Telegram Web Link
የምትፈልገው ጥግ ድረስ መሄድ የምትፈልግ ከሆነ መቼም የማይቆሙ ልማዶች ያስፈልጉሀል፤ እነዚሆኖ ልማዶች ለማስኬድ ደግሞ ዲስፕሊን ወሳኝ ነው!

ዲስፕሊን ማለት ቢመችህም ባይመችህም፤ ደስ ቢልህም ቢከፋህም በቀን ውስጥ ማድረግ ያለብህን ሁሉ ማድረግ ነው። ፀባይህ እንዲህ ከሆነ ከምታስበው በላይ ስኬታማ ትሆናለህ!

@mindset12
@mindset12
ለመሆኑ የአርባ ቀን እድል የሚባል ነገር አለ?
እጣ-ፋንታችን ቀድሞ ተወስኗል?
የአርባ ቀን እድል ምንድን ነው?
****************************
በአገራችን አንዳች ነገር ሞክረን ስንወድቅ 'የአርባ ቀን ዕድሌ ነው' ብለን ማማረር የተለመደ ነገር ነው ፡፡ በስኬት ላይ ስኬት የሚደርቡ ጠንካራ ሰዎችንም 'ብላ ብሎ ፈጥሮት አንዴ በጥሩ ቀን ተፈጥሮ ወዘተ' ስንል እንሰማለን ፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ የሰው ልጅ በራሱ ነጻ ፈቃድ የወደደውን እንዲያደርግ (free will) ፈጣሪ ፈቅዶለታል የሚሉ ሊቃውንት የዚያኑ ያህል የበዙ ናቸው ፡፡

አንድ ጥያቄ ብቻ ልጠይቅ
እጣ-ፋንታችን ቀድሞ ተወስኗል?###
****************************
'ሁሉም ነገር ቀድሞ የተወሰነ ነው' ብለው የሚያምኑ ሰዎች ምንም ስራ ሳይሰሩ ፈጣሪ የወሰነላቸውን ብቻ ቁጭ ብለው ሲጠብቁ አይተህ ታውቃለህ ? የየቀን ህይዎታቸውን የተሻለ ለማድረግ፡ የዕለት እንጀራቸውን ለማግኘት ደፋ ቀና አይሉም ? ገነት ለመግባት አይጸልዩም ?

እንግሊዛዊው ሳይንቲስት # ስቴቨን ሀውኪንግ በአንድ ወቅት "ሁሉም ነገር ቀድሞ ስለተወሰነ እኛ የምንለውጠው አንዳችም ነገር የለም ብለው የሚያምኑ ሰዎች እንኳ የመኪና መንገድ ሲያቋርጡ ግራ ቀኙን እንደሚያዩ አስተውያለሁ" ብሎ ነበር ፡፡ ዕጣ ፋንታችን ቀድሞ ተወሰነም አልተወሰነ እኛ 'ሰው' የመባል ግዴታችን የሚያዘንን ነገር ፈጽመን ማለፍ ይጠበቅብናል ፡፡

ጀርመናዊው ማርቲን ሉተርም "ነገ ጠዋት ዓለም ብትንትኗ እንደሚወጣ ባውቅ እንኳ የአፕል ዛፎቼን መትከሌን አላቆምም" ብሏል ፡፡ ስለዚህ ቆመህ ለመቅረትህ 'የአርባ ቀን ዕድል' የሚል የስንፍና ካባ አታላብሰው ፡፡ ሰዎች ነን! ለክሽፈታችን ሁሉ የአርባ ቀን ዕድልን እንደታርጋ ልንለጥፍ አንችልም ፡፡ ፈጣሪም ገና ከመፈጠራችን 'በግንባርህ ወዝ ጥረህ ግረህ ብላ' ብሎ እንድንለወጥ እና በራሳችን ልክ እንድንኖር አዞናል ፡፡

