✝ ቻይ እና ትዕግስተኛ የሆነ ሰው ይጸልያል ስለሚሰጠውም የእግዚአብሔር መልስ አይጨነቅም ። እግዚአብሔር ጸሎቱን እንደሚሰማው እርግጠኛ ነው ። ሁሉም ነገር በእግዚአብሔር ጥበብና ፈቃድ እንደሚሆን በተገቢው ጊዜና መንገድ መልስ እንደሚሰጠው በማመን ለእግዚአብሔር ፍቅር ይተዋል ። አንዳንድ ሰዎች ይህ መሰል ትዕግሥት የላቸውም ። እግዚአብሔርን መውቀስ እና ከእርሱ ስሕተት መፈለግ እንጂ መጠባበቅ አይችሉም ። እርሱን ይወነጅሉታል እርሱ ግን እጅግ ይታገሳቸዋል ወቀሳቸውንም ይሸከማል ። እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔር ለእነርሱ እንደሚሰራ ማመን አለባቸው ።
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
@menfesawimeker
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
@menfesawimeker
(በቀሲስ ህብረት የሺጥላ )
#ከግብረ_አውናን_እንዴት_መላቀቅ_ይቻላል?
#ሀ. ግብረ አውናን እንደ ማር ጠብታ ነው ። የማር ጠብታ ልብስ ላይ የወደቀ እንደሆነ በፍፁም የሚለቅ አይመስልም ፣ ነገር ግን ትንሽ ለቅለቅ ያደረጉት እንደሆነ ወዲያውኑ ይለቃል። ይህ ክፋ ልማድም እንደማር በቀላሉ ባይሆንም ከልብ በመፀፀት በጠንካራ መንፈስ ከተነሱ ሊያስወግዱት ይቻላል። በመጀመሪያ የሚያስፈልገው ከዚ ነገር መቼም መላቀቅ አልችልም ብሎ ተስፋ አለመቁረጥ ነው ። ከፍተኛ ትግልና ጥረት ይጠይቃል ። ስለዚህ ተስፋ መቁረጥ ፈፅሞ አይገባም ።
#ለ. ልማድ ነው ። ልማድ ደሞ በሌላ ልማድ ይሸነፋል። ጠንክረህ ከተነሳህ ይህን ተግባር በትዝታ ብቻ የምታስብበት ቀን ሩቅ አይሆንም ። ነገር ግን ከዚህ ልማድ ጋር ለመዋጋት ከመነሳትህ በፊት "ይህን ክፋ ልማድ ምን ያህል ከልቤ ጠልቼዋለው ? " በማለት ራስህን ጠይቅ ። መላልሰህ የምትሰናከለው ሳትፀፀት ወይም ሴጋን መተው ስላልፈለክ ሳይሆን ጣዕሙ በልቡናህ ስላለና ጎጂነቱ ዘልቆ ወደልብህ ስላልገባ ነው ። ስለዚህ ይህን ነገር ከልብህ ልትጠላው ይገባል።
#ሐ. ይህን ክፋ ልማድ እንደ እሳት የሚያያይዙት የራስህ ተግባርና በዙሪያህ ያሉ ነገሮች ናቸው ። ከዚህ እኩይ ተግባር መላቀቅ ከፈለክ #ተዐቅቦ ያስፈልግሀል። #ተዐቅቦ ማለት መከልከል መቆጠብ ማለት ነው ። የምትከለከለውም ወደዚህ መጥፎ ሐሳብ ልቡናህን የሚስቡትን ነገሮች ከማየት ፣ ከመስማት፣ ከመንካትና ፣ ከመሳሰሉት ነው ። ስለዚህ የሴቶችን ገላ በፊልምም ፣ በአካልም ቢሆን በምንም መልኩ ከማየት ተቆጠብ። በመዋኛና በመጠመቂያ ቦታዎች ራስህን ጠብቅ የሴት ልጅን መልክና ቅርፅ መርዘህና አተኩረህ አትመልከት ። ስለ ዝሙት የሚያሳስቡ ሥዕሎችን፣ ፅሁፎችን፣ ወሬዎችን ፣ የሴት ገላ የሚያሳዩ የሙዚቃ ክሊፖችን ፣ የወሲብ ፊልሞችን አጥብቀህ ሽሻቸው ።ስራህ ሁሉ አንተው እያራገብክ ለምን ይቃጠላል ? እንዳይሆንብህ ።
#መ. ዘወትር ልቡናህ የሚጠመድበትን ነገር ፈልገህ አድርግ ። ቦዘኔ አትሁን ትጉህ ሰራተኛ ሁን ።ስራህም አይምሮህን የሚያሰራ ቢዚ የሚያደርግ ይሁን ። ትርፍ ሰአት አይኑርህ ። የሚነበብ ወይም ሌላ የሚሰራ ስራ ፈጥረህ ሥራ ።
#ሠ. "ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው " የሚለውን የወንጌል ቃል አስብ ። በዚህ ክፋ ልማድ ተጠምደህ ሳለ ለብቻህ መሆንን አትውደድ ። ቢቻልህ አኗኗርህና መኝታህ ከምታፍረውና ከምታከብረው ሰው ጋር ይሁን ። ይህም ጓደኛህ ወይም ከቤተሰብህ አንዱ ሊሆን ይችላል። በፀሎት ከሚረዱህ መንፈሳውያን መምህራን አባቶች ጋር ጊዜ ማሳለፍን ውደድ።
#ረ. እንቅልፍ የያዘህ ስለ መሰለህ ብቻ ወደ መኝታህ አትሂድ ። አንዳንዴ ተኝተህ ውለህ እንቅልፍ ያምርሀልና ። ነገር ግን ሰይጣን ሊፈትንህ ከሆነ በምትነኛበት ጊዜ እንቅልፍ ከአይንህ ይርቃል ። ተከትሎም ፈተናው ይመጣና ወደ ዝሙት ህሊናህ ይሳባል ። ከዛ ሴጋ ትፈፅማለህ። ስለዚህ ከመተኛትህ በፊት በደንብ መድከምህንና ቶሎ ማሸለብ መቻልህን መርምረህ ተኛ።
#ሰ. ጸሎት ማድረግንም አትርሳ የሚረሳ ነገር አይደለምና ። ስትተኛም በጀርባህ ወይም በሆድህ አትተኛ ። ከዚህ ይልቅ በጎንህ ለመተኛት ሞክር። አመጋገብህ በልክ ይሁን ፣ ፆምን ፁም ፣ ቅዱሳት መፃህፍትን አንብብ። መዝሙርንም አዳምጥ ዘምር
#ሸ. እንዲህ ያለ ፈተና ሲነሳብህ /አድርግ አድርግ ሲልህ / ከቻልክ ስገድ ።ወይም የሆነ እንቅስቃሴ /ስፖርት / ስራ ። ሽንት መሽናትም ጥሩ መፍትሄ ነው አይምሮህ ሽፍት እንዲያደርግ ያደርገዋል። በየጊዜው ፀበል መጠመቅን ቸል አትበል ። የሴት ገላን ሳታይ
#ቀ. ሰውነትህን አትነካካ ቢበላህ እንኳን አትከከው ። ስታክና ስትነካካው በዛው አድርግ አድርግ ሊልህ ይችላልና ። ንፁህ ሁን ፣ ሻወር ውሰድ ፣ ወክ አድርግ ፣ አንብብ ። ከምንም በላይ አጥብቀህ ፀልይ ። ሁላችንንም እግዚአብሔር ይርዳን ።
@menfesawimeker
ለ አስተያየት @menfesawimekerbot

ተወዳጅ ሆይ! ክርስቶስ ኢየሱስ እንዲህ ይልሃል፦
"✔አንተ ግን ለድኾች ምጽዋትን ትሰጣለህ፤ እኔም እጄን ዘርግቼ ካንተ እቀበላለሁ፡፡
✔ የታረዙትን በምታለብሳቸው ጊዜ እኔን ታለብሰኛለህ፡፡ ...
