# በሰሙነ_ሕማማት_የሚፈጸሙ _ሥርዓቶች
1, # ስግደት :-
በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ
ይሰገዳል።
2, # ጸሎት :-
በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም
ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት;
6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው።
በእነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ
ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ።
3, # ጾም :-
በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት / አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች
አይበሉም። በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ # አንድ_ሰዓት እንድንጾም; ይኸውም
ቆሎ;ዳቦ;ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል።
4, # አለመሳሳም :-
አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም
አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም። መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ
የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን
ድረስ አንሳለመውም ገላ.3:13 ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29
5. # አክፍሎት :-
እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው
እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው።
6, # ጉልባን :-
ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም
የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው።
7, # ጥብጠባ :-
ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ
ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው። ይህም የጌታ ምሳሌ ነው።
8, # ቄጠማ :-
ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ
ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን።
እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻም ወድካም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ
እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም።

በሰሞነ ሕማማት የሚጸለዩት እና የማይጸለዩት ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው?
በቀሲስ መምህር ሄኖክ ወልደ-ማርያም
ሼር በማድረግ ለወዳጆቻችሁ አድርሱ አሳውቁ!
ተወዳጆች ሆይ ነገ የጌታችንን ሕማም የምናስብበት ሰሞን ነው። እንደ ቅድስት ቤተ-
ክርስትያናችን ሥርዓት በዚህ በሰሞነ ሕማማት የምንጸልያቸውና ለጊዜው የምንታቀባቸው
ጸሎቶች አሉ።
በሰሞነ ሕማማት የምንጸልያቸው ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው?
በሰሞነ ሕማማት አጥብቀን የምንጸልያቸው ጸሎቶች ውዳሴ ማርያም:ዳዊት: ሰይፈ
ሥላሴ:ሰይፈ መለኮት:ድርሳነ ማሕየዊ ውዳሴ አምላክ ናቸው።
ወለላይቱ እመቤት በዚህ በሰሞነ ሕማም በልጅዋ ምክንያት ብዙ እንግልት ስለደረሰባት
የእሷን ምስጋ የሆነውን ውዳሴ ማርያም አናስታጉልም። ውዳሴ ማርያም ማመስገኛ
መማጸኛ ስለሆነ እንጸልያለን። ምክንያቱም በዚህ በሰሞነ ሕማማት መከራ ተቀብሎ ሞቶ
ሕይወቱን የሰጠንን ጌታ በሥጋ ወልዳለችን በውዳሴዋ እናስባታለን።
የቅዱስ ዳዊት ድርሰት የሆነው ታላቁ መዝሙረ ዳዊት በትንቢት ክፍሉ ስለ ጌታችን ሕማም
ስቃይ እና ሞት የሚናገርና በዳዊት ምስጋና በምድር የሰው ልጆች በሰማይ ቅዱሳን
መላእክት ስለሚያመሰግኑ እንጸልየዋለን።
ሰይፈ ሥላሴ ከሦስቱ አካላት እግዚአብሔር ወልድን የሚያመሰግን አምላክነቱን
የሚመሰክር እና የሚመሰጥር በመሆኑ እንጸልየዋለን።
ሰይፈ መለኮት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ስለ ምስጢረ መለኮት እና ስለ ጌታችን
አምላክነት ስለሚናገር እንጸልየዋለን።
ድርሳነ ማሕየዊ በቅዱስ ዮሐንስ ወልደ-ነጎድጓድ የዓይን እማኝነት እና የቃል ምስክርነት
የተጻፈና የጌታችንን መከራ ስቃይ እንግልት እና ሞት በልዩ ሁኔታ የሚናገር በመሆኑ ልክ
እንደ ውዳሴ ማርየም የየእለት/የየቀን ስላለው ብንጸልየው በዓይነ ሕሊና ቀራንዮ ወሰዶ
በነፍሳችን የጌታችንን ሰማያዊ ውለታ የሚስልብንና በመጸለያችን ልዩ ጸጋና ክብር
የሚያሰጥ የቃል-ኪዳን ጸሎት በመሆኑ በዚህ በሰሞነ ሕማማት ብንጸልየው እጅጉን
እንጠቀምበታለን። ውዳሴ አምላክም የጌታችን ምስጋና በመሆኑ መጸለይ እንችላለን። ከዚህ
በተጨማሪ አርጋኖንና ጸሎተ ባርቶስን ልዩ ፈተና ያለብንና እመቤታችንን የምንወድ መጸለይ
አንከለከልም። ዋናው ትኩረታችን የጌታ መከራ ስቅለት እና ሞት ላይ ማድረጉን ሳንረሳ።
በሰሞነ ሕማማት የማይጸለዩት ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው?
በሰሞነ ሕማማት የማይጸለዩትን ጸሎቶች ጠቅለል አድርገን ስናያቸው ድርሳናት ገድላት እና
መልካ መልኮች ናቸው። ይህም የሆነው በሰሞነ ሕማማት ጌታችን ለእኛ ለሰው ልጆች ብሎ
የተቀበላቸውን ስቃይ እና መከራ ሞት የምናስብበት እና የምናለቅስበት እንጂ ሌሎቹን
በድርሳናቸው በገድላቸው በመልካቸው የምናመሰግንበት ጊዜ ስላልሆነ ነው። ከስሙ
እንደተረዳችሁት ሰሞኑ ሰሞነ ሕማማት የተባለው የጌታ ስቃይና ሞት መታሰብያ ስለሆነ
ነው።
በተረፈ በዚህ በሰሞነ ሕማማት ለራሳችሁ ለሀገራችሁ ብቻ አትጸልዩ ለዓለም ሕዝብ
ለአሕዛብ በሙሉ ጸልዩ። ምክንያቱም ለእነሱ የመጣ ሰማያዊ ቁጣ በቀጥታም
በተዘዋዋሪም ለእኛም ይተርፋልና። እንዲህ ያስጨነቀን መግቢያ መውጫ የከለከለን ቤተ-
ክርስትያናችንን ያዘጋብን ወረርሽን ከእነሱ ለእኛ የተረፈን ነው። ስለዚህ እነሱ ሲለበለቡ እኛ
መቃጠላችን እነሱ ሲሰበሩ እኛ ወለም ማለታችን እነሱ ሲሞቱ ሞት ደጃፋችን መቆምን
በማሰብ ለእነሱም እንጸልይ። የእነሱ መከራ ሲርቅ ነው የኛም የሚርቀው።
ከታላቁ ጻድቅ ከአቡነ ሐራ ድንግል ገዳም!
ሚያዝያ 4/8/12 ዓ.ም
♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️
@menfesawimeker
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
አሁንም ለ ጥያቄያችሁ
@menfesawimekerbot ይጠቀሙ

