የሙዕሚን መሳሪያ
ዘመናችን ከየትኛውም ግዜ እና ሰዓት በላይ ቀላል ምቹ ቢሆንም ከየትኛውም ዘመን በላይ ግን የሰው ልጆች ደም እንደ ወንዝ ዥረት በየቦታው እየፈሰሰ ይገኛል። በተለይም በአላህ አንድነት ጥርት አድርገው ባርነታቸውን ባረጋገጡት ሙዕሚኖች ደግሞ በጣም ባስ እያለ መጥቷል።ነገር ግን በአንፃራዊ ሰላም ላይ ያሉ ሙዕሚኖች ድቅድቅ ባለ የድሎት ዝንጋቴ ላይ መሆናቸውን በተለያዩ የህይወት ገጠመኞች ሲታይ ይስተዋላል። ለዚያም ይመስላል አላህ በተለያዩ የዱንያ ህይወት ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ፈተና ውስጥ የሚያስገባን! የሰላምን ትንፋሽ ተነፍገው በጥበት ላሉ ለወንድሞቻችን እና ለእህቶቻችን የነሱን ህመም ህመማችን ነው ብለን ከየትኛውም የአጀንዳ እንቅስቃሴ ነፃ ሁነን ልባችን ተቃጥሎ ዱዓ የማናረግላቸው..ምክንያቱም አላህ የሱን መሳሪያ በግልፅ ነፍጎናል። የሙዕሚን ዋነኛው መሳሪያ እና አስተማማኙ ዱዓ ብቻ ነው። ልባችን ተቃጥሎ ከውስጣችን ዱዓ ስናደርግ የኛም ህይወት ይቀላል።
አላህ ከልባቸው ዱዓ ከሚያደርጉት ባሮች ያድርገን!
#gaza
#dua
#islamindset
ዘመናችን ከየትኛውም ግዜ እና ሰዓት በላይ ቀላል ምቹ ቢሆንም ከየትኛውም ዘመን በላይ ግን የሰው ልጆች ደም እንደ ወንዝ ዥረት በየቦታው እየፈሰሰ ይገኛል። በተለይም በአላህ አንድነት ጥርት አድርገው ባርነታቸውን ባረጋገጡት ሙዕሚኖች ደግሞ በጣም ባስ እያለ መጥቷል።ነገር ግን በአንፃራዊ ሰላም ላይ ያሉ ሙዕሚኖች ድቅድቅ ባለ የድሎት ዝንጋቴ ላይ መሆናቸውን በተለያዩ የህይወት ገጠመኞች ሲታይ ይስተዋላል። ለዚያም ይመስላል አላህ በተለያዩ የዱንያ ህይወት ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ፈተና ውስጥ የሚያስገባን! የሰላምን ትንፋሽ ተነፍገው በጥበት ላሉ ለወንድሞቻችን እና ለእህቶቻችን የነሱን ህመም ህመማችን ነው ብለን ከየትኛውም የአጀንዳ እንቅስቃሴ ነፃ ሁነን ልባችን ተቃጥሎ ዱዓ የማናረግላቸው..ምክንያቱም አላህ የሱን መሳሪያ በግልፅ ነፍጎናል። የሙዕሚን ዋነኛው መሳሪያ እና አስተማማኙ ዱዓ ብቻ ነው። ልባችን ተቃጥሎ ከውስጣችን ዱዓ ስናደርግ የኛም ህይወት ይቀላል።
አላህ ከልባቸው ዱዓ ከሚያደርጉት ባሮች ያድርገን!
#gaza
#dua
#islamindset
👍6
I'm on Instagram as @nurahusu. Install the app to follow my photos and videos. https://www.instagram.com/invites/contact/?igsh=s9o8qnoy1hij&utm_content=m2i694c
ሰዎች በህይወት ኖረው እንደሞቱ ይቆጠራሉ። በተቃራኒው ደግሞ ሞተው በሰዎች መሀል ይኖራሉ። የሰዎችን ደረጃ የሚወስነው ለሰዎች ስብዕናቸው ሲሆን በአላህ ፊት ደግሞ ዚክር(አላህን በምላሳቸው ማስታወስ)ስንችሉ ብቻ ነው። ለዚያም ነው "እነዚያ አላህን የሚያስታዉሱ እና የማያስታዉሱ ምሳሊያቸው በህይወት እንደሚኖሩ እና እንደሞቱ አምሳያ ናቸው ያሉት ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁአለይሂ ወሰለም!)