✔ የታሰሩትን በምታረጋጋቸው ጊዜ በመካከላቸው ኾኜ በዚያ ታገኘኛለህ፡፡
✔ በሽተኛውንም በምትጎበኘው ጊዜ ከእርሱ ጋር በአልጋው ላይ ኾኜ ዳግመኛ ታገኘኛለህ፡፡
✔ በቦታው ኹሉ የራቅሁ አይደለሁም፡፡ ትእዛዜን በምትፈጽምበት ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር እኖራለሁና ችግረኞችን የምረዳቸው እኔ ነኝና፤ ለድኾች የምታደርገው ኹሉ ለእኔ ማድረግህ ነው፡፡ እኔም በእርሱ ፈንታ በጎ ዋጋ እከፍልሃለሁና፡፡
✔ በቤትህ ውስጥ እንግዳ በአሳደርክ ጊዜ እነሆ ከእንግዳው ጋር በማደሪያህ አስገባኸኝ፡፡
✔ እንደዚህ ለሚያደርግ ቁጣዬ ከእርሱ ይርቃል፤ ወደ ሕይወት ወደብም አደርሰዋለሁ፡፡ ከክፉ ነገር ኹሉ እጠብቀዋለሁ፡፡ እባርከዋለሁ፡፡ ዘሩንም አበዛለሁ፡፡ ዋጋውንም በሰማይ ባለው በአባቴ ዘንድ ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ፡፡ ዘለዓለማዊ ዕረፍትንም እሰጠዋለሁ፡፡"
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ)

አንድ በምሽት አቅጣጫ የጠፋበት መርከብ ከሩቅ ያየ ሰው ወደ እቤቱ ገብቶ ሻማ ይለኩሳል
ሻማውም ለምን ለኮስከኝ ቢለው ሰውዬው ‹‹አቅጣጫ የጠፋው መርከብ ከሩቅ ያታየኛል
ለሱ በእሳት ልጠቁመው ነው ይለዋል ሻማውም ‹‹ታዲያ እኔ ሻማ ነኝ እንዴት ከሩቅ እታያለሁ›› ቢል ሰውዬውም መለሰ ‹‹ሻማዬ ሆይ አንተ ብቻ የቻልከውን ብራ›› አለውና ይዞት ይወጣና ብዙ ደረቅ እንጨቶችን እንደ ዳመራ ከቆለለ ቦሃላ በሻማው እሳት እንጨቶቹን ለኮሰ ብርሃኑም ብዙ ሆነ
ያኔ መርከቡም ተመልክቶ መጣ
ሰውዬውም ለሻማው እንዲህ አለው ‹‹ሻማዬ ሆይ አየህ አንተ በቻልካት መጠን ስለበራህ ያንተን ብርሀን ተቀብለው የሚያደማምቁ ብዙዎች አሉ›› አለው፡፡
እንግዲህ እንዲህ ነው የኔ ጥረት ትንሽ ናት አትበል፡፡ የቻልከውን ካደረክ ሌሎች ያንተን ብርሃን የሚቀበሉ እልፎች አሉ
‹‹የትም ሁን ማንም ሁን ያቅምህን በጎ ለማድረግ ግን አትስነፍ ደግነት
እንደ ጥሩ ሽቶ ነው ከአንዱ ተነስቶ ወደ አንዱ ይጋባል››
እንግዲህ አንዲህ ነው ለመስጠት የግድ ሃብታም መሆን
አይጠበቅብህም፡፡ ደግሞ ማንም ሰው ልስጥ ካለ የሚሰጠው አያጣም፡፡
#ተወዳጆች_ጥሩቀን ይሁንላችሁ
@Likukidusmikeal
@Likukidusmikeal
ለአስተያየትዎ :- @menfesawitemertochbot

.:
+ ኮሮና ሀገራችን ገባ! እኛስ ንስሓ ገባን??? +
አኹንስ እስክትሞት ነው የምትጠብቀው? አኹንስ ንስሓ አትገባም? እንዲኹ ተቀምጠኽ ከኾነ ምን ተስፋ አድርገኽ ነው የተቀመጥኸው?
እንደበፊቱ ፣ "መቼ እንደምንሞት አናውቅምና ንስሓ እንግባ" የሚለው ስብከት ፣ "መሞቻችን ቀርቧልና ንስሓ እንግባ" በሚል ይስተካከል! "ምነው?" ቢሉ ኮሮና ቤተሰብ ኾኗልና! በግለሰብም በተቋምም ደረጃ በሽታ በመከላከል አቅማቸው ከፍ ያለውን የቻይናን ሕዝብ እንደዛ የጨፈጨፈ ፣ እኛንማ እንዴት አብዝቶ አይጨፈጭፍን! ሲኾን ሲኾን በዕጥፍ በሦስት ዕጥፍ! እንከሰ ምንተ ንግበር? ራስን ከመጠበቅ ጋር ንስሓ እንግባ! ነገ ነገ የሚል ካለ ፣ በእውነት ከዚኽ በላይ አእምሮ ማጣት ወዴት አለ? ነገ ነገ ለሚለው ወዮ ወዮ ልንለት ይገባል! ነገ ነገ ሲል ኮሮና ከሲኦል ጋር ቤተሰብ ያደርገዋልና!
ዲ/ን ፡ ዳዊት ፡ ሰሎሞን።

#እጆትን_ታጥበዋል_?