+ አንተ ክርስቶስ ከሆንህ እኛንም ራስህንም አድን +
ጌታችን በተሰቀለባት ዕለት በጎኑ ከተሰቀሉት ወንበዴዎች አንዱ የተናገረው የትዕቢት ቃል ነው:: መዳን ይፈልጋል በክርስቶስ ማመንን ግን አልፈለገም:: እስቲ ፈጣሪ ከሆንክ አድነን! እስቲ ኃይል ካለህ እንይህ! እያለ ነው:: ሰው ከሞት አፋፍም ሆኖ ይፎክራል:: ልመናውም እንዳይቀር ኩራቱም እንዳይቀር ነው ነገሩ::
ይህን ወንበዴ እዚያ ቆሜ ብሰማው ኖሮ ይሄንን ጥያቄ እጠይቀዋለሁ:-
አንተ ወንበዴ እውነት ቃልህን ሰምቶ ቢያድንህና ከመስቀሉ ቢያወርድህ ምን ልታደርግ አስበሃል?
ከሞት ብትድንና ብትተርፍ ምን ታደርጋለህ? ዝርፊያህን ካቆምክበት ትቀጥላለህ? ወይንስ መጽዋች ትሆናለህ?
ነፍሰ ገዳይ እንደሆንክ ትቀጥላለህ? ወይንስ ነፍስ አድን ትሆናለህ? ብዬ ብጠይቀው ደስ ይለኛል:: እርግጥ ነው ወንበዴው ከአነጋገሩ ትዕቢት እንደሚታየው ቢድንም በክፋቱ የሚቀጥል ይመስላል::
ወዳጄ መስቀል ላይ ያለውን ወንበዴ እንላለን እንጂ እኔና አንተም ያው ወንበዴዎች ነን:: እሱ ከመስቀል ላይ እያቃሰተ በሞት ፍርሃት ተከብቦ ነበር:: እኛን ደግሞ ወረርሽኝ ከፊታችን ቆሞ በሞት ፍርሃት ተሰቅለናል::
ፈጣሪን አድነን እያልን ነው:: እሺ ብሎ ቢያድንህ ምን ልትሠራ አስበሃል?
"ይህችን ያሳልፈኝ እንጂ እመነኩሳለሁ" ካልከኝ ስሜታዊ እንደሆንክ እረዳለሁ:: መነኮሰ ትርጉሙ ሞተ ነውና ከሞት ሸሽተህ ብትመነኩስ ለውጥ የለውም:: መነኮሳትም ተገንዘው "መቼ ትጠራኝ ይሆን? መች እደርሳለሁ የአምላኬንስ ፊት መቼ አየዋለሁ?" ብለው በናፍቆት የሚጠብቁ ናቸው እንጂ "ከመሞት መሰንበት" የሚሉ አይደሉምና ተዋቸው::
ይልቅ ንገረኝ እንደ ግራው ወንበዴ አድነን ካልን አይቀር ዕድሜ ቢሠጥህ ምን አስበሃል:: አሁንም በውንብድናህ ልትቀጥል ነው? አሁን ያለው ሁኔታ በግድ ያስቆመህን ኃጢአት ልትቀጥል ነው?
እነዚያን ጥላቻ የተሞሉ የዘረኝነት ስድቦች ካቆምክበት ልትጀምራቸው ነው? እነዚያን የግፍ ትርፎች ልትሰበስብ ነው? አሁን የያዘ ይዞህ ያቆምከውን ሴራ መጎንጎን ልትቀጥል ነው? ቂም የያዝክባቸውን ሰዎች ማጥቃትህን ልትገፋበት ነው? ሰላም የማትለውን ሰው እንደዘጋኸው ልትኖር ነው? ስካርህን ዝሙትህን ጥላቻህን እንደበፊትህ ልትገባበት ነው?
ከኮሮና ብታልፍ ምን ልታደርግ አቅደሃል? ግዴለም ከመስቀሉ ትወርዳለህ እንበል! ግን ምን አቅደሃል?
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሚያዝያ 1 2012 ዓ ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

#ቤተ_ክርስቲያን_መሄድ_ለማትችሉ_ሰሙነ_ሕማማትን_በስደት_በሥራ_ለምታሳልፉ_በየቤታችሁ_ሁናችሁ_ለምትሰግዱ_እንዲህ_እያላችሁ_ስገዱ
በመጀመሪያ በስመአብ ብለን የዘወትር ጸሎትን አድርሰን ውዳሴ ማርያምን ቆመን እንደግማለን
በመቀጠል
👉 ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም
👉 አማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከለዓለመ ዓለም
👉 ኦእግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከለዓለመ ዓለም
👉 ኃይልየ ወጸወንየ ውእቱ እግዚእየ እስመ ኮንከኒ ረዳእየ እብል በአኮቴት
🙏 አቡነ ዘበሰማያት / አባታችን ሆይ/
ከቻልን እየመላለስን 12 ግዜ እያልን መስገድ 12 ጊዜ ካልቻልን የቻልነውን ያህል
👇 ይህን ስንጨርስ በዛው ቀጥለን
🙏 ለአምላክ ይደሉ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም
🙏 ለስሉስ ይደሉ ክብር
🙏 ለማኅየዊ ይደሉ ክብር
🙏 ለእዘዙ ይደሉ ክብር
🙏 ለመንግሥቱ ይደሉ ክብር
🙏 ለሥልጣኑ ይደሉ ክብር
🙏 ለምኩናኑ ይደሉ ክብር
🙏 ለኢየሱስ ይደሉ ክብር
🙏 ለክርስቶስ ይደሉ ክብር
🙏 ለሕማሙ ይደሉ ክብር
👉 እስከ አርብ ድረስ እስከዚህ ሲሆን አርብ ለመስቀሉ ይደሉ ይጨምራል
እንዲህ እያልን ከሰገድን በኋላ መዝሙረ ዳዊትን መጽሐፍ ቅዱስ ከኦሪት ከነቢያት ከወንጌል የቻልነውን እናነባለን
ከዛም 👇
👉 ኪርያ ላይሶን ኪርያ ላይሶን ኪርያ ላይሶን ኪርያ ላይሶን
👉 ክርያላይሶን ኪርያላይሶን ዕብኖዲ ናይን ኪርያላስይሶን
🙌 ታኦስ
🙌 ማስያስ
🙌 ኢየሱስ
🙌 ክርስቶስ
🙌 አማኑኤል
🙌 ትስቡጣ
👇 እንዲህ እያልን ከሰገድን በኋላ
✋ 41 ጊዜ የቻለ ከዛም በላይ ኪርያላይሶን እያሉ መስገድ ነው።
✍ የቃላት ትርጉም
👉 ኪርያላይሶን ማለት ቃሉ ግሪከኛ ሲሆን አቤቱ ማረን ማለት ነው
👉 ዕብኖዲ ማለት የግጽ ቅብጥኛ ሲሆን አምላክ ማለት ነው
👉 ናይን /ናይናን/ ማለት እኛን ማረን / ቅብጥኛ/
👉 ታኦስ / ግሪከኛ / አምላክ
👉 ማስያስ ።/ እብርይስጥኛ / መሲሕ
👉 ኢየሱስ መድኃኒት
👉 ክርስቶስ ንጉሥ ቅቡዕ የባሕርይ አምላክ
👉 ትስቡጣ /ግሪክኛ / ደግ ገዥ
🤝 የቃሉን ትርጉም እንዲህ እያሰብንና እየተረዳን መስገድ ይገባናል ።ላስተማሩን አባቶቻችን ቃለ ህይወት ያሰማልን።

13ቱ ሕማማተ መስቀል!!!
1ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር)
2ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ)
3ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር(በምድር ላይ መውደቅ)
4ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድ መረገጥ)
5ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋር መላተም)
6ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት)
7ኛ. ተቀስፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ)
8ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት)
9ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት)
10ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም)
11ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር)
12ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ(በመስቀል ላይ መሰቀል)
13ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትን መጠጣት)
+ + + + + + +
ሰባቱ የመስቀሉ ቃላት!!!
1. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ (ማቴ 27፡46)
2. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው (ሉቃ 23፡34)
3. ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር እንድትኖር በእውነት እነግርሃለሁ (ሉቃ 23፡43)
4. እነሆ ልጅሽ አነኋት እናትህ (ዮሐ 19፡26-27)
5. ተጠማሁ (ዮሐ 19፡28)
6. አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ (ሉቃ 23፡46)
7. የተጻፈው ሁሉ ደረሰ ተፈጸመ አለ (ዮሐ 19፡30)
+ + + + + + +
ሰባቱ ተዐምራት !!!
ጌታ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈጸሙ ተዐምራት፦
1. ፀሐይ ጨልሟል
2. ጨረቃ ደም ሆነ
3. ከዋክብት ረገፉ
4. ዐለቶች ተሠነጠቁ
5. መቃብራት ተከፈቱ
6. ሙታን ተነሡ
7. የቤተ መቅደስም መጋረጃ ለሁለት ተቀደደ
+ + + + +
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቸነከረባቸው አምስቱ ችንካሮች፦
1. # ሳዶር ፣ በሚባል ችንካር ቀኝ እጁን ቸነከሩት
2. # አላዶር ፣ በሚባል ችንካር ግራ እጁን ቸነከሩት
3. # ዳናት ፣ በሚባል ችንካር ሁለት እግሩን ቸነከሩት
4. # አዴራ ፤ በሚባል ችንካር ማሀል ልቡን ቸነከሩት
5. # ሮዳስ ፣ በሚባል ችንካር ደረቱን ቸነከሩት
+ + + + +
# አምስቱ_የእመቤታችን ኃዘናት፦
1• ከአምስቱ አንዱ አይሁድ እንዲገድሉህ በቤተ መቅደስ ስምዖን ትንቢት በተናገረ ጊዜ ነው፡ ሉቃ 2:34-35
2• ሁለተኛውም ሦስት ቀን በቤተመቅደስ ፈልጌህ ባጣሁህ ጊዜ ነው፡ ሉቃ 2:41-48
3 • ሦስተኛውም እግርህንና እጅህን አሥረው በጲላጦስ አደባባይ የገረፉህን ግርፋት ባሰብኩ ጊዜ ነው፡ ዮሐ 19:1
4 • አራተኛውም በዕለተ ዓርብ ራቁትህን ቸንክረው በሁለት ወንበዴዎች መካከል እንደሰቀሉህ ባሰብኩ ጊዜ ነው አለችው፡ ዮሐ 19:17-22
5• አምስተኛውም ወደ ሐዲስ መቃብር ውስጥ እንዳወረዱህ ባሰብኩ ጊዜ ነው፡ ዮሐ 19:38-42

👉ጸሎት ለማድረግ አታቅማማ፤ ሥጋ ከምግብ በተከለከለ መጠን ደካማ እንደሚሆን ነፍስም ከጸሎት ስትከለከል ደካማ ትሆናለች፡፡ (አቡነ ማቴዎስ ግብፃዊ)
ስለሁሉም ነገር ሳታቋርጥ ጸልይ፤ እንዲህ ካላደረግክ ምንም ነገር ያለ ልዑል እግዚአብሔር ፈቃድ የማታከናውን ትሆናለህ፡፡ ያለጸሎት ራሱን በማንኛውም ዓለማዊ ጉዳዮች የሚያደክም ሰው በመጨረሻ ውጤታማ ሊሆን አይችልም፡፡ ሰው ራሱን ኃጢአተኛ እንደሆነ እያሰበ ወደ እግዚአብሔር ካለየ ጸሎቱ ተቀባይነት አይኖረውም ፡፡ (አባ አጋቶን)
እግዚአብሔር ለሰው ምሕረትን ሲያድል አንድ ሰው እንዲጸልይለት ያነሣሣዋል፡፡ በዚህ ጸሎት አማካኝነትም ይረዳዋል፡፡ በመከራ ጊዜ ያለማቋረጥ መሓሪውን አምላክ በጸሎት ጥራው፡፡ ባለማቋረጥ የእግዚአብሔርን ስም መጥራት ለነፍስ ቁስል መድኃኒት ነው፡፡ ሰው በታመመ ጊዜ ዶክተሩ ፍቱን መድኃኒትን ፈልጎ ለበሽተኛው እንደሚሰጠው መድኃኒቱም ወደ ሰውነቱ ገብቶ ሥራ ሲሠራ እንጂ እንዴት እንደሚሰራ እንደማናውቀው በተመሳሳይ ሁኔታ የእግዚአብሔርን ስም አዘውትረን ስንጠራ እንዴት ጸሎታችን እንደሰራ ሳናውቅ የእግዚአብሔርን ፍቅር ምህረትና ርኅራኄ በእኛ ላይ ሲደረግ እንመለከታለን፡፡
(አቡነ ማቴዎስ ግብጻዊ)

+ ፍቅር ቊስል ነው +
(በከመ ጸሐፈ ዲ/ን ኄኖክ ኃይሌ)
እውነቱ ይህ ነው ፣ ፍቅር የሚለካው በልባችን ላይ በተወው ቊስል ልክ ነው። እጅግ የምንወዳቸው ሰዎች አሳምመውን ይሆናል። እኛም እጅግ የሚወዱንን ሰዎች አሳምመን ይሆናል።ምክንያቱም ፍቅር የሚታየው በታገስነው ቊስል ውስጥu ነው። ፍቅር የሚታወቀው የተለዋወጥናቸውን ቃላት ሳይሆን በምንታገሠው ቊስል ፣ በተሰማን የውስጥ ሕመም ፣ በከፈልነውን መሥዋዕትነትና በተካፈልነውን ብርሃን ነው።
ከትንሣኤው በኋላ በሐዋርያቱ ፊት የተገለጠው ክርስቶስ እርሱ የሚወዱት ጌታ እንደሆነ ለማስረዳት ያሳያቸው የትንሣኤው ድል ማብሠሪያ መለከት አይደለም ፣ የፍቅሩ ማስረጃ ቊስሉ ነበር። "ወደ እኔ ኑ ቊስሌን ዳስሱ ፣ እጃችሁንም ስለ እናንተ ፍቀር በቆሰልሁት ቊስል አስገቡ" ነበር ያላቸው። "አታስታውሱኝም? አላወቃችሁኝም? እስከ ሞት ድረስ የወደድኳችሁ እኔ ነኝ። ለፍቅሬ ማረስጃ እንዲሆናችሁ ደግሞ ቊስሌን ተመልከቱ!" ነው ያላቸው። ፍቅር ቊስል ነው።
በእግዚአብሔር መንግሥት ክብርና ምስጋና የምናገኘውም በምድር ሳለን በነበሩ ስኬቶቻችንና ባስገኘናቸው ውጤቶቻችን ሳይሆን በታገሥናቸው መከራዎችና በተሰቃየንባቸው ሕመሞች ልክ ነው። ለዚህም ነው በአበው መጽሐፍ አንድ ቅዱስ አባት ለረጅም ዓመት በሰውነትዋ ላይ ቈስሎ የምትሰቃይን ሴት ሊጠይቁ ሲሔዱ "እዩት ቊስሌን ፣ አጎንብሰው ቢያዩት አጥንቴ ይታይዎታል" አለቻቸው። እርሳቸውም ጎንበስ ብለው "ብዙ ዓመት በታገስሽው በቊስልሽ ውስጥ የሚታየኝ አጥንት ሳይሆን ገነት ነው" አሏት።
ጸሐፊ: Fr Haralambos Libyos Papadopoulos
ተርጓሚ: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ግንቦት 10 2011 ዓ ም

+++ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሠሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም
እምይዕዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም+++
ዕለተ ቀዳሚት ሰንበት - ይህችንም ዕለት እንዳለፉት ቀናት ቅዱስ ያሬድ ቅዱሳት አንስት በማለት ሰይሟታል።- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውንና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸውን ይሰበካል፡፡
“የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን”
፩ቆሮ ፫፥ ፲፮

"የተሰረቀ ሞት"
🍇🍇🍇🍇🍇🍇
ከዕለታትም በአንደኛው ቀን አባ መርትያኖስ የተባለ በምግባር በሃይማኖቱ፣ በትሩፋት በተጋድሎው የተመሰገነ ታላቅ ጻድቅ በመንገድ ሲሔድ አንድ ሰው ሞቶ ሊቀብሩት
ሲወስዱት አየ፡፡ በዚያም ቦታ አንድ ዐመፀኛ ሰው በዚያ በሞተው ሰው ላይ ሐሰት በመናገር ‹‹ከዚህ ሰው ጋር አራት መቶ የወርቅ ዲናር አለኝ›› በማለት አላስቀብርም ብሎ
አወከ፡፡
አባ መርትያኖስም የሞተውን በሰላም ይቀብሩት ዘንድ ያን ዐመፀኛ ቢለምኑት ዳግመኛ አላስቀብርም ብሎ እምቢ አላቸው፡፡ ከዚኽም በኋላ አባ መርትያኖስ ወደ እግዚአብሔር እየጸለዩ በማለዱ ጊዜ ያ የሞተው ሰው ተነሥቶ የማንም ሰው ምንም ዓይነት ዕዳ እንደሌለበት ተናገረ፡፡
ከዚኽም በኋላ አባ መርትያኖስ ያንን ዐመፀኛ በሰው ሁሉ ፊት ‹‹ለምን በሐሰት ተናገርክ? የተሰወረውን የሚያውቅ እግዚአብሔርን አትፈራምን?›› አሉት፡፡ በዚያም ጊዜ ያ ዐመፀኛ ፈጥኖ ሞተ፣ ከሞት የተነሣው ሰው ግን በሰላም ወደቤቱ ተመልሶ ሔደ፡፡
ይህንንም ያዩ ሁሉ በቅዱሳኑ ላይ አድሮ ድንቅ ድንቅ ነገርን የሚያደርግ እግዚአብሔርን አመሰገኑት፡፡ አባ መርትያኖስም መላ ዘመኑን በታላቅ ተጋድሎ እግዚአብሔርን ሲያገለግል ኖሮ በሰላም ዐረፈ፡፡
ክፉዎችና በደለኞች የሌላውንም ሰው ሞት የሚሰርቁበት አጋጣሚ ብዙ ነው!!!
ለ አስተያየት ወይም መንፈሳዊ ጥያቄ ካሎት
@menfesawimekerbot