ISLAMINDSET
ISLAMINDSET
🥰7👍2
ዱንያ የሰው ልጆች ይሄን ያክል ትኩረት አድርገውባት ለፍተውባት ካልሞላች ያውም ከ40-60 አማካኝ እድሜ ለመኖር አኪራ ሳይለፋበት ይገኛል ብሎ የሚያስብ ካለ ተሳስቷል። አዕምሮው ራሱ ባልተገነዘበው ነፃ ሀሳብ ታሟል። ለሁሉም ህመም ደግሞ መድሀኒት አለው። ለደነዚህ አይነቱ በሽታ መድሀኒቱ ቁርአን ማንበብ እና በጥልቀት ማስተንተን ነው።
ISLAMINDSET
ISLAMINDSET
👍6
የአይናችን ተዓምሩ በብርሃን ነፀብራቅ የነገሮችን ምስል በቀለማቸው አማካኝነት መመልከት ማስቻሉ ነው። እንደዚህ አይነቱ ብርሃን የትኛውም ፍጥረት አይን እስካለው ድረስ መመልከት ይችላል። የልብ ብርሃን ግን ለአይን ከሚሰጠው ብርሃን ፍፁም የተለያየ ነው። ይሄም ብርሃን ያለው በቁርአን ውስጥ ብቻ ነው። የቁርአንን ብርሃን ያገኘ አይኑም ልቡም ይመለከታል። ያጣው ግን አጥቶታል። ለዛ ነው ብዙዎች በአይናቸው ማየት ችለው በልባቸው መመልከት ያቃታቸው!
ISLAMINDSET
ISLAMINDSET
👍4
ብዙዎች ነፃ መውጣትን ከጉልበት እና ከገንዘብ ጋር አያይዘው ይመለከቱታል። ጥቂቶች ደግሞ ከሞት በኋላ አላህ ቃል ስለገባው ጀነት እና ከቅጣት መዳንን ነፃ መውጣትን በማሰብ ነፃ ነን ይላሉ።ነገር ግን የተወሰኑ ሰዎች በዱንያ ላይ የማያልፍን ነገር በሚያልፈው ሰዓታቸው ስራን ሰርተው ነፃ የወጡ ሰዎች አሉ።ነፃ መውጣት ማለት አላህ በባሮቹ ላይ ግዴታ ካደረገው በላይ ትሩፋቶችን ጨምሮ መስራት ነው።ለዛ ነው እነዚያ የተወሰኑ ሰዎች ሳይሞቱ ዱንያን ላይ አላህ ጀነት ውስጥ የሚያስቀምጣቸው።...ምንኛ ያማረ ነፃነት ነው! አላህ ይወፍቀን!
ISLAMINDSET
ISLAMINDSET
👍3
"በአንድ ቀን ውስጥ ሱበሀነላህ ወቢሀምዲሂ 100 ግዜ ያለ ሰው ወንጀሉን አላህ ይምርለታል።ወንጀሉ እንደ ባህር አረፋ ቢበዛም!" ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ).
ISLAMINDSET
ISLAMINDSET
👍6❤2
ትልቅ ሰው ማለት ራሱ የሚድንበትን መንገድ ለማግኘት ሰበብ የሚያደርግ ነው። ብዙዎች ራሳቸውን ለማዳን ሁሌም ይሯሯጣሉ።ነገር ግን "ከምንድን ነው የምናድነው!?" የሚለው ጥያቄ ይለያያቸዋል።ሰዎች እዚህ ላይም ነው የሚለያዩት! ሙስሊም በባዶ ተስፋ ሳይሆን የኢኺራ እርግጠኝነትን(የቂንን) በልቡ ስላረጋገጠ, ሩጫው ሰላረጋገጠው አለም ብቻ ነው። አላህም ባረጋገጠው ኒያ መሰረት ይመነደዋል። ምክንያቱም ሙኽሊስ ባሪያው መሆኑን በተግባር ለአላህ አሳይቷልና!
ISLAMINDSET
ISLAMINDSET
❤6👍1
ገንዘብ ሲገኝ ሊያስደስት ይችል ይሆናል። ያስደስት እንጂ የውስጥን እርካታና መረጋጋትን በፍፁም አይሰጥም።ለዛ ነው ገንዘብ የሌላቸው ሰዎች ገንዘብን ሲያገኙ በፊት ላይ ከነበሩበት አላህ የሚወደው ቦታ የምናጣቻው። ገንዘብ ያላቸው ከሌላቸው ሰዎች ይበልጥ ሩጫ እና ጭንቀት ውስጥ ይገባሉ።አላህ ያዘነላቸው ሰዎች ሲቀሩ!...እንዲሁ ገንዘብ ሲታጣ ሊጠብ እና ሊያጨናንቅ ይችል ይሆናል። ነገር ግን አያስደነግጥም። ምክንያቱም መታጣቱ ቋሚ አይደለም።ግዜውን ጠብቆ ይመጣል። በነዚህ በሁለቱ ተቃራኒ ጎኖች አንድ ሙዕሚን ገንዘብን ሲያገኝ የሁሉ የበላይ እንደሆነ አያስብም...ሲያጣም ከሁሉ የበታች እንደሆነም አይሰማውም። ሙስሊም ገንዘብ ሲያገኝ ሆነ ሲያጣ አንድ አይነት ባህሪ ብቻ ነው ያለው... እሱም በአላህ ፈተና ላይ እንደሆነ ያስተነትናል።
ISLAMINDSET
ISLAMINDSET
❤4👍2
በየ አመቱ...በየ ወሩ...በየ ሳምንቱ...በየቀኑ...በየሰዓቱ..በየደቂቃው እንዲሁም በየሴኮንዶች አላህ በኛ ላይ እዝነቱን ፀጋው ምህረቱን ይውልልናል። ልባችን ከድንጋይ በላይ ስትደርቅ ከሰጠን ይልቅ በአብዘሀኛው ያልሰጠን ነገር እንዳለ እያስመሰልን አላህን"አልሀምዱሊላህ!!!" ከማለት እንኮራለን።ነገር ግን ልባችን የመርጠቧ ምልክት የትኛውንም የዱንያ ህመም ላይ እንሁን አላህ በሰጠን ፀጋ ስለምንሽር "አልሀምዱሊላህ!!" ከማለት አናርፍም። ምክንያቱም ፀጋውን በውስጡ ላመነ ሰው "አልሀምዱሊላህ!" እንዲል ያስገድደዋል። እንዳለመታደል ሆኖ ግን የአላህ አመስጋኝ ባሮቹ ትንሽ ሆነው በፀጋው የሚክዱት በዙ!