በወረርሺኝ መልክ ተከስቶ ከፍተኛ የዓለም ስጋት የሆነውን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል መፍትሄ ተብለው ከተቀመጡ ነገሮች አንዱ እጅን መታጠብ ነው ። ንፅህና ጥሩ ነው መታጠብም መልካም ነው ። ነገር ግን እንደ ክርስቲያን ገዳይ የሆነውን #ኃጢአት ለመከላከልስ #በንስሐ ታጥበዋል ? ኮሮና በዓለም ብዙ ሰዎችን ገድሏል ። መፅሐፍ ቅዱስም ስለ ኃጢአት ሲናገር " እርሷ ወግታ የገደለቻቸው ብዙ ናቸው ይላል ። የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያና የተጠርጣሪዎች ለ14 ቀን ማቆያ ማዕከል ሁሉም ሀገራት አዘጋጅተዋል ። ቤተክርስቲያንም የኛ የሀጢአት ህመምተኞች መታከሚያ ሆስፒታላችን ነች ። ካህናት መርማሪ ዶክተሮቻችን ናቸው ።አንድ ወጣት ወደ አንድ መነኩሴ ዘንድ ይሄድና ስለ ፅድቅ ማወቅ እፈልጋለው ስለ ፅድቅ ንገሩኝ አላቸው ። ና ልጄ ውስጥ ሻይ እየጠጣን እናውራ ብለው ወደ ባዕታቸው ይዘውት ገቡ ።ከዛ ማንቆርቆሪያቸውን ጥደው ሻዩ እስኪፈላ መጠበቅ ጀመሩ ። ልጁም በሚገርም የወሬ ፍጥነት አባ ፅድቅ እንዲ ነው አይደል ፡አባ ንፅህና ቅድስና እንደዛ ነው አይደል ? ሰዎች እኮ ነግረውኛል እያለ ከሰዎች የሰማውን ይቀባጥራል ። መነኩሴውም ዝም ብለው ሲሰሙት ቆዩና ሻዩ ሲፈላ ብርጭቆ አምጥተው ይቀዱለት ጀመረ ። ብርጭቆው ሞልቶ እየፈሰሰም ዝም ብለው ይቀዳሉ ። ከዛ አባ ብርጭቆውኮ ሞልቷል አላቸው ። አንተ ለምጭምሩበት ሻይ ቦታ የለውም አላቸው ። መነኩሴውም አየህ ልጄ አንተም እንደዚ ብርጭቆ ነህ ። ስለ ፅድቅ ስለ ንፅህና ቅድስና ማወቅ ትፈልጋለህ ነገር ግን ልብህ ሌሎች በነገሩህ አሉባልታ ተሞልቷል እኔ የምነግርህን ነገር የምትቀበልበት ቦታ በልብህ ውስጥ የለም ። ብነግርህም ታፈሰዋለህ ። ስለዚህ አሁን ሂድ ልብህ ባዶ ሲሆን ተመልሰህ ና ያኔ እነግርሃለው አሉት። እኛስ ዛሬ ልባችንን የሞላው ምንድነው ? ፍቅር ? ሰላም ? መቻቻል ? ታምኝነት ፣ ህብረት አንድነት ነው ወይስ አስቀድሞ ልባችን በተንኮል ፣ በሟርት ፣ በቅናት፣በሴሰኝነት ፣ በዘረኝነትና በጎጠኝነት ስለተሞላ ለመልካም ነገሮች ቦታ የለውም ? እስቲ እራሳችንን እንፈትሽ ልባችንን ሞልቶት እየፈሰሰ ያለው ምንድነው ? ፅድቅ ነው ኃጢአት ? ስለዚህ ከነዚህ ሁሉ ነፍስን ከሚያጠቁ የሀጢአት ቫይረሶች በንስሐ እንታጠብ ፣ ድጋሚም በነዚህ የሀጢአት ቫይረሶች እንዳንጠቃ እራሳችንን እንጠብቅ። ሀጢአት የዘላለም ሞትን የሚያመጣብን ቫይረስ ነው ። ቡሃላ እሳቱ ወደ ማይጠፋበት ፣ ጨለማው ወደ ማይገፋበት ፣ ትሉ ወደ ማያንቀላፋበት ወደ ገሀነመ እሳት የሚጥለን #ሀጢአት ነውና በንስሐ ታጥበን ነፅተን መንግስተ ሰማይ ለመግባት ያብቃን

"ይህቺ ጥፊ የኔ ናት"
መነኮስ አባ አርሳንዮስ በገባበት ገዳም ዉስጥ፣ እግዚአብሔርን
እያገለገለ ሲኖር አንድ ቀን ከገዳሙ ሕግ ዉጭ የሆነ ነገር
ይፈጽማል፡፡ ጥፋቱ ከገዳሙ አበምኔት ይደርስና አበምኔቱ አስበዉ
ብገስጸዉ ያፍራል፣ ዝም ብል ጥፋቱ ጥፋት ሳይመስለዉ ሊቀር ነዉ
አሉና፡፡ የሱን ረድዕ ጠርተዉ እንዲህ አሉት፡፡ "አርሳንዮስ ያጠፋዉን
ጥፋት እኔ እያየሁህ በእርሱ ፊት አንተ አጥፋ ከዛ በጥፊ
እመታሃለሁ፡፡ ያኔ እርሱ በአንተ ጥፊ ይማራል አሉት፡፡"
እንደተመካከሩት በአርሳንዮስ ፊት ረድኡ የእርሱን ጥፋት አጠፋ
አበምኔቱም ተቆጥተዉ በጥፊ መቱት በዚህ ጊዜ ነገሩን የተከታተለዉ
አርሳንዮስም "ይህች ጥፊ የኔ ናት" ብሎ ተናገረ፡፡
እግዚአብሔር እኛን ባጠፋነዉ ቅጣት የግድ እስከሚቀጣን ቁጭ
ብለን መጠበቅ የለብንም ፣ከሌላዉ ጥፋት፣ ከሌላዉ ቅጣት መማር
አለብን፡፡ ከሌላዉ ጥፋት መማር ትልቅ ዕዉቀት፣ ታላቅ ማስተዋል
ነዉ፡፡ አርሳንዮስ ጓደኛዉ በጥፊ ሲመታ፣ ይች ጥፊ የኔ ናት አለ እንጂ
ባጠፋዉ ጥፋት ነዉ የተቀጣዉ ብሎ አልፈረደበትም፡፡ እኛም ቁጣ፣
መቅሰፍት፣ እኛ ጋር እስኪመጣ መጠበቅ የለብንም ከጓደኞቻችን
ከጎረቤቶቻችን በሌላም ሀገር ከምናየዉ ከምንሰማዉ ተምረን ንስሓ
መግባት አለብን ጾም ማለትም ይህ ነዉ፡፡ ንስሐ የምንገባዉም
ኃጢአታችንን ስናስተዉል ነዉ፡፡ ማስተዋል ከሌለን ኃጢአቱን እንደ
ጽድቅ ቆጥረን ለንስሐ አንበቃም፡፡
ማስተዋልን ገንዘብ ያደረገ ምዕመን በሌላ ላይ የተደረገ ቅጣት
በርሱ ላይ እንደመጣ ይጠነቀቃል፡፡ እንደ ርግብ የዋህ እንደ እባብ
ብልህ በመሆን የነገሮችን ሁኔታ በማስተዋል ይከታተላል፡፡ ከሰብአ
ትካት ከሰዶም ይማራል ሎጥ የዳነበትን መንገድ ይከተላል ቃሉን
በመስማት በኖህ መርከብ በተመሰለች ቅድስት ቤተክርስቲያን
ይገኛል እራሱን በንስሐ በሥጋ ወደሙ በጸሎት በእግዚአብሔር
ቸርነት ከሚመጣዉ መቅሰፍት ያድናል፡፡
የአባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን አሜን፡፡
⛅⛅⛅⛅⛅⛅⛅⛅⛅
@menfesawimeker
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

ከኮሮና ቫይረስ ወይስ ከሞተ ነፍስ እራሳችንን እናድን?
በቀሲስ መምህር ሄኖክ ወልደ-ማርያም
ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያዳርሱ
ተወዳጆች ሆይ ዓለምን ያንቀጠቀጠ፣ በቻይና ሃምሳ ሚሊዮን ሰዎችን ከቤት ያስቀመጠ፣በአውሮፓ ሚሊዮኖችን ከቤት ያስደፈጠ ከሕክምና እና ከሰው ልጆች የእውቀት ልዕልና በላይ የሆነው ኮሮና ቫይረስ የሁላችንም ስጋት ሆኗል፡፡
ወዳጆቼ ብዙዎቻችን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለሚመጣው ሥጋ ሞት እንደተጨነቅን ለሞተ ነፍሳችን አልተጨነቅንም፡፡ ካወቅንበት ይህ ወረርሽን ከዓለም የሚያርቀን ከእግዚአብሔር በንስሐ የሚያስታርቀን ነው፡፡ በቻይና በጣልያን በተለያዩ ሀገራት በወረርሽኙ የሞቱት ሰዎች ወገኖቻችን ናቸው፡፡ የእነሱ ሞት የሚያሳዝነው ሞተ ነፍስንም ስለሚሞቱ ነው፡፡ ሞትን ክፉ የሚያደርገው በነፍስ ሲሞት ነው፡፡
ፈረንጆቹ በራሳቸው የተመኩ፣እግዚአብሔርን በእውቀታቸው የተኩ ቢሆንም ዛሬ እውቀታቸው፣መድኃኒታቸው ለኮሮና ቫይረስ ፈውስ መሆን አልቻለም፡፡ በሥጋዊ እውቀታቸው፣በሠራዊት ብዛታቸው፣በተምዘግዛጊ ሚሳኤል ጥራታቸው፣በአውዳሚ ቦንብ ትምክታቸው የሚመኩ ኃያላን ዛሬ ከኮሮና ቫይረስ በታች ሆነዋል፡፡ ዓለምን ያንቀጠቀጡ ኃያላን ዛሬ በኮሮና ቫይረስ እየተንቀጠቀጡ ናቸው፡፡ ፈጣሪን የማያውቁ፣የማያመልኩት ዛሬ ሕዝባቸውን ጸልዩ፣ዓለምን ጸልዩልን ማለት ጀመሩ፡፡ ሁሉንም የሰጣቸውን ፈጣሪ ትተው፣የሥጋ እውቀታቸውን ተከትለው እንዳልኖሩ ዛሬ ወረርሽኝ የቁምና የቤት እስረኛ አደረጋቸው፡፡
ተወዳጆች ሆይ በሕክምና ባለሞያዎች መጠንቀቅ እንዳለብን ቢነገረንም ስንቶቻችን ነን ለነፍሳችን የተጠነቀቅነው? ይህ መቅሰፍት የሆነ ወረርሽኝ በሥጋ ገድሎን፣በነፍሳችን ሲኦል ዶሎን የሁለት ዓለም ስደተኞች እንዳያደርገን ለክፉም ለደጉም ንስሐ ገብተን፣ከፈጣሪ ታርቀን የሚመጣውን በጸጋ ለመቀበል ዝግጁ መሆን ይገባናል፡፡
አሁን ያለንበት ዘመን በመጽሐፍ ቅዱስ እና በአባቶች ሲነገር የነበረው ትንቢት ተፈጽሟል፡፡ ስለዚህ መፍራት ያለብን በኮሮና ቫይረስ ስለሚመጣ የሥጋ ሳይሆን ሞተ ነፍስን ነው፡፡ እግዚአብሔር ‹‹እንግዲህ ንስሐ ግባ፤አለዚያ ፈጥኜ እመጣብሃለሁ፣በአፌም ሰይፍ እዋጋሃለሁ›› ብሏል፡፡ /ራዕ 2÷16/ ይኸው እንዳለው ንስሐ ሳንገባ ግራ ስንጋባ እግዚአብሔር በአስደንጋጭ፣በአቋራጭ መንገድ በወረርሽን መጣብን፡፡ ‹‹በአፌ ሰይፍ እዋጋሃለሁ›› እንዳለን አሻናፊ፣መካች በሌለው በሽታ የሞት ሰይፍ መዞ መጣብን ተዋጋን፡፡ ‹‹ንስሐ ባትገባ መቅረዝህን ከስፍራው እወስዳለሁ›› እንዳለ ለሥጋን መብራት እና ሕይወት የሆነችውን መቅረዝ ነፍሳችንን በሞት ሳይወስድብን ንስሐ እንግባ፡፡ /ራዕ 2÷5/
የተጣላን እንታረቅ፣የቀማን፣የሰረቅን እንመልስ፣የበደልን እንካስ፣ቂም የቋጠርን ቂሙን ከልባችን ከነሰንኮፉ አውጥተን እንጣላ፡፡ አሁን ጊዜው በብሔር የምንቧደንበት በዘር የምንናቆርበት ሳይሆን ስንሐ ገብተን ማረኝ፣ማረኝ የምንልበት ጊዜ ነው፡፡ ግን ልባችንን አደንድነን፣በሥጋ በነፍስ ተዘናግተን እያሾፍን፣እያላገጥን ከሄድን ሳንጠራው የመጣው የኮሮና ቫይረስ ለካህናት ኃጢአታችንን የምንናዘዝበት ጊዜ አሳጥቶ በሞት ጎትቶ መውሰዱ አይቀሬ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ለዕብራውያን ሰዎች ‹‹በእንባ ተግቶ ምንም ቢፈልገው ለንስሐ ስፍራ አላገኘም›› ያለው በእኛ ትንቢት ሆኖ እንዳይፈጸም ያሰጋል፡፡ /ዕብ 12÷17/ ቢያንስ ንስሐ ገብተን የፈለገው ቢመጣ፣ ሞት ቢቃጣ ከሞት በኃላ የነፍስ ዘላለማዊ ሕይወት ስላለን በሁለቱም አንጎዳም፡፡
ወዳጆቼ የእኛ መንግስት እንደሆነ ወረርሽኙን በግድ እስኪመስል ድረስ አምጥቶ እንኩ ለሞት ያለን ነው የሚመስለው፡፡ ቻይናውያንን በሳምንታት ውስጥ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩትን ቫይረሱ ሲይዛቸው እኛ ሀገር ለጥርጣሬ በሚያጋልጥ መልኩ በሁለት በሦስት ቀን አንድ ሰው ተገኘበት እያሉ በሞት እየቀለዱ ስለሆነ ንስሐ ገብቶ ተዘጋጅቶ የፈጣሪን ምህረት መጠበቁ አዋጪ ነው፡፡ እርግጠኛ ነኝ ከጥቂት ቀናት በኃላ አኃዙ አሻቅቦ፣ብዙ ቁጥሮችን አንግቦ መምጣቱ አይቀርም፡፡ ብቻ ንስሐ ገብቶ አድነኝ ማለቱ ይመረጣል፡፡
ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችንን በደብረ ዘይት ስለ እለተ ምጽዓት ምልክት በጠየቁበት ጊዜ ምልክቱና የምጥ ጣር መጀመርያ ተደርጎ ከተነገራቸው አንዱ ቸነፈር ነው፡፡ ይህንንም ጌታችን ‹‹ራብም ቸነፈርም የምድር መናወጥም በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል›› ብሏቸዋል፡፡ /ማቴ 24÷7/ እዚህ ላይ ልብ ልትሉት የሚገባው ‹‹ቸነፈር›› የሚለውን ዘርጋው ከፍተኛ የአማረኛ መዝገበ ቃላት ‹‹አጣዳፊ መቅሰፍት፣ተላላፊ በሽታ፣ተስቦ፣ ወረርሽኝ፣እልቂት፣መቅሰፍት›› ብሎ ይተረጉመዋል፡፡ ስለዚህ ጌታችን ‹‹ቸነፈር በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል›› ብሎ ከዛሬ ሁለት ሺህ ዓመታት በፊት በቅዱሳን ሐዋርያት በኩል ለእኛ የተናገረው የእለተ ምጽዓት ምልክት በዘመናችን ተፈጽሞ ይገኛል፡፡ ቸነፈሩም በልዩ ልዩ ስፍራ ሰዎችን ለመግደል እየተንጠራራ ነው። ጠቢባኑ ሳይንሳዊ ስም ሰጥተውት ኮሮና ቫይረስ ይበሉት እንጂ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ቸነፈር›› ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ቸነፈር መደናገጥ ሳይሆን ንስሐ ገብተን ከኃጢአት ተላቀን ልንለወጥ ይገባናል፡፡ ይህ ላወቀበት የማንቂያ ወደል ነው፡፡ ከዚህም የባሰ ሊመጣ ስለሚችል በንስሐ ሕይወታችን መቅሰፍቱን መልሰን ከፈጣሪ ታርቀን የኢትዮጲያን ትንሳኤና ደጉን ዘመን ለማየት ያብቃን፡፡ ስለዚህ በንስሐችን ከኮሮና ቫይረስ ብቻ ሳይሆን ከሞተ ነፍስ ለመዳን የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይርዳን!
መጋቢት 16/7/12 ዓ.ም
አዲስ አበባ

በመተያየት መጽናናት
መተያየት ያፀናል ያጽናናል፡፡ ጳውሎስ የቁም እስረኛ ሆኖ ወደ ሮም ሲወሰድ በመንገድ ላይ ክርስቲያኖችን አየ፡- “ጳውሎስም ባያቸው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገነ ልቡም ተጽናና” ይላል (የሐዋ.ሥ. 28 15)፡፡ ጳውሎስን የሚያህል ሐዋርያ በማየት ከተጽናና እኛማ እንዴት!? ክርስቲያን ሲገናኝ ምንም ባያደርግም በመተያየቱ ብቻ የሚያገኘው መጽናናት አለ፡፡ መጽናናት ከችግሩ በላይ በሆነ ምክንያት መደሰት ነው፡፡ ወይም መከራው እያለ ከመከራው በላይ በሆነ ምክንያት ማረፍ ነው፡፡ ይህም ብቻ አይደለም መጽናናት በእሳት ውስጥ ያለ ገነት ነው፡፡ ጳውሎስ ሰንሰለቱ በእጁ አለ፣ ነገር ግን ተጽናና፣ ክሱ አልተለወጠም፣ ነገር ግን ተጽናና፡፡ እግዚአብሔር የሚያጽናናን ችግሩን በማስወገድ ብቻ ሳይሆን ችግሩ እያለም ደስታን በመስጠት ያጽናናል፡፡ ችግሩን ስናይ እግዚአብሔር ይሰወርብናል፣ እግዚአብሔርን ስናይ ደሞ ችግራችን አንሶ እንበረታን፡፡ አንዳችን ለአንዳችን መጽናኛ አድርጎናልና እባካችሁ እንተያይ፣ ኅብረት እናድርግ፡፡
"ትጸኑ ዘንድ መንፈሳዊ ስጦታ እንዳካፍላችሁ ላያችሁ እናፍቃለሁና፤"
ሮሜ 1:11

‹በእግዚአብሔርን በሚያምን ሁሉ አጠገብ ጠባቂ መልአኩ አለና ስለዚህ ንስሐ ይግባ› በማለት ከንስሐ ሕይወት ጋር አያይዞ ያሳስበናል፡፡ ሊቁ ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያም ሰው ብቻውን ሆኖ እንኳን ቢጸልይ ጠባቂ መልአኩ ከእርሱ ጋር አብሮት እንደሚሆን የሚናገር ሲሆን ፤ ሊቁ ጠርጠሉስም ብዙውን ጊዜ በምንዘናጋበት በግል ጸሎታችን ጊዜ አብሮን ለምስጋና ከሚቆመው መልአክ ክብር የተነሣ መቼም ቢሆን ቁጭ ብለን እንዳንጸልይ ይመክራል፡፡
አበው ቅዱሳን እንደሚያስተምሩት ጸሎት እና ቃለ እግዚአብሔርን ከሚወድ ሰው ጋር እኒህ ጠባቂ መላእክት ዘወትር የማይለዩ ቢሆንም ፤ ኃጢአትን ባደረገ ጊዜ ግን ከእርሱ ያርቃቸዋል፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ‹በክፉ ሥራዎቻችን እስካላሸሸናቸው ድረስ መላእክት ከእኛ መቼም ቢሆን አይርቁም፡፡ ጭስ ንቦችን ፣ክፉም ሽታ ርግቦችን እንደሚያባርር እንዲሁ የሚከረፋው ኃጢአታችን ሕይወታችንን የሚጠብቁትን መላእክት ያርቃቸዋል› ሲል መልካሙን ባለማድረግ በኃጢአታችን ክፉ መዓዛ ጠባቂ መላእክቶቻችንን እንዳርቃቸው ያስጠነቅቀናል፡፡ ገነተ አበውም (Paradise of the holy fathers) ላይ አንድ የበቃ የእግዚአብሔር ሰው ያየው ራእይ ይህን በመሰለው ጉዳይ በቂ ዕውቀት የሚያስጨብጠን ነው፡፡ ‹በአንድ ወቅት አበው መነኮሳት ተሰብስበው ስለ ምናኔ ሕይወት መልካምነት ሲወያዩ ሳለ ከመካከላቸው ከነጽሮት (መላእክትን ከማየት) የደረሰ አንድ አረጋዊ ፤ ቅዱሳን መላእክት እኒህን አባቶች ረበው ሲበሩ ተመለከተ፡፡ ነገር ግን ወደ ሌላ ከንቱ ርእስ (ሥጋዊ) በተሸጋገሩ ጊዜ ዓሣሞች በዙሪያቸው ከበዋቸው በአረንቋ (ጭቃማ) ላይ ሲንከባለሉ ታየው፡፡ ዳግመኛም እኒሁ አባቶች ጨዋታቸውን ወደ መንፈሳዊ ወግ በማምጣት ባደሱት ጊዜ መላእክቱ ተመልሰው እግዚአብሔርን ሲያከብሩ ተመልክቷል›፡፡