+ እኔ ግን እኔ አይደለሁም +
አውግስጢኖስ ፈጣሪ የለም ባይ እና በዝሙት የተበላሸ ሕይወት ይኖር የነበረ ሰው ነው:: በቅዱስ አምብሮስ ስብከት ከተመለሰ በኁዋላ ግን ይህ ሰው ፍጹም በንስሓ ተለውጦ በምንኩስና መንገድ ሔዶ እስከ ጵጵስና ደረሰ:: ይህንን የንስሓ ሕይወት መኖር ከጀመረ በኁዋላ ቀድሞ በአመንዝራነት ሕይወት ሲኖር ወዳጁ የነበረች አንዲት ሴት መንገድ ላይ ከሩቅ አይታ ተከትላ ጠራችው::
ወደ ቀድሞ ትዝታውና ኃጢአቱ መመለስ ያልፈለገው ይህ አባትም ጥሪዋን እንዳልሰማ ሆኖ በፍጥነት መሔድ ጀመረ::
ይህች ሴትም እየሳቀች :-
አውግስጢኖስ እኔ እኮ ነኝ! ብላ ጮኸች
እርሱም ወደ እርስዋ ዞሮ :- "እኔ ግን እኔ አይደለሁም" አላት::
ክርስትና የወደቀ የሚነሣበት የረከሰው የሚነጻበት ሕይወት ነው:: በዚህ መስመር ያለፉ ሁሉ ትናንትን እየተዉ ሌላ ማንነትን ይለብሳሉ:: ትልቁ ፈተና ሰዎች ተነሥተህ እያዩህም እንኩዋን መውደቅህን አለመርሳታቸው ነው:: ፈጣሪ "ከእንግዲህ አትበድል" ብሎ ይቅር ቢልህም ሰዎች ግን ይቅር አይሉህም:: "ድመት መንኩሳ ዓመልዋን አትረሳ" እያሉ እየተረቱ ወደ ነበርክበት እንድትመለስ ይገፉሃል እንጂ እንድትለወጥ አይፈቅዱልህም::
ሳውል አሳዳጅ ነበረ ዛሬ ግን ሐዋርያ ነው:: ብዙ ክርስቲያኖች ግን እርሱን ለማመን ተቸግረው ነበር:: ከመመረጡ ጀምሮ "ኸረ እርሱ አይሆንም" ብለው ለፈጣሪ ምክር የሠጡም ነበሩ:: ከተመረጠ በኁዋላም ለመቀበል ተቸግረው ከሐዋርያት አሳንሰው ያዩት አልጠፉም:: እርሱም በትሕትና "ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ" ቢልም : "ጭንጋፍ" ብሎ ራሱን ያለ ጊዜው ከሚወለድ ጽንስ ጋር አነጻጽሮ ዘግይቶ የተጠራ መሆኑን ቢናገርም ከሐዋርያት በምንም የማያንስ ሐዋርያ ነበረ:: እነርሱ በትናንት ማንነቱ ሊያዩት ቢሹም እርሱ ግን "እርሱ አልነበረም" እርሱ መኖር አቁሞ በእርሱ ይኖር የነበረው ክርስቶስ ነበረ::
አንዳንድ ሰዎች የማያምኑህ ከክፋት ተመልሰህ መልካም ስትሆን ብቻ አይደለም:: በጣም መልካም ስትሆንላቸውም አያምኑህም:: ስታከብራቸው ምን አስቦ ነው? ብለው ይጠራጠራሉ:: መልካም ስታደርግላቸው "ምነው ደግነት አበዛሽ? ተንኮል አሰብሽ እንዴ? "ይህቺ ጠጋ ጠጋ ዕቃ ለማንሳት ነው" "there is no free lunch” ብለው ሊሰጉ ይችላሉ:: መልካም የሚያደርግላቸውን ሁሉ ሊያርድ የሚያሰባቸው የሚመስላቸው ሰዎች አሉ:: ፍቅር የትግል ስልት የሚመስላቸው ጨብጠውህ ጣታቸው እንዳልጎደለ የሚቆጥሩ ዓይነት ተጠራጣሪ ሰዎች አሉ::
ዮሴፍ የገጠመው ይህ ነበር:: በሃያ ብር ሸጠው ግብፅ ያወረዱት ወንድሞቹን ይቅር ብሎ በፍቅር ተቀበላቸው:: አባታቸውን ያዕቆብን አስመጥቶ በክብር በግብፅ እንዲኖሩ አደረጋቸው:: ከዓመታት በኁዋላ አረጋዊው ያዕቆብ ሞተ::
ይሄን ጊዜ የዮሴፍ ወንድሞች ድንገት ስብሰባ አደረጉ: "አባታችን ከሞተ በኁዋላ ቢበቀለንስ?!" ብለው ስጋታቸውን ተመካከሩ::
ስለዚህ ዶልተው መጡና እንዲህ አሉት :-
አባታችን ከመሞቱ በፊት እንዲህ ሲል ተናዝዞ ነበር:: እባክህን የወንድሞችህን በደል ይቅር በል:: (ዘፍ 50:15-21) ዮሴፍ ይኼን ሲሰማ አለቀሰ:: ይቅርታን አድርጎም አለመታመኑ አመመው::
እርሱ ለእነርሱ ድሮም ክፉ አልነበረም:: አሁን ደግሞ ላደረሱበት በደል እንኩዋን ፈጣሪውን የሚያመሰግን ሆኖአል:: "እናንተ ክፉ ነገርን አሰባችሁብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲድን ለማድረግ ለመልካም አሰበው" ነበር ያለው:: ምንም በደል ቢደርስበት እነርሱ አልተለወጡ ይሆናል እንጂ እርሱ ግን ትናንት የሚያውቁት ዮሴፍ አይደለም:: "እኔ ግን እኔ አይደለሁም" አላቸው::