የአርባ ቀን እድል የሚለው አስተሳሰብ ክሽፈታችንን ወደፈጣሪ የምናላክክበት የስንፍናችን መደበቂያ ነው ፡፡ ራሳችንን ከሀላፊነት ለማሸሽና ከተጠያቂነት ለማምለጥ የምንደረድረው ተልካሻ ሰበብ ነው ፡፡ ራሳችን ለራሳችን ሃላፊነት ካልወሰድን 'አለን' እንላለን እንጂ እየኖርን አይደለም ፡፡ 'አለሁ' ማለት (existence) እና 'መኖር' (living) ለየቅል ናቸው ፡፡

የአርባ ቀን ዕድል የተፈጠርኩበት ቀን ወዘተ የሚለው ሰበባችን ምክንያቱ የለውጥ ፍርሀት ነው ፡፡ ይህ ፍርሀት ምተፈጥሯዊ ነው ፡፡ ስፋትና ጥልቀቱ ይለያይ እንደሆን እንጂ በየትኛውም ማህበረሰብ ውስጥ ለውጥ ይፈራል ፡፡ ደረጃው ይለያያል እንጅ በሁሉም ሰው ዘንድ የለውጥ ፍርሀት አለ ፡፡ ሰዎች በተፈጥሯችን ያለንበት ስፍራ ይሞቀናል ፡፡ በአገራችን ደግሞ 'ከማያውቁት መልአክ የለመዱት ሰይጣን ይሻላል' የሚል አባባል እስከመፍጠር ደርሰናል ፡፡ ፍርሀቱ የተፈጥሮ መሆኑ እውነት ነው ፡፡ ግን ደግሞ ሌላ እውነት አለ ፡፡ በሰው ልጅ ታሪክ ታላቅና አሸናፊ የሆኑ ሰዎች የስኬታቸው ምስጢር የለውጥ ፍርሀትን መስበር መቻላቸው ነው ፡፡

በመሆኑም ሁለት ምርጫዎች በእጃችን ይገኛሉ ፡፡
1. ለውጥን በመፍራት ወደመጣንበት በክሽፈት መመለስ!
2. የለውጥ ፍርሀትን በመስበር አሸናፊና ኃያል ሰው ሆነን ወደመጣንበት
በድል መመለስ!
ከሁለቱ አማራጮች አንዱ ወደድንም ጠላንም የህይዎታችን መንገድ ይሆናል፡፡

ለተጨማሪ ምርጥና አስተማሪ የስኬት ፅሁፎች ቻናላችንን Join ያድርጉት
👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇
@mindset12 @mindset12
@mindset12
@mindset12



Mindset_eth

*******************************
@mindset12
-----------

"Happy are those who dream dreams and are ready to pay the price to make them come true."

-2pac
@mindset12
@mindset12
_____________

" Remember ur pain today
Will be strength tomorrow "

- 2pac
@mindset12
@mindset12
----------------------------

💓 💓
💓💓







To all mindset_ETH FAMILY'S

Easter is a promise
God renews to us in each spring.
May the promise of Easter
fill your heart with peace and joy!
Happy Easter
Ur problem might be as big as this ship.... but GOD will give u soln as wide as ocean


@mimdset12
@mindset12
^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^
Good morning🌤☀️
************************


ለመጀመር ትልቅ መሆን አይጠበቅብህም ነገር ግን ትልቅ ለመሆን መጀመር አለብህ ፡፡

-ዚግ ዚግላር
@mindset12
----------------------------

ወንዝ ድንጋይ ቦርቡሮ የሚገባው ሀይለኛ ስለሆነ ሳይሆን ያለማቋረጥ ስለሚፈስ ነው ፡፡


#-ጂም ዋትኪንስ
# @mindset12
@mindset12
---------------------------
ባለትላልቅ አእምሮ ሰዎች በሃሳብ ላይ ይወያያሉ ፣ መካከለኞች በ ድርጊት / ሁኔታዎች ላይ ይወያያሉ ባለትናንሾች ቁጭ ብለው ሰው ያማሉ ፡፡


#-ሪያኖር ሮዝቪልት
# @mindset12
@mindset12
÷=÷=÷=÷=÷=÷=÷=÷=÷=÷=÷=÷=


የምትታገሱትን ሁኔታ ለዩ!