በጣም በሚያስደንቅ ሁኔታ ክፉ በሠራን እና በአምላካችን ላይ ባመጽን ጊዜ የሚሸሹን መላእክት ወዴት ይሄዱ ይሆን? ብለን ከጠየቅን መጽሐፈ መነኮሳት ይመልስልናል፡፡ ተጠባቂው ሰው ጌታውን በምግባር አሳዝኖ ፣በሃይማኖት ክዶ የሆነ እንደሆነ ዑቃቢ መልአኩ ከእርሱ ይሸሽና ሌላ አንድን ጻድቅ ወደሚጠብቅ ወዳጁ መልአክ ፍቅሩ ስቦት ይሄዳል፡፡ ይህንንም ከሦስቱ መጻሕፍተ መነኮሳት አንዱ የሆነው ማርይስሐቅ ‹ያንዱ መልአከ ዑቃቢ ወዳንዱ የሄደ እንደሆነ ፤ያንዱ መልአከ ዑቃቢ ተከትሎት ይሄዳልና ‹እስመ በአሐዱ ፍቅር ይሰሐብ ካልዑ›/‹በአንዱ ፍቅር ሁለተኛው ይሳባል› እንዲል› በማለት ይገልጸዋል (ማርይስሐቅ. ገጽ 35)፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር ጠባቂ አድርጎ የሰጠን መላእክቶቻችን እንዳያዝኑብን እንጠንቀቅ፡፡ የኃጢአታችንም ክፉ ሽታ እንዳያርቃቸው በንስሓ እንባ ነፍሳችንን እንጠብ፡፡
ቀደምት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት በተለይ እንደነ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ነባቤ መለኮት፣ ቅዱስ አውግስጢኖስ ያሉ አባቶች ከሰው ልጆችም ውጪ እንደ ነፋስ፣ እሳት፣ ውኃና ሌሎችንም ፍጥረታት የሚጠብቁ መላእክት እንዳሉ በዮሐንስ ራእይ ላይ የተጠቀሱትን ‹የውኃውም መልአክ›፣ ‹አራት መላእክት አየሁ እነርሱም…አራቱን የምድር ነፋሳት ያዙ›፣ ‹በእሳትም ላይ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ› የሚሉትን የመጽሐፍ ክፍሎች በመጥቀስ ያስተምራሉ(ራእይ 7:1፣ 14:18 ፣ 16:5)፡፡ ለአገርም (ሕዝብ) ቢሆን ጠባቂ መልአክ እንደሚሾም ‹ሚካኤል አንተ ለያዕቆብ ኖላዌ ዘርዑ› ‹ለያዕቆብ እና ለዘሩ ጠባቂ (እረኛ) ሚካኤል አንተ ነህ› የሚለው ቃል የሚያስረዳን ሲሆን አንድ ሊቅ ደግሞ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ላይ ያለውን ለቅዱስ ጳውሎስ በራእይ በመቄዶንያ ሰው አምሳል ተገልጦ ‹ወደ መቄዶንያ ተሻገርና እርዳን› ያለውን መልአክ የመቄዶንያ ሀገር ጠባቂ መልአክ (shepherd angel) እንደሆነ ይናገራል (ሐዋ 06.9)፡፡ ታዲያ በዚሁ ተመሳሳይ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ላይ ፊሊጶስን ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚወስደው መንገድ ላይ ኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ እንዲያገኘው የነገረው መልአክ የኢትዮጵያ ሀገር (ሕዝብ) ጠባቂ መልአክ ይሆንን? (ሐዋ 8:26)::

#በገነት_ያሉ_ሦስት_አስደናቂ_ነገሮች!
አንድ አረጋዊ አባት በስጋ ሞተው ወደ ገነት ከገባ በሁዋላ ለሌላ አባት በሕልም እንዲህ ሲል ነገረው:- "ወደ ገነት በገባሁ ጊዜ ሦስት ነገሮች አስደነቁኝ
#የመጀመሪያው
ገነት ውስጥ ይገኛሉ ብዬ ፈጽሞ የማልጠብቃቸውን፣ በእኔ ዓይን ኃጢአተኞች የሆኑ ሰዎችን በገነት ውስጥ ማግኘቴ ነው።
#ሁለተኛው
በገነት እንደሚኖሩ በእርግጠኝነት የምገምታቸውን ጻድቃን መስለው የታዩኝን ሰዎች በገነት ውስጥ አለማግኘቴ ነው።
#ሦስተኛውና
ከሁሉም በላይ ያስደነቀኝ ግን እንደ እኔ ዓይነቱን እጅግ ኃጢአተኛ ሰው በገነት ውስጥ ማግኘቴ ነው" አለ!!
☨
እውነት ነው በሰው ፊት ፈሪሳዊው ጻድቅ ሲሆን ቀራጩ ደግሞ ኃጢያተኛ ነው። ነገር ግን እውነታው የተገላቢጦሽ ነበር (ሉቃ ፲፰፥፱-፲፬)።
"ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፡— እውነት እላችኋለሁ፥ ቀራጮችና ጋለሞቶች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት ይቀድሙአችኋል" (ማቴ ፳፩÷፴፩)
ስንቶቻችን በዓይናችን እየፈረድን ስንቱን አፅድቀን፤ ስንቱን ኮነንን? አምላክ ሆይ ማረን!
"እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፦ ፊቱን የቁመቱንም ዘለግታ አትይ፤ ሰው እንዲያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል አለው።" ፩ኛ ሳሙ ፲፮÷፯
📢
"#ብልህ_ሰው_ክፉን_አይቶ_ይሸሸጋል፤
#አላዋቂዎች_ግን_አልፈው_ይጐዳሉ።"
መጽሐፈ ምሳሌ ፳፪÷፫
#ፆምን_ቀድሱ
⛅
ልመናዋ ክብሯ የልጇም ቸርነት በእኛ ለዘልዓለሙ በእውነት ይደርብን።

🗒 አንዳንዴ እኛ መልካም ነገሮች ወደ ሕይወታችን ማምጣት እንፈልጋለን እነኛን መልካም ነገሮችን ለማስተናገድ የሚሆን መልካምነት ግን እኛጋ የለም ። እኛ ቁምነገረኛ ሳንሆን ቁምነገረኛ የሕይወት አጋር የምንፈልግ ብዙዎች ነን! ነገሮች ከኛ መጀመር እንዳለባቸው በራሳቸው ወደኛ ከመጡም መልካም ነገሮችን በመፍጠር ከኛ ጋር የሚሆኑበትን መንገድ ለመክፈት ቁልፉ በኛ እጅ መሆኑን አንዳንዴ እንዘነጋዋለን ። ይሄንን ያመጣው ከራሳችን የመስጠት ሳይሆን ከሰው ብቻ የመጠበቅ ፍላጎትን ብቻ የማድመጥ አባዜአችን አይመስላችሁም ?
🗒 " መልአክ የሆነ ጓደኛ ከፈለግህ ማረፊያውን ገነት ልትፈጥርለት ይገባል ምክንያቱም መልአክ ሲኦል ውስጥ አይቀመጥም "
... ብሎ ነበር አንድ ሥሙ ያልታወቀ ጀርመናዊ የካቶሊክ ጳጳስ...አንዳንዴ መነሻው እኛ መሆናችንን መዘንጋት የለብንም እኛጋ መልካምነት ሳይኖር ግን መልካም ነገር በኛ ሕይወት እንዲገጠር የምንፈልግ ስንት ራስ ወዳዶች በየቤቱ እንኖር ይሆን...? ስንቶቻችን ውስጣችን ነዲድ እሳትን ተላብሶ መልካም እሳቤዎችን አቃጥሎ ይሆን...?
ምላሹን ለህሊናችን...

ፈርቶ ከመኖር አምኖ መሞት ታላቅ ዋጋ አለው!!!
ሁሉም ሊሆን የሚችልባት ጠፊ ዓለም ላይ ነው ያለነው። በፍርሀት ሳይሆን በብልሀት እንኑር። በማመን አምነን መኖር ስንችል መቅሰፍት እረፍት አይነሳንም። ቀደም ሲልም ቀደምት አባቶች በእምነታቸው እንጂ በዓለማዊ ጥበብና ዕውቀታቸው ወንዙን አልተሻገሩም። መንፈሳዊ ጥንካሬአችን ከመዓቱ ይሰውረናል። የትኛውም ዕውቀት እምነትን አይበልጠውም። ከተራቀቁት ይልቅ ያመኑት ድነዋል። ለማያምን ፍርሀትና ስጋቱ ለሞቱ ምክንያቱ ይሆናል። ስጋት ብልሀትን አጨንግፎ በቁምም አበድኖ ለሞት አሳልፎ ሰጪ ነው። የሰው ልጆች ነንና ታላላቅ ፈታኝ ፈተናዎችን እንጋፈጣለን። ፈለግንም አልፈለግን በፈተና መፈተናችን አይቀርም። ነገር ግን የሕይወትን ትግል እምነት ድል ይነሳዋል።
ፈተናዎቻችን የጥንካሬአችን ማሳያዎች ናቸው። ከፈተናችን መጠንከር ይልቅ የእምነታችን መላላት በቁም ይጨርሰናል። አንፍራ ... መሬት ላይ ሁሉም ሊሆን ይችላል። የሚሆነው ሁሉ ግን አያሸንፈንም። አንጨነቅ ... ብንወድቅም እየተነሳን ብንሞትም እየተተካካን ሕይወት ትቀጥላለች። ብዙ ዳዴ ብለን የቆምን ሕዝቦች ነን። በምድር ላይ ሳለን የማይሆን አይኖርም። የሚሆነው ሁሉ ቢሆንም ግን እንድንገዳገድ እንጂ እንድንወድቅ የማያደርገን እምነት አለን። ፈጣሪ የምንማርበትን እንጂ የምንማረርበትን መከራ አይሰጠንም። በበርካታ ጭንቆች ውስጥ አልፈን በደስታ የኖርንበትን ዘመናት አንርሳ። ፈጣሪ ልክና አቅማችንን ያውቃልና በማይመጥነን ሚዛን አይመዝነንም። ለእኛ ከእኛ በላይ የሚያውቅ አምላክ አለና አንሰጋም! በእምነታችን ነፃ እንደምንወጣ አንጠራጠር። በፍርሀት የምንጨርሰውን ጊዜ ለፀሎቱ እናውለው።
አዎን አንስጋ ... ፍርሀታችን ዕድሜአችንን እንዲያሳጥር ጉልበት አንስጠው። በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ወደ ብርሃን እንድንሻገር ሀይል እየሰጠ ያኖረን አምላክ አለ። በሚያናውጥ ማዕበል ውስጥ ያለአንዳች እክል በምቾት ጠብቆ ወደ ድሎት የሚወስደን ፈጣሪ ከእኛ ጋር ነው። ኢትዮጵያን የታመነችው አምላኳ አይተዋትም። ሰውን ተከትለን ሳይሆን ፈጣሪን አምነን ወጀቡን እናልፋለን። ታሪክ ቀያሪ አምላክን አምነን ታሪካችን አይበላሽም። ጭንቀት ሞትን ይጠራል። ስለፈራንም ስጋታችን አይቀንስም። በእምነታችን ፀንተን በፀሎታችን ተግተን ደጉን ጊዜ እንጠብቅ። ፈጣሪን የፈሩ ትውልዶች መከራውን ሁሉ በድል ይሻገሩታል! አምላክ ሀገራችንን ብቻ ሳይሆን ዓለማችንንም ይጠብቅልን!!!
በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኩዝህ እነርሱ ያፅናኑኛል። መዝሙረ ዳዊት 23 : 4
ፈጣሪ ከውዶቻችን አይነጥለን! በፍቅር እና በምህረቱ ያቆየን!
♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️
@menfesawimeker
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
አሁንም ለ ጥያቄያችሁ
@menfesawimekerbot ይጠቀሙ

# ሳሙና የሚገድለው በሽታ ቤተ ክርስቲያንን
አዘጋ!
ሙት ያስነሳው የኤልያስ አምላክ ሆይ ወዴት
አለህ?
ከሞተ በሇላ በአጽሙ ሙት ያስነሰው የኤልሳዕ
አምላክ ሆይ ለምን ዝም አልክ?