"ክርስትና የሚጀምረዉ ከተግባር እንጂ ከወሬ አይደለም፡፡ ሕይወታችን በጥቅስ ተገንዞ በጥቅስ የተቀበረ ከሕይወትና ከሥራ የተለየ እንዲሆን አንፍቀድለት፡፡"
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ
‹‹ ዘመን ማለት አንተ ነህ ፡፡ አንተ ሰላማዊ ስትሆን ሰላማዊ ትሆናለች፡፡ አንተ የከፋህ እንደሆነ ትከፋለች፡፡››
አንጋረ ፈላስፋ
‹‹ራስህን ለማየት ወደ መስታወት ብትመለከት ዉበትህን ወይም ጉድለትህን ያሳይሀል፡፡ ምንም ነገር እንዳታይ ታደርግ ዘንድ ከመስታወቱ መሰወር አትችልም፡፡ ማንም ሊያመልጥበት በማይችለዉ በፍርድ ቀንም እንዲሁ ይሆናል፡፡››
አንጋረ ፈላስፋ
‹‹ የአንጥረኛ ዕቃ በየቀኑ በተመታ ቁጥር የበለጠ ጽሩይ እየሆነ እንደሚሄደዉ ሁሉ ሰዉነቱን ለማድከም ራሱን የሚያስገዛ ሰዉም እንዲሁ ነዉ፡፡ በየቀኑ እየተማረ፣ እየጠራ እየነጻ ከጠላት ስዉር ወጥመድ እየተጠበቀ ይሄዳል፡፡››
አንጋረ ፈላስፋ
‹‹ ሀብትን ብታከማች ያንተ አይደለም፡፡ ብትመፀዉተዉ ግን ታከማቸዋለህ፡፡››
ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ
‹‹ ስለ ወንድሙ መዳን የማይደክም ድኗል ብዬ አላምንም፡፡››
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
‹‹ እግዚአብሔር አንድን የመንፈስ ቅዱስ የፀጋ ስጦታ ሊሰጥህ ቢወድ ፀጋዉን ልትጠብቀዉ ከምትችለዉ ከትህትና ጋር ይሰጥህ ዘንድ ለምነዉ አለበለዚያ ግን ከአንተ እንዲያርቀዉ ጠይቅ፡፡››
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
‹‹ ኃጥእ ነኝ ማለት ብቻ እዉነተኛ ትህትና እንዳይደለ በእዉነት እናገራለሁ፡፡ እዉነተኛ ትህትና ትሩፋትን መሥራት ነዉ፡፡››
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
‹‹ ስለ ሌሎች ሰዎች ያለማቋረጥ ፀልዩ፡፡ወደ እግዚአብሔር ይደርሱ ዘንድ የንስሐ እድል አላቸዉና፡፡ ለእነርሱ ነቀፋ እናንተ ምላሻችሁ ፀሎት ይሁን፡፡››
ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥዉ ለአንበሳ

ወዳጄ ሆይ፦
ቤቱ ቆሽሾ ሳለ ውጫዊ በሩን ብቻ ለማሽቀርቀር ለምን ትጨነቃለህ? ነፍስህ በኀጢአት ተዳድፋ ሳለ ሥጋህን ብቻ ለማስደሰት ለምን ትሮጣለህ? አስቀድመህ ቤቱን (ነፍስህን) ለማስዋብ አትሽቀዳደምምን? አስቀድመህ ለነፍስህ የምታስብ ከኾነ ከሰው እጅ ሳይኾን ከክርስቶስ እጅ ሹመት ሽልማት ትቀበላለህ፡፡ ኹል ጊዜ “የማደርገው ነገር እግዚአብሔር ይከብርበታልን?” ብለህ አስብ እንጂ እንዲሁ በዘልማድ የምትመላለስ አትኹን ብዬ እመክርኻለሁ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲመክረን፡- “እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትኾኑ ወይም ማናቸውም ነገር ብታደርጉ ኹሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት” ያለንም ስለዚሁ ነውና በድርጊቶቻችን ኹሉ እግዚአብሔርን ለማክበር እንዘጋጅ (1ኛ ቆሮ.10፡31)፤ ፡፡
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

ማግባት ስትፈልጉ ይህን አስተውሉ፦
የትዳር ተቀዳሚ ዓላማ #ጽድቅን #መፈጸም ነው፡፡ ሌሎቹ የትዳር ዓላማዎች ኹሉ በዚህ የሚጠቃለሉ ናቸውና፡፡ ስለዚህ አንድ ወጣት፡-
ልጅን ለመውለድ ብቻ አስቦ ማግባት የለበትም፤ የትዳር አንዱ ዓላማ ልጅ መውለድ ቢኾንም ቅሉ፥ ላይወልድም ይችላልና፡፡
“በየምግብ ቤቱ መብላት ወጪውን አልቻልኩትም” ብሎ ማግባት የለበትም፡፡ “በገንዘብ እንድንረዳዳ” ብሎ ማግባት የለበትም፡፡ ወጪ መቀነስ መልካም ቢኾንም፥ የትዳር ዋናው ዓላማ ግን ከዚህ ከፍ ያለ ነውና፡፡ እንዲያውም ሊቁ፡- “ክርስቲያን ኾነህ ሳለ ከትዳር አጋርህ ገንዘብ ለማግኘት ብለህ ወደ ትዳር ከምትገባ ምድር ተከፍታ ብትውጥህ ይሻላል” ይላል፡፡ ስለዚህ “ገንዘብን አትሹ፤ የወላጆቹን ባለጸግነት አትመልከቱ፡፡ የትውልድ ቀዬውን ታላቅነትም አትዩ፡፡ እነዚህ ኹሉ ዋና ነገሮች አይደሉምና፡፡ ከትዳር አጋራችሁ ጋር በተድላ በደስታ መኖርን ስትሹ ማየት የሚገባ’ችሁ ንጽሃ ነፍስን፣ ደግነትን፣ ልባምነትንና ፈሪሐ እግዚአብሔርን ነው፡፡”
አንድ ለአንድ መወሰን ጥሩ ነው በሚል ብቻ ማግባት የለበትም፡፡ ይህ በራሱ መልካም ቢኾንም በውስጡ ከዝሙት ተጠብቆ ጽድቅን ለመፈጸም ካልኾነ አንድ ለአንድ መወሰን ብቻውን የትዳር ተቀዳሚ ዓላማ አይደለምና፡፡ ከአሕዛብም የጽድቅ አሳብ ሳይኖራቸው አንድ ለአንድ የሚወሰኑ አሉና፡፡
ዕድሜዬ እንዳያልፍ ብሎም ኾነ ሰው አግባ ብሎ አስጨንቆት ማግባት የለበትም፡፡ ትዳር ከ “ለምን አታገባም?” ጭቅጭቅ ለማምለጥ የተሰጠ አይደለምና፡፡
“መልኳን ወደድኳት” ብሎ ማግባት አይገባም፡፡ ውበት ባይጠላም እርሱ ግን የትዳር ዓላማ አይደለምና፡፡ ይህን አድንቆ ወደ ትዳር ከገባ ያ የማረከው ውበት ከሃያ ወይም ከሠላሳ ቀናት በኋላ አይማርከውምና፤ ይለምደዋልና፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
(ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ መጽሐፍ በገብረ እግዚአብሔር ኪደ)