አላህ ከጥቂት ባሮቹ ያድርገን!...ምክንያቱም አመስጋኝ ባሮቹ ጥቂት ናቸውና!
➙ መልካም የጁሙኣ ግዜ ይሁንልን።
ISLAMINDSET
አላህ ከጥቂት ባሮቹ ያድርገን!...ምክንያቱም አመስጋኝ ባሮቹ ጥቂት ናቸውና!
➙ መልካም የጁሙኣ ግዜ ይሁንልን።
ISLAMINDSET
❤4👍2
ሁሉም ነገር ያልፋል።ሲያልፍ ግን ግዜ በክንውን ነው...እንጂ ክንውን በግዜ አይደለም። ሁሉም ነገር ሲፈፀም ግዜን ተከትሎ ነው የሚፈፀመው! አላህ ፈፅሙ ያለንን ስንፈፅም አፈፃፀማችን ግዜ አለው። ለዚያ ነው ግዴታ፣ሱና፣ዋጂብ እንዲሁም ፈረድ የሚባሉት በግዜ ላይ ጥገኛ የሆኑት።ከተገበርናቸው በግዜ ተጠቀምን ይባላል። በተቃራኒው አራም፣ ሙነከር፣ ቢድዓ እንዲሁም ኩፍር የሚባሉት ሰዎች ሲተገብሯቸው ባላቸው ግዜ ላይ ነው። ከተተገበሩ ግዜ ባከተነ ይባላል። አንድ ሰው ግዜውን ከሚያባክኑ ሰዎች ውስጥ ነው, አልያም ግዜያቸውን ከሚጠቀሙ ሰዎች ውስጥ ነው።ልብ በሉ መሀል ሰፋሪ የሚባል ነገር በዚች አለም ላይ እንደሌለ! ለዚያም ነው አላህ ስለሰራነው ስራ የቂያማ ቀን ሲጠይቀን ሁሉም ጥያቄዎቹ ከግዜ ጋር የተያያዙ ናቸው።ለዚህም ረቂቅ ምክንያቱ ግዜ ማለት ህይወት ስለነበረ ነው!
ትክክለኛ ሙስሊም ሁሌም ግዜውን ይጠቀምበታል..ምክንያቱም ለዚያ የአላህ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሆኑት ዘንድ ማለት ነው።
------------------- መልካም ግዜ ------------------
ISLAMINDSET
ትክክለኛ ሙስሊም ሁሌም ግዜውን ይጠቀምበታል..ምክንያቱም ለዚያ የአላህ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሆኑት ዘንድ ማለት ነው።
------------------- መልካም ግዜ ------------------
ISLAMINDSET
👍5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በጁመዓ ቀናችሁ እጃችሁን አንስታችሁ በዚህ ዱዓ አላህን ለምኑት...ኢንሻአላህ ሩህሩህ የሆነው አላህ(ሱ.ወ) ያስደስተናል።ከዱዓ አንዘናጋ ..ቀኑ ጁሙዓ ነውና! ብዙዎች ያላገኙት አሉ።
ISLAMINDSET
ISLAMINDSET
❤4👍1
ሰዉ ሆነን በመፈጠራችን እድለኞች ብንሆንም ቅኑን እና ቀጥተኛውን መንገድ ካልተመራን ግን እድለቢስነት ነው። ዘመናችን የምንፈልገውን ሁሉ በቀላሉ ሰጥቶን ቀጥተኛውን መንገድ ካልተመራን ራሳችንን መመልከት ይጠበቅብናል። ምናልባች ይሄንን ሁሉ ዘመናችን በቀላሉ የሰጠን እድለቢስ ሊያደርገን ሊሆን ይችላል።
ISLAMINDSET
ISLAMINDSET
👍3❤1