ ሁሉ ክብርዋ ነው
👍2❤1
የዕለቱ መልዕክት ቁጥር 1
✨
ስንደሰት ወደ አለም ስናዝንና ስንከፋ ደግሞ ወደ ቤተክርስትያን የምንመጣው ነገር ማብቃት አለበት።
ስናዝንም ስንደሰትም ወደ ቤተክርስትያን...❤️🩹
✨
ስንደሰት ወደ አለም ስናዝንና ስንከፋ ደግሞ ወደ ቤተክርስትያን የምንመጣው ነገር ማብቃት አለበት።
ስናዝንም ስንደሰትም ወደ ቤተክርስትያን...❤️🩹
❤15👍11🔥2🥰1
አንዳንዴ ገጣሚም ቃላት ይርቁታል
ደራሲም ሀሳቦች ይተናነቁታል
ሰአሊም አልሰምር ይሉታል እጆቹ
ተራኪም ይስታል ላፍታ በድምፀቱ
ሀኪምም እውቀቱ አልገለጥ ይላል
ሹፌርም መኪናው አልሄድም ይለዋል
ተርጓሚም መተርጎም ሲያቅተው ለአንዴ
ሯጩም ሲሸነፍ ከአንዴም ሁለት ሶስቴ
አስታራቂም ሳይችል ማስታረቅ ለሰዎች
ጥበብ ስትሸሸግ ተቀብራ ከአንዳንዶች
አስተወል ወዳጄ‼️⁉️
ባለህ አትመካ ሁሉም አላፊ ነው
ተጠጋ ከአምላክህ ዘመን ከማይሽረው
✍ብሩክ ተፈራ
ደራሲም ሀሳቦች ይተናነቁታል
ሰአሊም አልሰምር ይሉታል እጆቹ
ተራኪም ይስታል ላፍታ በድምፀቱ
ሀኪምም እውቀቱ አልገለጥ ይላል
ሹፌርም መኪናው አልሄድም ይለዋል
ተርጓሚም መተርጎም ሲያቅተው ለአንዴ
ሯጩም ሲሸነፍ ከአንዴም ሁለት ሶስቴ
አስታራቂም ሳይችል ማስታረቅ ለሰዎች
ጥበብ ስትሸሸግ ተቀብራ ከአንዳንዶች
አስተወል ወዳጄ‼️⁉️
ባለህ አትመካ ሁሉም አላፊ ነው
ተጠጋ ከአምላክህ ዘመን ከማይሽረው
✍ብሩክ ተፈራ
❤14👍9
Forwarded from ፀዊረ መስቀል
7/12/2017
ማቴዎስ 16:13-21
👉ቅዳሴ ዘእግዝእትነ (ጐሥዐ)
ብፁዕ ብእሲ ዘአንተ ገሠጽኮ እግዚአ
ወዘመርሀኮ ሕገከ
ከመ ይትገኀሥ እመዋዕለ እኩያት
አቤቱ አንተ የገሠጽኸው ሰው ብፁዕ ነው
ሕግህንም ያስተማርኸው
ከክፉዎች ዘመናት ይወገድ ዘንድ
ማቴዎስ 16:13-21
ጌታችን ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፥ “የሰውን ልጅ ሰዎች ማን ይሉታል?” ብሎ ጠየቃቸው። "እነርሱም፥ “መጥምቁ ዮሐንስ ነው የሚሉ አሉ፤ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ፥ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ” አሉት። "እርሱም፥ “እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?” አላቸው። "ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፥ “አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህ” አለው። ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፥ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ አንተ ብፁዕ ነህ፤ በሰማይያለው አባቴ ነው እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና። እኔም እልሃለሁ፤ አንተ ዐለት ነህ፤ በዚያች ዐለት ላይም ቤተ ክርስቲያኔን እሠራታለሁ፤ የሲኦል በሮችም አይበረታቱባትም። የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድርም የምትፈታው በሰማይ የተፈታ ይሆናል።” ከዚህም በኋላ እርሱ ክርስቶስ፤ እንደ ሆነ ለማንም እንዳይናገሩ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው...