አንድ ተማሪ በፈተና አዳራሽ ገብቶ ሁለት ጥያቄዎችን እንዲሠራ ተሰጠው። ጥያቄዎቹ እነዚህ ናቸው።
1. ስለ እግዚአብሔር ጻፍ
2. ስለ ሰይጣን ጻፍ የሚሉ ነበሩ።
ጥያቄዎቹን ካነበበ በኋላ ስለእግዚአብሔር ጻፍ የሚለውን ይጽፍ ጀመረ። ነገር ግን የተሰጠው ጊዜ አንድ ሰዓት ብቻ ስለነበር ሙሉውን ሰዓት ስለ እግዚአብሔር ሲጽፍ ቆይቶ ሰዐቱን ጨረሰ።
የፈተናውን ወረቀት የሚሰበስበት ጊዜ ደርሶ ደውል ተደወለ ብልሁም ተማሪ ሁለተኛውን ጥያቄ አለመሥራቱን ተረድቶ "ለሰይጣን ጊዜ የለኝም" ብሎ በአንድ መስመር መልስ ሰጠ።
ወንድሜ ሆይ ለሰይጣን ጊዜ አይኑርህ።
@menfesawimeker
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
አሁንም ለ ጥያቄያችሁ
@menfesawimekerbot ይጠቀሙ
1. ስለ እግዚአብሔር ጻፍ
2. ስለ ሰይጣን ጻፍ የሚሉ ነበሩ።
ጥያቄዎቹን ካነበበ በኋላ ስለእግዚአብሔር ጻፍ የሚለውን ይጽፍ ጀመረ። ነገር ግን የተሰጠው ጊዜ አንድ ሰዓት ብቻ ስለነበር ሙሉውን ሰዓት ስለ እግዚአብሔር ሲጽፍ ቆይቶ ሰዐቱን ጨረሰ።
የፈተናውን ወረቀት የሚሰበስበት ጊዜ ደርሶ ደውል ተደወለ ብልሁም ተማሪ ሁለተኛውን ጥያቄ አለመሥራቱን ተረድቶ "ለሰይጣን ጊዜ የለኝም" ብሎ በአንድ መስመር መልስ ሰጠ።
ወንድሜ ሆይ ለሰይጣን ጊዜ አይኑርህ።
@menfesawimeker
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
አሁንም ለ ጥያቄያችሁ
@menfesawimekerbot ይጠቀሙ
በአንድ ወቅት አንድ መንፈሳዊ አባት ከነበሩበት ቦታ ወደ በረሃ መሰደድ ግድ ሆነባቸው። ከቅዱስ መጽሐፋቸው ሌላ ሦስት ነገሮች ነበሯቸው።
እነሱም፦ ቅዱስ መጽሐፉን በጨለማ ወቅት ለማንበብ የሚጠቅማቸው ኩራዝ ፣ጎህ ከመቅደዱ በፊት ከእንቅልፍ የሚቀሰቅሳቸው አንድ አውራ ዶሮ እና ለመጓጓዣነት የሚገለገሉበት አንድ አህያ ነበሩ።
አንድ ቀን ምሽት ከጉዞ የተነሣ በጣም ስለ ደከሙ እኚህ መንፈሳዊ አባት ወደ አንድ መንደር ቀርበው ማደሪያ ቢጠይቁም መንደርተኛው ፈቃደኛ ባለመሆኑ ማንም አላሳደራቸውም። ስለዚህም ከመንደሩ አቅራቢያ አንድ ጉድጓድ ያገኙና በዚያ ውስጥ ገብቶ ለማደር በመወሰን ገብተው አደሩ። እንደ ወትሮው ቅዱስ መጽሐፋቸውን ለማንበብ ኩራዛቸውን ቢለኩሱትም የነበረው ብርቱ ነፋስ አጠፋባቸው።
ስለዚህም ለመተኛት ጋደም እንዳሉ ተኩላ መጥቶ አውራ ዶሮዋቸውን፣ አንበሳም አህያቸውን በሉባቸው። የተደራረበ ጉዳት ስለደረሰባቸው ሽማግሌው እርዳታን በመሻት ወደዚያ መንደር ቢመለሱ ዘራፊ ሽፍታዎች የመንደሩን ነዋሪዎች በሙሉ ገድለው ንብረት ዘርፈው ዖና መንደር ሆኖ አገኙት።
ሽማግሌው ይህን ሁሉ ባጤኑ ጊዜ እግዚአብሔር ምን ያህል መልካም ነገርን እንዳደረገላቸው አስተዋሉ። በዚያች ምሽት በመንደርተኞቹ በአንዱ ቤት ቢያድሩ ኖሮ የዘራፊዎች ሰለባ ሆነው ሊገደሉ በቻሉ ነበር። ቀንዲላቸውንም ነፋስ ባያጠፋው የብርሃኑ ወጋገን እዚህ ጋር ሰው አለ በማለት ለሽፍታዎቹ ያሳብቅ ነበር። አውራ ዶሮአቸውና አህያቸውም ባይበሉ ኖሮ ከሽፍታዎቹ ተደብቀው ማደር ባልቻሉ ነበር።” እግዚአብሔር ከክፉ ነገሮች ውስጥ መልካም ነገር ማውጣት የሚችል አምላክ ነው።"
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ስለዚህ እንዲህ በሉ፦ "የሚደርስብኝ ፤ የሚገጥመኝ ፈተናና መከራ ሁሉ አምላኬ ሆይ ለበጎ ታደርግልኛለህና አመሰግንሐለሁ" አሜን

መንፈሳዊ የህይወት ምክር via @like
የምትልኩልኝን መንፈሳዊ ጥያቄዎች በተቻለኝ መጠን ቶሎ ቶሎ እየመለስኩኝ ነው. አብዛኛዎቻችሁን ከ ቅኖና :ዶግማ : ሰርዓት ቤተ ክርስትያን :መንፈሳዊ ህይወት :የ ወጣቶች ህይወት :የ ን ፅህና ህይወት : ብዙ ጥያቂዎች ሰላሉ ከዘገየሁ አንድትረዱኝ በ እግዚአብሔር ትግስት እለምናችሁአለሁ ::
ጊዜው የ ቤተ ክርስትያን ፈተና ሰለሆነ ሁላችሁም ከ መንፈሳዊ አባታችሁ ሳትርቁ ቶሎ ቶሎ ንስሀ በመግባ ት በ ፅድቅ ስራ በ ፀሎት አንድትቆዩ እጠይቃችሁለሁ
ሰለሞትሰጡኝ መልካም አስተያየት አግዚአብሔር ይስጥልኝ

🧡💛አባ ጥጦስ🧡❤️
አንድ ወንድም አባ ጥጦስን "እንዴት ልቤን መጠበቅ እችላለሁ?" ሲል ጠየቀው ።
አባ ጥጦስም "አፋችንና ሆዳችን ክፍት ከሆነ እንዴት ልባችንን መጠበቅ ይቻለናል?" ሲል መለሰለት።
💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢
ሁለት ከመናገር አንድ ማድመጥ ይላሉ አበው። አንደበታችንን ሳንገታ ቅድስና የለም
@Menfesawimeker

+++ ልብስህን ማን ወሰደው? +++
በአንድ ወቅት አባ ሰራብዮን ወደ እስክንድርያ በሄደ ጊዜ፣ በገበያም ስፍራ አንድ ከልብስ የተራቆተ ነዳይ አገኘ፡፡ ለራሱም ‹ይህ ደሃ ሰው ታርዞ መነኩሴ የተባልኩ እኔ እንዴት ለብሼ እታያለሁ? በእውነት ይህ ‹ታርዤ አልብሳችሁኛልና› ብሎ የተናገረው ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለምን? በዚህ ብርድ እየተሰቃየ ነው እኮ!› ብሎ ፈጥኖ የገዛ ልብሱን ከራሱ በማውለቅ ይለብስ ዘንድ ለዚያ ደሃ ሰጠው፡፡ ከዚያም በእጁ ያለውን መጽሐፍ ቅዱስ እንደያዘ እርቃኑን በጎዳናው ዳር ተቀመጠ፡፡ እርሱን የሚያውቀው አንድ የከተማው ባለጠጋ ሰው አባ ሰራብዮን ባለበት ሥፍራ ሲያልፍ ተመልክቶት ወደ እርሱ ቀረበና ‹አባ ሰራብዮን ሆይ ልብስህን ማን ወሰደው?› ሲል ጠየቀው፡፡ ቅዱሱም በእጁ ወደ ያዘው መጽሐፍ ቅዱስ እየጠቆመ ‹ልብሴን የወሰደው ይህ ነው!› አለው፡፡ ያም ባለጠጋ አዲስ ልብስ ገዝቶ አለበሰው። ከዚህም በኋላ አባ ሰራብዮን ከእርሱ እንደ ተለየ በመንገድ ሲሄድ ዕዳውን መክፈል ባለመቻሉ እያንገላቱ ወደ ወኅኒ ቤት የሚወስዱትን አንድ ሰው ተመለከተ፡፡ እርሱም የያዘውን መጽሐፍ ቅዱስ ፈጥኖ በመሸጥ የዚያን ሰው ዕዳ ከፍሎ ነጻ አደረገው፡፡ ይህንንም አድርጎ ጉዞውን ሲጀምር እንደ ገና ሌላ የታረዘ ነዳይ ሲለምን ተመለከተ። አባ ሰራብዮንም እንደ ቀድሞው የለበሰውን ልብስ አውልቆ ለነዳዩ በመስጠት እርሱ እርቃኑን ወደ በአቱ ተመለሰ፡፡ ደቀ መዛሙርቱም መምህራቸውን እርቃኑን ባዩት ጊዜ ደንግጠው ‹መምህር! ልብስህ ወዴት አለ?› ብለው ጠየቁት፡፡ እርሱም ‹መጸወትኩት› አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም መልሰው ‹እኛን የምታጽናናበት መጽሐፍ ቅዱስህስ አባታችን?› ሲሉ ደግመው ጠየቁት፡፡ አባ ሰራብዮንም ‹በእጄ የነበረው መጽሐፍ ቅዱስ ሁል ጊዜ ‹ሂድ ያለህን ሽጠህ ለድሆች ስጥ› ይለኛል፤ ስለዚህ ያለኝ እርሱ ነበር እርሱንም ሸጥኩት› አላቸው፡፡
ምንጭ :–Paradise of the monks, P 89
ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንደሚናገረው ምጽዋት የፊት መብራት ናት፡፡ አንድ ሰው በጨለማ ሲጓዝ ከኋላው መብራት ቢያበሩለትም እንኳ ከፊቱ የሚቀድመው የገዛ የአካሉ ጥላ እንቅፋት እየሆነበት ይጥለዋል፡፡ ወደ ፊት ያለውን መንገድ አጥርቶ እያየ ያለ ስጋት ለመሄድ እንዲችል የግድ የፊት መብራት ያስፈልገዋል፡፡ ጾም ፣ጸሎት እና ሌሎች መንፈሳዊ ትሩፋት እንደ ኋላ መብራት ናቸው፡፡ የፊት መብራት የተሰኘች ምጽዋት ካልታከለችባቸው እነዚህ ብቻቸውን ዋጋን አያሰጡንም፡፡ ከምጽዋት በላይ ታላቅ ነገር እንደሌለ ልንረዳ ይገባል፡፡ ዓለም ሁሉ ከነበረበት የበደል ዕዳ የዳነው ቸር እረኛ በሆነው በመድኃኔ ዓለም በአካሉ ምጽዋትነት (በሥጋው በደሙ መሰጠት) ነውና!!!
♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️
@menfesawimeker
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ለ ጥያቄያችሁ