ባህር የከፈለው የሙሴ አምላክ ሆይ ወዴት
ነህ?
በእጣኑ በሽታን አርቆ ምሙማንን የፈወሰው
የአሮን አምላክ ሆይ ለምን ዝም አልክ?
ፀሐይን ያቆመው የኢያሱ አምላክ ሆን ለምን
ተውከን?
ጣቢታን ከሞት ያስነሳው የጴጥሮስ አምላክ ሆይ
ወዴት ነህ?
በቤተ መቅደሱ በር ድውያንን የፈወሱ የጴጥሮስ
የዮሐንስ አምላክ ሆይ መቅደስህ ሲዘጋ ለምን ዝም አልክ?
በልብሳቸው ድውያንን የሚፈውሱ በጥላቸው
ምህረትን የሚያመጡ የቅዱሳን አምላካቸው ሆይ
ተለመነን
የነቢያት አምላካቸው ምህላችን ስማን
የሐዋርያት አምላካቸው ጸሎታችን ከፊትህ
ትድረሰን
የሰማእታት አምላካቸው ስለእነሱ ብለህ ራራልን
በቃል ዐላዛርን ጠርተህ ከሞት ያስነሳሀው
የአላዛር አምላክ ሆይ ሞትና ህማም በአንተ
ዘንድ ኢምንት ናቸውና እባክህ እንደክፋታችን
አትክፈለን
በዘመነ ሰማእታት በከሀድያን ነገስታት ቤተ
ክርስቲያን ተዘግታ ነበር
ዛሬ ደግሞ ሳሙና በሚገድለው በሽታ ምክንያት
በደምህ የዋጀሃት ቤተ ክርስቲያንህ ስትዘጋ ዝም
አትበል
በቆሮንቶስ የፈተነህ ሰይጣን ዛሬም በዓለም ዙሪያ
በሽታ ዘርቶ ቤተ ክርስቲያንህን ፈትኗታል
በቆሮንቶስ ድል እንደነሳሀው ዛሬም ድል
መንሳትህ ከቤተ ክርስቲያንህ አታርቅ
አምላክ ሆይ ታረቀን ተለመነን ማረን እዘንልን
እንደ ኀጢአታችን አትፍረድብን
ቁጣህን በምረትህ መልስልን
አምላክ ሆይ ከአንተ ደጅ ተለይቶ ከመኖር ከባድ
ሞት ነው ከጅህን ክፈትልን
ሳሙና የሚገድለው በሽታ ሰውን በመግደል
ሰውን አስጨንቋልና
ለዓለም ፈውስህን ላክላት እጆችህን ዘርጋላት
በዚህ ቤተ ክርስቲያን በምትዘጋበት ዘመን
መፈጠሬን አምርሬ ጠላሁት
ሞተ ሥጋ የማይቀር ነው ከደጅህ መቅረት ግን
ከባድ ሞት ነው
መጻጉን የፈወሱ እጆችህ
አላዛርን ያነሳ ድምጽህ
ወለተ ኤያኤሮስን ያነሳ ዝምታህ
አጋንንትን ያወጣ ኀይልህ
ድውያንን የፈወሰ ምህረት
አይለየን፡፡
♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦
@menfesawimeker
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
አሁንም ለ ጥያቄያችሁ
@menfesawimekerbot ይጠቀሙ
አዘጋ!
ሙት ያስነሳው የኤልያስ አምላክ ሆይ ወዴት
አለህ?
ከሞተ በሇላ በአጽሙ ሙት ያስነሰው የኤልሳዕ
አምላክ ሆይ ለምን ዝም አልክ?
ባህር የከፈለው የሙሴ አምላክ ሆይ ወዴት
ነህ?
በእጣኑ በሽታን አርቆ ምሙማንን የፈወሰው
የአሮን አምላክ ሆይ ለምን ዝም አልክ?
ፀሐይን ያቆመው የኢያሱ አምላክ ሆን ለምን
ተውከን?
ጣቢታን ከሞት ያስነሳው የጴጥሮስ አምላክ ሆይ
ወዴት ነህ?
በቤተ መቅደሱ በር ድውያንን የፈወሱ የጴጥሮስ
የዮሐንስ አምላክ ሆይ መቅደስህ ሲዘጋ ለምን ዝም አልክ?
በልብሳቸው ድውያንን የሚፈውሱ በጥላቸው
ምህረትን የሚያመጡ የቅዱሳን አምላካቸው ሆይ
ተለመነን
የነቢያት አምላካቸው ምህላችን ስማን
የሐዋርያት አምላካቸው ጸሎታችን ከፊትህ
ትድረሰን
የሰማእታት አምላካቸው ስለእነሱ ብለህ ራራልን
በቃል ዐላዛርን ጠርተህ ከሞት ያስነሳሀው
የአላዛር አምላክ ሆይ ሞትና ህማም በአንተ
ዘንድ ኢምንት ናቸውና እባክህ እንደክፋታችን
አትክፈለን
በዘመነ ሰማእታት በከሀድያን ነገስታት ቤተ
ክርስቲያን ተዘግታ ነበር
ዛሬ ደግሞ ሳሙና በሚገድለው በሽታ ምክንያት
በደምህ የዋጀሃት ቤተ ክርስቲያንህ ስትዘጋ ዝም
አትበል
በቆሮንቶስ የፈተነህ ሰይጣን ዛሬም በዓለም ዙሪያ
በሽታ ዘርቶ ቤተ ክርስቲያንህን ፈትኗታል
በቆሮንቶስ ድል እንደነሳሀው ዛሬም ድል
መንሳትህ ከቤተ ክርስቲያንህ አታርቅ
አምላክ ሆይ ታረቀን ተለመነን ማረን እዘንልን
እንደ ኀጢአታችን አትፍረድብን
ቁጣህን በምረትህ መልስልን
አምላክ ሆይ ከአንተ ደጅ ተለይቶ ከመኖር ከባድ
ሞት ነው ከጅህን ክፈትልን
ሳሙና የሚገድለው በሽታ ሰውን በመግደል
ሰውን አስጨንቋልና
ለዓለም ፈውስህን ላክላት እጆችህን ዘርጋላት
በዚህ ቤተ ክርስቲያን በምትዘጋበት ዘመን
መፈጠሬን አምርሬ ጠላሁት
ሞተ ሥጋ የማይቀር ነው ከደጅህ መቅረት ግን
ከባድ ሞት ነው
መጻጉን የፈወሱ እጆችህ
አላዛርን ያነሳ ድምጽህ
ወለተ ኤያኤሮስን ያነሳ ዝምታህ
አጋንንትን ያወጣ ኀይልህ
ድውያንን የፈወሰ ምህረት
አይለየን፡፡
♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦
@menfesawimeker
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
አሁንም ለ ጥያቄያችሁ
@menfesawimekerbot ይጠቀሙ