እብራውያን 9:1-11
1 ጴጥሮስ 2:6-18
ሐዋ.ሥራ 10:1-30
👉ቅዳሴ ዘእግዝእትነ (ጐሥዐ)
ምስባክ
መዝሙር 93:12-13
ብፁዕ ብእሲ ዘአንተ ገሠጽኮ እግዚአ
ወዘመርሀኮ ሕገከ
ከመ ይትገኀሥ እመዋዕለ እኩያት
ትርጉም
አቤቱ አንተ የገሠጽኸው ሰው ብፁዕ ነው
ሕግህንም ያስተማርኸው
ከክፉዎች ዘመናት ይወገድ ዘንድ
❤11
Forwarded from ፀዊረ መስቀል
8/12/2017
ማቴዎስ 7:12-26
👉ቅዳሴ ዘእግዝእትነ (ጐሥዐ)
ወድቀት እሳት ወኢርኢክዋ ለፀሐይ
ዘእንበለ ይትዐወቅ ሦክክሙ ክክሙ ሕለተ ኮነ
ከመ ሕያዋን በመዓቱ ይውኅጠክሙ
እሳት ወደቀች፥ ፀሐይንም አላየኋትም
እሾኻችሁ ሳይታወቅ በትር ሆነ
ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ይውጣችኋል
ማቴዎስ 7:12-26
ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ኦሪትም፥ ነቢያትም የሚያዝዙት ይህ ነውና ።
በጠባቢቱ በር ግቡ፤ ወደ ጥፋት የምትወስድ ሰፊ በር፥ ሰፊ መንገድም አለችና፤ ወደ እርስዋም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው። "ወደ ሕይወት የምትወስደው በር እጅግ ጠባብ፥ መንገድዋም ቀጭን ናትና፤ የሚገቡባትም ጥቂቶች ናቸው።
“የበግ ለምድ ለብሰው ወደ እናንተ ከሚመጡ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ፤ በውስጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ናቸው። "ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ፤ ከእሾህ ወይን፥ ከአሜከላም በለስ ይለቀማልን? እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬን ያፈራል፤ ክፉ ዛፍም ክፉ ፍሬን ያፈራል። መልካምም ዛፍ ክፉ ፍሬን ማፍራት፥ ክፉ ዛፍም መልካም ፍሬን ማፍራት አይችልም። "መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል፤ ወደ እሳትም ይጣላል። “እንግዲህ ከፍሬያቸው ታውቋቸዋ ላችሁ።
“በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ ከሚያደርግ በቀር አቤቱ! አቤቱ! የሚለኝ ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። «በዚያች ቀን ብዙዎች አቤቱ! አቤቱ! በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል። ያንጊዜ ከቶ አላውቃችሁም፤ ዐመፅን የምታደርጉ ሁላችሁ ከእኔ ራቁ እላቸዋለሁ። ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዐለት ላይ የሠራ ብልህ ሰውን ይመስላል። ዝናም ዘነመ፤ ጐርፍም ጐረፈ፤ ነፋስም ነፈሰ፤ ያንም ቤት ገፉት፤ ነገር ግን አልወደቀም፤ በዐለት ላይ ተመሥርቶአልና.......
ሮሜ 9:24-ፍጻሜ
1 ጴጥሮስ 4:12-ፍጻሜ
ሐዋ.ሥራ 16:35-ፍጻሜ
👉ቅዳሴ ዘእግዝእትነ (ጐሥዐ)
ምስባክ
መዝሙር 57:8-9
ወድቀት እሳት ወኢርኢክዋ ለፀሐይ
ዘእንበለ ይትዐወቅ ሦክክሙ ክክሙ ሕለተ ኮነ
ከመ ሕያዋን በመዓቱ ይውኅጠክሙ
ትርጉም
እሳት ወደቀች፥ ፀሐይንም አላየኋትም
እሾኻችሁ ሳይታወቅ በትር ሆነ
ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ይውጣችኋል
❤11👍2
መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒
የዕለቱ መልዕክት ቁጥር 1 ✨ ስንደሰት ወደ አለም ስናዝንና ስንከፋ ደግሞ ወደ ቤተክርስትያን የምንመጣው ነገር ማብቃት አለበት። ስናዝንም ስንደሰትም ወደ ቤተክርስትያን...❤️🩹
የዕለቱ መልዕክት ቁጥር 2
✨
ነገ ተስተካክዬ እመጣለሁ አትበል !
ኃጢአትንም እየሠራህ ቢሆን እዛው ቤተክርስትያን ውስጥ ሆነህ ተስተካከል።
ወደ እግዚአብሔር መምጣትን የነገ ቀጠሯችን አናድርገው...🙏
✨
ነገ ተስተካክዬ እመጣለሁ አትበል !
ኃጢአትንም እየሠራህ ቢሆን እዛው ቤተክርስትያን ውስጥ ሆነህ ተስተካከል።
ወደ እግዚአብሔር መምጣትን የነገ ቀጠሯችን አናድርገው...🙏
👍14❤8🥰1