በሕይወታችሁ ለመታገስ የወሰናችሁት ነገር ነው እናንተው ጋር የሚከርመው ፡፡ አንድ ነገርም ሆነ አንድ ሰው ምንም ያህል አስቸጋሪ ቢሆንና ለእናንተ እንደማይበጃችሁ ብታውቁም ሁኔታው ከእናንተ ጋር ያለው እድሜ ከትእግስታችሁ መጠን ጋር የተያያዘ ነው ፡፡

ለምንድን ነው ያንን ለጤንነታችሁ አደገኛ የሆነን ነገር ደጋግማችሁ የምታደርጉት ? ሕመሙን ስለታገሳችሁት!

ለምንድን ነው ያንን ሆን ብሎ ስሜታችሁን የሚጎዳውን ሰው ደጋግማችሁ የምታገኙት ? የሰውዬው ባህሪይ የሚያስከትልባችሁን የስሜት ቀውስ ስለታገሳችሁት!

ለምንድን ነው ከዚያ በገቢም ሆነ በሁለንተናዊ እድገት ከማደግ ይልቅ ጭራሹኑ እያሽቆለቆላችሁ እንደትሄዱ የሚያደርጋችሁን ስራ ያላቆማችሁት ? እየደረሰባችሁ ያለውን ክስረት ስለታገሳችሁ!

---------------------------
**************************
-_-_-_-_-_-_-_-__-_-_-_-_-_
@mindset12
----------------------------

ዛሬ ካልሆነ ነገ ይሆናል ።
ነገ ካልሆነ ከነገ ወድያ ይሆናል ።
እሱም ካልሆነ ደግሞ አንድ ቀን መሆኑ አይቀርም ።
ብቻ ተሰፋ አትቁረጥ መውድቅ እንዳለ መነሳትም አለ ።
መዋረድ እንዳለ መክበርም አለ ።
@mindset12
---------------------------- 🕋🕌እንኳን አደረሰን፤ አደረሳችሁ !🕌🕋

ለመላው እስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1442ኛው ለኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሰን ፤ አደረሳችሁ። ዒድ ሙባረክ !

በዓሉ የሰላም ፣ የአንድነት ፣ የፍቅር እንዲሁም የመተሳሰብ ይሆንልን ዘንድ እንመኛለን።
--------------------------


@mindset12
@mindset_contact_us_bot
@mindset12
📑📑📑📑📑📑📑📑📑📑

ጀማሪዎቹ ለመስራት ከሞከሩት ጊዜ በላይ አለቃቸው ብዙ ጊዜ ወድቋል ፡፡

# -ስቴፈን ማክክሬን
______÷_÷_÷_÷_÷_÷_÷______
@mindset12
📑📑📑📑📑📑📑📑📑📑📑

ብዙ ጊዜ ላለመስራት የምትተዋቸው ስራዎች በውስጣቸው ብዙ እድልን የያዙ ናቸው

@mindset12
@mindset_contact_us_bot
@mindset12
📑📑📑📑📑📑📑📑📑📑📑

. የዛሬ አመት በዚህ ሰአት ምናለ ምናለ ከአመት በፊት በጀመርኩ የምትላቸው ብዙ ነገሮች ይኖራሉ፡፡

#-ካረን ላንብ
@mindset_contact_us_bot
Forwarded from mInd SET-ETH
📲Contact us at
🖥 @mgrll
@mind_set_contact_us_bot 📩
♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡

For any announcement🔉📢
Question📝
Promotion📢
-------------------------
@mindset12
@mgrll
@mind_set_contact_us_bot
@mindset12
■■■■■■■■■■■■■■■■■■■
እውቀት ብቻ አይበቃም ተግባራዊ ካልተደረገ በስተቀር ፣ ፍቃደኛነት ብቻ አይበቃም ካልተሰራ በስተቀር ፡፡

🦾🦾 ብሩስli
------------------------□
@mindset_contact_us_bot
@mindset12
@mgrll
What u love
What u like
Share for ur bests...
Stay wiz us As a family 🙌🙌


@mindset12 📌📌📌
@mgrll 📲
@mindset_cobtact_us_bot 📩📩
2025/07/07 20:14:19
Back to Top
HTML Embed Code: